ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
Kanalga Telegram’da o‘tish
ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።
Ko'proq ko'rsatishMamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
318
Obunachilar
-424 soatlar
-77 kun
+5430 kun
Postlar arxiv
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
አቡ ሙዓዝ ሆይ! መልስ መስጠት ከቻልክ እጠይቅሃለሁ፦
~ ክልክል የሆኑ ነገሮችን ለመፈጸም የሚያስገድደው አጣብቂኝ ችግር (ዶሩራ) በእጅ፣ በአንገት፣ በእግር መቆረጥ ወይም በሞት ብቻ የተገደበ ነውን? ይህንን ማን አለህ? ከእውነተኞቹ ከሆንክ ማስረጃህን አምጣ። ከቁርአንና ከሱና የተቀዳውንና የታወቀውን "አስገዳጅ ሁኔታዎች ክልክል ነገሮችን ያስፈቅዳሉ" የሚለውን የሸሪዓ ደንብ (ቃዒዳ) በእጅና በእግር መቆረጥ ወይም በግድያ ብቻ የገደበው ማን ነው?
~ አቡ ሙዓዝ ሆይ! ዑለማኦች 'አድ-ደሩሪያት አል-ኸምስ' ብለው የሚጠሯቸውን አታውቅምን? ለመሆኑ ዲናዊ ጉዳት 'አደጋ' ክልክል ነገሮችን ለመፈጸም ከሚያስፈቅዱት ውስጥ አንዱና ዋነኛው አይደለምን? ከእነዚህ ሰዎች ጋር ደዕዋችንን ለማስጠበቅና የነቢያዊ ፈለግ ምንጭ፤ የብዙ ሺህ ሱንዮች የዐይን ማረፊያ የሆኑትን የሰለፊያ መስጂዶችና መርከዞችን ለመጠበቅ መቀመጥ እግርህ ወይም እጅህ እንዳይቆረጥ ፈርተህ ከእነርሱ ጋር ከመቀመጥ የተሻለና በላጭ አይደለምን?
~ እንዲሁ በቅጡ ሳናስተነትን ከመቀባጠራችን በፊት የራሳችንን አቅምና የአስተሳሰብና የግናዛቢያችንን ምጥቀትና ጥልቀት ማወቅና መፈተሹ ለእኛ የተሻለ ነው። እንዲህ ተብሏልና፦ "ዓዋቂ ማለት መልካምን ከክፉ የሚለይ አይደለም፤ ይልቁንም ከሁለት መልካም ነገሮች የተሻለውን፣ ከሁለት ክፉ ነገሮች ደግሞ አነስተኛውን የሚያውቅ ነው። የሸሪዓ መሰረቱም ጥቅምን ማስገኘትና ማሟላት፣ ጉዳትን ደግሞ ማስቀረትና መቀነስ እንደሆነ የሚያውቅ ነው። ይህ ካልሆነ ግን በመስራትና በመተው መካከል ያለውን ሚዛን የማይጠብቅ ሰው፤ ግዴታዎችን ሊተውና የተከለከሉ ነገሮችን ሊፈጽም ይችላል፤ ይህንንም እንደ ጥንቃቄና ደግነት (ወረዕ) ይቆጥረዋል።"
7. በመጨረሻም እንዲህ ትላለህ፦ "እስኪ ንገሩኝ፤ ከእኛ መካከል ትክክለኛው ማን ነው? ሰዎችን ለስሜት ባለቤቶች ፍቅር እንዲኖራቸውና ለእነርሱ እንዲለዝብ የሚያነሳሳው? ወይስ እንደ ቀደምቶች ከቢድዓ ባለቤቶች እንዲጠነቀቁና ከመንገዳቸው እንዲርቁ የሚያነሳሳው?"
