قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
رفتن به کانال در Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
912
مشترکین
-224 ساعت
-127 روز
+5130 روز
آرشیو پست ها
Repost from Abu_Oubeida~channel
ይሄ አሁን "ሙመይዕ ነው ወይንስ ኢኽዋኒ" ነው የሚያስብለው⁈
﴿إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا وَأَصْلَحُوا وَبَيَّنُوا فَأُولَئِكَ أَتُوبُ عَلَيْهِمْ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ ﴿ سورة البقرة 160﴾
ይሄ መርህ ነው። ጥፋተኞች ይቅር ይባልላቸው ዘንድ ከቀድሞው እኩይ ድርጊታቸው፡ መቶበት፣ ማስተካከልና ግልጽ ማድረግ አለባቸው ነው የሚለው መመሪያው። ለዛም ይመስለኛል አቡ ሙዓዝ ከቀጥተኛው የሰለፍያ መንሀጅ በቃኝ ብሎ ወደ እናንተ ሲመጣ መጀመሪያ ተውበትህን ኢዕላን አድርግ ብላችሁ ስትወተውቱት የነበረው። ስለዚህ እንዲያ ከሆነ ነገሩ ሽይኽ አቡ ዘር ከተምይዕ/ከኢኽዋንነት/ መንገድ ወደ ሰለፊያ መንሀጅ ሲቀላቀል የቶበተበትንና ግልጽ ያደረገበትን የድምጽ ቅጅ ስጡን። አበቃ!! አሁን ያለበት መንሀጅ ላይ ሁኖ ሰፊ ስራ መስራቱ የተውበቱ ማሳያ ነው ብላችሁ ልtሸውዱኝ እንዳትሞክሩ እኔ በዚህ የምታለል ህጻን አይደለሁም። የቢድዓ ባለቤት ዘንድ መማር ቀርቶ መቀማመጥ ሁክሙ ምንድን ነው? በሉ አሁን ቪድዮውን እዩና ፈትዋውን አያዩይዛችሁ መልሱልኝ። ይልቅስ ነገሮችን በልክ ካልተያያዝን እራሳችሁ የቦረቦራችሁት ቅርቃር ውስጥ የምትገቡበትን ነው እየበረበርኩ የምበትንላችሁ።
*ለማንኛው ቪደዎዉ ለ Africa Tv በሚቀርብ ቀረጻ ላይ ሸይኽ ሰዒድ አሕመድ ሙስጦፋ ላይ "ሲ*ራ" ሲቀራ የሚያሳይ ነው።
*ከዚህ መንሀጅ የቶበተበትን ማስረጀ ከሰጣችሁኝ እኔ ጽሁፌን አነሳለሁ። እውነታን የመነጋገር እንጂ የእልህ አካሄድ የለብኝም። ይሄን የማትሰጡኝ ከሆነ ግን ሌላ ጨምሬ እመጣለ ኢንሻ አላህ።
አቡ ዑበይዳ
t.me/AbuOubeida
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
➤ ❝ግጥም ❞
በከላላ መስጂደ-ሰላም ላይ የቀረበ!!
✔️ ❝ቦረና” ይለያል❞,,,,,,።✔️
ሐጃዊራን ያንጫጫው ግጥም
🎙 ❝በኑረዲን አል አረቢ❞
t.me/nuredinal_arebi/16051
t.me/nuredinal_arebi/16051
Repost from የወረኢሉ ሙስሊም ወጣቶች ድምፅ
አንተ የሰው ልጅ ሆይ ከጌታህ ምን አታለለህ
👉ሰዎችን ወደ ደን የምንጠራበት መንገድ ምን መምሰል አለበት በሰፊው ተዳሷል
👉በተለይ እዚህ ወሎ አካባቢ ያሉ ቤተሰቦቻችንን እንደት ነው መጥራት ያለብን ?
