cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

ዳዕዋ ሰለፍያ በአርባ ምንጭ AMUጫሞ ካምፓስ ሃቅን ፍለጋ ከቁርዓንንና ከትክክለኛ ሃድስ በነዚያ ደጋግ ቀደምቶች ( በሰለፉነ–ሷሊሂን) አረዳድ ! "ከሃቅ በሗላ ጥሜት እንጅ ምን አለ! ? " ስለዚህ ሃቅን ብቻ ተከተል ! ማሳሰቢያ: –ለማንኛውም አስተያየትዎ ከታች ባለው ቦት ያስቀምጡልን ጀዛኩሙላህ ኸይር @JemalEndroAbuMeryem

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
2 364
Obunachilar
-324 soatlar
-77 kunlar
-2730 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ወቅታዊ ሙሓደራ ርዕስ አያመተሽሪቅ የመብል እና የመጠጥ አላህን የማስታወሻ ጊዜ❜ 🎙በኡስታዝ አቡ ሓቲም ኸድር አሕመድ አል-ኸሚሴ «ሐፊዘሁሏህ» ⌲ T.me/Ustaz_Kedir_ahmed_2
Hammasini ko'rsatish...
ሙሓደራ_156_አያመተ1.47 MB
ደግሞም ልንገርህ! አካደሚ እውቀት ቀርቶ ሌሎች የሸሪዐ ዘርፎች እንኳ ዋጋ ይኖራቸው ዘንድ ተውሒድ ላይ የተንጠለጠሉ ናቸው። ሸምሰዲን አሰፋሪኒ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ “ሌሎች የእውቀት ዘርፎች ለተውሒድ እውቀት ቅርንጫፎች ናቸው። ምክንያቱም እሱ ከአምልኮቶች ሁሉ የላቀው፣ ከትእዛዛት ሁሉ በላጩ እንዲሁም እያንዳንዱ አምልኮትና ትእዛዝ፣ ጤናማ ይሆን ዘንድ ብሎም ዋጋ ይኖረው ዘንድ መስፈርቱ ነውና። የክብርና የልቅና ባለቤት የሆነው (ጌታ ምንነት) የሚታወቅበትም ነውና።” [ለዋሚዑል አንዋሪል በሂያ፡ 1/57] ስለዚህ በቅድሚያ ለራስህ ሁን! ለራስህ ሳትሆን ለህዝብ አትሆንም። ያለበለዚያ አስር ገንብተህ ሺ ታፈርሳለህ። ምንም ላይ ሳትሆን ትልቅ ነገር ላይ ያለህ ይመስልሃል። በተውሒድ የምትሳለቅ፣ ለቀብር አምልኮ የምትወግን ከሆንክ የታሪክም ሆነ የፖለቲካ አስተዋፆህ የዜሮ ብዜት ነው የሚሆነው። አልዓስ ብኑ ዋኢል በጃሂሊያ መቶ ግመል ሊያርድ ስለት ተስሎ ነበር። ስለቱን ሳይፈፅም ስለሞተ ልጁ ሂሻም ሃምሳ ግመል አረደለት። ሌላኛው ልጅ ዓምር ግን የድርሻውን ከማረዱ በፊት የአላህ መልእክተኛን ﷺ ስለ ጉዳዩ ቢጠይቅ {አባትህማ ተውሒድን ቢቀበል ኖሮ ብትፆምለት ብትሰድቅለት ይጠቅመው ነበር} ነው ያሉት። [አሶሒሐህ፡ 1/180] ሰላም!! ~ ~ https://t.me/IbnuMunewor
Hammasini ko'rsatish...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

