MESOB_Initiative (MI)
Відкрити в Telegram
🌈 Mesob Initiative : An Ethiopian queer arts and advocacy collective using media, literature, and creative expression to advance LGBTQ+ rights and visibility.✊✨ 🕊 PEACE AND FREEDOM FOR ALL! 🌍 YOUR Voice , OUR Freedom! 🏳️
Показати більше405
Підписники
-224 години
-17 днів
+14630 день
Триває завантаження даних...
Схожі канали
Немає даних
Виникли проблеми? Будь ласка, оновіть сторінку або зверніться до нашого support-менеджера.
Хмара тегів
Немає даних
Виникли проблеми? Будь ласка, оновіть сторінку або зверніться до нашого support-менеджера.
Вхідні та вихідні згадування
---
---
---
---
---
---
Залучення підписників
червень '26
червень '26
+178
в 1 каналах
травень '26
+19
в 0 каналах
Get PRO
квітень '26
+31
в 0 каналах
Get PRO
березень '26
+34
в 0 каналах
Get PRO
лютий '26
+20
в 0 каналах
Get PRO
січень '26
+28
в 0 каналах
Get PRO
грудень '25
+19
в 0 каналах
Get PRO
листопад '25
+23
в 1 каналах
Get PRO
жовтень '25
+31
в 0 каналах
Get PRO
вересень '25
+51
в 2 каналах
Get PRO
серпень '25
+60
в 1 каналах
Get PRO
липень '25
+56
в 2 каналах
Get PRO
червень '25
+81
в 1 каналах
Get PRO
травень '25
+148
в 2 каналах
Get PRO
квітень '250
в 0 каналах
Get PRO
березень '25
+121
в 1 каналах
Get PRO
лютий '250
в 1 каналах
Get PRO
січень '250
в 2 каналах
Get PRO
грудень '24
+56
в 0 каналах
| Дата | Залучення підписників | Згадування | Канали | |
| 22 червня | +3 | |||
| 21 червня | +1 | |||
| 20 червня | +1 | |||
| 19 червня | +1 | |||
| 18 червня | +4 | |||
| 17 червня | +5 | |||
| 16 червня | +3 | |||
| 15 червня | +1 | |||
| 14 червня | +2 | |||
| 13 червня | +5 | |||
| 12 червня | +6 | |||
| 11 червня | +10 | |||
| 10 червня | +109 | |||
| 09 червня | +2 | |||
| 08 червня | +2 | |||
| 07 червня | 0 | |||
| 06 червня | +2 | |||
| 05 червня | +1 | |||
| 04 червня | +1 | |||
| 03 червня | +1 | |||
| 02 червня | +7 | |||
| 01 червня | +11 |
Дописи каналу
እነዚህን ታሪኮች ስሰማ የተሰማኝ ነገር ምን ያህል በተለያዩ ከተሞች እየኖርን የማመሳሰሉ ፍርሃት ፣ ስጋት ፣ ጥንቃቄ ፣ ፍላጎት እንዳለን እና ከምናስበው በላይ የምንመሳሰል መሆናችንን ነበር።
ይህ ሁሉ የሚያስተምረን ብዬ የማስበው ምን ያህል አንዳችን ለአንዳችን ልናዝን ፣ ልንጠነቀቅ ልንተሳሰብ እንደሚገባን ነው። አንድነታችን ብርታታችን ነው። ከሁሉ በላይ የነበረው አንዱ ትልቅ ነገር #ራስንመቀበል ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ ነው።
መልካም ንባብ እንደሚሆንላችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።
የዲ - Yedi ለዚህ ድንቅ ስራ ተሳታፊ ስላደረጋችሁኝ አመሰግናለሁ 🥰
ከላይ ያለውን ሊንክ በመጠቀም መፅሐፉን ማንበብ ይችላሉ 🥰
#የእናንተድምፅየሁላችንነፃነት
#ሰላምእናነፃነትለሁሉም
| 2 | https://yedi.media/%e1%8b%a8%e1%8a%ad%e1%8d%8d%e1%88%88-%e1%88%83%e1%8c%88%e1%88%ad-%e1%8b%88%e1%8c%8d-2/ | 45 |
| 3 | https://yedi.media/%e1%8b%a8%e1%8a%ad%e1%8d%8d%e1%88%88-%e1%88%83%e1%8c%88%e1%88%ad-%e1%8b%88%e1%8c%8d-2/ | 1 |
| 4 | "አኩኩሉው ፍቅሬ"
ምዕራፍ ሁለት ፦ ክፍል ሶስት
መልሷን ለመስማት ይበልጥ እየጓጓው ከመደገፊያዬ ቀና ብዬ ወደፊት እየተጠጋው እና አይኗን እያየው "እሺ ግን ስለ homosexuality ምን ታስቢያለሽ" አልኳት
"እስኪ አንቺ ምን ታስቢያለሽ ያንቺን ንገሪኝ እና የኔን ስለነሱ ማስበውን ትክክለኛውን ነግርሻለሁ" አለችኝ
ተግባሯ ፣ ቃላቶቿ እና አይኗ ውስጥ መልሱን ያገኘሁት ይመስለኛል በእርግጠኝነት ሌዝቢያን ወይም ባይሴክሽዋል መሆኗን ባልናገርም more than 70% ግን አረጋግጫለሁ ይሄም ከሷ ጋር open ሆኖ ለማውራት ነፃነት ሰቶኛል በዚ ላይ even ሆሞሴክሹዋል ባትሆን እንኳን open minded ስለሆነች ከዚ ከተደናቆረዎ ማህበረሰብ የተለየ እሳቤ እንዳላት እርግጠኛ ነኝ ፤ ዘና ብዬ ለመቀመጥ እየሞከርኩ "አልደግፋቸውም ፣ አልቃወማቸውም" አልኳት ያው እራሴን ላለማጋለጥ እየሞከርኩ ነው
"እንዴት?" አለችኝ
"የሁሉንም ሰው ፍላጎት አከብራለሁ ሴክሹዋሊቲ ደግሞ በተፈጥሮ እንጂ ተገዶ ሚሰጠን ነገር ነው ብዬ አላስብም ግን ደግሞ ይሄንን ሙሉ ለሙሉ አምኜ እንዳልቀበል ምንም እንኳን ሀይማኖተኛ ባልሆን ያደኩበት ሀይማኖቴ እና ማህበረሰቤ ጫና አሳድሮብኛል ቢሆንም ግን አንድ ሰው መቶ ጌ ነኝ ቢለኝ ለዛ ሰው ምንም አይነት የተለየ ጥላቻ አይኖረኝም"
በረጅሙ ተንፍሳ "በጣም ጥሩ እሺ እኔ ሌዝቢያን መሆኔን ብነግርሽ ምን ታደርጊያለሽ?" ብላ ጠየቀችኝ
ልመልስላት ስዘጋጅ አስተናጋጁ ሞሂቶአችንን ይዞ መጣ ፤ አስተካክሎ ካስቀመጠልን በኋላም በመጣበት ተመለሰ ፣ አሁን ግን የሱ አረማመድ እና ውበት አላሳሰበኝም ግን አጠገባችን ቢቆይና የፅኑን ጥያቄ አስቤ ምመልስበት ሰአት ባገኝ ደስ ባለኝ ነበር ግን አልሆነም
"እሺሺ ካቆምንበት እንቀጥል" አለችኝ
እጄን አፌ ላይ አድርጌ እንደማሰብ አልኩና "እኔ አንቺነትሽ እንጂ ሴክሸዋሊትሽ matter አያረግልኝም" ብዬ መለስኩሏት
በመልሴ እረፍት ያገኘች ይመስል በስሱ ተነፈሰች ፤ በአተነፋፈሷ አንዳች ነገር የነገረችኝ መሰለኝ "ይሄ ቆንጆ እይታ ነው" አለችኝ
ፈገግ እያልኩ"አመሰግናለሁ እሺ በይ አሁን ያንቺን እይታ ንገሪኝ" አልኳት
"እኔ እይታ ሳይሆን ኖሬ ያየሁትን እውነታ ነው ምነግርሽ" ሞሂቶዋን ተጎነጨች እና ማውራቷን ቀጠለች "በህይወቴ ውስጥ ጌ ካፕሎች አሉ" ስለተገረምኩ ድምፅ ሳላወጣ "ኦው" አልኩኝ ፣ ፅኑ አይታኝ ስለነበር ቀጠል አድርጋ " አዎ አሉ" አለችኝ "በጣም ነው ምወዳቸው እና ማከብራቸው ፤ ስለ ሆሞሴክሽዋልቲ ትክክለኛነት ከጠየቅሽኝ እኔ ሴት ስለመሆኔ እርግጠኛ የሆነኩትን ያህል ስለነሱ ትክክለኛነት እርግጠኛ ነኝ" አለችኝ
"ግሩም ነው ደስ ይላል" አልኳት እየሳኩ
"ምን ያስቅሻል" አለችኝ ፈገግ እያለች
"እኔ እና አንቺም ሌዝብያን ልንሆን እንደምንችል አስቤ" አልኳት ፤ እውነት ለመናገር ፅኑ "እንዴት?" ብላ እስክትጠይቀኝ ድረስ አስቤበት ያወራሁት ቃል ነበር ፤ ግን እሷ ስጠይቀኝ ምመልሰው ጠፋኝና አፌ ላይ የመጣውን ቃል "ሁለታችንም ጋር ያንን የሚመስል ተሞክሮዎች አሉ" አልኳት
"የምን ተሞክሮ"
"አንቺን ጓደኞችሽ ሌዝብያን ናት ብለው ጠርጥረውሽ ነበር እኔንም ጓደኞቼ ጠርጥረውኝ ነበር" ስላት የምርሽን ነው "አንቺን እንዴት ጠረጠሩሽ"አለችኝ በመገረም
"ኦዎይ የኔ እናት በባዶ ህዴማ ይሄን አልነግርሽም ምሳ እንዘዝ እና እነግርሻለሁ" አልኳት ፤ እውነት ለመናገር በጣም እርቦኝ ስለነበር እና ታሪኩ እረጅም ስለሆነ ነው እንደዛ ያልኳት
"እሺ እንዘዝና ምግቡ እስኪመጣ ትነግሪኛለሽ" ብላ ለአስተናጋጁ እንዲመጣ ምልክት ሰታው ሜኑ እንዲያመጣልን ነግራ መለሰችው እሱም ደቂቃ ሳይቆይ ሜኑ ይዞ መጣና ሁለታችንም ምንፈልገውን ለማዘዝ የምግብ ሜኑአችን ላይ ተተከልን ፤ ምግባችንን አዘን ፅኑ እንዳለችው ምግቡ እስኪመጣ የግቢ የመጀመሪያ አመት ተማሪ ሆኜ ሳለ ከአንዷ ቆንጅዬ እንስት ጋር ስለተወራብን ወሬ ማውራቴን ቀጠልን።(ይሄንን ታሪክ ማወቅ ከፈለጋቹ ከዚህ በፊት የፃፍኩትን "የህልሜ ንግስት" የተሰኘውን ኢ-ልቦለድ ማንበብ ትችላላቹ)
ምሳችንን በልተን ፣ ቡናችንን ጠጥተን ፣ የልብ የልባችንን አውግተን ከዛ ሬስቶራንት ስንወጣ 10 ሰአት ሆኖ ነበር የመሸኛኛ እንዲሆነን Ice cream ልጋብዝሽ ብያት አንድ ማውቀው ቆንጆ Ice cream ቤት ስላለ እኔ መንገዱን እየጠቆምኳት መሪውን እሷ እየነዳች ጉዞአችንን ቀጠልን።
ከፅኑ ጋር ወሬ አያልቅብንም ብዙ ሼር ምናረጋቸው ሀሳቦች አሉን ፤ አንዱን ርዕስ ስንጥል ሌላ እናነሳለን ፤ ፅኑ ማንበብ ምትወድ ሰው ነች ስለ አንድ ነገር ጠይቄያት አስር መልሶችን ትሰጠኛለች ፤ እኔ ማውቃቸውም ነገሮች ሲኖሩ እንወያያለን በመሀል የሀሳብ መለያየቶች ይነሱ እና ክርክር እንጀምራለን ግን ሁሉንም በሚባል ደረጃ የእሷ ሀሳብ ሚዛን ይደፋብኝና ላለመሸነፍ ስል "ይሁንልሽ" እላታለሁ ፅኑም ይሄኛው ፀባዬ ገባት መሰለኝ "እሺ" ወይም "በደንብ አስቢበት" ብላኝ ትታው ወደሌላ ርዕስ እንሄዳለን።
አንድ ሰአት ሊሆን አከባቢ ግቢ በር ላይ አድርሳኝ እዛው መኪና ውስጥ ዝም ተባብለን ቁጭ አልን፤ መለያየት የፈለግን አይመስልም እኔም ወርጄ መሄድ አልፈለኩም እሷም ጥላኝ መሄዱን የፈለገች አይመስልም ዝምታውን ለመስበር ስል "ስለነበረን ግዜ አመሰግናለሁ ቆንጆ ቀን ነበር" አልኳት
"እኔም አመሰግናለሁ ፤ ባንለያይ ደግሞ በጣም ቆንጆ ይሆን ነበር" አለችኝ እየሳቀች
እኔም እየሳኩኝ "እና ይዘሽኝ ትጠፊ?" አልኳት
"ቢፈቀድልኝማ ደስ ይለኝ ነበር"
"የኔ እናት አንቺ ከሰሙሽ ብዙ ታወሪያለሽ ደህና እደሪልኝ" ብያት ጉንጯን ስሜ ላቅፋት ስጠጋ እሷም ወደኔ ስትዞር ከንፈሯን ሳምኩት...
