ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
Kanalga Telegram’da o‘tish
ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።
Ko'proq ko'rsatishMamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
321
Obunachilar
+124 soatlar
-77 kun
+5830 kun
Postlar arxiv
Repost from ከ ደጋጎቹ ዓለም
"ጁለይቢብ! አታገባምን?" አሉት ረሱል صلى الله عليه وسلم
"ያ ረሱለላህ صلى الله عليه وسلم በዱንያ ላይ ማን ሊድረኝ ይችላል? እኔ ሃብትም፣ክብርም የለኝም" አለ።
"እንዲህ ወዳለ የ አንሷር ቤት ሂድና ሴት ልጃቸውን ጠይቅ።ወደ እናንተ የላኩኝ ረሱል ናቸው። ' ልጃችሁን እንድታጋቡት!' ብለዋል በላቸው" አሉት።ጁለይቢብም ሄዶ " የ አላህ መልእክተኛ ሰላምታ ያደርስላችኋል።ልጃችሁንም እንድታጋቡኝ ጠይቀዋል" አላቸው።
አባትየውም "አንተ ጁለይቢብ! ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? አንተኮ ሃብትም፣ክብርም የለህም" አለ። ነገር ግን ልጅቷ የ ነቢዩን ትእዛዝ ስትሰማ ከ ውስጥ ክፍል ወጥታ "የ አላህ መልእክተኛ የላኩትን ሰው ትመልሳላችሁን?! እኔ ተቀብዬዋለሁ፤ አገባዋለሁ " አለች። እንዲህም ሆኖ ትዳር ተጀመረ።
ከዚያም የጂሃድ ጥሪ ተሰማ። ጁለይቢብ ግን አዲሷን ሙሽራ ትቶ ወደ ጦርነት ወጣ።ጦርነቱ ካበቃ ቡሃላ ረሱል صلى الله عليه وسلم ሶሃቦችን "ከናንተ መሃል የጠፋ ሰው አለ?" ብለው ጠየቁ። ሶሃቦቹም የጠፉትን ሰዎች አንድ በ አንድ ጠቀሱ። ረሱል ግን "የምወደውን ሰው አትፈልጉምን?" አሏቸው።"ማንን ነው?" አሏቸው።
እሳቸውም ጁልይቢብን ነው ምፈልገው። ሄዳችሁ የሱን ዜና ፈልጉ" አሉ። በኋላም አገኙት።ሰባት ጠላቶችን ገድሎ እርሱም ሸሂድ ሆኖ ነበር። ረሱልም ወደሱ መጥተው "አንተ ከእኔ ነህ፣ እኔም ከ አንተ ነኝ" አሉ። በእጃቸው ሰውነቱ ተሸክመው መቃብሩ እስኪቆፈር ድረስ ያዙት። ሰዎች ዘንድ ስሙ ትንሽ ቢሆንም በ አላህ ዘንድ ግን ቦታው ታላቅ ነበር።
አላህ ሆይ! እንደ ጁለይቢብ አድርገን። በምድር ላይ ብንረሳም በሰማይ ዘንድ የታወቅን የተወደድን አድርገን።
#ትዝብት
በመኖርህ ውስጥ ስለኖሩልህ ሰዎች ውለታ ታስባለህ። በአንፃሩ ስለምትኖርላቸው ሰዎች እጣ ፈንታም ትጨነቃለህ። ህይወት ፍቅርን ታስተምርሀለች። በልምድ ጉዞህ ውስጥ ሰውን በማንነቱ መምረጥ ትችላለህ። ማንን መውደድ እንዳለብህም ትገነዘባለህ። በተለያዩ ክስተቶች መሀል የእውነት አንተን የሚወድህ ማን እንደሆነም ታውቃለህ ። ክስተቶች ሰዎችን ያበጥራሉ። ምርጫህን ለይ!
⚠️መስቀል በአል ና ሙስሊም አይገናኙም
መጀመሪያ ፈጣሪ አለምን የፈጠረ ሁሉን ነገር ማድረግ የሚችል የሁሉ ባለቤት ከሰው የማይከጅል ነገር ግን እነሱ (ፍጡራን) በሙሉ ወደሱ የሚከጅሉ ታላቅ ሆኖ እያለ ከክብሩ ጋር የማይሄድ ህፃን የማያስበውን ተወለደ, ተሰቀለ, ተገረፈ, የባልደረቦቹን አግር አጠበ,,,,,, ብሎ መናገር ይሄ የጤነኛ አስተሳሰብ አይደለም ።
አላህ ሁሉን ማድረግ የሚችል ነው
📌وهو على كل شئ قدير
" እሱ በማንኛውም ነገር ቻይ ነው።"
⭕️ምንም ነገር አይሳነውም ማዳን መፍጠር መግደል መቀስቀስ ሁሉ በእጁ ነው ሁን ይለዋል ይሆናል። እንዲህ ይላል:
📌"إذاقضى أمرا فإنما يقول له كن فيكون "
አንዳችን በሻ ጊዜ ሁን ይለዋል ወዲያውኑም ይኾናል።
⭕️ ለማዳን እንግዲህ መሰቀል አያስፈልገውም ነቁ።
ኢሳ (እየሱስ) እንዳልተሰቀለ በቁርአን አላህ እንዲህ ሲል ይናገራል
📌"وبكفرهم على مريم بهتانا عظما وقولهيم إنا قتلنا المسيح عيسى ابن مريم رسول الله وما قتلوه وما صلبوه ولكن شبه لهم وإن الذين اختلفوا فيه لفي شك منه مالهم به من علم إلا اتباع الظن وماقتلوه يقينا بل رفعه الله إليه وكان الله عزيز حكيما "
እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየም ልጅ አልመሲህ ኢሳን ገደልን በማለታቸው (ረገምናቸው ) አልገደሉትም አልሰቀሉትምም ግን ለእነሱ (የተገደለው ሰው በኢሳ) ተመሰለ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዪት ከእርሱ (መገደል) በመጠራጠር ውስጥ ናቸው ።ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም። በእርግጥም አልገደሉትም።
