4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች
እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች ቻናላችን በሰላም መጣቹ እሄ ቻናል ያላወቀቹትን አስገራሚ ነገር በቪድዮ አልያም በፎቶ እና በፅሁፍ የምታገኙበት፣ የተለያዩ አስቂኝ የሆኑ አስገራሚ ነገሮች የምታገኙበትና እውቀትን የምትጨብጡበት ቻናል ነው። ለማስታወቂያ ስራ - @Marketing_team433
Показати більше📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу 4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች
Канал 4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች (@amazing_fact_433) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 100 099 підписників, посідаючи 125 місце в категорії Факти та 324 місце у регіоні Ефіопія.
📊 Показники аудиторії та динаміка
З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 100 099 підписників.
За останніми даними від 05 вересня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на 477, а за останні 24 години на -106, загальне охоплення залишається високим.
- Статус верифікації: Не верифікований
- Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 12.27%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 9.40% реакцій від загальної кількості підписників.
- Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 12 281 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 9 410 переглядів.
- Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 225.
📝 Опис та контентна політика
Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
“እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች ቻናላችን በሰላም መጣቹ
እሄ ቻናል ያላወቀቹትን አስገራሚ ነገር በቪድዮ አልያም በፎቶ እና በፅሁፍ የምታገኙበት፣ የተለያዩ አስቂኝ የሆኑ አስገራሚ ነገሮች የምታገኙበትና እውቀትን የምትጨብጡበት ቻናል ነው።
ለማስታወቂያ ስራ - @Marketing_team433”
Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 06 вересня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Факти.
Триває завантаження даних...
| Дата | Залучення підписників | Згадування | Канали | |
| 05 вересня | 0 | |||
| 04 вересня | 0 | |||
| 03 вересня | 0 | |||
| 02 вересня | 0 | |||
| 01 вересня | 0 |
| 2 | 🫡ጅቦች ከኋላ እየተንቀሳቀሱ፤ ኳስ ሲጫወቱ የታዩት ታዳጊዎች ምስል በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኑ😁
በአንድ ክፍት የሳር ሜዳ ላይ ታዳጊዎች ዘና ብለው ኳስ ሲጫወቱ፣ ከበስተጀርባቸው ጥቂት ሜትሮች ራቅ ብለው የዱር አራዊት የሆኑት ጅቦች በነፃነት ሲንቀሳቀሱ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል (ቪዲዮ) በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።
ታዳጊዎቹ ከአራዊቱ ሊሰነዘር የሚችልን ስጋት ወይም ፍርሃት ሳይታይባቸው፣ ይልቁንም እየሳቁና እየተጫወቱ ኳስ ሲቀባበሉ የሚታዩበት ይህ አጋጣሚ ለተመልካቾች አስገራሚና አዝናኝ ሆኗል። ጅቦቹም ቢሆኑ በታዳጊዎቹ ጨዋታ ላይ ምንም አይነት የጥቃት እንቅስቃሴ ሳያሳዩ እንደ ታዛቢ በመስኩ ዳርቻ ሲዘዋወሩ ይታያሉ።
በሰውና በዱር አራዊት መካከል ያለውን ያልተለመደ የልምድና የትስስር ሁኔታ የሚያሳየው ይህ ምስል፣ በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ «የታዳጊዎቹ ድፍረት» እና «የሁኔታው አዝናኝነት» በሚል ሰፊ መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል። | 5 236 |
| 3 | 👣👌ገራሚ የፍልስፍና ቻናል ልጋብዛችሁፍልስፍናን ከኛ ጋር ⚱ | 4 625 |
| 4 | ሰሞኑን በቻይና ኔፓል ድንበር ተከስቶ በነበረው አስከፊ የጎርፍ አደጋ ምክንያት ወደ 40 km የአስፓልት መንገድ ከጥቅም ውጭ ሆኗል ።
.....
