cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

የሰለምቴዎች ቻናል

وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?

Більше
Рекламні дописи
3 046
Підписники
+524 години
+447 днів
+23530 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Показати все...
09:37
Відео недоступнеДивитись в Telegram
◆▮ነቢያት በባይብል▮◆ "ዳዊት (ዳውድ) የሰው ሚስት ቀምቶ አገባ ለእርሷም ብሎ 100 ሰው እና ባሏን አስገደለ እግዚአብሔር እርሱን ለመቅጣት የዳዊትን ሚስት አስደፈረ ልጁንም ገደለ?" ◍እኅት ዘሐራ ሙስጥፋ
Показати все...
▯▩ ወይይት ▩▯ "ምልጃ" ◍ ወንድም ዒምራን 🆅🆂 ◍ ወገናችን አዲሱ
Показати все...
ኤክሌሲያ ገቢር አንድ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 3፥70 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ በአላህ አንቀጾች ለምን ትክዳላችሁ? يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لِمَ تَكْفُرُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ وَأَنتُمْ تَشْهَدُونَ "ኤክሌሲያ" ἐκκλησία የሚለው የግሪኩ ቃል ከሁለት ቃላት የተዋቀረ ቃል ነው፥ እርሱም "ኤክ" ἐκ ማለትም "ከ" ከሚል መስተዋድድ እና "ካሌኦ" καλέω ማለትም "የተጠራ" ከሚል ግስ ነው። በጥቅሉ "ተጠርተው የወጡ" ማለት ነው፥ ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን ሙያዊ ፍቺው ደግሞ "ጉባኤ" "ማኅበር" "ስብሰባ" ማለት ነው፦ ሐዋ. ሥራ 7፥38 ይህ ሰው በሲና ተራራ ከተናገረው መልአክ እና ከአባቶቻችን ጋር በምድረ በዳ "በማኅበሩ" ውስጥ የነበረው ነው። οὗτός ἐστιν ὁ γενόμενος ἐν τῇ ἐκκλησίᾳ ἐν τῇ ἐρήμῳ μετὰ τοῦ ἀγγέλου τοῦ λαλοῦντος αὐτῷ ἐν τῷ ὄρει Σινᾶ እዚህ አንቀጽ ላይ በብሉይ ኪዳን በሙሴ ዘመን የነበረው ጉባኤ፣ ማኅበር፣ ስብሰባ "ኤክሌሲያ" ἐκκλησία እንደተባለ አንባቢ ልብ ይለዋል፦ ዘዳግም 9፥10 "ስብሰባ" ተደርጎ በነበረበትም ቀን እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ የነገራችሁ ቃል ሁሉ ተጽፎባቸው ነበር። καὶ ἐπ᾿ αὐταῖς ἐγέγραπτο πάντες οἱ λόγοι, οὓς ἐλάλησε Κύριος πρὸς ὑμᾶς ἐν τῷ ὄρει ἡμέρᾳ ἐκκλησίας· አሁንም እዚህ የብሉይ አንቀጽ ላይ "ስብሰባ" ለሚለው የገባው የግሪክ ሰፕቱአጀንት ቃል "ኤክሌሲያ" ἐκκλησία ነው። እዚህ ድረስ ከተግባባን ኢየሱስ በጴጥሮስ "እሠራለው" ያለው ስብስብ "ኤክሌሲያ" ተብሏል፦ ማቴዎስ 16፥18 እኔም እልሃለሁ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚህም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የሲዖል ደጆችም አይችሉአትም። κἀγὼ δέ σοι λέγω ὅτι σὺ εἶ Πέτρος, καὶ ἐπὶ ταύτῃ τῇ πέτρᾳ οἰκοδομήσω μου τὴν ἐκκλησίαν, καὶ πύλαι Ἅιδου οὐ κατισχύσουσιν αὐτῆς. "ቤተ-ክርስቲያን" ማለት ትርጉሙ "የክርስቲያን ቤት" ማለት ነው፥ "ክርስቲያን" የሚለው ቃል ለኢየሱስ ባዕድ ከመሆን ባሻገርም ዐረማዊ ሰዎች ለደቀመዛሙርቱ ያወጡላቸው የለበጣ እና የሽሙጥ ስም ነው። "ክርስቲያን" ማለት "ክርስቶሳውያን" "ቅቡዓን" "መሢሓውያን" ማለት ነው፥ ስለዚህ ግሪኩ ላይ "የክርስቲያን ቤት" የሚል የለም። ከዚያ ይልቅ "ኤክሌሲያ" ἐκκλησία የሚለው ቃል እንደተቀመጠ ልብ አድርግ! "ሐዴስ" ᾍδης ማለት "ሲዖል" "መቃብር" ማለት ነው፥ የሲዖል ደጆች አይችሉአትም የተባለችው ኤክሌሲያ በአንስታይ መደብ ብዜትን ለማመልከት የገባች "ጉባኤ" ወይም "ማኅበር" ናት፦ የሐዋርያው ሥራ 19፥41ይህንም ብሎ "ጉባኤውን" ፈታው። καὶ ταῦτα εἰπὼν ἀπέλυσεν τὴν ἐκκλησίαν. ዕብራውያን 12፥23 በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት "ማኅበር"። καὶ ἐκκλησίᾳ πρωτοτόκων ἀπογεγραμμένων ἐν οὐρανοῖς, እነዚህ ሁለቱ አናቅጽ ላይ "ጉባኤ" ወይም "ማኅበር" ለሚለው የገባው ቃል "ኤክሌሲያ" ἐκκλησία መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። "ፔትሮስ" Πέτρος ማለት "ዓለት" ማለት ሲሆን የዐረማይክ ይዘቱ "ኬፋስ" Κηφᾶς ነው፥ ኢየሱስ ጴጥሮስን፦ "ዓለት ነህ" "በዚህ ዓለት ላይ ኤክሌሲያ እሠራለው" ብሏል። ጴጥሮስም፦ "እኔ ጴጥሮስ መንፈሳዊ አባታችሁ ነኝ፥ በዚህ የሾመኝ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። "ዓለት" ተብዬ በእርሱ ዘንድ ተሹሜአለው፥ እናንተ በእኔ መሠረታት ላይ ትታነጹ ዘንድ እኔም በተሰጠኝ ችሎታ ይህንን ሠራሁኝ" ብሏል፦ ቀለሜንጦስ 10፥4 "እኔ ጴጥሮስ መንፈሳዊ አባታችሁ ነኝ፥ በዚህ የሾመኝ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። "ዓለት" ተብዬ በእርሱ ዘንድ ተሹሜአለው፥ እናንተ በእኔ መሠረታት ላይ ትታነጹ ዘንድ እኔም በተሰጠኝ ችሎታ ይህንን ሠራሁኝ"። የጴጥሮስ የተጸውዖ ስሙ "ስምዖን" ሲሆን "ጴጥሮስ" ግን የማዕረግ ስሙ ነው፥ የሮሙ ክሌመንት(ቀለሜንጦስ) ደግሞ የጴጥሮስ ተማሪ እና የጴጥሮስ ወንበር ምትክ ነው፦ ቀለሜንጦስ 10፥4 "ልጄ ቀለሜንጦስ ሆይ! የሠራሁልህን ሥርዓት በጥንቃቄ ጠብቅ"። ይህንን የክሌመንት