ru
Feedback
MESOB_Initiative (MI)

MESOB_Initiative (MI)

Открыть в Telegram

🌈 Mesob Initiative : An Ethiopian queer arts and advocacy collective using media, literature, and creative expression to advance LGBTQ+ rights and visibility.✊✨ 🕊 PEACE AND FREEDOM FOR ALL! 🌍 YOUR Voice , OUR Freedom! 🏳️

Больше
401
Подписчики
-124 часа
-57 дней
+13630 день

Загрузка данных...

Похожие каналы
Нет данных
Возникли проблемы? Пожалуйста, обновите страницу или обратитесь к нашему support-менеджеру .
Облако тегов
Нет данных
Возникли проблемы? Пожалуйста, обновите страницу или обратитесь к нашему support-менеджеру .
Входящие и исходящие упоминания
---
---
---
---
---
---
Привлечение подписчиков
июнь '26
июнь '26
+183
в 1 каналах
май '26
+19
в 0 каналах
Get PRO
апрель '26
+31
в 0 каналах
Get PRO
март '26
+34
в 0 каналах
Get PRO
февраль '26
+20
в 0 каналах
Get PRO
январь '26
+28
в 0 каналах
Get PRO
декабрь '25
+19
в 0 каналах
Get PRO
ноябрь '25
+23
в 1 каналах
Get PRO
октябрь '25
+31
в 0 каналах
Get PRO
сентябрь '25
+51
в 2 каналах
Get PRO
август '25
+60
в 1 каналах
Get PRO
июль '25
+56
в 2 каналах
Get PRO
июнь '25
+81
в 1 каналах
Get PRO
май '25
+148
в 2 каналах
Get PRO
апрель '250
в 0 каналах
Get PRO
март '25
+121
в 1 каналах
Get PRO
февраль '250
в 1 каналах
Get PRO
январь '250
в 2 каналах
Get PRO
декабрь '24
+56
в 0 каналах
Дата
Привлечение подписчиков
Упоминания
Каналы
27 июня0
26 июня+2
25 июня0
24 июня0
23 июня+2
22 июня+4
21 июня+1
20 июня+1
19 июня+1
18 июня+4
17 июня+5
16 июня+3
15 июня+1
14 июня+2
13 июня+5
12 июня+6
11 июня+10
10 июня+109
09 июня+2
08 июня+2
07 июня0
06 июня+2
05 июня+1
04 июня+1
03 июня+1
02 июня+7
01 июня+11
Посты канала
So ሁል ጊዜ የአባላዘር በሽታ/ተላላፊ በሽታ ሲነበብ ፣ ሲፃፍ ቆይቷል አሁን ስለሱ አላወራም የገጠመኝን ነው የምነግራችሁ the guy I start sex with ነው ይህ የተፈጠረው፥ ብዙ ጊዜ እዚ ግቡ የማይባሉ የብድ ሰከንዶች ነበሩን🤭 (you know what I meant : pleasee guys do kegel) ብቻ ያው የጠረረባት ስትሆኑ እንደኔ ክፍለሀገር (ለነገሩ አአ የተለየ ነገር የለውም (I didn't mean አአ ሁሉንም  ቀመስኩ🤭  don't judge)) እና ከዚ ወጣት ጋር ያው አልፎ አልፎ እንዋሰብ ነበር (why I keep going? tbh I don't even know) ከዛ አንድ ቀን እንደተለመደው ጠራኝ እኔም why not  አልኩና ሸከተፍ ሸከተፍ 🚶‍♀️🚶‍♂️ እያልኩ መሄድ ከዛ ያው የጠራራ ፀሐይ መንፈስ አስጀመረን ኮንዶም ተጠቀምን ከዛ ተደረገ .... አ አ አ.... አለ ...ከዛ አለቀ my 🍑 disappointed ከዛ ወደቤት ፣ ሻወር የታጠበ ልብስ እና ፓንት አደረኩ nothing new የተለመደ ነበር ፊልም አየው ከዛ በንጋታው ስራ መሄድ እንደ አጋጣሚ ሆኖ there was this presentation I had to give in a meeting እና ቆሜ መናገር፦ ይኮሰኩሰኝ ጀመረ ፣ በአለቆቼ ፊት ፣ በከፋዮቼ ፊት ፓንቴን አላወልቀው ወይ አላከው ወይ አልጎረጉረው ብቻ ጨረስኩና ከ2ሰዓት በኋላ ሽንት ቤት ሮጥኩ ሞባይል አበራው ፈለኩ ፈለኩ ምን ሆኜ ነው ብዬ it seems same nothing የለው (fyi this is me in my innocent era, so no knowledge ) ብቻ በረድ ፣ ምጥት ፣ መለስ ፣ ሽብረክ ፣ አከክ ፣ ቁንጥጥ እያደረገኝ ዋልኩና ቤት ስገባ ተገለባብጬ ፣ ተበለቃቅጬ ሳይ ስጋዬ ላይ የተጣበቁ ቅማሎች ነበሩ 🤮🤮🤮 ጌታዬ this much ግማታም ግድ የለሽ አይደለውም ቅማል ያለብኝ ለውድ ቃልአብ ደወልኩና ኡኡኡኡኡኡ ጉድ ሆንኩ አልኩ እንደዛሬው ቻትጂፒቲን ብዙ አላቅም ነበረና ጎግል አደረኩ  መዳኒት ጠቆመኝ ወደ መድሃኒት ቤት ሮጥኩ። ግን የሆነ የጤና ባለሙያ ደወልኩና አማከርኩ ማድረግ ያለብኝን ነገረኝ ተላጨው ፣ ልብሶቼን የተነካኩትን በፈላ ውሃ አጠብኩ ፣ ራሴን እንደ ዶሮ እየዘፈዘፍኩ ሳምንት ሰይሞላ ከላዬ አራገፍኩ። Imagine me ፡ doing other things using 👄 on  🍆 🙄 jeeዝ ነዛዘረኝ  ይህን ስፅፍ ራሱ #Bottomline why I am telling this is not because I wanna joke about it ለእኔ አስቀያሚ እና አሳፋሪ ጊዜ ነበረ። እንደ እኔ ኮንዶም በቂ መስሎኝ ነበረ apparently its not duh ... የማቀው ሰው ነበረ ልል እችላለሁ ግን ይሃም አልታደገኝም ፣ ምክንያቱም እኔም እሱም የተለያየ ሰው ጋር ሂያጅ ነን። የአባላዘር በሽታ ማለት በኮንዶም ብቻ የምንከላከለው አይደለም በቆዳ ንክኪ የሚተላለፍ ፣ በoral sex ፣ በሰክ እና ከዘር በፊት ባለ ፈሳሽ  ፣ በምራቅ የሚተላለፉ ሁሉ አሉ። so what are we doing to prevent us from contracting those things? STI/STD መያዝ የሚያሳፍር ነገር አይደለም ነገር ግን የሚያሳፍረው ቼክ ለመደረግ አለመድፈር ወይም ደግሞ ሌሎችን ለማሳፈረ መሞከር ነው። እኔ ስዳራ ቀኑን እና ሰውየውን የምይዝበት አጀንዳ አለኝ (nOT SAYING ተዳሩ ያለገደብ🤭)  cz የሆነ ሰዓት ላይ እኔ ጥንቃቄ ጎሎኝ ወይም ወይም ሳላውቅ በበሽታ ብያዝ Timeline አይቼ ለሰዎቹ ለመንገር ነው(bitch don't think there are a lot off people I hooked up with) ለእነዛ ሰዎች ከተናገርን የሚመጣ ድራማ አለ ? አዎ ይኖራል ከእነሱ ተቀብለነውም ቢሆን ማለት ነው። that was what happened with me፣ ስነግረው ተለዋወጠ ፣ ተሳደበ ነገር (እንዴት እንዳልበሉት ፈጣሪ ይወቀው ወይ የተኩስ አቁም ስምምነት ተስማምተው ይሆን🤔 እንጃ) #sex_matters  so does our #precious_body and #life too. STI/STD ያዘህ no big deal ብቻ ሳታረፍድ ማሸነፍ ነው። ደግሞ ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደር ነገር ራሳችሁን ጠብቁ ፣ ቼክ ተደረጉ ለማለት ነው እንጂ ለማስፈራራት አይደለም one more thing chatgpt said pubic lice is not STI🤭  ብቻ ዋና ነጥቤ ገብቷቹሃል። ሌላው በርካታ ተላላፊ በሽታዎች (sexual I mean) ምልክት ለማሳየት ሊቆዩ ይችላሉ ከየሰው ሰው የተለያየ ነው። ግን እስከዛሬ ድረስ ስንት ጊዜ ተመርምራቹሃል ? comment አድርጉ እስኪ #ሀፍረት በዚህ ስፍራ የለውም! for those who are wondering Currently ተፈውሻለው😁 ምንም ተላላፊ በሽታ የለብኝም as far as The medical professionals said . 🤭 #SexMatters #SexualHealth #STIAwareness #GetTested #KnowYourStatus #SafeSex #ProtectYourself #HealthIsWealth #QueerHealth #LGBTQHealth #CommunityCare #EndTheStigma #BreakTheSilence #TalkAboutSex #SexEducation #PublicHealth #HealthyRelationships #BodyAwareness #PreventionMatters #YourHealthYourChoice #የወሲብጤና #የጤናግንዛቤ #ምርመራይደረግ #ለጤናቅድሚያ #ከማፈርይልቅመመርመር #ጥንቃቄይበልጣል #እንወያይ

2
Нет текста...