ይቀጥላል....
✍ አቢጌል
#ሰላምእናነፃነትለሁሉም | 87 |
| 5 | "አኩኩሉው ፍቅሬ"
ምዕራፍ ሁለት ፦ ክፍል ሶስት
መልሷን ለመስማት ይበልጥ እየጓጓው ከመደገፊያዬ ቀና ብዬ ወደፊት እየተጠጋው እና አይኗን እያየው "እሺ ግን ስለ homosexuality ምን ታስቢያለሽ" አልኳት
"እስኪ አንቺ ምን ታስቢያለሽ ያንቺን ንገሪኝ እና የኔን ስለነሱ ማስበውን ትክክለኛውን ነግርሻለሁ" አለችኝ
ተግባሯ ፣ ቃላቶቿ እና አይኗ ውስጥ መልሱን ያገኘሁት ይመስለኛል በእርግጠኝነት ሌዝቢያን ወይም ባይሴክሽዋል መሆኗን ባልናገርም more than 70% ግን አረጋግጫለሁ ይሄም ከሷ ጋር open ሆኖ ለማውራት ነፃነት ሰቶኛል በዚ ላይ even ሆሞሴክሹዋል ባትሆን እንኳን open minded ስለሆነች ከዚ ከተደናቆረዎ ማህበረሰብ የተለየ እሳቤ እንዳላት እርግጠኛ ነኝ ፤ ዘና ብዬ ለመቀመጥ እየሞከርኩ "አልደግፋቸውም ፣ አልቃወማቸውም" አልኳት ያው እራሴን ላለማጋለጥ እየሞከርኩ ነው
"እንዴት?" አለችኝ
"የሁሉንም ሰው ፍላጎት አከብራለሁ ሴክሹዋሊቲ ደግሞ በተፈጥሮ እንጂ ተገዶ ሚሰጠን ነገር ነው ብዬ አላስብም ግን ደግሞ ይሄንን ሙሉ ለሙሉ አምኜ እንዳልቀበል ምንም እንኳን ሀይማኖተኛ ባልሆን ያደኩበት ሀይማኖቴ እና ማህበረሰቤ ጫና አሳድሮብኛል ቢሆንም ግን አንድ ሰው መቶ ጌ ነኝ ቢለኝ ለዛ ሰው ምንም አይነት የተለየ ጥላቻ አይኖረኝም"
በረጅሙ ተንፍሳ "በጣም ጥሩ እሺ እኔ ሌዝቢያን መሆኔን ብነግርሽ ምን ታደርጊያለሽ?" ብላ ጠየቀችኝ
ልመልስላት ስዘጋጅ አስተናጋጁ ሞሂቶአችንን ይዞ መጣ ፤ አስተካክሎ ካስቀመጠልን በኋላም በመጣበት ተመለሰ ፣ አሁን ግን የሱ አረማመድ እና ውበት አላሳሰበኝም ግን አጠገባችን ቢቆይና የፅኑን ጥያቄ አስቤ ምመልስበት ሰአት ባገኝ ደስ ባለኝ ነበር ግን አልሆነም
"እሺሺ ካቆምንበት እንቀጥል" አለችኝ
እጄን አፌ ላይ አድርጌ እንደማሰብ አልኩና "እኔ አንቺነትሽ እንጂ ሴክሸዋሊትሽ matter አያረግልኝም" ብዬ መለስኩሏት
በመልሴ እረፍት ያገኘች ይመስል በስሱ ተነፈሰች ፤ በአተነፋፈሷ አንዳች ነገር የነገረችኝ መሰለኝ "ይሄ ቆንጆ እይታ ነው" አለችኝ
ፈገግ እያልኩ"አመሰግናለሁ እሺ በይ አሁን ያንቺን እይታ ንገሪኝ" አልኳት
"እኔ እይታ ሳይሆን ኖሬ ያየሁትን እውነታ ነው ምነግርሽ" ሞሂቶዋን ተጎነጨች እና ማውራቷን ቀጠለች "በህይወቴ ውስጥ ጌ ካፕሎች አሉ" ስለተገረምኩ ድምፅ ሳላወጣ "ኦው" አልኩኝ ፣ ፅኑ አይታኝ ስለነበር ቀጠል አድርጋ " አዎ አሉ" አለችኝ "በጣም ነው ምወዳቸው እና ማከብራቸው ፤ ስለ ሆሞሴክሽዋልቲ ትክክለኛነት ከጠየቅሽኝ እኔ ሴት ስለመሆኔ እርግጠኛ የሆነኩትን ያህል ስለነሱ ትክክለኛነት እርግጠኛ ነኝ" አለችኝ
"ግሩም ነው ደስ ይላል" አልኳት እየሳኩ
"ምን ያስቅሻል" አለችኝ ፈገግ እያለች
"እኔ እና አንቺም ሌዝብያን ልንሆን እንደምንችል አስቤ" አልኳት ፤ እውነት ለመናገር ፅኑ "እንዴት?" ብላ እስክትጠይቀኝ ድረስ አስቤበት ያወራሁት ቃል ነበር ፤ ግን እሷ ስጠይቀኝ ምመልሰው ጠፋኝና አፌ ላይ የመጣውን ቃል "ሁለታችንም ጋር ያንን የሚመስል ተሞክሮዎች አሉ" አልኳት
"የምን ተሞክሮ"
"አንቺን ጓደኞችሽ ሌዝብያን ናት ብለው ጠርጥረውሽ ነበር እኔንም ጓደኞቼ ጠርጥረውኝ ነበር" ስላት የምርሽን ነው "አንቺን እንዴት ጠረጠሩሽ"አለችኝ በመገረም
"ኦዎይ የኔ እናት በባዶ ህዴማ ይሄን አልነግርሽም ምሳ እንዘዝ እና እነግርሻለሁ" አልኳት ፤ እውነት ለመናገር በጣም እርቦኝ ስለነበር እና ታሪኩ እረጅም ስለሆነ ነው እንደዛ ያልኳት
"እሺ እንዘዝና ምግቡ እስኪመጣ ትነግሪኛለሽ" ብላ ለአስተናጋጁ እንዲመጣ ምልክት ሰታው ሜኑ እንዲያመጣልን ነግራ መለሰችው እሱም ደቂቃ ሳይቆይ ሜኑ ይዞ መጣና ሁለታችንም ምንፈልገውን ለማዘዝ የምግብ ሜኑአችን ላይ ተተከልን ፤ ምግባችንን አዘን ፅኑ እንዳለችው ምግቡ እስኪመጣ የግቢ የመጀመሪያ አመት ተማሪ ሆኜ ሳለ ከአንዷ ቆንጅዬ እንስት ጋር ስለተወራብን ወሬ ማውራቴን ቀጠልን።(ይሄንን ታሪክ ማወቅ ከፈለጋቹ ከዚህ በፊት የፃፍኩትን "የህልሜ ንግስት" የተሰኘውን ኢ-ልቦለድ ማንበብ ትችላላቹ)
ምሳችንን በልተን ፣ ቡናችንን ጠጥተን ፣ የልብ የልባችንን አውግተን ከዛ ሬስቶራንት ስንወጣ 10 ሰአት ሆኖ ነበር የመሸኛኛ እንዲሆነን Ice cream ልጋብዝሽ ብያት አንድ ማውቀው ቆንጆ Ice cream ቤት ስላለ እኔ መንገዱን እየጠቆምኳት መሪውን እሷ እየነዳች ጉዞአችንን ቀጠልን።
ከፅኑ ጋር ወሬ አያልቅብንም ብዙ ሼር ምናረጋቸው ሀሳቦች አሉን ፤ አንዱን ርዕስ ስንጥል ሌላ እናነሳለን ፤ ፅኑ ማንበብ ምትወድ ሰው ነች ስለ አንድ ነገር ጠይቄያት አስር መልሶችን ትሰጠኛለች ፤ እኔ ማውቃቸውም ነገሮች ሲኖሩ እንወያያለን በመሀል የሀሳብ መለያየቶች ይነሱ እና ክርክር እንጀምራለን ግን ሁሉንም በሚባል ደረጃ የእሷ ሀሳብ ሚዛን ይደፋብኝና ላለመሸነፍ ስል "ይሁንልሽ" እላታለሁ ፅኑም ይሄኛው ፀባዬ ገባት መሰለኝ "እሺ" ወይም "በደንብ አስቢበት" ብላኝ ትታው ወደሌላ ርዕስ እንሄዳለን።
አንድ ሰአት ሊሆን አከባቢ ግቢ በር ላይ አድርሳኝ እዛው መኪና ውስጥ ዝም ተባብለን ቁጭ አልን፤ መለያየት የፈለግን አይመስልም እኔም ወርጄ መሄድ አልፈለኩም እሷም ጥላኝ መሄዱን የፈለገች አይመስልም ዝምታውን ለመስበር ስል "ስለነበረን ግዜ አመሰግናለሁ ቆንጆ ቀን ነበር" አልኳት
"እኔም አመሰግናለሁ ፤ ባንለያይ ደግሞ በጣም ቆንጆ ይሆን ነበር" አለችኝ እየሳቀች
እኔም እየሰመኩኝ "እና ይዘሽኝ ትጠፊ?" አልኳት
"ቢፈቀድልኝማ ደስ ይለኝ ነበር"
"የኔ እናት አንቺ ከሰሙሽ ብዙ ታወሪያለሽ ደህና እደሪልኝ" ብያት ጉንጯን ስሜ ላቅፋት ስጠጋ እሷም ወደኔ ስትዞር ከንፈሯን ሳምኩት...