👉በዳዕዋ ላይ እዝነት ማለት ምን ማለት ነው ተዳሷል
🎙 በሸህ ከማል መኪይ ሃፊዘሁላህ
🕌 ወረኢሉ ፉርቃን_መስጅድ
📝 ነሃሴ 15/2018 E.C
https://t.me/YewereiluMuslimoch/6278
የሸህ ከማል መኪይ ሃፊዘሁላህ
ወረኢሉ_ፉርቃን መስጅ ያደረጓቼውን ዳዕዋዎች ለማገኘት ከ1_4
1👇👇👇👇👇
https://t.me/YewereiluMuslimoch/6275
2👇👇👇👇
https://t.me/YewereiluMuslimoch/6276
3 👇👇👇👇👇
https://t.me/YewereiluMuslimoch/6277
4👇👇👇👇
https://t.me/YewereiluMuslimoch/6278
Repost from የወረኢሉ ሙስሊም ወጣቶች ድምፅ
የመካነ ሰላምና የከላላ ወንድምና እህቶቻችን አዛኙ ጌታችን በእዝነቱ ይጠብቃችሁ እሱ ሁሉን በማድረግ ላይ ቻይ ነውና 🤲✍️
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
"ኪታቡን (መጽሐፉን) ሰዎች እንዳደነቁት ሆኖ አላገኘሁትም"
~
አንዳንዴ አንድን ኪታብ (መጽሐፍ) ሰዎች ሲያደንቁት አይተን ወይም ሰምተን ስናነበው ግን እንደተገለፀልን ሆኖ ላላገኘው እንችላለን። የዚህ ስሜት ምክንያቶቹ ደግሞ የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላሉ ይላሉ ሸይኽ ዐብዱረሕማን አስ-ሱደይስ፦
❀ መጽሐፉ ከአድናቂው ሰውየ አንፃር እንደተገለፀልህ ጥሩ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አንተ ከመጽሐፉ ውስጥ ያሉትን አብዛኛዎቹን ፋይዳዎች ከዚያ በፊት በማግኝተህ ሊሆን ይችላል እንደተደነቀልህ ያልሆነልህ።
❀ መጽሐፉን ያደነቀልህ አካል በሚወደውና ዝንባሌ ባለበት የዕውቀት ዘርፍ ላይ የሚመለከት ሊሆን ይችላል፤ አንተ ግን በዚያ ዘርፍ ላይ ዝንባሌ ከሌለህ ኪታቡ በተገለፀልህ መጠን ላይሆንልህ ይችላል።
❀ ኪታቡን ያደነቀልህ አካል በባህሪው ነገሮችን ከመጠን በላይ የሚያጋንንና በማድነቅ ላይ የሚጨምር ሊሆን ይችላል።
❀ መጽሐፉ የእውነትም እንደተባለው ጥሩ ሆኖ ነገር ግን ለአንተ ከባድ ሆኖ ሊሆን ይችላል። አንተ ገና ያልደረስክበት የእውቀት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያለ ከሆነ በተጠቀሰልህ መጠን አይስብህም።
❀ መጽሐፉ ያን ያህል ምስጋናና ማወደስ የሚገባው ሆኖ ሳይሆን፤ ነገር ግን አድናቂው አካል እንዲሁ ሌሎችን ተከትሎ ያላግባብ አድንቆ ሊሆንም ይችላል።
❀ አድናቂው አካል መጽሐፉን ገና ጀማሪ በነበረበት ጊዜ ስላነበበው እና የዚያ መጽሐፍ ትዝታ በልቡ ስለቀረ በቀደመ ጥሩ ግምቱ ላይ ሆኖ ሊሆን ይችላል። በዚህም የተነሳ ከዕውቀት ደረጃው ከፍ ካለ በኋላ ወደ መጽሐፉ እንደገና ስላልተመለሰ፣ ቀድሞ በአእምሮው የነበረውን የተሳሳተ ግንዛቤ አላወቀ ይሆናል።
❀ አድናቆቱ ለአንድ ዓሊም ወይም ለአንድ መዝሃብ ወይም ለአንድ አገር ከመወገን የተነሳ ሊሆንም ይችላል።
❀ አድናቆቱ የኪታቡ/ መፅሀፉ አዘጋጅ ጓደኛው በመሆኑ የመጣ አጉል መመሳሰል ወይም መጽሐፉ በስጦታ ስለተሰጠው ውዳሴ ከንቱ ሊሆንም ይችላል!
ስለዚህ ስለ አንድ ኪታብ/ መጽሐፍ አድናቆት ስትሰማ እነኚህን ነገሮች በአእምሮህ ታሳቢ አድርግ። ለትችትም እንዲሁ የተለያዩ ጤነኛም፣ ጤነኛ ያልሆኑም ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ።
ፀሐፊው ዐብዱረሕማን ብኑ ሷሊሕ አስ-ሱደይስ ነው። ታዋቂው የመስጂደል ሐራም ኢማም አይደለም፣ ሌላ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
أَذْكَارُ الصَّبَاحِ
١. «أَصْبَحْنَا وَأَصْبَحَ الْمُلْكُ لِلَّهِ، وَالْحَمْدُ لِلَّهِ، لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ، وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ، رَبِّ أَسْأَلُكَ خَيْرَ مَا فِي هَذَا الْيَوْمِ وَخَيْرَ مَا بَعْدَهُ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا فِي هَذَا الْيَوْمِ وَشَرِّ مَا بَعْدَهُ، رَبِّ أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْكَسَلِ، وَسُوءِ الْكِبَرِ، رَبِّ أَعُوذُ بِكَ مِنْ عَذَابٍ فِي النَّارِ وَعَذَابٍ فِي الْقَبْرِ».
٢. «اللَّهُمَّ بِكَ أَصْبَحْنَا، وَبِكَ أَمْسَيْنَا، وَبِكَ نَحْيَا، وَبِكَ نَمُوتُ، وَإِلَيْكَ النُّشُورُ».