117
3
MESOB THURSDAY CONFESSION To: Y Looking back now, I don't think we loved each other fully or maybe not enough. Because if we did, why couldn't we make it through this? Maybe we were in love with the idea of us. Maybe we met at the wrong time. I don't know. What I do know is that you were the person who made me believe in love. For that, I will always be grateful. Perhaps one day life will give us another chance. Until then, a part of me will still be waiting, still looking for you in crowded rooms and unexpected places. I don't know how I'm supposed to learn to live without you in my life. And if I'm honest, I'm a little sad that the friendship you promised never came when the relationship ended. So this is my goodbye for now. Not with bitterness, but with hope. Hope that one day our paths will cross again, and we'll meet each other once more under kinder circumstances. ❤️ — Anonymous Share your feelings, fears, experiences, laughs, and everything in between. Send your confession to @MesobConfessBot every Thursday : a space to vent, reflect, and be heard. ✨ #peaceandfreedomforall #yourvoiceourfreedom
115
4
አኩኩሉው ፍቅሬ       ምዕራፍ ሁለት ፦ ክፍል አምስት እየዘለልኩ የወረድኩትን ደረጃ እየሮጥኩ ወጥቼ ወደ ዶርም ተንደርድሬ ተመልሼ ገባው ፤ የዛች ሴት ሽቶ የእኔን ሽቶ አለመቀባት አስታውሶኝ ስለነበር ወደ ዶርም ተመልሼ ሽቶዬን አርከፍክፌ ወጣው። ከዶርም ወጥቼ የግቢ በራፍ ላይ እስክደርስ ያለው ርቀት የሰማይን ያክል እራቀብኝ ፣ ብሄድም አልደርስበት አልኩኝ እንደምንም በራፍ ጋር ስደርስ ሰአቱ 6:25 ይላል ከደወለች በኋላ Almost ሀምሳ ደቂቃ አርፍጃለሁ ፣ የባለፈዋን መኪና ፍለጋ ሳማትር ፊቷን ወደ ምስራቅ አዙራ ከበራፋችን ትንሽ ሜትሮችን ርቃ ቆማለች ፣ ወደ መኪናዋ እርምጃዬን ስጀምር ተነስታ ሄደች እየተገረምኩ ቆሜ አየኋት ተመልሳ ቆማ ወደ ኋላ መጣች ፣ አጠገቤ ቆማ መስኮቱን ዝቅ እያረገች "እንደው ብችል እና ጥዬሽ ብሄድ" አለችኘሰ ቅጥል ብላ ንዴቷ ፊቷ ላይ በደንብ ይታያል ፣ ምንም ሳላወራ መኪናዋን ከፍቼ ገባው እና ተቀመጥኩ (ጥፋቴን አውቃለዋ ምን አፍ አለኝ)። ፅኑ እንደዛው እሳት እንደጎረሰች ቀጠል አርጋ "ሰው እንዴት አንድ ሰአት ሙሉ ያረፍዳል" አለችኝ "ይቅርታ የኔ ቆንጆ በእውነት እየመጣሁ ነው ስትይኝ ምትቆዪ ነበር የመሰለኝ" ስላት ቁና ተነፈች እና "አሳዛኝ በይ ነይ አሁን እቀፊኝ" ብላ እጆቿን ዘረጋችልኝ ፣ ምን አይነት ፊት አሳይቼያት ይሆን? እንጃ! ብቻ ጊዜ ሳላጠፋ ፈጠን ብዬ ተጠመጠምኩባት ፣ እቅፏም ገብቼ በጠረኗ እዛው የቀለጥኩ መሰለኝ ፣ አንገቷ ስር ገብቼ ጠረኗን መማግ ጀመርኩ ቀስ ብዬም ከእቅፏ ወጥቼ ጉንጮቿን ሳምኳቸው(በሀሳቤ ግን ምን አለበት እንደባለፈው ዞር ብላ ከንፈሮቿን በሳምኳቸው እያልኩ ነበር)። "ጠረንሽ ልቀቂኝ ልቀቂኝ አይልም" አልኳት እየተሽኮረመመች "እና ለምን ለቀቅሽኝ" ስትለኝ "በአንድ አፍ" ብዬ ድጋሜ አቀፍኳት እሷም መልሳ አቀፈችኝ ፣ ስሜቱ ደስ ሲል መሀል ላይ ያለውን ነገር በሙሉ አንስቼ በደንብ ጥብቅ አድርጌ ማቀፍ ፈለኩኝ "አሁንስ አይበቃንም" ስትለኝ ጭንቅላቴን እየነቀነኩ "እእ" ስላት ጥብቅ አርጋ አቅፋኝ አንገቴ ስር እየሳመችኝ "ይብቃን እንሂድ" ስትለኝ ከንፈሯ ከአንገቴ ስር ሲገባ በጃጉላር ቬኔ በኩል አርጎ ውስጤ ያሉትን ቃላቶቼንም ፣ ተግባሮቼንም የመጠጠው ይመስል የምላት ስለጠፋኝ ዝም ብዬ እንዳለቺኝ ለቀኳት (ነው ወይስ ማደንዘዣ ይሆን በከንፈሮቿ የሰጠችኝ እእ? እንጃልኝ!)። መኪናዋ ፊቷን አዙሯ ባቆመችበት በምስራቅ አቅጣጫ አድርጋ ሞተሯን አስነስታ እንጋልበው ጀመር ፤ እንደተለመደው ቆንጆ  ፣ በውይይት እና በመሽኮርመም የተዋሀደ ቀንን አሳልፈን ፅኑ የፕሮግራሙ መሪ ስለሆነች እና በቅድሚያ እዛ መገኘት ስላለባት አስር ተኩል አከባቢ ሄድን። በቦታው ስንደርስ ከፅኑ ጋር አብሮ ፕሮግራም ሚመራው ልጅ እና የክበቡ ፕሬዝደንት ብቻ ነበሩ ሰላም ካልኳቸው በኋላ ፅኑ ቦርሳዋን እንድይዝላት ሰታኝ እዛጋ ተቀመጪ በቃ መጣው ብላኝ ከነሱ ጋር ማውራት ጀመሩ እኔም ቦርሳዋን አጠገቤ ካለው ወንበር ላይ አስቀምጬ ቲክቶክ ስክሮል ማድረጌን ጀመርኩ ፣ ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ ሰዉ ይመጣ ጀመር ፣ ፅኑም ትንሽ ቆይታ መጣች እና አጠገቤ ቆሟ አጎንብሳ ስታወራኝ  ቦርሳዋን አንስቼ ወንበሩ ላይ እንድትቀመጥ ጋበዝኳት ፣ እሷም ከጎኔ ቁጭ ብላ ታወራኝ ጀመር ሰው በርከት ሲል ፕሮግራማቸውን ለመጀመር ተነስታ ሄደች እኔም ስገባ አዝዤ የነበረውን ውሀዬን እየተጎነጨው መታደም ጀመርኩኝ። "ሄይ አቢጉ እንዴት ነሽ? ይሄ ቦታ ሰው አለው" "አዎ አለው" ለማለት ቀና ስል ሊዮራ በፈገግታ ታጅባ አጠገቤ ቆማለች      ይቀጥላል... ✍ አቢጌል
106
5
አኩኩሉው ፍቅሬ         ምዕራፍ ሁለት ፦ ክፍል አራት ለመሰናበቻ ይሆነን ዘንድ ጉንጯን ስሜ ላቅፋት ስጠጋ እሷም ወደኔ ስትዞር ከንፈሯን ሳምኩት ከመደንገጤ የተነሳ የማደርገው ሁሉ ነው የጠፋኝ ማድረግ የቻልኩት ብቸኛ ነገር "ይቅርታ" ማለት ነበር ፣ ፅኑም "It's okay አስበሽበት ያረግሽው ነገር አይደለም" ስትለኝ በአዎንታ እራሴን ነቅንቄ ከመኪናዋ እየተጣደፍኩ ልወርድ ስል ፅኑ እጆቼን ይዛ "አረ ቀስ ወዴት ነው ሩጫው" አለችኝ ፤ እኔም የምለው ስለጠፋኝ ስቄ ዝም አልኩ ፅኑም ቀጠል አርጋ "መች ነው ቀጣይ ምንገናኘው" ስትለኝ ሀሙስ ጠዋት ፈተና ስላለኝ ከፈተና መልስ አብረን ምሳ በልተን በዛው Coffee time ለመሄድ ወስነን ተለያየን። ከመኪናዋ ወርጄ መጓዜን ጀመርኩ እሷም መኪናዋን እያሽከረከረች ሄደች ፣ ስለያት ልቤን ቅር አለው የሆነ በጣም ቅርቤ የሆነን ሰው ለረጅም አመታት እየተለየው ያለው ይመስል ከፋኝ ስለመሳሳማችን ሳስብ ደግሞ ትንሽ አፈር ብዬ ፈገግ አልኩና ጭንቅላቴን በአግራሞት ከግራ ወደ ቀኝ(ከቀኝ ወደ ግራ) ወዘወዝኩት ፤ ዶርም ገብቼም ትንሽ እንደቆየው ገብታ እንደሆን ብዬ ደወልኩላት አታነሳም ፤ መኪና እየነዳች ይሆናል ብዬ ለማሰብ ሞከርኩ ግን ሰፈሯን ነግራኛለች እዛ ለመድረስ ይሄን ያህል ጊዜ አይፈጅባትም። አንዱ ልቤ ምን ሆና ይሆን ብሎ ሲያስብ ቀናተኛው ልቤ ደግሞ በዚ ሰአት ሌላ ቦታ ሄዳስ ቢሆን ብሎ ያቃጥሩልኝ ጀመሩ ከዛ ደግሞ መለስ ብዬ ምን አገባኝ እልና ላለማሰብ እሞክራለሁ ፤ ውጭ መቆሙ ስለሰለቸኝ ወደ ዶርም ከመግባቴ በፊት ብዬ አንዴ ብደውልላትም አታነሳም በቃ ይቅርብኝ ብዬ ወደ ዶርሜ ሄድኩ ግን ልክ የዶርማችንን በር ስከፍት ደወለችልኝ ሰከንድ ሳላጠፋ አነሳሁላት "ምነው ሳይጠራ አነሳሽው ቆንጅት" አለችኝ እየሳቀች "ኦው ቆንጂት የሚለው ቃል ደስ ይላል" አልኳት እየሳኩ "ስለሆንሽ ነዋ ደስ ያለሽ" ስትለኝ መሽኮርመሜን ጀመርኩ "ተይ አታሽኮርምሚኝ አፍራለሁ" ብላት "ቀኑን ሙሉ እኔን ስታሽኮረምሚኝ ነበር አሁን ተራው የኔ ነው" ብላኝ Flirtatious የሆነ ወሬያችንን ስንጨርስ ስልክ ያላነሳችው ሻወር እየወሰደች ስለነበር ነግራኝ ወደ ሌላ ወሬያችን ቀጠልን ። እያወራን ደቂቃዎች አልፈው ሰአታት ተቆጠሩ ሁለት ሰአት ያህል ካወራን በኋላ ኢትዮ ቴሌኮም በቃቹ ብሎ ቢዘጋብንም ሁለተኛ ዙር ደውላልኝ ካቆምንበት ማውጋታችንን ቀጠልን ስድስት ሰአት ሊሆን ሲል ሲደክመን ቻው ተባብለን ተኛን። ጠዋት ስነሳ "Good morning lovely" የሚል ቴክስት ልካልኝ ነበር ፤ ፈገግ አልኩኝ ቀኔን ያበራችልኝ መሰለኝ እኔም በምላሼ "Good morning gorgeous" ብዬ ልኬላት ሽንት ቤት ገብቼ ከዛ ሻወር ልገባ ተነሳው ፣ የዛሬው እቅዴ ክላስ ስለሌለኝ ቁርሴን በልቼ ወደ ላይበራሪ መግባት ፣ ምሳ በልቼ ላይበራሪ መዋል ነው ማታም እንደዛው ማምሸት ነው። ሁለቱን ቀናት በእቅዴ መሰረት ምግብ እና  ጥናቴን እያከታተልኩ ነው ከፅኑም ጋር በደንብ እየተሽኮረማመንን ነው(ቃሉን እናንተ ድረሱበት መሽኮርመም + ማሽኮርመም = መሽኮረማመን 😁)። ሊዮራ በመሀል ሀሳቤ ላይ ብትመጣው አሁን ላይ ለፅኑ ያለኝ ስሜት አድጎአል። ሀሙስ አይደርስ የለ ደረሰ ፈተናዬ ጠዋት አራት ሰአት ስለነበር በጠዋት ፅኑ "የመልካም ፈተና እና የእንዴት አደርሽ" መልክት ልካልኝ ስለነበር የእሷን ቴክስት ብቻ መልሼ ስልኬን ከአጠገቤ አርቄ  Revise ማድረጌን ጀመርኩ ። ሻወር ወስጄ ስወጣ ሰአቱ ለስድስት ሀያ ጉዳይ ይላል ፣ ስልኬ ላይ ፅኑ ሁለቴ ደውላለች መልሼ ደወልኩላት ፤ ስልኩን አንስታ እየተናደደች ማውራት ጀመረች "ለምንድ ነው ስልክ ማታነሺው" ጮኸችብኝ "ይቅርታ ፅኑዬ ሻወር እየወሰድኩ ነበር" "ገና!" ብላ ጮኸችብኛና "ውይ አቢጌል አይሞላልሽም አ!? በራፍ ላይ እየጠበኩሽ ነው ቶሎ ውጪ" አለችኝ ጩኸቷ ሳይበርድ ንዴቷ ትክክል ነው እኔ እልል ያልኩ አርፋጅ ነኝ ግን ከዚ በኋላም በትንሹ ሰላሳ ደቂቃ ስለምቆይባት ፈራ ተባ እያልኩ "ኦው ፅኑዬ ይቅርታ ግን እቆይብሻለሁ በቃ አንቺ ሂጂና እኔ እመጣለሁ location share አርጊልኝ" አልኳት "አይሆንም እዚሁ እጠብቅሻለሁ ቶሎ ነይ ሀያ ደቂቃ ሰጥቼሻለሁ" "አይበቃኝም ፅኑ" "እሺ ሰላሳ ደቂቃ" "እሞክራለሁ" "አቢጌል ቶሎ በይ" "እሺ" ስልኩ ተዘጋ ፤ ከፈተና ስወጣ ደውዬላት ስለነበር እየመጣው ነው ስትለኝ በዚ ፍጥነት ምትደርስ ስላልመሰለኝ በጣም ተረጋግቼ ነበር ስዘጋጅ የነበረው አሁን ግን ጩኸቷን ስታቀልጥብኝ ከመቸኮሌ የቸነሳ የምይዝ የምጨብጠው ግራ ገባኝ አልጋዬ ላይ ስለብስ ሳወልቃቸው ፣ ሳማርጥ የቆየዋቸው ልብሶች ተደርድረዋል በተቻለኝ መጠን ቶሎ ለመውጣት እየሞከርኩ ነው ፣ ፀጉሬን አስተካክዬ ጫማዬን ለብሼ ስወጣ ሰአቱ 6:16 ይል ነበር ደንግጬ ደረጃውን መውረድ ጀመርኩ ፣ ደረጃውን ስወርድ ደረጃውን እየወጣች ያለች የአንዷ እንስት ሽቶ አፍንጫዬን ያውደው ጀመር ልጅቱም አልፋኝ ከሄደች በኋላ ወደ ኋላ ተመልሼ የወረድኩትን ደረጃ ወጣሁት።        ይቀጥላል.... ✍አቢጌል
93
6
በኢትዮጵያ ውስጥ የሥርዓተ-ፆታ ልዩነት፡ ይህ ትክክለኛ ቅርስ ነው እንጂ ከውጭ የመጣ አይደለም ክፍል ሰባት፡ በጋምቤላ የኑዌር ማኅበረሰብ "ሴት-ባሎች (Female Husbands)" በዚህ ተከታታይ ጽሑፋችን የመጨረሻ ክፍል፣ የኑዌር ሕዝብ ወደሚኖርበት ወደ ምዕራብ ኢትዮጵያ ወደ ጋምቤላ ክልል እንሄዳለን። እዚህም "ሴት-ባሎች" በመባል የሚታወቀውን ልዩ ባሕል እንመለከታለን። እነዚህ ሴቶች ልጆችን ለመውለድ ሲሉ ሌላ ሴት ሊያገቡ የሚችሉ፣ ነገር ግን እንደ ሴት መኖራቸውን የሚቀጥሉ ነበሩ። ጉዳዩ ስለ ፍቅር ወይም ዝንባሌ አልነበረም። ይልቁንም፣ ቤተሰቦች ልጆች እንዲኖራቸው እና ንብረት በወንዶች በኩል በሚመራው የትውልድ መስመር ውስጥ እንዲቀጥል ለማድረግ የተነደፈ ማኅበራዊ መንገድ ነበር። ይህንን ከክዌር (Queer) አንፃር ስንመለከት፣ "ሴት-ባል" የሚለው ባሕል ኑዌሮች ሥርዓተ-ፆታንና ግንኙነቶችን በጥብቅ በወንድ-ሴት ሕግጋት እንደማይመለከቱ ያረጋግጣል። ስለ "ሴት-ባል" ያለን ግንዛቤ የመጣው በ1930ዎቹ በኑዌር መካከል ይኖር ከነበረውና የዝምድናና የጋብቻ ልማዶቻቸውን በKinship and Marriage Among the Nuer (1951) በተሰኘው መጽሐፋቸው ከመዘገቡት ከብሪቲሽ የሰብአዊ ሳይንስ ተመራማሪ ኤድዋርድ ኢቫን ኢቫንስ-ፕሪቻርድ (Edward Evan Evans-Pritchard) ነው። "ሴት-ባሎች" እነማን ነበሩ? "ሴት-ባል" ማለት ለማኅበራዊ ወይም ሕጋዊ ምክንያቶች ሌላ ሴት የምታገባ ሴት ናት። ሁሉም ሁኔታዎች ተመሳሳይ አልነበሩም፦ አንዳንድ ሴቶች ልጅ መውለድ ባይችሉም፣ የቤተሰባቸው ስም እንዲቀጥል በጽኑ ይፈልጋሉ። ስለዚህም፣ ለ"ሴት-ባል" ስም ልጆች የምትሰጥ ሚስት ያገባሉ። ወንድ ልጅ በሌለባቸው ቤተሰቦች ውስጥ፣ የአባታቸውን የደም መስመር ለመጠበቅ ሚስት ያገባሉ። ሀብታም ሴቶች ደግሞ ይህን መንገድ በመጠቀም በማኅበራዊ ደረጃ ተጽዕኖአቸውን ለማሳደግ፣ ልክ እንደ ብዙ አጋሮች ያለው ወንድ፣ ቤተሰባቸውን ያስፋፉ ነበር። በሁሉም ሁኔታዎች፣ "ሴት-ባል" ለሚስት ቤተሰቦች የሙሽራ ዋጋ (Bride-price) ትከፍል ነበር። ይህንን ከክዌር እይታ ስንመለከት፣ "ሴት-ባል" የሚለው ባሕል ኑዌሮች የተለዋዋጭና ለልዩነት የበለጠ ተቀባይነት እንደነበራቸው እና ሥርዓተ-ፆታንና ግንኙነቶችን በጠባብ "ወንድ-ሴት" ደንቦች እንደማይመለከቱ ያሳያል። ለምን ጠፉ? ኢቫንስ-ፕሪቻርድ "ሴት-ባሎች" የጠፉበትን ምክንያት ፈጽሞ አልገለጹም። ጽሑፎቻቸው በ1930ዎቹ በኑዌር ማኅበረሰብ ውስጥ ባሕሉ እንዴት እንደሚሠራ ብቻ ነው ያሳዩት። እንደ ኢኮኖሚያዊ ለውጦች፣ ከክርስትና ወይም ከኢስላም የመጡ ሃይማኖታዊ ተጽዕኖዎች፣ እንዲሁም ዘመናዊ ሕጎች ወይም የከተማ ኑሮ የመሳሰሉት ምክንያቶች ሚና ተጫውተው ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን እርሳቸው አልመዘገቧቸውም። እነዚህ ምክንያቶች በእርግጥም በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ኡራኒንና አሽቲሜ ያሉ ተመሳሳይ ጉዳዮችን በመመልከት የተገመቱ ናቸው። ልናስታውሰውና ልናከብረው የሚገባ ቅርስ የ"ሴት-ባሎች" ታሪክ ባህላዊ የወንድ ሚናዎችን መውሰዳቸው ኢትዮጵያ ቤተሰብንና ሥርዓተ-ፆታን ለመቆጣጠር ብልህና ተለዋዋጭ መንገዶች እንደነበሯት ያሳያል፤ በእውነተኛ ፍላጎቶች ላይ ተመስርቶ የመቀየር ቦታም ነበረ። የሥርዓተ-ፆታ ልዩነት ከሩቅ የመጣ አይደለም፤ ይልቁንም በኑዌር ሕዝብ ዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ የተዋሐደና የሚታመንበት ነበር። ይህንን ታሪክ ማክበር ስለ ሥርዓተ-ፆታና ቤተሰብ ያሉ ሐሳቦች አሁን ሰዎች እንደሚያስቡት ፈጽሞ ጥብቅ አልነበሩም የሚለውን ያሳያል። ማንነትና የሰዎች ትስስር ከሌላ ቦታ የመጡ አይደሉም፤ ለዘመናት በአፍሪካ ሕይወት ውስጥ ኖረዋል። ምንም እንኳ የቅርብ ጊዜ ለውጦችና ሕጎች እንደነዚህ ያሉ ልማዶችን ያነሱ ቢያደርጉም፣ የእኛ ማንነት መደበኛ ክፍሎች አድርገን ልንመለከታቸው የሚገባን ቦታ መፍጠር አለብን። Gloria Victor June 2026