እልሃለሁ፦ "ትክክለኛው መልስ ያለምንም ጥርጥር ሁለተኛው ነው። ነገር ግን ሰዎችን የስሜት ባለቤቶችን በመውደድ ላይና በመለዘብ ላይ ያነሳሳው ማን ነው? ይህንን የምታደርግ ከነበርክ አንተ በእርግጥም የጠፋህ 'ሙመዪዕ' ነህ፤ ከእርሱ መመለስህም ላንተ በላጭ ነው። አንተ "አብሬያቸው ነበርኩ" የምትላቸው ሰለፊዮች ግን ከምትለው ነገር በጣም የራቁ ናቸው። ይልቁንም ከእነርሱ ዘንድ የሚታወቀው ከቢድዓና ከባለቤቶቿ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ማስጠንቀቂያ መስጠት ነው።
ታላቅና የተከበረው የዓርሽ ባለቤት የሆነው አላህ ቀጥተኛውን መንገድ እንዲመራንና ከእርሱ ጋር እስከምንገናኝበት ቀን ድረስ በእርሱ ላይ እንዲያጸናን እለምነዋለሁ። እርሱ የዚህ ባለቤትና በእርሱም ላይ ቻይ ነውና።
በታናሹ ወንድምህ አቡ ዑምራን አል-አሰሪ ተፃፈ።
ትርጉም: ሙሐመድ አያሌው
=
የቴሌግራም ቻናል
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
#ይህ መልእክት ወደ አማርኛ ሲመለስ የሚከተለውን ይመስላል፦
~ ይድረስ ለኡስታዝ አቡ ሙዓዝ
ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ ሆይ! በቻናልህ የለጠፍከውን አዋጅ አንብቤ የሚከተለውን ላቀርብልህ ወደድኩ፦
1. እንዲህ ብለሃል፦ "ወደ ሐቅ መመለስን የለገሰኝን አላህ አመሰግነዋለሁ። በዲን ጉዳዮች እና በሰለፊያ መርሆች ላይ ከነበረብኝ የ'ተምዪዕ' (ለዘብተኝነት) እና የመዘናጋት አካሄድ እውነተኛ ተውበት ማድረጌን አውጃለሁ። አላህ ያለፈውን ስህተቴንና ጥፋቴን እንዲምረኝ እለምነዋለሁ።"
እልሃለሁ:- "ቀደም ሲል ራስህን እንደገለጽከው መንገድ የሳትክ ሙመይዕና በሰለፊያ መርሆች ላይ ቸልተኛ ከነበርክ በእርግጥም ለተውበት ተገቢ ነህ። እኛ ሰለፊዮች ግን -ለአላህ ምስጋና ይገባውና- በቻልነው መጠን በሰለፊያ መርሆች ላይ አንድም ቀን አላለሰለስንም፣ አልተዘናጋንምም። ነገር ግን ከለተሚዮች በኩል የሚመነጩ ብይኖችን አለመቀበላችንን ከሆነ 'ተምዪዕ' እና 'መዘናጋት' ብለህ የምትጠራው ይህ ግልጽ ስህተት ነው። ካልሆነማ አንተ ራስህ እንደምታውቀውና ውስጥህ እንደሚያረጋግጠው እኛ አልተዘናጋንም፤ ይልቁንም የነቢዩንﷺ መንገድ በተቃረኑት በሱፊዮች፣ ኢኽዋኒዮች፣ ሱሩሪዮች፣ ሙመዪዓዎችን፣ የተክፊሪያ ሐዳዲዮች፣ የለተሚያ ሐዳዲዮችና ሌሎችም ላይ ሁሉ መልስ (ረድ) ከመስጠት ቦዝነን አናውቅም። ባይሆን ይህን የምናደርገው ከቁርአንና ከሱና በተቀዳ ዘዴ (ኡስሉብ) እንጂ በሐዳዲዮች ስልት አይደለም።
2. እንዲህም አልክ፦ "እንዲሁም ደግሞ የቀደምቶችን መንገድ እና መርሆቻቸውን ወደ ማፍረስ የሚያደርሱ በሆኑ ከፊል መርሆች በተለይ ከአህሉስ-ሱና መርሆች አንዱ በሆነው በ 'ባቡል ወላዕ ወል በራእ' (ለአላህ ብሎ መውደድና መጥላት ዘርፍ) መሸንገሌንና መታለሌን አምናለሁ፤ አረጋግጣለሁም። እኔና አምሳያዎቸ በጥቅል መልኩም ይሁን በተናጥል ደረጃ ግልጽ ማብራሪያና ማስጠንቀቂያ መስጠት በሚገባቸው ቦታዎች ላይ ዝም በማለታችንና በመዘናጋታችን ተሸንግለናል።"
ቀደም ሲል እንዳልኩህ እልሃለሁ፦ "በጠቀስካቸው ነገሮች የተሸነገልክ፣ የሰለፎችን መንሀጅና መርሆች አፍራሽ፣ እንዲሁም ማብራሪያና ማስጠንቀቂያ በሚገባቸው ቦታዎች ዝም የምትልና የምትዘናጋ ከነበርክ፤ እውነት ነው ሞት ከመምጣቱ በፊት ወደ ቅናቻው መመለስህ የተገባ ነው። እኛ ሰለፊዮች ግን ተሸንግለን መንገድ አልሳትንም። ነገር ግን ተማርንና አወቅን እንጅ። መርሆችንም አላፈረስንም። የሰለፎችን መርህ አፍርሰን ከዲን ውጭ ከመሆን በአላህ እንጠበቃለን። ነገር ግን በእኛ ብልሃትና ሃይል ሳይሆን የአላህ ማግራት ሁኖ (መርሆችን) ገነባን፣ አስተካከልን፣ በእነርሱም ላይ ተጓዝን፤ በአላህ ፈቃድ በእነርሱ ላይ እንሞታለን። ማድረግ እየቻልን ማብራሪያና ማስጠንቀቂያ በሚገባቸው ብዙ ቦታዎች ይቅርና አንድ ቦታ ላይ እንኳ ዝም አላልንም።
ነገር ግን እጠይቅሃለሁ፦
~ የሰለፎችን መንሀጅና መርሆች ወደ ማፍረስ የሚያመሩትና አንተ የተታለልክባቸው እነዚያ 'ቃዒዳዎች' (ደንቦች) ምንድን ናቸው?
~ ማብራሪያና ማስጠንቀቂያ በሚገባቸው ቦታዎች ዝም ያሉትና የተዘናጉት እነዚያ 'አንተን መሰል' ሰዎችስ እነማን ናቸው?
