قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
رفتن به کانال در Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
907
مشترکین
-224 ساعت
-127 روز
+4630 روز
آرشیو پست ها
Repost from N/a
⚠️ የምዝገባ ማስታወቂያ 📄
✨ የ3 ወር የቃኢደቱ ኑራኒያ ኮርስ ✨
🔘 የኮርሱ ዝርዝሮች፡-
⏺️የኮርሱ ስም፡ የ3 ወር የቃኢደቱ ኑራኒያ ኮርስ
⏺️የኮርሱ ደረጃ: ለጀማሪዎች
⏺️የሚፈጀው ጊዜ: 3 ወር ብቻ
⏺️የሚሰጥበት ሁኔታ: በቴሌግራም ላይቭ
⏺️የሚሰጥበት ቀናት: ከሰኞ - ቅዳሜ
⏺️የሚሰጥበት ሰአት: ከቀኑ: 8፡00 - 9፡30
ምሽት፡ 2፡30 - 4:00
⏺️የአንድ ወር ክፍያ: 400 ብር ብቻ
⏺️ ኮርሱ የሚጀመረው: ከመስከረም 1/2019
🥳 የሴቶችና የወንዶች ለየብቻ ነው🥳💧 ኮርሱን ልዩ የሚያደርጉት:- ✅ ቀላል፣ ግልፅና በጥራት የተዘጋጀ ቪዲዮች ✅ የተግባር ልምምዶች ✅ ሴቶች በሴት ኡስታዛ ✅ ዝቅተኛ የሆነ ወርሀዊ ክፍያ ✅ በሳምንት 6 ቀናት
🔘የሚፈለገው ጥቂት ተሳታፊዎች ብቻ በመሆኑ ፈጥናችሁ ተመዝገቡ ‼️🖊 ለመመዝገብ ⬇ ✈️ @Al_FurqanMedresa 📞 +251958413872 ላይ ይደውሉ 📚 ፉርቃን አካዳሚ — የስኬትዎ መንገድ!
ወሳኝ ፣ወቅታዊ አሳሳቢ ምክር ነው ባረከላሁ ፊክ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
Repost from ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
አንድም ለፍርሀት፤ አንድም ለተስፋ!ስቃይ በሞላበት የሕይወት ሰማይ ስር ስንከንፍ፣ ሞትን ብንመኝም፣ ልባችን ቢደማም መኖረን መርጠን መብረራችንን የቀጠልነው ለሁለት ነገር ስንል ብቻ ነው። አንድም ለፍርሀት፣ አንድም ለተስፋ። ለፍርሀት ቁጣውንና ቅጣቱን ሸሽተን፤ ለተስፋ ደግሞ እዝነቱንና ውዴታውን ከጅለን። አላህን መፍራት አንዱ ክንፍ ሲሆን፣ እዝነቱን መከጀል ደግሞ ሌላኛው ክንፍ ነው። ቀልባችን በወንጀል ፍላጻ ስትወጋ፣ ፍርሀቱን ጥለን «አብሽር አላህ መሀሪ ነው» ብለን፣ በተስፋ ብቻ ለመብረር ከሞከርን፣ ከሰርን፣ ጣፋንም። በአንድ ክንፍ መብረር የለም። ከፍታ የለም። ሰላም የለም። ነፃነት የለም። ማረፍም የለም። እዝነቱንም ጥለን ቅጥ ባጣ ሰቆቃ ተስፋ ቆርጠን በፍርሀት ከከነፍን፣ አሁንም ውድቀት፣ አሁንም ዝቅጠት ነው። ቀልባችን ብትሞትም፣ በወንጀል የቆሰለውን ልባችን በአላህ ውዴታ እያከምን፣ በተስፋና በፍርሀት ክንፍ ከፍ ብለን መብረራችንን እንቀጥላለን። እንጂማ ድሮ ወድቀን ነበር፤ ድሮም ሞተን ነበር። በስቃዩ ዓለም ስትበሩ አንዳዴ መንገዱ ይረዝማል። የተስፋ ክንፋችሁ ይዝላል። «እንደው መቼ ይሆን ከማረፊያዬ የምደርሰው?! መቼ ይሆን ነፍሴ እርፍ የምትለው?» ትሉ ይሆናል።
ግን አብሽሩ! ዱንያ መቼም የሙስሊም ማረፊያው አይደለችም አይደል? ግድ የለም! በተስፋ፣ በፍርሀትና በላህ ውዴታ መብረራችንን እንቀጥል። ጀነት ላይ እርፍ እስክንል ድረስ!