102
7
እነዚህን ታሪኮች ስሰማ የተሰማኝ ነገር ምን ያህል በተለያዩ ከተሞች እየኖርን የማመሳሰሉ ፍርሃት ፣ ስጋት ፣ ጥንቃቄ ፣ ፍላጎት እንዳለን እና ከምናስበው በላይ የምንመሳሰል መሆናችንን ነበር። ይህ ሁሉ የሚያስተምረን ብዬ የማስበው ምን ያህል አንዳችን ለአንዳችን ልናዝን ፣ ልንጠነቀቅ ልንተሳሰብ እንደሚገባን ነው። አንድነታችን ብርታታችን ነው። ከሁሉ በላይ የነበረው አንዱ ትልቅ ነገር #ራስንመቀበል ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ ነው። መልካም ንባብ እንደሚሆንላችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። የዲ - Yedi ለዚህ ድንቅ ስራ ተሳታፊ ስላደረጋችሁኝ አመሰግናለሁ 🥰 ከላይ ያለውን ሊንክ በመጠቀም መፅሐፉን ማንበብ ይችላሉ 🥰 #የእናንተድምፅየሁላችንነፃነት #ሰላምእናነፃነትለሁሉም
204
8
https://yedi.media/%e1%8b%a8%e1%8a%ad%e1%8d%8d%e1%88%88-%e1%88%83%e1%8c%88%e1%88%ad-%e1%8b%88%e1%8c%8d-2/
184
9
https://yedi.media/%e1%8b%a8%e1%8a%ad%e1%8d%8d%e1%88%88-%e1%88%83%e1%8c%88%e1%88%ad-%e1%8b%88%e1%8c%8d-2/
1
10
"አኩኩሉው ፍቅሬ"          ምዕራፍ ሁለት ፦ ክፍል ሶስት መልሷን ለመስማት ይበልጥ እየጓጓው ከመደገፊያዬ ቀና ብዬ ወደፊት እየተጠጋው እና አይኗን እያየው "እሺ ግን ስለ homosexuality ምን ታስቢያለሽ" አልኳት "እስኪ አንቺ ምን ታስቢያለሽ ያንቺን ንገሪኝ እና የኔን ስለነሱ ማስበውን ትክክለኛውን ነግርሻለሁ" አለችኝ ተግባሯ ፣ ቃላቶቿ እና አይኗ ውስጥ መልሱን ያገኘሁት ይመስለኛል በእርግጠኝነት ሌዝቢያን ወይም ባይሴክሽዋል መሆኗን ባልናገርም more than 70% ግን አረጋግጫለሁ ይሄም ከሷ ጋር open ሆኖ ለማውራት ነፃነት ሰቶኛል በዚ ላይ even ሆሞሴክሹዋል ባትሆን እንኳን open minded ስለሆነች ከዚ ከተደናቆረዎ ማህበረሰብ የተለየ እሳቤ እንዳላት እርግጠኛ ነኝ ፤ ዘና ብዬ ለመቀመጥ እየሞከርኩ "አልደግፋቸውም ፣ አልቃወማቸውም" አልኳት ያው እራሴን ላለማጋለጥ እየሞከርኩ ነው "እንዴት?" አለችኝ "የሁሉንም ሰው ፍላጎት አከብራለሁ ሴክሹዋሊቲ ደግሞ በተፈጥሮ እንጂ ተገዶ ሚሰጠን ነገር ነው ብዬ አላስብም ግን ደግሞ ይሄንን ሙሉ ለሙሉ አምኜ እንዳልቀበል ምንም እንኳን ሀይማኖተኛ ባልሆን ያደኩበት ሀይማኖቴ እና ማህበረሰቤ ጫና አሳድሮብኛል ቢሆንም ግን አንድ ሰው መቶ ጌ ነኝ ቢለኝ ለዛ ሰው ምንም አይነት የተለየ ጥላቻ አይኖረኝም"  በረጅሙ ተንፍሳ "በጣም ጥሩ እሺ እኔ ሌዝቢያን መሆኔን ብነግርሽ ምን ታደርጊያለሽ?" ብላ ጠየቀችኝ ልመልስላት ስዘጋጅ አስተናጋጁ ሞሂቶአችንን ይዞ መጣ ፤ አስተካክሎ ካስቀመጠልን በኋላም በመጣበት ተመለሰ ፣ አሁን ግን የሱ አረማመድ እና ውበት አላሳሰበኝም ግን አጠገባችን ቢቆይና የፅኑን ጥያቄ አስቤ ምመልስበት ሰአት ባገኝ ደስ ባለኝ ነበር ግን አልሆነም "እሺሺ ካቆምንበት እንቀጥል" አለችኝ እጄን አፌ ላይ አድርጌ እንደማሰብ አልኩና "እኔ አንቺነትሽ እንጂ ሴክሸዋሊትሽ matter አያረግልኝም" ብዬ መለስኩሏት በመልሴ እረፍት ያገኘች ይመስል በስሱ ተነፈሰች ፤ በአተነፋፈሷ አንዳች ነገር የነገረችኝ መሰለኝ "ይሄ ቆንጆ እይታ ነው" አለችኝ ፈገግ እያልኩ"አመሰግናለሁ እሺ በይ አሁን ያንቺን እይታ ንገሪኝ" አልኳት "እኔ እይታ ሳይሆን ኖሬ ያየሁትን እውነታ ነው ምነግርሽ" ሞሂቶዋን ተጎነጨች እና ማውራቷን ቀጠለች "በህይወቴ ውስጥ ጌ ካፕሎች አሉ" ስለተገረምኩ ድምፅ ሳላወጣ "ኦው" አልኩኝ  ፣ ፅኑ አይታኝ ስለነበር ቀጠል አድርጋ " አዎ አሉ" አለችኝ "በጣም ነው ምወዳቸው እና ማከብራቸው ፤ ስለ ሆሞሴክሽዋልቲ ትክክለኛነት ከጠየቅሽኝ እኔ ሴት ስለመሆኔ እርግጠኛ የሆነኩትን ያህል ስለነሱ ትክክለኛነት እርግጠኛ ነኝ" አለችኝ "ግሩም ነው ደስ ይላል" አልኳት እየሳኩ "ምን ያስቅሻል" አለችኝ ፈገግ እያለች "እኔ እና አንቺም ሌዝብያን ልንሆን እንደምንችል አስቤ" አልኳት ፤ እውነት ለመናገር ፅኑ "እንዴት?" ብላ እስክትጠይቀኝ ድረስ አስቤበት ያወራሁት ቃል ነበር ፤ ግን እሷ ስጠይቀኝ ምመልሰው ጠፋኝና አፌ ላይ የመጣውን ቃል "ሁለታችንም ጋር ያንን የሚመስል ተሞክሮዎች አሉ" አልኳት "የምን ተሞክሮ" "አንቺን ጓደኞችሽ ሌዝብያን ናት ብለው ጠርጥረውሽ ነበር እኔንም ጓደኞቼ ጠርጥረውኝ ነበር" ስላት የምርሽን ነው "አንቺን እንዴት ጠረጠሩሽ"አለችኝ በመገረም "ኦዎይ የኔ እናት በባዶ ህዴማ ይሄን አልነግርሽም ምሳ እንዘዝ እና እነግርሻለሁ" አልኳት ፤ እውነት ለመናገር በጣም እርቦኝ ስለነበር እና ታሪኩ እረጅም ስለሆነ ነው እንደዛ ያልኳት "እሺ እንዘዝና ምግቡ እስኪመጣ ትነግሪኛለሽ" ብላ ለአስተናጋጁ እንዲመጣ ምልክት ሰታው ሜኑ እንዲያመጣልን ነግራ መለሰችው እሱም ደቂቃ ሳይቆይ ሜኑ ይዞ መጣና ሁለታችንም ምንፈልገውን ለማዘዝ የምግብ ሜኑአችን ላይ ተተከልን ፤ ምግባችንን አዘን ፅኑ እንዳለችው ምግቡ እስኪመጣ የግቢ የመጀመሪያ አመት ተማሪ ሆኜ ሳለ ከአንዷ ቆንጅዬ እንስት ጋር ስለተወራብን ወሬ ማውራቴን ቀጠልን።(ይሄንን ታሪክ ማወቅ ከፈለጋቹ ከዚህ በፊት የፃፍኩትን "የህልሜ ንግስት" የተሰኘውን ኢ-ልቦለድ ማንበብ ትችላላቹ) ምሳችንን በልተን ፣ ቡናችንን ጠጥተን ፣ የልብ የልባችንን አውግተን ከዛ ሬስቶራንት ስንወጣ 10 ሰአት ሆኖ ነበር የመሸኛኛ እንዲሆነን Ice cream ልጋብዝሽ ብያት አንድ ማውቀው ቆንጆ Ice cream ቤት ስላለ እኔ መንገዱን እየጠቆምኳት መሪውን እሷ እየነዳች ጉዞአችንን ቀጠልን። ከፅኑ ጋር ወሬ አያልቅብንም ብዙ ሼር ምናረጋቸው ሀሳቦች አሉን ፤ አንዱን ርዕስ ስንጥል ሌላ እናነሳለን ፤ ፅኑ ማንበብ ምትወድ ሰው ነች ስለ አንድ ነገር ጠይቄያት አስር መልሶችን ትሰጠኛለች ፤ እኔ ማውቃቸውም ነገሮች ሲኖሩ እንወያያለን በመሀል የሀሳብ  መለያየቶች ይነሱ እና ክርክር እንጀምራለን ግን ሁሉንም በሚባል ደረጃ የእሷ ሀሳብ ሚዛን ይደፋብኝና ላለመሸነፍ ስል "ይሁንልሽ" እላታለሁ ፅኑም ይሄኛው ፀባዬ ገባት መሰለኝ "እሺ" ወይም "በደንብ አስቢበት" ብላኝ ትታው ወደሌላ ርዕስ እንሄዳለን። አንድ ሰአት ሊሆን አከባቢ ግቢ በር ላይ አድርሳኝ እዛው መኪና ውስጥ ዝም ተባብለን ቁጭ አልን፤ መለያየት የፈለግን አይመስልም  እኔም ወርጄ መሄድ አልፈለኩም እሷም ጥላኝ መሄዱን የፈለገች አይመስልም ዝምታውን ለመስበር ስል "ስለነበረን ግዜ አመሰግናለሁ ቆንጆ ቀን ነበር" አልኳት "እኔም አመሰግናለሁ ፤ ባንለያይ ደግሞ በጣም ቆንጆ ይሆን ነበር" አለችኝ እየሳቀች እኔም እየሳኩኝ "እና ይዘሽኝ ትጠፊ?" አልኳት "ቢፈቀድልኝማ ደስ ይለኝ ነበር" "የኔ እናት አንቺ ከሰሙሽ ብዙ ታወሪያለሽ ደህና እደሪልኝ" ብያት ጉንጯን ስሜ ላቅፋት ስጠጋ እሷም ወደኔ ስትዞር ከንፈሯን ሳምኩት...          ይቀጥላል.... ✍ አቢጌል #ሰላምእናነፃነትለሁሉም