3. እንዲህም ብለሃል፦ "ቀደም ሲል ከቢድዓ ባለቤቶችና ፈር ከለቀቁት ጋር ከመቀመጥ እንዲሁም እነርሱን ከመስማት በሚገባ እናስጠነቅቅ ነበር፤ ነገር ግን ከቆይታ በኋላ ዝም አልን፣ ሰዎችንና ተማሪዎችንም ዝም አሰኘን። በዚህም የ'ወላዕ ወል በራእ' መንሀጅን አቀለጥን ፣ ቀደም ሲል ኢኽዋኖች እንደገደሉት እኛም ልንገድለው ተቃርበን ነበር።"
እልሃለሁ፦ "ከቢድዓ ባለቤቶችና ከፈር ከለቀቁ ጠማማዎች ጋር መቀመጥንና ለእነርሱ ጆሮ ከመስጠት ማስጠንቀቅን ትተህ ከነበርክ፣ እንደዚሁም ዝም ብለህና ሰዎችንና ተማሪዎችንም ዝም አሰኝተህ የ'ወላዕ ወል በራእ' መንሀጅን አላልተህና ልትገድለው ተቃርበህ ከሆነ፤ ይህ ያንተ ብቻ ግልጽ ስህተትና ገሃድ የወጣ ጥመት ነው። እኛ ግን በአቅማችን ልክ ከቢድዓ ባለቤቶችና ከጠማማዎች ጋር ከመቀመጥና እነርሱን ከመስማት እያስጠነቀቅን ነው። ዝም አላልንም፣ ሰዎችንና ተማሪዎችንም ዝም አላሰኘንም፣ የ'ወላዕ ወል በራእ' መንሀጅንም አላቀለጥንም። በምንለው ነገር ላይ አላህ ምስክር ነው።
በድጋሜ እጠይቅሃለሁ፦
~ እነዚያ ከአንተ ጋር የነበሩት፣ ዝም ያሉ፣ ሰዎችንና ተማሪዎችንም ዝም ያሰኙ፣ የ'ወላዕ ወል በራእ' መንሀጅን ያላሉና ሊገድሉት የተቃረቡት እነማን ናቸው?
4. እንዲህ ብለሃል፦ "እኔ ዛሬ እውነቱ ከተገለጸልኝ በኋላ፣ ቀደም ሲል ወደ ነበርኩበት የመጀመሪያው አቋሜ ከመመለስ ውጭ ሌላ አላደረግኩም። ይህም ከቢድዓ ባለቤቶች መጠንቀቅና ማስጠንቀቅ፣ ከእነርሱ ጋር አለመቀመጥና እነርሱን አለመስማት ነው፤ ይህንንም ያደረግኩት ቀደምቶች -አላህ ይዘንላቸውና- የነበሩበትን መንገድ ለመያዝ ነው።"
በአጭሩ የምልህ፦ "እኛ -ችሮታም ይሁን ልግስና 'መመፃደቅ' ለአላህ ነውና- አቋማችን፤ ከዚህ ቀደምም ይሁን ወደ ፊት -በአላህ ፈቃድ- ከቢድዓ ባለቤቶች መጠንቀቅና ማስጠንቀቅ፣ ከእነርሱ ጋር አለመቀማመጥና እነርሱን አለመስማት፣ እንዲሁም የሰለፎችን መንገድ አጥብቆ መያዝ ነው። ነገር ግን ብይኖችን ያለ በቂ ማስረጃ አንቀበልም፣ ለማንም ጯሂ ቦታ አንሰጥም፣ የሐዳዲዮችም ጩኸት አያስደነግጠንም፤ እነርሱ ወሰን እንዳለፉት እኛ ወሰን አናልፍም።
5. እንዲህ ብለሃል፦ "በአላህ እምላለሁ! እኔ እንደተገነዘብኩት ብትገነዘቡ ኖሮ፤ የኛ ጉዳይ በዚህ አቋም ከቀጠለ "ከሱፊያና ከኢኽዋን ጋር አብሮ መስራትና ግንኙነት ማድረግ ይቻላል" በማለታችንና አንዳንዴም ከእነርሱ ጋር እንዳንቀመጥ የሚከለክሉንንና የሚያስጠነቅቁንን ሰዎች በመተቸት፤ ቢድዓንና ባለቤቶቹን እንዲወዱ በማድረጋችን ሰዎችን እንደጎዳን ታውቁ ነበር።"
እልሃለሁ፦ "ሰዎችን ቢድዓንና ባለቤቶቿን እንዲወዱ የምታደርግ ከነበርክ፣ ከሱፊያና ከኢኽዋን ጋር ግንኙነት ማድረግ በደፈናው ይቻላል የምትል ከነበርክና ከእነርሱ ጋር እንዳይቀመጡ የሚከለክሉትን የምትነቅፍ ከነበርክ፤ ይህ ካንተ ጥመቶች ውስጥ አንዱ ነበር ማለት ነው። አዎ! በዚህ መንገድህ ብትቀጥል ኖሮ አንተን የሚሰሙትን ትጎዳ ነበር። እኛ ግን ሰዎችን ቢድዓንና ባለቤቶቿን እንዲወዱ አላደረግንም። -እኛ ይህንን እንድንሰራ ከማድረግ አላህ የጠራ ነው- ይልቁንም እኛ -ቅርቡም ሩቁም ዘንድ እንደሚታወቀው- ከሁሉም የቢድዓ አይነቶችና ከባለቤቶቿ እናስጠነቅቃለን። ከእነዚህ ሰዎች ጋር ሸሪዓው ባስቀመጣቸው ገደቦች እንጅ ግንኙነት ማድረግ አንድም ቀን ይቻላል ብለን አናውቅም። ከዚህ የሚከለክልንም አልነቀፍንም፤ ነገር ግን ስህተት በሰራ ሰው ላይ ምላሽ ሲሰጡ ወሰን የሚያልፉትን በእውቀትና በግልጽ ማስረጃ መለስን እንጅ።
አሁንም በድጋሜ ልጠይቅህና፦
~ በዚህ አቋምህ ላይ ከአንተ ጋር የነበረውና ሰዎችን ቢድዓንና ባለቤቶቿን እንዲወዱ ያደረገው ማን ነበር?
