uk
Feedback
ወርቃማ ምክሮች

ወርቃማ ምክሮች

Відкрити в Telegram

የተለየዩ አስተማሪ ታሪኮች ፣ወርቃማ ምክሮች የስኬታማ ሰዎች ልምድ፣ የተለያዩ መጣጥፎች የሚቀርቡበት ቻናል ነው ‼️ ☞https://t.me/eross_eross ▮Share and Join

Показати більше
2 761
Підписники
-324 години
-137 днів
-6430 днів

Триває завантаження даних...

Хмара тегів
Немає даних
Виникли проблеми? Будь ласка, оновіть сторінку або зверніться до нашого support-менеджера.
Вхідні та вихідні згадування
---
---
---
---
---
---
Залучення підписників
вересень '26
вересень '26
+1
в 1 каналах
серпень '26
+18
в 2 каналах
Get PRO
липень '26
+22
в 1 каналах
Get PRO
червень '26
+14
в 0 каналах
Get PRO
травень '26
+19
в 0 каналах
Get PRO
квітень '26
+13
в 0 каналах
Get PRO
березень '26
+15
в 0 каналах
Get PRO
лютий '26
+23
в 2 каналах
Get PRO
січень '26
+15
в 1 каналах
Get PRO
грудень '25
+23
в 1 каналах
Get PRO
листопад '25
+24
в 1 каналах
Get PRO
жовтень '25
+183
в 1 каналах
Get PRO
вересень '25
+315
в 1 каналах
Get PRO
серпень '25
+325
в 0 каналах
Get PRO
липень '25
+246
в 1 каналах
Get PRO
червень '25
+243
в 3 каналах
Get PRO
травень '25
+212
в 0 каналах
Get PRO
квітень '25
+195
в 1 каналах
Get PRO
березень '25
+350
в 0 каналах
Get PRO
лютий '25
+240
в 1 каналах
Get PRO
січень '25
+599
в 2 каналах
Get PRO
грудень '24
+892
в 2 каналах
Get PRO
листопад '24
+897
в 0 каналах
Get PRO
жовтень '24
+44
в 1 каналах
Get PRO
вересень '24
+5
в 0 каналах
Get PRO
серпень '24
+6
в 1 каналах
Get PRO
липень '24
+1
в 0 каналах
Get PRO
червень '24
+7
в 0 каналах
Get PRO
травень '240
в 1 каналах
Get PRO
квітень '240
в 2 каналах
Get PRO
березень '240
в 1 каналах
Get PRO
лютий '240
в 2 каналах
Get PRO
січень '240
в 1 каналах
Get PRO
грудень '230
в 1 каналах
Get PRO
листопад '23
+1
в 0 каналах
Get PRO
жовтень '23
+12
в 1 каналах
Get PRO
вересень '23
+4
в 0 каналах
Get PRO
серпень '23
+20
в 0 каналах
Get PRO
липень '23
+8
в 0 каналах
Get PRO
червень '23
+15
в 0 каналах
Get PRO
травень '23
+17
в 0 каналах
Get PRO
квітень '23
+7
в 0 каналах
Get PRO
березень '23
+85
в 0 каналах
Get PRO
лютий '23
+30
в 0 каналах
Get PRO
січень '23
+59
в 0 каналах
Get PRO
грудень '22
+43
в 0 каналах
Get PRO
листопад '22
+32
в 0 каналах
Get PRO
жовтень '22
+39
в 0 каналах
Get PRO
вересень '22
+25
в 0 каналах
Get PRO
серпень '22
+29
в 0 каналах
Get PRO
липень '22
+19
в 0 каналах
Get PRO
червень '22
+20
в 0 каналах
Get PRO
травень '22
+20
в 0 каналах
Get PRO
квітень '22
+7
в 0 каналах
Get PRO
березень '22
+16
в 0 каналах
Get PRO
лютий '22
+29
в 0 каналах
Get PRO
січень '22
+22
в 0 каналах
Get PRO
грудень '21
+15
в 0 каналах
Get PRO
листопад '21
+12
в 0 каналах
Get PRO
жовтень '21
+43
в 0 каналах
Get PRO
вересень '21
+21
в 0 каналах
Get PRO
серпень '21
+41
в 0 каналах
Get PRO
липень '21
+50
в 0 каналах
Get PRO
червень '21
+83
в 0 каналах
Get PRO
травень '21
+69
в 0 каналах
Get PRO
квітень '21
+64
в 0 каналах
Get PRO
березень '21
+47
в 0 каналах
Get PRO
лютий '21
+96
в 0 каналах
Get PRO
січень '21
+119
в 0 каналах
Get PRO
грудень '20
+2 729
в 0 каналах
Дата
Залучення підписників
Згадування
Канали
04 вересня0
03 вересня0
02 вересня0
01 вересня+1
Дописи каналу
🦅ንስር አሞራ እና አንተ አንቺ ፣ እኔ እና እኛ 🦅 👉 ስለ ንስር አሞራ ስነግርህ ከሚገርም መሳጭ ታሪክ ጋር ነው ... እውነት እውነት እልሃለሁ የንስር አሞራ ታሪክ በሁላችንም ህይወት ውስጥ አለና ከራስህ ጋር እያዛመድክ ካነበብከው መጨረሻህን ድል ድል ታሸተዋለህና በፍቅር ተከተለኝ። #ልጀምርልህ ... ንስር አሞራ እስከ 70 አመት የሚኖር የእድሜ ባለፀጋ ነው ካልክ ልክ ነህ ... ግና 70 አመት ሙሉ በደስታ ከመኖሩ በፊት በእድሜው አጋማሽ ማለትም በ35 - 40 ባለው እድሜው ላይ ከባድ ነገር ይገጥመዋል ... √ የመጀመሪያው :- ምግቡን ለማደን የሚገለገልበት ጥፍሮቹ ከመጠን በላይ ስለሚያድጉ ምግቡን ከመሬት ላይ ማንሳት ያቅተዋል ... √ ሁለተኛው :- አጥንትን ሳይቀር መስበር አቅም ያለው አፉ(መንቁሩ) ስለሚታጠፍና