218
11
"አኩኩሉው ፍቅሬ"          ምዕራፍ ሁለት ፦ ክፍል ሶስት መልሷን ለመስማት ይበልጥ እየጓጓው ከመደገፊያዬ ቀና ብዬ ወደፊት እየተጠጋው እና አይኗን እያየው "እሺ ግን ስለ homosexuality ምን ታስቢያለሽ" አልኳት "እስኪ አንቺ ምን ታስቢያለሽ ያንቺን ንገሪኝ እና የኔን ስለነሱ ማስበውን ትክክለኛውን ነግርሻለሁ" አለችኝ ተግባሯ ፣ ቃላቶቿ እና አይኗ ውስጥ መልሱን ያገኘሁት ይመስለኛል በእርግጠኝነት ሌዝቢያን ወይም ባይሴክሽዋል መሆኗን ባልናገርም more than 70% ግን አረጋግጫለሁ ይሄም ከሷ ጋር open ሆኖ ለማውራት ነፃነት ሰቶኛል በዚ ላይ even ሆሞሴክሹዋል ባትሆን እንኳን open minded ስለሆነች ከዚ ከተደናቆረዎ ማህበረሰብ የተለየ እሳቤ እንዳላት እርግጠኛ ነኝ ፤ ዘና ብዬ ለመቀመጥ እየሞከርኩ "አልደግፋቸውም ፣ አልቃወማቸውም" አልኳት ያው እራሴን ላለማጋለጥ እየሞከርኩ ነው "እንዴት?" አለችኝ "የሁሉንም ሰው ፍላጎት አከብራለሁ ሴክሹዋሊቲ ደግሞ በተፈጥሮ እንጂ ተገዶ ሚሰጠን ነገር ነው ብዬ አላስብም ግን ደግሞ ይሄንን ሙሉ ለሙሉ አምኜ እንዳልቀበል ምንም እንኳን ሀይማኖተኛ ባልሆን ያደኩበት ሀይማኖቴ እና ማህበረሰቤ ጫና አሳድሮብኛል ቢሆንም ግን አንድ ሰው መቶ ጌ ነኝ ቢለኝ ለዛ ሰው ምንም አይነት የተለየ ጥላቻ አይኖረኝም"  በረጅሙ ተንፍሳ "በጣም ጥሩ እሺ እኔ ሌዝቢያን መሆኔን ብነግርሽ ምን ታደርጊያለሽ?" ብላ ጠየቀችኝ ልመልስላት ስዘጋጅ አስተናጋጁ ሞሂቶአችንን ይዞ መጣ ፤ አስተካክሎ ካስቀመጠልን በኋላም በመጣበት ተመለሰ ፣ አሁን ግን የሱ አረማመድ እና ውበት አላሳሰበኝም ግን አጠገባችን ቢቆይና የፅኑን ጥያቄ አስቤ ምመልስበት ሰአት ባገኝ ደስ ባለኝ ነበር ግን አልሆነም "እሺሺ ካቆምንበት እንቀጥል" አለችኝ እጄን አፌ ላይ አድርጌ እንደማሰብ አልኩና "እኔ አንቺነትሽ እንጂ ሴክሸዋሊትሽ matter አያረግልኝም" ብዬ መለስኩሏት በመልሴ እረፍት ያገኘች ይመስል በስሱ ተነፈሰች ፤ በአተነፋፈሷ አንዳች ነገር የነገረችኝ መሰለኝ "ይሄ ቆንጆ እይታ ነው" አለችኝ ፈገግ እያልኩ"አመሰግናለሁ እሺ በይ አሁን ያንቺን እይታ ንገሪኝ" አልኳት "እኔ እይታ ሳይሆን ኖሬ ያየሁትን እውነታ ነው ምነግርሽ" ሞሂቶዋን ተጎነጨች እና ማውራቷን ቀጠለች "በህይወቴ ውስጥ ጌ ካፕሎች አሉ" ስለተገረምኩ ድምፅ ሳላወጣ "ኦው" አልኩኝ  ፣ ፅኑ አይታኝ ስለነበር ቀጠል አድርጋ " አዎ አሉ" አለችኝ "በጣም ነው ምወዳቸው እና ማከብራቸው ፤ ስለ ሆሞሴክሽዋልቲ ትክክለኛነት ከጠየቅሽኝ እኔ ሴት ስለመሆኔ እርግጠኛ የሆነኩትን ያህል ስለነሱ ትክክለኛነት እርግጠኛ ነኝ" አለችኝ "ግሩም ነው ደስ ይላል" አልኳት እየሳኩ "ምን ያስቅሻል" አለችኝ ፈገግ እያለች "እኔ እና አንቺም ሌዝብያን ልንሆን እንደምንችል አስቤ" አልኳት ፤ እውነት ለመናገር ፅኑ "እንዴት?" ብላ እስክትጠይቀኝ ድረስ አስቤበት ያወራሁት ቃል ነበር ፤ ግን እሷ ስጠይቀኝ ምመልሰው ጠፋኝና አፌ ላይ የመጣውን ቃል "ሁለታችንም ጋር ያንን የሚመስል ተሞክሮዎች አሉ" አልኳት "የምን ተሞክሮ" "አንቺን ጓደኞችሽ ሌዝብያን ናት ብለው ጠርጥረውሽ ነበር እኔንም ጓደኞቼ ጠርጥረውኝ ነበር" ስላት የምርሽን ነው "አንቺን እንዴት ጠረጠሩሽ"አለችኝ በመገረም "ኦዎይ የኔ እናት በባዶ ህዴማ ይሄን አልነግርሽም ምሳ እንዘዝ እና እነግርሻለሁ" አልኳት ፤ እውነት ለመናገር በጣም እርቦኝ ስለነበር እና ታሪኩ እረጅም ስለሆነ ነው እንደዛ ያልኳት "እሺ እንዘዝና ምግቡ እስኪመጣ ትነግሪኛለሽ" ብላ ለአስተናጋጁ እንዲመጣ ምልክት ሰታው ሜኑ እንዲያመጣልን ነግራ መለሰችው እሱም ደቂቃ ሳይቆይ ሜኑ ይዞ መጣና ሁለታችንም ምንፈልገውን ለማዘዝ የምግብ ሜኑአችን ላይ ተተከልን ፤ ምግባችንን አዘን ፅኑ እንዳለችው ምግቡ እስኪመጣ የግቢ የመጀመሪያ አመት ተማሪ ሆኜ ሳለ ከአንዷ ቆንጅዬ እንስት ጋር ስለተወራብን ወሬ ማውራቴን ቀጠልን።(ይሄንን ታሪክ ማወቅ ከፈለጋቹ ከዚህ በፊት የፃፍኩትን "የህልሜ ንግስት" የተሰኘውን ኢ-ልቦለድ ማንበብ ትችላላቹ) ምሳችንን በልተን ፣ ቡናችንን ጠጥተን ፣ የልብ የልባችንን አውግተን ከዛ ሬስቶራንት ስንወጣ 10 ሰአት ሆኖ ነበር የመሸኛኛ እንዲሆነን Ice cream ልጋብዝሽ ብያት አንድ ማውቀው ቆንጆ Ice cream ቤት ስላለ እኔ መንገዱን እየጠቆምኳት መሪውን እሷ እየነዳች ጉዞአችንን ቀጠልን። ከፅኑ ጋር ወሬ አያልቅብንም ብዙ ሼር ምናረጋቸው ሀሳቦች አሉን ፤ አንዱን ርዕስ ስንጥል ሌላ እናነሳለን ፤ ፅኑ ማንበብ ምትወድ ሰው ነች ስለ አንድ ነገር ጠይቄያት አስር መልሶችን ትሰጠኛለች ፤ እኔ ማውቃቸውም ነገሮች ሲኖሩ እንወያያለን በመሀል የሀሳብ  መለያየቶች ይነሱ እና ክርክር እንጀምራለን ግን ሁሉንም በሚባል ደረጃ የእሷ ሀሳብ ሚዛን ይደፋብኝና ላለመሸነፍ ስል "ይሁንልሽ" እላታለሁ ፅኑም ይሄኛው ፀባዬ ገባት መሰለኝ "እሺ" ወይም "በደንብ አስቢበት" ብላኝ ትታው ወደሌላ ርዕስ እንሄዳለን። አንድ ሰአት ሊሆን አከባቢ ግቢ በር ላይ አድርሳኝ እዛው መኪና ውስጥ ዝም ተባብለን ቁጭ አልን፤ መለያየት የፈለግን አይመስልም  እኔም ወርጄ መሄድ አልፈለኩም እሷም ጥላኝ መሄዱን የፈለገች አይመስልም ዝምታውን ለመስበር ስል "ስለነበረን ግዜ አመሰግናለሁ ቆንጆ ቀን ነበር" አልኳት "እኔም አመሰግናለሁ ፤ ባንለያይ ደግሞ በጣም ቆንጆ ይሆን ነበር" አለችኝ እየሳቀች እኔም እየሰመኩኝ "እና ይዘሽኝ ትጠፊ?" አልኳት "ቢፈቀድልኝማ ደስ ይለኝ ነበር" "የኔ እናት አንቺ ከሰሙሽ ብዙ ታወሪያለሽ ደህና እደሪልኝ" ብያት ጉንጯን ስሜ ላቅፋት ስጠጋ እሷም ወደኔ ስትዞር ከንፈሯን ሳምኩት...          ይቀጥላል.... ✍ አቢጌል
3
12
Today marks World Refugee Day! QE is proud to launch a special edition celebrating the Queer Ethiopian refugee community whil
Today marks World Refugee Day! QE is proud to launch a special edition celebrating the Queer Ethiopian refugee community while raising awareness about their experiences. https://queerethiopia.com/between-borders-and-identity/
187
13
