uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Kanalga Telegram’da o‘tish

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
906
Obunachilar
-124 soatlar
-127 kun
+4430 kun
Postlar arxiv
አብሮ ላለመቆየት ስህተትህን የሚፈልግ እንዳለ ሁሉ አንተን ላለማጣት ሲል ብቻ ለስህተቶችህ አይኑን የሚጨፍን አለ። አጂብ ነው!!! የቴሌግራም ቻናል http://t.me/Abulabas1444 http://t.me/Abulabas1444

"በእንቁላሌ በቀጣሽኝ!" ~ "ከነቢ ሙሐመድ በኋላ ሌላ ነብይ አይመጣም። ይገባሀል አይደል? እንዲህ ተቸገርን። ወልይ ካልኩትስ ምን ትላለህ?" ይሄ እንግዲህ ሰሞኑን በመጅሊሱ መሪ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበ መወድስ ነው። ይህንን ንግግር እንደ ሙስሊም የምንቃወመው የመንግስት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ወይም ያኮረፉ አሕባሾች በሚያዩት መነፅር እየተመለከትን አይደለም። ይልቁንም ከኢስላማዊ መርህ አንጻር ነው። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙስሊም አለመሆን የሚታወቅ ነው። ሙስሊም ያልሆነን አካል በዚህ መልኩ መግለፅ ደግሞ ከባድ ጥፋት ነው። እንኳን ሙስሊም ያልሆነን ሰው፣ ሙስሊም የሆነን ደግ መሪ እንኳ በዚህ መልኩ መግለፅ ድንበር ማለፍ ነው። በኢስላም በደጋጎች ላይ ድንበር ማለፍን የሚያስጠነቅቁ የሸሪዐ ማስረጃዎችና የዑለማእ ማሳሰቢያዎች ብዙ ናቸው። ዛሬ ዛሬ ግን ሙስሊም ባልሆኑ አካላት ላይ ድንበር ስለማለፍ እንድንነጋገር እየተፈረደብን ነው። አላሁል ሙስተዓን! ልብ በሉ! እንዲህ ዓይነት ጥፋት ሲገጥመን የመጀመሪያችን አይደለም። ምን ማለት ፈልጌ ነው? እንዲህ አይነት ጥፋቶችን ማውገዝ ያለብን የጠቅላዩ ሁኔታ ሲደብረንና ስናኮርፍ እየጠበቅን አይደለም። እንዲህ አይነቱ አካሄድ የፖለቲከኛ እንጂ የዲን አካሄድ አይደለም። የአሁኑ የሐጂ ኢብራሂም ጥፋት ጫጫታ የበዛበት ጥፋቱ ከባድ ስለሆነ ብቻ አይደለም። ይልቁንም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ያኮረፈው ህዝብ ስለበዛ ነው። እንጂ ከዚህ ጥፋት ጋር ተመሳሳይ ወይም የሚቀርቡ ብዙ ጥፋቶች ከዚህ በፊት ተፈጽመዋልኮ። ያኔ ግን ልክ እንዳሁኑ የሐጂ ኢብራሂም ሁኔታ አብዛኛው ህዝብ ምርቃና ላይ ነበር። በዚያን ሰሞን ስለ ጠቅላዩ የተባሉትን ላስታውሳችሁ:- * አደም ካሚል፡ "ሙሳም ቢመጡ፣ ዒሳም ቢመጡ ፣ ነብያችን ሙሐመድም ቢመጡ..." እያለ ዘግናኝ ንፅፅር ሲሰራ አይተናል። ያኔ ይህንን ንግግር ስንተች አሁን ከሚንጫጫው ውስጥ ቀላል የማይባለው ሲሰድበን ነበር። ሌላው ደግሞ ጥፋቱን እንዳላየ እንዳልሰማ ፀጥ ብሎ ነበር። የአደም ካሚል ንግግር ከአሁኑ የመጅሊሱ መሪ ንግግር ያነሰ ነው ወይ? * የ"ሙፍቲ" ዑመር ደጋፊዎች በአሁኑ የሐጂ ኢብራሂም ጥፋት ጮቤ ሲረግጡ እያየን ነው። "ሙፍቲው" ጠቅላይ ሚኒስትሩን "ከሰማይ የወረደ መለይካ ይመስላል" ያሉበትን የረሳን መስሏቸው ይሆን? ወይስ ይሄኛው ጥፋት ቀላል መስሏቸው ነው? "መለስ የጀነት ነው" ሲል የነበረው የነ ያቁተል ዐርሽ ጀማዐ ዝም ቢል ይሻለው ነበርኮ። * "ያ በዲዐ ዘማን" የሚል ረጅም መወድስ በዐረብኛ የፃፈ ዳዒያም አለ። አሁን ላይ አዲስ አበባ ውስጥ ኢማም መሰለኝ። የአፄዎቹን ዜና መዋእል ሲፅፉ የነበሩትን ደብተራዎች የሚያስታውስ አካሄድኮ ነው የሄዱት። * ጠቅላዩ ሙስሊም ነኝ ባላለበት "ከፊርዐውን ቤት የወጣ ሙሳ ነው"፣ "ከዑመር ብኑ ዐብዲል ዐዚዝ ወዲህ አምሳያው አልታየም"፣ "ከዐረብ መሪዎች ይሻላል"፣ "ከሸይኽ ረቢዕ ይሻላል" እየተባለ ሲፃፍ አይተናልኮ። * አቡበክር አለሙ:- (إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَاهُ عَلَيْكُمْ وَزَادَهُ بَسْطَةً فِي الْعِلْمِ وَالْجِسْمٌِ) በማለት ስለ ጧሉት በቁርኣን የተወሳውን ሙስሊም ላልሆነው ሰው ሲሸልም ነበር። * የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር ልክ እንደ ደዕዋ መስጂድ ውስጥ ከፍተው በማይክ ሲያሰሙ የነበሩ አካላት