✍️ ኢብኑ አይደሩስRepost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
በአካባቢያችሁ ስም ዲናችሁን መማማሪያ፣ አንገብጋቢ መልእክቶችን መለዋወጫ፣ መሻይኾችን፣ ደረሶችንና አቅመ ደካማ ወገኖችን ማገዣ፣ ጎበዝ ተማሪዎችን ማበረታቻ፣ ... የቴሌግራም ወይም መሰል መሰባሰቢያ ግሩፕ/ ቻናል ይኑራችሁ።
* ከቻላችሁ የራሳችሁን፣ ካልተቻለ ከሌሎች ምንጮች በመውሰድ ጠቃሚ መልእክቶችን ማሰራጨት፣
* ከማህበራዊ ሚዲያ ባለፈ መሬት ላይ ስራ እንዲኖር እንዳቅማችሁ ሞክሩ።
* አካባቢያችሁ ኢስላማዊ እውቀት የራቀው ከሆነ የትምህርት አሰጣጡ የህብረተሰቡን የግንዛቤ መጠን ያገናዘበ ይሁን። በቅድሚያ መሰረታዊ የእስልምና ክፍሎች ማሳወቅ፣ ከከባባድ ወንጀሎች ማስጠንቀቅ፣ መተዛዘንና መተባበር እንዲኖር መስራት ላይ ማተኮር፣
* በተቻለ መጠን ትምህርታችን ቁርኣን እና ሐዲሥ ላይ ያተኮረ ይሁን። የመሻይኾች ስም በሌሎች አካላት ቀድሞ የጠለሸ ከሆነ ስም እየጠቀስን ከምናስበረግግ የምንፈልገውን መልእክት ቁርኣን እና ሐዲሥ ላይ ተመስርተን ብናስተምር። ካስፈለገ ብዙም ስማቸው ግርታ የማያስነሳ የሆኑ የጥንት ዑለማኦችን ማጣቀስ፣
* ስብስቡ ከህብረተሰቡ አቅም በላይ የሆኑ ቡድናዊ ጉዳዮችን በማቀንቀን መነታረኪያ እንዳይሆን መጠንቀቅ፣
* ቁርኣን ለልጆች የምናስተምርበት መንገድ የተሻለ ጥራት እንዲኖረው መጣር፣
* በደረስነት ላይ የተሰማሩ ተወላጆች ካሉ በምንችለው መልኩ ከጎናቸው መቆም። ሁልጊዜ ኡስታዝ ፈልጉልን ከማለት የራስን ልጅ እንደማብቃት ያለ የተሻለ አማራጭ የለም። ሩቅ የመሰለን ነገር ባጭር ጊዜ ይሳካል። ከጎኑ ስንቆም አደራም እያሸከምነው እንደሆነ ይታወቅ።
* ለአቅመ ደካማ ተማሪዎች የዓመቱ መጀመሪያ ላይ ዩኒፎርም፣ ደብተር፣ ... አስተባብሮ ማቅረብ እና የተሻለ አፈፃፀም ያላቸውን መጨረሻ ላይ በመሸለም ሌሎቹን ማነቃቃት ትልቅ ስራ ነው። ሲታገዝ የነበረ አንድ ተማሪ ተሳክቶለት ቁም ነገር ላይ ቢደርስ አካባቢውን፣ ወገኑን አይረሳም።
* በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ መተጋገዝ ለደዕዋ ስራ በጣም አስፈላጊ ነውና በዚህም ላይ መስራት ይገባል። ረዳት የሌላቸው እናቶችንና አባቶችን ማገዝ፣ ያዘመመ ጎጇቸውን ማቃናት፣ እርሻ ካላቸው አስተባብሮ ማረስ፣ የቲሞችን መርዳት፣ ወዘተ.