"አኩኩሉው ፍቅሬ"           ምዕራፍ ሁለት ፦ ክፍል ሁለት ፅኑ "ተጫወቺ እንጂ" ብላ መኪናውን በአንድ እጇ እየነዳች በሌላኛው እጇ እጆቼን ያዘቻቸው ፤ የምይዝ የምጨብጠው ነበር የጠፋኝ ልቤ እኔን ጥላ በአፌ የወጣችም መሰለኝ እንደምንም እያማጥኩ እና እጆቿን እኔም መልሼ እየያዝኳቸው "እየተጫወትኩ ነው አንቺ ዝም አልሽ እንጂ" አልኳት "እኔማ መኪና እየነዳው ስለሆነ ነው" "እና መኪና ምትነጂው በእጅሽ እንጂ በአፍሽ ነው እንዴ" አልኳት እየሳኩ "እጄን ስትይዥው በምላሴም መንዳት ጀመርኩ መሰለኝ" አለችኝ ፈገግ እያለች ለካ የእጇ ልስላሴ ማርኮኝ እጆቿን እንደያዝኳቸው በዛው ቀርቻለው "ኦው ለካ እጅሽን ይዤዋለሁ" ብያት ለቀኳት "ብትይዣቸውም አይደብረኝም ነበር" አለችኝ አይኗን እያስለመለመች እያየችኝ "እኔም ደስ ይለኝ ነበር ግን ያንን ጋወን ለብሼ ሳልመረቅ መገልበጥ አልፈልግም" አልኳት እየሳኩ "አታስቢ ደርሰናል" ብላኝ ከአንድ ተለቅ ካለ ሬስቶራንት በራፍ መኪናዋን አቆመች "ኦው ዝም ያለ እና ደስ የሚል ቦታ ይመስላል" አልኳት ወደውጭ አንጋጥቼ እየተንጠራራው እያየው "አዎ ትወጂዋለሽ በጣም በይ ነይ ውረጂ" ብላኝ ወረድን ስራመድ ብዙ ጊዜ እንደማደርገው እጄን ኪሴ ውስጥ ከትቼ ከመኪናው ቦርሳዋን ይዛ እስከምትወርድ ጠበኳት እና ስትመጣ በአንዱ እጄ ቦርሳዋን ልቀበላት እጄን ስዘረጋላት በሚያሳዝን እና ደስ ባለው ፊት "Ow u r so sweet" ስትለኝ እኔም ይሄ ጉራዬ አለቀቀኝም እና እየሳኩኝ "I know" ስላት "ጉረኛ" ብላኝ እጆቿን ኪሴ ውስጥ ካኖርኩት እጄ ጋር እያቆላለፈች ወደ ሬስቶራንቱ ለመግባት መራመድ ጀመርን ፅኑ እረዘም ያለች ብትሆንም ከኔ በቁመት ማነሷ እና ምንም እንከን ማይወጣላት Fem ሴት መሆኗ ከኔ Soft masculinity energy ጋር ተዋህደው የሆነ ለየት ያለ Chemistry ፈጥረው ግርማ ሞገስ የሰጡን ይመስላል ፤ እውነቱን ለመናገር ሁለት ሴቶች እንደፈለጉት ቢቀራረቡ ትኩረት የመሳብ እድላቸው በጣም አነስተኛ ነው በተለይ ከወንዶች አንፃር እጅግ ትልቅ ነፃነት አለን ወደ ውስጥ ስንገባ ሬስቶራንቱ ከውጭ እንደሚታየው ውስጡም እጅግ ዝም ያለ እና የተዋበ ነው ፤ የተቀባው ነጭ ቀለምም ለቤቱ ብርሀንን ሰቶት ያፈካው ይመስላል ፤ ተቀምጠን ስለ ቤቱ ውበት እያወጋን ሳለን "እንኳን ደህና መጣቹ ፤ ምን ልታዘዝ!?" በሚል ድምፅ እና ደስ በሚል ፈገግታ የሱፍ ሰደርያ በነጭ ሸሚዝ የለበሰ ቆንጅዬ አስተናጋጅ እጆቹን ወደኋላ አጣምሮ ከወገቡ ጎንበስ ብሎ ተቀበለን ፤ አቤት ውበት! ውበት ያለው እኮ አስተናጋጆች ጋር ነው ከሴቱ ቢባል ከወንዱ አብዛኞቹ ቆንጆ ናቸው ፤ እኔም በልቤ "አሁን ምን አለበት ይሄ ሸበላ ጌ ቢሆንና ከሮቢ ጋር ባጋባው" ብዬ አሰብኩ(ብዙ ጊዜ ቆንጆ ወንድ ሳይ በአይምሮዬ ሚመጣ ሀሳብ ነው 😁)። ፅኑም "እንኳን ደህና ቆየኸን ለኔ ሌመን ሞሂቶ አምጣልኝ እና ምንበላውን ደግሞ አስበን እንነግርሀለን" አለችው በፈገግታ ታጅባ "እሺ ፤ ላንቺስ ምን ይምጣልሽ" ብሎ የቅድሙ ፈገግታው ሳይደበዝዝ ወደኔ ዞረ እውውይ የኔ ሸበላ ውበቱ ከቅድሙ እጅግ ጎልቶ ታየኝ ፤ ቀይ ወንዶች ደካማ ጎኔ ናቸው በጣም ይስቡኛል ይሄም ልጅ ቅላቱ ከውበቱ ጋር ተዳምሮ ማርኮኛል "እምም ለኔ ደግሞ ክላሲክ ሞሂቶ አምጣልኝ" በፈገግታ ታጅቦ "እሺ" ብሎን ሄደ ልክ ልጁ እንደተራመደ "እንዴት አባቱ ነው ሚያምረው በጌታ!" አልኳት ለፅኑ የልጁ አረማመድ ላይ እያፈጠትኩ "አዎ በጣም ቆንጅዬ ግን እኔ ብዙም የወንድ ልጅ ውበት አድናቂ አይደለሁም" አለችኝ ፈገግ እያለች "የሴቶችስ" አልኳት እየሳኩ የመገረም እና የአድናቆት ፊት እያሳየችኝ "እንዴዴ የነሱንማ ውበት አለማድነቅ አልችልም ፤ ባይሆን አንቺ የወንድ ልጅ ውበት በዚ ልክ ማድነቅሽ ገርሞኛል" አለችኝ "እኔ ቆንጆ ፍጥረታትን በሙሉ ማደንቅ ሰው ነኝ ግኔ ለምን ገረመሽ?"ብላት ትከሻዋን ሰበቅ እያረገች "እኔንጃ" አለችኝ "ባይሆን ከኔ ይልቅ ያንቺ ከወንድ ልጅ በላይ የሴትን ልጅ ውበት ማድነቅ ገርሞኛል" "በኔ አምሳል የተፈጠሩ ፍጡሮችን ውበት ማድነቄ ለምን ይገርምሻል" አለችኝ አይኔን ትኩር ብላ እያየች ፤ በርግጥ ሴት ልጅ እውነትም በሷ ሀምሳል የተሰራች ነው ሚመስለው I mean she is so gorgeous "ምን አልባት በማህበረሰብ ስላልተለመደ" አልኳት ወደ ኋላ ለጠጥ ብዬ ወንበሩን እየተደገፍኩ "ልክ ነሽ ግን እኔ ችግሩ አይታየኝም ፤ እንደውም ብዙ ጊዜ የሴትን ውበት አብዝቼ ከማድነቄ የተነሳ ጓደኞቼ የሆነ ጊዜ ላይ  ሌዝብያን ነሽ እንዴ ብለው ጠይቀውኛል" ብላ ሳቀች ፤ እኔም አብሬያት ሳኩኝ "እና ነሽ እንዴ!?" አልኳት እኔም ፈገግ እያልኩ እና መልሷን ለመስማት እየጓጓው "እመስላለው!?" ብላ ጥያቄዬን በጥያቄ መለሰችልኝ "እኔንጃ ያው Sexual orientationን በማየት ብቻ መለየት አይቻልም" አልኳት "እሱስ ልክ ነሽ ግን አይደለሁም" አለችኝ መልሷን ለመስማት ይበልጥ እየጓጓው ከመደገፊያዬ ቀና ብዬ ወደፊት እየተጠጋው እና አይኗን እያየው "እሺ ግን ስለ homosexuality ምን ታስቢያለሽ" አልኳት እሷም በአትኩሮት አይን አይኔን እያየች ወደፊት ጠጋ ብላ...       ይቀጥላል... ✍ አቢጌል
238
14
በኢትዮጵያ ውስጥ የሥርዓተ-ፆታ ልዩነት፡ ይህ ትክክለኛ ቅርስ ነው እንጂ ከውጭ የመጣ አይደለም ክፍል ሰባት፡ የኤርትራ "ዲያቮሌቲ (Diavoletti)" ይህ ጽሑፍ ወደ ኢትዮጵያ ጥልቅ የሥርዓተ-ፆታ ልዩነት ታሪክ ጉዞአችንን ይቀጥላል። ቀደም ሲል አሽቲሜን፣ ኡራኒንን፣ እንዲሁም ዋንደርወራድን አይተናል። አሁን ደግሞ ወደ ኤርትራ እየተጓዝን ነው፤ በ1900ዎቹ መጀመሪያ ላይ የተገኙ መረጃዎች ሌላ ብርቅዬ የሥርዓተ-ፆታ ልዩነት ያሳያሉ። እነርሱም "ዲያቮሌቲ" ተብለው ይጠሩ ነበር—ከሰፋሪ ወንዶች ጋር ግንኙነት የሚፈጥሩ ወጣት ወንዶች—በጣሊያናዊው ተመራማሪ ፓኦሎ አምብሮጌቲ (Paolo Ambrogetti) በ1900ዎቹ ውስጥ ተመዝግበዋል። ይህም የሥርዓተ-ፆታ ልዩነት ከውጭ የመጣ ወይም አዲስ ሳይሆን፣ የአፍሪካ ማኅበራዊ አደረጃጀት አካል እንደነበር ያረጋግጣል። "ዲያቮሌቲ" እነማን ነበሩ? አምብሮጌቲ በወቅቱ ዲያቮሌቲዎች በኤርትራ ማኅበረሰብ ውስጥ ልዩ ሚና የነበራቸው ወጣት ወንዶች እንደነበሩ ተመልክቷል። አብዛኞቹ በጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ፣ ከትልልቅ ወንዶች ጋር ግንኙነት የነበራቸው እና ይህም በአካባቢው መደበኛ ነበር። ግንኙነታቸው የተደበቀ አልነበረም፣ ምክንያቱም በቤተሰብ ዕውቅና ሥር ይካሄድ ነበር። መልክአቸው እንደ አሽቲሜ ወይም ዋንደርወራድ የተለየ አልነበረም፤ በዚያን ጊዜ እንደማንኛውም ወጣት ወንዶች ይመስሉ ነበር—በአለባበሳቸው ወይም በመልካቸው እነርሱን ለይቶ ማወቅ አይቻልም ነበር። "አሳዳጊዎች" (Patrons) በመባል የሚታወቁት ትልልቅ ወንዶች በአብዛኛው የጓደኝነት ምትክ ለ"ዲያቮሌቲ"ዎች እርዳታ ያደርጉ ነበር። አብዛኞቹ "ዲያቮሌቲዎች" እያደጉ ሲሄዱ ከአሳዳጊዎቻቸው ጋር የነበራቸውን ግንኙነት አቁመው ወደ ቀጥተኛ ትዳር ይገቡ ነበር። ሆኖም፣ ጥቂቶች በእድሜያቸው እየገፉ ሲሄዱም ግንኙነታቸውን ቀጥለዋል፤ ይህም ትስስሩ ከጥቅም ግንኙነት የላቀ፣ ስሜታዊ ጎንም እንደነበረው ያሳያል። አምብሮጌቲ 25 ዓመት የሆነ፣ ያገባ ቢሆንም ከአሳዳጊው ጋር ግንኙነቱን የቀጠለ አንድ "ዲያቮሌቲ" መኖሩን ጠቅሷል። ይህ የሚያሳየው አንዳንድ ግንኙነቶች ሁልጊዜ ጥቅማጥቅም ብቻ ሳይሆኑ፣ ስሜታዊ ትስስርም ይዘው እንደነበር ነው። እንዴት ጠፉ? ስለ አሽቲሜ፣ ኡራኒን እና ዋንደርወራድ ካጠናሁት በመነሳት—"ዲያቮሌቲዎች" የጠፉት በተደባለቀ ምክንያቶች እንደሆነ አምናለሁ። · የማኅበራዊ ደንቦች ጥብቅነት: ማኅበረሰቡ ወንድ ወይም ሴት መሆን ምን ማለት ነው በሚለው ሐሳብ ላይ ይበልጥ ጥብቅ የሆኑ አመለካከቶችን መከተል ጀመረ። የተለየ መሆን አስቸጋሪ እና ተቀባይነት የሌለው ሆነ። · የቤተሰብ ግፊት: ቤተሰቦች ወንዶቹን እንደ ጋብቻ እና መደበኛ ሥራ ባሉ "መደበኛ" በሚባሉ መንገዶች እንዲሄዱ ገፋፏቸው። ይህ ደግሞ ሕይወታቸውን ይበልጥ የግል እንዲሆን ያደረገ ሲሆን፣ ታሪኮቻቸው የመቀጠል ዕድል አነሰ። · የመረጃ እጥረት: በመጨረሻም፣ ማንም ሰው ስለእነርሱ መጻፍ ባለመቀጠሉ፣ እንደሌሎች ቡድኖች ሁሉ ታሪካቸው ተረሳ። መጥፋታቸው "ከተፈጥሮ ውጭ" ስለነበሩ አይደለም። የሆነው ማኅበረሰቡ ስለተለወጠ እና በግልጽ ለመኖር የሚያስችል ቦታ ስላልሰጣቸው ነው። ልናውቀው የሚገባ ቅርስ የ"ዲያቮሌቲ" ታሪክ አፍሪካ የሥርዓተ-ፆታ ልዩነትን እንደ እንግዳ ነገር ፈጽሞ አትመለከትም እንደነበር ያረጋግጣል። ይልቁንም "መደበኛ"፣ ተቀባይነት ያለው እና የሚከበር ነበር። "ዲያቮሌቲ"ን ማስታወስ ልዩነት የአፍሪካ ባህል ጥልቅና ትክክለኛ ክፍል እንደሆነ ያስታውሰናል፣ ከውጭ የመጣ ነገር አይደለም። Gloria Victor June 2026