አሉኮ። የሚገርም እብ^ ደትኮ ነው ያለፈው። * "መኖር ከጀመርን ገና ሶስት ወራችን" እስከማለት የደረሱም ነበሩ። እንዲያውም ይሄ በንፅፅር ቀላሉ ነው። ይሄ ሁሉ ሲሆን "ኧረ አላህን እንፍራ!" በማለት ባደባባይ ደፍሮ የተናገረ ምን ያህል ሰው ነበር?! በሃገራችን አንድ አባባል አለ። ልጅ ከጎረቤት እንቁላል እየሰረቀ ሲያመጣ እናት እየተቀበለች ስትበላና ስታበላ ቆይታ፣ ልጅ አመሉ ስር ሶዶ አ^ህያ ሰርቆ ይያዛል። አ^ህያው ላይ አስቀምጠው በህዝብ መሀል "እኔን ያየ ይቀጣ" እያስባሉ ሲያዞሩት እናት አይታ ስትሸማቀቅ ልጅ ምን አላት? "በእንቁላሌ በቀጣሽኝ!" ብቻ የሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ዘግናኝ ንግግር ጥፋትነቱ ለማንም የማይሰወር ነው። እንደምናየውም ብዙ ሰው እየጮኸበት ነው። ከመሆኑም ጋር ትኩረት የሚሹ ነገሮች አሉ። 1ኛ፦ የሐጂ ኢብራሂም ንግግር በሐዲሥ የተገለፀው "አላህ ሆይ! አንተ ባሪያዬ ነህ፤ እኔ ጌታህ ነኝ" በማለት በደስታ ብዛት እንደተሳሳተው ሰው አይነት ጥፋት ነው የሚል አይቻለሁ። ይሄ በጭራሽ ልክ አይደለም። በሐዲሡ ላይ የተገለፀው ሰውየኮ አስቦበት አይደለም ጥፋቱን የተናገረው። ሳያስበው ነው በስህተት ያመለጠው። ያሁኑ እንደዚያ እንዳልሆነ ግልፅ ነው፡፡ በምርቃና/ በነሻጣ መናገር እና ሳያስቡት የሆነ ቃል ማምለጥ የተለያዩ ናቸውኮ። ደግሞም ጥፋቱ ሲስሰማ መደንገጥና ማረም ሳይሆን በተክቢራ ማጀብ ነው የተሰማው። ስለዚህ የጥፋቱን ክብደት ለማቃለል አላስፈላጊ ንፅፅር መጠቀም ተገቢ አይደለም። ተሰራ የተባለው ልማት በዚህ ደረጃ 0ቅልን የሚያስት አድርጎ ማቅረቡም ሌላ የሚገርም ነገር ነው። 2ኛውና ዋናው ማንሳት የምፈልገው በመንግስትም ሆነ በመጅሊስ ኃላፊነት ላይ በየተዋረዱ ላላችሁ መልእክት ማስተላለፍ ነው። እንዲህ አይነት የእምነትን መርሆዎች እየጨፈለጉ ሰዎችን ማወደስ የምታስቡትን ትርፍ ሊያስገኝላችሁ ቀርቶ ውርደትና መንናቅን ነው የሚያመጣባችሁ። አንደኛ ህዝብ ይተፋችኋል። ይሄ ትልቅ ኪሳራ ነው። ሁለተኛ በሹማምንቱም ዘንድ ያስንቃችኋል። ትልቁ አደጋ ደግሞ ከአላህ ጋር መጣላታችሁ ነው፡፡ በተሳሳተ መንገድ ጥቅምንና ክብርን መሻት ውርደትን ነው የሚያመጣው። 3ኛ፦ እንዲህ ዓይነት ጥፋት ሲከሰት በምንም መነሻና ማመሀኛ መከላከል አይገባም። ቢያንስ ዳግም እንዳይደገም ጥፋቱን ማመንና ጫን አድርጎ መነጋገር ነው የሚሻለው። (አንዳንዶች እንደሚሉት ማስተካከያ ይሰጣሉ ብዬ አልገምትም። ከሆነ ቀላል ነገር አይደለም።) ይልቅ እነዚህ የሚያሳቅቁ ጥፋቶች እንዲቆሙ ጫና መፍጠር ነው የሚሻለው። ከሁለት ዓመት በፊት እዚሁ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተናገርኩትን ደግሜ ልናገር፦ "አንዳንድ በመጅሊስ አመራሮች ሚዲያ ላይ የሚቀርቡ ንግግሮች የሚያሳቅቁ ናቸው። አድማጭን የሚያሳቅቅ ወይም ከዲን ጋር የሚጋጭ ንግግር ከሚወጣ ወይ ቀድሞ መዘጋጀት አልያ ፅፎ ማንበብ ይሻላል።" ያሁኑ ይባስ! የሆነ ሆኖ ጩኸታችን መርህ ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይገባል። ውግንናችንም ሆነ ተቃውሟችን እንደ ሙዳችን የሚቀያየር መሆን የለበትም። የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ መንግስት ለሙስሊሞች ያለው ቀረቤታና አያያዝ ካለፉት ስርአቶች ይሻላል ወይስ ይብሳል በሚለው ላይ አተያያችን ልዩነት እንደሚኖረው የሚጠበቅ ነው። ችግሩ ግን ደጋፊውም ሆነ ተቃዋሚው በአመዛኙ "እኔ የያዝኩትን አቋም ካልያዛችሁ" የሚል ፅንፈኛ ነው። የፈለገ ቢሆን ግን ድጋፍም ይሁን ተቃውሞ ዐቅል ሊያሳጣን አይገባም። በዚህ አጋጣሚ ሙስሊም ያልሆኑ አካላት የሐጂ ኢብራሂምን ንግግር በማስታከክ እንደለመዱት "ወሃ^ቢያ" እያሉ እያላዘኑ፣ "ሙፍቲ ዑመር አማራ ስለሆኑ ነው የተገለሉት" እያሉ ወደ ኋላ ተመልሰው ሙሾ እያወረዱ እያየን ነው። እነ አባይ ፀሐዬን እየቀሰቀሰ ህዝበ ሙስሊሙን ለማስመታት ሲሰራ እንደነበረ በራሱ አንደበት የመሰከረን አካል በመና ^ፈቅ የምንቆዝም እንዳይመስላችሁ። የዛሬ ጥፋት ትናንትን አያስናፍቀንም። የዛሬን ለማውገዝ ትናንት ውስጥ አንወሸቅም። በግራም በቀኝም ካለ የዘር ትብታብም ውስጥ አንገባም። ችግር ያለበት ባይጠፋም፣ አብዛኛው ሙስሊም የትናንቱም የዛሬውም ጥፋት ያለምንም ሽፋን