🚫በጣም ገርሞ የሚገርመው ነገር ግን ሙስሊሞች ይሄን እየሰሱ ተሰቀል እያሉ የሚያምኑበትን ቀን ነው መስቀል እያል የሚያከብሩት
🚫ኧረ ሙስሊሞች ንቁ ተውው ዛሬም ድረሰ አለ መስቀል እየተባ የሚያከብር ሙስሊም ተው ውጡ ከዚህ አላህን ፍሩ
እደት ክርስቲያኖች ጌታ ተሰቀለ እያሉ የሚከበርውን በአል አንድ ሙስሊም ነኝ የሚል ሰው ያከብራል ኢላሂ‼️
🇸🇦የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/KedmiyaLetewhid9
🟢አርቴፊሻሉን AI ተጠቅመው የራሳቸው ፅሁፍ አስመስለው
� سؤال وجواب �
↞ ما نصيحتكم للدعاة الذين يستعملون الذكاء الاصطناعي في كتابة الردود والمقالات وينشرونها بأسمائهم؟
▫️إجابة الشيخ العلامة أ .د:
عبد الله بن عبد الرحيم البخاري
حفظه الله ونفع بعلمه
🎙مقتطف من الدرس التاسع من شرح «الأربعون في الأحكام»
الذكاء الاصطناعي
Artificial Intelligence
(AI)
አርቴፊሻሉን AI ተጠቅመው የራሳቸው ፅሁፍ አስመስለው የሚለቁ ዳዒይ ተብዬዎች
ረድ እና ሌላም ፅሁፍ ይፅፋሉ የሚገርመው
አርቴው ከተሳሳተ እነርሱም ከነ ስህተቱ በጭፍን ተቅሊድ ይለቁታል ወይም ፕሮፋይል ያደርጉታል። ያልሆነውን አስመስለው ያቀርቡታል። እነዚህን ዳዒይ ተብዬ አብረቅራቂዎችን ተጠንቀቁ። የዲን ሿሿ እንዳይሰሯችሁ።
አንዳንድ ዳቦ ቤቶች ደጅ ላይ የተለጠፈው ያማረ ዳቦ ቢጤ ነው።ፍቶውን የሚመስል ዳቦ ያመርታሉን!? ጠይቋቸው
https://t.me/Abulabas1444
https://t.me/Abulabas1444.
Repost from قناة فضيلة الشيخ أ.د. عبد الله البخاري
•
� سؤال وجواب �
↞ ما نصيحتكم للدعاة الذين يستعملون الذكاء الاصطناعي في كتابة الردود والمقالات وينشرونها بأسمائهم؟
▫️إجابة الشيخ العلامة أ .د:
عبد الله بن عبد الرحيم البخاري
حفظه الله ونفع بعلمه
🎙مقتطف من الدرس التاسع من شرح «الأربعون في الأحكام»
•
https://t.me/dr_elbukhary/5261
•
Repost from N/a
ሱፍያን ኢብኑ ዑየይና ረሂመሁላህ እንድህ ይላሉ፦
👉ዱዓ ማድረግን አትተው። ስለራሳችሁ የምታውቁት ድክመት፣ ጉድለት ወይም ኃጢዓት ዱዓዕ ከማድረግ አይከልክላችሁ። #ኢብሊስ ከፍጡራኖች ሁሉ የከፋ ከመሆኑ ጋር አላህ ዱዓውን ተቀብሎለታል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/AbulBuhari46
https://t.me/AbulBuhari46.
ጥያቄ ? 📮📮
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል።
📝 ጥያቄ እውነት/ ሀሰት በማለት መልሱ ።
ለመጀመሪያ ግዜ ሳሙና ያዘጋጀው ነብይ ነብዩሏህ ሱለይማን ናቸው።
♦️በልብ ውስጥ የሚቀመጥ መርዝ‼️
ደስት ስሜት ሳይሆን ውስጣዊ ሰላም ነው። ደስታ ማለት የውስጥ ሰላም ሲሆን ጠላቶቹ ደግሞ ቂም እና ጥላቻ ናቸው።
ቂመኛ አትሁኑ፣
በማንም ላይ ጥላቻ አይኑርባችሁ።
ቂም በሰው ልብ ውስጥ ተቀምጦ የሰውን ህይወት የሚያበላሽ እና የሚበላ #ትል ነው።
የሰውን ህይወት የሚጎዳው ደስታ አልባ የሚያደርገን አንዱና ዋናው #ቂም ነው።
..#ቂመኛ ሰው ሰላም የለውም፣
..#ቂመኛ ሰው የህሊና እረፍት የለውም፣
..#ቂመኛ ሰው እውነተኛ ደስታም የለውም፣
#ቂመኛ ሰው ትክክለኛ ስኬትም የለውም፣
#ቂመኛ ሰው የአሏህ ፍቅር የራቀው ነው።
ትል የቆሰለ እና የተጎዳ አካል እንደሚበላ ሁሉ ቂምም የሰውን ህሊና የሚበላ እና የሚጎዳ በሰው ልጅ አእምሮ ውስጥ የተቀበረ #አውሬ ነው።
.......ቂም ውስጥን እየቦረቦረ፣
......እንቅልፍ የሚያሳጣ፣
.....ደስታን የሚቀማ፣
በስራችን ስኬት እና ውጤት አልባ የሚያደርግ፣ከመሰሎቻችን ጋር በሰላም እንዳንንኖር በማድረግ ከሰውነት ተራ የሚያወጣ በሽታ ነው።
#ቂመኛ ሰው ቂም የያዘበትን ሰው ባየው እና ባስታወሰው ቁጥር አዕምሮው እንዲደማ የሚያደርግ #አሲድ በውስጡ ማስቀመጥ ማለት ነው።
የሰላም ህይወት መኖር ከፈለክ በሰው ላይ ቂም አትያዝ፣ጥላቻ አይኑርብህ።
ድንገት ካለብህም ያልተጣለ ቆሻሻ እየሸተተ እንደሚመጣ ሁሉ ያልተሻረ ቂምም እየመረዘህ ይመጣልና ቶሎ በይቅርታ አስወግደህ የውስጥ ሰላምህን አግኝ።
......ሰላማዊ ሰው ማለት ሰውን ያልበደለ እና በሰው ላይ ቂም የለለበት ሰው ነው።
ቂም በልብ ውስጥ የሚቀመጥ መርዝ ነው።
♦️#ወገኖቸ_ሆይ‼️
ወላሒ በልባችሁ ቂም አይኑርባችሁ።
ጠልታችሁ እና ቂም ይዛችሁ እንዳትሞቱ ተጠንቀቁ ለማለት እወዳለሁ።
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
Repost from Abu Hayder Aliy
🌿حقوق المسلم على المسلم🌿
قال النبي ﷺ:
«حَقُّ الْمُسْلِمِ عَلَى الْمُسْلِمِ سِتٌّ»
قِيلَ: مَا هُنَّ يَا رَسُولَ اللَّهِ؟ قَالَ:
«إِذَا لَقِيتَهُ فَسَلِّمْ عَلَيْهِ، وَإِذَا دَعَاكَ فَأَجِبْهُ، وَإِذَا اسْتَنْصَحَكَ فَانْصَحْ لَهُ، وَإِذَا عَطَسَ فَحَمِدَ اللَّهَ فَسَمِّتْهُ، وَإِذَا مَرِضَ فَعُدْهُ، وَإِذَا مَاتَ فَاتْبَعْهُ»
رواه مسلم
1⃣. ردُّ السلام وإفشاؤه
قال الله تعالى:
﴿وَإِذَا حُيِّيتُمْ بِتَحِيَّةٍ فَحَيُّوا بِأَحْسَنَ مِنْهَا أَوْ رُدُّوهَا﴾ [النساء: 86].
አንድ ሙስሊም ወንድሙን ሲያገኘው ሰላምታ መስጠት እና ሰላምታውን በተሻለ ወይም በተመሳሳይ መመለስ ከሙስሊም መብቶች ነው።
2⃣. دعوتُه إذا دعاك
ሙስሊም ወንድምህ ወደ ሚፈቀድ ጉዳይ ከጋበዘህ በተቻለህ መጠን ግብዣውን መቀበል ይገባል።
3⃣. النصيحة
قال النبي ﷺ:
«وَإِذَا اسْتَنْصَحَكَ فَانْصَحْ لَهُ»
የሙስሊም ወንድምህ ምክር ከጠየቀህ፣ በቅንነት መምከር አለብህ። ለእርሱ መልካም የሆነውን እንጂ የሚጎዳውን አትመክረው።
4⃣. تشميتُ العاطس
إذا عطس المسلم وقال: الحمد لله، تقول له:
يرحمك الله
فإذا قال:
يهديكم الله ويصلح بالكم
فقد ورد ذلك في الحديث.
አንድ ሙስሊም ካስነጠሰ በኋላ «الحمد لله» ካለ፣ «يرحمك الله» ማለት ከመብቶቹ ነው።
5⃣. عيادة المريض
قال النبي ﷺ:
«وَإِذَا مَرِضَ فَعُدْهُ»
ሙስሊም ወንድምህ ሲታመም ሊጠይቀው መሄድ ከመብቶቹ ነው። ይህም ለታመመው ሰው መጽናናትና መደገፍ ነው።
6⃣. اتباعُ جنازته
قال النبي ﷺ:
«وَإِذَا مَاتَ فَاتْبَعْهُ»
ሙስሊም ወንድምህ ከሞተ የጀናዛውን ሥርዓት መከተልና ቀብሩ ላይ መገኘት ከመብቶቹ ነው።
ومن أعظم حقوق المسلم أيضًا
قال الله تعالى:
﴿إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ فَأَصْلِحُوا بَيْنَ أَخَوَيْكُمْ﴾ [الحجرات: 10].
«ምእመናን በእርግጥ ወንድማማቾች ናቸው፤ ስለዚህ በሁለቱ ወንድሞቻችሁ መካከል እርቅ አድርጉ።»
እንዲሁም ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«الْمُسْلِمُ أَخُو الْمُسْلِمِ، لَا يَظْلِمُهُ، وَلَا يَخْذُلُهُ، وَلَا يَحْقِرُهُ»
رواه مسلم.
«ሙስሊም የሙስሊም ወንድም ነው፤ አይበድለውም፣ አይጥለውም፣ አያዋርደውም።»
ስለዚህ ከሙስሊም ወንድማችን መብቶች መካከል ሰላምታ፣ ምክር፣ በችግር መርዳት፣ በሕመም መጠየቅ፣ ክብሩን መጠበቅ፣ አለመበደል፣ አለመናቅ እና በመልካም ነገር መተባበር ይገኙበታል።
https://t.me/abu_hayder_aliy
https://t.me/abu_hayder_aliy
Repost from قَنَاةُ أَبِــي حَسَان عَلْي بن يُوسُف
🤩የሆነ ጊዜ ሚዳቆን ለምን ሁሌ እንደሚበልጠዉ ዉሻ ጠየቀ ይባላል..
ሚዳቆዉም :-እኔ የምሮጠዉ ሁሌ ለነፍሴ ነዉ ሩሄን ለማትረፍ ነዉ ..አንተ ደሞ ለአለቃህ ነዉ የምትሮጠዉ...
ለእዉነት ሚዳቆ መሆን ባትችል ለስህተት ዉሻ አትሁን!