~ ከሱፊያና ከኢኽዋን ጋር ግንኙነት ማድረግን በደፈናው የፈቀደውስ ማን ነበር?
~ ከቢድዓ ባለቤቶች ጋር ከመቀማመጥ የሚከለክሉትንና የሚያስጠነቅቁትን የተቸውስ ማነው?
6. እንዲህ ብለሃል፦ "ይህ አካሄድ አጣብቂኝ (ዱሩራ) ነው። ስለሚባለው አባባል የምለው፦ ከቢድዓ ባለቤቶች ጋር መቀመጥን ብንተው እጃችንን፣ አንገታችንን ወይም እግራችንን የሚቆርጥብን ወይም የሚገድለን አለን?! ይህ ቸልተኝነትና መዘናጋት ብቻ ነው። አላህ ይቅርታውንና ደህንነትን እንዲሰጠን እንለምነዋለን።"
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
فأسألك يا أبا معاذ: إن كنت مجيبا:
~ هل الضرورة الملجئة إلى ارتكاب المحظور منحصرة في قطع الأيدي أو الأعناق أو الأرجل، أو القتل؟ من قال لك هذا؟ هات برهانك إن كنت من الصادقين، من الذي قيد لك القاعدة المقررة المستمدة من الكتاب والسنة قاعدة "الضرورات تبيح المحظورات" بقطع الأيدي والأرجل أوالقتل؟
~ أما تدري يا أبا معاذ ما يسميها العلماء بالضروريات الخمس؟ أليس الضرر الديني أولى وأحرى ما تستباح به المحظورات؟ أليست المجالسة مع هؤلاء لأجل حماية دعوتنا ووقاية مساجد ومراكز السلفيين التي هي منبع منهاج النبوة، وقرة عيون آلاف الألوف من أهل السنة خيرا من مجالستهم خوفا على قطع رجلك أو يدك؟
~ وأيضا أن نعرف قدرنا ومدى فكرتنا خير لنا من نتفوه بادي الرأي، فإنه قد قيل "ليس العاقل الذي يعلم الخير من الشر، وإنما العاقل الذي يعلم خير الخيرين وشر الشرين، ويعلم أن الشريعة مبناها على تحصيل المصالح وتكميلها، وتعطيل المفاسد وتقليلها، وإلا فمن لم يوازن ما في الفعل والترك، فقد يدع واجبات ويفعل محرمات، ويرى ذلك من الورع،"
7. وأخيرا قلت: "وأخبروني: من المصيب منا؟ أَمَن يحثّ الناس على مودة أهل الأهواء والتساهل معهم، أم من يحثّ على الحذر من أهل البدع والبعد عن طرائقهم كما كان عليه السلف؟"
فأقول: الجواب المتعين هو الثاني بلا شك، ولكن من الذي حث الناس على مودة أهل الأهواء والتساهل معهم؟ إن كنت تفعل هذا فأنت مميع تائه حقا، فرجوعك منه خير لك، أما السلفيون الذين تزعم أنك كنت معهم فهم بعيدون مما تقول، بل المعروف منهم التحذير العلمي من البدع وأهلها،
أسأل الله العظيم رب العرش الكريم أن يهدينا الصراط المستقيم، ويثبتنا عليه، إلى يوم لقائه، إنه ولي ذلك والقادر عليه،
كتبه أخوك الصغير أبو عمران الأثري
=
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
~ إلى أستاذ أبي معاذ وفقه الله
يا أستاذ أبا معاذ! قد قرأت ما أعلنته فى قناتك فأردت أن أوجه لك ما يلي:
1. قلتَ "فإني أحمد الله تعالى الذي منّ عليّ بالرجوع إلى الحق وأُعلن توبتي الصادقةَ مما كنتُ عليه من منهج التمييع والتساهل في أمور الدين وأصول السلفية وأسأل الله أن يغفر لي ما مضى من زلل وخطأ."