* ወጣቱን ከሱስ ለማውጣት ከማስተማር ባሻገር ከዲናቸው እንዳይርቁ አድርጎ አማራጮችን መዘርጋት። ለምሳሌ የእግር ኳስ እና የመረብ ኳስ ማመቻቸት፣ የቴኳንዶና መሰል ስልጠናዎችን ማመቻቸት፣
* በዓመቱ መጨረሻ ላይ የተሰሩ ስራዎችን ለህበረተሰቡ በማቅረብ የተሻለ ትስስርና መነቃቃትን መፍጠር፣
* በተለያዩ አካባቢዎች የተበተኑ ተወላጆችን ማስተባበር። ለስራው እገዛ የሚያደርጉ ከሆነ አፈፃፀሞችን በማሳየት ላይ ማስረጃ የሚሆኑ የፎቶና የቪዲዮ ማስረጃዎችን ለሚመለከታቸው አካላት ማቅረብ የተሻለ መተማመን እንዲኖር፣ ሌሎች አህለል ኸይሮችን ለማሳየት እና ማህበረሰቡን ለማነሳሳት መጠቀም ዑለማኦች የሚፈቅዱት ነው። ለምሳሌ ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ ሱለይማን አር-ሩሐይሊይ፣ ወዘተ.
* በማስተባበር ላይ የሚደክሙ አካላትን ሞራላቸው እንዳይቀዛቀዝ ትርጉም ያለው እገዛ ማድረግ፣
* ወሳኝ እገዛ የሚያደርጉ ወገኖችን ማመስገን እና ኢኽላሳቸውን በማይጎዳ መልኩ እውቅና መስጠት፣
* ባጠቃላይ ሂደቱ ላይ አላህን መፍራት፣ ኢኽላስ፣ ሙታበዐህ፣ ስሜትን መቆጣጠር፣ ስክነት፣ ... እንዳይርቀው አጥብቆ መመካከር ይገባል። እንዲህ አይነት ስራ ላይ ንትርክና መለያየት የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ነውና አስቀድሞ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
እነዚህ እና መሰል ስራዎች በያካባቢው ቢሰራባቸው ውጤታቸው ቀላል አይደለም። ድንገት አላህ ያለለት ሊሰራው ይችላል በሚል ነው ማስታወስ የፈለግኩት።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from የከለላ ሰለፍዮች የዳዕዋ እና የቂርዐት ማዕከል ቻናል
ሙታንን ስለ መጣራት፣
ከአላህ ውጪ አትለምን፣
የማይጎዳ የማይጠቅም፣
ይሄን ካርክ አንተ ትሆናለህ ዟሊም፣
የሞተን ከአላህ ውጪ ሌላን የሚጠራ፣
ጀሀነም ይገባል በአላህ ያጋራ፣
ስለት የሚገባው ለአላህ ብቻ ነው፣
በሞተ መሳሉ ትርፉ ኪሳራ ነው፣
ለጌታህም ስገድ ለጌታህ እረ፣
በየ ቀብሩ እየሄድክ አትወላገድ፣
ከቁርአን የለ ከፊቂህ ከሱንና፣
ከምን የመጣ ነው ይህ ሁሉ ፈተና?
በየ አመት ሲመጣ ጥቅም አስራ አምስት፣
ሰው ሁሉ ይጓዛል በቀን በሌሊት፣
ኮርማ እየሳበ ስንቅ እየሰነቀ፣
ከመንገድ ይገባል እየተሳሳቀ፣
እየሄደ እያለ ሲጠፋው መንገድ፣
አንቱ ምሩኝ ይላል ሸሪፍ የኔ ውድ፣
ይሄንን ሲሰማ ሸይጧን አባ ሞራ፣
ያካብባቸዋል በቀኝም በግራ፣
ከዛ ይነሳና አንዱ ዘያርተኛ፣
የአባባ ኮርማ ነህ መንገዱን ምራኛ፣
እያለ ፍየሉን ከምንገድ ሲያስገባው፣
ደገር ይደርሳሉ ሸይጧን እየሳበው፣
ከኋላየም ግፉኝ ከፊቴም ሳቡኝ፣
አባባ ያላንቱ እኔ ማን አለኝ፣
የቦረና ጌታ ሸህዬ የደገሩ፣
ሁሉን የምታውቁ የገባሁ ሚስጥሩ፣
ሚስቴም አልወለደች አልሞላም ጎታዬ፣
ጥላት በዝቶብኛል ከፊት ከኋላዬ፣
በአንቱ እጅ ነው ያለው እድሜና ጤናዬ፣
እስኪ አንቱ ግቡበት የኔ አባባዬ፣
እያለ ብሶቱን ከውስጡ ያወጣል፣
ከሞተ ሰው እና ካለ ማን ይበልጣል?