Repost from N/a
⚠️ የምዝገባ ማስታወቂያ 📄 ✨ የ3 ወር የቃኢደቱ ኑራኒያ ኮርስ ✨ 🔘 የኮርሱ ዝርዝሮች፡- ⏺️የኮርሱ ስም፡ የ3 ወር የቃኢደቱ ኑራኒያ ኮርስ ⏺️የኮርሱ ደረጃ:  ለጀማሪዎች ⏺️የሚፈጀው ጊዜ:  3 ወር ብቻ ⏺️የሚሰጥበት ሁኔታ:  በቴሌግራም ላይቭ ⏺️የሚሰጥበት ቀናት: ከሰኞ - ቅዳሜ ⏺️የሚሰጥበት ሰአት: ከቀኑ: 8፡00 - 9፡30 ምሽት፡ 2፡30 - 4:00 ⏺️የአንድ ወር ክፍያ: 400 ብር ብቻ ⏺️ ኮርሱ የሚጀመረው: ከመስከረም 1/2019
🥳 የሴቶችና የወንዶች ለየብቻ ነው🥳
💧 ኮርሱን ልዩ የሚያደርጉት:- ✅ ቀላል፣ ግልፅና በጥራት የተዘጋጀ ቪዲዮች ✅ የተግባር ልምምዶች ✅ ሴቶች በሴት ኡስታዛ ✅ ዝቅተኛ የሆነ ወርሀዊ ክፍያ ✅ በሳምንት 6 ቀናት
🔘የሚፈለገው ጥቂት ተሳታፊዎች ብቻ በመሆኑ ፈጥናችሁ ተመዝገቡ ‼️
🖊 ለመመዝገብ ⬇ ✈️ @Al_FurqanMedresa 📞 +251958413872 ላይ ይደውሉ 📚 ፉርቃን አካዳሚ — የስኬትዎ መንገድ!