ተቀላቀሉ💗
💗💗💗💗💗💗
https://t.me/abu_hassan_aliy_yusuf
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
አቡል ዓሊያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
- “የቱስተር ከተማን በከፈትን ጊዜ በሁርሙዛን ግምጃ ቤት ውስጥ አስከሬን ያለበት አልጋ አገኘን። … አስራ ሶስት የተበታተኑ ቀብሮችን በቀን ቆፈርንና (ካንዱ) ውስጥ በሌሊት ቀበርነው። ከዚያም ሰዎች እንዳያወጡት በመስጋት እንዳይለይ አድርገን ቀብሮቹን ሁሉንም (በተመሳሳይ ከመሬት) አስተካከልናቸው።”
* “ከሱ ምን ይፈልጋሉ?” ተብለው ሲጠየቁ፣
- “ድርቅ ሲሆንባቸው አልጋውን ይዘውት ይወጡና ዝናብ ይለምኑበታል” አሉ አቡል ዓሊያ።
* “ሰውየው ማነው ብላችሁ ትገምታላችሁ?” ብለው ጠየቋቸው።
- “ዳንኤል የሚባል ነው” አሉ።
* “ስታገኙት ከሞተ ምን ያክል ሆኖታል?”
- “ሶስት መቶ አመት ሆኖታል።”
* “ከሱ ምን የተቀየረ አለው?”
- “ከማጅራቱ አካባቢ ጥቂት ፀጉሮች እንጂ የተቀየረ የለም። የነብያትን ስጋ'ኮ አፈር አይበላውም።” [አልመጋዚ፣ ኢብኑ ኢስሓቅ፡ 6]
ኢብኑል ቀይም ረሒመሁላህ ከዚህ ታሪክ ስር እንዲህ ይላሉ፡-
“በዚህ ታሪክ ውስጥ ሙሃጂሮችና አንሷሮች የፈፀሙት ተግባር ሰዎች እንዳይፈተኑበት ቀብሩን እንዳይለይ ማድረግ ነው እንጂ እሱ ዘንድ ዱዓእ እንዲደረግና በረካ እንዲፈልጉበት ግልፅ ማድረግ አይደለም። ዘግይተው የመጡት ሰዎች ቢያገኙት ኖሮ ለሱ ሲሉ በሰይፍ ይሞሻለቁ ነበር። ከአላህ ውጭም ያመልኩት ነበር። በርግጥም ከዚህ ጋር የማይነፃፀሩና የማይቀራረቡ መቃብሮችን ጣኦቶች አድርገው ይዘዋል። አገልጋዮች መድበውላቸዋል። ከመስጂዶች የበለጡ የአምልኮት ቦታዎችም አድርገዋቸዋል።
መቃብር ዘንድ ዱዓእ ማድረግ፣ እዚያም ሶላት መስገድ፣ በነሱም በረከትን መሻት ትሩፋት ቢኖረው ኖሮ ወይም ሱና ቢሆን ኖሮ ወይም የተፈቀደ ቢሆን ኖሮ ሙሃጂሮችና አንሷሮች ይህን ቀብር ለእንዲህ አይነት ተግባር ምሳሌ ያደርጉት ነበር። እሱም ዘንድ ዱዓእ ያደርጉ ነበር። ከኋላቸው ለሚመጣ ትውልድም ፍኖት ያደርጉት ነበር። ነገር ግን ከኋላቸው ከመጡ ክፉ ምትኮች በተሻለ አላህን፣ መልእክተኛውንና እምነቱን የሚያውቁ ነበሩ። እነሱን በመልካም የተከተሉ ታቢዒዮችም እንደዚያው በዚሁ መንገድ ላይ ነው የተጓዙት። እነሱ በብዛት እያሉ ከነሱ ዘንድ የሶሐቦች መቃብር በየሀገራቱ በብዛት ነበር። ከመሆኑም ጋር ከነሱ ውስጥ አንድም ከሶሐቦች ቀብር ዘንድ ሄዶ እርዳታ የጠየቀ፣ እሱንም የለመነ፣ በሱም የተመጀነ፣ በሱ ፈውስን፣ ዝናብን፣ እገዛን የጠየቀ የለም።” [ኢጋሠቱል ለህፋን፡ 1/202-203]
* ይህንን ፅሁፍ ያስታወሰኝ የያያዝኩት ቪዲዮ ነው። ለማንኛውም በሆነ ምክንያት ለየት ያለ ቦታ ላይ የሆነ ነገር የምትቀብሩ ከሆነ ሱፊያ እንዳያያችሁ ጥንቃቄ አድርጉ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ያ ሁሉ ወጣት እንደ ቅጠል ረግፎ፣ ካለፈው ከደረሰው እንደ መማር ዛሬም ጠበንጃ መወልወል አሳዛኝ ነገር ነው። ክፉ ልክፍት! ደም የማይጠግብ አእምሮ!! የወጣቶች በአጭር መቀጨት፣ የእናቶች በሀዘን መሰበር፣ የአዛውንቶች ያለ ጧሪ ቀባሪ መቅረት፣ የሃገር መቆርቆዝ የማያስደነግጠው ልብ ከጠላት በላይ ጨካኝ ነው። ሰው ሌሎች ላይ ከደረሰው፣ ከጎረቤቱ ይማራል። እሱ ቢቀር እንዴት በራስ ላይ ከደረሰው መማር ያቅታል?!
ለማንኛውም ወጣት ሆይ! ለራስህ እወቅበት። በስምህ የሚምለው ሁሉ ተቆርቁሮልህ እንዳይመስልህ። ጀግና ጀግና የሚልህ ጀግና ስለሆንክ አይደለም። እየሸነገለህ ነው። ራሱንም ቤተሰቡንም ከእሳቱ አርቆ ነው አንተን የሚማግደው። ካንተ ሞት በኋላ ልጅህን፣ እናትህን ዞሮ አያይም። ግፋ ቢል ነገ ካንተ ሞት በኋላ የሰማእታት ሀውልት ብሎ የድንጋይ ክምር ቢያቆምልህ ነው። ይሄ ላንተም ለቤተሰብህም የሚጠቅመው ነገር የለም። ህዝብ ማደንዘዣ፣ ሌላ እልቂት ማቀጣጠያ እንጂ የሚፈይደው አንዳች ነገር የለም። ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from አቡ አዩብ ሙሃመድ ሰይድ ሙሃመድ
📖📖📖 የቁርዐን ጉዞህን አታቋርጥ!