በአንዳንድ ቦታዎች ላይ መንገዶቹ ጭቃማው ጎርፍ ትቶት በሄደው የአፈር ደለልና የድንጋይ ክምር የተሸፈኑ ሲሆን ፡ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ደግሞ ፡ ሀይለኛው ጎርፍ ብዙ ኪሎሜትር የሚሆነውን የአስፓልት መንገድ እንደ ምንጣፍ ከስሩ ጠቅልሎ ወስዶት የሚታየው ከአስፓልቱ ስር የነበረው አፈር ነው ።
አስፓልት እንደምንጣፍ ጠቅልሎ የሚወስድ ጎርፍ !
....
ይህ አደጋ ከተከሰተ በኋላ የቻይና መንግስት በተለይ በድንበር አካባቢ የሚገኙትን የተበላሹ መንገዶች የመጠገን ስራ የጀመረው አደጋው ከተከሰተ ከሶስት ቀናት በኋላ ወዲያውኑ ነው ።
....
በዚህም የጥገና ስራ እስካሁን ስድስት መቶ ሜትር የሚሆነውን መንገድ ጠርገው እና ለትራንስፖርት ምቹ አድርገው ሰብአዊ እርዳታ መድረስ እንዲችል ቀንና ለሊት እየሰሩ ነው ።
....
ይህ በህይወት የተረፉ ሰወችን ከመፈለጉ ስራ ጎን ለጎን እየተካሄደ የሚገኘው የመንገድ ጥገና ቀን ብቻ አይደለም ለሊትም ቀጥሏል ።
እርግጥ በአካባቢው የነበረው የኤሌትሪክ መሰረተ ልማት ሙሉ በሙሉ ወድሟል ። እና ይህ የህይወት አድንና የመንገድ ጥገና እንዴት በለሊትም ይቀጥላል ?
....
ቻይና ሰሞኑን በዚህ አካባቢ ለሊቱን ወደቀን ለመቀየር እየተጠቀመችበት ያለው መብራት Tethered illumination drones ይባላል ።
እነዚህ በአየር ላይ ተንሳፋፊ ፓውዛ ድሮኖች በሺህ የሚቆጠር LED መብራቶች የተገጠሙላቸው ሲሆን ፡ ከሰላሳ እስከ ሀምሳ ሜትር በሚሆን የኤሌትሪክ ገመድ በምድር ላይ ካለው ጄኔሬተር ጋር ይያያዙና ከዛ የሚያገኙትን የኤሌትሪክ ሀይል በመጠቀም በአንድ ቦታ ቆመው ለለሊቱን ሙሉ ሀይለኛ ብርሀን መስጠት የሚችሉ ናቸው ።
እና ቻይና በሰሞኑ የተፈጥሮ አደጋ ምክንያት የጠፉ ሰወችን እየፈለገች በጎንም የተበላሸውን መንገድ በለሊትም ጭምር መጠገን የጀመረችው በነዚህ ድሮኖች ነው ።
እዛ ፀሀይ 24 ሰአት አትጠልቅም ። | 6 645 |
| 5 | UFC PARIS ተጀምሯል 🔥😱
በ @MMA_433 ቻነላችን በቀጥታ ይከታተላሉ
@Bisrat_sport_433et @Bisrat_sport_433et | 4 653 |
| 6 | ሎሎ ጆንስ
...........
" ትዳር መያዝ እና ልጆች መውለድ የአመታት ህልሜ ነው ። ዘወትር እያነባሁ ፈጣሪ ትዳር እንዲሰጠኝ እለምነዋለሁ ፡ የኔ የሆነውን ሰው ስጠኝ ፡ ወይም ትዳር የሚባለው ነገር ከላይ ያልተጻፈልኝ ከሆነ ፡ ከውስጤ አውጣልኝ እላለሁ ። ሆኖም እድሜዬ እየገፋ በመጣ ቁጥር ይበልጥ ስለትዳር አስባለሁ. .. ይበልጥ ትዳርን እፈልጋለሁ ፡ እና .. የራሴ የሆኑ ልጆች ፡ የተባረከ ባል እና ደስ የሚል ቤተሰብ እንዲኖረኝ እንደተመኘሁ ይኸው አለሁ "
...........