ወሳኝ ፣ወቅታዊ አሳሳቢ ምክር ነው ባረከላሁ ፊክ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

አንድም ለፍርሀት፤ አንድም ለተስፋ! ስቃይ በሞላበት የሕይወት ሰማይ ስር ስንከንፍ፣ ሞትን ብንመኝም፣ ልባችን ቢደማም መኖረን መርጠን መብረራችንን የቀጠልነው ለሁለት ነገር ስንል ብቻ ነው። አንድም ለ
አንድም ለፍርሀት፤ አንድም ለተስፋ!
ስቃይ በሞላበት የሕይወት ሰማይ ስር ስንከንፍ፣ ሞትን ብንመኝም፣ ልባችን ቢደማም መኖረን መርጠን መብረራችንን የቀጠልነው ለሁለት ነገር ስንል ብቻ ነው። አንድም ለፍርሀት፣ አንድም ለተስፋ። ለፍርሀት ቁጣውንና ቅጣቱን ሸሽተን፤ ለተስፋ ደግሞ እዝነቱንና ውዴታውን ከጅለን። አላህን መፍራት አንዱ ክንፍ ሲሆን፣ እዝነቱን መከጀል ደግሞ ሌላኛው ክንፍ ነው። ቀልባችን በወንጀል ፍላጻ ስትወጋ፣ ፍርሀቱን ጥለን «አብሽር አላህ መሀሪ ነው» ብለን፣ በተስፋ ብቻ ለመብረር ከሞከርን፣ ከሰርን፣ ጣፋንም። በአንድ ክንፍ መብረር የለም። ከፍታ የለም። ሰላም የለም። ነፃነት የለም። ማረፍም የለም። እዝነቱንም ጥለን ቅጥ ባጣ ሰቆቃ ተስፋ ቆርጠን በፍርሀት ከከነፍን፣ አሁንም ውድቀት፣ አሁንም ዝቅጠት ነው። ቀልባችን ብትሞትም፣ በወንጀል የቆሰለውን ልባችን በአላህ ውዴታ እያከምን፣ በተስፋና በፍርሀት ክንፍ ከፍ ብለን መብረራችንን እንቀጥላለን።  እንጂማ ድሮ ወድቀን ነበር፤ ድሮም ሞተን ነበር። በስቃዩ ዓለም ስትበሩ አንዳዴ መንገዱ ይረዝማል። የተስፋ ክንፋችሁ ይዝላል። «እንደው መቼ ይሆን ከማረፊያዬ የምደርሰው?! መቼ ይሆን ነፍሴ እርፍ የምትለው?» ትሉ ይሆናል። ግን አብሽሩ! ዱንያ መቼም የሙስሊም ማረፊያው አይደለችም አይደል? ግድ የለም!  በተስፋ፣ በፍርሀትና በላህ ውዴታ መብረራችንን እንቀጥል። ጀነት ላይ እርፍ እስክንል ድረስ! ✍️ ኢብኑ አይደሩስ