📍ቁርዐንን መሐፈዝ ጀምራችሁ በመካከል ያቋረጣችሁ ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣
አደራችሁን! የጀመራችሁትን የአላህን ቃል አትተዉ!
አዎን፣ ሕይወት ሁልጊዜ ቀላል አይደለም።
📍 የሚያደክሙን ሁኔታዎች፣ የሚያስቆሙን ችግሮች፣ የሚያዘናጉን ነገሮች ሊያጋጥሙን ይችላሉ። ከቁርዐን ልንርቅ፣ ልንደክም፣ እንኳን ልንቆም እንችላለን።
ግን ለዘላለም አንቁም!
🌿 ትናንት ብትቆሙ፣ ዛሬ ተመለሱ።
🌿 ትናንት ብትደክሙ፣ ዛሬ እንደገና ጀምሩ።
🌿 ትናንት ብትረሱ፣ ዛሬ እንደገና አስታውሱ።
🌿 ብዙ ጊዜ ቢያልፍም፣ የተዘጋውን ሙስሐፍ እንደገና ክፈቱ።
📍የቀራችሁ ብዙ ከሆነ አትፍሩ። አንድ ገጽ በአንድ ገጽ፣ አንድ አንቀጽ በአንድ አንቀጽ፣ አንድ እርምጃ በአንድ እርምጃ ቀጥሉ።
ትልቁን ርቀት ስለማትችሉ አትቁሙ፤ የምትችሉትን ትንሽ እርምጃ ዛሬ ውሰዱ።
📍ወንድሜ፣ እህቴ… የትናንት ድካምህ የዛሬ ተስፋህን እንዳይገድልብህ። ያለፈውን ተወው፤ ወደ ቁርዐን ተመለስ።
📖 ሙስሐፍህን ክፈት።
ከቆምክበት ቦታ ጀምር።
የረሳኸውን እንደገና ድገም።
በትንሹም ቢሆን ቀጥል።
አንድ ቀን ወደ ኋላ ተመልሰህ ስታይ፣ ዛሬ የወሰድከው ትንሽ እርምጃ ትልቅ ጉዞ እንደነበር ትገነዘባለህ።
🌹 አትተዉ… ተመለሱ!
አትቁሙ… ቀጥሉ!
ተስፋ አትቁረጡ… አላህን ተስፋ አድርጉ!
🤲 አላህ የቁርዐንን ፍቅር በልባችን ያስርጽ፣ ለመማርና ለመሐፈዝ ያበረታን፣ የተቋረጠውን ጉዞ እንድንቀጥል ያግዘን፣ ቁርዐንንም የሕይወታችን ጓደኛ እና የልባችን ብርሃን ያድርግልን። አሚን። 🤲
ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ
https://telegram.me/abutoiba
https://telegram.me/abutoiba
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
👉ፍፁም ሴት አለች⁉️
---------------------
አታስመስይ ራስሽን ሆነሽ ኑሪ ለሆነ ሰው ልዩ ፍጡር ልትሆኝ ትችያለሽ እንጂ በፍፁም ስህተት አልባ ልቶኝ አትችይም።
المرأة هي الأساس الذي يقوم عليه المجتمع،
فهي الأم،
والأخت،
والزوجة،
والابنة،
والصديقة، فهي مربية الأجيال..
ሴት ማለት ማህበረሰቡ የሚገነባበት መሰረት ነች።
እሷ እናት፣
እህት፣
ሚስት፣
ሴት ልጅ፣ጓደኛ ብሎም የትውልዶች መሸጋገሪያ ድልድይ ነች።
ولها الدور الأكبر في بناء المجتمع وتقدمه، وشاركت في بناء الحضارات منذ القدم
وكان لها دور بارز في الحروب،
ማህበረሰቡን በመገንባት እና በማሳደግ ትልቁን ሚና አላቸው።
ከጥንት ጀምሮ ሥልጣኔዎችን በመገንባት ላይ ተሳትፈዋል።
በጦርነትም ውስጥ ትልቅ ሚና ነበራቸው።الرجل يعشق بعينيه والمرأة بأذنيها ወንድ ልጅ በአይኑ ሴት ደግሞ በጆሮዋ ትወዳለች ይባላል። 👉በጆሯቸው ስለሚወዱ ነው መሰል.... لا تعرف المرأة قيمة سعادتها مع زوجها إلّا عندما تفارقه.... አንዲት ሴት ከባሏ ጋር ያላትን የደስታ ዋጋ እስክትለየው ድረስ አታውቀውም ይባላል። 👉ይህ ብቻ አይደለም ሴቶች ስኬትም ናቸው። وراء كل رجل عظيم امرأة. ከእያንዳንዱ ታላቅ ወንድ ጀርባ ሴት አለች። وراء كل رجل سعيد امرأة لا تفارق الابتسامة شفتيها. ከእያንዳንዱ ደስተኛ ወንድ ጀርባ በከንፈሮቿ ላይ ፈገግታ የማይለያት ሴት አለች። 👉ይህ ሁሉ ማለት ግን ስህተት አልባ ናችሁ ማለት አይደለም። ብዙ ሴቶች ግን በሆነ ሰው በተፈለጉ ቁጥር ለሁሉም ሰው ፍፁም እንከን አልባ የሆኑ ይመስላቸዋል ይህ ትልቅ #ስህተት ነው። «በሆነ ሰው የተወደድሽው ፍፁም ሆነሽ ሳይሆን የወደደ ሰው አይን መልካምሽን ብቻ እንጂ ስህተትሽ ወይም ድክመትሽ ላይ ስለማያተኩር ነው ገባሽ⁉️» በህይወት ግቡ ላይ የሆነችው ሀሴት፡ በወንድ ልጅ ጀርባ አለችው ልዩ ሴት፡ ይወዳታል እንጂ እሱን ስላልከዳች፡ ፍፁም አይደለችም ከስህተት የፀዳች፡ 👉.....በአንድ ወቅት አንድ ሰው ተጠየቀ⁉️ ፍፁም ሴት አለችን አሉት⁉️ «እርሱም እንዲህ ሲል መለሰ፦ "ስለ ፍፁምነት የሚጨነቀው ማን ነው?
