uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Відкрити в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 16 047 підписників, посідаючи 5 283 місце в категорії Релігія і духовність та 2 238 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 16 047 підписників.

За останніми даними від 26 жовтня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на 518, а за останні 24 години на 5, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 25.13%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 10.43% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 4 033 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 1 674 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 29.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 27 жовтня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Релігія і духовність.

16 047
Підписники
+524 години
+1057 днів
+51830 днів
Архів дописів
#ከሰይጣን_ጋር_የተደረገ_ቃለ_ምልልስ (#ተዋስኦተ_ጳውሊ_ምስለ_ሰይጣን_)፤ #ክፍል፪_ #ሰይጣን_ምንጊዜም_ቢሆን_እንደየሰው_ምኞትና_ፍላጎት፥ #እንደ_ጊዜውና_እንደ_ሰዐቱ፥ #እንደ_ዘመኑና_እንደ_ወቅቱ_ተጨባጭ_ሁኔታ_የማሳት_ጥበቡን_እየለዋወጠ_ይጠቀማል፡፡ (ሳኦል የአማሌቃውያንን ምርኮ ባገኘበት ወቅት፣ ሐናንያ ገንዘብ በእጁ በገባበት ወቅት ሰይጣን እንደፈተናቸው ልብ ይሏል /ሐናንያ ሆይ መንፈስ ቅዱስን ታታልል ዘንድ ከመሬቱ ሽያጭ ታስቀር ዘንድ ሰይጣን በልብህ ስለምን ሞላ?፡፡›› ሐዋ. ፭፥፫/ እኛንም እንዲሁ እንደ ዘመናችን ሁኔታ መልኩን እየለዋወጠ ይፈትነናል፡፡ እርሱ የ7511 ዓመታት የመፈተን የሥራ ልምድ ያለው ነውና!!፡፡ ##መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም የመጣውና መጽሐፍ ቅዱስም የተጻፈበት ዐቢይ ጉዳይ ሰይጣን በሰው ልጆች ላይ እያደረሰ ካለው ጉዳትና ጥፋት ለመታደግና ችግሩንም በዝርዝር ለማሳወቅና ሰዎችም የሰይጣንን ክፉ ሥራ ዐውቀው እንዲርቁ ለማድረግ ነው፡፡ /‹‹የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ፡፡›› ፩ዮሐ. ፫፥፰/ ‹‹በእኔም የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር እኔ ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፡፡›› ዮሐ. ፲፪፥፵፮ ***ነገር ግን ጌታችን ወደዚህ ዓለም በመምጣቱ፤ ሰው በመሆኑ ይህ የሕይወት ብርሃን ለዓለም ቢበራም፤ ሁሉም #ሰው ነፃ ፈቃዱን ተጠቅሞ ከዲያብሎስ ሽንገላ ለመላቀቅ ፈቃደኛ አለመሆኑን ተመልክቶ /‹‹ወደ ሕይወት የሚወስደው በር የጠበበ መንገዱም የቀጠነ ነውና የሚገቡትም ጥቂቶች ናቸው፡፡›› ብሏል ማቴ. ፯፥፲፬/ ጌታችን እንዲህ ያለው ሰዎች ነፃ ፈቃዳቸውን ተጠቅመው የሰይጣንን ፈቃድ በመፈጸም በፈቃደ ሥጋቸው ስለሚመሩና የእርሱን ትዕዛዝ ለመፈጸም ደስተኛና ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ለመግለጽ እንጂ ወደ ሕይወት የሚወስደው መንገድ የሚጠብ ሁኖ አይደለም፡፡ ይህ የሕይወት