٣. «اللَّهُمَّ أَنْتَ رَبِّي، لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ، خَلَقْتَنِي وَأَنَا عَبْدُكَ، وَأَنَا عَلَى عَهْدِكَ وَوَعْدِكَ مَا اسْتَطَعْتُ، أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا صَنَعْتُ، أَبُوءُ لَكَ بِنِعْمَتِكَ عَلَيَّ، وَأَبُوءُ بِذَنْبِي، فَاغْفِرْ لِي؛ فَإِنَّهُ لَا يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا أَنْتَ».
٤. «اللَّهُمَّ إِنِّي أَصْبَحْتُ أُشْهِدُكَ، وَأُشْهِدُ حَمَلَةَ عَرْشِكَ، وَمَلَائِكَتَكَ وَجَمِيعَ خَلْقِكَ، أَنَّكَ أَنْتَ اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ وَحْدَكَ لَا شَرِيكَ لَكَ، وَأَنَّ مُحَمَّدًا عَبْدُكَ وَرَسُولُكَ». (أَرْبَعَ مَرَّاتٍ)
٥. «اللَّهُمَّ مَا أَصْبَحَ بِي مِنْ نِعْمَةٍ، أَوْ بِأَحَدٍ مِنْ خَلْقِكَ، فَمِنْكَ وَحْدَكَ لَا شَرِيكَ لَكَ، فَلَكَ الْحَمْدُ وَلَكَ الشُّكْرُ».
٦. «اللَّهُمَّ عَافِنِي فِي بَدَنِي، اللَّهُمَّ عَافِنِي فِي سَمْعِي، اللَّهُمَّ عَافِنِي فِي بَصَرِي، لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ. اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْكُفْرِ، وَالْفَقْرِ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ عَذَابِ الْقَبْرِ، لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ». (ثَلَاثَ مَرَّاتٍ)
٧. «حَسْبِيَ اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ، عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ، وَهُوَ رَبُّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ». (سَبْعَ مَرَّاتٍ)
٨. «اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الْعَفْوَ وَالْعَافِيَةَ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ، اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الْعَفْوَ وَالْعَافِيَةَ فِي دِينِي وَدُنْيَايَ وَأَهْلِي وَمَالِي، اللَّهُمَّ اسْتُرْ عَوْرَاتِي، وَآمِنْ رَوْعَاتِي، اللَّهُمَّ احْفَظْنِي مِنْ بَيْنِ يَدَيَّ، وَمِنْ خَلْفِي، وَعَنْ يَمِينِي، وَعَنْ شِمَالِي، وَمِنْ فَوْقِي، وَأَعُوذُ بِعَظَمَتِكَ أَنْ أُغْتَالَ مِنْ تَحْتِي».
٩. «اللَّهُمَّ عَالِمَ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ، فَاطِرَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ، رَبَّ كُلِّ شَيْءٍ وَمَلِيكَهُ، أَشْهَدُ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ، أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ نَفْسِي، وَمِنْ شَرِّ الشَّيْطَانِ وَشِرْكِهِ، وَأَنْ أَقْتَرِفَ عَلَى نَفْسِي سُوءًا، أَوْ أَجُرَّهُ إِلَى مُسْلِمٍ».
١٠. «بِسْمِ اللَّهِ الَّذِي لَا يَضُرُّ مَعَ اسْمِهِ شَيْءٌ فِي الْأَرْضِ، وَلَا فِي السَّمَاءِ، وَهُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ». (ثَلَاثَ مَرَّاتٍ)
١١. «رَضِيتُ بِاللَّهِ رَبًّا، وَبِالْإِسْلَامِ دِينًا، وَبِمُحَمَّدٍ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ نَبِيًّا». (ثَلَاثَ مَرَّاتٍ)
١٢. «يَا حَيُّ، يَا قَيُّومُ، بِرَحْمَتِكَ أَسْتَغِيثُ، أَصْلِحْ لِي شَأْنِي كُلَّهُ، وَلَا تَكِلْنِي إِلَى نَفْسِي طَرْفَةَ عَيْنٍ».
١٣. «أَصْبَحْنَا وَأَصْبَحَ الْمُلْكُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ، اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ خَيْرَ هَذَا الْيَوْمِ: فَتْحَهُ، وَنَصْرَهُ، وَنُورَهُ، وَبَرَكَتَهُ، وَهُدَاهُ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا فِيهِ وَشَرِّ مَا بَعْدَهُ».
١٤. «أَصْبَحْنَا عَلَى فِطْرَةِ الْإِسْلَامِ، وَعَلَى كَلِمَةِ الْإِخْلَاصِ، وَعَلَى دِينِ نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، وَعَلَى مِلَّةِ أَبِينَا إِبْرَاهِيمَ، حَنِيفًا مُسْلِمًا، وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ».