240
15
https://open.substack.com/pub/climaxlgbtq/p/the-climax-douching-guide?utm_source=share&utm_medium=android&r=4utnvb
270
16
"አኩኩሉው ፍቅሬ"       ምዕራፍ ሁለት ፦ ክፍል አንድ ፀሀይዋ ከነ ዘር ማንዘሯ የወጣች ይመስላል ፣ አናቴ ላይ ወታ በቃጠሎ እየጨፈረችብኝ ነው «የማያውቁት ሀገር አይናፍቅም» ብዬ ሊዮራን ትቼ መሄዴ ልቤን ቅር ቢያሰኘውም  መንገዴን ወደ ፅናት አዙሬ እየተጓዝኩ ነው። ስልኬን በእጄ እንደያዝኩት ይነዝረኝ ጀመር ፣ ፅኑ እየደወለች ነው "ሄሎ ፅኑዬ" "ወዬ አቢጉ ቆየሽ እኮ" "ይቅርታ የተከበሩ እየመጣው ነው ደርሻለው" "እሺ ቶሎ በያ" "ይኸው ደርሻለው በራፋ ጋር ነኝ ፣ የቱ ጋር ነሽ" "በራፉ ጋር ስትደርሺ አይሻለሁ" "ደርሻለሁ ብዬ መዋሸት እንኳን አልቻልኩምኮ" አልኳት እየሳኩ "ሲጀምር ውሸት እንደማልወድ እያወቅሽ ለምን ትዋሺኛለሽ" ድምጿ ሲቀየርብኝ ታወቀኝ ፣ ውሸትን አምርራ ነው ምትጠላው በርግጥ እኔም ውሸት አልወድም ግን ብዙ ጊዜ አርፋጅ ስለሆነኩ እዚ ደርሻለሁ እያልኩ መዋሸቱን ተላምጄዋለሁ "እሺ በቃ አትኮሳተሪ ፣ ማርያምን አሁን በራፉ ጋር ነኝ" "ምንድ ነው የለበሽው?" "ነጭ ቲሸርት በቡኒ ሸሚዝ እና ሰማያዊ ጂንስ ሱሪ" "አየሁሽ አዎ ፣ ከፊት ለፊትሽ ቀይ Swift መኪና አትታይሽም?" "ትታየኛለች" "በቃ አስፓልቱን ተሻግረሽ ወደ መኪናዋ ነይ" በመኪና እንዳልገጭ ብዬ ግራ ቀኜን አይቼ አስፓልቱን በጥድፊያ ተሻግሬ ወደተባልኩት መኪና አቀናው ፣ መኪናዋ ጋር ስደርስ ፅኑ ከውስጥ ወርዳ ለረጅም አመት ሳይገናኙ እንደቆዩ እህትማማቾች ተቃቅፈን ሰላም ተባባልን ፤ እውነት ለመናገር ገና ሳቅፋት ነው ልቤ እርግት ብሎ ሰላሙን ያገኘው በቃ እቅፏ ማላውቀውን እረፍት ሰቶኝ ነበር እንደዛው ብንቀር ምኞቴም ነበር ግን መላቀቃችን ግድ ሆነና ተላቀቅን "አንቺ አርፋጅ" አለችኝ እየፈገገች "አርፋጅ መሆኔን እኮ ባለፈው ስናወራ ነግሬሻለሁ" "ደሞኮ አታፍሪም ታወሪያለሻ" አለችኝ አይን አይኔን እያየች "እውነታው እኮ ነው ባይሆን አንቺን የመሰለች ቆንጆ ብቻሽን ስላስጠበኩሽ ይቅርታ" "ምንም አይደለም ለቅጣት ግን ተዘጋጂ" "ንግስት ሆይ ሺ ቅጣት ቢቀጡኝ ለመቀጣት ዝግጁ ነኝ" አልኳት ፈገግ እያልኩ ፣ በውስጤ ግን ምናለበት ቅጣቱ ፊት ለፊቴ እራቁትሽን ቁሚ ወይ ከንፈሬን ሳሚኝ በሆነ ብዬ እየተመኘው ነው "ባንዳፍ ፣ ነይ ግቢ አሁን በዚ በፀሀይ አንቃጠል" ብላኝ ወደ መኪናዋ ጠቆመችኝ እኔም በመገረም "ያንቺ መኪና ነው እንዴ!?" ብዬ ጠየኳት "አዎ" "ኦው እና ባለፈው ያለአቅሜ ነዋ ካልከፈልኩ ብዬ ስታገል የነበረው" እየሳቀች "እኔ ግን አልከፋኝም ይኸው በዛ ምክንያት ድጋሜ ልጋብዝሽ ተገናኘን"አለችኝ "እኔ ግን ባንገባበዝም አንቺን ሁሌም ባገኝሽ ደስ ይለኛል" "እኔስ መች ጠልቼው" ብላኝ ወደ መኪናዋ ገባን ከፅኑ ጋር ኢነርጂያችን በጣም ተስማምቷል ፣ ምን እንደነካኝ ባላውቅም ከሷ ጋር በጣም ግልፅ እየሆንኩ ነው ፣ ሳሽኮረምማት እራሱ በነፃነት ነው በእርግጥ እሷም ትሽኮረመምልኝና መልሳ ታሽኮረምመኛለች ፤ በመሀላችን አንዳች ልዩ ነገር እየተፈጠረ እንዳለም እየተሰማኝ ነው። ውስጤ ሌዝቢያን እንደሆነች እየነገረኝ ሲሆን ተግባሯ ፣ አነጋገሯ እና አስተያየቷ ደግሞ እየመሰከሩልኝ ነው ። "እና ቆይ ደግሞ ባለመኪና ሆነሽ ስለምን ታክሲ መጠቀምን መረጥሽ?" "ሰሞኑን የመንዳት ሙድ ላይ አልነበርኩም ፣ አንዳንዴ መንዳት ያስጠላኛል" አለችኝ እየተንዘፈዘፈች እና እየተንገሸገሸች ፤ ለጉራ አልነበረም ያለችኝ እውነትም መንዳት ያስጠላት ትመስላለች "አቤት አቤት ልዩነታችንን አየሽልኝ አ ፣ አንቺ መንዳት ያስጠላሻል እኔ ደግሞ ብነዳ ብዬ ሁሌ እመኛለሁ" አልኳት ከንፈሬን እየመጠጥኩ ፣ እውነት ለመናገር ወደፊት የምወዳትን ላንድክሩዘሬን እንደምነዳ ስለማውቅ አሁን ላይ ብዙም አልጓጓም ግን መኪና በጣም ነው ምወደው "እና ምን ችግር አለው ትነጃለሻ" አለችኝ ትከሻዋን እየሰበቀች "በደስታ ነዋ" አልኳት እኔም እየሳኩ "በቃ ከሰሞኑ አንድ ቀን አለማምድሻለሁ ከዛን እኔ ሲደብረኝ አንቺ ትነጂልኛለሽ" "መንጃ ፍቃዱስ?" "ውስጥ ውስጡን አንቺ አስፓልት አስፓልቱን እኔ" ብላኝ ተሳሳቅን "የት ነው ግን ምንሄደው" ጠየኳት "ምነው እንዳላግድሽ ፈራሽ እንዴ" "አንቺን በመሰለች ቆንጆ መታገድኮ መመረቅ ነው ፣ እንደውም ካገድሽኝ የቅም ቅም አያቶቼ ምርቃት ለኔ እንደሰራ ነው ምቆጥረው" ስላት ከትከት ብላ ሳቀች "አቤት አቤት ምላሳም! እኔ እንደውም ሳስበው የቅም ቅም አያቶችሽን ምላስ በሙሉ የወሰድሽው ነው ሚመስለኝ" "ቆንጆ ቆንጆዎችን በቃላቶቼ ለማስደሰት እና ለመሳም ከሆነ አይደብረኝም" "እና እኔስ አይደርሰኝም" አለችኝ አይኔን እያየች ፣ አስተያየቷ የሆነ ነገር ከፊቴ ምታነብ ይመስላል "ላንቺማ ምላሴን ብቻ ሳይሆን ልቤንም ነው ምሰጥሽ" ብዬ ስመልስላት ሁለታችንም በዝምታ ተዋጥን ፤ እኔ እንኳን ዝም ያልኩት ከአፌ አምልጦኝ በወጣው ቃል ነው ፣ አፍ አውጥቼ ልሳምሽ ማለት እኮ ነው የቀረኝ እሷስ ግን ለምን ዝም አለች!? አስደብሬያት ይሆን? ልጠይቃት ወይስ ዝም ልበል እያልኩ ከራሴ ጋር ስጣላ "ተጫወቺ እንጂ" ብላኝ መኪናውን በአንድ እጇ እየነዳች በሌላኛው እጇ እጆቼን ያዘቻቸው ፤ የምይዝ የምጨብጠው ነበር የጠፋኝ ልቤ እኔን ጥላ በአፌ የወጣችም መሰለኝ       ይቀጥላል... ለታሪኩ አዲስ ከሆናቹ ምዕራፍ አንድን ማንበብ እንዳትረሱ! አመሰግናለሁ 🙏         ✍ አቢጌል ነኝ
277
17
