uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Kanalga Telegram’da o‘tish

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
913
Obunachilar
-324 soatlar
-177 kun
+5330 kun
Postlar arxiv
ተክፊሮችን ተጠንቀቋቸው! ከሸይኽ ፈውዛን በርካታ ንግግሮች፡ 👉 ከቢድዓ ስዎች የከፉ እነርሱ ተክፊሮች ናቸው። 👉 ከአላህ ውጭ ያለን ለእገዛ የሚጣራ (መደድ የሚል)  መረጃ ሳይብራራለት አይከፍርም። ኡዝር_ቢልጀህል_አለ። የሙስጤዎቹ አዲሶቹ ተክፊሮች ሙቀት ላይ ስለሆኑ በእርጋታ አይሰሙም እንጂ ጉዳዩ በብዙ ዑለማዎች ፍንትው ብሎ ተብራርቷል። ሙቀቱ ሲበርድላቸው ይሰሙት ይሆናል ኢንሻአላህ። https://t.me/Abulabas1444 https://t.me/Abulabas1444.

Repost from N/a
ሀራም መመገብ ጉዳቱ 🎙በኡስታዝ አረቡ ሰዒድ 🕌በደገር ከተማ መስጂድ ሰላም   ላይ የተደረገ_መሳጭ ነሲሀ የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Yedeger_selefioch_jemea

የባልን የሞት ዜና ለሚስት በብልሃት የማድረስ ምርጥ ዘዴ በአንዲት መንደር ውስጥ "ሙቅቢል" የሚባል ሰው ነበር የአላህ ውሳኔ ሆነና በድገት ሞተ። ጎረቤቶቹ መሞቱን ሲያረጋግጡ አጠቡት ከፈኑት ከዚያም ሬሳውን በሳጥን ተሸክመው ወደ ቤቱ ወሰዱት፤ ግን በሩ ላይ ቆመው እየፈሩና እየተጨነቁ፡ "የባሏን መሞት ለሚስቱ ሳናስደነግጣት እንዴት ብለን እንንገራት?" ተባባሉ። ድንገት ነው የሞተው እንደት ሳናስደነግጥ እናስረዳት በማለት ግራ ገብቷቸው እያለ ​አንዱ ቀረብ ብሎ በሙሉ እምነት፡ "ነገሩን ለእኔ ተዉልኝ፤ እኔ ከሴቶች ጋር እንዴት እንደሚወራ አውቃለሁ" አለ። ​ከዚያ "ሳጥኑን ይዛችሁ ከቤት በስተጀርባ ተሸሸጉ፤ እኔ ስጠራችሁ ወዲያው አምጡት" አላቸው። ​ሰውዬው ሄዶ በሩን አንኳኳ፤ ሚስቲቱም ማነው ብላ በሩን ከፈተች፡ "ሰላም ነው? ሰውየውም አንች የሙቅቢል ሚስት ነሽ ብሎ ጠየቃት ? እሷም አወ ምነው በባሌ ላይ የተፈጠረ ነገር አለእንዴ?" አለችው። ​ሰውዬው በተረጋጋ መንፈስ፡ "አይዞሽ፣ ምንም መጥፎ ነገር አልሆነም.. ግን ባልሽ ሙቅቢል ባንች ላይ ሌላ ሚስት አገባ!" አላት። ​ሚስቲቱም በቁጣ አብዳ መርገም ጀመረች፡ "በእኔ ላይ ሌላ አገባ?!⁉️ 1️⃣አምላክ ይበቀለው! 2️⃣እልም አላህ ያርገው 3️⃣በጁሱ መርዝ እምታጠጣ ይስጠው እያለች ተራገመች ​ከዚያም ሰውዬው ዞር ብሎ "እልል በይ! አላህ ዱአሽን ተቀብሎሻል ሰምቶሻል!.. አምጡት ወጣቶች!" ብሎ ጮኸ። ​ወጣቶቹ ሳጥኑን አምጥተው ፊቷ አስቀመጡት። ሚስቲቱም ሳጥኑን አይታ ረጋ ባለ ድምፅ፡ "አላህ ይማረው፣ ይህ የአላህ ውሳኔና ፍቃድ ነው.. ዋናው ነገር በእኔ ላይ ሌላ አለማግባቱ ነው!" አለች። ክክክ copy

የማለዳ መልእክት (51) ~ ቢድዐዎች መጠናቸው ይለያያል። 1. አንዳንዶቹ በመሰረታዊ ኢዕቲቃድ ላይ የተከሰቱ ከባባድ ቢድዐዎች (بدع اعتقادية كبرى) ናቸው። ለምሳሌ የጀህሚያ፣ የሙዕተዚላ፣ የአሻዒራ እና መሰል ቢድዐዎች። 