ይቀጥላል....
✍ አቢጌል | 3 |
| 6 | Today marks World Refugee Day! QE is proud to launch a special edition celebrating the Queer Ethiopian refugee community while raising awareness about their experiences.
https://queerethiopia.com/between-borders-and-identity/ | 93 |
| 7 | "አኩኩሉው ፍቅሬ"
ምዕራፍ ሁለት ፦ ክፍል ሁለት
ፅኑ "ተጫወቺ እንጂ" ብላ መኪናውን በአንድ እጇ እየነዳች በሌላኛው እጇ እጆቼን ያዘቻቸው ፤ የምይዝ የምጨብጠው ነበር የጠፋኝ ልቤ እኔን ጥላ በአፌ የወጣችም መሰለኝ
እንደምንም እያማጥኩ እና እጆቿን እኔም መልሼ እየያዝኳቸው "እየተጫወትኩ ነው አንቺ ዝም አልሽ እንጂ" አልኳት
"እኔማ መኪና እየነዳው ስለሆነ ነው"
"እና መኪና ምትነጂው በእጅሽ እንጂ በአፍሽ ነው እንዴ" አልኳት እየሳኩ
"እጄን ስትይዥው በምላሴም መንዳት ጀመርኩ መሰለኝ" አለችኝ ፈገግ እያለች
ለካ የእጇ ልስላሴ ማርኮኝ እጆቿን እንደያዝኳቸው በዛው ቀርቻለው
"ኦው ለካ እጅሽን ይዤዋለሁ" ብያት ለቀኳት
"ብትይዣቸውም አይደብረኝም ነበር" አለችኝ አይኗን እያስለመለመች እያየችኝ
"እኔም ደስ ይለኝ ነበር ግን ያንን ጋወን ለብሼ ሳልመረቅ መገልበጥ አልፈልግም" አልኳት እየሳኩ
"አታስቢ ደርሰናል" ብላኝ ከአንድ ተለቅ ካለ ሬስቶራንት በራፍ መኪናዋን አቆመች
"ኦው ዝም ያለ እና ደስ የሚል ቦታ ይመስላል" አልኳት ወደውጭ አንጋጥቼ እየተንጠራራው እያየው
"አዎ ትወጂዋለሽ በጣም በይ ነይ ውረጂ" ብላኝ ወረድን
ስራመድ ብዙ ጊዜ እንደማደርገው እጄን ኪሴ ውስጥ ከትቼ ከመኪናው ቦርሳዋን ይዛ እስከምትወርድ ጠበኳት እና ስትመጣ በአንዱ እጄ ቦርሳዋን ልቀበላት እጄን ስዘረጋላት በሚያሳዝን እና ደስ ባለው ፊት "Ow u r so sweet" ስትለኝ እኔም ይሄ ጉራዬ አለቀቀኝም እና እየሳኩኝ "I know" ስላት "ጉረኛ" ብላኝ እጆቿን ኪሴ ውስጥ ካኖርኩት እጄ ጋር እያቆላለፈች ወደ ሬስቶራንቱ ለመግባት መራመድ ጀመርን
ፅኑ እረዘም ያለች ብትሆንም ከኔ በቁመት ማነሷ እና ምንም እንከን ማይወጣላት Fem ሴት መሆኗ ከኔ Soft masculinity energy ጋር ተዋህደው የሆነ ለየት ያለ Chemistry ፈጥረው ግርማ ሞገስ የሰጡን ይመስላል ፤ እውነቱን ለመናገር ሁለት ሴቶች እንደፈለጉት ቢቀራረቡ ትኩረት የመሳብ እድላቸው በጣም አነስተኛ ነው በተለይ ከወንዶች አንፃር እጅግ ትልቅ ነፃነት አለን
ወደ ውስጥ ስንገባ ሬስቶራንቱ ከውጭ እንደሚታየው ውስጡም እጅግ ዝም ያለ እና የተዋበ ነው ፤ የተቀባው ነጭ ቀለምም ለቤቱ ብርሀንን ሰቶት ያፈካው ይመስላል ፤ ተቀምጠን ስለ ቤቱ ውበት እያወጋን ሳለን
"እንኳን ደህና መጣቹ ፤ ምን ልታዘዝ!?" በሚል ድምፅ እና ደስ በሚል ፈገግታ የሱፍ ሰደርያ በነጭ ሸሚዝ የለበሰ ቆንጅዬ አስተናጋጅ እጆቹን ወደኋላ አጣምሮ ከወገቡ ጎንበስ ብሎ ተቀበለን ፤ አቤት ውበት! ውበት ያለው እኮ አስተናጋጆች ጋር ነው ከሴቱ ቢባል ከወንዱ አብዛኞቹ ቆንጆ ናቸው ፤ እኔም በልቤ "አሁን ምን አለበት ይሄ ሸበላ ጌ ቢሆንና ከሮቢ ጋር ባጋባው" ብዬ አሰብኩ(ብዙ ጊዜ ቆንጆ ወንድ ሳይ በአይምሮዬ ሚመጣ ሀሳብ ነው 😁)።
ፅኑም "እንኳን ደህና ቆየኸን ለኔ ሌመን ሞሂቶ አምጣልኝ እና ምንበላውን ደግሞ አስበን እንነግርሀለን" አለችው በፈገግታ ታጅባ
"እሺ ፤ ላንቺስ ምን ይምጣልሽ" ብሎ የቅድሙ ፈገግታው ሳይደበዝዝ ወደኔ ዞረ
እውውይ የኔ ሸበላ ውበቱ ከቅድሙ እጅግ ጎልቶ ታየኝ ፤ ቀይ ወንዶች ደካማ ጎኔ ናቸው በጣም ይስቡኛል ይሄም ልጅ ቅላቱ ከውበቱ ጋር ተዳምሮ ማርኮኛል "እምም ለኔ ደግሞ ክላሲክ ሞሂቶ አምጣልኝ"
በፈገግታ ታጅቦ "እሺ" ብሎን ሄደ
ልክ ልጁ እንደተራመደ "እንዴት አባቱ ነው ሚያምረው በጌታ!" አልኳት ለፅኑ የልጁ አረማመድ ላይ እያፈጠትኩ
"አዎ በጣም ቆንጅዬ ግን እኔ ብዙም የወንድ ልጅ ውበት አድናቂ አይደለሁም" አለችኝ ፈገግ እያለች
"የሴቶችስ" አልኳት እየሳኩ
የመገረም እና የአድናቆት ፊት እያሳየችኝ "እንዴዴ የነሱንማ ውበት አለማድነቅ አልችልም ፤ ባይሆን አንቺ የወንድ ልጅ ውበት በዚ ልክ ማድነቅሽ ገርሞኛል" አለችኝ
"እኔ ቆንጆ ፍጥረታትን በሙሉ ማደንቅ ሰው ነኝ ግኔ ለምን ገረመሽ?"ብላት
ትከሻዋን ሰበቅ እያረገች "እኔንጃ" አለችኝ
"ባይሆን ከኔ ይልቅ ያንቺ ከወንድ ልጅ በላይ የሴትን ልጅ ውበት ማድነቅ ገርሞኛል"
"በኔ አምሳል የተፈጠሩ ፍጡሮችን ውበት ማድነቄ ለምን ይገርምሻል" አለችኝ አይኔን ትኩር ብላ እያየች ፤ በርግጥ ሴት ልጅ እውነትም በሷ ሀምሳል የተሰራች ነው ሚመስለው I mean she is so gorgeous
"ምን አልባት በማህበረሰብ ስላልተለመደ" አልኳት ወደ ኋላ ለጠጥ ብዬ ወንበሩን እየተደገፍኩ
"ልክ ነሽ ግን እኔ ችግሩ አይታየኝም ፤ እንደውም ብዙ ጊዜ የሴትን ውበት አብዝቼ ከማድነቄ የተነሳ ጓደኞቼ የሆነ ጊዜ ላይ ሌዝብያን ነሽ እንዴ ብለው ጠይቀውኛል" ብላ ሳቀች ፤ እኔም አብሬያት ሳኩኝ
"እና ነሽ እንዴ!?" አልኳት እኔም ፈገግ እያልኩ እና መልሷን ለመስማት እየጓጓው
"እመስላለው!?" ብላ ጥያቄዬን በጥያቄ መለሰችልኝ
"እኔንጃ ያው Sexual orientationን በማየት ብቻ መለየት አይቻልም" አልኳት
"እሱስ ልክ ነሽ ግን አይደለሁም" አለችኝ
መልሷን ለመስማት ይበልጥ እየጓጓው ከመደገፊያዬ ቀና ብዬ ወደፊት እየተጠጋው እና አይኗን እያየው "እሺ ግን ስለ homosexuality ምን ታስቢያለሽ" አልኳት
እሷም በአትኩሮት አይን አይኔን እያየች ወደፊት ጠጋ ብላ...
ይቀጥላል...