​​#ምልስት These are the days I saw him... the man I will never date! ለመጀመሪያ ጊዜ ያየውት ከጽንኤል ጋር ሻይ ቡና ብለን ስንወጣ ነበር. I thought we had a moment when we stared at each other. ሲያየኝ ድንገጥ ያለ ይመስላል እኔም ሳየው ብደነግጥም ላላማስነቃት ሞክሪያለው ኮፍያ አድርጎ ነበር የሆነ ሰማያዊ ነገር ያለበት የስፖርት ጃኬት አድርጎ ነበር ጽኒ" wow" እንዳለ አስታውሳለሁ ያው መልሶ ቢክደውም የሆነ ሳየው የተሰማኝ ነገር ነበር። በሳምንቱ ጽንኤል ስለ ልጁ ረስቷል እኔ ግን አልረሳውም ነበር የሆነ ሰው መንገድ ላይ ከማረከኝ ከአዕምሮዬ አይጠፋም ሴሰኝነት ይሁን አይሁን አላቅም ምክንያቱም ካየዋቸው እና ከተመቹኝ ጋር ስለ ሩካቤ አስቤ አላቅም, but what if we had something real with someone I admire and am passionate about? የሚል ጥማት እንጂ ስለዚ ያየውትን እና ውስጤ የገባን ሰው አልረሳም ለነገሩ ሰው ጭራሽ አልረሳም ስምም እንደዛው አሁን ሳረጅ  እንደሰነፍኩት አይደለም ልቤ እነሱ ጋራ የለም ለዛ ይሆናል እኔነቴ ከጠፋ ቆይቻለሁ። ይህን ሰው ሁለተኛ ጊዜ ያየውት ቀኑን አላስታሳውስም ወይ ምን አድርጌ ከየት እየተመለስኩ እንደነበር አላቅም 81 ባጃጅ ውስጥ ተቿክዬ ገባው መሽቶ ነበር ጠጋ ብዬ ሌላ ሰው እስኪገባ ስጠብቅ በተቀመጥኩበት ባጃጅ በኩል አንድ ሰው አለፈ ጠረኑ ደስ ይላል ወዲያው አወኩት እሱ ነበር ከላይ ወይንጠጅ የሚመስል ሹራብ ለብሷል ከታች ነጭ ስስራይፕ ያለው ሱሩ(የሱፉ ሱሪ) አድርጓል እጁን ኪሱ ከቶ እየሄደ ነበር ስፓርኛ አቋም አለው ቸስቱም ደስ ይላል፥ በልብስ ውስጥ ሲታይ። ሶስተኛ ጊዜ ሳየው ከሀዋሳ እየተመለስኩ ነበር ታንቶስቲና አከባቢ እንደደረስን ሰው ለማውረድ ሲቆም ከመኪናው በስተግራ በኩል ቁልቁል ሲወርድ ተመለከትኩት የለበሰውን ልብስ አላስታሳውስም። አራተኛ ጊዜ ያየውት አቦስቶ ነው ዛሬ ለብሶ የነበረውን ጥቁር ጃኬት አድርጓል ጥቁር ሱሪ በቦታው ላይ ውርውር እንል ከነበርን ሁሉ ዘንጦ የሚታየው እሱ ነው ያምር ነበር ባየውት ቁጥር ለአለባበሱ ትኩረት የሚሰጥ እንደሆነ ተረድቻለው። He must, because he is pretty, and pretty guys must ራሳቸውን ማሳመር ። ዛሬ ሳየው መሽቶ ነበር እሱ መሆኑን አላወኩም ለአንድ ጓደኛዬ ወደ እሱ ጠቁሜ ይኸውልህ ይሃ በጣም ቆንጆ ነው አቋሙ ብትል ደስ ይላል ቀረብ ስል እና ትንሽ ዘወር ሲል እሱ ነው ጥቁር ጃኬት በፈዛዛ ጎመኔ ካኪ ሱሪ አድርጓል He just looks pretty. I didn't even see his face at first, but his energy pulled me toward him. I don't need to see someone's face to feel attracted; sometimes I just feel attracted to them even if I am walking behind them. I don't know what this means, but when I see him, I get sad and happy at the same time. ለጓጀኛዬም ከዚ በፊት ስለነገርኩት ላስታውሰው ሞከርኩ እሱ ጭራሽ ረስቷል ሰው ይረሳል እኔ ግን አልረሳም ባጃጅ እየጠበቀ ወዲ ወዲያ ይላል ብቻዬን ብሆን እስኪሳፈር ቆሜ ባየውት ከጓደኞቼ ስለይ የለም ሄዷል። የማላገኘው ሰው ነው። አሁን ባለውበት ሰዓት ፍቅረኛ እንደማያስፈልገኝ አስረግጬ አቃለሁ ግን I can't stop wanting someone's companionship, such a deep connection and intimacy that one gets from a friend and a lover. What I want in all this admiration of young men is not sex or something lustful; it's something different. I want to feel welcomed in a pretty young man's arms with love. I want to feel that I can also be as astonishing as they are to me. I want to feel wanted, desired, and loved, and for them to want my company as much as I want theirs. Those people whom I am attracted to are, or might be, out of my league in the context of sexuality, but that is not necessarily the case. I think I have a belief that says I am not good enough for such people who are pretty, sexy, and beautiful. I truly wish to have coffee with this man. Whenever I see him, he is always alone. He seems ጭምት and introverted, ሰው የማይረዳው ይመስለኛል. When I see him, I think he is cool, wise, content, and unhurried. But that contentment is not necessarily about his surroundings. He might not even love the way he is living iko, but his core seems still. My inner self is not content or at rest. I want to share what he has inside with what I have inside. @2015 | የተፃፈ ሻሸመኔ #ሰላምእናነፃነትለሁሉም #የእናንተድምፅየሁላችንነፃነት #የማይረሱ @mesobinitiative
319
18
ከዚ በፊት እዚህ Page ላይ ስለቀው የቆየሁት "አኩኩሉው ፍቅሬ" የተሰኘው የሳፎ(የሌዝቢያን) ተከታታይ የፍቅር ታሪክ ምዕራፍ ሁለት ከእሮብ አጀምሮ ይለቀቃል ፤ ይሄንን ድንቅ የፍቅር ታሪክ በኩራት
ከዚ በፊት እዚህ Page ላይ ስለቀው የቆየሁት "አኩኩሉው ፍቅሬ" የተሰኘው የሳፎ(የሌዝቢያን) ተከታታይ የፍቅር ታሪክ ምዕራፍ ሁለት ከእሮብ አጀምሮ ይለቀቃል ፤ ይሄንን ድንቅ የፍቅር ታሪክ በኩራት ወራችን ላይ ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ!?😊 እስከዛ ድረስ ያላነበባችሁት ምዕራፍ አንድ ፣ ክፍል አንድን ከላይ አታች ስላረኩላቹ አንብቡት 🙏 ወይም እዚሁ ቻናል ላይ "አኩኩሉው ፍቅሬ" ብላቹ  Search ብታረጉት ሁሉንም ክፍል ታገኙታላቹ(6 ክፍል ነው ያለው) 😊 መልካም ንባብ መልካም የኩራት ወር 🌈 #ሰላምእናነፃነትለሁሉም
372
19
እስኪ አድነኝ ሁነኝ ረዴት ከጠፋውበት ከተደበኩበት ፈልገህ አግኝተህ አባብለህ አስታመህ ሰው አድርገኝ ፍቅርን መግበህ #ሰላምእናነፃነትለሁሉም #የእናንተድምፅየሁላችንነፃነት
እስኪ አድነኝ ሁነኝ ረዴት ከጠፋውበት ከተደበኩበት ፈልገህ አግኝተህ አባብለህ አስታመህ ሰው አድርገኝ ፍቅርን መግበህ #ሰላምእናነፃነትለሁሉም #የእናንተድምፅየሁላችንነፃነት
385
20
እራስን መውደድ ብልህነት ነው!! ወረቀት ሲመረት ነጭ ነው ፣ ሲፃፍበት የተፃፈበትን ቀለም ይይዛል ፤ ወረቀት ምንም ብንፅፍበት ወረቀትነቱን አይተውም ይልቁንስ ባዶ ወረቀት ከመሆን አልፎ እውቀትን ያዝላል ፤ ነገር ግን ወረቀት ስራውን እና እራሱን ጥሎ ቢቃጠል ወይ ቢቀደድ ዋጋውን ያጣል ፣ ጥቅም የለውም እንደውም አመድ ወይ ቁርጥራጭ ቆሻሻ ሆኖ አከባቢያችንን እንዳያበላሽ ከቆሻሻ ጋር ይጣላል።(አንቺ ሴት ምንድ ነው ምትዘላብጂው እንዳትሉኝ!? 😁) ምን ልላቹ ፈልጌ ነው!? 😊 እራሳችሁን ስትወዱ እና በተዘጋጀላቹ ቦታ ስትገኙ ልክ እንደዚ ወረቀት እራሳችሁንም ሌሎችንም ትጠቅማላቹ ‟አይ እምቢየው አሻፈረኝ” ካላቹ ግን ተቃጥላቹ እና ስሜታቹ ተሰባብሮ የማይሆን መንገድ ላይ እራሳችሁን ታገኛላቹ!!  ስለሆነም እራሳችሁን ውደዱ ፣ ቦታችሁን አትሳቱ ፤ እራስን መውደድ Selfish መሆን ሳይሆን ብልህነት ነው ፤ አስታውሱ እናንተ ከሌላቹ የለፋችሁለት እና እራሳችሁን ያጣቹለት ነገርም የለም ፣ ሁሉም ይጠፋል!!😊 በሉ በቃ ከመሸ አላዝጋችሁም ደህና እደሩልኝ 🙏 #ሰላምእናነፃነትለሁሉም
405