በአካባቢያችሁ ስም ዲናችሁን መማማሪያ፣ አንገብጋቢ መልእክቶችን መለዋወጫ፣ መሻይኾችን፣ ደረሶችንና አቅመ ደካማ ወገኖችን ማገዣ፣ ጎበዝ ተማሪዎችን ማበረታቻ፣ ... የቴሌግራም ወይም መሰል መሰባሰቢያ ግሩፕ/ ቻናል ይኑራችሁ። * ከቻላችሁ የራሳችሁን፣ ካልተቻለ ከሌሎች ምንጮች በመውሰድ ጠቃሚ መልእክቶችን ማሰራጨት፣ * ከማህበራዊ ሚዲያ ባለፈ መሬት ላይ ስራ እንዲኖር እንዳቅማችሁ ሞክሩ። * አካባቢያችሁ ኢስላማዊ እውቀት የራቀው ከሆነ የትምህርት አሰጣጡ የህብረተሰቡን የግንዛቤ መጠን ያገናዘበ ይሁን። በቅድሚያ መሰረታዊ የእስልምና ክፍሎች ማሳወቅ፣ ከከባባድ ወንጀሎች ማስጠንቀቅ፣ መተዛዘንና መተባበር እንዲኖር መስራት ላይ ማተኮር፣ * በተቻለ መጠን ትምህርታችን ቁርኣን እና ሐዲሥ ላይ ያተኮረ ይሁን። የመሻይኾች ስም በሌሎች አካላት ቀድሞ የጠለሸ ከሆነ ስም እየጠቀስን ከምናስበረግግ የምንፈልገውን መልእክት ቁርኣን እና ሐዲሥ ላይ ተመስርተን ብናስተምር። ካስፈለገ ብዙም ስማቸው ግርታ የማያስነሳ የሆኑ የጥንት ዑለማኦችን ማጣቀስ፣ * ስብስቡ ከህብረተሰቡ አቅም በላይ የሆኑ ቡድናዊ ጉዳዮችን በማቀንቀን መነታረኪያ እንዳይሆን መጠንቀቅ፣ * ቁርኣን ለልጆች የምናስተምርበት መንገድ የተሻለ ጥራት እንዲኖረው መጣር፣ * በደረስነት ላይ የተሰማሩ ተወላጆች ካሉ በምንችለው መልኩ ከጎናቸው መቆም። ሁልጊዜ ኡስታዝ ፈልጉልን ከማለት የራስን ልጅ እንደማብቃት ያለ የተሻለ አማራጭ የለም። ሩቅ የመሰለን ነገር ባጭር ጊዜ ይሳካል። ከጎኑ ስንቆም አደራም እያሸከምነው እንደሆነ ይታወቅ። * ለአቅመ ደካማ ተማሪዎች የዓመቱ መጀመሪያ ላይ ዩኒፎርም፣ ደብተር፣ ... አስተባብሮ ማቅረብ እና የተሻለ አፈፃፀም ያላቸውን መጨረሻ ላይ በመሸለም ሌሎቹን ማነቃቃት ትልቅ ስራ ነው። ሲታገዝ የነበረ አንድ ተማሪ ተሳክቶለት ቁም ነገር ላይ ቢደርስ አካባቢውን፣ ወገኑን አይረሳም። * በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ መተጋገዝ ለደዕዋ ስራ በጣም አስፈላጊ ነውና በዚህም ላይ መስራት ይገባል። ረዳት የሌላቸው እናቶችንና አባቶችን ማገዝ፣ ያዘመመ ጎጇቸውን ማቃናት፣ እርሻ ካላቸው አስተባብሮ ማረስ፣ የቲሞችን መርዳት፣ ወዘተ. * ወጣቱን ከሱስ ለማውጣት ከማስተማር ባሻገር ከዲናቸው እንዳይርቁ አድርጎ አማራጮችን መዘርጋት። ለምሳሌ የእግር ኳስ እና የመረብ ኳስ ማመቻቸት፣ የቴኳንዶና መሰል ስልጠናዎችን ማመቻቸት፣ * በዓመቱ መጨረሻ ላይ የተሰሩ ስራዎችን ለህበረተሰቡ በማቅረብ የተሻለ ትስስርና መነቃቃትን መፍጠር፣ * በተለያዩ አካባቢዎች የተበተኑ ተወላጆችን ማስተባበር። ለስራው እገዛ የሚያደርጉ ከሆነ አፈፃፀሞችን በማሳየት ላይ ማስረጃ የሚሆኑ የፎቶና የቪዲዮ ማስረጃዎችን ለሚመለከታቸው አካላት ማቅረብ የተሻለ መተማመን እንዲኖር፣ ሌሎች አህለል ኸይሮችን ለማሳየት እና ማህበረሰቡን ለማነሳሳት መጠቀም ዑለማኦች የሚፈቅዱት ነው። ለምሳሌ ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ ሱለይማን አር-ሩሐይሊይ፣ ወዘተ. * በማስተባበር ላይ የሚደክሙ አካላትን ሞራላቸው እንዳይቀዛቀዝ ትርጉም ያለው እገዛ ማድረግ፣ * ወሳኝ እገዛ የሚያደርጉ ወገኖችን ማመስገን እና ኢኽላሳቸውን በማይጎዳ መልኩ እውቅና መስጠት፣ * ባጠቃላይ ሂደቱ ላይ አላህን መፍራት፣ ኢኽላስ፣ ሙታበዐህ፣ ስሜትን መቆጣጠር፣ ስክነት፣ ... እንዳይርቀው አጥብቆ መመካከር ይገባል። እንዲህ አይነት ስራ ላይ ንትርክና መለያየት የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ነውና አስቀድሞ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። እነዚህ እና መሰል ስራዎች በያካባቢው ቢሰራባቸው ውጤታቸው ቀላል አይደለም። ድንገት አላህ ያለለት ሊሰራው ይችላል በሚል ነው ማስታወስ የፈለግኩት። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ሙታንን ስለ መጣራት፣ ከአላህ ውጪ አትለምን፣ የማይጎዳ የማይጠቅም፣ ይሄን ካርክ አንተ ትሆናለህ ዟሊም፣ የሞተን ከአላህ ውጪ ሌላን የሚጠራ፣ ጀሀነም ይገባል በአላህ ያጋራ፣ ስለት የሚገባው ለአላህ ብቻ ነው፣ በሞተ መሳሉ ትርፉ ኪሳራ ነው፣ ለጌታህም ስገድ ለጌታህ እረ፣ በየ ቀብሩ እየሄድክ አትወላገድ፣ ከቁርአን የለ ከፊቂህ ከሱንና፣ ከምን የመጣ ነው ይህ ሁሉ ፈተና? በየ አመት ሲመጣ ጥቅም አስራ አምስት፣ ሰው ሁሉ ይጓዛል በቀን በሌሊት፣ ኮርማ እየሳበ ስንቅ እየሰነቀ፣ ከመንገድ ይገባል እየተሳሳቀ፣ እየሄደ እያለ ሲጠፋው መንገድ፣ አንቱ ምሩኝ ይላል ሸሪፍ የኔ ውድ፣ ይሄንን ሲሰማ ሸይጧን አባ ሞራ፣ ያካብባቸዋል በቀኝም በግራ፣ ከዛ ይነሳና አንዱ ዘያርተኛ፣ የአባባ ኮርማ ነህ መንገዱን ምራኛ፣ እያለ ፍየሉን ከምንገድ ሲያስገባው፣ ደገር ይደርሳሉ ሸይጧን እየሳበው፣ ከኋላየም ግፉኝ ከፊቴም ሳቡኝ፣ አባባ ያላንቱ እኔ ማን አለኝ፣ የቦረና ጌታ ሸህዬ የደገሩ፣ ሁሉን የምታውቁ የገባሁ ሚስጥሩ፣ ሚስቴም አልወለደች አልሞላም ጎታዬ፣ ጥላት በዝቶብኛል ከፊት ከኋላዬ፣ በአንቱ እጅ ነው ያለው እድሜና ጤናዬ፣ እስኪ አንቱ ግቡበት የኔ አባባዬ፣ እያለ ብሶቱን ከውስጡ ያወጣል፣ ከሞተ ሰው እና ካለ ማን ይበልጣል? እያንጎራጎረ ሲደርስ ባቄሎ፣ ጓዝና ኮርማውን ለጓደኛ ጥሎ፣ እያለ ይጮሀል መጣሁኝ አባባ፣ ሐጃዬ ወጥቶልኝ ይዘ ሐምድ ገባ፣ አፈር እየበላ ድንጋይ እየሳመ፣ ጉሪያ ይጀምራል በአንድ እግሩ እየቆመ፣ የሙታንን ቀብር ሲዞሩ እያደሩ፣ እንቅልፍ የላቸውም በሺርክ የሰከሩ፣ እዛ በመሄዱ የሚያገኝ መስሎታ፣ የሱ እድል በአዘል ተቀድሮለታል፣ አላህ ያልሰጠውን ሰው ላያድለው፣ አላህ የሰጠውን ሰው ላይከለክለው፣ እንዲሁ በከንቱ ሰው ሁሉ ይለፋል፣ አገኛለሁ ብሎ በየ ቀብር ይደፋል፣ ኧረ አይጠቅማችሁም ተው አትሳሳቱ፣ ከተውሒድ አትውጡ መንገድ አትሳቱ፣ ወደ አላህ ብቻ ነው የኛ መለመኛ፣ ድካም የሌለበት ሁሌም የማይተኛ፣ ሳይደክም መጋቢ ለዓለም ፍጥረት፣ ሁሌ አስተናባሪ በማታም በጧት፣ መሬት ሲዘረጋ ከአንድ ጎን ወጠሩ፣ ጭቃም አቡክተዋል አደም ሲፈጠሩ፣ እያሉ የሚያወሩ የወሬ ማስጠሎ፣ ይሄንን ከአላህ ውጪ ከቶስ ማን ችሎ፣ ኧረ ተው ሰዎች በአላህ አታጋሩ፣ ፍርደ ገምድል አንሁን ሳይገባን ሚስጥሩ፣ በሕይወት እያለህ ለድን ልፋ ትጋ፣ ጀነት ነው ክፍያህ የልፋትህ ዋጋ፣ መንገድህን ቀይር ወደ ተውሒድ ግባ፣ ራስህን ለውጥ ቀብር ሳትገባ፣ ከቀብር ስንገባ ብዙ አለ ጥየቃ፣ እህን ጊዜ ጠንክር ወገኔ ተው ንቃ፣ በዱኒያ አንታለል እሷ ናት ጨምላቃ፣ አዳልጦ እንዳይጥለን የወንጀሉ ጭቃ፣ አላህ ቀጥ ያድርገን በእስልምና ላይ፣ በፅናት እንኑር አንሁን ወላዋይ፣ ✍በወንድም ሙሐመድ ሐጅ የቴሌግራም ቻናል፦ ¤t.me/kelelaqiratcenter/3216 ¤t.me/kelelaqiratcenter/3216 የቴሌግራም ጉርፕ፦ ¤t.me/yeselefyadaewakelela ¤t.me/yeselefyadaewakelela