١٥. «سُبْحَانَ اللَّهِ وَبِحَمْدِهِ». (مِائَةَ مَرَّةٍ)
١٦. «لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ، وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ». (عَشْرَ مَرَّاتٍ، أَوْ مَرَّةً وَاحِدَةً عِنْدَ الْكَسَلِ)
١٧. «لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ، وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ، وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ». (مِائَةَ مَرَّةٍ إِذَا أَصْبَحَ)
١٨. «سُبْحَانَ اللَّهِ وَبِحَمْدِهِ، عَدَدَ خَلْقِهِ، وَرِضَا نَفْسِهِ، وَزِنَةَ عَرْشِهِ، وَمِدَادَ كَلِمَاتِهِ». (ثَلَاثَ مَرَّاتٍ إِذَا أَصْبَحَ)
Repost from አቡ አዩብ ሙሃመድ ሰይድ ሙሃመድ
💰 ገንዘብ ሲሆን የልብ ጌታ…
🎙አቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ
https://telegram.me/abutoiba
https://telegram.me/abutoiba
Repost from አቡ አዩብ ሙሃመድ ሰይድ ሙሃመድ
💰 ገንዘብ ሲሆን የልብ ጌታ…
📍ዛሬ ዛሬ በሚያሳዝን ሁኔታ፣ የብዙ ሰዎች ለገንዘብ ያላቸው ፍቅር ከመጠን እየበለጠ መጥቷል። ገንዘብ እንደ መሣሪያ ሊጠቀሙበት ሲገባ፣ አንዳንዶች ግን ራሳቸውን ለገንዘብ አሳልፈው እስከመስጠት ደርሰዋል።
📍ለገንዘብ ሲባል እውነት ይተዋል፤ እምነት ይሸጣል፤ የሰው ሀቅ ይበላል፤ እንዲያውም አንድ ሰው ብር ለማግኘት ሲል “ይህ ሀላል ነውን? ወይስ ሀራም?” ብሎ መጠየቅን እስከሚረሳ ድረስ ይደርሳል።
በጣም የሚያስደነግጠው ሀራም መሆኑ በቁርዐናዊ እና በሀዲሳዊ ማስረጃ ሲነገረው አይ ቢሆንም የሚለው ነገር አንዳንዶች እማ ካገኘሁ ቡኋላ እቶብታለሁ የሚሉትስ ነገር ⁉️
ይህ ግን ቀላል ነገር አይደለም።
ምክንያቱም ገንዘብ በእጅ የሚያልፍ ነገር ነው፤ ነገር ግን ለገንዘብ ተብሎ የተሠራ ሐራም በልብ ላይ የሚቀር ነው።
ወንድሜ ሆይ! “ምን ያህል አገኛለሁ?” ብለህ ብቻ አትጠይቅ፤ “ከየት አገኘዋለሁ?” ብለህም ጠይቅ።
📍ብር ብዙ ሊሆን ይችላል፤ ግን በረከት ከሌለው ምን ይጠቅማል?
📍ቤትህ ሊሞላ ይችላል፤ ግን ልብህ ከአላህ ከራቀ ምን ይጠቅማል?
ኪስህ ሊደልብ ይችላል፤ ግን የአኼራህ መዝገብ በሐራም ከተሞላ ምን ይጠቅማል?
ሐላል ትንሽ ቢሆንም እንኳ ከሐራም ብዙ ይበልጣል።
ሐላል በረከት አለው፤ ሐራም ግን ብዛት ቢኖረውም በረከት የለውም።
📍አንድ ቀን ይህን ሁሉ እንተወዋለን። የሰበሰብነው ገንዘብ፣ የገነባነው ቤት፣ የገዛነው ንብረት ሁሉ ከኋላችን ይቀራል።
📍 ከእኛ ጋር የሚጓዘው ግን ምን እንደሠራን እና ከየት እንዳገኘነው ብቻ ነው።
ስለዚህ ገንዘብ በእጃችን ይሁን፤ በልባችን ግን አይንገሥ።
ገንዘብን እንጠቀምበት፤ ገንዘብ ግን እኛን እንዳይጠቀምብን እንንጠንቀቅ።
ከማግኘታችን በፊት መንገዱን እንመርምር፤
ከመብላታችን በፊት ምንጩን እንጠይቅ፤
ከመደሰታችን በፊት የአላህን ውዴታ እናስብ።
አላህ ሆይ! ሐላልን የምንፈልግ፣ ሐራምን የምንርቅ፣ ገንዘብን በእጃችን እንጂ በልባችን ውስጥ የማናስገባ አድርገን። ለእኛ በሰጠኸን ላይ በረከትን ስጠን፤ ከሐራም ሁሉ ጠብቀን፤ በሐላልህም ከሐራምህ አብቃቃን።
አሚን።
ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ
https://telegram.me/abutoiba
https://telegram.me/abutoiba
Repost from فوائد ابن القيم
التقوى ثلاث مراتب:
إحداها: حميةُ القلبِ والجوارح عن الآثام والمحرَّماتِ.
الثانية: حميتُها عن المكروهات.
الثالثة: الحميةُ عن الفُضول وما لا يعني.
فالأولى تُعطي العبدَ حياتَه، والثانيةُ تفيدُهُ صحَّتَه وقوَّتهُ، والثالثةُ تُكسِبُهُ سرورَه وفرحهُ وبهجَتَهُ.