✍ አቢጌል | 145 |
| 8 | በኢትዮጵያ ውስጥ የሥርዓተ-ፆታ ልዩነት፡ ይህ ትክክለኛ ቅርስ ነው እንጂ ከውጭ የመጣ አይደለም
ክፍል ሰባት፡ የኤርትራ "ዲያቮሌቲ (Diavoletti)"
ይህ ጽሑፍ ወደ ኢትዮጵያ ጥልቅ የሥርዓተ-ፆታ ልዩነት ታሪክ ጉዞአችንን ይቀጥላል። ቀደም ሲል አሽቲሜን፣ ኡራኒንን፣ እንዲሁም ዋንደርወራድን አይተናል። አሁን ደግሞ ወደ ኤርትራ እየተጓዝን ነው፤ በ1900ዎቹ መጀመሪያ ላይ የተገኙ መረጃዎች ሌላ ብርቅዬ የሥርዓተ-ፆታ ልዩነት ያሳያሉ። እነርሱም "ዲያቮሌቲ" ተብለው ይጠሩ ነበር—ከሰፋሪ ወንዶች ጋር ግንኙነት የሚፈጥሩ ወጣት ወንዶች—በጣሊያናዊው ተመራማሪ ፓኦሎ አምብሮጌቲ (Paolo Ambrogetti) በ1900ዎቹ ውስጥ ተመዝግበዋል። ይህም የሥርዓተ-ፆታ ልዩነት ከውጭ የመጣ ወይም አዲስ ሳይሆን፣ የአፍሪካ ማኅበራዊ አደረጃጀት አካል እንደነበር ያረጋግጣል።
"ዲያቮሌቲ" እነማን ነበሩ?
አምብሮጌቲ በወቅቱ ዲያቮሌቲዎች በኤርትራ ማኅበረሰብ ውስጥ ልዩ ሚና የነበራቸው ወጣት ወንዶች እንደነበሩ ተመልክቷል። አብዛኞቹ በጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ፣ ከትልልቅ ወንዶች ጋር ግንኙነት የነበራቸው እና ይህም በአካባቢው መደበኛ ነበር። ግንኙነታቸው የተደበቀ አልነበረም፣ ምክንያቱም በቤተሰብ ዕውቅና ሥር ይካሄድ ነበር።
መልክአቸው እንደ አሽቲሜ ወይም ዋንደርወራድ የተለየ አልነበረም፤ በዚያን ጊዜ እንደማንኛውም ወጣት ወንዶች ይመስሉ ነበር—በአለባበሳቸው ወይም በመልካቸው እነርሱን ለይቶ ማወቅ አይቻልም ነበር።
"አሳዳጊዎች" (Patrons) በመባል የሚታወቁት ትልልቅ ወንዶች በአብዛኛው የጓደኝነት ምትክ ለ"ዲያቮሌቲ"ዎች እርዳታ ያደርጉ ነበር። አብዛኞቹ "ዲያቮሌቲዎች" እያደጉ ሲሄዱ ከአሳዳጊዎቻቸው ጋር የነበራቸውን ግንኙነት አቁመው ወደ ቀጥተኛ ትዳር ይገቡ ነበር። ሆኖም፣ ጥቂቶች በእድሜያቸው እየገፉ ሲሄዱም ግንኙነታቸውን ቀጥለዋል፤ ይህም ትስስሩ ከጥቅም ግንኙነት የላቀ፣ ስሜታዊ ጎንም እንደነበረው ያሳያል። አምብሮጌቲ 25 ዓመት የሆነ፣ ያገባ ቢሆንም ከአሳዳጊው ጋር ግንኙነቱን የቀጠለ አንድ "ዲያቮሌቲ" መኖሩን ጠቅሷል። ይህ የሚያሳየው አንዳንድ ግንኙነቶች ሁልጊዜ ጥቅማጥቅም ብቻ ሳይሆኑ፣ ስሜታዊ ትስስርም ይዘው እንደነበር ነው።
እንዴት ጠፉ?
ስለ አሽቲሜ፣ ኡራኒን እና ዋንደርወራድ ካጠናሁት በመነሳት—"ዲያቮሌቲዎች" የጠፉት በተደባለቀ ምክንያቶች እንደሆነ አምናለሁ።
· የማኅበራዊ ደንቦች ጥብቅነት: ማኅበረሰቡ ወንድ ወይም ሴት መሆን ምን ማለት ነው በሚለው ሐሳብ ላይ ይበልጥ ጥብቅ የሆኑ አመለካከቶችን መከተል ጀመረ። የተለየ መሆን አስቸጋሪ እና ተቀባይነት የሌለው ሆነ።
· የቤተሰብ ግፊት: ቤተሰቦች ወንዶቹን እንደ ጋብቻ እና መደበኛ ሥራ ባሉ "መደበኛ" በሚባሉ መንገዶች እንዲሄዱ ገፋፏቸው። ይህ ደግሞ ሕይወታቸውን ይበልጥ የግል እንዲሆን ያደረገ ሲሆን፣ ታሪኮቻቸው የመቀጠል ዕድል አነሰ።
· የመረጃ እጥረት: በመጨረሻም፣ ማንም ሰው ስለእነርሱ መጻፍ ባለመቀጠሉ፣ እንደሌሎች ቡድኖች ሁሉ ታሪካቸው ተረሳ።
መጥፋታቸው "ከተፈጥሮ ውጭ" ስለነበሩ አይደለም። የሆነው ማኅበረሰቡ ስለተለወጠ እና በግልጽ ለመኖር የሚያስችል ቦታ ስላልሰጣቸው ነው።
ልናውቀው የሚገባ ቅርስ
የ"ዲያቮሌቲ" ታሪክ አፍሪካ የሥርዓተ-ፆታ ልዩነትን እንደ እንግዳ ነገር ፈጽሞ አትመለከትም እንደነበር ያረጋግጣል። ይልቁንም "መደበኛ"፣ ተቀባይነት ያለው እና የሚከበር ነበር። "ዲያቮሌቲ"ን ማስታወስ ልዩነት የአፍሪካ ባህል ጥልቅና ትክክለኛ ክፍል እንደሆነ ያስታውሰናል፣ ከውጭ የመጣ ነገር አይደለም።
Gloria Victor
June 2026 | 151 |
| 9 | https://open.substack.com/pub/climaxlgbtq/p/the-climax-douching-guide?utm_source=share&utm_medium=android&r=4utnvb | 181 |
| 10 | "አኩኩሉው ፍቅሬ"
ምዕራፍ ሁለት ፦ ክፍል አንድ
ፀሀይዋ ከነ ዘር ማንዘሯ የወጣች ይመስላል ፣ አናቴ ላይ ወታ በቃጠሎ እየጨፈረችብኝ ነው «የማያውቁት ሀገር አይናፍቅም» ብዬ ሊዮራን ትቼ መሄዴ ልቤን ቅር ቢያሰኘውም መንገዴን ወደ ፅናት አዙሬ እየተጓዝኩ ነው።
ስልኬን በእጄ እንደያዝኩት ይነዝረኝ ጀመር ፣ ፅኑ እየደወለች ነው
"ሄሎ ፅኑዬ"
"ወዬ አቢጉ ቆየሽ እኮ"
"ይቅርታ የተከበሩ እየመጣው ነው ደርሻለው"
"እሺ ቶሎ በያ"
"ይኸው ደርሻለው በራፋ ጋር ነኝ ፣ የቱ ጋር ነሽ"
"በራፉ ጋር ስትደርሺ አይሻለሁ"
"ደርሻለሁ ብዬ መዋሸት እንኳን አልቻልኩምኮ" አልኳት እየሳኩ
"ሲጀምር ውሸት እንደማልወድ እያወቅሽ ለምን ትዋሺኛለሽ" ድምጿ ሲቀየርብኝ ታወቀኝ ፣ ውሸትን አምርራ ነው ምትጠላው በርግጥ እኔም ውሸት አልወድም ግን ብዙ ጊዜ አርፋጅ ስለሆነኩ እዚ ደርሻለሁ እያልኩ መዋሸቱን ተላምጄዋለሁ
"እሺ በቃ አትኮሳተሪ ፣ ማርያምን አሁን በራፉ ጋር ነኝ"
"ምንድ ነው የለበሽው?"
"ነጭ ቲሸርት በቡኒ ሸሚዝ እና ሰማያዊ ጂንስ ሱሪ"
"አየሁሽ አዎ ፣ ከፊት ለፊትሽ ቀይ Swift መኪና አትታይሽም?"
"ትታየኛለች"
"በቃ አስፓልቱን ተሻግረሽ ወደ መኪናዋ ነይ"
በመኪና እንዳልገጭ ብዬ ግራ ቀኜን አይቼ አስፓልቱን በጥድፊያ ተሻግሬ ወደተባልኩት መኪና አቀናው ፣ መኪናዋ ጋር ስደርስ ፅኑ ከውስጥ ወርዳ ለረጅም አመት ሳይገናኙ እንደቆዩ እህትማማቾች ተቃቅፈን ሰላም ተባባልን ፤ እውነት ለመናገር ገና ሳቅፋት ነው ልቤ እርግት ብሎ ሰላሙን ያገኘው በቃ እቅፏ ማላውቀውን እረፍት ሰቶኝ ነበር እንደዛው ብንቀር ምኞቴም ነበር ግን መላቀቃችን ግድ ሆነና ተላቀቅን
"አንቺ አርፋጅ" አለችኝ እየፈገገች
"አርፋጅ መሆኔን እኮ ባለፈው ስናወራ ነግሬሻለሁ"
"ደሞኮ አታፍሪም ታወሪያለሻ" አለችኝ አይን አይኔን እያየች
"እውነታው እኮ ነው ባይሆን አንቺን የመሰለች ቆንጆ ብቻሽን ስላስጠበኩሽ ይቅርታ"
"ምንም አይደለም ለቅጣት ግን ተዘጋጂ"
"ንግስት ሆይ ሺ ቅጣት ቢቀጡኝ ለመቀጣት ዝግጁ ነኝ" አልኳት ፈገግ እያልኩ ፣ በውስጤ ግን ምናለበት ቅጣቱ ፊት ለፊቴ እራቁትሽን ቁሚ ወይ ከንፈሬን ሳሚኝ በሆነ ብዬ እየተመኘው ነው
"ባንዳፍ ፣ ነይ ግቢ አሁን በዚ በፀሀይ አንቃጠል" ብላኝ ወደ መኪናዋ ጠቆመችኝ
እኔም በመገረም "ያንቺ መኪና ነው እንዴ!?" ብዬ ጠየኳት
"አዎ"
"ኦው እና ባለፈው ያለአቅሜ ነዋ ካልከፈልኩ ብዬ ስታገል የነበረው"
እየሳቀች "እኔ ግን አልከፋኝም ይኸው በዛ ምክንያት ድጋሜ ልጋብዝሽ ተገናኘን"አለችኝ
"እኔ ግን ባንገባበዝም አንቺን ሁሌም ባገኝሽ ደስ ይለኛል"
"እኔስ መች ጠልቼው" ብላኝ ወደ መኪናዋ ገባን
ከፅኑ ጋር ኢነርጂያችን በጣም ተስማምቷል ፣ ምን እንደነካኝ ባላውቅም ከሷ ጋር በጣም ግልፅ እየሆንኩ ነው ፣ ሳሽኮረምማት እራሱ በነፃነት ነው በእርግጥ እሷም ትሽኮረመምልኝና መልሳ ታሽኮረምመኛለች ፤ በመሀላችን አንዳች ልዩ ነገር እየተፈጠረ እንዳለም እየተሰማኝ ነው። ውስጤ ሌዝቢያን እንደሆነች እየነገረኝ ሲሆን ተግባሯ ፣ አነጋገሯ እና አስተያየቷ ደግሞ እየመሰከሩልኝ ነው ።
"እና ቆይ ደግሞ ባለመኪና ሆነሽ ስለምን ታክሲ መጠቀምን መረጥሽ?"