እያንጎራጎረ ሲደርስ ባቄሎ፣
ጓዝና ኮርማውን ለጓደኛ ጥሎ፣
እያለ ይጮሀል መጣሁኝ አባባ፣
ሐጃዬ ወጥቶልኝ ይዘ ሐምድ ገባ፣
አፈር እየበላ ድንጋይ እየሳመ፣
ጉሪያ ይጀምራል በአንድ እግሩ እየቆመ፣
የሙታንን ቀብር ሲዞሩ እያደሩ፣
እንቅልፍ የላቸውም በሺርክ የሰከሩ፣
እዛ በመሄዱ የሚያገኝ መስሎታ፣
የሱ እድል በአዘል ተቀድሮለታል፣
አላህ ያልሰጠውን ሰው ላያድለው፣
አላህ የሰጠውን ሰው ላይከለክለው፣
እንዲሁ በከንቱ ሰው ሁሉ ይለፋል፣
አገኛለሁ ብሎ በየ ቀብር ይደፋል፣
ኧረ አይጠቅማችሁም ተው አትሳሳቱ፣
ከተውሒድ አትውጡ መንገድ አትሳቱ፣
ወደ አላህ ብቻ ነው የኛ መለመኛ፣
ድካም የሌለበት ሁሌም የማይተኛ፣
ሳይደክም መጋቢ ለዓለም ፍጥረት፣
ሁሌ አስተናባሪ በማታም በጧት፣
መሬት ሲዘረጋ ከአንድ ጎን ወጠሩ፣
ጭቃም አቡክተዋል አደም ሲፈጠሩ፣
እያሉ የሚያወሩ የወሬ ማስጠሎ፣
ይሄንን ከአላህ ውጪ ከቶስ ማን ችሎ፣
ኧረ ተው ሰዎች በአላህ አታጋሩ፣
ፍርደ ገምድል አንሁን ሳይገባን ሚስጥሩ፣
በሕይወት እያለህ ለድን ልፋ ትጋ፣
ጀነት ነው ክፍያህ የልፋትህ ዋጋ፣
መንገድህን ቀይር ወደ ተውሒድ ግባ፣
ራስህን ለውጥ ቀብር ሳትገባ፣
ከቀብር ስንገባ ብዙ አለ ጥየቃ፣
እህን ጊዜ ጠንክር ወገኔ ተው ንቃ፣
በዱኒያ አንታለል እሷ ናት ጨምላቃ፣
አዳልጦ እንዳይጥለን የወንጀሉ ጭቃ፣
አላህ ቀጥ ያድርገን በእስልምና ላይ፣
በፅናት እንኑር አንሁን ወላዋይ፣
✍በወንድም ሙሐመድ ሐጅ
የቴሌግራም ቻናል፦
¤t.me/kelelaqiratcenter/3216
¤t.me/kelelaqiratcenter/3216
የቴሌግራም ጉርፕ፦
¤t.me/yeselefyadaewakelela
¤t.me/yeselefyadaewakelela
Repost from سلسلة الهدى والنور🔊
اللهم اغفر للعلامة محمد ناصر الدين الألباني، وارحمه رحمةً واسعة، وارضَ عنه، وتقبّل ما قدّم من علمٍ ونصحٍ وخدمةٍ لكتابك وسنة نبيك ﷺ.
اللهم اجزه عن المسلمين خير الجزاء، وارفع درجته في المهديين، واجعل علمه الذي علّمه ونشره صدقةً جاريةً له إلى يوم الدين.
اللهم نوّر قبره، وآنس وحشته، ووسّع مدخله، واجعل قبره روضةً من رياض الجنة، واحشره مع النبيين والصديقين والشهداء والصالحين.