اللهم اغفر للعلامة محمد ناصر الدين الألباني، وارحمه رحمةً واسعة، وارضَ عنه، وتقبّل ما قدّم من علمٍ ونصحٍ وخدمةٍ لكتابك وسنة نبيك ﷺ. اللهم اجزه عن المسلمين خير الجزاء، وارفع درجته في المهديين، واجعل علمه الذي علّمه ونشره صدقةً جاريةً له إلى يوم الدين. اللهم نوّر قبره، وآنس وحشته، ووسّع مدخله، واجعل قبره روضةً من رياض الجنة، واحشره مع النبيين والصديقين والشهداء والصالحين. اللهم اجمعنا وإياه في جنات النعيم، برحمتك يا أرحم الراحمين. اللهم آمين.

‏﴿ رَبِّ إِنِّي لِمَا أَنزَلْتَ إِلَيَّ مِنْ خَيْرٍ فَقِيرٌ ﴾

Repost from N/a
➲ የሱና ቴሌግራም ቻናላችሁን እና ግሩፓችሁን ባጭር ግዜ ዉስጥ በነፃ ማሳደግ የሚያስችል ዌቭ በአዲስ መልክ ጀምረናል 🍖በነፃ ነዉ ፈጥነው ያስመዝግቡ 🍒       ➦ ከ #300 በላይ ተከታዮች ከ #500 እና #1000 በላይ ተከታዮች ላላቸው  🍯 የሱና ቻናል ለማስመዝገብ አናግሩኝ  👉 @Quran_mylife1

Repost from N/a
🚨ፈጥኖ ማን ይመልስ ‼️🏃‍➡️🏃‍➡️ ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  ብዙ  ጠቃሚ ኢስላማዊ ቻናሎችን add የሚለውን በመጫን ያገኛል ። Free promoter👉 @selluhi 👉ጥያቄ፦  ቁርዓን ስንት ምዕራፍ አለው⁉

አንዳንድ መጥፎ አጋጣሚዎች ባይመጡ ኖሮ ወዳጂ እና ጠላትን መለየት አንችልም ነበር።

የብዙዎቻችን የውስጥ ስብራት የሚገልጽ "አንድ ሀቅ" አለ።እሱም ሕመም መጀመሪያ ላይ "እንግዳ" ነው፤ በኋላ ግን "መኖርያ" ይሆናል። መድኃኒት መፈለጋችንን የምናቆመው ሕመሙ ጠፍቶ ሳይሆን፣ ሕመሙ የኛ አንድ አካል ሆኖ ስለሚዋሃድህ ነው። "የሆነ ጊዜ ላይ... ሕመማችንን ማከም እንተዋለን፤ ተሽሎን ሳይሆን ሕመሙን ለምደነው ነው።" ይህ ንግግር በውስጡ ብዙ ያልተነገሩ ታሪኮችን ይዟል። መጀመሪያ ላይ ሕመም (የልብ ስብራት፣ህመም ስቃይ የሰው መራቅ፣ ማጣት ወይም ተስፋ መቁረጥ) ሲመጣብን እንታገላለን። እናለቅሳለን፣ መፍትሄ እንፈልጋለን፣ "ለምን እኔ?" ብለን እንጮኻለን። ያኔ ሕመሙ እንደ እሳት ይፋጃል። ነገር ግን ጊዜ እያለፈ ሲሄድ፣ ጩኸታችን ወደ ዝምታ ይቀየራል። የቆሰለው ልባችን መድኃኒት መፈለጉን ያቆማል። ይህ ግን "ድኗል" ማለት አይደለም፤ ይልቁንም ሕመሙ የዕለት ተዕለት ሕይወታችን አካል ሆኗል ማለት ነው። ልክ እንደምንለብሰው ልብስ፣ ልክ እንደምንተነፍሰው አየር... ሕመሙ አብሮን ይውላል፣ አብሮን ያድራል። ✨ ታድያ ሕመምን መልመድ ድክመት ነውን? ✨ በፍጹም! ሕመምን መልመድ ማለት ትልቅ "ጽናት" (Resilience) ማለት ነው። * ሕመሙ እያለ ፈገግ ማለት መቻል፤ * ልባችን እንደቆሰለ ለሰዎች መልካም መዋል፤ * ውስጣችን እየደማ የሰዎችን እንባ ማበስ... ይህ ትልቅነት ነው። መልመድ ማለት ሕመሙን "ማሸነፍ" ሳይሆን ከሕመሙ ጋር "መኖር" መቻል ነው። ብዙዎቻችን ዛሬ የምናሳየው ፈገግታ የጤነኝነት ሳይሆን፣ የለመድነው ሕመም ውጤት ነው። በሰዎች ዘንድ "ጠንክሯል" ተብሎ የሚታሰበው ልብ፣ ውስጥ ውስጡን በጠባሳ የተሞላ ሊሆን ይችላል። 🕯️ ሶብር ሊኖረን ይገባል በእስልምናችን "ሶብር" (ትዕግስት) ማለት ሕመሙ እንዲጠፋ መመኘት ብቻ አይደለም። ይልቁንም ሕመሙ ባለበት ሁኔታ አላህን እያመሰገኑ ቀጥ ብሎ መቆም ነው። "አልሐምዱሊላህ" የምንለው ነገር ሁሉ ስለተስተካከለ ሳይሆን፣ በሕመሙ ውስጥም ቢሆን አላህ የሰጠንን ጥንካሬ ስለምናምን ነው። ⚠️ ወዳጆቼ ለቆሰለው ልባችን እንዲህ እንበለው፦ "ሕመሜን ብለምደውም እንኳ፣ አላህ ነገ የተሻለ ነገር እንደሚሰጠኝ ተስፋ አልቆርጥም። ጠባሳዬ የጥንካሬዬ ምልክት ነው እንጂ የሽንፈቴ አይደለም። ዛሬ ከሕመሙ ጋር መኖር የለመድኩት፣ ነገ ደስታን በደንብ እንዳጣጥም ሊያስተምረኝ ይሆናል።" ባለንበት ሕመም ውስጥ ሆነን ቀጥ ብለን በመቆማችን እኛ ጀግኖች ነን! አላህ ሕመማቸውን ለምደው ሳይሰበሩ ለሚኖሩት ሁሉ ሰላሙንና እረፍቱን ይላክላቸው። የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