أقول: إن كنت من قبل كما وصفت نفسك بأنك مميع ضال ومتساهل فى أصول السلفية فأنت حقيق بالتوبة، ولكن نحن معشر السلفيين -ولله الحمد- ما ميعنا وما تساهلنا يوما ما من أصول السلفية قدر المستطاع، أما إن كنت تسمي عدم قبولنا للأحكام الصادرة من قِبل اللتميين تمييعا وتساهلا فهذا غلط بين، وإلا نحن كما تعلم أنت وتقر به نفسك ما تساهلنا، بل وما برحنا نرد على كل من خالف منهاج النبوة من الصوفية والإخوانية والسرورية والمميعة والحدادية التكفيرية والحدادية اللتمية ووو، ولكن على أسلوب مستمد من الكتاب والسنة لا على أسلوب الحدادية.
2. قلت: "أُقرّ وأعترف أيضا أني قد اغتررتُ ببعض القواعد التي تؤدي إلى هدم منهج السلف الصالح وأصولهم، لا سيما في باب الولاء والبراء، وهو أصل من أصول أهل االسنة . وقد اغتررت أنا وأمثالي حيث سكتنا وتساهلنا في مواطن يجب فيها البيان والتحذير. إما بالجنس وإمابالتعيين"
أقول: كما قلت لك آنفا إن كنت مغترا بما ذكرت وهادما منهج السلف الصالح وأصولهم وساكتا ومتساهلا فى مواطن يجب فيها البيان والتحذير فأنت جدير بالرجوع إلى رشدك قبل حضور أجلك، أما نحن -معشر السلفيين- فما اغتررنا فجهلنا، ولكن تعلمنا فعلمنا، وما هدمنا الأصول ونعوذ بالله من أن نهدم أصول السلف فنمرق من الدين، ولكن بَنَينا وأصلحنا وسرنا عليها بتوفيق من الله لا بحول منا ولا قوة وعليها نموت إن شاء الله، وما سكتنا فى موطن يجب البيان فيه والتحذير -ونحن قادرون- فضلا عن المواطن،
ولكن أسألك:
~ ما هي القواعد التي اغتررت بها التي تؤدي إلى هدم منهج السلف الصالح وأصولهم؟
~ ومن هم أمثالك الذين سكتوا وتساهلوا فى مواطن يجب فيها البيان والتحذير؟
3. قلت: "وكنا قبل نُحَذِّر من مجالسة أهل البدع والمنحرفين والاستماع إليهم، كما ينبغي ولكن بعد حين سكتنا وأسكتنا الناس والطلاب فميعنا منهج الولاء والبراء وكدنا أن نقتله كماقتلته الإخوانية قبل"
فأقول: لك أيضا إن كنت تركت أنت التحذير من مجالسة أهل البدع والمنحرفين والاستماع إليهم، كما ينبغي وسكت وأسكت الناس والطلاب فميعت منهج الولاء والبراء وكدت أن تقتله كما قلت فهذا خطأ واضح وضلال فاضح منك فحسب، أما نحن فما زلنا نُحَذِّر من مجالسة أهل البدع والمنحرفين والاستماع إليهم حسب الطاقة، ما سكتنا ولا أسكتنا الناس والطلاب ولا ميعنا منهج الولاء والبراء، والله على ما نقول وكيل.،
وأسألك أيضا:
~ من الذين كانوا معك وسكتوا وأسكتوا الناس والطلاب وميعوا منهج الولاء والبراء وكادوا أن يقتلوه؟
4. قلت: "وإني اليوم، بعد أن تبيّن لي الحق، ما صنعتُ إلا الرجوع إلى موقفي الأول الذي كنتُ عليه من الحذر والتحذير من أهل البدع وعدم مجالستهم أو الاستماع إليهم، التزامًا بما كان عليه سلف الأمة رحمهم الله."