ስለሚጣመም ምግቡን እንደወትሮው መመገብ ይሳነዋል ... √ ሶስተኛው:- ክንፉና በአካሉ ላይ ያሉ ላባዎች ስለሚከብዱት ያ ሰማየ ሰማያትን እየሰነጠቀ ይበር የነበረው ሀይሉ ይክደዋል። #እነዚህ ሶስት ከባድ ነገሮች ንስር አሞራ በእድሜው አጋማሽ የሚያጋጥሙት ከባድ ችግሮች ናቸው። አሁን ንስር አሞራ ያለው ምርጫ ሁለት ነው። √ 1ኛ. ካረጀ አካሉ ጋር ዝም ብሎ በመቀመጥ ሞቱን መጠበቅ ? √ 2ኛ. አምስት ወር የሚፈጅ ስቃይና መከራ ያለበት መስዋዕትነትን ከፍሎ ቀሪውን 35 አመት በደስታ ማሳለፍ ? • የመጀመሪያውን ከመረጠ በእድሜው አጋማሽ ይሞታልና ታሪኩ እዛ ጋር ያበቃል። • ሁለተኛውን ምርጫ ከመረጠ ግን እነዚህን አምስት መስዋዕትነቶች ማለፍ ይኖርበታል። √ 1ኛ. ከፍተኛ ተራራ ላይ በመውጣት የብቻውን ጎጆ ይቀልሳል። √ 2ኛ. ጎጆ ከቀለሰ በኋላ የመጀመርያ ስራዉ የአፉን መንቁር ከአለት ጋር በማጋጨት ነቅሎ ይጥላል። √ 3ኛ. ይህን ካደረገ በኋላ አዲስ መንቁር ይወጣለታል፡፡ መንቁሩ እስኪያድግ ድረስ ታግሶ በጎጆው ምንም አይነት ምግብ ሳይመገብ መቆየት ግዴታው ይሆናል፡፡ √ 4ኛ. አዲስ መንቁር ከበቀለለት በኋላ በአዲሱ መንቁሩ የገዛ እግሩን አሮጌ ጥፍር ነቃቅሎ ይጥለዋል። √ 5ኛ. አዲሱ የእግር ጥፍር ከበቀለለት በኋላ ደግሞ ይህንን አዲስ ጥፍር እንደ መሳርያ በመጠቀም በሰዉነቱ የተጣበቁትን እንዳይበር እንቅፋት የሆኑትን የገዘፉና ያረጁ ላባዎችን ነቃቅሎ ይጥላል። በምትኩ አዲስ ላባ ያበቅላል። #ይህን 5 ወር በዚህ መልኩ በጀግንነት ከተወጣ በኋላ እንደገና ራሱን በራሱ ወልዶና ወጣት ሆኖ ወደ ንስሮች መንደር ብቅ ይላል፡፡ • • 🔥 ወዳጄ ሆይ:- 🔥 √ ችግር ገጠመኝ ብለህ ያዙኝ ልቀቁኝ አትበል ፣ √ ችግሬ ... ችግሬ ... እያልክም ነጠላ ዜማ አትልቀቅ ፣ √ ፊትህንም ችግር ፊት አታስመስል ፣ √ ጥቅም ላይ እያፈጠጠ የሚከተል ሰው በበዛበት አለም ላይ መውደቅህን መጥሪያ ካርድ አታሰራበት ፣ √ መራብ መጠማትህን ፖስት ለማድረግ አትቸኩል ፣ √ መገፋትህን እንደ ትልቅ ነገር ቆጥረህ ኡኡኡ አትበል ፣ √ ስንት ነገር መስራት የምትችልበትን አዕምሮ ለሃሜትና "አሉ ... አለች" መሳሪያ በመጠቀም "የውሸት እየኖርክ - የእውነት አትሙት" ... በቃ ! ... √ ልክ እንደ ንስር አሞራ በህይወትህ አጋማሽ ላይ ምርጫ መቶልሃል ... 1ኛ. ችግሩን ታቅፎ መሞት ... 2ኛ. ለችግሩ መስዋትነት ከፍሎ ማለፍ ... ••• ♦ አስተውል ... ♦••• ሁለተኛውን ከመረጥክ ልክ እንደ ንስሩ አምስት ዋጋዎችን መክፈል አለብህና ዝግጁ ሁን ... √ 1ኛ. ራስህን ከነገሮች አርቀህ በፅሞና ሃሳብህን መግራት ጀምር ... እዚህ ጋር ከወዳጅም ከጠላትም መራቅ ፍቱን መድሃኒት ነው ... ንስር አሞራው ከፍተኛ ተራራ ላይ የሚወጣው ከሁሉም ንስሮች እርቆ ለህይወቱ ዋጋ ለመክፈል ነው ... ይህን አይነት መላ ምሁራኑ "የስኬት ሱባኤ" ይሉታል። √ 2ኛ. አንገብጋቢ ችግርህን ለመፍታት ቁርጥ ያለ አቋም ይዘህ እስከ ሞት የሚያደርስ መስዋትነት መክፈል። ንስሩ አፉ ላይ ያለውን ምግብ ማምጫ መንቁሩን እንደሚያስወግደው ሁሉ። √ 3ኛ. መስዋት የከፈልክለት ነገር እስኪመጣ በትዕግስት መጠበቅ ... ይህ ደግሞ ንስሩ መንቁሩ እስኪያድግለት ድረስ ምግብ ሳይበላ እንደሚኖረው ሁሉ አንተም ዋጋ የከፈልክለት ነገር እስኪመጣ በትእግስት እና እምነት መጠበቅ። √ 4ኛ. በትእግስት ጠብቀህ ያሰብከው ነገር ከመጣ በዋላ ህይወትህን ጠፍንገው የያዙህን ነገሮች መፍታት ... ልክ ንስሩ መንቁሩ እንዳደገለት የእግሩን ጥፍሮች በመንቁሩ እየወጋ እንደሚያስወግዳቸው ሁሉ። √ 5ኛ. ሁሉን ካሳካህ በዋላ ወደ ህልምህ መብረር ... ይህ ማለት ንስሩ የእግሮቹን ጥፍር አስወግዶ እና አሮጌ ክንፎቹን አስወግዶ ከጠበቀ በዋላ አዲስ ክንፍ ፣ አዲስ መንቁር እና አዲስ ጥፍር ካበቀለ በዋላ እንደ አዲስ ጉልበታም ንስር ቀሪ ዘመኑን ይኖራል። #ሲጠቃለል ... 👉 አንተም ፣ አንቺም ፣ እኔም በዚህ ሁሉ መንገድ አልፈን ከባዱን ጊዜ ካለፍን በዋላ በአዲስ የህይወት መንቁር ፣ የተስፋ ጥፍር እና የስኬት ክንፍ ከፍ ብለን እንበር ዘንድ ..... ኑ ንስር አሞራን እንምሰል። 👉@eross_eross

2
"ሰው ማለት የትዝታውና የትውስታው ድምር ነው። ሕይወት የመርሳትና የማስታወስ ሚዛን ናት። መርሳት ያለብንን መርሳት ሲያቅተን ሕይወታችን ይመሳቀላል፡፡ ደግሞ ማስታወስ ያለብንን የሕይወት ልምዶች ፣ ጠቃሚ ሰዎችና ነገሮች ከረሳን የእኛነታችን መለያና የስብእናችን ድንበር ይጠፋና ሌላ ሰው እንሆናለን።" ____ አዎ ዛሬ ላይ በትምህርታችን ፣ በስራችን ፣ በፍቅር ህይወታችን በአጠቃላይ በማህበራዊ ህይወታችን መጥፎ የሚባልን ጊዜ እያሳለፍን ይሆናል፡፡ ነገር ግን የዛሬ መጥፎ ክስተቶችና ገጠመኞች አስተምረውን ዛሬ ላይ ተቀብረው መቅረት ይገባቸወዋል፡፡ ምክንያትም እነሱን ዳግም በማስታወስ የምናገኘው አንድ ነገር ቢኖር ዳግም ማዘንን ነውና፡፡ __ በሌላ በኩል ደሞ በህይወታችን ያሳለፍናቸው መልካም ሁነቶች ያገጠሙን መልካም ሰዎች ዛሬም ነገም ወደ ፊትም እንደአዲስ የደስታ ምንጮቻችን ይሆናሉ፡፡ መረሳትም የለባቸውም፡፡ ማይጠቅመውን መርሳት የሚችል፤ ሚጠቅሙትን የመይዘነጋ አእምሮ አሏህ ይስጠን፡፡ @eross_eross
51
3
ተናጋሪ በዝቷል ፤ ተንታኝ በርክቷል። ብልህ ሁኑ። ከብዙ የወሬ ማዕዶች ገለል በሉ። ከሥራ ፈቶች ተነጠሉ። ከዑለሞችና አላህን ፈሪዎች ተጠጉ። ሞት እንዳለባችሁ አትዘንጉ። ሕይወታችሁን ለአፍታም ቢሆን ከፈጠራችሁ አምላክ አትነጥሉ። ጊዜያችሁን ጥርግ አድርጋችሁ በመልካም ነገር ላይ አውሉ። አዝካሮችን ተላመዱ። ፨ በ ‹ላ ኢላሀ ኢለላህ› ተንፍሱ፡፡ ፨ በ ‹አስተግፊሩላህ ወአቱቡ ኢለይህ› ጥፋታችሁንና ጉድለታችሁን ተናዘዙ፡፡ ፨ ‹ሱብሓነከ ኢንኒ ኩንቱ ሚነዟሊሚን› በማለት ዘወትር ራሣችሁን ዉቀሱ፡፡ ፨ በ ‹አልሐምዱ ሊላህ› ህመማችሁን አስታግሱ፡፡ ፨ በ ‹ሱብሓነላህ› ስለ ፈጣሪያችሁ ሥራና ተዓምር ተደነቁ ፡፡ ፨ በ "አላሁ አክበር " አምላካችሁን አወድሱ፤ አልቁ። ፨ በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ላይ ሶለዋት በማውረድ ጭንቀታችሁን አስወግዱ፡፡ ፨ በ ‹ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን› ተፅናኑ፡፡ ፨ መልካም ነገሮችን ሁሉ በአላህ ሥም ጀምሩ። ፨ በ ‹አልሐምዱ ሊላህ› ጨርሱ፡፡ ፨ አላህን ስሙ ፣ ለአላህ ታዘዙ፣ ለአላህ ምላሽ ስጡ ፡፡ መልዕክቱ ለሁላችንም ነውና ሼር አድርጉ። እዚህ ተነጥለን እንተዋወስ። http://t.me/eross_eross