2. ሌሎች ደግሞ በዒባዳዎች ውስጥ የሚከሰቱ (بدع عملية) ናቸው። ይሄ እንዲሁ በግርድፉ ሲታይ ነው። እንጂ መሀል ላይ ብዙ የተራራቁ የቢድዐ መጠኖች አሉ። በአንድ ምድብ ውስጥ ያሉ ቢድዐዎች ራሱ መጠናቸው በጣም ይራራቃል። ለምሳሌ የጀህሚያ ቢድዐ ከአሽዐሪያ በጣም የከፋ ነው። "አላህ ከፍጡሩ ጋር ተዋህዷል" ወይም "ሰፍሯል" የሚለው እንደነ ሐላጅ፣ ኢብኑ ዐረቢ፣ ኢብኑል ፋሪድ፣ ዐፊፉ ቲልሚሳኒይ፣ ኢብኑ ሰብዒን፣ ... ያሉ ሱፍዮች ቢድዐ ክብደቱ እንግዳ ዒባዳዎችን ወይም የዒባዳ አፈፃፀሞችን ካመጡ አካላት ቢድዐ በጣም የከፋ ነው። የሁለተኞቹ ክፍሎች ቢድዐ ከመጀመሪያዎቹ በንፅፅር በጣም ያነሰ ነው። የመጀመሪያዎቹ ከኢስላም ጠርጎ የሚያስወጣ ነው። ይህንን መለየታችን 1ኛ፦ ጥፋቶችን የክብደታቸውን መጠን እንድንለይ ያግዘናል። 2ኛ፦ በዚሁ መሰረትም ለአጥፊዎቹ የሚኖረን አቋምና አያያዛችንም ይለያያል። መቼስ በሁሉም ላይ ያለን አቋም እንደ ሳሙና አንድ ቁርጥ ሊሆን አይችልም። 2 ኛ፦ ቢድዐ ከወንጀል የከፋ እንደሆነ የሚጠቁሙ የቀደምት ዑለማኦችን ንግግሮች ያላግባብ እንዳንረዳም ያግዘናል። እንደ ዝሙት፣ ነፍስ ማጥፋት፣ ወለድ (አራጣ) መብላት፣ ... ያሉ ከባባድ ወንጀሎች (کبائر الذنوب) ከተወሰኑት የቢድዐ አይነቶች (بدع عملية) ያነሱ አይደሉም፣ የከበዱ እንጂ። በመሰረታዊ ዐቂዳ ላይ የመጡ ከባባድ ቢድዐዎች ደግሞ ከተዘረዘሩት ከባባድ ወንጀሎች (کبائر الذنوب) በጣም የከፉ እንጂ ያነሱ ጥፋቶች አይደሉም። እና የቢድዐን አደጋ ለማጉላት የምናደርገው "ቢድዐ ከወንጀል የከፋ ነው" የሚለው ገለፃ ባላሰብነው አቅጣጫ እነዚህን ወንጀሎች አቅልሎ እንዳያሳይ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ወላሁ አዕለም። (ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል ኣኺር 24/1448) = የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

የተጠናቀቀ የመንሀጁ ሳሊኪን ኪታብ ደርስ ~ ከክፍል 1 - 61 = ክፍል __ 1 t.me/IbnuMunewor/4756 ክፍል __ 2 t.me/IbnuMunewor/4833 ክፍል ___ 3 t.me/IbnuMunewor/4884 ክፍል __ 4 t.me/IbnuMunewor/4888 ክፍል __ 5 t.me/IbnuMunewor/4914 ክፍል __ 6 t.me/IbnuMunewor/4934 ክፍል __ 7 t.me/IbnuMunewor/4955 ክፍል __ 8 t.me/IbnuMunewor/4975 ክፍል __ 9 t.me/IbnuMunewor/4992 ክፍል __10 t.me/IbnuMunewor/5036 ክፍል __11 t.me/IbnuMunewor/5052 ክፍል __ 12 t.me/IbnuMunewor/5077 ክፍል __ 13 t.me/IbnuMunewor/5173 ክፍል __ 14 t.me/IbnuMunewor/5173 ክፍል __ 15 t.me/IbnuMunewor/5238 ክፍል __ 16 t.me/IbnuMunewor/5274 ክፍል __ 17 t.me/IbnuMunewor/5357 ክፍል __ 18 t.me/IbnuMunewor/5376 ክፍል __ 19 t.me/IbnuMunewor/5670 ክፍል __ 20 t.me/IbnuMunewor/5672 ክፍል __ 21 t.me/IbnuMunewor/5703 ክፍል __ 22 t.me/IbnuMunewor/5767 ክፍል __ 23 t.me/IbnuMunewor/5771 ክፍል __ 24 t.me/IbnuMunewor/5811 ክፍል __ 25 t.me/IbnuMunewor/5872 ክፍል __ 26 t.me/IbnuMunewor/5873 ክፍል __ 27 t.me/IbnuMunewor/5899 ክፍል __ 28 