• ابن القيم | الفوائد صـ (٤٥)
Repost from N/a
💎 بشرى لطلاب العلم:
ستبدأ بعون الله تعالى دفعة جديدة من بعض البرامج العلمية بإشراف الشيخ عبد الرزاق البدر، وذلك يوم السبت ٢٩ / ٤ / ١٤٤٨ الموافق ١٠ / ١٠ / ٢٠٢٦م.
📍والبرامج هي:
١- برنامج فقه الصلاة، ومدته أربعة أشهر تقريبا، ورابطه في التليجرام:
https://t.me/fiqhalhajj
٢- برنامج السيرة النبوية، ومدته ثمانية أشهر تقريبا، ورابطه في التليجرام:
https://t.me/alsseerah
ልዩ የኢልም ጥቆማ ሁለት ልዩ እና በፋኢዳ የተሞሉ ጥልቅ ማብራርያ ያካተቱ ልዩ የኢልም ደርሶች የመጀመሪያው ፊቂሁ ሰላት ለ4 ወራት የሚቆይ ሁለተኛው ደሞ ሲረቱ ነበዊያ አረበኛ የምትችሉ እና እነዚህን ሁለት ደማቅ የኢልም ኮርሶችን መካፈል የምትፈልጉ ከላይ ያሉትን የቴሌግራም ቻናሎችን ተቀላቀሉ እያንዳንዱ ደርሶች እራሳቸውን የቻሉ ፈተና አላቸው ፈተናዎቹን ለሚያልፉ የምስክር ወረቀት ይሰጣል::
ደርሶቹ የሚሰጡት በታላቁ ሸይኻችን አብዱረዛቅ አል-በድር ነው::
❗️ሙሉ ለሙሉ ከክፍያ ነፃ ነው❗️
https://t.me/Abbu_Abdillah
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የየመን ሑሢ ሺዐዎች ባበል መንደብን እና ዙባብን ለቀው ሸሽተዋል። በየቦታው እየተንጠባጠቡ ነው። በሑሢ መስፋፋት ሲቦርቁ የነበሩ ኢስላማዊ ዐቂዳ የማይገዳቸው የሺዐ ፈረሶች ዜናውን ላይነግሯችሁ ይችላሉ ብዬ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
بسم الله الرحمن الرحيم
ታላቅ የትምህርት ብስራት ከ«ኢብኑ ዐብባስ» Online መድረሳ!
እውቀት የልብ ብርሃን፣ የሕይወት መመሪያ ነው። የዲንዎን እውቀት በጥራትና በስርዓት ለመቅሰም ካለዎት ፍላጎት በመነሳት «ኢብኑ ዐብባስ» የኦንላይን መድረሳ አዲስ ትምህርት ይዞላችሁ ቀርቧል።
📌 የኮርሱ ዝርዝር መረጃ፦
➠ የሚቀራው ኪታብ፦ «መሳኢሉል ጃሂልያ» (مسائل الجاهلية) — በሸይኽ ሙሐመድ ብን ዐብደልወሃብ (ረሒመሁልላህ)
◈ አስተማሪ፦ ኡስታዝኸድርአሕመድአል-ኬሚሴሀፊዘሁሏህ
📲 የምዝገባ አድራሻዎች እና በቂ መረጃዎችን ለማግኘት ፦
🔹 ለወንዶች፦
👉 @Hussein_cod018
👉 @Yufa4
በሴቶች ለመመዝገብእናበቂመረጃዎችንለማግኘት ፦
🔹 ለሴቶች፦
👉 @bint_Adem15
👉 @Riiche1
📖 «እውቀትን መፈለግ በምእመናን ላይ ግዴታ ነው!»
💡 ቦታ ሳይሞላ በፍጥነት ይመዝገቡ፤ ለሌሎችም በማጋራት የእውቀት ጥሪውን ያድርሱ!
አስገዳጅ ሁኔታ ሲገጥም ፊትን ለወንድ መግለጥ
~
አንዳንዴ ፊታቸውን ከባዳ ወንዶች የሚሸፍኑ እህቶቻችን እንዲገልጡ የሚገፋ ጫና ይገጥማቸዋል። ለምሳሌ ጥጋበኛ እጅ ላይ ወድቀው ካልገለጡ ለከባድ ጥቃት ሊጋለጡ ይችላሉ። በመሰል ሁኔታዎች ላይ መግለጥ ይችላሉ? ወይስ ችግሩ የፈለገ ቢከፋ እምቢ ማለት አለባቸው?