ሎሎ ጆንስ. . ይህ ስም በአሜሪካውያን ዘንድ የጀግና አትሌት ስም ነው ። ሎሎ በኦሎምፒክ መንደር ፡ በሀገር ውስጥና በአለም አቀፍ የአትሌቲክስ መድረኮች የሀገሯን ባንዲራ ከፍ አድርጋለች ። የነሀስና የብሩን ሜዳልያ ሳንቆጥረው ፡ ከሀያ በላይ የወርቅ ሜዳልያዎች ፡ በአንገቷ ላይ አጥልቃለች ነገር ግን ለአመታት ባለፈችበት የአትሌትነት ህይወቷ ደስተኛ ብትሆንም ፡ የምትመኘውን የቤተሰብ ህይወት ለመመስረት ባለመቻሏ እያዘነች ነው ።
......
በፊት በፊት በፍቅር የሚፈልጓት ወንዶች ቀርበው ያናግሯት ነበር ፡ ነገር ግን በአንድ ወቅት በአንድ ቴሌቪዥን ቀርባ ቃለመጠይቅ ካደረገች በኋላ ፡ በፍቅር ሊቀርቧት የሚሞክሩ ወንዶች ራቋት ። ከዛን ጊዜ በኋላ ቀርቦ እንኳን ለፍቅር የሚጠይቃት ሰው ጠፋ ።
.............
በዛ ቴሌቪዥን ቀርባ ምን ተናገረች ?
............
ሎሎ ጆንስ በአንድ ወቅት ለኢንተርቪው ቀርባ ፡ ጋዜጠኛው ፍቅረኛ አለሽ ወይ ብሎ ይጠይቃታል ፡ ሎላ ፡ እኔ ፍቅረኛ የምይዘው የማገባውን ሰው ብቻ ነው እስከዛ በዚህ ህይወት ውስጥ ማለፍ አልፈልግም ስትል መለሰች ።
ጋዜጠኛው በመገረም ጥያቄውን ቀጠለ
አሁን 30 አመትሽ ነው እና እስካሁን ቦይፍሬንድ ይዘሽ አታውቂም ?
አዎ አላውቅም
ሴክስ አርገሽስ ታውቂያለሽ ?
በፍፁም ፡ አድርጌ አላውቅም ፡ እኔ ሴክስ የማደርገው ሳገባ ነው ፡ ክብረንፅህናዬ ለባሌ የምሰጠው ስጦታ ነው ። ስትል ነበር የመለሰችው ። አሁን በቅርቡ አድርጋ በነበረው ኢንተርቪው ግን ፡ በዛን ወቅት ይህን መናገር አልነበረብኝም ። እንደዛ ብዬ ወንዶችን ከሚሸሹኝ ፡ የውስጤን በውስጤ ይዤ ፡ ለፍቅር ቀርበውኝ ስንግባባ ፡ ቀስ እያልኩ ማስረዳት እችል ነበር ። አሁን ግን ይህን እድልም አጥቻለሁ ፡ ማንም በፍቅር አይቀርበኝም ምክንያቱም ከጋብቻ በፊት ወሲብ እንደማላደርግ ስለተናገርኩ ፡ ይሄ ጉዳይ የወንዶቹን ፍላጎት ቀንሶታል ብላለች ።
........
ይህ ጉዳይ በተለይ በኛ ሀገር ( ኢትዮጵያዊ ) ቢሰማው ግራ ሊያጋባው ይችላል ፡ ምክንያቱም በኛ ሀገር ቨርጂኒቲ ማለት ባብዛኛው ሰዎች ዘንድ የክብር መግለጫ የጨዋነት መለኪያ ተደርጎ የሚወሰድ ነገር ነው ። በነሎላ ጆንስ ሀገር ደግሞ ከላይ እንደሰማነው ነው ።
.......