መኖርህ እዳ አይሁን! ላንተ ነው! “ቀለም ለገባህ”! ~~ 1. አንተ ልዩ አይደለህም ሙስሊሙ፤ እንደ ማህበረሰብ ሰቅዘው የያዙት ብዙ አይይነት ችግሮች እንዳሉበት ግልፅ ነው። በኛ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አለማት ኢኮኖሚው የደቀቀ፣ ማህበራዊ ህይወቱ የተናጋ፣ ፖለቲካዊ ስርኣቱና ሚናው የወረደ፣... ብዙ ሙስሊም ማህበረሰብ አለ። ችግሩን ‘ፍሬም’ በማድረግና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ላይ ሃሳቦች ሊለያዩ ቢችሉም ይህን እውነታ በመረዳት አንተ ብቸኛ አይደለህም። እራስህን ከማህበረሰቡ አንዱ እንጂ ልዩ አድርገህ አትሳል። ሙስሊሙ ኡማ ውስጥ የተማረው የቀለለ ከመሆኑ ጋር የተማርከውን የተማሩ፣ የምትረዳውን የሚረዱ ብዙ እንዳሉ አትዘንጋ። ይህንን እውነት ለነፍስህ ሹክ በላት። “ብርቅየ አይደለሽም” በላት። ያኔ እብጠቷ ይተነፍሳል። መንጠራራቷ ይቀንሳል። 2. የደዕዋው ዘርፍ የመፍትሄዎቻችን ሁሉ እናት ነው ቀዳዳዎቻችን ብዙ ናቸው። በዚያው መጠን ዘርፈ ብዙ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ያስፈልጉናል። በሆነች ዘርፍ ላይ ትንሽ አስተዋፅኦ ስለኖረችህ ለሌሎች በተለይም ለደዕዋው ዘርፍ ያለህ እይታ አይንሸዋረር። ለደዕዋው ዘርፍ ያለህ አክብሮት ለኢስላምህ ያለህ አክብሮት ነው። የደዕዋውን ዘርፍ ሳታከብር ለኢስላም አክብሮት ሊኖርህ አይቻልም። ኢስላም ያለ ደዕዋ ምንም ነው። አዎ በደዕዋው ዘርፍ ላይ ብዙ ችግሮች አሉ። ግና “ችግሩ የሚፈታው በማነው?” ብለህ እራስህን ጠይቅ። አንተ ለዚህ ብቃቱ አለህ? የተማርከው ትምህርት ለዚህ የሚያበቃህ ነው? የእውነት አካደሚ ስለተማርክ ብቻ ያለውን መሰረታዊ ችግር የምታውቀው ይመስልሃል? እንዴት ሆኖ?! 3. አንጃዎችን መኮነን ከአንጃ ውጭ አያደርግህም ብዙ የተማሩ ወንድሞች አንጃዎችን ስላወገዙ ብቻ ገለልተኛ የሚሆኑ ይመስላቸዋል። ነገሮችን በዚህ መጠን መረዳት ሲበዛ ግልብነት ነው። በቅድሚያ ገለልተኝነትህ ከሐቅም ሊሆን ስለሚችል ጉዳዩን ከልብ መርምር። ጉዳዩን ቀርበው ሳይመረምሩ ሁሉንም በጭፍንና በጅምላ ማውገዝ በስንፍና ውስጥ ማድፈጥ እንጂ ልዩነትን መፀየፍ አይደለም። ይህንን ለማድረግ አቅምና ፍላጎቱ ከሌለህ ዝምታን ማን ያዘብህ? ምላስህንም ብእርህንም ከንዲህ አይነቱ ጉዳይ ሰብስበህ በምትችለው ሙያ ወገንህን አገልግል። በአደብህ ተከበር። የማትችለውን ገብቼ አቦካለሁ ስትል፣ በምትችለው ዘርፍ ልታበረክተው የምትችለውን አስተዋፅኦ ታመነምነዋለህ። ልንገርህ ወዳጄ! የሆኑ የሚፋጩ አካላትን ስላየህ፣ የሚወረወሯቸውን ቃላት ስለሰማህ ብቻ ስለጉዳዩ ያለህን መረዳት በዚያ መጠን አቅልለህ አትመልከት። እንዲህ አይነቱ ጥራዝ ነጠቅ ድምዳሜ ነው አንዳንዶችን በመሰረታዊ የኢስላም ክፍል ላይ እንዲሳለቁ እየገፋቸው ያለው። ሳይረዱ እንደተረዱ ማሰብ። እንዲያውም የአንዳንዶቹ ገለልተኝነት ከማስመሰል የዘለለ አይደለም። ክስተቶችን እየጠበቁ ለይተው ሲያጠቁ፣ ለይተው ደግሞ ሲያደንቁ ታገኛቸዋለህ። “የአይነላህ ተቆርቋሪዎች” እያለ በነብዩ ﷺ ሐዲሥ ላይ የሚያሾፍ ሰው፣ “ተው” እና “ሂድ” እያለ በተውሒድ ላይ የሚሳለቅ ሰው በየትኛው ሞራሉ ነው ስለ ገለልተኝነት የሚያደነቁረን? ለኡማው መትረፉ ቀርቶ እራሱን ባዳነ! 4. ይልቅ ለኡማው ሸክም አትሁን! እራስህን ብቻ ሁን! ሁለት እግር አለኝ ብሎ ሁለት ዛፍ ላይ አይወጣም። ማኔጅመንት ወይም ፖለቲካ ተምረህ የደዕዋ ስልጠና ካልሰጠሁ አትበል። በዱዓት ላይ መዘባነንህን አቁም። ፖለቲካ ብትደሰኩርም፣ ታሪክ ብትተርክም፣ መድረክ ብታደምቅም ዋጋ የሚኖረው ለተውሒድ በሚኖርህ ክብር ነው። አክብሮቱ ቀርቶ ሸክም የምትሆን ከሆነ የትኛውም ያንተ አበርክቶ ገለባ ነው። ተውሒድና ሺርክን የማትለይ፣ በተውሒድ ላይ እየተሳለቅክ ለቀብር አምልኮ የምትወግን ከሆነ፣ ወይም ደግሞ በገለልተኝነት ስም ተውሒድንም ሺርክንም እኩል የምታወግዝ ከሆነ እውነቴን ነው የምልህ ከመኖርህ አለመኖርህ የሚሻል ለመባል እንኳን አትመጥንም። እንዲያውም ለሙስሊሙ ኡማ ከጠላት የከፋ እዳ ነህ። 