መንገድ የሚሰፋው የራስ ፈቃደኝነት ሲታከልበት ነው፡፡ #ለሰው ልጅ ወደ ሕይወት ለመግባት ወሳኙ ነገር ፈቃደኝነት ነው፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ ቢሆንም የሰውን ልጅ ሲፈጥረው ነጻ ፈቃድ ያለው አድርጎ ስለፈጠረው መልካሙን ነገር ሊያደርግ በሚፈልግበት ጊዜ ፈቃደኝነታቸው ይጠይቃል፡፡ /ድውያንን ሲፈውስ ልትድን ትወዳለህን እያለ የሚጠይቃቸውን ልብ ይሏል፡፡ ዮሐ. ፭፥፮/ #የራስ ፈቃደኝነት ካለ ትእዛዛትን መጠበቅ ቀላል ይሆናል፡፡ /የዘለዓለምን ሕይወት እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ ብሎ ለጠየቀው ሀብታም ጎልማሳ ‹‹ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ትእዛዛትን ጠብቅ … ፍጹም ልትሆን ብትወድ ሂደህ ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፤ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፡፡›› ነገር ግን ሀብታሙ ጎልማሳ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ታላቅ ሐዘን ተሰምቶታል፡፡ ማቴ. ፲፱፥፳፩/ #ጽድቅ፣ ቅድስናና ሰይጣንን ማሸነፍ የሚመጣው በራስ ፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ #አንድ_ሰው_በፍጹም_ትሕትና_ትእዛዛትን_ለመጠበቅ_የራስ_ፈቃደኝነት_ካለውና_ንስሐ_ከገባ__በቀላሉ_ሰይጣንን_የሚያሸንፍበት_ኀይል_ከእግዚአብሔር_ያገኛል፡፡ ሰይጣንም የብዙ ዘመን ልምድ ስላለው ይህን ሁኔታ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ሰዎች፤ ++ሰዎች ትእዛዛትን ለመጠበቅ የራስ ፈቃደኝነት እንዳይኖራቸው የተለያየ ምክንያት በመፍጠር አጥብቆ ይዋጋቸዋል፡፡ ++ሰዎች ትእዛዛትን ሊጠብቁና ንስሐ ሊገቡ ሲያስቡ በታላቅ ፍርሃትና ስጋት እንዲያዙ ያደርጋቸዋል፡፡ ++ሰዎችን ሕግና ትእዛዛትን መፈጸም ከባድና ጭንቅ፥ በሩም የጠበበ፥ ፈጽሞም የማያሳልፍ አድርጎ ያሳያቸዋል፡፡ ++ሰዎች ትእዛዛትን የሚጠብቁና በቁርጠኝነት ንስሐ የሚገቡ ከሆነ በዚህ ምድር ላይ መኖር እንደማይችሉና ታላቅ ጉዳት እንደሚደርስባቸው ደጋግሞ በማሳሰብና በማስፈራራት ያሳምናቸዋል፡፡ … ነገር ግን በፍጹም ትሕትናና በራስ ፈቃደኝነት ትእዛዙን በመጠበቅና ንስሐ በመግባት ከዚህ ሰይጣናዊ ውጊያ ነጻ ይወጣሉ፤ ነጻ ሲወጡም በሰይጣን አሳሳቢነትና ማስፈራርት ከባድ መስሎ ይታያቸው የነበረው ትእዛዛት ለእነርሱ የደስታና የሰላም ምንጭ ይሆንላቸዋል፡፡ /ይህንንም በሐዋርያትና በቅዱሳንና ቅዱሳት ሕይወት ታውቋል ማቴ. ፲፩፥፳፰/ ከእውነተኛ (መንፈሳዊ) ሕይወት ርቀው የሚኖሩ ሰዎች በጥቂት የፈተና ሰዐት ስንኳ መታገሥና መረጋጋትን፥ ሰላማዊነትንና አስተዋንትን አጥተውና ተስፋ ቆርጠው ለከፋ ችግር የሚጋለጡት አስቀድሞ የጠጠጋቸው ሰይጣናዊ መንፈስ ስለሚያስጨንቃቸውና ስለሚያስፈራራቸው ነው፡፡ #የሰው ልጅ በምድር ላይ እስካለ ድረስ በጥንተ ጠላቱ ሰይጣን በየጊዜው መፈተኑ አይቀሬ በመሆኑ /ዘፍ. ፫፥፲፭/ ውጊያውም ከደምና ከሥጋ ጋር ሳይሆን ከጨለማ ዓለም ገዦች፣ ከአለቆችና ከሥልጣናት እንዲሁም ከረቂቃን ሰይጣናት ከዲያብሎስ ሠራዊት ጋር በመሆኑ፤ ፈተናውን ለማለፍ የሰይጣን መግቢያ የሆኑ ቀዳዳዎችን ለመድፈን እንዲያስችለው መንፈሳዊ ዝግጅት ማድረግ አለበት፡፡ ከኃጢአት ንጹሕ ሁኖ ሀብተ መንፈስ ቅዱስን ገንዘብ ያደርግ ዘንድ ስለሰይጣን አስከፊነት በእጅጉ መማርና ማወቅ፥ መረዳትና ማስተዋል ይገባዋል፡፡ +‹‹ከሚመጣው ሁሉ መዳን ትችሉ ዘንድና በሰው ልጅ ፊትም ለመቆም እንድትችሉ ሁል ጊዜ በጸሎት ትጉ፡፡›› ሉቃ. ፳፩፥፮ +‹‹ለጸሎት ትተጉ ዘንድ … ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ ደግሞ አብራችሁ ሁኑ፡፡›› ፩ቆሮ. ፯፥፭ +‹‹የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ፡፡›› ኤፌ. ፮፥፲፩ +‹‹በመጠን ኑሩ፥ ንቁም ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፡፡›› ፩ጴጥ. ፭፥፰ +‹‹በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፤ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት፡፡›› ኤፌ. ፬፥፳፯ #አንድ ሰው ካመነና ከተጠመቀ በኋላ ስለሰይጣን ክፋትና ተንኮል ጥልቅ እውቀት ከሌለውና በመንፈሳዊ ትሩፋት የማይተጋ ከሆነ በቀላሉ ተመልሶ በሰይጣን አገዛዝ ሥር ይወድቃል፡፡ ከዚያ በኋላም ሕይወቱ በእጅጉ የከፋ ይሆንበታል፡፡ /‹‹ርኩስ መንፈስ ከሰው ከወጣ በኋላ ዕረፍት ለማድረግ ፈልጎ ውኃ ወደሌለበት ምድረ በዳ ይዞራል፤ አያገኝም፡፡ ከዚህም በኋላ እንግዲህስ ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ ይላል፡፡ በመጣም ጊዜ ባዶ ሁኖ ተጠርጎና ተጊጦ ያገኘዋል፤ ከዚህም በኋላ ይሄዳል፤ ከእርሱም የሚከፉ ሌሎች ሰባት አጋንንትን ያመጣል፤ ገብተውም በዚያ ይኖራሉ፤ ለዚያም ሰው የኋላ ኑሮው ከፊተኛው የከፋ ይሆናል፡፡›› ማቴ. ፲፪፥፵፫ ‹‹በጌታችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ ዳግመኛ በእርሷ ተጠልፈው ከተሸነፉ ከፊተኛው ኑሯቸው ይልቅ የኋለኛው ኑሯቸው የባሰና የከፋ ይሆንባዋቸዋል፡፡›› ፪ጴጥ. ፪፥፳/፡፡ ሰዎች ዳግመኛ በሰይጣን ሽንገላ ተታለው በዓለም ርኵሰት እንዳይወድቁ የሚረዳ እውቀት ማግኛ የሚሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብና ማወቅ እንዲረዳ መምህረ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ ፲፭፥፬ ላይ .. መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ ይሆንልን ዘንድ አስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፏልና ብሎ እንደተናገረው:: #ቀሲስ_ጳውሊ_ወደ_ጭፈራ_ቤት_የሚሄዱትን_ሰዎች_የሚያስተውን_ሰይጣን_በዙ_ጥያቄዎችን_ሊጠይቀው_እንደገዘተው፤ #ሰይጣን_ሰዎችን_እንዴት_እንደሚፈትንና_ኃይል_እንዴት_እንደሚያገኝ_፤ #ክፍል_፫ _.… #ይቀጥላል_ይጠብቁን_/ #በፌስቡክ_ሊያገኙን_ከፈለጉ_፤ የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔዓለምና ደ/ትጉሃን ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት፡፡ #በቴሌግራም_ሊያገኙን_ከፈለጉ_፤ https://t.me/medihanaelem

#የዐቢይ_ጾም_የሱባኤ_መርሐ_ግብር፡፡ ፠ከሰኞ የካቲት 16 - ዐርብ የካቲት 20/2012 ዓ.ም. *ጠዋት ጠዋት ከ12-1 ሰዐት፤ የማኅበር ጸሎት *ማታ ማታ፤ ከ12፡30-2፡00 ሰዐት መሐረነ አብ ጸሎትና ትምህርት፡፡ ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

በዐቢይ ጾም በተከታታይ ክፍል፤ ሰኞና ኀሙስ፡፡ #ከሰይጣን_ጋር_የተደረገ_ቃለ_ምልልስ (ተዋስኦተ ጳውሊ ምስለ ሰይጣን)፤ #ክፍል_፩ ፠ ‹‹እነሆ በትዕግስት የጸኑትን ብፁዓን እንላቸዋለን፤ ኢዮብ እንደታገሠ ሰምታችኋል፥ ጌታም እንደፈጸመለት አይታችኋል፡፡›› ያዕ. ፭፥፲፩ ሰይጣንን በዘመናቸው ታግሰው ያሸነፉ ሰዎች ልቡናቸው አስተሳሰባቸው አጠቃላይ አኗኗራቸው ንጹሕና ቅዱስ ስለሚሆን ፍጹም ይቅር ባይና ቸሮች ርኅሩኆችና አዛኞች ናቸው፤ ሐዘኔታቸውም ለወዳጆቻቸውም ብቻ ሳይሆን ለጠላቶቻቸው ጭምር ነው (ቅዱስ ዳዊት /፩ኛ ሳሙ. ፳፬፥፲፰/ ና ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን /ሐዋ. ፯፥፰/ ልብ ይሏል) ቅዱሳን ከሰው ልጆች አልፈው ለአራዊት፣ ለአዕዋፍና ለእንስሳ እንዲሁም ለታላቁ ጠላት ለሰይጣን ሳይቀር የሚያዝኑ ናቸው፡፡ (ነቢዩ ሳሙኤል /፩ኛ ሳሙ. ፲፮፥፩/፣ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን /ገድለ ክርስቶስ ሰምራ/ ልብ ይሏል::) ፠ ቅዱሳን ሰዎች እንዲህ ዓይነቱን ጸጋ ሊያገኙ የሚችሉት የሰይጣንን ክፋት ለይተው ተረድተው ሰይጣንን በፍጹም ትዕግስትና ትሕትና ማሸነፍ በመቻላቸውና ከሰይጣን ባርነት ነጻ ወጥተው የእግዚአብሔርን መንፈስ ገንዘብ በማድረጋቸው ነው፡፡ ፠፠ በተቃራኒ ደግሞ በዓለም ላይ ለተፈጠሩትና እየተፈጠሩም ላሉት ችግሮች መንስኤያቸውና ምንጫቸው የሰይጣን ሰለባና ማደሪያ በሆኑ ሰዎች አማካይነት የሚከሠት ነው፡፡ (ቃዔልን /ዘፍ.፬፥፰፣ ሄሮድስን /ማቴ. ፪፥፲፮/፣ አምኖንን /፪ኛ ሳሙ. ፲፫፥፩/፣ ሰዶማውያንን /ዘፍ. ፲፱፥፩፣ ሮሜ. ፳፮፥፳፱፣ ፪ጴጥ. ፪፥፮/ …. ሌሎችንም …. ልብ ይሏል፡፡ ምክንያቱም፤ *ሰይጣን ተዘክሮተ እግዚአብሔርንና መንፈሳዊ ተግባራትን ካስተወ በኋላ በኃጢአት ላይ ኃጢአት እንዲጨምሩ እንጂ *ሰይጣን ኃጢአትን በቃኝ እንዳይሉ ስለሚያደርጋቸው ነው /ዘዳ. ፮፥፲፫/፡፡ *ሰይጣን ኃጢአትንም ተዉ ብሎ በሚመክራቸው ሰው ላይ በጠላትነት እንዲነሳሡ ያደርጋቸዋል፡፡ *ሰይጣን ቀና የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ክፉ አስመስሎ ስለሚያሳያቸው ቅን አሳቢዎችንና ለመልካም ሥራ የተሰለፉትን እንዲጠሉ ያደርጋቸዋል፡፡ *ሰይጣን ቅን አስተሳሰብን መንፈሳዊ ሥራን ሰላምን ፍቅርን ርኅራኄን ከውስጣቸው አሟጦ አውጥቶ የራሱን መንፈስ ስለሚሞላባቸው ማንኛውንም ዓይነት ወንጀል ቢሠሩ ወንጀል የሠሩና ጥፋት ያጠፉ አይመስላቸውም፡፡ እውነተኛ ሕይወት እንደሚኖሩ ያስመስላቸዋልም፡፡ *ሰይጣን ዲያብሎስ የጥፋተኝነት ስሜት እንዳይሰማቸው ስለሚያደርጋቸው ለጥፋታቸው ገደብ የለውም፡፡ ፠ ##መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ከሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም የተወለደው ሰው ሁሉ የሰይጣንን የክፋት ሥራ ተረድቶ ከሰይጣን እንዲሸሽና የእግዚአብሔርን ልጅነት አግኝቶ የዘለዓለም ሕይወት መንግሥተ ሰማያትን እንዲወርስ ለማድረግ ነው፡፡ /‹‹ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፡፡ ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ኃጢአትን ያደርጋልና፤ ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ፡፡ ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔር ተወልዷልና ኃጢአትን ሊያደርግ አይችልም፡፡ የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ የተገለጡ ናቸው፡፡›› ፩ዮሐ.፫፥፰/ /‹‹ክፉ ፍሬ የሚያፈራ መልካም ዛፍ የለምና እንዲሁም መልካም ፍሬ የሚያፈራ ክፉ ዛፍ የለም፡፡ ዛፍ ሁሉ ከፍሬው ይታወቃልና፤ …. መልካም ሰው ከመልካም ልቡ መልካሙን ያወጣል፡፡›› ሉቃስ ፮፥፵፫/ #ማንኛውም ሰው በሚሠራው ሥራ የማን ወገንና የማን ማደሪያ እንደሆነ ለመረዳትና ራሱንም ለመፈተሸ ይችላል፡፡ ፠ ##ጠላት ዲያብሎስ ንስሐ ገብተን መንግሥተ ሰማይትን እንዳንወርስ ማድረግ ብቻ ሳይሆን በሥጋዊ ኑሯችንም ቢሆን በተገቢው ሰዐትና ጊዜ ተምረን ተገቢውን እውቀት ይዘን ሥራችንን በተገቢው ሰዐትና ጊዜ እንዳንሠራ በማድረግ፤ ሠርተንም እንዳንጠቀም ዕንቅፋት በመፍጠር (በስንፍናና በውሸት፤ በዝሙትና በስካር፤ በቃሚነትና በአጫሽነት፤ በጨፋሪነትና በዳንሰኛነት፤ በስርቆትና በአጭበርባሪነት፤ …. በተለያዩ የኃጢአት አሸክላዎች ተብትቦ ይይዘናል፤ እንዲህ ካደረገን በኋላም ሰይጣን በሚያመነጭልን አእምሯዊ ስሜትና ጭፍን አስተሳሰብ እየነዳን መልካም ሥራን ለሚሠሩ ለእውነተኛ ሰዎች እንቅፋት እንድንሆን በመሣሪያነት ይጠቀምብናል፡፡ /‹‹ወደ እናንተ ልንመጣ ወደን ነበር … አንድና ሁለት ጊዜ ሰይጣን አዘገየን፡፡›› ፩ተሰ. ፪፥፲፰/ /አንተ (ኤልማስ የተባለ አስማተኛን/ ተንኮልንና ክፋትንም ሁሉ የሞላብህ የዲያብሎስ ልጅ የጽድቅም ሁሉ ጠላት የቀናውን የጌታን መንገድ ከማጣመም አታርፍምን?›› ሐዋ. ፲፫፥፮/ /እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁን ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ፡፡ እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለሌለ በእውነት አልቆመም፡፡ ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፡፡ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና፡፡›› ዮሐ. ፰፥፵፬/ #ከላይ ባየነው ዓይነት ሕይወት ሰይጣን በእጁ ያደረጋቸውን ሰዎች፤ **ለሕይወታቸው ጠቃሚ ምክርና ትምህርት በሚሰጣቸው ሰዐት ወዲያው እንዲዘነጉትና እንዳይቀበሉት ያደርጋል፡፡ /‹‹ወዲያው እንደሰሙ ሰይጣን መጥቶ በልባቸው የተዘራውን ቃል ይወስዳል፡፡›› ማር. ፬፥፲፭/ **ቢመከሩም ምክርን አይሰሙም አይቀበሉምም፤ /ይሁዳ ሕይወት የሚሆን የጌታን ትምህርት አልሰማ ብሎ ነው ጌታን አሳልፎ የሰጠው፡፡ ማቴ. ፳፮፥፵፱/ /አምኖንም የእኅቱን የትዕማርን ምክር አልሰማ ብሎ ነው አስነዋሪ ጥፋት በእኅቱ ላይ የፈጸመው፡፡ ፪ሳሙ. ፲፭፥፲፱/ /እንዲሁም ደግሞ ሳዖልም የነቢዩ ሳሙኤልን ምክር አልሰማ ብሎ ነው ከአማሌቃውያን ለማረከው ምርኮ በመሣሣት ክፉ መንፈስ ሊያድርበትና በጠላት እጅ ሊወድቅ የቻለው፡፡ ፩ሳሙ. ፲፭፥፲፱/ /#ከሰይጣን_ጋር_የተደረገ_ቃለ_ምልልስ (ተዋስኦተ ጳውሊ ምስለ ሰይጣን)፤ #ክፍል_፪_ #ሰይጣን_ምንጊዜም_ቢሆን_እንደየሰው_ምኞትና_ፍላጎት፥ #እንደ_ጊዜውና_እንደ_ሰዐቱ፥ #እንደ_ዘመኑና_እንደ_ወቅቱ_ተጨባጭ_ሁኔታ_የማሳት_ጥበቡን_እየለዋወጠ_ይጠቀማል፡፡ .… ይቀጥላል ከነገ ወዲያ ይጠብቁን/ #በፌስቡክ_ሊያገኙን_ከፈለጉ_፤ የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔዓለምና ደ/ትጉሃን ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት፡፡ #በቴሌግራም_ሊያገኙን_ከፈለጉ_፤ https://t.me/medihanaelem

እናስተዋውቅዎ፤ ቢከታተሏቸው ይጠቅማሉ የምንላቸው ገጾች እናስተዋውቃችሁ፤ #ዐበይትና_ዐይናማ_መምህራንና_ሊቃውንት_ትምህርት_የሚሰጡበት_ገጽ፤ Kofeda Tube ኮፌዳ ቲዩብ #Kofeda_Tube http
እናስተዋውቅዎ፤ ቢከታተሏቸው ይጠቅማሉ የምንላቸው ገጾች እናስተዋውቃችሁ፤ #ዐበይትና_ዐይናማ_መምህራንና_ሊቃውንት_ትምህርት_የሚሰጡበት_ገጽ፤ Kofeda Tube ኮፌዳ ቲዩብ #Kofeda_Tube https://www.youtube.com/channel/UC55ZqqlOX090QK9X_5L-zMg/featured (እነሆ ለሕዝቡ የሚሆን ታላቅ ደስታ …. ሠለስቱ አዕማድ/ሦስቱ ምሰሶዎች/ ቀጭን ጥያቄ? አጭር መልስ …..) … ሌሎችንም ትምህርቶች ያገኛሉ፡፡ ለሌሎችም ያጋሩ፨

ክብር ለአባቶቻችን አምላክ ይሁን፡፡ የማንቂያ ደወል ከአዲስ አበባ ውጭ ለመጀመሪያ ጊዜ በምሥራቅ ሸዋ ናዝሬት (አደማ) ከተማ ምሥራቀ ፀሐይ ማርያም፤ እልፍ አእላፋት (በመቶ ሺህ የሚቈጠሩ) ክርስቲያኖ
+6