የሎሎ ጆንስ ጉዳይ አላበቃም ። ከሶስት አመት በፊት አርባኛ አመት ሊሞላት አስር ቀን ሲቀረው እንቁላል የሚያመርተው የሰውነቷ ክፍል በእድሜ ምክንያት ስራ ከማቆሙ በፊት ወደሆስፒታል ሄዳ የዘር እንቁላሏን አስቀምጣለች ። እና የዛን እለት እያለቀሰች ፡ ከዛሬ ነገ ባሌን አግኝቼ እንወልዳለን ብዬ ስጠብቅ ነበር ፡ ካሁን በኋላ ግን ዘሬን እዚህ ሳላስቀምጥ እንቁላል ማኩረት ባቆም ቁጭቱን አልችለውምና ይህን አድርጌያለሁ ። በርግጠኝነት እስካሁን የቆየው ባሌ አንድ ቀን ሲመጣ ፡ እድሜዬ ገፍቶ ቢሆን እንኳን እዚህ ያለውን ተጠቅመን የራሳችን ልጅ ይኖረናል ብላለች ።
......
አሁን ላይ ወደሁለት ሚሊየን ዶላር የተጣራ ሀብት ያላት ሎሎ ጆንስ በቅርቡ ከስፖርቱ አለም ተሰናብታ ፡ ተያያዥ በሆኑ ቢዝነሶች ላይ ተሰማርታ እየሰራች ትገኛለች
Wassihun tesfaye | 6 802 |
| 7 | በትዳራቸው አምስተኛ ዓመት ላይ ኤሚ በድንገት ትሰወራለች። ከዛ ግን ቤቱ ውስጥ የእግር አሻራና የደም ምልክቶች ይታያሉ። ፖሊሶች ባሏን ኒክን መጠርጠር ይጀምራሉ። የቴሌቪዥን ጣቢያዎችና ጋዜጦችም ኒክ እንደገደላት አድርገው ይዘግባሉ። ነገር ግን እውነቱ ፖሊሶች ከሚገምቱት በላይ እጅግ የተወሳሰበና አስፈሪ ነው።አንብባችሁ እስክጨርሱት ድረስ በጥርጣሬና በጭንቀት የሚይዘው Gone Girl የተሰኘው አስፈሪ መጽሐፍ በአማርኛ ተለቋል(በPdf)
👇👇
https://t.me/Bemnet_Library/7376
https://t.me/Bemnet_Library/7376 | 92 |
| 8 | ✅በአለም ብቸኛው ጥይት የማይበሳው ቆዳ ያለው እንስሳ Pangolin የተሰኘው የዱር እንስሳ ነው፡፡
በሀገራችን ኢትዮጵያም Ground Pangolin የተሰኘው የዚሁ እንስሳ ዝርያ እንዳለ ይታመናል
@amazing_fact_433
@amazing_fact_433 | 10 334 |
| 9 | ✅በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው መፅሀፍ በአማርኛ Pdf ተለቀቀ ዳርክ_ሳይኮሎጂ
👍 ይሄ #ዳርክ_ሳይኮሎጂ የተሰኘው መጽሐፍ ማንም እንደፈለገ እንዳይጫወትብህ የሚረዳ አስተሳሰብህን የሚቀይርና በሕይወትህ እንዴት በጥበብ መጫወት እንዳለብህ የሚያስተምር እጅግ ምርጥ መጽሐፍ ነው።
አሁኑኑ ያንብቡ
🌐https://t.me/Enmare1988/16655
🌐https://t.me/Enmare1988/16655 | 6 877 |
| 10 | 🌟 በሲነስቴዢያ (Synesthesia) የሚታወቁ የታወቁ ዓለም አቀፍ ሰዎች፦