t.me/IbnuMunewor/5969 ክፍል __ 29 t.me/IbnuMunewor/6058 ክፍል __ 30 t.me/IbnuMunewor/6156 ክፍል __ 31 t.me/IbnuMunewor/6157 ክፍል __ 32 t.me/IbnuMunewor/6218 ክፍል __ 33 t.me/IbnuMunewor/6238 ክፍል __ 34 t.me/IbnuMunewor/6275 ክፍል __ 35 t.me/IbnuMunewor/6424 ክፍል __ 36 t.me/IbnuMunewor/6492 ክፍል __ 37 t.me/IbnuMunewor/6525 ክፍል __ 38 t.me/IbnuMunewor/6577 ክፍል __ 39 t.me/IbnuMunewor/6666 ክፍል __ 40 t.me/IbnuMunewor/6669 ክፍል __ 41 t.me/IbnuMunewor/6713 ክፍል __ 42 t.me/IbnuMunewor/6786 ክፍል __ 43 t.me/IbnuMunewor/6789 ክፍል __ 44 t.me/IbnuMunewor/6946 ክፍል __ 45 t.me/IbnuMunewor/6983 ክፍል __ 46 t.me/IbnuMunewor/7073 ክፍል __ 47 t.me/IbnuMunewor/7077 ክፍል __ 48 t.me/IbnuMunewor/7503 ክፍል __ 49 t.me/IbnuMunewor/7590 ክፍል __ 50 t.me/IbnuMunewor/7656 ክፍል __ 51 t.me/IbnuMunewor/9706 ክፍል __ 52 t.me/IbnuMunewor/9713 ክፍል __ 53 t.me/IbnuMunewor/9727 ክፍል __ 54 t.me/IbnuMunewor/9765 ክፍል __ 55 t.me/IbnuMunewor/9811 ክፍል __ 56 t.me/IbnuMunewor/9843 ክፍል __ 57 t.me/IbnuMunewor/9920 ክፍል __ 58 t.me/IbnuMunewor/10013 ክፍል __ 59 t.me/IbnuMunewor/10147 ክፍል __ 60 t.me/IbnuMunewor/10150 ክፍል __ 61 t.me/IbnuMunewor/10249

💡እውቀት የሌለው አካል ያለ እውቀት ሺርክ ቢሰራ  ስራው ሽርክ ነው ሰውየው ግን በጅህልናው ዑዝር ይሰጠዋል  ይላሉ ሸይኽ ፈውዛን

​بسم الله الرحمن الرحيم ​ ታላቅ የትምህርት ብስራት ከ«ኢብኑ ዐብባስ» Online መድረሳ! ​እውቀት የልብ ብርሃን፣ የሕይወት መመሪያ ነው። የዲንዎን እውቀት በጥራትና በስርዓት ለመቅሰ
​بسم الله الرحمن الرحيم ​ ታላቅ የትምህርት ብስራት ከ«ኢብኑ ዐብባስ» Online መድረሳ! ​እውቀት የልብ ብርሃን፣ የሕይወት መመሪያ ነው። የዲንዎን እውቀት በጥራትና በስርዓት ለመቅሰም ካለዎት ፍላጎት በመነሳት «ኢብኑ ዐብባስ» የኦንላይን መድረሳ አዲስ ትምህርት ይዞላችሁ ቀርቧል። ​📌 የኮርሱ ዝርዝር መረጃ፦ ➠ ​የሚቀራው ኪታብ፦ «መሳኢሉል ጃሂልያ» (مسائل الجاهلية) — በሸይኽ ሙሐመድ ብን ዐብደልወሃብ (ረሒመሁልላህ) ◈ ​አስተማሪ፦ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል-ኬሚሴ ሀፊዘሁሏህ ​📲 የምዝገባ አድራሻዎች እና በቂ መረጃዎችን ለማግኘት ፦ ​🔹 ለወንዶች፦ 👉 @Hussein_cod018 👉 @Yufa4 ​በሴቶች ለመመዝገብ እና በቂ መረጃዎችን ለማግኘት ፦ 🔹 ለሴቶች፦ 👉 @bint_Adem15 👉 @Riiche1 ​📖 «እውቀትን መፈለግ በምእመናን ላይ ግዴታ ነው!» ​💡 ቦታ ሳይሞላ በፍጥነት ይመዝገቡ፤ ለሌሎችም በማጋራት የእውቀት ጥሪውን ያድርሱ!