አስገዳጅ ሁኔታ ሲገጥም የማይፈቀድ ነገር ይፈቀዳል። الضرورات تبيح المحظورات የሚለው የፊቅህ መርህ ጠንካራ መነሻ ያለውና የታወቀ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦
{ لَا یُكَلِّفُ ٱللَّهُ نَفۡسًا إِلَّا وُسۡعَهَاۚ }
አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም።" [አልበቀረህ: 286]
በአስገዳጅ ሁኔታ ህይወትን ለማትረፍ በክት መብላት ይቻላል። ተጨባጭ የሆነ አስገዳጅ ሁኔታ ከገጠመ የክህደት ንግግር በመናገርም ራስን ማትረፍ ይቻላል።
{ مَن كَ.فَرَ بِٱللَّهِ مِنۢ بَعۡدِ إِیمَـٰنِهِۦۤ إِلَّا مَنۡ أُكۡرِهَ وَقَلۡبُهُۥ مُطۡمَىِٕنُّۢ بِٱلۡإِیمَـٰنِ }
"ከእምነቱ በኋላ በአላህ የካደ ሰው (ብርቱ ቅጣት አልለው)፡፡ ልቡ በእምነት የረጋ ሁኖ (በክህደት ቃል በመናገር) የተገደደ ሰው ብቻ ሲቀር።" [አነሕል: 106]
ሌሎችም ጉዳዮች እንዲሁ ይታያሉ። የሙስሊሟ ለባዳ ወንዶች ፊቷን መግለጥም በዚሁ አግባብ የሚታይ ይሆናል። ይህንን መርህ በመንተራስ አስገዳጅ ጉዳይ ሲገጥም ጊዜ ሴት ልጅ ፊቷን መግለጥ እንደምትችል ዓሊሞች ይገልፃሉ። በዚህ ላይ በምሳሌነት ከሚጠቀሱ ምክንያቶች ውስጥ የሚከተሉትን ማንሳት ይቻላል:-
1ኛ፦ በማጨት ጊዜ :- ይሄ ሐዲሦች የመጡበት እንዲሁም ኢጅማዕ ያለበት በመሆኑ ለብዙ ሰውም የሚሰወር ስላልመሰለኝ ለማሳጠር ያክል በዚሁ ልለፈው።
2ኛ፦ ለህክምና፦ ጉዳቱ ያለበት ክፍል ፊትም ሆነ ሌላ ክፍል መግለጥ ይቻላል። ከተቻለ ባል ወይም ሌላ መሕረም (ቅርብ ቤተሰብ) አብሮ መኖር አለበት። ባይሆን ሴት ሃኪም ካለ ወደ ወንድ፣ ሙስሊም ካለ ወደ ሌላ መሄድ አይገባም ይላሉ ዓሊሞች። ለህክምና በሚያስፈልገው መጠን ሃኪሙ አካሏን መመልከት ይችላል ይላሉ ኢብኑ ቁዳማ። [አልሙግኒ፡ 7/459]
በነገራችን ላይ ጦር ሜዳ ላይ ሴቶች ሶሐቢያት ወንዶችን ያክሙ ነበር። ኡሙ ዐጢያህ - ረዲየሏሁ ዐንሃ - እንዲህ ትላለች፦
غَزَوْتُ مَعَ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ سَبْعَ غَزَوَاتٍ أَخْلُفُهُمْ فِي رِحَالِهِمْ، فَأَصْنَعُ لَهُمُ الطَّعَامَ، وَأُدَاوِي الْجَرْحَى وَأَقُومُ عَلَى الْمَرْضَى
"ከአላህ መልእክተኛ ﷺ ጋር ሰባት ዘመቻዎችን ዘምቻለሁ። እቃዎቻቸውን እጠብቅ፣ ምግባቸውን አዘጋጅ፣ ቁስለኞችን አክም እንዲሁም ህመምተኞችን እንከባከብ ነበር።" [ሙስሊም፡ 1812] የቡኻሪን باب هل يداوي الرجل المرأة، والمرأة الرجل እንዲሁም ዘርዘር ያለ ነገር የፈለገ ፈትሑል ባሪን መመልከትም ይቻላል።
3ኛ፦ ችሎት ላይ፦ በፍርድ ችሎት ላይ ፍርድ ለመስጠት ዳኛው አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ፊቷን ይመለከታል። ካልሆነ ሐቅን ማስከበር አስቸጋሪ ሊሆንበት ይችላል። ምስክር ሆና ስትቀርብ ወይም በሷ ላይ ምስክርነት ለመስጠትም እንዲሁ መገለጥ ግዴታ ሊሆን ይቻላል። ኢብኑ ቁዳማ እንዲህ ይላሉ፦
وللشاهد النظر إلى وجه المشهود عليها لتكون الشهادة واقعة على عينها، قال أحمد: لا يشهد على امرأة إلا أن يكون قد عرفها بعينها
"መስካሪ ሰው ምስክርነቱ ቦታው ላይ ያረፈ ይሆን ዘንድ የሚመሰከርባትን ሴት ሊመለከት ይችላል። (ኢማሙ) አሕመድ 'በትክክል ለይቶ እስካላወቃት ድረስ አንዲት ሴት ላይ አይመሰክርም' ብለዋል።" [አልሙግኒ፡ 7/459]
ይሄ የሳቸው ሃሳብ ብቻ አይደለም። ሌሎችም "ኒቃብ በለበሰች ሴት ላይ ፊቷን ሳትገለጥ መመስከር አይቻልም" ይላሉ። [አሸርሑል ከቢር፣ ደርዲር፡ 4194]