"ሰሞኑን የመንዳት ሙድ ላይ አልነበርኩም ፣ አንዳንዴ መንዳት ያስጠላኛል" አለችኝ እየተንዘፈዘፈች እና እየተንገሸገሸች ፤ ለጉራ አልነበረም ያለችኝ እውነትም መንዳት ያስጠላት ትመስላለች
"አቤት አቤት ልዩነታችንን አየሽልኝ አ ፣ አንቺ መንዳት ያስጠላሻል እኔ ደግሞ ብነዳ ብዬ ሁሌ እመኛለሁ" አልኳት ከንፈሬን እየመጠጥኩ ፣ እውነት ለመናገር ወደፊት የምወዳትን ላንድክሩዘሬን እንደምነዳ ስለማውቅ አሁን ላይ ብዙም አልጓጓም ግን መኪና በጣም ነው ምወደው
"እና ምን ችግር አለው ትነጃለሻ" አለችኝ ትከሻዋን እየሰበቀች
"በደስታ ነዋ" አልኳት እኔም እየሳኩ
"በቃ ከሰሞኑ አንድ ቀን አለማምድሻለሁ ከዛን እኔ ሲደብረኝ አንቺ ትነጂልኛለሽ"
"መንጃ ፍቃዱስ?"
"ውስጥ ውስጡን አንቺ አስፓልት አስፓልቱን እኔ" ብላኝ ተሳሳቅን
"የት ነው ግን ምንሄደው" ጠየኳት
"ምነው እንዳላግድሽ ፈራሽ እንዴ"
"አንቺን በመሰለች ቆንጆ መታገድኮ መመረቅ ነው ፣ እንደውም ካገድሽኝ የቅም ቅም አያቶቼ ምርቃት ለኔ እንደሰራ ነው ምቆጥረው" ስላት ከትከት ብላ ሳቀች
"አቤት አቤት ምላሳም! እኔ እንደውም ሳስበው የቅም ቅም አያቶችሽን ምላስ በሙሉ የወሰድሽው ነው ሚመስለኝ"
"ቆንጆ ቆንጆዎችን በቃላቶቼ ለማስደሰት እና ለመሳም ከሆነ አይደብረኝም"
"እና እኔስ አይደርሰኝም" አለችኝ አይኔን እያየች ፣ አስተያየቷ የሆነ ነገር ከፊቴ ምታነብ ይመስላል
"ላንቺማ ምላሴን ብቻ ሳይሆን ልቤንም ነው ምሰጥሽ" ብዬ ስመልስላት ሁለታችንም በዝምታ ተዋጥን ፤ እኔ እንኳን ዝም ያልኩት ከአፌ አምልጦኝ በወጣው ቃል ነው ፣ አፍ አውጥቼ ልሳምሽ ማለት እኮ ነው የቀረኝ እሷስ ግን ለምን ዝም አለች!? አስደብሬያት ይሆን? ልጠይቃት ወይስ ዝም ልበል እያልኩ ከራሴ ጋር ስጣላ "ተጫወቺ እንጂ" ብላኝ መኪናውን በአንድ እጇ እየነዳች በሌላኛው እጇ እጆቼን ያዘቻቸው ፤ የምይዝ የምጨብጠው ነበር የጠፋኝ ልቤ እኔን ጥላ በአፌ የወጣችም መሰለኝ
ይቀጥላል...
ለታሪኩ አዲስ ከሆናቹ ምዕራፍ አንድን ማንበብ እንዳትረሱ! አመሰግናለሁ 🙏
✍ አቢጌል ነኝ | 200 |
| 11 | #ምልስት
These are the days I saw him... the man I will never date!
ለመጀመሪያ ጊዜ ያየውት ከጽንኤል ጋር ሻይ ቡና ብለን ስንወጣ ነበር. I thought we had a moment when we stared at each other. ሲያየኝ ድንገጥ ያለ ይመስላል እኔም ሳየው ብደነግጥም ላላማስነቃት ሞክሪያለው ኮፍያ አድርጎ ነበር የሆነ ሰማያዊ ነገር ያለበት የስፖርት ጃኬት አድርጎ ነበር ጽኒ" wow" እንዳለ አስታውሳለሁ ያው መልሶ ቢክደውም የሆነ ሳየው የተሰማኝ ነገር ነበር።
በሳምንቱ ጽንኤል ስለ ልጁ ረስቷል እኔ ግን አልረሳውም ነበር የሆነ ሰው መንገድ ላይ ከማረከኝ ከአዕምሮዬ አይጠፋም ሴሰኝነት ይሁን አይሁን አላቅም ምክንያቱም ካየዋቸው እና ከተመቹኝ ጋር ስለ ሩካቤ አስቤ አላቅም, but what if we had something real with someone I admire and am passionate about? የሚል ጥማት እንጂ ስለዚ ያየውትን እና ውስጤ የገባን ሰው አልረሳም ለነገሩ ሰው ጭራሽ አልረሳም ስምም እንደዛው አሁን ሳረጅ እንደሰነፍኩት አይደለም ልቤ እነሱ ጋራ የለም ለዛ ይሆናል እኔነቴ ከጠፋ ቆይቻለሁ።
ይህን ሰው ሁለተኛ ጊዜ ያየውት ቀኑን አላስታሳውስም ወይ ምን አድርጌ ከየት እየተመለስኩ እንደነበር አላቅም 81 ባጃጅ ውስጥ ተቿክዬ ገባው መሽቶ ነበር ጠጋ ብዬ ሌላ ሰው እስኪገባ ስጠብቅ በተቀመጥኩበት ባጃጅ በኩል አንድ ሰው አለፈ ጠረኑ ደስ ይላል ወዲያው አወኩት እሱ ነበር ከላይ ወይንጠጅ የሚመስል ሹራብ ለብሷል ከታች ነጭ ስስራይፕ ያለው ሱሩ(የሱፉ ሱሪ) አድርጓል እጁን ኪሱ ከቶ እየሄደ ነበር ስፓርኛ አቋም አለው ቸስቱም ደስ ይላል፥ በልብስ ውስጥ ሲታይ።
ሶስተኛ ጊዜ ሳየው ከሀዋሳ እየተመለስኩ ነበር ታንቶስቲና አከባቢ እንደደረስን ሰው ለማውረድ ሲቆም ከመኪናው በስተግራ በኩል ቁልቁል ሲወርድ ተመለከትኩት የለበሰውን ልብስ አላስታሳውስም።
አራተኛ ጊዜ ያየውት አቦስቶ ነው ዛሬ ለብሶ የነበረውን ጥቁር ጃኬት አድርጓል ጥቁር ሱሪ በቦታው ላይ ውርውር እንል ከነበርን ሁሉ ዘንጦ የሚታየው እሱ ነው ያምር ነበር ባየውት ቁጥር ለአለባበሱ ትኩረት የሚሰጥ እንደሆነ ተረድቻለው። He must, because he is pretty, and pretty guys must ራሳቸውን ማሳመር ።
ዛሬ ሳየው መሽቶ ነበር እሱ መሆኑን አላወኩም ለአንድ ጓደኛዬ ወደ እሱ ጠቁሜ ይኸውልህ ይሃ በጣም ቆንጆ ነው አቋሙ ብትል ደስ ይላል ቀረብ ስል እና ትንሽ ዘወር ሲል እሱ ነው ጥቁር ጃኬት በፈዛዛ ጎመኔ ካኪ ሱሪ አድርጓል He just looks pretty. I didn't even see his face at first, but his energy pulled me toward him. I don't need to see someone's face to feel attracted; sometimes I just feel attracted to them even if I am walking behind them. I don't know what this means, but when I see him, I get sad and happy at the same time.
ለጓጀኛዬም ከዚ በፊት ስለነገርኩት ላስታውሰው ሞከርኩ እሱ ጭራሽ ረስቷል ሰው ይረሳል እኔ ግን አልረሳም ባጃጅ እየጠበቀ ወዲ ወዲያ ይላል ብቻዬን ብሆን እስኪሳፈር ቆሜ ባየውት ከጓደኞቼ ስለይ የለም ሄዷል።
የማላገኘው ሰው ነው። አሁን ባለውበት ሰዓት ፍቅረኛ እንደማያስፈልገኝ አስረግጬ አቃለሁ ግን I can't stop wanting someone's companionship, such a deep connection and intimacy that one gets from a friend and a lover. What I want in all this admiration of young men is not sex or something lustful; it's something different. I want to feel welcomed in a pretty young man's arms with love. I want to feel that I can also be as astonishing as they are to me. I want to feel wanted, desired, and loved, and for them to want my company as much as I want theirs.
Those people whom I am attracted to are, or might be, out of my league in the context of sexuality, but that is not necessarily the case. I think I have a belief that says I am not good enough for such people who are pretty, sexy, and beautiful.
I truly wish to have coffee with this man. Whenever I see him, he is always alone. He seems ጭምት and introverted, ሰው የማይረዳው ይመስለኛል. When I see him, I think he is cool, wise, content, and unhurried. But that contentment is not necessarily about his surroundings. He might not even love the way he is living iko, but his core seems still. My inner self is not content or at rest. I want to share what he has inside with what I have inside.
@2015 | የተፃፈ
ሻሸመኔ
#ሰላምእናነፃነትለሁሉም
#የእናንተድምፅየሁላችንነፃነት
#የማይረሱ
@mesobinitiative | 255 |
| 12 | ከዚ በፊት እዚህ Page ላይ ስለቀው የቆየሁት "አኩኩሉው ፍቅሬ" የተሰኘው የሳፎ(የሌዝቢያን) ተከታታይ የፍቅር ታሪክ ምዕራፍ ሁለት ከእሮብ አጀምሮ ይለቀቃል ፤ ይሄንን ድንቅ የፍቅር ታሪክ በኩራት ወራችን ላይ ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ!?😊
እስከዛ ድረስ ያላነበባችሁት ምዕራፍ አንድ ፣ ክፍል አንድን ከላይ አታች ስላረኩላቹ አንብቡት 🙏 ወይም እዚሁ ቻናል ላይ "አኩኩሉው ፍቅሬ" ብላቹ Search ብታረጉት ሁሉንም ክፍል ታገኙታላቹ(6 ክፍል ነው ያለው) 😊
መልካም ንባብ
መልካም የኩራት ወር 🌈
#ሰላምእናነፃነትለሁሉም | 298 |
| 13 | እስኪ አድነኝ ሁነኝ ረዴት
ከጠፋውበት ከተደበኩበት
ፈልገህ
አግኝተህ
አባብለህ
አስታመህ
ሰው አድርገኝ ፍቅርን መግበህ
#ሰላምእናነፃነትለሁሉም
#የእናንተድምፅየሁላችንነፃነት | 319 |
| 14 | እራስን መውደድ ብልህነት ነው!!