📢 ለአዳማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና በአካባቢው ላሉ ሁሉ የምሥራች! ኢንሻ አላህ፣ በሚከተለው መርሃ ግብር ትምህርቶችን እንጀምራለን። 📚 ከዙህር ሰላት በኋላ፦ የዕውቀት ፈላጊ ተማሪ መሠረታዊ መጻሕፍት
📢 ለአዳማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና በአካባቢው ላሉ ሁሉ የምሥራች! ኢንሻ አላህ፣ በሚከተለው መርሃ ግብር ትምህርቶችን እንጀምራለን። 📚 ከዙህር ሰላት በኋላ፦ የዕውቀት ፈላጊ ተማሪ መሠረታዊ መጻሕፍት – የመጀመሪያ ደረጃ በዚህ ደረጃ የሚከተሉት መጻሕፍት ይማራሉ፦ • አል-ኡሱሉ አስ-ሰላሳህ ወአዲላቱሃ — الأصول الثلاثة وأدلتها • አል-ቀዋዒዱ አል-አርበዓ — القواعد الأربع • ነዋቂዱል ኢስላም — نواقض الإسلام • አል-አርበዒን አን-ነወዊያ — الأربعون النووية 📖 ከመግሪብ ሰላት በኋላ፦ • ኪፋያቱል ሙተዓቢድ — كفاية المتعبد • የነቢዩ ﷺ ሕይወትና ታሪክ — سيرة الرسول ﷺ 📍 ቦታ፦ መስጂድ ኸዲጃ — ቡሊ — አዳማ 📅 ቀናት፦ ከቅዳሜ እስከ ሰኞ 🗓 የመጀመሪያ ቀን፦ ቅዳሜ፣ ረቢኡል አኺር 15/1447 ሂጅሪ, (መስከረም 30,2019), 🎙 በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ኡመር ሐሰን  አልአሩሲ አል-አይመሮ (ሀፊዘሁላህ) 🌿 ሁላችሁም በደህና መጡ! አላህ በዕውቀት እንዲጠቅመን፣ ከእርሱም ዘንድ ቅንነትንና ጽናትን እንዲሰጠን እንለምነዋለን። 📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ 👇👇👇 🌐 https://t.me/AbumuslimAlarsi

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 💗 የተከበራችሁ እህቶች በየትኛውም ዩንቨርሲቲ የምትገኙ የሙስሊም ሴት ዓሚሮች ሁላችሁንም የምንፈልጋችሁ ስለሆነ ባረከላሁ ፊኩነ ከዚህ በታች ባለው ዩዘር ኔም አናግሩን። 💗 የቻናል እና የግሩፕ ባለቤቶች ሸርርር በማድረግ ተባበሩን ባረከላሁ ፊኩም። 👇👇👇 @umureyan_33

መንገዱ ቢርቅም #የመን አድርሱልኝ አደራ #መርከዘልፈዩሽ!! ------------------------------- ትንኝ ምንም ቢሮጥ መንገድ ላይ ቢያመሽም፡ ከጩጯን አንደበት ቅጥፈት ቢቀረሽም፡ መሰላቸው እንጂ ሰው አይረበሽም፡ ሀሸራት ተፈርቶ ከአላማ አይሸሽም፡ በባጉንቸር ዝላይ ውቅያኖስ አይጓሽም፡ የሚዳቆወች ድምፅ ተራራ አይረብሽም፡ የአይጦች ድንፋታ ከድመት አያልፍም፡ ውሀ ከተረጨ አመድ ይሆናል ፍም፡ #የመንፈዩሽ_!! ብዙ ጀግና አፍርቷል የየመን ማህፀን፡ ተውሒድና ሱናን ሀቅን የሚማፀን፡ ሽርክና ቢዲዐን