ደብዳቤ የጻፈው እራሱ ቀለሜንጦስ ነው፥ "ካቴድራ" καθέδρα ማለት "መንበር" "ወንበር"cathedral" ማለት ሲሆን ሮም ላይ ያለው የጴጥሮስ መንበር ነው። ይህችን ኤክሌሲያ "ዓለም ዓቀፍ" ያላት የአንጾኪያው ኤጲስ ቆጶስ አግናጥዮስ በ 110 ድኅረ-ልደት ነው፥ "ክርስትና" የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ያመጣው ይህ ሰው ነው። በሮም የሞተው የአንጾኪያው ኤጲስ ቆጶስ አግናጥዮስ ለሰርምኔስ በጳፈው ደብዳቤ በግሪኩ "ካቶሊኮስ" καθολικός የሚል ቃል የተጠቀመ ሲሆን ትርጉሙ "ዓለም ዐቀፍ" በግዕዝ "ኲላዊት" በሮማይስጥ "ካቶሊክ" ነው፥ የፈረንሳዩ ኤጲስ ቆጶስ ሔራንዮስ በ 180 ድኅረ-ልደት ላይ፦ "እውነታው ያለው በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንጂ ሌላ በየትም አይደለም" ብሏል፦ የምንፍቅናዎች ተቃውሞ 3፥4 "እውነታው ያለው በኩላዊቷ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንጂ ሌላ በየትም አይደለም"። Against heresies 3፥4 "The truth is to be found nowhere else but in the Catholic Church". ይህቺ ሮም መቀመጫ ያደረገው የካቶሊክ ጉባኤ በሮም መንግሥት በቆስጠንጢኒዎስ ዕውቅና ያገኘችው በ 313 ድኅረ-ልደት ነው፥ ሮም ውስጥ የጴጥሮስ መንበር የያዘችው የካቶሊክ ኤክሌሲያ በ 325 ድኅረ-ልደት በሮሙ ንጉሥ በቆስጠንጢኒዎስ ሊቀ መንበርነት የተዘጋጀው የኒቂያ ጉባኤ በ318 ኤጲስ ቆጶሳት ማዕከል ያደረገ ነበር። በመቀጠል ታላቁ እና ፊተኛው ቴዎዶስዮስ የሮም ንጉሥ በሆነበት ዘመን በ 380 ድኅረ-ልደት ላይ ኤክሌሲያ በሮም መንግሥት ውስጥ የመንግሥት ሃይማኖት ሆነች። 381 ድኅረ-ልደት በሮሙ ንጉሥ በታላቁ እና ፊተኛው ቴዎዶስዮስ ሊቀ መንበርነት የተዘጋጀው የቆስጠንጥኒያ ጉባኤ በ150 ኤጲስ ቆጶሳት ውሳኔ የቆስጠንጥኒያ አንቀጸ እምነት ጸደቀ፥ ይህም የቆስጠንጥኒያ አንቀጸ እምነት፦ ፨በግሪክ፦ "Εἰς μίαν, ἁγίαν, καθολικὴν καὶ ἀποστολικὴν Ἐκκλησίαν"· ፨በግዕዝ፦ "ወነአምን በአሐቲ፣ ቅድስት፣ ኲላዊት ወሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን" ፨በኢንግሊሽ፦ "we believe in one, holy, Catholic and Apostolic Church". ፨በዐማርኛ፦ "በአንዲት፣ ቅድስት፣ ኲላዊት እና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን" የሚል ነው። የኤክሌሲያ አራት ምልክቶች እና ባሕርዮት "አንዲት፣ ቅድስት፣ ኩላዊት እና ሐዋርያዊት" የሚል ነው፥ ከዚያ በኃላ የተደረጉ ጉባኤያትስ? የኤክሌሲያ ታሪክ ኢንሻሏህ በክፍል ሁለት ይቀጥላል.... ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Показати все...