ጨረቃ እንኳን ፍፁም አይደለችም።በሽንቁሮች የተሞላች ናት። ባሕሩ በሚያስደንቅ ሁኔታ ቆንጆ ነው፤ግን ጨዋማና ጥልቁ ጨለማ ነው። ሰማዩ ማለቂያ የለውም፤ ግን ብዙውን ጊዜ ደመናማ ነው። ስለዚህ የሚያምር ነገር ሁሉ ፍፁም ሳይሆን ልዩ ነው። እናም እያንዳንዷ ሴት ለአንድ ሰው ልዩ ልትሆን ትችላለች እንጂ ፍፁም አይደለችም። ስለዚህ "ፍፁም" ለመሆን መሞከርሽን አቁሚ። የማትፈልጊውን በመሆን፤ ያላመንሽበትን ነገር በማድረግ ሌሎችን ለመማረክ አትሞክሪ። «እኔም በዚህ ቋጨሁ» ከውብ ማህፀኗ በምጧ የወጣሁ፡ እስካሁኗ ሰዓት የሷ አይነት ሴት ያጣሁ፡ ግን በህይወቴ ውስጥ ባሳለፍኩት ሁሉ፡ እጂግ ልዩ ፍጡር ሴት ልጅ አለች አሉ፡ ባያስመርጠኝም ፀባይና መልኬ፡ ውብ የትዳር አጋር ባይጠፋም በልኬ፡ ወንድ ልጅ ነኝና ሴት ልጅ ነች ታሪኬ፡ ሐቁን ለመናገር ፈፅሞ አልሰለችም፡ አወ እርግጠኛ ነኝ ፍፁም ሴት የለችም፡ ሁሉም እንድሰማ መልዕክት እየረጨሁ፡ ሀሳቤ ባያልቅም ቃሌን በዚህ ቋጨሁ፡ «ፍፁም ግን ማንም የለም» .....ኑረዲን አል-ዓረብ http://t.me/nuredinal_arebi http://t.me/nuredinal_arebi
ጥያቄ ? 📮📮
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል።
📝 ጥያቄ እውነት ሀሰት በማለት መልሱ ።
ነቢዩሏህ ኢብራሂም ለመጀመሪያ ጊዜ በሰይፍ የተዋጉ ነቢይ ናቸው ፡፡
ኡስታዛችን ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ባለህበት አላህ ይጠብቅህ እንወድኃለን። እናከብርሃለን።
ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሐፊዘሁላሁ ''ትልቅ ባለውለታችን'' ነው። በተለያዩ ጊዜዎች በሚፅፋቸው ወቅቱን በጠበቁ ፅሑፎቹና በጣፋጭ አንደበቱ በሚያደርጋቸው ሙሐደራዎች በተሳሳቱ አመለካከቶችና ግለሰቦች ላይ በሚሰጣቸው ምላሾቹ ብዙ የተሳሳቱ የጥመት ቡድኖችን አውቀን እንድንርቅ ሰበብ ሆኖናል። አላህ ይጠብቀው። ሙሉ ጤናውን ይመልስለት ብለን ዱዓዕ ከማድረግ ውጪ ውለታውን ችለን መመለስ አንችልም። ብቻ አላህ ይውደደው በጀነትም ይመንዳው። ኡስታዛችንን እንወደዋለን፣ እናከብረዋለን፣ ስንወደው ግን በምክኒያት ነው ፣ በሐቅ በሰለፊያ መንገድ ላይ እስካለ ድረስ እንወደዋለን በምንችለው ነገር ሁሉ ከጎኑ እንቆማለን ኢንሻአላህ።
አረቦች እንዲህ ይላሉ፦
"من لم يستطع الصعود يسب الجبل"
ምን ማለት መሰላችሁ " ተራራ ላይ መውጣት ያልቻለ ተራራውን ይሳደባል" ማለት ነው። ለማለት የፈለኩት አንዳንድ የአህባሽ፣ የኢኽዋን እና የለተሞ መንጋዎች የኡስታዛችንን ሀሳብ በመረጃ መሞገት ሲያቅታቸው መሳደብንና ቅጥፈት መንዛትን ተያይዘውታል። በተለይ የለተሞ መንጋ ቅጥፈትን ቁርስ ምሳና እራቱ አድርጎታል። መች በዚህ ብቻ አበቃ! ሱብሀነላህ! ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ታሞ በነበረ ጊዜ አህባሾች እና የለተሞ መንጋዎች አላህ በዛው በወሰደው በማለት ሞቱን ሲመኙለት ነበር። ይህ የሚያሳየው የአህባሽ እና የለተሞ መንጋዎች ምን ያክል ውስጣቸው እንደተቃጠለ ነው። የኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ብዕር ለመንጋዎች ሚሳይል ሆኖባች እረፍት እና ምቾት ነስቷቸዋል። ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር የሆነ ፅሑፍ ከለቀቀ ልክ ቦምብ እንደተለቀቀባቸው ነው የሚንቀጠቀጡት። ቃጠሎውን ይጨምርላችሁ ብያለሁ። ደግሞ በጣም የሚገርመኝ የተፃፈውን አማርኛ እንኳን ማንበብ አቅቶት ገልብጦ የሚያነብ ንግግሩን ከአውዱ አውጥቶ አዛብቶ የሚረዳ የለተሞ መንጋ ወንድ ሴቱ ትልቅ ትንሹ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ላይ ተናበው ዘመቻ ሲከፍቱ ማየት ነው።
እናንተ ከንቱ የለተሞ ስብስቦች ሆይ! እንዲህ ሲባል አልሰማቹምዴ?