117
4
"እኔ ሰሚ ነኝ " "እኔ ቅርብ ነኝ።" ብሏል አላህ። ሰማይ ሩቅ ነው፤ ግና አላህ ቅርብ ነው። ምንም ማለት ባትችሉ እንኳን "አላህ! አላህ!" በሉ። ቅርብ የሆነው አምላክ ይደርስላችኋል።
132
5
•.¸♡ ሁለት ግን አንድ ፣አንድ ግን ሁለት ♡¸.• አሏህ( ሱብሃነሁ ታአሏህ) ለሰው ልጅ ሁለት አይኖችን ሰጠ። ብዙዎች ግን የሚጠቀሙት አንድ ዓይናቸውን ነው ። አንድ ምላስና ሁለት ጆሮዎችንም ሰጣቸ
•.¸♡ ሁለት ግን አንድ ፣አንድ ግን ሁለት ♡¸.• አሏህ( ሱብሃነሁ ታአሏህ) ለሰው ልጅ ሁለት አይኖችን ሰጠ። ብዙዎች ግን የሚጠቀሙት አንድ ዓይናቸውን ነው ። አንድ ምላስና ሁለት ጆሮዎችንም ሰጣቸው ፤ ብዙዎች የሚጠቀሙት ግን ሁለት ምላሰ አንድ ጆሮ ነው።ሁለት እጅም ሰጣቸው ብዙዎች የሚጠቀሙት አንዱን ብቻ ነው። ሁለት እግርም ሰጣቸው ብዙዎች አንድ እግራቸውን ብቻ ነው ፋይዳ ላይ ያዋሉት ። እንዴት ለሚለው ምላሹ የሚከተለውን ነው _ብዙዎች በተሰጣቸው ዓይን ላይ እላይን እንጂ ትክክለኛ ትርጉምን ጠልቀው አይመለከቱም ። _ብዙ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ያወራሉ ። _በእጃቸው በርካቶች ለመቀበል እንጂ ለመስጠት አልታደሉም ። _በእግራቸውም ወደ መጥፎ እንጂ ወደ መልካም ነገር በብዛት አይሄዱም። ለአንተም በርሱ እውቀት የሌለህን ነገር አትከተል ። መስሚያም ፣ማያም፣ልቦናም እነዚህ ሁሉ (በእለት ትንሣኤ በድርጊታቸው )ተጠያቂዎች ናቸው ። ❮አል _ኢስራእ:36❯ መልካም ቀን ተመኝሁ https://t.me/eross_eross
165
6
#ፈገግታም #ቁምነገርም አንድ ሰውዬ በውኃ ጉድጓድ አጠገብ ተቀምጣ ወደነበረች አንዲት ሴት ቀርቦ እንዲህ ሲል ጠየቃት፦“የሴቶች ብልህነት ምንድን ነው?” እሷም ይህንን ስትሰማ ከጉድጓዱ አጠገብ በመቆም የሰፈሯ ሰዎች እንዲሰሟት ጮክ ብላ ማልቀስ ጀመረች። ሰውዬው በመደናገጥ፡- “ፈርተሽኝ ነው? ለምን ፈራሽኝ እኔ እኮ ምንም ላደርግሽ አይደለም!።” እሷም፡- “የመንደሩ ሰዎች እንደሚመጡ ስላወቅክ እንጂ ልትጎዳኝና ልትገድለኝ ነበር” ሰውዬውም፦ “አንቺን ለመጉዳት ወደዚህ አልመጣሁም ነገር ግን ብልህነትሽን አይቻለሁና ጠየቅኩሽ። እና ካንቺ ጋር ለመነጋገር ያለኝ ፍላጎት ከመጥፎ እምነት የመነጨ አይደለም ምክንያቱም ቆንጆ ሴት ነሽ” ልጅቷ የሰውዬውን ንግግር ስትሰማ። ከጉርጓዱ አጠገብ የነበረውን የውሃ ባልዲ በማንሳት በራሷ ላይ አፈሰሰችው። ሰውዬው በልጅቷ ተግባር ተደንቆ ጠየቃት፡-“ለምንድነው ይህን ያደረግሽው?” ንግግሩን ሳይጨርስ ጩኸቱን የሰሙት የመንደሩ ሰዎች በአጠገባቸው ተሰበሰቡ። ልጅቷም የፈጠነ፡- “ጉርጓድ ውስጥ ወድቄ ነበር እና ይህ ሰውዬ ነው ያዳነኝ” አለቻቸው። ሰዎቹም በደሰታ እንደጀግና አመስግነው ሸለሙት። ከሄዱ በኋላ ጠየቃት፦“ከተግባርሽ በስተጀርባ ያለው ጥበብ ምንድን ነው?” እሳም መለሰች:- ሴቶች እንደዚህ ናቸው። ከጎዳሀት ትገድልሀለች!፤ ብታስደስታት ግን የበለጠ ደስ ታሰኝሃለች። copied ወንዶች ጠንቀቅ በሉ👇 👉@eross_eross