أقول: لك مختصرا نحن ولله الفضل والمنة موقفنا من قبل ومن بعد -إن شاء الله- هو الحذر والتحذير من أهل البدع وعدم مجالستهم والاستماع إليهم، والتمسك بما كان عليه السلف الصالح، ولكن لا نقبل الأحكام إلا بأدلتها، ولا نلتفت إلى كل ناعق وناهق، ولا يزعجنا صراخ الحدادية، فنغلو كما غلوا،
5. قلت: "ووالله لو تذكرتم كما تذكرتُ أنا لعلمتم أنه لو استمر أمرنا على هذا الموقف لأضررنا بالناس، حيث حببنا إليهم البدع وأهلها، حيث قلنا بجواز المعاملة مع الصوفية والإخوانية بل وربما جرحنا من ينهانا عن مجالستهم ويحذرنا من ذلك"
فأقول: إن كنت تحبب إلى الناس البدع وأهلها وقلت بجواز المعاملة مع الصوفية والإخوانية على الإطلاق كما هو المتبادر وجرحت من ينهى عن مجالستهم ويحذر من ذلك، فهذا أيضا من ظلاماتك وضلالاتك أنت، فنعم لو استمر أمرك على هذا لأضررت بمن يصغي إليك، أما نحن فما حببنا إلى الناس البدع وأهلها، -حاشا لله- بل -كما هو معلوم لدى القريب والبعيد- نحذر من أصناف البدع وأهلها، وما قلنا يوما ما بجواز المعاملة مع هؤلاء إلا بالضوابط المقررة ليس هذا موضع بسطها، وما جرحنا الناهي عن المجالسة والمحذر منها، ولكن رددنا بعلم وبصيرة على من يجاوز الحد في الرد على من أخطأ،
وأيضا أسألك:
~ من الذي كان معك فى موقفك هذا وحبب إلى الناس البدع وأهلها؟
~ ومن الذي أجاز المعاملة مع الصوفية والإخوانية إطلاقا؟
~ من الذي جرح من ينهى عن مجالسة أهل البدع ويحذر من ذلك؟
6. وقلت: "وأما القول بأن هذا المسلك ضرورة، فأقول: هل عندنا من يقطع أيدينا أو أعناقنا أو أرجلنا، أو يقتلنا لو تركنا مجالسة أهل البدع؟! إنما هو تهاون وتفريط، نسأل الله العفو والعافية"
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ፖለቲካዊ ስጋቶችን ጠዋት ማታ ማስጠንቀቁን ከተውሒድ ትምህርት በላይ የሚያደርግ ሰው ማስተማር ሳይሆን ቀድሩን አውቆ መማር ነው ያለበት። የሙታን አምልኮን፣ መሰረታዊ የዐቂዳ ልዩነትን አቅልሎ በመመልከት በጥቃቅን ነገሮች ልንለያይ አይገባም የሚል ሰው መሰረታዊ የግንዛቤ ችግር ያለበት ሰው ነው። ተውሒድ የሌለበት አንድነት ዋጋ የለውም።
ኢስላም፣ ኢማን፣ ላ ኢላሀ ኢለላህ ከቃላት ያልፋል። በተግባር ያልተገኘ ላ ኢላሀ ኢለላህ ባዶ መፈክር ነው። ከአላህ በስተቀር የሐቅ አምላክ የለም ብሎ የመሰከረ ሰው ምስክርነቱ በተግባር መገኘት አለበት። ላ ኢላሀ ኢለላህ እያለ ለጭንቅ ለመከራው እነ ጫሊን፣ አብሬትን፣ ቃጥባሬን፣ ገታን፣ አባድርን፣ ደገርን፣ ወዘተ. የሚማፀን ከሆነ በምላሱ የሚናገረው ከልቡ የለም። ባዶ መፈክር ምን ይሰራል?! እነዚህ አካላት ደካማ ፍጡሮች ናቸው። ከሞቱ በኋላ ቀርቶ በህይወት እያሉም ልጅና ዝናብ አይሰጡም። ቀጥታ ከአላህ መጠየቅ እየቻልክ ማርያምን፣ ገብረኤልን፣ ሚካኤልን እንደሚማፀኑ ኦርቶዶክሶች አትሁን። በኢስላም እየሱስን ብቻ ሳይሆን ሙሐመድንም ማምለክ አይቻልም። (ሰላም በሁለቱም ላይ ይሁን።)
(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 13/2017)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ኢብኑ ተይሚያህ (አላህ ይዘንላቸው) እንዲህ ብለዋል፦
ومن اعتادَ الانتِقام ولم يصبِر لا بُدَّ أن يقَع في الظُّلم
"በቀልን የለመደና የማይታገስ ሰው፣ በደል ላይ መውደቁ አይቀሬ ነው።"
[ቃዒደህ ፊ'ሶብር፡ 102]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ሶብር ከጀነት በሮች አንዱ በር ነው።
ሶብር፦ ማለት ተሰብረህ እና አቅም አጥተህ ህመምን መቻል ማለት አይደለም። ይልቁንም መፍትሔው መቼ እንደሚመጣ ሳታውቅ በአላህ ላይ ሙሉ እምነት ማሳደር ማለት ነው።
ሁሉም ነገር እንዳመፀብህ፣ ዱዓህ እንደዘገየብህ እና የመፍትሔ በሮች እንደተዘጉብህ የሚሰማህ ቀናት ሊያልፉብህ ይችላሉ። ነገር ግን አስታውስ! አላህ የታገሰን ልብ፣ ወደ እርሱ የተነሳን ዱዓ፣ እንዲሁም አላህን ከመፍራትም ሆነ ከህመም የተነሳ የፈሰሰችን እንባ በፍጹም አይረሳም።
ታገስ! የተመኘኸው ነገር መዘግየቱ ራሱ የነገሮች ሁሉ ትልቁ እዝነት ሊሆን ይችላል፤ እንዲሁም አላህ ከዚህ ሁሉ ድካም በኋላ፣ ስታለቅስለት የነበረውን ሁሉ የሚያስረሳህን ትልቅ ደስታ ደብቆልህ ሊሆን ይችላል።
አላህ (ሱ.ወ) በቁርዓኑ እንዲህ ብሏል፦
﴿إِنَّ اللَّهَ مَعَ الصَّابِرِينَ﴾ «አላህ ከታጋሾች ጋር ነው።»
ስለዚህ ምድር በጠበበችብህ ጊዜ በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ። እጆችህን ወደ አላህ አንሳና እንዲህ በል፦ "ጌታዬ ሆይ! እኔ ሶብርን እንጂ ምንም አልملكም። አንተ ደግሞ የሁሉ ነገር ባለቤት ነህ።"
እወቅ! ሌሊት ምንም ያህል ቢረዝም ንጋት መምጣቱ አይቀርም።ችግርም ምንም ያህል ቢከብድ፣ ከችግር ጋር ምቾት አለ።
ታገስ! አላህ ድካምህን ያያል። ዱዓህን ይሰማል። በልብህ ውስጥ ያለውንም ሁሉ ያውቃል። እናም "አልሀምዱሊላህ ታግሼ በማለፌ የምትልበት ቀን በእርግጥ ይመጣል።
Repost from ስለ ዲናችን
إذا وفقك الله أن تصلى الفجر فى وقته، فأبشر! فإن الذي رزقك صلاة خير من الدنيا وما فيها قادر على أن يرزقك الدنيا وما فيها ❤
Repost from قناة أبي ماهر الأثري الحبشي𝐀bu Mahir )
الصبر باب من أبواب الجنة
الصبر… ليس أن تتحمل الألم وأنت مكسور، بل أن تثق بالله وأنت لا تعرف متى سيأتي الفرج.