5. ከ“ንቃትህ” ንቃ! መንቃት ማለት እንግሊዝኛ እየቀላቀሉ ማውራት አይደለም። መንቃት ማለት በግምት የታጨቀ የሴራ ፖለቲካ መፈትፈት አይደለም። መንቃት ማለት የራስን እያናናቁ በፈረንጅ ፍልስፍና ላይ መራቀቅ አይደለም። መንቃት እራስን ማወቅ ነው። መንቃት የማህበረሰብን መሰረታዊ ችግር መለየት ነው። ተውሒድና ሺርክን የማትለይ፣ የወገንህ የሙታን አምልኮ ላይ መነከር የማይቆጠቁጥህ ከሆነ እንኳን ለሰው ልትተርፍ ለራስህ አንቂ ያስፈልግሃል። ደግሞም እወቅ! ይሄ ሌሎችን ማናናቅና እራስን መቆለል የጀርባ መንሴው ለዘመናዊ ትምህርት ያለህን የተንሸዋረረ እይታ ነው የሚያጋልጠው። ትምህርቱ አስፈላጊ እንደሆነ የሚያከራክር አይደለም። ህዝበ ሙስሊሙ ባለመማሩ የደረሰብት ውስብስብ ችግር እንዳለ የሚዘነጋ አይደለም። ቢሆንም በልክ አድርገው። የቀለም ትምህርት ከዲን ትምህርት፣ እንግሊዝኛ ከዐረብኛ፣ የነ ዑመር፣ የነ ሙዓዊያ ታሪክ፣ ከነ ሶቅራጠስ ሊነፃፀር አይችልም። በቅድሚያ እራስህን ከአስተሳሰብ ተፅእኖ ነፃ አውጣ! እነ ፍሮይድና ማስሎውን እያደነቅክ ዑለማዎችን የምትንቅ ከሆነ ብሽቅነትህን ብቻ ነው የምታሳየው። “የፋርስና የሮማ ፈላስፎች ጥበብ ላይ የሚያተኩር ለኢስላማዊ ጥበብና ስርኣት ልቡ ውስጥ ቦታ አይኖርም” ይላሉ ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ። [አልኢቅቲዷእ፡ 217] 6. ሚናህን ለይ! ዱዓት መሃል ብዙ ችግሮች እንዳሉ የሚታወቅ ነው። የምታየው ቢያምህ ሰውኛ ስሜት ነው። ሃሳብ ካለህ ዲኑ ያንተም ነውና እርምትና ሃሳብ መስጠት ያባት ነው። ችግር የሚመጣው ያልገባህን እያወራህ የእብድ ገላጋይ ስትሆን ነው። ወይ ዲንህን ተማር! ወይ ሃሳብህ የተመጠነ ይሁን። ባቅምህ ልክ ብቻ አውራ። ቀይ መስመር አትለፍ። ማኔጅመንት ተምረህ ቀዶ ጥገና ህክምና ካላደረግኩ ትላለህ እንዴ? ሳይኮሎጂ ላይ እድሜህን ፈጅተህ ተፍሲር ካላስተማርኩ ይባላል ወይ? ልክ ሃያ ሰላሳ አመት እድሜህን የቀለም ትምህርት ላይ ስለፈጀህ ብቻ ይሄ ነው የሚባል ትኩረት ባልሰጠኸው እምነት ላይ ፈራጅ ቀዳጅ ካልሆንኩ አይባልም። በቃ አቅምህንና ተሰጥኦህን ለይ! የግድ ስለ ሁሉም ማውራት አይጠበቅብህም። 7. ስለ ዲንህ ተማር በቀለም ትምህርት ላይ መራቀቅ እንደምትሻው ሁሉ ለዲናዊ ትምህርትም ጊዜ ስጥ። ከምንም በላይ የዚያኛውን አለም ስንቅ ታዘጋጅበታለህ። በመተጓዳኝ የራስህን ጨምሮ የወገንህን ችግርና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ትለይበታለህ። በርግጠኝነት ነገሮችን የምትመለከትበት መነፅርም ይቀየራል። በተለይም ደግሞ መሰረታዊ የእምነትህን ክፍል ተውሒድን ተማር። አካደሚ ስለተማክ ብቻ ከሺርክ የምትርቅ ከመሰለህ ሞኝ ነህ ወላህ! በአለም ላይ ቁራጥራጭ እንጨቶችን፣ ያሸበረቁ ስዕሎችን፣ ላሞችን፣ አይጦችን፣ በሰው ልጅ ብልት አምሳል የተቀረፁ ሀውልቶችን የሚያመልኩ ህልቆ መሳፍርት ዶክተሮች፣ ፕሮፌሰሮች አሉ። የተማሩት ትምህርት፣ የሚቀናጡበት ቴክኖሎጂ፣ የተቆናጠጡት ስልጣን፣ የሚያጋብሱት ሀብት ግኡዛንና እንስሳትን ከማምለክ አላወጣቸውም። ብልህ በሌሎች ይማራል። ሞኝ በራሱ ላይ በሚደርሰው ይማራል። አንተ ከሁለቱም ተራ ወጥተህ ሳይማሩ የተማሩ ከሚመስላቸው አትሁን።
Hammasini ko'rsatish...
የዘመኑ ሰዉስ፦ እፍፍ ቢሉት ንፋስ       ቢደገፉት ድርምስ    ቢከፋፈት ፍስስ          ቢከዳደን ቸሰስ    ቢለቁት ትርምስምስ    ቢጨብጡት ቅንስ   የዘመኑ ሰዉስ             ስትቀርበዉ ቀልበስ ስትርቀዉ ምልስ          ነፍሲያዉን ዉድስ    ስራዎቹን ቅድስ            የዘንድሮ ሰዉስ ሰፍሰፍ ስትወደስ          ክስስ ስትወቀስ ስትወደዉ ለምን       ስትርቀዉ ልምን       ስትረዳዉ ልቅም       ስትረሳዉ እርግም   ችላ ስትል ድርግም    ስትመክረዉ ግግም ሲሞላልህ ሞልቶ ወንድም ስትቼገር የለም አንድም ሲሳካልህ ፈገግ         ስትከስር ጨፍገግ ስልጣን ሲኖር ዉድድ  ስልጣን ሲያጣ ዉርድ ስትወደድ ስግድ         ስትጠላ ሽዉድ 🎙𝐀𝐛𝐝𝐮 𝐒𝐡𝐢𝐤𝐮𝐫 𝐀𝐛𝐮 𝐅𝐞𝐰𝐳𝐚𝐧 t.me/abu_fewzan_abdu_shikur t.me/abu_fewzan_abdu_shikur
Hammasini ko'rsatish...
Abdu shikur abu fewzan