👍 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
አሰላሙዐለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካቱሁ ውድ ሙስሊም እህት ወንድሞቻችን! እነሆ የአል ሙኒር ቁርኣን አካዳሚ "በገጠሩ ክፍል ለበርካታ ተማሪዎች የቁርኣን ትምህርት እድል ለመፍጠር" አለም-አቀፍ  የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በ MAY 18 እና 26 /2024 በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት (ከኢሻ ሰላት በኋላ) እንደሚከናወን እያበሰርን ለፕሮግራሙ መሳካት በያላችሁበት ዱዐ እንድታደርጉና የምንለጥፋቸዉን ማስታወቂያዎች ለዘመድ ወዳጆቻችሁ ታጋሩ ዘንድ በአላህ (ሱ.ወ) ስም እንጠይቃለን። ___ ለ1 ተማሪ አመታዊ 2500 ብር ብቻ በመለገስ ቁርኣን እንዲማር ሰበብ እንሁን ____ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ : 1000626070004 ሂጅራ ባንክ :   1005552520001 ሂጅራ አጭር ቁጥር : 555252 ዘምዘም ባንክ : 0040450720101 ዘምዘም አጭር ቁጥር : 404507 ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ : 1053000066613 ___ አሜሪካና አካባቢዋ በተቅዋ ሀበሻ በኩል መለገስ ትችላላችሁ For USA Only THMWGO Zelle number 240-887-4910 for any queries, contact sister zenith mohammed 240-476-5129 ዋትስ አፕ ግሩፕ 👇👇👇 https://chat.whatsapp.com/BeWTXzCakK8C7A1BKaQqAr ቴሌግራም ሊንክ 👇👇👇 https://t.me/almuniracademy1 የዞም ሊንክ 👇👇👇 Meeting https://us02web.zoom.us/j/6138373158?pwd=bFo5ZVFrcUpWbFV5YVNZMDlwZ2piQT09 Meeting ID: 613 837 3158 Passcode: 12345
Показати все...
፨ሢሰልስ “በመቃብሯ ውስጥ አብሬ ተጋደምኩኝ” اضْطَجَعَ معها في قبرها ማለት “ወሰብኩኝ” “ተራከብኩኝ” ብሎ የተረጎመላችሁ ማን ነው? “አድጦጀዐ” اضْطَجَعَ ማለት “ተኛ” ማለት እንጂ “ወሰበ” አሊያም “ተራከበ” ማለት አይደለም። ይህ ዐረቢኛው ባይብል ላይ ኤልሳዕ ከሕፃኑ ጋር የተኛውን ለማመልከት አገልግሎት ላይ ውሏል፦ 2 ነገሥት 4፥34 መጥቶም በሕፃኑ ላይ "ተኛ"፤ አፉንም በአፉ፥ ዓይኑንም በዓይኑ፥ እጁንም በእጁ ላይ አድርጎ "ተጋደመበት"፤ የሕፃኑም ገላ ሞቀ። ثُمَّ صَعِدَ وَاضْطَجَعَ فَوْقَ الصَّبِيِّ وَوَضَعَ فَمَهُ عَلَى فَمِهِ وَعَيْنَيْهِ عَلَى عَيْنَيْهِ وَيَدَيْهِ عَلَى يَدَيْهِ እዚህ አንቀጽ ላይ “ተኛ” ለሚለው ቃል የገባው ቃል “አድጦጀዐ” اضْطَجَعَ እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። ታዲያ ኤልያስ ከሕጻኑ ጋር ወሲብ አደረገ ማለት ነውን? አዎ ካላችሁን ነብዩ ኤልሳዕ ግብረ ሰዶማዊ ነው ልትሉ ነው? ምክንያቱም ሕጻኑ ወንድ ሕጻን ነውና። አይ “ተወሰበ” “ተራከበ” ለሚለው ቃል “ነከሐ” نَكَحَ እንጂ “አድጦጀዐ” اضْطَجَعَ አይደለም" ካላችሁ እንግዲያውስ ቅጥፈታችሁን እዚህ ጋር ይብቃ! ምነው በተመሳሳይ ሙሴ ከአባቶቹ ጋር በመቃብር እንደሚተኛ ፈጣሪ ነግሮታል፥ በተጨማሪም ኢዮብ ሰው ከአጥንቱ ጋር በመቃብር እንደሚተኛ ተናግሯል። ኢሳይያስም ነብርም ከፍየል ጠቦት ጋር ይተኛል ብሏል፦ ዘዳግም 31፥16 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ እነሆ፥ *ከአባቶችህ ጋር ትተኛለህ*፤ وَقَال الرَّبُّ لِمُوسَى: «هَا أَنْتَ تَرْقُدُ مَعَ آبَائِك ኢዮብ 20፥11 አጥንቶቹ ብላቴንነቱን ሞልተዋል፤ ነገር ግን ከእርሱ ጋር በመሬት ውስጥ "ይተኛል"። عِظَامُهُ مَلآنَةٌ قُوَّةً وَمَعَهُ فِي التُّرَابِ تَضْطَجِعُ. ኢሳይያስ 11፥6 ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋር ይቀመጣል፥ ነብርም ከፍየል ጠቦት ጋር "ይተኛል"፤ فَيَسْكُنُ الذِّئْبُ مَعَ الْخَرُوفِ وَيَرْبُضُ النَّمِرُ مَعَ الْجَدْيِ وَالْعِجْلُ ሰው በመሬት ውስጥ “ይተኛል” ለሚለው ቃል የወደፊት ግስ የተጠቀመበት “ተድጦጂዑ” تَضْطَجِعُ ሲሆን የእርሱ አላፊ ግስ “አድጦጀዐ” اضْطَجَعَ ነው፥ እና ሰው አፈር ውስጥ ወሲብ ያረጋል ማለቱ ነውን? እረ “መተኛት” ሲባል "ተራክቦ ወይም ወሲብ ማለት አይደለም" ካላችሁ እንግዲያውስ ቅጥፈት ይብቃ! ከላይ ያለውን ዶዒፍ ሐዲስ በዚህ ስሌትና ቀመር ተረዱት። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Показати все...