ወረቀት ሲመረት ነጭ ነው ፣ ሲፃፍበት የተፃፈበትን ቀለም ይይዛል ፤ ወረቀት ምንም ብንፅፍበት ወረቀትነቱን አይተውም ይልቁንስ ባዶ ወረቀት ከመሆን አልፎ እውቀትን ያዝላል ፤ ነገር ግን ወረቀት ስራውን እና እራሱን ጥሎ ቢቃጠል ወይ ቢቀደድ ዋጋውን ያጣል ፣ ጥቅም የለውም እንደውም አመድ ወይ ቁርጥራጭ ቆሻሻ ሆኖ አከባቢያችንን እንዳያበላሽ ከቆሻሻ ጋር ይጣላል።(አንቺ ሴት ምንድ ነው ምትዘላብጂው እንዳትሉኝ!? 😁)
ምን ልላቹ ፈልጌ ነው!? 😊
እራሳችሁን ስትወዱ እና በተዘጋጀላቹ ቦታ ስትገኙ ልክ እንደዚ ወረቀት እራሳችሁንም ሌሎችንም ትጠቅማላቹ ‟አይ እምቢየው አሻፈረኝ” ካላቹ ግን ተቃጥላቹ እና ስሜታቹ ተሰባብሮ የማይሆን መንገድ ላይ እራሳችሁን ታገኛላቹ!! ስለሆነም እራሳችሁን ውደዱ ፣ ቦታችሁን አትሳቱ ፤ እራስን መውደድ Selfish መሆን ሳይሆን ብልህነት ነው ፤ አስታውሱ እናንተ ከሌላቹ የለፋችሁለት እና እራሳችሁን ያጣቹለት ነገርም የለም ፣ ሁሉም ይጠፋል!!😊
በሉ በቃ ከመሸ አላዝጋችሁም ደህና እደሩልኝ 🙏
#ሰላምእናነፃነትለሁሉም | 348 |
| 15 | በኢትዮጵያ ውስጥ የሥርዓተ-ፆታ ልዩነት፡ ይህ ትክክለኛ ቅርስ ነው እንጂ ከውጭ የመጣ አይደለም
ክፍል አምስት፡ በኮንሶ ባህል ውስጥ የነበሩት "ሳጎዳ (Sagoda)"
በኢትዮጵያ ውስጥ የሥርዓተ-ፆታ ልዩነትን በተመለከተ፣ እንግዳ የሆኑ ታሪኮችን መፈለግ አያስፈልግም። ይልቁንም፣ የዕለት ተዕለት ሕይወት እውነተኛ አካል በሆኑ የባህል ክፍሎች ላይ ትኩረት እናደርጋለን። አሁን ወደ ደቡብ ክልሎች ወደምትገኘው ኮንሶ እንሂድ። በ1960ዎቹ አካባቢ፣ ተመራማሪው ክሪስቶፈር ሮቢን ሃልፓይክ (Christopher Robin Hallpike) ያደረጉት ጥናት "ሳጎዳ" የሚል ስም የነበረው የሚታወቅ ሦስተኛ-ሥርዓተ-ፆታ ሚና ላይ ግልጽ እይታ ይሰጠናል።
"ሳጎዳ" እነማን ነበሩ?
ሃልፓይክ እንዳብራሩት፣ ኮንሶዎች "ሴትነት የሚታይባቸው ወንዶች" የሚል ትርጉም ያላቸው በርካታ ቃላት ነበሯቸው፣ እና "ሳጎዳ" ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ነበር። ይህ ደግሞ ፈጽሞ ያላገቡ ወንዶችን፣ በአካልም ሆነ ከማኅበረሰቡ ከሚጠበቀው የወንድነት ሚና አኳያ ደካማ ተብለው የሚታዩ ወንዶችን፣ እና አንዳንድ ጊዜ ቀሚስ ይለብሱ የነበሩ ወንዶችን ያካትታል። ሃልፓይክ ከጋሆ መንደር የመጣ፣ ብዙውን ጊዜ ከሴቶች ሥራ ጋር የተያያዘ የሆነውን ቆዳ የማድበስበስ ሥራ የሚሠራ፣ እንዲሁም ለስላሳ፣ ከሴት ልጅ ጋር የሚመሳሰል ድምፅና ምግባር የነበረው ሰው መኖሩን ገልጿል።
"ሳጎዳ" የተወሰኑ ጾታዊ ባህሪያት ጋርም ይያያዙ ነበር። ሃልፓይክ አንዳንድ "ሳጎዳዎች" በአንድ ዓይነት የፍቅር ግንኙነት ውስጥ የተገዥ (Passive) ሚና ይወስዱ እንደነበር ተመልክቷል። እርሳቸው የሰበሰቧቸው መግለጫዎች እውነተኛ እንደነበሩና በማኅበረሰቡ ውስጥ በሰፊው የታወቀውን እንደሚያንፀባርቁ ያምኑ ነበር። እንደነዚህ ያሉት ባህሪያት በ"ሳጎዳ" ብቻ የተገደቡ እንዳልነበሩ ያምናል፤ ምንም እንኳ አብዛኞቹ የኮንሶ ወንዶች ስለ ጾታ በግልጽ ማውራት ቢርቁም፣ አንዳንድ ወንዶች እርስ በእርስ በአንድ ዓይነት የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ይሳተፉ ነበር። አልፎ አልፎ፣ "ሳጎዳ" ነው ተብሎ የሚታሰበውን ሰው ወደ እርሻ ጎትቶ ስለማጥቃት ከባድ ቀልዶች ይሰሙ ነበር። እነዚህ ቀልዶች ሁሉም ሰው "ሳጎዳ" ምን ማለት እንደሆነ፣ አምነውትም ይሁን አልፈለጉም፣ እንደሚያውቁ ያሳያሉ።
ለምን ጠፉ?
ስለ አሽቲሜ፣ ኡራኒን እና ዋንደርወራድ ከተማርኩት አንፃር ስመለከት፣ "ሳጎዳ" ቀስ በቀስ የጠፉት በተደባለቀ ማኅበራዊና ባህላዊ ምክንያቶች እንደሆነ እገምታለሁ። ከጊዜ ወደ ጊዜ፣ የኮንሶ ሕዝቦች ወንዶች በጣም ጥብቅ በሆኑ መንገዶች እንዲመሩ መጠበቅ እንደጀመሩ አስባለሁ። ገር ወይም ሴትነት የሚታይባቸው ወንዶች "ልዩ" ተብለው መታየት ጀመሩ፤ በግልጽ መኖርም ለእነርሱ አስቸጋሪ ሆነ። በተመሳሳይ ጊዜ፣ አዳዲስ ትውልዶች ከሃይማኖት እና ጠባብ የሆነ የወንድና የሴት ሚናዎችን ከሚያበረታቱ የመንግሥት ሕጎች ግፊት ገጠማቸው። ቤተሰቦች "ሳጎዳዎችን" እንዲያገቡና "መደበኛ" የሚባሉ ሥራዎችን እንዲይዙ ያበረታቱ ነበር፤ በዚህም በማኅበረሰቡ ውስጥ የመታየት ዕድላቸው እየቀነሰ ሄደ።
መጥፋታቸው ማንነታቸው የተሳሳተ ወይም ከተፈጥሮ ውጭ ስለሆነ አይደለም። ይልቁንም ማኅበረሰቡና ባህሉ ጥብቅ የሆኑትን ደንቦች ከማያሟሉ ሰዎች ጋር ምንም ቦታ በማይሰጥ መልኩ ቀስ በቀስ በመቀየሩ ነው።
ልናስታውሰው የሚገባ ቅርስ
የ"ሳጎዳ" ታሪክ በኢትዮጵያ ውስጥ የሥርዓተ-ፆታ ልዩነት ጥልቅ ሥሮች እንዳሉት ያሳየናል። እነዚህ ወንዶች የማኅበረሰባቸው አካል ነበሩ፤ ማኅበረሰቡ በአንድ ወቅት የተገነዘባቸው፣ ሁልጊዜም ሙሉ በሙሉ ባይቀበልም እንኳ፣ የራሳቸው ሚናዎች፣ ግንኙነቶች እና የአኗኗር መንገዶች ነበሩ። "ሳጎዳ"ን ማስታወስ በሥርዓተ-ፆታና በማንነት ላይ ያሉ ልዩነቶች አዲስ ወይም ከውጭ የመጡ እንዳልሆኑ ያስታውሰናል፤ እነርሱ የእውነተኛ ባህላችን አካል ናቸው።
Gloria Victor
June 2026 | 363 |
| 16 | አንዳንድ ቀን በራሳችሁ ማንነት መለወጥ ገርሟችሁ አያውቅም? ጣልነው የምትሉት ማንነት ይኖራችሁ ይሆናል? ግን የምንፀፀትበት ነው? ወይስ ማደጋችንን የምጋውቅበት ነው? የሚለው እንደየሰዉ ይለያያል። ግን ልንረሳ የማይገባን ነገር ቢኖር ትላንት ያለፈ ፣ ነገ ደግሞ የማይጨበጥ መሆኑና ዛሬ ላይ ያለው እኛ የተሻለ ግንዛቤ ያለው፣ ከትላንቱ የተሻለ እውቀት ያለው፣ የበለጠ ኃላፊነት መቀበል የሚችል ሰው እንደሆነ ነው። ዛሬ ላይ ቆመን በጥበብ ከተናገርን ትላንት ይሻላል ማለት አንችልም!!!
ዛሬን መኖር ነፃነት ነው!
መልካም ከሰዓት!
#ሰላም_እና_ነፃነት_ለሁሉም
#የእናንተድምፅየሁላችንነፃነት | 271 |
| 17 | MESOB THURSDAY CONFESSION
Content Warning: Suicide, self-harm, homophobia, mental health struggles.
#Submittedanonymously.
I have a confession.
I tried to kill myself so many times, but I couldn't do it, and I don't know why.
There was a time when my dad owned a gun. I put it inside my mouth. I could taste the cold metal on my tongue. I was going to shoot myself and get it over with. Make everything end.