4ኛ፦ በግብይት ላይም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ሻጭ ወንድ ገዢዋን ሴት ሊመለከት እንደሚችል ዑለማኦች ይገልፃሉ። [አልሙግኒ፡ 7/459] ያለበለዚያ በግብይቱ ላይ ለተፈጠረ ክፍተት ማስተካከያ ለማድረግ ሊቸገር ይችላል። ለምሳሌ እቃ ሽጦላት ፊቷን ካላየ ኋላ ላይ እቃው ችግር ኖሮበት መመለስ ቢያስፈልግ በትክክል እሷ መሆኗን መለየት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።
5ኛ፦ አስገዳጅ ህግ ባለበት ሁኔታ፦ በአንዳንድ ሃገራት ህግ ወይም ኤርፖርት አካባቢ ወይም ሌላ አስገዳጅ ሁኔታ ከገጠመም ፊቷን መግለጥ ትችላለች። ለምሳሌ በመጥፎ ሰዎች እጅ ላይ ወድቃ ራሷን አደጋ ላይ ከምትጥል ፊቷን በመግለጥ ራሷን ማትረፍ ትችላለች። "አስገዳጅ ሁኔታዎች የተከለከለን ነገር ያስፈቅዳሉ።" ስለዚህ ማንነቷን ለመለየት የሚጠይቅ አስገዳጅ ሁኔታ ቢገጥም ወይም ሌላ ተጨባጭ ምክንያት ከኖረ ፊቷን መግለጥ ትችላለች ማለት ነው።
ይሄ እንግዲህ ከዑለማኦች አቋም ውስጥ ለደረሰች ሴት ልጅ ፊትን መሸፈን ግዴታ ነው የሚለውን ስንወስድ ነው። የሆነ ሆኖ ጫን ያለ ሁኔታ ካልገጠማት በስተቀር ለትንሽ ለትልቁ እጅ ልትሰጥ አይገባም። ፍተሻና መሰል ቦታዎች ላይ ሴቶችን መጠቀም የሚቻልበት ሁኔታ ካለ ወይም ደግሞ ጉዳዩ አንገብጋቢ ካልሆነ ባዳ ለሆኑ ወንዶች ፊትን መግለጥ አይገባም። አስገዳጅ ችግር ሲገጥም ደግሞ ጉዳዩን በችግሩ መጠን ብቻ ማስተናገድ ይገባል። "አስገዳጅ ሁኔታዎች በልካቸው ነው የሚስተናገዱት።" እንጂ ችግሩን ማመሀኛ አድርጎ አጉል መዘናጋት ውስጥ መግባት አይገባም። #ወላሁ_ አዕለም።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 01/2017)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from ስለ ቀልባችን
ችግሮችን አትጥሉ፣ ተግዳሮቶችን አትፍሩ፡፡ ለዉድቀት ሁሉ አሉታዊ ትርጉም አትስጡ፡፡ከማይመቹ ነገሮች አዳዲስ ነገር ይወለዳሉ፡፡ ጨለማ ባይኖር ኖሮ መብራት ለመፍጠር ማን ይጥር ነበር?፡፡ ጎረቤቶቻችን ዕቃ ባይከለክሉን ዕቃ አንገዛም ነበር፡፡ አከራዮች የቤት ኪራይ ባይጨምሩብን የራሣችን ቤት አንሠራም ነበር..፡፡
አዎ! ለችግራችን መፍትሄው ያለው ችግሩ አጠገብ ነውና ዙሪያችሁን ቃኙ፡፡
Repost from 𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
ምናልባት ከእናንተ የምርቅበት፣ ድምፄ ዝምታን የሚመርጥበትና ፅሁፎቼም እንደ ቀደመው ወደ እናንተ መድረስ የሚያቆሙበት ወቅት ቢመጣ… ከራሴ ነፍስና ከጊዜ እጥረት ጋር በብርቱ እየታገልኩ መሆኑን እወቁልኝ።
አንድ ቀን ስሜ ቢጠፋችሁ፣ የፃፍኩት ሁሉ ቢረሳ እንኳ፤ እጆቻችሁን ወደ ሰማይ ዘርግታችሁ ከ አላህ ጋር በምትገናኙበት በዚያ የዱዓ ሰዓት፣ በልባችሁ ጥግ ላይ ይህንን ደካማና ወንጀለኛ ባሪያ ቅንጣት ታክልም ብትሆን አስታውሱኝ።
ያቺን ያበረከትኳትን ትንሽ ጥረቴን አላህ በራህመቱ እንዲቀበለኝ፣ ጉድለቴንና ወንጀሌን በይቅርታው ሸፍኖ ቀልቤን እንዲያበጅልኝ፣
በውስጤ የቋጠርኳቸውን መልካም ምኞቶች ሁሉ እንዲያሳካልኝ ከአንጀታችሁ ዱዓ አድርጉልኝ።
በዚህች አላፊ ዓለም ውስጥ ለእኔ ከዚህ የላቀ ውድ ስንቅ የለምና… ሁሌም በኸይር አስቡኝ።
Repost from قَنَاةُ أَبِــي حَسَان عَلْي بن يُوسُف
እውነት ለማናገር ደረስነት ማለት ቀላል ሂወትን አያስተናግድም
እውቀትም ትንሽም ይሁን ብዙ በቀላል አይመጣም
ይሄ የምታውት ቀልዲና ዝም ብሎም ለቲክቶክ የተሰራ አይደለም
ወላሂ ወቢላህ እኔ እራሴ በሰፈር ሂወቴ አሳልፌዋለሁ ተጠቅሜዋለሁ
ሙሉ እንጀራው ደረቅ ሲሆን በርበሬ በመነስነስ በውሀ ተፈትፍቶ ነው የሚበላው በሰአቱ በጣም ይጣፍጣል
ለእውቀት መሰዋትነት ከፈሉ መማር መታደል ነው በቦታው ያላችሁ ሙሳፊሯች ፅኑ
እኔ ዛሬ እሚቆጨኝ ይሄን መብላቴ ሳይሆን ይሄን እየበላሁ በዛው ቆይቸ ተምሬ በሆን ብየነው።
ከ7አመት በላይ ሰፈር ቆይቻለሁ ምናል በቀላሉ 7 ጨምሬ ቢሆን እላለሁ ለንጀራው አይደለም ለትምህርቱ!!