ቅጥፈት ይብቃ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 16፥105 ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አንቀጾች የማያምኑት ብቻ ናቸው፤ እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው፡፡ إِنَّمَا يَفْتَرِي الْكَذِبَ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ ۖ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْكَاذِبُونَ ግብጻዊ ቄስ ዘካሪያስ لَعْنَتَ اللَّهِ عَلَيْهِ ሁልጊዜ ለሚቀጥፈው ቅጥፈት ምላሽ ሲሰጠው እየተገለባበጠ ኢሥላምን የሚያጠለሽበት ጥላሸት ለመፈለግ ቀን ከሌሊት ይዳክራል፥ ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አንቀጾች የማያምኑት ብቻ ናቸው። እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው፦ 16፥105 ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አንቀጾች የማያምኑት ብቻ ናቸው፤ እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው፡፡ إِنَّمَا يَفْتَرِي الْكَذِبَ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ ۖ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْكَاذِبُونَ ከቀጠፈው ቅጥፈት አንዱ ነቢያችንን”ﷺ” ከሬሳ ጋር ተራክቦ እንዳደረጉ አድርጎ መቅጠፉ ነው፥ ወሊ-አዑዝቢሏህ እኔ ለደገሙት ቃል ሰቀጠጠኝ። ኅሊናውን ለሸጠ ሰው እና ሐሰትን ለተከናነበ ሰው ይህን ማድረግ ውስጡን ሰላም አይሰጠውም። እስቲ የሚያነሳቸውን ሐዲሳት እንመልከት፦ ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 23, ሐዲስ 98 አነሥ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ ”የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ሴት ልጅ የቀብር ሥርአት ላይ ነበርን፤ የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” በመቃብር አቅራቢያ ተቀምጠው ዓይኖቻቸው በእንባ ሞልተው አየዋቸው፤ እርሳቸውም፦ “ከመካከላችሁ በዚህ ሌሊት ከሚስቱ ጋር ተራክቦ ያላደረገ አለን? አሉ፤ አቡ ጠልሓህም፦ “እኔ አለሁ” ብሎ መለሰ፤ እርሳቸውም፦ “ወደ መቃብሯ ውረድ” አሉት፤ እርሱም ወደ መቃብሯ ወረዶ ቀበራት"። عَنْ أَنَسٍ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ شَهِدْنَا بِنْتَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَرَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم جَالِسٌ عَلَى الْقَبْرِ، فَرَأَيْتُ عَيْنَيْهِ تَدْمَعَانِ فَقَالَ ‏”‏ هَلْ فِيكُمْ مِنْ أَحَدٍ لَمْ يُقَارِفِ اللَّيْلَةَ ‏”‌‏.