ይህ አእምሮአዊ ስጦታ ያላቸው ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የፈጠራ ችሎታ (Creativity) አላቸው፦
🎼 ቢሊ ኢሊሽ (Billie Eilish)፦ ዘፈኖቿን የምትጽፈውና የምታዘጋጀው በሙዚቃው ውስጥ የምታያቸውን ቀለሞችና ቅርጾች መሠረት በማድረግ ነው።
🎼 ካንዬ ዌስት (Kanye West)፦ ድምፆችን ወደ ቀለም ቀይሮ ማየት እንደሚችል ገልጿል።
🎼 ቪንሰንት ቫን ጎህ (Vincent van Gogh)፦ ታዋቂው ሰዓሊ ሙዚቃ ሲሰማ የሚፈጠሩለትን ቀለሞች በስዕሎቹ ላይ ይጠቀም እንደነበር ይነገራል።
ሳይንቲስቶች እንደሚሉት በልጅነታችን ሁላችንም የስሜት ህዋሶቻችን የተቀላቀሉ ነበሩ። እያደግን ስንመጣ አእምሯችን አላስፈላጊ ግንኙነቶችን ይቆርጣል። ሲነስቴዢያ ያላቸው ሰዎች ግን እነዚህ የግንኙነት መስመሮች ሳይቆረጡ አብረዋቸው ያድጋሉ።
ይህ ሁኔታ በሽታ ወይም እክል ሳይሆን እጅግ ልዩ የሆነ የአእምሮ ስጦታ ነው!
እናንተ ጋር እንደዚህ አይነት ስሜት አጋጥሟችሁ ያውቃል? ለምሳሌ የሆነ ዘፈን ሲሰሙ የሚታያችሁ ቀለም አለ?
@Amazing_fact_433 | 10 654 |
| 11 | ድምፅን ማየት እና ቀለሙን መቅመስ የሚችሉ ሰዎች እንዳሉ ያውቃሉ?
በተፈጥሮ የሰዎች የስሜት ህዋሳት (ማየት፣ መስማት፣ መቅመስ፣ ማሸተት እና መንካት) የተለያዩና የተነጠሉ ናቸው። ነገር ግን እነዚህ ሰዎች አእምሮ ውስጥ የእነዚህ የስሜት ህዋሳት የመልዕክት መስመሮች እርስ በእርስ የተቀላቀሉ (Cross-wired) ናቸው!
ሲነስቴዢያ (Synesthesia) በመባል የሚጠሩት እንዚህ ስዎች ሙዚቃ፣ የሰው ድምፅ ወይም የማሽን ጩኸት ሲሰሙ አእምሯቸው ድምፁን ወደ ተለያዩ ቀለማት እና ቅርጾች ይለውጠዋል።
ለምሳሌ፡ የፒያኖ ድምፅ ሰማያዊ የቫዮሊን ድምፅ ደግሞ ብሩህ ቢጫ ሆኖ ይታያቸዋል!
😄 በሌላ በኩል የተወሰኑ ቃላትን ሲያነቡ ሲሰሙ ወይም ሲያስቡ በአፋቸው ውስጥ የተለየ የምግብ ወይም የመጠጥ ጣዕም ይመጣል።
ለምሳሌ፡- "ፍቅር" የሚለው ቃል የማር ጣዕም "ሰኞ" የሚለው ቃል ደግሞ የቸኮሌት ጣዕም ሊኖረው ይችላል!
😁 ለእነሱ እያንዳንዱ ቁጥር እና ፊደል የራሱ የተወሰነ ቀለም አለው። ለምሳሌ "5" ቁጥር ሁልጊዜ አረንጓዴ "A" ፊደል ደግሞ ሁልጊዜ ቀይ ሆኖ ነው የሚታያቸው።
@Amazing_fact_433 | 10 022 |
| 12 | ይህንን ያውቃሉ ??
ቮልስዋገን
የቡጋቲ ፣የአውዲ፣ላበርጊኒ፣ቤንትለይ፣ዱካቲ እና ፓርሽ ባለቤት ነው ።
@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433 | 10 747 |
| 13 | በ 1 ወር ውስጥ እንግሊዘኛን አቀላጥፈህ መናገር ትፈልጋለህ?