But I didn't.
I always thought of myself as cursed, a mistake, an abomination. I hated myself.
I could handle physical pain, but this was different. This pain lived inside me. I couldn't see it I could only feel it. It felt like drowning in darkness with no light.
I couldn't accept myself. I kept asking, "Why me? Why am I like this?" I never found an answer.
So I wanted it all to end.
I tried many ways to kill myself. I tried jumping off a cliff. I tried drowning. Nothing worked.
Then one day, I had a sleepover at a friend's house. We ate dinner, got drunk, and went to bed.
In the middle of the night, I woke up and saw him sleeping.
I don't know what I was thinking, but I kissed him.
It felt good.
I kept kissing him and cuddling with him until he woke up. He saw me lying on his chest, got shocked, and pushed me away.
The next morning, he looked at me with disgust and said:
"You cuddled with me last night. That's so gross. I've never even cuddled with girls like that."
I started having panic attacks.
I told myself what society had always told me: that I was a sin, a mistake, cursed.
And once again, I wanted to die.
I got my dad's gun, closed my eyes, put it in my mouth, and pulled the trigger.
Nothing happened.
I had forgotten to take the safety off.
I dropped the gun. I was shaking.
For the first time, I asked myself a different question:
"What if I stop trying to kill myself and start listening to myself?"
So I stopped.
I started trying to understand myself.
I started listening to myself.
I'm okay now, but I'm still trying.
Trying not to lose myself.
፦ Anonymous
If you are struggling with thoughts of suicide or self-harm, please reach out to someone you trust or a mental health professional. You do not have to face it alone.።።።
Even if Mesob doesn't provide professional mental health we can listen and talk. Feel free fo DM.
#peaceandfreedomforall
#yourvoiceourfreedom
#MesobThursdayConfession
#MentalHealthMatters #YouAreNotAlone #SurvivorStory #SelfAcceptance#HealingJourney | 421 |
| 18 | በኢትዮጵያ ውስጥ የሥርዓተ-ፆታ ልዩነት፡ ይህ ትክክለኛ ቅርስ ነው እንጂ ከውጭ የመጣ አይደለም
ክፍል አራት፡ ዋንደርወራድ (Wandarwarad)—በአማራ ማኅበረሰብ የሥርዓተ-ፆታ ተለዋዋጭነት
ይህ ጽሑፍ የሥርዓተ-ፆታ ልዩነት ከኢትዮጵያ ባህል ውጭ የሆነ ነው የሚለውን የተሳሳተ አመለካከት የሚፈታተን የጽሑፎች ተከታታይ ክፍል ነው። በምዕራብ ስለነበሩት "አሽቲሜ" እና በሐረር ስለነበሩት "ኡራኒን" ካደረግነው ዳሰሳ በኋላ፣ አሁን ደግሞ ወደ አማራ ክልል እንዞራለን። ታሪካዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የሥርዓተ-ፆታ ልዩነት ለኢትዮጵያ እንግዳ አልነበረም፤ ይልቁንም በዚያን ጊዜ የማኅበረሰቡ ተፈጥሯዊና አስፈላጊ አካል ነበር። ከአምሳ ዓመት በፊት የተደረገ አንድ ጥናት በአማራ ተራራማ መንደሮች ውስጥ በቀላሉ "ወንድ" ወይም "ሴት" ብቻ ሊባል የማይችል ማንነት መኖሩን አስመዝግቧል። እነርሱም "ዋንደርወራድ" የሚል የራሳቸው ስም ነበራቸው፤ ይህም የሥርዓተ-ፆታ ተለዋዋጭነት የተፈጥሮ እና የመንደር ሕይወት አካል እንደነበረ ያሳያል።
"ዋንደርወራድ" እነማን ነበሩ?
በ1950ዎቹ ውስጥ፣ ተመራማሪው ሳይመን ሜሲንግ (Simon Messing) በአማራ መንደሮች ውስጥ በመወለድ ወንድ ሆነው የተመደቡ ቢሆንም፣ ከባህላዊው የወንድነት ሚናዎች በእጅጉ የተለዩ ሚናዎችንና ባህሪያትን የተከተሉ ግለሰቦችን መዝግቧል። እነርሱም "ዋንደርወራድ" ተብለው ይጠሩ ነበር—ይህ ቃል በከተሞች የማይታወቅ ቢሆንም በአካባቢው ተቀባይነት ነበረው። እነዚህ ግለሰቦች ብዙውን ጊዜ ልቅ ያለ ልብስ ይለብሱ ነበር፣ በለስላሳ ይናገሩ ነበር፣ እና እንደ ምግብ ማብሰል ወይም እንጨት መሰብሰብ ባሉ ሥራዎች ይሳተፉ ነበር። በጣም አስፈላጊው ነገር፣ ልዩነታቸው እንደ ተቃውሞ ወይም ግጭት አይታይም ነበር፤ ይልቁንም በቀላሉ ተቀባይነት አግኝቶ ነበር።
ከሴቶች ጋር ጠንካራ ትስስር ፈጥረው ነበር፤ ወንዶች ብዙውን ጊዜ ራሳቸውን ቢያርቁም፣ በጋራ ማኅበራዊ ዝግጅቶች ላይ ሙሉ በሙሉ ይሳተፉ ነበር። ማንነታቸው ዘመናዊ የሆኑ እንደ "(Gay)" ወይም "የሥርዓተ-ፆታ ሽግግር ያደረጉ (Transgender)" ባሉ ቃላት ሳይሆን፣ በመንደሩ ሕይወት የተገለጸ፣ ተፈጥሯዊ አካል ነበር።
የማንነት መጥፋት
"ዋንደርወራድ" የጠፉበትን ምክንያት ለመረዳት ስሞክር፣ በአንድ ምክንያት ብቻ እንዳልሆነ ግልጽ ሆነ። ይልቁንም ህልውናቸውን ቀስ በቀስ እንዲደበዝዝ እና በመጨረሻም ከሰዎች ትዝታ እንዲጠፉ ያደረጉ የተቀናጁ ምክንያቶች ነበሩ።
· የሃይማኖት ተጽዕኖ: ቀደም ሲል፣ የመንደር ሕይወት ሰዎች በሥነ-ምግባር እስከተመሩ ድረስ በሥርዓተ-ፆታ ሚናዎች ላይ የተወሰነ ተለዋዋጭነት ይፈቅድ ነበር። ነገር ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እየጠነከረች ስትመጣ፣ "ወንድ" እና "ሴት" ተብለው በሚታሰቡት መካከል ግልጽ ድንበሮች እንዲኖሩ አጥብቃ በመጠየቋ፣ አካባቢው ይበልጥ ግፊት የበዛበት እና ለተለየ ሰው ተቀባይነቱ የቀነሰ ሆነ። ብዙውን ጊዜ ቀጥተኛ ቅጣት ባይኖርም፣ ከመደበኛው ጋር የማይጣጣሙ ሰዎች በማኅበረሰቡ ውስጥ ያላቸው ቦታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠበበ እንደሄደ ተሰማቸው።
· የቤተሰብ እና የአካባቢ ማኅበረሰብ ጫና: ከእነዚህ ግለሰቦች መካከል ብዙዎቹ ከዘመዶቻቸው እፍረት ወይም ጫና ገጥሟቸዋል፤ እንዲያገቡ ተገፋፍተዋል፤ ወይም ከሕዝብ ሕይወት እንዲርቁ ተበረታተዋል። ይህ ደግሞ በዝምታ እንዲኖሩ አስገድዷቸዋል፤ በዚህም ታሪኮቻቸውንና ልምዶቻቸውን ለወደፊት ትውልዶች የማስተላለፍ ዕድል ቀንሷል።
· ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ለውጦች፡ በመጨረሻም፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ለውጦች "ዋንደርወራድ" ላይ ተጽዕኖ አሳድረዋል። ማዕከላዊ መንግሥት እየጠነከረ ሲሄድና መንደሮች ከከተሞች ጋር እየተገናኙ ሲሄዱ፣ የመንደሩ ሕይወት መለወጥ ጀመረ። "ወንድ" እና "ሴት" ብቻ የሚለው አዲስ አስተሳሰብ ከአገር ውስጥ ልማዶች የበለጠ አስፈላጊ እየሆነ በመጣ ምክንያት፣ ከዚያ የተለዩ የሥርዓተ-ፆታ ማንነቶች ቀስ በቀስ ጠፉ።
በደቡብ ለነበሩት አሽቲሜ፣ በሐረር ለነበሩት ኡራኒን፣ እና ለ"ዋንደርወራድ" የደረሰውን ስንመለከት፣ የተለመደ ንድፍ ይወጣል፡- የሃይማኖት፣ የቤተሰብ እና የማኅበራዊ-ፖለቲካዊ ለውጥ ጥምር ግፊቶች ከሕዝብ ሕይወትና ከትዝታ እንዲጠፉ አድርጓቸዋል—ማንነታቸው "ከተፈጥሮ ውጭ" ስለነበር ሳይሆን፣ ማኅበረሰቡ ለልዩነት የነበረው ተቀባይነት ስለቀነሰ ነው።