https://t.me/abu_hassan_aliy_yusuf
https://t.me/abu_hassan_aliy_yusuf
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
(12) ከደባል ሱሶች ራቅ። አላማ ያለው ሰው ከሱስ ጋር አይነካካም። ለነፃነቱ ዋጋ የሚሰጥ ሰው በተልካሻ ነገሮች አይታሰርም። ደግሞም ውለታ ቢስ አትሁን። አንተ አክብረህ ያማረ ቪላ፣ ወይም ቆንጆ መኪና፣ ወይም ሚሊየን ገንዘብ ቆጥረህ የሰጠኸው ሰው አይንህ እያየ ከፊትህ በእሳት ቢያጋየው ምን ይሰማሀል? ሰውስ ምን ይላል? አላህ በክብር የሰጠህን ህይወት በጫትና በሲጋራ መግደል ማለት ከዚህ የከፋ ውለታቢስነት ነው። ራስህን በሱስ የምትገድለው ከቤተሰብ በተቆነጠረ ሳንቲም ከሆነ ግን አንተ ዘመን ተሻጋሪ ገልቱ ነህ። እንስሳ ነህ ብየ የእንስሳን ክብር ዝቅ ማድረግ አልፈልግም።
"ራስን በሱስ በመጉዳትና ራስን በማጥፋት መካከል ያለው ልዩነት የጊዜ ርዝማኔ ነው።"
(13) ለወላጆችህ በጎ ሁን። አቅምህ የሚችለውን ሁሉ ሁንላቸው። የሚረኩብህ እንጂ የሚሸማቀቁብህ፤ የሚዘኑብህ እንጂ የሚሳቀቁብህ፤ የምታሳርፋቸው እንጂ የምታሳፍራቸው አትሁን። ቤተሰብህ ላይ ጥገኛ ሆነህ ሳለ አልፈህ የምትፏልልባቸው ከሆነ ግን በርግጠኝነት መጥፊያህን ይዘሀል። "የማያድግ ልጅ ታዝሎ ያፏጫል" ይባላል።
"የቤት ቀጋ፣ የውጭ አልጋ አትሁን።"
(14) አላማ ይኑርህ። ለአላማህ ትጋ። ወደ አላማህ ተጓዝ። ወዴት ነው የምትሄደው? ታውቀዋለህ? ምንድነው የምትፈልገው? ይገባሃል? ምን ሰበብ እያደረስክ ነው? መቼስ ሰሜን ለመድረስ ወደ ደቡብ አይኬድም። ጤፍ ዘርቶ ባቄላ አይጠበቅም። ባጭሩ አላማህንም፣ አቅጣጫህንም፣ ሚናህንም እወቅ።
"የሚሄድበትን የማያውቅ የትኛውም መንገድ ይወስደዋል።"
(15) የኢንተርኔት አጠቃቀም ላይ ቁርጠኛ ሁን። የሶላትና የጥናት ጊዜህን የሚበላ፣ አሰተሳሰብህን የሚበክል፣ መጥፎ ምስሎችን ከመመልከት ሱስ የሚያጣብቅ እንዳይሆን ደጋግሞ ማሰብ ይገባል። ማህበራዊ መገናኛዎችም ሱስ እንዳይሆኑብህ ተጠንቀቅ። ብትችል ቲክቶክ ከሚሉት ጥሩ ያልሆነ ሰፈር ከነጭራሹ ብትርቅ መልካም ነው። አጠቃላይ ከኢንተርኔት ጋር ያለህ ትስስር የሚያንፅህ እንጂ የሚያጠፋህ እንዳይሆን ደጋግመህ አስብበት።
ሰላም!
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 21/2011)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