‏ فَقَالَ أَبُو طَلْحَةَ أَنَا‏.‏ قَالَ ‏”‏ فَانْزِلْ فِي قَبْرِهَا ‏”‌‏.‏ فَنَزَلَ فِي قَبْرِهَا فَقَبَرَهَا‏.‏ ከመነሻው እዚህ ሐዲስ ላይ፦ "እከሌ ከሬሳ ጋር ወሲብ ፈጸመ" የሚል ሽታው እንኳን ቢፈለግ የለም፥ ውሸት ሲጋለጥ ከዚህ ይጀመራል። ሲቀጥል “ኔክሮፊሊያ”Necrophilia” ማለት ከሬሳ ጋር የሚደረግ ተራክቦ ነው፥ በኢሥላም አይደለም ከሞተ ሰው ይቅርና በቁም ካለ ሰው ጋር ተራክቦ ለማድረግ ኒካሕ ይወጅባል። እስቲ ሁለተኛውን ሐዲስ እንመልከት፦ ከንዙል ዑማል 242218 ኢብኑ አባስ እንደተረከው የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ ”የጀነትን ልብስ እስከምትለብስ ልብሴን አለበስኳት፣ በመቃብሯ ውስጥ አብሬ ተጋደምኩኝ፣ ምናልባት የመቃብሩ ጫና ይቀንሳል ብዬ። ለእኔ ከአቡ ጠሊብ በኃላ ከአላህ ፍጥረት በላጭ ናት። ነቢዩም”ﷺ” ይህንን ያሉት የዐሊይ እናት ስለሆነችው ስለፋጢማ ነበር"። “ከንዙል ዑማል” كنز العمال ማለት “የሠናይ ገባሪ ጥሪኝ” ማለት ነው፥ ዐሊ ኢብኑ ዐብዱል ማሊክ አል-ሂንዲ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 1517 ድህረ-ልደት ያዘጋጀው ሐዲስ ነው። ፨ሲጀመር ይህ ሐዲስ ከመነሻው ዶዒፍ ነው። ፨ሲቀጥል የዐሊይ እናት ለነቢያችን”ﷺ” አክስት ናት፥ ከአቡ ጠሊብ ጋር ሆና ያሳደገቻቸው እርሷ ናት። ከአክስት ጋር አይደለም ሞታ ወሲብ ይቅርና በቁምም ከአክስት ጋር ጋብቻ ክልክል ነው፦ 4፥23 እናቶቻችሁ፣ ሴት ልጆቻችሁም፣ እኅቶቻችሁም፣ "አክስቶቻችሁም፣ የሹሜዎቻችሁም፣" የወንድም ሴቶች ልጆችም፣ የእኅት ሴቶች ልጆችም፣ እነዚያም ያጠቡዋችሁ እናቶቻችሁ፣ ከመጥባት የኾኑትም እኅቶቻችሁ፣ የሚስቶቻችሁም እናቶች፣ እነዚያም በጉያዎቻችሁ ያሉት የእነዚያ በእነርሱ የገባችሁባቸው ሚስቶቻችሁ ሴቶች ልጆች፣ "ልታገቧቸው በእናንተ ላይ እርም ተደረጉባችሁ"፡፡ حُرِّمَتْ عَلَيْكُمْ أُمَّهَاتُكُمْ وَبَنَاتُكُمْ وَأَخَوَاتُكُمْ وَعَمَّاتُكُمْ وَخَالَاتُكُمْ وَبَنَاتُ الْأَخِ وَبَنَاتُ الْأُخْتِ وَأُمَّهَاتُكُمُ اللَّاتِي أَرْضَعْنَكُمْ وَأَخَوَاتُكُم مِّنَ الرَّضَاعَةِ وَأُمَّهَاتُ نِسَائِكُمْ وَرَبَائِبُكُمُ اللَّاتِي فِي حُجُورِكُم مِّن نِّسَائِكُمُ اللَّاتِي دَخَلْتُم بِهِنَّ فَإِن لَّمْ تَكُونُوا دَخَلْتُم بِهِنَّ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ وَحَلَائِلُ أَبْنَائِكُمُ الَّذِينَ مِنْ أَصْلَابِكُمْ وَأَن تَجْمَعُوا بَيْنَ الْأُخْتَيْنِ إِلَّا مَا قَدْ سَلَفَ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا
Показати все...