እንግዲያውስ ይህ ቻናል ላንተ ነው በነጻ ለመማር Join በል👇✅
➡️ @EnglishLearn_Ethiopia
➡️ @EnglishLearn_Ethiopia | 10 171 |
| 14 | Open Ai እጅግ በጣም ኃይለኛ የሆነውን የ Ai ሞዴል 'GPT-6 Astra' ግልጋሎትን መስጠት ጀምሯል።🥶🥶
GPT-6 Astra ምንድን ነው? በምሳሌ እንካቹ...
የዱሮ Ai
👉 “ኢሜይል ጻፍልኝ” ብለን ስንጠይቅ ኢሜሉን ይፅፋል...
አዲሱ GPT-6 Astra ግን ፦
👉 “ይህን የደንበኛ ቅሬታ አስተካክልልኝ” ስትሉት እሱም ችግሩን ተረድቶ → ምላሽ አዘጋጅቶ → መረጃዎችን አጣርቶ → አስፈላጊ መሣሪያዎችን ተጠቅሞ → ለውጦችን አድርጎ → ስራውን ሰርቶ ይጨርሳል።
ስለዚህ ትልቁ ለውጥ፦
AI ከማስረዳት ወይም ከመመለስ አልፎ “ሙሉ ስራን ለኛ ወደ መሥራት” ተሸጋግሯል።
🧠 ቀላል ምሳሌ
የቀድሞውን Ai ፦
“ለንግድ ድርጅቴ የሚሆን ዌብሳይት ሠራልኝ።” ብለን ስንጠይቅ የቀድሞ AI የተወሰነ የኮድ ጽሁፍ ይልካል።
ይህ አዲሱ Ai ግን፦
የዌብሳይቱን እቅድ ያወጣል፤
ኮዱን ይጽፋል፤
ገጾቹን ይፈጥራል፤
ይፈትሻቸዋል (Test ያደርጋል)፤
ስህተቶችን ፈልጎ ያርማል፤
ዲዛይኑን ያሻሽላል፤
በመጨረሻም የተጠናቀቀውን ዌብሳይት በእጅዎ ያስገባል።
Share
https://t.me/+5sCQf3Z1UUAxZDAy
https://t.me/+5sCQf3Z1UUAxZDAy | 10 699 |
| 15 | "አንድ ስፐርም 37.5 MB፣ በአንድ ጊዜ ደግሞ 16 TB ዳታ ይተላለፋል አሉ።እኔ ግን የሚገርመኝ... ይሄ ሁሉ GB ተራምዶ 9 ወር ሙሉ 'Download' ሆኖ መጨረሻ ላይ 'Storage Full' ሆኖ የሚወጣው ልጅ ግን ለምን 'Error' ይበዛበታል? 🤦♂️😂" | 12 087 |
| 16 | ለየት ለየት ያሉ አስገራሚ ድረ-ገፆች
radiooooo.com
በየአመተምህረቱ የወጡ የሀገራትን ዘፈኖች ያጫውታል። የሀገራችንም አለ።
visquill.com/gallery/world-demographics/
የየሀገራትን የህዝብ ፒራሚድ (Population)፣ የሞትና የውልደትና ምጣኔ interactive በሆነ መንገድ ያሳያል።
thetruesize.com
ትክክለኛ የሀገራት ስፋት ከሌሎች ሀገራት ጋር ለማነፃፀር ያስቻል።
worldometers.info
Live የአለማችን የህዝብ ቁጥር፣ የሚሞተውን፣ የሚወለደውን ማየት ያስችላል።
internetlivestats.com
በየቀኑ ያለውን የinternet መረጃ በቊጥር ያሳያል።
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
Credit bighabesha_softwares | 12 051 |