قد تمرّ عليك أيام تشعر فيها أن كل شيء ضدك، وأن دعاءك تأخر، وأن أبواب الفرج أُغلقت… لكن تذكّر: الله لا ينسى قلبًا صبر، ولا دعاءً رُفع إليه، ولا دمعةً نزلت من خشيةٍ أو ألم.
اصبر، فربما كان تأخير ما تتمناه هو عين الرحمة، وربما يخبئ الله لك بعد هذا التعب فرحًا يجعلك تنسى كل ما بكيت بسببه.
قال تعالى: ﴿إِنَّ اللَّهَ مَعَ الصَّابِرِينَ﴾.
فإذا ضاقت بك الدنيا، لا تستسلم… ارفع يديك إلى الله، وقل: يا رب، أنا لا أملك إلا الصبر، وأنت تملك كل شيء.
واعلم أن الليل مهما طال، فلا بد للفجر أن يأتي، وأن العسر مهما اشتد، فإن مع العسر يسرًا.
اصبر… فالله يرى تعبك، ويسمع دعاءك، ويعلم ما في قلبك، وسيأتي يوم تقول فيه: الحمد لله أنني صبرت.
ድርሻህን ነዉ የምትኖረዉ።ስለዚህ ባለፈዉ አትዘን ፣በሚመጣዉም አትስጋ፣ የጀሊሉ ዉሳኔ ሁሌም መልካምነዉ።
Repost from نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے
"ሁሉም ሰው የርሱ ታሪክ ባልሆነ ነገር ላይ ጠቢብ ነው።" [ዓባስ አል-ዒቃድ]
በመከራው ያልተገረፈ ሰው ስለትዕግስት ለማውራት ጠቢብ ይሆናል። የድህነትን ህይወት ያላየ ሰው ድሆችን ስለሀብትና ድህነት በመንገር ሊቅ ይሆናል። ፈተናውን ያልተቋደሰ ሰው ስለፅናት በመምከር አዋቂ ይሆናል። ሁሉም ባልደረሰበት የችግር ህይወትና ታሪክ ውስጥ ጉምቱ ጠቢብ ነው።
t.me/abdu_rheman_aman
t.me/abdu_rheman_aman
Repost from Ustaz Mubarek Ebrahim Channel
«የወዲያኛዋን ዓለም (የአኼራን) እውነተኛ ሁኔታ የተረዳ ሰው፤ የዚህችን ዓለም መለያየት ቀላል ሆኖ ይታየዋል።»
ይህ አባባል ከታላቁ እስላማዊ ምሁር ከኢብኑ አል-ቀይም (رحمه الله) «አል-ፈዋኢድ» የተወሰደ ሲሆን፤ የዚህችን ዓለም ጊዜያዊነት እና የወዲያኛዋን ዓለም (አኼራ) ዘላለማዊ ክብር የተገነዘበ ሰው፣ የዓለማዊ ነገሮችን እና መለያየትን በቀላሉ ሊያልፋቸው እንደሚችል ይገልጻል።
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የሶሪያው ድል በየመን ይደገማል፣ ኢንሻአላህ። የራፊዷ እግር ይነቀላል። የኢራን ቀኝ እጅ ይቆረጣል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
📢 ልዩ የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም!