"نبح الكلاب لا يضر السحاب"
"የውሻ ጩኸት ደመናን አይጎዳውም"
ሺህ ጊዜ ጧት ማታ ብትጮሁ ነውራችሁን በአደባባይ ከማስወጣት ውጭ ምንም የምትጨምሩ ሆነ የምትቀንሱት ነገር የለም። ምናልባት ጯሂ ሁሉ ተከታይ አያጣምና የናንተ አይነት አስተሳሰብ ያላቸውን muغ ፈሎች ከዙሪያችሁ ተሰባስበው ሊያጨበጭቡ ይችሉ ይኖናል። አንድ ነገር ግን ልንገራችሁ፦ ዛሬ ሰው ላይ እየዋሻችሁና እየቀጠፋችሁ ከሰበሰባችኃቸው ሰዎች ውስጥ በጊዜያዊ ጩኸታችሁ የተታለሉ ማስተዋል የሚችሉ ሰዎች ነገ ላይ ነውራችሁን ሲያውቁ አኝከው ይተፋችኃል።
👉 እስቲ ንገሩኝ! የተውሂድና የሱና ኪታቦችን በማቃጠል ምን አተረፋችሁ? ለኡስታዙ ሞትን በመመኘትስ ምን አይነት ደስታ ተሰማችሁ? ደግሞ የምቀኝነት መጥፎነቱ ባለቤቱን ራሱን መብላቱ ነው።ገጣሚው እንዲህ ይላል፦
(لله در الحسد ما أعدله
بدأ بصاحبه فقتله)
وقال الشاعر :
*اصبرْ على حسدِ الحسودِ .... فإنَّ صبرَك قاتلُه
النارُ تأكلُ بعضَها .... إن لم تجدْ ما تأكلُه
ምቀኛን የፀጋ መወገድ እንጂ ሌላ ምንም አያስደስተውም።
قال معاوية بن أبي سفيان رضي الله عنهما: (كلُّ الناس أستطيع أن أرضيه إلا حاسد نعمة، فإنه لا يرضيه إلا زوالها)
📜المجالسة وجواهر العلم(3/50)
ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወርን ያለ ምንም ድንበር ማለፍ እንወደዋለን። የሰው ልጅ እንደመሆኑ ሊሳሳት ይችላልና በተሳሳተበት ነጥብ ላይ ግን አንከተለውም።
لأنه بشر يصيب ويخطئ وليس بمعصوم.
↪️ ዘመናዊ ሙሪድነታችሁ እንዳይነቃባችሁ ያን የሽማግሌ ተሳዳቢ በዱኒያዊ ጥቅም ሰክሮ እልል በል ሲሉት እንደ ሴት እልል የሚል ዐብዱል ሀማድ አልለተሚ የበቀልና የእልህ ትችቶቹን ስላልተቀበልን ለተራ ወሬዎቹ ግምት ስላልሰጠን የኢብኑ ሙነወር ሙሪዶች ትሉናላችሁ። የእናንተ ሁኔታኮ፦ "رمتني بدائها وانسلت "
"በሽታዋን ወርውራበኝ አፈተለከች'' እንደተባለው ምሳሌ ነው።
ሸይኻችሁ መርቀን ሲለው ትዝ ያለውን ፉላን ሙብተዲዕ፣ፉላን ዷል ሙዲል፣ ሙመይዕ… እያለ ሲቀባጥር ከስር ሆናችሁ ያን የከረፋ ጩኸቱን እየሰማችሁ ከማስተጋባት በስተቀረ ለምን ብላችሁ መጠየቅ የማታውቁ كالميت بين يدي" غاسله" አጣቢ ፊት እንደቀረበ ጀናዛ"
የሆናቹ ፉጡሮች ሌሎችን ሙሪዶች እያላችሁ ለመወንጀል ሞራሉን ከየት አመጣችሁ!? እናንተኮ እፍረት የሚባል ነገር ስለማታቁ እንጅ አይደለም ሌሎች ላይ አፍ መክፈት ቀርቶ ነውራችሁን ተሸክማችሁ መደበቅ የነበረባችሁ ከንቱ የመንጋ ጥርቅም ናችሁኮ።"ሞኝ ካመረረ በግ ከረረ መመለሻ የለውም" ይባል የለ?! ከራሳችሁ ጋር ተጋጭታችሁ እስከምትናከሱ ድረስ ለጊዜው እንደ ደነበረ በሬ ተራገጡ ተራው የናንተ ነውና።አላህ በሃያት ካቆየን መጨረሻችሁን የምናይ ይሆናል። ያን በዘረኝነት ላይ የቆመ እልህና በቀልን አንግቦ የተነሳ በዲን ሽፋን በመሪነትና በዱኒያ ጥቅማጥቅም የሰከረ የለተሞ መንጋ ኢንሻአላህ መጨረሻቸውን አላህ ያሳየናል።
✍️ አቡ ሰህላ ሙስጠፋ ሰኢድ
☕🌿 የቡና ልዩ ጥቅሞች ! 🌿☕
ሸይኽ ዐብደረዛቅ አልበድር ሀፊዘሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦
«فَعَلَيْكَ بِشُرْبِ الْبُنِّ فِي كُلِّ لَحْظَةٍ
فَإِنَّ بِهَا يَا صَاحِ خَمْسَ فَوَائِدِ»
“ስለዚህ ወዳጄ ፣ ቡናን መጠጣትን አትተው፤ በእሷ ውስጥ አምስት ጥቅሞች አሉ” ይላል። ☕
🌿 ① نَشَاط — ንቃትና ብርታት ይሰጣል