| 17 | ✅ቫይኪንጎች ከ8ኛው እስከ 11ኛው ክፍለ ዘመን (ከ793 እስከ 1066 ዓ.ም ገደማ) በሰሜን አውሮፓ የሚኖሩ የነበሩ የባህር ተጓዦች፣ ነጋዴዎች፣ ተዋጊዎች እና ወራሪዎች ነበሩ። በታሪክ "የቫይኪንግ ዘመን" ተብሎ በሚጠራው በዚህ ወቅት ከአውሮፓ እስከ ሰሜን አሜሪካ ባሉ አካባቢዎች ትልቅ ተፅዕኖ አሳድረዋል።
✅ የመጡት ከአሁኗ ዴንማርክ፣ ኖርዌይ እና ስዊድን (ስካንዲኔቪያ) ከሚገኙ የኖርስ (Norse) ህዝቦች ነው።
✅አብዛኞቹ ቫይኪንጎች ዘወትር ወራሪዎች አልነበሩም፤ በዋናነት ገበሬዎች፣ አሳ አጥማጆች፣ የእደ-ጥበብ ባለሙያዎች እና ነጋዴዎች ነበሩ።
✅ሎንግሺፕ (Longship) በመባል የሚታወቁ ረጅም፣ ጠባብ እና ፈጣን የእንጨት ጀልባዎችን በመስራት በጠለቀ ውቅያኖስም ሆነ በራሳች ወንዞች ላይ በቀላሉ ይጓዙ ነበር።
✅ከክርስቶፎር ኮሎምበስ 500 ዓመታት በፊት ሌይፍ ኤሪክሰን (Leif Erikson) በተባለ መሪያቸው አማካኝነት ሰሜን አሜሪካ (ካናዳ) ደርሰዋል። በተጨማሪም አይስላንድ እና ግሪንላንድን የሰፈሩበት የመጀመሪያዎቹ ህዝቦች ናቸው።
ከእንግሊዝ እና ፈረንሳይ እስከ ሩሲያ፣ ቁስጥንጥንያ (ኢስታንቡል) እና ባግዳድ ድረስ የንግድ መስመሮችን ዘርግተዋል።
✅ክርስቲያን ከመሆናቸው በፊት ባለብዙ አማልክት እምነት ይከተሉ ነበር። ዋና አማልክቶቻቸው ኦዲን (Odin - የጥበብና የጦርነት አምላክ)፣ ቶር (Thor - የነጎድጓድ አምላክ) እና ፍሬያ (Freya) ናቸው።
✅በውጊያ ላይ መሞት ትልቅ ክብር እንደሆነ ያምኑ ነበር፤ በጀግንነት የሞተ ተዋጊ ወደ "ቫልሃላ" (Valhalla) ወደተባለው የጀግኖች መንግስት ይሄዳል ብለው ያምኑ ነበር።
✅በ11ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ የቫይኪንጎች ዘመን ያበቃው በአውሮፓ ጠንካራ መንግስታት በመመሥረታቸው፣ የክርስትና እምነት በመስፋፋቱ እና የኖርማን ወረራ በእንግሊዝ ላይ ከተካሄደ በኋላ ከባህላዊ አኗኗራቸው ጋር በመቀላቀላቸው ነው | 12 687 |
| 18 | "የደግነት ንግስት" -ዶሊ ፓርተን
--
በህይወት ዘመኗ ለበጎ አድራጎት ድርጅት ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ የለገሰችው የደግነት፣የቸርነት ንግስት ናት።
በአንድ ዘፈን ብቻ በዓለም ዙሪያ ከ100 ሚሊዮን በላይ የሙዚቃ ሪከርዶችን ሸጣለች።በሙዚቃ ስራዋ ከፍተኛ ሽያጭ ካላቸው የሙዚቃ አርቲስቶች መካከል ስኬታማ ሴት አንዷ ነች።
በመዝናኛ ዓለም ውስጥ ካሉት እጅግ ለጋስ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ የበጎ አድራጎት እንስት አንዷ እንደሆነች በሰፊው ተነግሮላታል።
እ.ኤ.አ. በ2016፣ በትውልድ ግዛቷ በምስራቅ ቴነሲ በተከሰተው የዱር እሳት አደጋ ቤታቸው ለወደመባቸው ከ12 ሚሊዮን ዶላር በላይ እርዳታን ለግስላች።
ቤታቸውን ላጡ 900 ቤተሰቦች ለስድስት ወራት በጥሬ ገንዘብ በወር 1,000 ዶላር ሰጥታለች፣ ይህም ቤታቸውን ላጡ 900 ቤተሰቦች የቤት ኪራይ፣ የምግብ እና አስፈላጊ ነገሮችን በመገንባት ላይ እንዲከፈል አድርጋለች ።
እ.ኤ.አበ1995 "የዶሊ ፓርተንን የኢማጂኔሽን ቤተ መጻሕፍት" አስመረቀች።ማንበብና መጻፍ ፈጽሞ ያልተማረው በአባቷ ሮበርት አነሳሺነት የመጽሐፍ ስጦታ የሚሰጥ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት መስርታለች ።
በመሰረተችው የኢማጂኔሽን ቤተ መፃህፍት በዓለም ዙሪያ ላሉ ህጻናት ከ325 ሚሊዮን በላይ ነፃ መጽሐፍትን ሰጥታለች።
በ1989 ዶሊ በአሜሪካን በሴቪየር ካውንቲ፣ ቴነሲ ውስጥ በሂዋሲ ኮሌጅ ከፍተኛ ትምህርት ለመከታተል ለሚፈልግ ለማንኛውም ተማሪ ከኪሷ 500 ዶላር የትምህርት ዕድል ሰጥታለች።
በ2020፣ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት፣ ዶሊ ለቫንደርቤልት ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ማዕከል 1 ሚሊዮን ዶላር ልገሳ አድርጋለች።
እ.ኤ.አ. በ2021፣ ዶሊ በከባድ የአካባቢ ጎርፍ ለተጎዱ የቴነሲ ነዋሪዎች 700,000 ዶላር ለግሳለች።
የህፃናት ሆስፒታል ለማቋቋም 1 ሚሊዮን ዶላር ልገሳ አድርጋለች።
ለሌሎች ለሰባአዊ ድጋፍ እና እርዳታ ለሚውል ገንዘብና ፀጋን ለግሳለች።
ዶሊ ፓርተንን የምንወዳት በምታቀነቅነው 'አገርኛ' ሙዚቃ ብቻ ሳይሆን አለምአቀፋዊ የቸርነት ንግስት በመሆናም ነው!
-- | 11 667 |
| 19 | በ2009 እ.ኤ.አ. በ13 ዓመቷ ለብቻዋ ዓለምን በጀልባ ለመዞር አልማ የተነሳችው ሆላንዳዊቷ ላውራ ዴከር፣ በወቅቱ የሀገሯ ባለስልጣናት «ለህይወቷና ለዕድገቷ አደገኛ ነው» በማለት በፍርድ ቤት እቅዷን አግደውባት ነበር።
ሆኖም በ2010 እ.ኤ.አ. ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ለወላጆቿ በመተው ፈቃድ ስለሰጣት፣ ነሐሴ 21 ቀን 2010 እ.ኤ.አ. ከጂብራልታር «ጉፒ» በተሰኘችው 38 ጫማ ርዝመት ባላት ጀልባዋ ጉዞዋን ጀምራለች። ላውራ ከ518 ቀናት የባህር ላይ ጉዞ በኋላ ጥር 21 ቀን 2012 እ.ኤ.አ. በ16 ዓመቷ ስንት ማርተን በመድረስ፣ በብቸኝነት ዓለምን በጀልባ በመዞር የዓለማችን ትንሿ ታሪክ ሰሪ በመሆን እስካሁንም ያልተሰበረ ድንቅ ሪከርድ አስመዝግባለች። | 11 766 |
| 20 | 💥የአለማችን ቀጫጫ ሰዎች ቪዲዮ👇ይመልከቱ
https://youtu.be/X7YD6c9N3Lw?si=LbcBg38_hYwM1GQk | 11 324 |