اللهم اجمعنا وإياه في جنات النعيم، برحمتك يا أرحم الراحمين.
اللهم آمين.
﴿ رَبِّ إِنِّي لِمَا أَنزَلْتَ إِلَيَّ مِنْ خَيْرٍ فَقِيرٌ ﴾
Repost from N/a
➲ የሱና ቴሌግራም ቻናላችሁን እና ግሩፓችሁን
ባጭር ግዜ ዉስጥ በነፃ ማሳደግ
የሚያስችል ዌቭ በአዲስ መልክ ጀምረናል
🍖በነፃ ነዉ ፈጥነው ያስመዝግቡ 🍒
➦ ከ #300 በላይ ተከታዮች
ከ #500 እና #1000 በላይ ተከታዮች
ላላቸው
🍯 የሱና ቻናል ለማስመዝገብ አናግሩኝ
👉 @Quran_mylife1
Repost from N/a
🚨ፈጥኖ ማን ይመልስ ‼️🏃➡️🏃➡️
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው ብዙ ጠቃሚ ኢስላማዊ ቻናሎችን add የሚለውን በመጫን ያገኛል ።
Free promoter👉 @selluhi
👉ጥያቄ፦ ቁርዓን ስንት ምዕራፍ አለው⁉
አንዳንድ መጥፎ አጋጣሚዎች ባይመጡ ኖሮ ወዳጂ እና ጠላትን መለየት አንችልም ነበር።
የብዙዎቻችን የውስጥ ስብራት የሚገልጽ "አንድ ሀቅ" አለ።እሱም ሕመም መጀመሪያ ላይ "እንግዳ" ነው፤ በኋላ ግን "መኖርያ" ይሆናል። መድኃኒት መፈለጋችንን የምናቆመው ሕመሙ ጠፍቶ ሳይሆን፣ ሕመሙ የኛ አንድ አካል ሆኖ ስለሚዋሃድህ ነው።
"የሆነ ጊዜ ላይ... ሕመማችንን ማከም እንተዋለን፤ ተሽሎን ሳይሆን ሕመሙን ለምደነው ነው።"
ይህ ንግግር በውስጡ ብዙ ያልተነገሩ ታሪኮችን ይዟል። መጀመሪያ ላይ ሕመም (የልብ ስብራት፣ህመም ስቃይ የሰው መራቅ፣ ማጣት ወይም ተስፋ መቁረጥ) ሲመጣብን እንታገላለን። እናለቅሳለን፣ መፍትሄ እንፈልጋለን፣ "ለምን እኔ?" ብለን እንጮኻለን። ያኔ ሕመሙ እንደ እሳት ይፋጃል።
ነገር ግን ጊዜ እያለፈ ሲሄድ፣ ጩኸታችን ወደ ዝምታ ይቀየራል። የቆሰለው ልባችን መድኃኒት መፈለጉን ያቆማል። ይህ ግን "ድኗል" ማለት አይደለም፤ ይልቁንም ሕመሙ የዕለት ተዕለት ሕይወታችን አካል ሆኗል ማለት ነው። ልክ እንደምንለብሰው ልብስ፣ ልክ እንደምንተነፍሰው አየር... ሕመሙ አብሮን ይውላል፣ አብሮን ያድራል።
✨ ታድያ ሕመምን መልመድ ድክመት ነውን? ✨
በፍጹም! ሕመምን መልመድ ማለት ትልቅ "ጽናት" (Resilience) ማለት ነው።
* ሕመሙ እያለ ፈገግ ማለት መቻል፤
* ልባችን እንደቆሰለ ለሰዎች መልካም መዋል፤
* ውስጣችን እየደማ የሰዎችን እንባ ማበስ... ይህ ትልቅነት ነው።
መልመድ ማለት ሕመሙን "ማሸነፍ" ሳይሆን ከሕመሙ ጋር "መኖር" መቻል ነው። ብዙዎቻችን ዛሬ የምናሳየው ፈገግታ የጤነኝነት ሳይሆን፣ የለመድነው ሕመም ውጤት ነው። በሰዎች ዘንድ "ጠንክሯል" ተብሎ የሚታሰበው ልብ፣ ውስጥ ውስጡን በጠባሳ የተሞላ ሊሆን ይችላል።
🕯️ ሶብር ሊኖረን ይገባል በእስልምናችን "ሶብር" (ትዕግስት) ማለት ሕመሙ እንዲጠፋ መመኘት ብቻ አይደለም። ይልቁንም ሕመሙ ባለበት ሁኔታ አላህን እያመሰገኑ ቀጥ ብሎ መቆም ነው። "አልሐምዱሊላህ" የምንለው ነገር ሁሉ ስለተስተካከለ ሳይሆን፣ በሕመሙ ውስጥም ቢሆን አላህ የሰጠንን ጥንካሬ ስለምናምን ነው።