الجرح والتعديل من مسائل الاجتهاد الجرح والتعديل من أجلِّ علوم الحديث، وهو قائم على معرفة أحوال الرواة، والنظر في عدالتهم وضبطهم، والموازنة بين أقوال النقاد وقرائن الأحوال؛ ولذلك كان اختلاف أئمة الحديث في الجرح والتعديل من جنس الاختلاف الاجتهادي، وليس كل حكمٍ يصدر عن ناقدٍ يكون قطعيًّا لا يحتمل النظر. قال الحافظ المنذري رحمه الله: «اختلاف المحدثين في الجرح والتعديل كاختلاف الفقهاء عن اجتهاد». ثم قال: «كل ذلك يقتضيه الاجتهاد؛ فإن الحاكم إذا شهد عنده بجرح شخص، اجتهد في أن ذلك القدر مؤثر أم لا؟ وكذلك المحدث إذا أراد الاحتجاج بحديث شخص، ونُقل إليه فيه جرح، اجتهد فيه: هل هو مؤثر أم لا؟» 📚 جواب الحافظ المنذري عن أسئلة في الجرح والتعديل. وقال الخطيب البغدادي رحمه الله في بيان تفاوت أهل النقد: «وليس كلُّ من وُصف بالعلم والمعرفة بأحوال الرواة يكون قوله في ذلك مقبولًا، حتى يكون من أهل المعرفة والتمييز». 📚 الكفاية في علم الرواية. وقال ابن الصلاح رحمه الله في مسألة تعارض الجرح والتعديل: «إذا اجتمع في شخص جرح وتعديل، فالجرح مقدم؛ لأن مع الجارح زيادة علم لم يطلع عليها المعدِّل». 📚 مقدمة ابن الصلاح. وقال النووي رحمه الله: «إذا اجتمع في شخص جرح وتعديل، فالجرح مقدم»، ثم ذكر التفصيل المعروف عند أهل هذا الفن في الجرح المفسَّر وغير المفسَّر. 📚 التقريب والتيسير. وقال السخاوي رحمه الله في بيان اختلاف النقاد وأسبابه: «وقد يختلفون في الجرح والتعديل لاختلاف الاجتهاد». 📚 فتح المغيث بشرح ألفية الحديث. وقال الذهبي رحمه الله، وهو من أئمة هذا الشأن، في بيان أن كلام النقاد ليس على درجة واحدة: «كلام الأقران بعضهم في بعض لا يُعبأ به، ولا سيما إذا لاح لك أنه لعداوة أو لمذهب أو لحسد». 📚 ميزان الاعتدال. وهذا يدل على أن النظر في كلام الناقد نفسه، ومعرفة سببه واصطلاحه، ومقارنة كلامه بكلام غيره، أمرٌ لا غنى عنه. ولهذا قال ابن حجر رحمه الله في بيان اختلاف مراتب النقاد وألفاظهم: «ينبغي أن لا يُحمل كلام الأئمة في الجرح والتعديل على ظاهر واحد، بل يُنظر في اصطلاح كل إمام». 📚 لسان الميزان وما قرره في كتب المصطلح. فالنتيجة: أن الجرح والتعديل علمٌ نقديٌّ اجتهاديٌّ منضبط، لا يقوم على الهوى، وإنما على العلم والقرائن والخبرة؛ ولذلك اختلف أئمة الحديث في كثير من الرواة، وقد يكون الصواب مع أحدهم بحسب قوة الدليل https://t.me/A2mnt

በእስልምና ሚዛን የሚከተሉትን መሰረታዊ ልዩነቶች ማወቅና መለየት ያስፈልጋል፦ ጥፋት(ወንጀል) እና ቢድዓ ይለያያሉ፦ ጥፋተኛ መሆን እና "ሙብተዲዕ" ተብሎ መፈረጅ ይለያያሉ፦ አንድ ሰው በሆነ ነገር ላይ ተሳስቶ ጥፋተኛ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን የሸሪዓ መስፈርቶች ሳይሟሉ እና ከልካይ ነገሮች (እንደ አለማወቅ፣ በስህተት መረዳት) ሳይወገዱ ሰዎችን ወዲያውኑ "ሙብተዲዕ" ብሎ መፈረጅ ድንበር ማለፍ ነው። እነዚህን መሰረታዊ የሸሪዓ ልዩነቶች ሳያውቁና ሳይረዱ ሰዎችን በጅምላ መፈረጅ የመንሃጅ ጥልቀት ማጣትን ያሳያል።      ✍️ አቡ ተይሚያ

قد أفلح من زكاها كلمة للشيخ رشاد الحبيشي في 14 ربيع الأول 1448