በአብዱ ሽኩር አቡ ፈዉዛን የሚሰጡ የተለያዩ የኪታቦች እና ዳእዋዎች የሚለቀቅበት ቻናል ነዉ፡፡ ቻናላችንን ይቀላቀሉ ተጠቃሚም ይሁኑ! አስተያየትና ገንቢ ምክር ካለዎት በዚህ ያቀብሉን @Abu_fewzan_bot

السلام عليكم ورحمتله وبركاته ውድ የአላህ ባሮች እንኳን ለዚህ ለተከበረው ኢደል አድሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ኢድ ሙባረክ عيد مبارك تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال እንኳን በሰላም ለዒደ አል አድሃ አደረሳችሁ ------------------ @✍🎙ወንድማችሁ ጀማል እንድሮ ከወሎ–ወረኢሉ 🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Hammasini ko'rsatish...
03:15
Video unavailableShow in Telegram
ስዕል አምላኪ ስትሆን እንዲ ይደናገርሀል! እስከዛሬ አርሴማ ብለን ያመለክናት ልክ አይደለም ስዕል ተሳስተናል ስለዚህ የአምላክ (የስዕል) ለዉጥ አድርጉ እያሉ ነዉ!:: አልሀምዱሊላህ አላ ኒዕመቲል ኢስላም! t.me/NABAWITUBE
Hammasini ko'rsatish...
16.65 MB
ኡስታዝ ሳዳት ከማል ከዱዐ ሁሉ በላጭ የዐረፋ ቀን የሚደረግ ዱዐ ነው። t.me/NABAWITUBE
Hammasini ko'rsatish...
የአረፋ ዱዓ.mp39.86 KB
👍 2
📢 አስደሳች ዜና ለተፍሲር እውቀት ፈላጊዎች! 📖 አዲስ የደርስ ማስታወቂያ 📚 የሚጀመረው ደርስ :- تيسير الكريم الرحمن في تفسير كلام المنان ✍ የኪታቡ አዘጋጅ :- الشيخ العلامة عبد الرحمن بن ناصر السعدي -رحمه الله- 🎙 ትምህርቱን የሚሰጡት :- ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም -ሐፊዘሁላህ- 🕌 ትምህርቱ የሚሰጥበት ቦታ:- ፉሪ (በፉሪ ሜዳ ፊት ለፊት ባለው ቅያስ ገባ ብሎ) አቡበክር አስሲዲቅ መስጂድ 🕔 ትምህርት የሚሰጥበት ቀንና ሰዐት :-  ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከረፋዱ 4:00 ጀምሮ እስከ 5:00 🗓 ትምህርቱ ሚጀመረው :- ሰኞ ዙልሒጃህ 18,1445 ሂጅሪ (ሰኔ 17,2016 E.C) - * ለሴቶች በቂ ቦታ አለ * በአካል ተገኝታችሁ መከታተል ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል እንዲሁም ሪከርዱም ይለቀቃል ኢንሻአሏህ። የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam
Hammasini ko'rsatish...
قناة دروس فضيلة الشيخ محمد زين بن آدم الحبشي - Sheikh Muhammed Zain Adam - ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ይህ የሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም ትምህርቶች ብቻ የሚለቀቅበት ቻናል ነው። ቴሌግራም -