⚠️ ወዳጆቼ ለቆሰለው ልባችን እንዲህ እንበለው፦ "ሕመሜን ብለምደውም እንኳ፣ አላህ ነገ የተሻለ ነገር እንደሚሰጠኝ ተስፋ አልቆርጥም። ጠባሳዬ የጥንካሬዬ ምልክት ነው እንጂ የሽንፈቴ አይደለም። ዛሬ ከሕመሙ ጋር መኖር የለመድኩት፣ ነገ ደስታን በደንብ እንዳጣጥም ሊያስተምረኝ ይሆናል።"
ባለንበት ሕመም ውስጥ ሆነን ቀጥ ብለን በመቆማችን እኛ ጀግኖች ነን! አላህ ሕመማቸውን ለምደው ሳይሰበሩ ለሚኖሩት ሁሉ ሰላሙንና እረፍቱን ይላክላቸው።
የቴሌግራም ቻናል፦
t.me/Abu_hibetillah_AsselfiyRepost from قناة أبي ماهر الأثري الحبشي𝐀bu Mahir )
الجرح والتعديل من مسائل الاجتهاد
الجرح والتعديل من أجلِّ علوم الحديث، وهو قائم على معرفة أحوال الرواة، والنظر في عدالتهم وضبطهم، والموازنة بين أقوال النقاد وقرائن الأحوال؛ ولذلك كان اختلاف أئمة الحديث في الجرح والتعديل من جنس الاختلاف الاجتهادي، وليس كل حكمٍ يصدر عن ناقدٍ يكون قطعيًّا لا يحتمل النظر.
قال الحافظ المنذري رحمه الله:
«اختلاف المحدثين في الجرح والتعديل كاختلاف الفقهاء عن اجتهاد».
ثم قال:
«كل ذلك يقتضيه الاجتهاد؛ فإن الحاكم إذا شهد عنده بجرح شخص، اجتهد في أن ذلك القدر مؤثر أم لا؟ وكذلك المحدث إذا أراد الاحتجاج بحديث شخص، ونُقل إليه فيه جرح، اجتهد فيه: هل هو مؤثر أم لا؟»
📚 جواب الحافظ المنذري عن أسئلة في الجرح والتعديل.
وقال الخطيب البغدادي رحمه الله في بيان تفاوت أهل النقد:
«وليس كلُّ من وُصف بالعلم والمعرفة بأحوال الرواة يكون قوله في ذلك مقبولًا، حتى يكون من أهل المعرفة والتمييز».
📚 الكفاية في علم الرواية.
وقال ابن الصلاح رحمه الله في مسألة تعارض الجرح والتعديل:
«إذا اجتمع في شخص جرح وتعديل، فالجرح مقدم؛ لأن مع الجارح زيادة علم لم يطلع عليها المعدِّل».
📚 مقدمة ابن الصلاح.
وقال النووي رحمه الله:
«إذا اجتمع في شخص جرح وتعديل، فالجرح مقدم»، ثم ذكر التفصيل المعروف عند أهل هذا الفن في الجرح المفسَّر وغير المفسَّر.
📚 التقريب والتيسير.
وقال السخاوي رحمه الله في بيان اختلاف النقاد وأسبابه:
«وقد يختلفون في الجرح والتعديل لاختلاف الاجتهاد».
📚 فتح المغيث بشرح ألفية الحديث.