172
7
ትዳሬ ለምን ዘገየ!? አውቃለሁ፤ አንዳንድ ጊዜ የጥበቃው ሰዓት ሲረዝም፣ በዙሪያሽ ያሉ እኩዮችሽ የራሳቸውን ጎጆ ሲቀልሱ ስታይ፣ ልብሽ ውስጥ የሚፈጠረውን ስሜት አላህ ያውቃል። ነገር ግን አንድ ነገር ልንገርሽ፤ የዘገየው ነገር ሁሉ የቀረ አይደለም፤ የዘገየው አላህ ባንቺ ልክ፣ ለልብሽ በሚመጥንና ለአኺራሽ በሚበጅ መልኩ እያሰናዳው ስለሆነ ነው። ይፍጠንም ይዘግይ፤ እርግጠኛ ነኝ ያሰብሽው ዓይነት፣ በሱጁድ ወርደሽ ያለቀስሽለት ዓይነት፣ «ጌታዬ ሆይ እንዲህ ያለውን ስጠኝ» ብለሽ የተመኘሽው ዓይነት አጋር አላህ ይሰጥሻል። የጌታሽ ካዝና አይጎድልም፤ ጊዜው ሲደርስ "ሁን" ይለዋል፤ ይሆናል። ውድ እህቴ... ዐይንሽን ከአላህ ላይ አትንቀይ። የልብሽን መልሕቅ በረብሽ ላይ ጣይው።  የዘገየው ባንቺ ላይ ካለው ክፋት ሳይሆን፣ ለአንቺ ካለው የእዝነት ጥበብ የተነሳ ነው። ስለዚህ መልካም ጥርጣሬሽን ንፋስ አይግባው። «ለምን ዘገየ?» የሚለው የሸይጧን ሹክሹክታ ኢማንሽን፣ ተወኩልሽንና ያቂንሽን  እንዲፈታተነው አትፍቀጂ። ያ የለመንሽው ዱዓ አየር ላይ አልቀረም፤ አላህ እየሰማሽ ነው።  አሁንም በፊት እንደምታስቢው፣ በፊት እንደምትመኚው አድርገሽ አስቢ። ተስፋሽን አዳብሪ። አላህ ነገ በተባረከ ትዳር፣ የዲን መሰረት ባለው ቤተሰብ፣ በሱና በደመቀች ጎጆ እንደሚክስሽ አስቢ። የአላህ ውሳኔ ሁሌም ከምኞታችን በላይ ውብ ነው። ትዕግስትሽ ጣፋጭ ነው፤ ፍሬውም ያማረ ይሆናል። አንቺ ብቻ ከደጃፉ አትጥፊ፤ ዱዓሽን አታቋርጪ። ያሰብሽውን፣ የተመኘሽውን፣ ለዱኒያም ለአኺራሽም የሚሆነውን የልብ ወዳጅ አላህ በቅርቡ ያምጣልሽ። አላህ የልብሽን መሻት ያሳካ፤ ሷሊህ የሆኑ ልጆች አባት ከሆነ ምርጥ ባሪያው ጋር ያጣምርሽ። አሚን! @eross_eross
151
8
  የህይወት እይታ ባህሪህን እወቅ በመንገድ ላይ ሲጓዝ የነበረ አንድ ሰውዬ መርዛማ የሆነ እባብ በእሳት ሲቃጠል ተመለከተና ከእሳቱ ውስጥ ሊያወጣው ወሰነ። ከእሳቱ ውስጥ ሊያወጣ ሲያነሳው እባቡ እጁ ላይ ነደፈው። ሰውዬው በድንጋጤ እባቡን ወረወረው እባቡም ተመልሶ እሳቱ ውስጥ ወደቀ። ሰውዬውም በድጋሚ ሁለት እንጨቶችን ተጠቅሞ ከእሳቱ አወጣው። እናም የእባቡ ሕይወት ተረፈ። ቆሞ ድርጊቱን ይመለከት የነበረ አንድ ሰው ወደ ሰውየው ቀርቦ "ይህ እባብ በመርዙ ነድፎህ ሳለ ድጋሚ ልታድነው የምትሞከረው ለምንድነው?" ብሎ ጠየቀው። ሰውየውም "የእባቡ ባህሪ መንደፍ ነው የእኔ ደሞ ማትረፍ ነው። ሁለታችንም ያለንን ነው ያንፀባረቅነው። ለሱ ክፉ ባህሪ ብዬ የኔን መልካም ባህሪ መለወጥ የለብኝም" ብሎ መለሰ። ክፉ ነገር በክፉ ሊመለስ አይገባም። መጥፎ ሰዎች በዙሪያህ ቢኖሩም፣ የቱንም ያህል ክፋት ቢሰሩብህ አንተ የራስህን መልካም ብህሪ አንፀባርቅ እንጂ በነሱ ውስጥ አትዋት።አንድ ቀን ከዚህ ስራቸው ታድናቸዋለህ። ሀል ጊዜም እራስህን ሁን!!!! የእውነት የሰውኛ ባህሪያችን ምንድነው?እየሆንን ያለውስ.? @eross_eross
187
9