ልናውቀው የሚገባ ቅርስ
ስለ "ዋንደርወራድ" ታሪክ ሳስብ፣ እነርሱ ከውጭ የመጡ ሳይሆኑ የመንደር ሕይወት አስፈላጊ አካል እንደነበሩ ያረጋግጣል። ህልውናቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ሥርዓተ-ፆታ ተለዋዋጭና ተስማሚ እንደነበረ፣ በዕለት ተዕለት ተግባራትና ግንኙነቶች ውስጥ በዝምታ የተሸመነ እንደነበር ያሳያል።
ይህንን መረዳት የሥርዓተ-ፆታ ልዩነት ከውጭ የመጣ ወይም የገባ ሐሳብ ነው የሚለውን አመለካከት ለመቀበል አስቸጋሪ ያደርገዋል። በተቃራኒው፣ የአገር ውስጥ ባህል አካል ነበር፤ ሰዎች ራሳቸውን የሚገልጹበትንና የሚኖሩበትን መንገድ የውጭ ተጽዕኖዎች ለማጥበብ ከመሞከራቸው ከረጅም ጊዜ በፊት የነበረ ነው። ታሪካቸው የኢትዮጵያ ያለፈው ዘመን እኛ ከምንገምተው በላይ ክፍትና ውስብስብ እንደነበረ ያስታውሰናል፤ ይህንን ልዩነት ማወቅ ደግሞ ታሪካችንን ለመረዳት ወሳኝ ነው።
Gloria Victor
June 2026 | 413 |
| 19 | እና በቃ ማንም ኑዛዜ የለውም🤭🙄
@MesobConfessBot
አናቆርፍደው እንጂ🤭
#ስላምእናነፃነትለሁሉም
#የእናንተድምፅየሁላችንነፃነት | 410 |
| 20 | ምዕራፍ አንድ
እኔ እና ሜሮን
2010ዓ.ም (እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ)
በህይወቴ እንኳን ለሌላ ለራሴ እንኳ ለወንድ ያለኝን ስሜት ደግሜ ተናግሬ አላቅም ፆታዊ ፍላጎቴን ማወቅ ከጀመርኩ ወዲህ ያለኝ ነገር በሙሉ ለወንድ ነው ለሴት ትልቅ ክብርና ፍቅር ያለኝ ቢሆንም በፃታዊ መንገድ ለማሰብ አቅሙ ኖሮኝም አያውቅም ለምን እኔም አላቅም…..ይህ አመት እኔ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ከመጣ በኋላ ጊቢ የተባለ መካነ አዕምሮ የገባውበት ነበር ብዙም ምጠብቀው ነገር ስለሌለ የተሰጠኝን ነገር በፀጋ ተቀብዬ አስፓልት ሆነ ኮብልስቶን የሌለበት ካለውበት ከተማ እጅግ የሚርቅ ጠረፍ ድንበር ገብቻለው መንገዱ አዛ ነው አድካሚ ነው የአካባቢው ሙቀት አንደኛ ነው ቢሆንም ግን ለእኔ ምንም ነበር ሁሉ መቻል ስንፈለግ እንችለዋለን።
ጊቢ ከገባው በርካታ ጊዜያት በኋላ በርካታ ሰዎችን በአንድ ጊዜ ለመተዋቅ ጊዜ አልፈጀብኝም ተጫዋችነቴ እና ተግባቢነቴ እንኳን ፍሬሽ የሲኒየር ሲኒየር ነበር ያስመሰለኝ ቤተ ክርስቲያን ላይ ክላስ ላይ እንዲው ከመላው የጊቢው ሰው ጋር ተዋወኩ(እንደ ጋደኞቼ ከሆነ ጊቢ ውስጥ 5ሺ ሰው ቢኖር 3ሺውን ያውቃል ይላሉ) ሜሮን ቤተ ክርስቲያን ላይ ከተዋወካቸው ሰዎች አንደኛዋ ናት ሲበዛ ለሰው ፍቅር ያላት የዋህና ትሁት ንፁህ ሴት ናት በእድሜ ታላቄም ብትሆን ልጅነት አለባት ነገር ግን ሰው ስትወድ ከልቧ ነው፡፡
አንድ ቀን ማታ ስለፍቅር እየተወራ በነበረበት የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት ጊዜ በእኛ ቡድን ስር ያሉት ራሳቸውን እየደበቁ አንዳንድ ነገር ገልጠው ተናገሩ እኔ ምናገረው ምንም ነገር አልነበረም ብቻ ልጅ ሳለው እወዳት ስለነበረች የእቃቃ ሚስቴ አወራው ..ፍቅር እጅግ ጥልቅና ኃያል ነገር ነው መኃልየ መኋልዬ ፍቅርን ሲገልፀው፦
“በልብህ እንዳለ፣ በክንድህም እንደምትይዘው ማኅተም አስቀምጠኝ፤ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች፣ ቅናቷም(ጥልቅ ስሜት) እንደ መቃብር(ሲኦል) ጨካኝ ነትና፤እንደሚንቦገቦግ እሳት፣እንደ ኀይለኛም ነበልባል ትነዳለች፡፡የውሃ ብዛት ፍቅርን ሊያጠፋ አይችልም፣ ፈሳሾችም አያሰጥሟትም.”
በዚ ክፍል ለበርካታ ሰዓታት ስንመካከር ቆይተን ወደ ጊቢ ገባን እኔና ሜሪ እንደ ለመድነው ቀደም ቀደም እያልን እያወራን እንሄዳለን ሜሪ ለኔ የአንድ አመት ሲኒየሬ ናት ቢሆንም እንደ ጓደኛ ቀለል ያለችም ናት አንድ ነገር ሂንት ነግራችኋት ሙሉ ነገሩን ካልሰማች አትፋታችሁም አወራቸው ስለነበረች የልጅነት ሚስቴ እየጠየቀችኝ ወደ ጊቢ አመራን እኔም የመጣው ይምጣ መናገር አለብኝ ስሜቴን ስል ላወራት እንደ ምፈልግ ነገርኳት፡፡
ሁሉንም ተሰናብተን በላውንቹ ፊት ጨለም ካለው ስፍራ ተቀመጥን..ምን ተብሎ ነው ሚጀመረው ግራ ገባኝ መናገር እንደጀመርኩ ማልቀስ ጀመርኩ አሁን ስስቅ የነበርኩት ልጅ በአንዴ እንባ በእንባ ንፍጥ በንፍጥ ሆንኩኝ ለስሜቴ ይሄን ያህል ቅርብ ነበርኩ ለረጀም ጊዜያት ማንንም ሳላወራ የታፈነው ብቸኝነቴን የዛን ቀን ማታ አፈረጥኩት…ለወንድ ልጅ ስሜት እንዳለኝም ነገርኳት ጊቢ ከገባው አይቼ ማላቀው የወንድ ልጅ እርቃን ገላ በየቀኑ ዶርሜ ፊት ራቁታቸውን ሻወር የሚወስዱ ወንዶች ሰለም ነስተውኛል ማታ በህልሜ ሁሉ ድንገት ብቅ እያሉ ያስጨንኩኝ ጀምረዋል ዶርም ውስጥ ወንድ ለወንድ አይተፋፋር የተባለ ይመስል መለመላቸውን ፓንት ሲቀይሩ አንዴ ቂውን ቁውን ሳይ ድንግጥ እላለው ነገር ግን የዶርሙን እንኳ ለመከላከል ችያለው ማንም እኔ ስኖር እንደዛ እንዲቀይሩ እንደማልፈለግ በግልጥ ነው የተናገርኩት ሁሉም ስለሚወዱኝና ሲለሚያከብሩኝ ታዘዙልኝ ፡፡
ሜሪ የምነግራት ነገር ፈፅሞ ሰምታ የማታቀው እንግዳ ነገር እንደሆነ ተረዳው ለማን ምን መናገር እንዳለብን ማውቅ ትልቅ ብልሃት ነው ምክንያቱም እናንተ አውርታችሁ ቀለል ሊላችሁ ይችላል ይሃ ሰው ግን ምንም ማድረግ በለመቻሉ የሚሰማውን ስቃይ መረዳት አንችልም ፡፡አብራኝ ማልቀስ ጀመረች coming out እንደዚ መሆኑን መቼ አወኩ ስናለቅስ ድምፃችን ሁሉ ይሰማ ነበር ብቻ ኃይሏን አሰባስባ ‹‹ እሺ አባ ኪያ አድርገህ ታቃለህ..›› ስትል እንባ ባነቀው ድምፅ ጠየቀችኝ ‹‹ በየሱስ ስም ሞቻለው እንዴ ይሃን የማደርገው….›› እውነት ነው አሁን ላይ ከዚ ቃሌ የተነሳ ሞቻለው ከወንድ ጋር ወሲብ ማድረግ ያነፃፀርኩት ከሞት ጋር ነበር ይህም ከተጨመረብኝ አስተሳሰብ የተነሳ እንደሆነ መለስ ብዬ ሳስበው እገረማው ምን ያህል ማህረሰቡ ሆነ ያመናቸው ያከበርናቸው ሰዎች ራሳችንን እንድንጠላ የማድረግ አቅም እንዳቸው እረዳለሁ፡፡
ብዙም አልቆየንም አለቀስን በምትችለው መንገድ ከዚ ነገር መውጣት እንድችል ልትረዳኝ ቃል ገባችልኝ የዋህነቷ ሻወር ውጪ እንድወስድ ሁላ ሃሳብ አቅርባልኝ ነበር፡፡ አንዳልፈተን ቤት ውጪ ልትከራይልኝ ሁሉ ነበር ምንም እንኳ 2011 የአመቱ መጨረሻ ላይ በዚ ነገር አሳንሳ እንደምታየኝ እስከምረዳ ድረስ ጥሩ ወዳጅነት አሳይታኛለች ምንም እንኳ ባልጠላት ለሷ መንገሬን እፀፀትበታለው ክፉ ሆና አይደለም ነገር ግን መፍትሄ የሌለውን ነገር መፍትሄ ለመፈለግ የማትወጣው ጉድ ውስጥ ስለጨመርኳት በራሴ እናደዳለው …የዛን ቀን ማታ እኔ ወደ ዶርም እፎይ ብዬ ስገባ ሰዎች እንደነገሩኝ ስታለቅስ እንዳመሸች እና ቤተ ክርስቲያን ላይ አብሯት የሚያገለግለውን በተለምዶ DAD የምንለውን ሰው ጠርታ ነገሩን ነገረችው ልንገረው ስትለኝ እሺታዬን ገልጬ ስለሆነ በፍቃዴ ነው ከዛ ቀስ በቀስ እያለ በህይወቴ ያማልረሳው ጠባሳ ጥሎ ለመሄድ በቃ 2011 የአመቱ መጨረሻ ላይ 10-15 የሚደርሱ የቤተ ክርስቲያን የወጣቶች ህብረት መሪዎቸ እና አንዳንድ ሰዎች ስለ እኔ ለማወቅ በቅተዋል፡፡ከዚ ቀደም ብሎ ባለው 2010 ክረምት ቤት መታ ለቤተሰቤ ካልተናገርኩ ብላ አስደንግጣኝ ነበር፡፡
እሷ መታ ለእናቴ እንደ ምትናገር ስለነገረችኝ ሳልወድ በግዴ ለቤተሰቤም HALF COMING OUT ለማድረግ ተገድጄ ነበር እነሱ ባደረሱብኝ ነገር ከትምህርት ገባታ ሁሉ አቋርጬ ሁሉ ለመሄድ እስከመወሰን ደርሼ ነበር ነገር ግን ይሃ አልሆነም እነሱ ተመርቀው ሲወጡ የተሰበረውን ልቤን ደብቄ ጠንካራ መስዬ ለመኖር ሞክሪያለው ጓደኞቼ ለእነሱ ነግሬ ለነሱ ያልተናገርኩት ነገር ምን እንደሆነ እስከዛሬ ባለማወቃቸው ነገሩ ሲነሳ ጥፋቱ የእኔ እንደሆነ ይወቅሱኛል ልክ ናቸው ጥፋቱ የእኔ ነው ፡፡
#ስላምእናነፃነትለሁሉም
ገጠመኝ (2014) የተወሰደ
#የእናንተድንፅ የእኛ ነፃነት
ገጠመኛችሁን በዚ👇 በኩል መልዕክት መላክ ትችላላችሁ!
@MesobConfessBot | 408 |
Вже доступно! Дослідження Telegram за 2025 — головні інсайти року 