ቡና ለአንዳንድ ሰዎች ንቃትን የምትጨምርና ድካምን የምታሳንስ መጠጥ ናት። ጠዋት ላይ የቡናዋ መዓዛ እና ጣዕም ቀኑን በንቃት ለመጀመር ደስ የሚል ጓደኛ ያደርጋታል።
🌿 ② هَضْم ምግብን ለመፍጨት ይረዳል
ቡና ከምግብ በኋላ ለአንዳንድ ሰዎች የምግብ መፍጨትን እንደምትረዳ ይነገራል።
🌿 ③ قَطْعُ الْبَلَاغِم — አክታን ለማስወገድ ይረዳል
“በላግም” የሚለው ቃል አክታንና በጉሮሮ የሚሰበሰብን ነገር ያመለክታል። ስለዚህ ቡና እነዚህን ለገሮች ለማስወገድ ይረዳል።
🌿 ④ نُورٌ لِلْعَيْن — ለዓይን ብርሃን ይጨምራል
ቡና በውስጡ ለዓይን ንቃትና ብርሃን እንደምትሆን ተገልጻለች። በተለይም የጠዋት ቡና ከንቃት ጋር ተያይዞ የሚሰማውን ያን የልዩ ደስታ ስሜት ያስታውሳል። ☕
🌿 ⑤ قُوتٌ لِعَابِد — ለዓምላኪ ሰው ኃይል ናት
ይህ በጣም ውብ የሆነው ክፍል ነው።
“ለዓምላኪ ኢባዳ ላይ ላለ ሰው ኃይል ናት” ይላል።
ማለትም የቡና መጠጣት እንደ መጠጥ ደስታ ብቻ ሳይሆን፣ ሰውነትን እንዲነቃና ሰውየው በሚፈልገው መልካም ሥራ ላይ እንዲበረታ የሚያግዝ ነገር እንደሆነ ሸይኹ ያቀርባታል።
☕ ቡና ለአንዳንዶች መጠጥ ብቻ አይደለችም፤ የጠዋት አጋር፣ የውይይት ጓደኛ፣ የእንግዳ አቀባበል ምልክት እና የተለያዩ ትዝታዎች አካል ናት።
🌿 “فَعَلَيْكَ بِشُرْبِ الْبُنِّ…” 🌿
ወዳጄ ፣ የቡናዋን ጣዕም ብቻ አትውደድ፤ ከእሷ ጋር የሚመጣውን የጓደኝነት፣ የእንግዳ አቀባበልና የውብ ውይይት ጊዜም ውደድ። ☕
🌿 ማስታወሻ፦ እነዚህ የተገለጹት ጥቅሞች ናቸው፤ የሕክምና ምክር ወይም ለሁሉም ሰው የሚሰራ የጤና ዋስትና አይደሉም። በተቃራኒው ጉዳት የሚያመጣባቸው ሰዎችም መጠጣት የለባቸውም በተለይ በሀኪም ከተከለከሉ አይጠጡ።
እዚህ እያወራን ያለነው ለቡና አፍቃሪያንና ለሚስማማቸው ጥቅም ለምታመጣላቸው ሰዎች ነው።
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy☕ ለቡና ወዳጆች ☕
የቡና መጠጥ ለሰውነት አካላት አነቃቂ ነው፤
ጣዕሙም እንደ ስንዴና እንደ ማር የሚያስደስት ነው።
በጉዞ ወቅት የዕድሜ ሙሉ አጋርና አጽናኝ ናት፤
መዓዛዋም ሲሰራጭ እንደ ሚስክ መዓዛ ያለ ማንኛውንም ክርክር የማያስፈልገው ደስታ ትሰጣለች።
በጠዋት የነፍስ ምኞትና ደስታ ናት፤
በረጋ መንገድ በጊዜዋ ስትመጣ፣ የሚወዳትን ሰው ልብ ታስደስታለች።
በችሎታ የተዘጋጀች ቡና ምንኛ ደስ የምትል ናት!
የመጣውንም ሆነ ሊጓዝ የተዘጋጀውን እንግዳ ለማክበር የምትቀርብ።
በየቤቱ ሁሉ ስሟና በጎነቷ ይነገራል፤
ወዳጅንም ያለ ብዙ ንግግር በመደሰትና በማስደሰት ታስቃለች።
“እንኳን ደህና መጣህ!” ትላለች፤ ፈገግታዋም ሁልጊዜ ከአንደበቷ አይርቅም፤
ክብርና መልካም ምግባር ላለው እንግዳም ይህንኑ የአቀባበል ቃል በደስታ ደጋግማ ትናገራለች።
በእሷ ላይ ጉድለት የለም፤ ከጉዳትም የጸዳች ናት፤
ስለዚህ ንጹሕ ቡና ጠጣ፤ ከጉዳትም አትፍራ።
— ሸይኽ ዘይድ ቢን ሃዲ አል-መድኸሊ رحمه الله
📖 المنظومات الحسان (الديوان المليح)، ص 343.
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_AsselfiyRepost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
ሀገሬ ወሎ ሲናፍቀኝ እፍፍፍፍ
«እንደዚህ ነው ወሎ»
፧
፧
የዘር ጂኒ-ጃንካ አይደርስም ከደጁ፡
ሁሉንም አክባሪ እንደዚህ ነው የጁ፡
እኔም ወደዛው ነኝ #ወሎዬ ነኝ ልጁ፡
፧
፧
ከሰፊው ሜዳ ላይ ተጫውቶ ገራዶ፡
ከወሎ ከተማ #ደሴ ላይ ተወልዶ፡
ከእንቅልፉ ሲነቃ #ጦሳን ያዬ ማልዶ፡
ፍቅር ነው መለዮው ይኖራል ቀልዶ፡
ፈገግ ይላል ፊቱ #በሙሀባ ነ'ዶ
🎙✍️ በኑረዲን አል-ዓረቢ
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