https://t.me/Sheikhmuhammedzainadam

📡 livestream ⚙️ 🎁የመጀመሪያው የመሀደራ ፕሮግራም 🎁     ርዕስ ✅ አረፋ በጉራጌ ማህበረሰብ በሚል...🖋👇 🎙<ኡስታዝ_አብዱናስር_መኑር> 🌹ተ     🌹ጀ         🌹ም             🌹ሯ                  🌹ል ገባ ገባ በሉ ባረከሏሁ ፊኩም ተከታተሉ ሼር አድርጉት: 📎📎📎📎📎📎📎📎🔗🔗🔗🔗 https://t.me/tdarna_islam?livestream https://t.me/tdarna_islam?livestream
Hammasini ko'rsatish...
የመጀመሪያው የሙሓደራ ፕሮግራም የዙልሒጃ 10 ቀናቶች ትሩፋት በሚል ርእሥ በወንድማችን አቡ ዑሰይሚን ሀፊዞሁሏህ 🌹ተ    🌹  ጀ             🌹ሯ                     🌹ል https://t.me/nikab_jilbab_group?videochat=d170dcf68cbbf84cf4
Hammasini ko'rsatish...
የጂልባብና የኒቃብ ባንክ ግሩፕ

የግሩፑ አላማ የኒቃብና ጂልባብን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ በአላህ ፍቃድ ሰፊ እቅድ ይዘን ተነስተናል። እህቶች ካላቸው ኒቃብና ጅልባብ አንድ ቀንሰው ለተቸገሩ እህቶቻችን በመስጠት ፣ ወንድሞች ደግሞ በሚችሉት አቅም በገንዘብም ይሁን አልባሳቱን በመግዛት እህቶችን እንዲረዱ የምናደርግበት ነው። አካውንት 1000588690486 ሂክማ&/አህላም&/ ሙሂባ

Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.