وقال الذهبي رحمه الله، وهو من أئمة هذا الشأن، في بيان أن كلام النقاد ليس على درجة واحدة:
«كلام الأقران بعضهم في بعض لا يُعبأ به، ولا سيما إذا لاح لك أنه لعداوة أو لمذهب أو لحسد».
📚 ميزان الاعتدال.
وهذا يدل على أن النظر في كلام الناقد نفسه، ومعرفة سببه واصطلاحه، ومقارنة كلامه بكلام غيره، أمرٌ لا غنى عنه.
ولهذا قال ابن حجر رحمه الله في بيان اختلاف مراتب النقاد وألفاظهم:
«ينبغي أن لا يُحمل كلام الأئمة في الجرح والتعديل على ظاهر واحد، بل يُنظر في اصطلاح كل إمام».
📚 لسان الميزان وما قرره في كتب المصطلح.
فالنتيجة: أن الجرح والتعديل علمٌ نقديٌّ اجتهاديٌّ منضبط، لا يقوم على الهوى، وإنما على العلم والقرائن والخبرة؛ ولذلك اختلف أئمة الحديث في كثير من الرواة، وقد يكون الصواب مع أحدهم بحسب قوة الدليل
https://t.me/A2mnt
በእስልምና ሚዛን የሚከተሉትን መሰረታዊ ልዩነቶች ማወቅና መለየት ያስፈልጋል፦
ጥፋት(ወንጀል) እና ቢድዓ ይለያያሉ፦
ጥፋተኛ መሆን እና "ሙብተዲዕ" ተብሎ መፈረጅ ይለያያሉ፦ አንድ ሰው በሆነ ነገር ላይ ተሳስቶ ጥፋተኛ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን የሸሪዓ መስፈርቶች ሳይሟሉ እና ከልካይ ነገሮች (እንደ አለማወቅ፣ በስህተት መረዳት) ሳይወገዱ ሰዎችን ወዲያውኑ "ሙብተዲዕ" ብሎ መፈረጅ ድንበር ማለፍ ነው።
እነዚህን መሰረታዊ የሸሪዓ ልዩነቶች ሳያውቁና ሳይረዱ ሰዎችን በጅምላ መፈረጅ የመንሃጅ ጥልቀት ማጣትን ያሳያል።
✍️ አቡ ተይሚያ
Repost from ዳዕዋ ሰለፍያ በአልብኮ ወረዳ ሶባ እና ጀብል ቀበሌ(አሸዋዉ) ✈
🪴ኢስቲቃማን እንዴት እናምጣ?
በእስልምና ኢስቲቃማ (الاستقامة) ማለት በአላህ ትእዛዝ ላይ ጸንቶ መቆም፣ ከኃጢአት መራቅና በመልካም ሥራ ላይ መቀጠል ነው። በነገራችን ላይ ኢስቲቃማ ማምጣት በተለይ በችግር ጊዜ ትልቅ መፍትሔ ነው።
💎ነገር ግን ኢስቲቃማ ማለት ችግር ፈጽሞ አይመጣም ማለት አይደለም፤ ችግር ሲመጣ በአላህ ላይ ተማምኖ፣ በትዕግሥትና በትክክለኛ መንገድ መቆም ነው።
ኢስቲቃማን እንዴት እናምጣ?