ሌት ቀን የሚዋጋ፡ በገንዘብ በነፍሱ የሚከፍል ዋጋ፡ ሱናን ለማስረዳት የሚል ከላይ ከታች፡ ሀቅን የሚጠብቅ ከፈጣሪ በታች፡ #የመን____!! የታሪክ ሀገር ነው የጀግና መፍለቂያ፡ የኢስላም አርማ ነው ግሩም መታወቂያ፡ ለደነዘዘ ሰው ቆንጆ ማነቃቂያ፡ መርከዝ እየሰራ ኪታብ የሚሰድር፡ ሀቅን ከማንም ጋር የማያወዳድር፡ የሊቆች ሀገር ነው ይህ የየመን ምድር፡ #የመን___!! ከነብያት ዘመን ከድሮ ጀምሮ፡ አለ በየመን ውስጥ ታሪክ ተከምሮ፡ እስከ ዛሬ ድረስ ተነግሮ አላለቀም፡ ጦርነት ቢኖርም #ታሪኳ አልደቀቀም፡ አጂግ በጣም ብዙ ፈተና ቢኖርም፡ የየመን ዑለማዕ ክንዱ አይሰበርም፡ በተውሒድ በሱና በሒፍዝ ጠንክሯል፡ ኢስላም በሽምደዳ አዕምሮው ላይ ሰፍሯል፡ #የመን....!! ምንም ቢፈጠርም ፊትናን አቀጣጣይ፡ ለትውልድ መድረስ አይችልም ለቀጣይ፡ ብዙ ነገር መጥቶ እንዳልነበር ከስሟል፡ የየመን ዑለማዕ በተጠንቀቅ ቆሟል፡ በእምነቱ ለመጣ ማንንም አይሰማም፡ በእውቀትም በተግባር የመን አይታማማም፡ የየመኖች ምድር ጀግና በቅሎበታል፡ ገና ብዙ ኸይራት ይፈፀምበታል፡ የየመን ዑለሞች እውቀት እየሰጡ፡ ▸#ፊትና__ናፋቂወች_እየተዳመጡ፡ ተውሒድና ሱና ኸይሩ ይቀጥላል፡ የፊትናው ናፋቂ ገና ይቃጠላል፡ በተአሱብ ሰክሮ እስበሱ ይባላል፡ የመን ጀግኖቹ ጋር ታሪኩን ያድሳል፡ ገና ብዙ ጀግና አርበኛ ይነሳል፡ ሱናው እያበበ ቢዲዐው ይከሳል፡ #ኢንሻ_አሏህ_!! የመን ላይ ሔዳችሁ የምትበጠብጡ፡ ነገር ከዚያ ከዚህ የምታሯሩጡ፡ ወይ ስርዐት አረጉ አልያ ደግሞ ውጡ፡ ከሀበሻ ድረስ ሀገር አቋርጣችሁ፡ ከታሪኳ ቦታ #የመን ላይ ሔዳችሁ፡ ፊትና ስትፈጥሩ አለማፈራችሁ⁉️ #ለማንኛውምግን_ ከፍ ያለች ሀገር ነች በታሪኳ የመን፡ አላት ብዙ ጀግና ለአሏህ የሚታመን፡ ከትላንት እስካሁን የመን ባዶ አልሆነም፡ የመን በእውቀት እንጂ በሽርክ አልገነነም፡ መጥፎወች ቢኖሩም ይፀዳሉ ገና፡ ድጋሜ ያፈራል ተውሒድና ሱና፡ በሶሀቦች ፈለግ በእውነተኞች ፋና፡ ይህን የሚሰሩ#የመን አሏት ልጆች፡ በቁርዐን በሀዲስ በእውነት ፈራጆች፡ #የመን_!! እንኳንስ ዛሬና መረጃው ተዳርሶ፡ ብዙ የሽርክ ቋት እየጠፋ ፈርሶ፡ አለም ጫፍ እስከጫፍ ተውሒዱ ተዳርሶ፡ የየመኑ አሊም ጫካውን መንጥሮ፡ በአሏህ ተወክሎ ትንሽ ስንቅ ቋጥሮ፡ ደማጅን መስርቷል ሀቅን አስተምሮ፡ በተውሒድ በሱና ሽርክን አሶግዶ፡ ጥመት ኹራፋትን በሀቅ ገርምዶ፡ አልሀምዱ ሊላሒ ምድሪቷ ጀግና አላት፡ ለተውሒድ ለሱና ህይወቱን ገብሮ የሚታገልላት፡ 👉#እስኪ__አስቡት‼️ ደማጂን ሸይኽ ሙቅቢል እንደመነጠሩት፡ ያኔ በምን መልኩ እንዳስተዳደሩት፡ #የህያ ፋትና ፈጥሮ እስኪያፈርሰው ድረስ፡ ደማጅ ግሩም ነበረ ውብ የሱና ፈረስ፡ ሜዳ ነበር ደማጅ የተውሒድ የሱና፡ #አበላሸው እንጂ#ሀጁሪ መጣና፡ ምንም በዚያ ፊትና ብዙ ግፍ ቢሰራም፡ ኪሳራ ቢያደርሱም የስሜት ሰካራም፡ #ሙቅቢል የለኮሱት አልጠፋም ችቧቸው፡ አለ ዛሬም ድረስ ውብ ነው ታሪካቸው፡ ፊትና ቢፈራገጥ ምን ከዚያ ከዚህ ቢል፡ የቆሸሸ ውሀ እንደያዘ ዘንቢል፡ በአሏህ ታግዞ መስርቶታል ሙቅቢል፡ ወደ ባለቤቱ አሁን ተመልሷል፡ ጨርሶ ባይጠፋም ፊትናውም ፈራርሷል፡ ይቀጥላል ገና ድጋሜ ታድሷል፡ 👉#እናም_ወዳጀ_ሆይ__!! የታላቁ አሊም የሙቅቢል ተማሪ፡ የተውሒድ የሱና የኢስላም ዘማሪ፡ የዚያ የጀግና#ሸይኽ የሙቅቢል ደረሳ፡ ፊውሽን ቆርቁረው#የአደኑ አንበሳ፡ ሽርክና ቢዲ ን ሲያሳዩት ሀበሳ፡ ጥመት ኹራፋቱን በመረጃ ገርፈው፡ ሞት አይቀርምና እርሳቸውም አርፈው፡ ሌሎች ተተክተው ዛሬም ድረስ አሉ፡ ተውሒድና ሱናን በደስታ እየበሉ፡ ሀቅን እንደ ምግብ እየተመገቡ፡ ኢስላምን ለመጥቀም ሱና እንዳነገቡ፡ ለጠላቶቻቸው ሆነው የግር እሳት፡ ሁሌም ለሚለፋ ሰውን ለማሳሳት፡ ፊትናን ለሚናፍቅ ሆነውት ትኩሳት፡ አሉ ዛሬም ድረስ ሀቅን ባለመርሳት፡ ሁሉንም ቻል አርገው ለሱና እንደቆሙ፡ ለደረሶቻቸው የኢልምን ጎዳና ሁሌ እየጠቆሙ፡ ------------------------------------------------ ......#አወና....... ያንን ግሩም መርከዝ ቦታው ላይ የሰሩት፡ መርከዘል-ፈዩሽን እንድህ ያሳመሩት፡ አብደረህማን ናቸው የአደኑ ነብር፡ በሀቅ ፈላጊ በጀግኖች ትብብር፡ ከዛን ቀን አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ፡ አለ ለህዝባችን#ኢልማቸው ሲዳረስ፡ መርከዙን#ጌታ እንጂ ሰው አይችልም ማፍረስ፡ ይህንን ራዕይ በቅድሚያ ያሰቡት፡ በትኩረት በጥልቀት ቆርጠው ያነገቡት፡ #የአደኑ__አንበሳ ናቸው የገነቡት፡ እውቀት እንድቀስም ወጣቱን የሳቡት፡ #ፈዩሽ____ ቁርአንና ሀዲስ ተውሒድና ሱናን ያስተምሩበታል፡ ዒልሙ ከሸይኽ ሙቅቢል ተመስክሮለታል፡ የጥመትን ቡድን በደሊል ይማታል፡ ሱናን ከመጠበቅ መች ስራ ይፈታል፡ ብዙ ኸይር ስራ ይፈፀምበታል፡ የሀቅ ዘበኛ ተተኪ ያመርታል፡ #መርከዘል--#ፈዩሽ___!! ጠላት ቢኖሩትም ጥቁር እንደ ከሰል፡ ሀሰድ ምቀኝነት ተንኮል በማውሰልሰል፡ ውሸትና ቅጥፈት ሁሌ በማማሰል፡ ቀሩ እንደከሰሩ አያውቁትም መሰል!! ተመስርቷልና በእሳት ተፈትኖ፡ መርከዛችን ደምቋል ጠላቱን በትኖ፡ የመርከዙን ውብ ስም በመጥፎ ለማንሳት፡ እውቀት እንዳይፈልግ ህዝቡን ለማሳሳት፡ በስሜት ተነስተው ብዙ ግፍ ቢሰሩም፡ የሌለ ቢቀጥፉ ምንም ቢናገሩም፡ ለዚህ ታላቅ መርከዝ ምንም አልፈጠሩም፡ #ፈዩሽ.....!! ይህ መርከዝ የማን ነው ብለው ሳይጠይቁ፡ ዘለው እየገቡ ቀሩ እየደቀቁ፡ ለማይጥሱት አጥር እየነቀነቁ፡ ከሰሙ ጠቅላላ ዳግም ላይነሱ፡ ተመናምነው ጠፉ እየተቀነሱ፡ ምን ከፊትና ሰው ሴራ ቢጠነሰስ፡ በውሸት በቅጥፈት መርከዙ ቢከሰስ፡ መርከዙ ልምዱ ነው ባጢልን መከስከስ፡ በነጋ በመሸ ተንኮል ቢቀምሩም፡ በፅኑው መርከዝ ላይ ምንም አልፈጠሩም፡ ከወዳ ከወድህ#ሙፍቲኖች ቢዘሉም፡ ፈዩሾች በተንኮል የሚጠፉ አይደሉም፡ በውሸት ትረካ ይጠፋል መስሏቸው፡ #ፈዩሽ እየፀና አልወድቅም አላቸው፡ ረግጧቸው ዘምቷል እንኳን ሊሰማቸው፡ ትርጉም አልባ ሆኖ ቀረ ልፋታቸው፡ የሱና ጠላቶች ወይ ማሳዘናቸው‼️ ------------------------------------------- ምላስን በመሳል በማሾል ከሲኪን፡ ምኞትን ማሳካት አይቻልም ሚስኪን፡ በእውቀት ጠንክሩ ቢጠቅማችሁ ላኪን፡ ይህን ትልቅ መርከዝ ጠማሞች ቢገፉት፡ ለርሱ ገቢ ሆኖ የበለጠ አሰፉት፡ የወደደ ይውደድ የከፋውም ይክፋው፡ መርከዘል__ፈዩሽን፤ ከጌታችን ውጭማንም አያጠፋው፡

በሑዘይፋ መስጂድ ሲቀርብ የነበረው የመንሀጁ ሳሊኪን ኪታብ ደርስ ተጠናቋል፣ አልሐምዱ ሊላህ። በቀጣይ የምንጀምረው - ኪታቡ ገበያ ላይ የሚገኝ ከሆነ - የኢብኑ ተይሚያን አልሐመዊያህ ይሆናል፣ ኢንሻአላህ። ኪታቡ ካልተገኘ የምንጀምረውን ኪታብ አሳውቃለሁ፣ ኢንሻአላህ። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ኢብራሂም ኢብኑ አድሃም (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦ "ከሰዎች ጋር ምን አገባኝ!! በእናቴ ሆድ ውስጥ ብቻዬን ነበርኩ፤ ወደዚች ዓለም የወጣሁት ብቻዬን ነው፤ የምሞተውም ብቻዬን ነው፤ ወደ ቀብሬ የምገባው ብቻዬን ነው፤ የምጠየቀው ብቻዬን ነው፤ ከመቃብሬ የምቀሰቀሰው ብቻዬን ነው፤ የምተሳሰበውም ብቻዬን ነው፤ ጀነት ብገባ ብቻዬን እገባለሁ፤ እሳት ብገባም ብቻዬን እገባለሁ፤ በእነዚህ ሁሉ ሁኔታዎች ውስጥ ማንም አይጠቅመኝም። ታዲያ ከሰዎች ጋር ምን አገባኝ!!" — ኢቃዙል ሂመም፣ በኢብኑ አጂባ [1/176]

በነገራቹህ ላይ በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ጊዜ ለመፃፍ አስብና እትወዋለሁ። የተውኩትም ኸይርን ያሰቡ በርካታ የቻናል፣ የግሩፕና የ"ዋቭ" ባለቤቶች ፅሁፌን በመልካም ሳይረዱት ይቀሩና አንድም ቅር እንዳይሰኙብኝ ሲቀጥል ደግሞ ሰዎችን ከኸይር ማሰናከል እንዳይሆን በሚል ስጋት ነበር። የቻናል ማሳደጊያ ተብለው በሚለቀቁ ማስታወቂያና ጥያቄና መልስ ምክኒያት እኔን ጨምሮ ብዙ ሰዎች ከምንወዳቸው የሱና ወንድሞች ቻናል ለመውጣት ተገደናል። ምክኒያቱም የቴሌግራም ተጠቃሚ የሚፈልገው ከሁሉም የተለያዩ ቻናሎች የተለያዩ ቁምነገሮችን መውሰድ እንጅ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ቻናሎች ተመሳሳይ ማስታወቂያና ጥያቄና መልስ ማንበብ አይደለም። ለማንኛውም ወንድሜ አቡ ሱፍያን ጀዛከላሁ ኸይራ = t.me/Abu_lmran_Alaseriy