ስለ ንፅህና ስናወራ… እድፍ ውስጥ የነበርን  እንደሆነ የምታስቡ… ስለ መለያየት ስንፅፍ…  ክህደት ተፈፅሞብን የእንባ ዓለማችንን እያስተጋባን የሚመስላችሁ… ስለ ፍቅር ስናስረዳ… ልባችን በፆታዊ ፍቅር የተነደፈ እንደሆነ የምትደመድሙ… ይህንንም አንብቡልኝ…  እዚህ የተፃፈ ሁሉ አልተኖረም… የተኖረው ሁሉም አይፃፍም እሺ… ያየነውንም ፣ የሰማነውንም በአንድ ሜዳ ለማጋራት ያህል ነው…  ከዚህ ውጪ ታድያ ምን እንፃፍላችሁ??… 👉t.me/eross_eross
230
10
🔺ቀሲዳ *☝️ أتُعلنُ حرباً أيا مُسلماً ..* *🎙️ نشيد عن المعاصي* 👉@eross_eross
249
11
የፍቅር ጥግ ስለ ፍቅር ከተነገረው ትልቁ አቡበክር ምን አስለቀሰህ ተባለ እርሱም፡- የአላህን መልእክተኛን እያለቀሱ አየሁ እኔም አለቀስኩ https://t.me/eross_eross
የፍቅር ጥግ ስለ ፍቅር ከተነገረው ትልቁ አቡበክር ምን አስለቀሰህ ተባለ እርሱም፡- የአላህን መልእክተኛን እያለቀሱ አየሁ እኔም አለቀስኩ https://t.me/eross_eross
265
12
↬የምትወደውን ሰው ማጣት ህመም አለው በጣም! ከዚሁ ሱራ ውስጥ ከምናገኛቸው ነገሮችመካከል  የዩሱፍ አባት በሱፍ ሀዘን ግሎ ሳይጨርስ ሌላ ዱብዳ ለሁለተኛ ጊዜ ሌላ የልጅ ማጣት መጣበት  ካአለው አሏህ ላይ ተወኩልም ጋ አሏህ ካሳወቀው ጥበብም ጋ  ስሞታው ወዳአሏህ ከመመለሱጋ ከወዳጅ ቹ መለያየት ሀዘኑ በጣም ጥልቅ ስለሆነ የአይን ብርሃን እስከማጣት ደረሰ … ( وتَوَلَّىٰ عَنْهُمْ وَقَالَ يَٰٓأَسَفَىٰ عَلَىٰ يُوسُفَ وَٱبْيَضَّتْ عَيْنَاهُ مِنَ ٱلْحُزْنِ فَهُوَ كَظِيمٌۭ ) " ከእነሱም ዘወር አለና ኣ«በዩሱፍ ላይ ዋ ሐዘኔ!» አለ ፡፡ ዓይኖቹም ከሐዘን (ለቅሶ) የተነሳ ነጡ ፡፡ እርሱም በትካዜ የተሞላ ነው ፡፡"  ዩሱፍ 84 አዎን የምትወደውን ሰው ስታጣ ህመም አለው!!!!! 👉@eross_eross
223
13
Голосове повідомлення
169
14
ስለ እናት ጣፋጭ ግጥም በአረብኛ ተ➖ጋ➖በ➖ዙ➖ል➖ኝ🤌 ☔️ስለ #እናት መካሪና ጣፋጭ የሆነ ቀሲዳ‼️ 📎https://t.me/eross_eross
211
15
ሸይኽ_ሷሊህ_አልፈውዛን ሐፊዞሁሏህ እንዲህ ይላሉ : - «አግብተህ፣ ነፍስህን (ከዝሙት) መጠበቅህ፣ ሴቲቱንም እንዲሁ መጠበቅህ እና ዝርያዎችንም መተካትህ ትርፍ ዒባዳዎችን ለመፈፀም ለብቻህ ከመገለልህ
ሸይኽ_ሷሊህ_አልፈውዛን ሐፊዞሁሏህ እንዲህ ይላሉ : - «አግብተህ፣ ነፍስህን (ከዝሙት) መጠበቅህ፣ ሴቲቱንም እንዲሁ መጠበቅህ እና ዝርያዎችንም መተካትህ ትርፍ ዒባዳዎችን ለመፈፀም ለብቻህ ከመገለልህ የበለጠ ነው። @eross_eross
262
16
የዛሬው ጠቅላላ እውቀት 💥 ስለ መውሊድ ትክክል ያልሆነው የቱ ነው።
191
17
፣ والله ከባድ ገፍላ ላይ እኮ ነው ያለነው ውዶች ጨልሞብናል ማለት ይቻላል ያረበና መጨረሻችን አሳምርልን https://t.me/eross_eross
፣ والله ከባድ ገፍላ ላይ እኮ ነው ያለነው ውዶች ጨልሞብናል ማለት ይቻላል ያረበና መጨረሻችን አሳምርልን https://t.me/eross_eross
182
18
•.,¸¸,.•´¯ ስለ ቀልበችን ክፍል ❻ ¯•.,¸¸,.•´ ❹ ቀልቡን ወጂል ፦ ለሰራችው መልካም ስራ አሏህ ተቀብሎኝ ይሆን በማለት የምትሰጋ ቀልብ ፦ (አሏህ ሱብሃነሁ ታዕሏህ) እንዲህ ይለናል ፦ እ