1. እምነትን ማስተካከል – ተውሂድን ማጠናከርና ልብን ከአላህ ጋር ማያያዝ።
2. ግዴታዎችን መጠበቅ – በተለይ አምስቱን ሶላቶች በጊዜያቸው መስገድ።
3. ኃጢአትን መተው – ትንሽ ነው ብሎ ኃጢአትን አለመናቅ።
4. በቁርአንና በሱና ላይ መጠንከር።
5. ዱዓን ማብዛት። ነቢዩ ﷺ በብዛት ይሉ ነበር፦
«يا مقلب القلوب ثبت قلبي على دينك»
“የልቦች ቀያሪ ሆይ! ልቤን በዲንህ ላይ አጽናው።”
6. መልካም ጓደኞችን መምረጥ – ሰው በሚያደርገው አካባቢና ጓደኛ በጣም ይጎዳል ወይም ይጠቀማል።
7. ትንሽ ትንሽ ቢሆንም በመልካም ሥራ መቀጠል። ዋናው ነገር ብዙ ጀምሮ ቶሎ መተው ሳይሆን በቀጣይነት መሥራት ነው።
አላህ ሲል፦
> ﴿إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا تَتَنَزَّلُ عَلَيْهِمُ الْمَلَائِكَةُ أَلَّا تَخَافُوا وَلَا تَحْزَنُوا﴾
“ጌታችን አላህ ነው ካሉ በኋላም ጸኑ፣ መላእክት በእነርሱ ላይ ይወርዳሉ፤ ‘አትፍሩ፣ አትዘኑም’ ይሏቸዋል።” (ፉሲለት 41፥30)
ስለዚህ ኢስቲቃማ በችግር ላይ የሚሰጠን መፍትሔ ነው፣ ነገር ግን ችግሩን በአንድ ጊዜ የሚያጠፋ ፈጣን መፍትሔ አይደለም። ችግሩን እንዴት እንደምንጋፈጠው የሚያስተካክል የልብ ጥንካሬና የሕይወት መንገድ ነው።
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ለሶስቱ "ዝሆኖች"!
~
ትግራዋይ ነኝ ታታሪ - ስራዬን ብቻ የምሰራ
ትብታባችሁ የማይገባኝ - ለፍቶ አዳሪ ነኝ አማራ
ይሁንታችሁ የማያሻኝ - ኦሮሞ ነኝ ዋዠራ
የለት ጉርሴን የማሳድድ - እሩቅ ነኝ ከናንተ ሴራ
ፍጥጫችሁ ማይጥመኝ - ሁሌ የሚሆንብኝ ግራ
ከጫካው አውሬ በላይ - ፍረጃችሁን የምፈራ
አንዱ እንዳይገድለኝ በጨለማ - አንዱ እንዳያስረኝ በጠራራ
ልርቃችሁ የሚከብደኝ - ልቀርባችሁ የምፈራ
ከዝርፊያችሁ የሌለሁኝ - ብጣሽ ያላየሁ ሰባራ
ከፌሽታችሁ ያልታደምኩኝ - ከጭፈራው ከዳንኪራ
ጦሳችሁ ግን የሚተርፈኝ - ባልዋልኩበት የምጠራ
ፍቅራችሁ ለይቶ አግላይ - ጥላችሁ ሁለት ግራ
ምቾት ድሎታችሁ የግል - ሰቀቀናችን የጋራ
የግጭት ጅምላ አቅራቢ - የብሶት የመከራ
ደም መጣጭ እንደ መዥገር - እንብላው ባይ በየተራ
እስቲ አርፋችሁ አሳርፉን - ለሰላም ቁሙ በጋራ።
* አብዛኛው ያገሪቱ ችግር መነሻ የሶስቱ ብሄር #ፖለቲከኞች ስግብግብ ፖለቲካ ነው። ሶስቱም የራሳቸውን ጥለው ወደ ሌላው ጣት ይቀስራሉ። እነሱ ባልተግባቡበት የሃገሪቱ ሰላም የራቀ ነው። በነሱ ጦስ ፍዳቸውን የሚያዩት ከየብሄሮቹ የወጡት ምስኪኖች ናቸው። አላህ ሁሉንም ልቦና ይስጣቸው።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ህዳር 01/2014)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
አልሓሪሥ ብኑ ሐቢብ ስምንት ልጆቹን በሞት አጣ። በዚህ መሀል አንድ በጉ በተኩላ የተበላችበት ሰው አዝኖ ሲያለቅስ አየ። በዚህን ጊዜ አልሓሪሥ ለሰውየው አንዲት ግመል ሰጠውና፦ "ይህችን በበግህ ምትክ ውሰድ፤ ማልቀስን ግን ለሚገባው (እውነተኛ ሐዘን ላለበት) ሰው ተወው" አለው።
📚 ዑዩኑል አኽባር — ኢብኑ ቁተይባህ
"እናቱ የሞተችበትና ገበያ የሄደችበት እኩል ያለቅሳል" ይላል ያገራችን ብሂል። ሆድ የባሰው ሁሉ የከፋ ሁኔታ የገጠማቸውን ቢያስብ አርፎ ይቀመጥ ነበር።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