❝ሰይድ ቁጥብ ማን ነው? ለተሳሳቱ ውዳሴዎችና ማደናገሪያዎች የሚሰጥ ምላሽ❞
🎙 አቅራቢ፦ ኢብኑ ሙነወር
🗓 ቀን፦ ነገ ማክሰኞ
⏰ ሰዓት፦ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ
◇ የቀጥታ ስርጭት አድራሻ👇
t.me/IbnuMunewor
t.me/IbnuMunewor
Repost from Abdulkerim Hussein Channel
ከሺአ ጋር የሚደረግ ትግል ለእስልምና የሚደረግ ትግል ነው። ለተጣሰው #የአላህ እና #የመልእክተኛው ሀቅ ሲባል የሚደረግ ትግል! ለበረዙት #ቁርአን ለተሳለቁበት #ሃዲስ ጥብቅና! #ለሙእሚን እናቶች #ለነቢ ባለቤቶች ክብር እና ንፅህና የሚደረግ ውግያ ነው! ክብር ደረጃቸው ለተጣሰው ተንቀው ለተዋረዱ #ሶሃቦች ክብር እና ልቅና ሲባል የሚደረግ ትግል ነው። ለዚህ ሲባል እንኳን በባዶ እግር በእፉቅቅ ይኬዳል! አላህ ለሰለፍዮች ድልን ያጎናፅፍ!
#የመንን_በሰለፍዮች_ክንድ_አላህ_እንደሚያፀዳት_አልጠራጠረም!
በነገራችን ላይ የለተሞው ሰፈር ኡስታዝ ተብዬዎች «በራስ መታበይ የተጠናወታቸው፣ ሌሎችን በዝቅታ ዓይን መመልከት የለመደባቸውና የጅሕልናን አክሊል በራሳቸው ላይ የደፉ ሚስኪን ናቸው» ። ተከታዮቻቸውማ¡ "የማይበስሉ የድንጋይ ንፍሮዎች ናቸው!።"
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
«ኢብኑ ሙነወር»
አንተ ስለ ኢኽዋን ታስጠነቅቃለህ፡
ራቋቸው ብለህ ታስተምረናለህ፡
መረጃ ላይ ሆነህ መልስ ትሰጣለህ፡
መንጋው ከኢኽዋን ጋር እያለ ያማሀል፡
ጩኸታቸው ሁሉ ላንተ ይሰማሀል!?
እንገረማለን እኛ በዚህ መሀል፡
በጉጉት በስስት እንጠብቅሀለን፡
ያለ ድንበር ማለፍ አወ እንወድሀለን፡
በአካል ቀርቤ እጂግ ስለማውቅህ፡
ንግግሬ አንድ ነው አሏህ ይጠብቅህ፡
በስሜት ቢሰክሩም ሐቅን በመታወር፡
ደጋግመው ቢጮሁም ሳምንታትና ወር፡
ሐቅ ላይ እስካለ ጀግና ነው ሙነወር፡
.....ኸላስ....
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
"በሰሞኑ የሰይዪድ ቁጥብ ጉዳይ ከተመቸኝ ዛሬ ከመግሪብ በኋላ በድምፅ ለመግባት አስቤያለሁ" ብዬ ነበር። አሁን ላይ ስላልቻልኩኝ ከቻልኩ ምሽት 3:00 ላይ በቴሌግራም ቻናሌ ( https://t.me/IbnuMunewor ) በቀጥታ (live) ለማቅረብ እሞክራለሁ ኢንሻ አላህ።
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
" ﻭﺃﻣّﺎ ﻛﺜﻴﺮٌ ﻣِﻦَ ﺍﻟﻨﺎﺱ ﻓﻬﻮ ﻣﻊ ﺍﻟﺤﻖ ﺇﺫﺍ ﻭﺍﻓَﻖَ ﺍﻟﻬﻮﻯ ، ﻭﺿﺪّﻩ ﺇﺫﺍ ﺧﺎﻟﻒ ﺍﻟﻬﻮﻯ ، ﻓﻬﻮ ﻓﻲ ﺍﻟﺤﻘﻴﻘﺔ ﻣﺎ ﺍﺗَّﺒَﻊَ ﺇﻻ ﻫﻮﺍﻩ "
"ብዙ ሰው ከስሜቱ ጋር ሲገጥምለት ከሐቅ ጋር ይሆናል። ከስሜቱ ጋር ሲቃረንበት ደግሞ በተቃራኒው ይሆናል። ይህ ማለት በተጨባጭ ስሜቱን ብቻ እንጂ የሚከተል አይደለም ማለት ነው።" [አት-ተዕሊቃቱል ባዚያህ ዐላ ሸርሒ አጥ-ጦ ሐዊየህ፡ 1253]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from ስለ ቀልባችን
የሀራም ፍቅር መነሻው «ስሜት»፣ መድረሻው ደግሞ «ክህደት» ነው።
የአንዳንዱ ወንድ ውሸታም ናፍቆት ኒቃብሽን አስገልጦ የተሸፈነውን እስኪያይ ድረስ ብቻ ነው፤ በሀራም መንገድ ፊትሽን አይቶ ጉጉቱ
ሲበርድ ግን «ይህች ናት እንዴ?» ብሎ ድራሹ ይጠፋል።
እህቴ ሆይ! በሀራም መንገድ ኒቃብሽን የሚያስወልቅሽ ሰው የፈለገው የተከለከለውን ስሜቱን እንጂ አንቺን አይደለም። ውበትሽም ሆነ ክብርሽ የሚገባው በኒካህ ለሚያከብርሽ ለሀላልሽ ብቻ ነው!
t.me/Sle_qelbachn1
t.me/Sle_qelbachn1