ክብር ለአባቶቻችን አምላክ ይሁን፡፡ የማንቂያ ደወል ከአዲስ አበባ ውጭ ለመጀመሪያ ጊዜ በምሥራቅ ሸዋ ናዝሬት (አደማ) ከተማ ምሥራቀ ፀሐይ ማርያም፤ እልፍ አእላፋት (በመቶ ሺህ የሚቈጠሩ) ክርስቲያኖች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡ የማንቂያ ደወሉ ሰኞ በአዲስ አበባ ይቀጥላል፡፡

#ዘወረደ_መዝሙር፣ #ምንባባት፣ #ምስባክ፣ #ወንጌል መዝሙር ዘወረደ፤ተቀነዩ ለእግዚአብሔር ሃሌ ሉያ ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት በፍርሃት ወተኃሠዩ ሎቱ በረዓድ፤ /መዝ.፪፥፲፩/ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ፤ ባኡ ቅድሜሁ በተጋንዮ ወውስተ አዕጻዲሁ በስብሐት እመንዎ፤ /መዝ.፺፫፥፫-፭/ እስመ … ንጹም ጾመ ወናፈቅር ቢጸነ ፥ ወንትፋቀር በበይናቲነ፤ እስመ … አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ እስመ ሰንበትሰ በእንተ ሰብእ ተፈጥረት፤/ማቴ.፲፪፥፰/ እስመ … ምሕረተ ወፍትሐ አሀሊ ለከ እዜምር ወእሌቡ ፍኖተ ንጹሐ፤ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ አባግዓ መርዔቱ፨ ትርጕም፤ እግዚአብሔርን በመፍራት ተገዙለት፤ለእርሱ መገዛትም ደስ ያሰኛችሁ፡፡ እግዚአብሔር ቸር ምሕረቱም ለዘለዓለም፣ እውነቱም ለልጅ ልጅ ነው፡፡ እኛስ ሕዝቡ የመሰማርያው በጎች ነን፡፡ ወደ ደጁ በመገዛት፤ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፤ ጾምን እንጹም፤ ጓደኞቻችንን እናፍቅር፤ እርስ በርሳችንም እንፋቀር፡፡ ሰንበት ስለሰው ተሠርታለችና፤ ሰንበትን እናክብር፡፡ እውነትንም እንሥራ፤ አቤቱ ምሕረትንና ፍርድን እቀኝልሃለሁ፤ እዘምራለሁ፤ ንጹሕ መንገድንም አስተውላለሁ፡፡ #ምንባባት †ዕብ.13÷7-17፤ ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ለእርሱ እናቅርብ፡፡ /ቊ.7/ †ያዕ.4÷7-17፤ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ፡፡ /ቊ.7/ †የሐዋርያት ሥራ 25፥13-27        #ምስባክ፤ መዝ. ፪÷፲፪ ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት፤ ወተሐሰዩ ሎቱ በረዓድ፤ አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመአዕ እግዚአብሔር፡፡ (ትርጕም፤ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፤ በረዓድም ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር እንዳይቆጣ ጥበብን አጥኗት፡፡)        #ወንጌል፤ ዮሐ. ፫÷፲-፳፭ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን፡፡ /ቊ. ፲፩/)        #ቅዳሴ፤ ቅዳሴ ዘእግዚእነ ꕥꕥꕥ ፨፨፨ ꕥꕥꕥ #ዘወረደ_መዝሙር፣ #ምንባባት፣ #ምስባክ፣ #ወንጌል በድምፅ ከፈለጉ በቴሌግራም አድራሻችን ያገኛሉ፡፡ ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

#ዘወረደ_መዝሙር፣ #ምንባባት፣ #ምስባክ፣ #ወንጌል መዝሙር ዘወረደ፤ተቀነዩ ለእግዚአብሔር ሃሌ ሉያ ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት በፍርሃት ወተኃሠዩ ሎቱ በረዓድ፤ /መዝ.፪፥፲፩/ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ፤ ባኡ ቅድሜሁ በተጋንዮ ወውስተ አዕጻዲሁ በስብሐት እመንዎ፤ /መዝ.፺፫፥፫-፭/ እስመ … ንጹም ጾመ ወናፈቅር ቢጸነ ፥ ወንትፋቀር በበይናቲነ፤ እስመ … አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ እስመ ሰንበትሰ በእንተ ሰብእ ተፈጥረት፤/ማቴ.