•.,¸¸,.•´¯ ስለ ቀልበችን ክፍል ❻ ¯•.,¸¸,.•´ ❹ ቀልቡን ወጂል ፦ ለሰራችው መልካም ስራ አሏህ ተቀብሎኝ ይሆን በማለት የምትሰጋ ቀልብ ፦ (አሏህ ሱብሃነሁ ታዕሏህ) እንዲህ ይለናል ፦ እንዚያ ከሰጠናቸው (ሲሳይ)የሚመጸውቱ ሲሆኑ (ቀልባቸው)ልባቸው (አይቀበለንምይሆን በማለት) የሚፈሩ ናቸው እንሱም ወደ ጌታቸው ተመላሾች ናቸው ። (አል _ሙእሚኑን:60) አማኞች ሆነው ንፁህ ቀለብ ያላቸው ሰዎች ጌታቸው ያዘዛቸውን አምልኮት በሚገባ ከፈጸሙ በኋላ ይህ አምልኮዬ ጌታዬ እንደሚፈልገው ሆኖ ይቀበለኝ ይሆን ??? የሚል ስጋት ያድርባቸዋል እንጂ እንደ እኔ ማን ለጌታው ተገዢ ፣ታዣዥ አለ በማለት አይመፃደቁም ። ይህ ተግባር ደግሞ የቀልብ ንጹህነትንና የኢማን ጥንካሬን ያንጸባርቃል ። _________________________ {[ይቀጥላል }} ኢባዳችሁ ተቀባይነት ያለው ምሸት አሏህ ያድርግልን ያረብ https://t.me/eross_eross
201
19
🤩ባለ ተሰጥኦዎች የታላቹ🤩 አሰላሙ አለይኩም እንዴት ናቹ ውድ የተከበራቹ የቻናል ሜምበሮች ዛሬ አዲስ ነገር ይዘንላቹ መተናል የግጥም ውድድር ልናደርግ ነው ሽልማቱም የሚሆነው አንደኛ ለወጣ......150 ብር ካርድ 🤩 ሁለትኛ ለወጣ.....100 ብር ካርድ🤩 ሶስተኛ ለወጣ..... 50 ብር ካርድ 🤩 ግጥሙ <ስለ ቁርዓን አጠር መጠን ያለ >ብቻ እና ብቻ መሆን አለበት። አሸናፊው የሚሆነው በላይክ ብዛት ይሆናል። ውድድሩ ለሶስት ቀን የሚቆይ ሲሆን ከአሁን  ሰአት ጀምሮ  እስከ ሶስት ቀን መላክ ትችላላቹ😊 ማስጠንቀቂያ ❗️ copy right ማረግ በፍፁም ያተከለከለ ነው።ባለ ትክክለኛ ተስጥኦዎች ብቻ ይወዳደሩ። ውድድሩ የሚሆነው ወርቃማ ምክሮች ቻናል ላይ ነው። ግጥሙን በዚ ይላኩ 👉@eross_63 መልካም እድል ሼር አርጉ @eross_eross
216
20
#አኩራፊ_ሰው_ብዙ_ነገር_ያመልጠዋል ባል እና ሚስቱ በመሀላቸው ግጭት ተፈጥሮ አይነጋገሩም፡፡ ሁለቱም በረጅም ትዝታ ተውጠዋል፡፡ መጀመሪያ ማውራት ሽንፈት መስሎ ስለታያቸው ሳይነጋገሩ መተኛ ሰዓታቸው ደረሰ፡፡ ድንገት ግን ባል የሆነ ነገር ትዝ አለው፡፡ ነገ በጠዋት የስራ ስብሰባ ለመታደም ወደ ሌላ ሀገር ለመሄድ በረራ አለው፡፡ ሁሌ ደሞ ወደ ስራ ሲሄድ እንቅልፋም በመሆኑ የምትቀሰቅሰው ሚስቱ ናት፡፡ እናም የነገው ስበሰባ እንዳያመልጠው ለሚስቱ "11 ሰዓት ቀስቅሽኝ" ብሎ በአፉ መናገር ሞት መስሎ ታየው፡፡ እና ወረቀት ላይ "ነገ የስራ ስብሰባ ስላለበኝ ወደ ሌላ ሀገር እበራለው፡፡ አደራ 11 ሰዓት ቀስቅሽኝ" ብሎ በወረቀት ፅፎ እሷ የምታየው ቦታ አስቀምጦላት ምንም ቃል ሳይተነፍስ ተኛ፡፡ ጠዋት ሰውየው ከእንቅልፉ ሲነቃ ከጠዋቱ 3ሰዓት ሆኖ በረራውም ስብሰባውም አምልጦታል፡፡ "እንዴት እንደዛ አስጠንቅቄ ነግሪያት አትቀሰቅሰኝም?" ብሎ በጣም ተበሳጨ፡፡ ከአልጋው ለመነሳት ሲሞክር አንድ ወረቀት ኮመዲኖ ላይ ተቀምጦ አየ፡፡ "11 ሰዓት ሆኗል ተነስ ስብሰባ እንዳያመልጥህ" የሚል ፁፍ ተፅፎበታል፡፡ ✍️ማነው ስህተት የሰራው? ማነው ልክ? ወዳጄ ሴትን ልጅ በተንኮልም ሆነ በፍቅር ልትበልጣት አትችልም፡፡ ዝምታ ደሞ መቼም መፍትሔ ሁኖ አያውቅም፡፡ https://t.me/eross_eross
241