እውነቱን ለመናገር፣ በአሁኑ ወቅት በንቃት የምከታተላቸው የቴሌግራም ቻናሎች ከአምስት እንኳ አይበልጡም። ቴሌግራም እንደ ቀድሞው ማራኪነቱ ቀርቶ እጅግ አሰልቺ መድረክ እየሆነ መጥቷል። በተለይ "ዋቭ" በሚል ሰበብ የሚለጠፉት የቻናል ማሳደጊያ ማስታወቂያዎች ቻናሎችን ከመረጃና ዕውቀት ማዕከልነት ይልቅ ወደ አደባባይ ልመና ቀይረዋቸዋል። በዚያ ላይ አስር አድሚን ተሹሞበት፣ እንደ ሰፈር ስብሰባ እያንዳንዱ ሰው የፈለገውን እየረጨ የሚወጣበት የተዘበራረቀ ጓዳ ሆነዋል። ሐቂቃ ኢኽላስ እና የሚጨበጥ ጠቃሚ ይዘት ያለው ሰው እንዲህ ዓይነት የቁጥር ብዛት አያስጨንቀውም። ያለ ምንም ማስታወቂያ በይዘታቸው ጥንካሬ ብቻ ከዜሮ ተነስተው በአስር እና በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ተከታዮችን ያፈሩ ብዙዎች አሉ። ቻናል ማስተዳደር ቀላል ነገር ሳይሆን ትልቅ አማናና ኃላፊነት ነው። የቁጥር መብዛት ሳይሆን ተከታዮቻችሁን ማክበር እና ለነሱ የሚመጥን ጥራት ያለው ነገር ማቅረብ ይቅደም።ይዘታችሁ ይመስክርላችሁ፤ ተከታይ በራሱ ይመጣል! t.me/AbuSufiyan_Albenan

ስለ ሽርክ   የተደረጉ በውድ እና በሱና ኡስታዞች  ሙሓደራወች ስብሰብ በቀላሉ ለማገኘት👇👇👇👇👇👇
የተለያዩ መሳጭ ዳእዋወች ርዕሶቹ ከዚህ በታች ናቸው ርዕሱን አንዲ ብቻ በመካት  ማዳመጥ ይችላሉ ➍❹አከባቢ ሙሓደራወች
❶ ሽርክ ታላቁ በደል ❷ከሽርክ ለመውጣት ❸የቀብር አምልኮ ❹ሽርክ ሲፈርስ ❺ሽርክ ላይ መዳረሻ ምክናያቶች ❻ለምን ሽርክ ይፈፀማል ❼ሸይኽ ኑሩ ሁሴን እና ሽርክ ➑በዱአ ስም የሚሰራ ሽርክ ❾ የሽርክአስከፊነት ➓ትንሹ ሽርክ ❶❶ሽርክ እና ተያያዥ ነገሮች ❶❷ሽርክ ምንድነው ❶❸የአብሬት ሽርክ ❶❹መጠበቅ በአላህ ብቻ ነው ❶❺የሽርክ አደገኛነት ❶❻ወሎ ላይ ሽርክ በየአይነቱ ❶❼ስለሽርክ ❶➑ሽርክ ❶❾ሽርክ ከወንጀለኞች ሁሉ የከፋ ነው ❷0የሽርክ አደጋ ❷❶ከሽርክ ነፃ መውጫ መንገዱ ❷❷አብሬት እና ሽርክ ❷❸ሽርክ ሸይኽ አወል ❷❹ሽርክ እና ማህበረሰባችን ❷❺ከአላህ ውጭ ማረድ ሽርክ ነው ❷❻በገድ ማመን ሽርክ ነው ❷❼ሽርክ ሲኮታኮት ❷➑ትንሹ ሽርክ ዩዩልኝ እና ይስሙልኝ ❷❾አላህ ሽርክን አይምርም ❸0የሽርክ ሰወች ቅጥፈት ❸❶ርዕሱ አይቀርም ❸❷ደገር እና ሽርክ ❸❸የሽርክ አስከፊነት ❸❹ስለ ሽርክ እና ንፍቅና ❸❺ሽርክ ማለት ምን ማለት ነው ❸❻ሽርክ እና ውደታ ❸❼በመታዘዝ የሚመጣ ሽርክ ❸➑ግጥም ስለ ሽርክ ❸❾ሽርክን ኑዛዜ ❹0የሽርክ ተግባር ❹❶የሽርክ ጠበቃ አትሁን ❹❷መጠንቆል ሽርክ ነው ❹❸የአህባሽ ቲቪ እና ሽርክ ❹❹ሽርክን ተጠንቀቁ