፲፪፥፰/ እስመ … ምሕረተ ወፍትሐ አሀሊ ለከ እዜምር ወእሌቡ ፍኖተ ንጹሐ፤ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ አባግዓ መርዔቱ፨ ትርጕም፤ እግዚአብሔርን በመፍራት ተገዙለት፤ለእርሱ መገዛትም ደስ ያሰኛችሁ፡፡ እግዚአብሔር ቸር ምሕረቱም ለዘለዓለም፣ እውነቱም ለልጅ ልጅ ነው፡፡ እኛስ ሕዝቡ የመሰማርያው በጎች ነን፡፡ ወደ ደጁ በመገዛት፤ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፤ ጾምን እንጹም፤ ጓደኞቻችንን እናፍቅር፤ እርስ በርሳችንም እንፋቀር፡፡ ሰንበት ስለሰው ተሠርታለችና፤ ሰንበትን እናክብር፡፡ እውነትንም እንሥራ፤ አቤቱ ምሕረትንና ፍርድን እቀኝልሃለሁ፤ እዘምራለሁ፤ ንጹሕ መንገድንም አስተውላለሁ፡፡ ምንባባት †ዕብ.13÷7-17፤ ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ለእርሱ እናቅርብ፡፡ /ቊ.7/ †ያዕ.4÷7-17፤ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ፡፡ /ቊ.7/ †የሐዋርያት ሥራ 25፥13-27        ምስባክ፤ መዝ. ፪÷፲፪ ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት፤ ወተሐሰዩ ሎቱ በረዓድ፤ አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመአዕ እግዚአብሔር፡፡ (ትርጕም፤ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፤ በረዓድም ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር እንዳይቆጣ ጥበብን አጥኗት፡፡)        ወንጌል፤ ዮሐ. ፫÷፲-፳፭

#ዘወረደ_ወይም_ሕርቃል_ወይም_ሙሴኒ ጾም ማለት፤ ፨ ከእህልና ከውኃ እንዲሁም ከሥጋ ፈቃድ ጾሙ እስኪፈጸም ድረስ መተው ማለት ነው። ፨ ጾም ማለት በጾም ወቅት ሥጋ ነክ ምግቦችንም ሆነ ወተትን፤ ቅቤን የመሳሰሉትን የምግብ እና የመጠጥ ዓይነቶችን ጥሉላትነት በሌላቸው ምግቦች መለወጥ ብቻ ሳይሆን የምንወደውን የሥጋ ፍላጎት ስለ እግዚአብሔር ብለን መተው ማለት ነው። ራስን መግዛት በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ ትልቅ ዋጋ እንዳለው ሁሉ አንድ ሰው የሥጋ ፍላጎቱን ወይም የዓለም ምኞቱን ትቶ እግዚአብሔርን እያሰበ የሚጾም ከሆነ በፈጣሪው ዘንድ ጾሙ ተቀባይነት አለው። ፨ ጾም ለእግዚአብሔር ያለንን ታዛዥነት የምንገልጽበት የፍቅር መገለጫ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ዐቢይ ጾም ስንጾምም፤ ፠ ዐይናችን ትጹም (ክፉ ከማየት)፤ ፠ ጆሮም ትጹም (ክፉ ከመስማት ወይም ሰውን ከማማት እንታቀብ)፤ ፠ አፋችን ትጹም (ከመሳደብ ሆነ ክፉ ከማውራት)፤ ፠ እጅም ትጹም (ከመስረቅም ሆነ ሰውን ከመደብደብ)፤ ፠ አግርም ትጹም (ወደ ኀጢአት ቦታዎች ከመሄድ ምሳሌ ከጭፈራ ወይም ዳንኪራ ቤቶች)፤ ….. ሁላችንም በተሰበረ ልብ ሆነን እንጹም። ዐቢይ ጾም ማለት ታላቅ ጾም ማለት ነው። ታላቅ ጾም የተሰኘበት ምክንያት ለ55 ቀናት መጾሙና ከሌሎች አጽዋማት ጋር ሲነጻጸር በቊጥር መብለጡ ብቻ ሳይሆን ፍጥረታትን የፈጠረ አምላክ፤ ስለ ሰው ልጅ ፍቅር ሲል ከዙፋኑ ወርዶ ከእመቤታችን ተወልዶ፤ መጾም ሳይገባው ለእኛ አርአያ ለመሆን ሲል በገዳመ ቆሮንጦስ የጾመው ጾም ነው። የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ዘወረደ ወይም ጾመ ሕርቃል በተጨማሪም ሙሴኒ በመባል ይታወቃል፤ ለምን እንደተባለ በዝርዝር ስንመከለከታቸው፤ ፩ኛ. #ዘወረደ_ይባላል፤ ‹‹ #ሃሌ_ሃሌ_ሉያ_ዘወረደ_እምላዕሉ_አይሁድ_ሰቀሉ፤ #ወሚመ_ኢያእመሩ፤ #እግዚአ_ኵሉ_ዘየሐዩ_በቃሉ፡፡›› ‹‹ #ዘወረደ_እምላዕሉ_እመልዕልተ_ኵሉ››፡፡ «ዘወረደ» ማለትም በቀጥታ፣ ቃል በቃል ሲተረጐም «የወረደ» ማለት ነው፡፡ ይህም በምሥጢሩ አምላክ፥ ወልደ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም፥ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን፤ በፈቃዱ ሰው ሆኖ ከሰማየ ሰማያት ከባሕርይ ልዕልናው በትሕትና መውረዱን፥ ከድንግል ማርያም መወለዱን፥ የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ ይህ እንዲታወስበት፣ እንዲወሳበት የዐቢይ ጾም የመጀመሪያውን ሳምንትን ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው ላይ ‹‹ዘወረደ›› ብሎ ሰይሞታል፡፡ /ዮሐ.3፥13፣ ጾመ ድጓ፡፡/ ፪ኛ. #ጾመ_ሕርቃል_ይባላል፡፡ የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት ሌላ መጠሪያ ስሙ ‹‹ጾመ ሕርቃል›› ነው፡፡ ሕርቃል ማን ነው? ለምንስ በስሙ ተሰየመ? በ614 ዓ.ም. ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ንግሥቲቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ካህናትን አሸክሞ፥ ሌላውን ንዋያተ ቅድሳት ዘርፎ፥ 60ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ፥ 3ሺ የሚሆኑትን ማርኮ፥ ከተማዋንም አቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲያኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል፤ እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርግ? አላቸው፤ እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን ፩ ሱባኤ ጾመውታል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉ ያለበትን አጥቶ ሲቸገር ኪርዮስ መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቊስጥንጥንያ ተመለሰ፤ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ፤ ይህንን ለማሰብ፥ ለማስታወስ የምንጾመው ሲሆን፤ ዛሬም እኛ በመስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን እያልን፥ ለሕርቃል በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳትን፥ መንፈሳዊ ኃይልን እንዲበዛልን እንጾመዋለን፡፡ በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡ የእኛ ጠላት የጨለማ ገዥ የሆነው ዲያቢሎስ ነውና እሱን ደግሞ በጾም እንደምናሸንፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡ ፫ኛ. #ሙሴኒ የመጀመሪያው ሳምንት ሙሴኒ የተባለበት ምክንያትም፤ በዚሁ ሳምንት መጀመሪያ የሰኞ ዕዝል «ከመዝ ይቤ ሙሴ ፀዓቱ እምትእይንት (ሙሴ ከከተማ መውጣቱ እንደዚህ ነው አለ») ስለሚል እንደዚሁም የዚሁ ዕለት ማለት የሰኞ አቡን «ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት ምድር ሰናይት» እያለ የሙሴን ታሪክ ስለሚጠቃቅስ ሳምንቱ ሙሴኒ ተባለ፡፡ ነቢያትም አርባ አርባ ቀን ጾመው ካለፉ በኋላ የሙሴ ሕግና ትንቢተ ነቢያት ፈጻሚ የሆነው አምላካችን እንደ እነሱ 40 ቀንና 40 ሌሊት መጾሙን የሚያስታውስ ነው፡፡ /ዘፀ.24፥18፤ 1ኛ.ነገ.19፥8፤ ማቴ.4፥1-4/፡፡ ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem