ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

تُعد قناة Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 16 047 مشتركاً، محتلاً المرتبة 5 283 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 238 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 16 047 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 26 أكتوبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 518، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 5، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 25.13‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 10.43‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 4 033 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 674 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 29.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 27 أكتوبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.

16 047
المشتركون
+524 ساعات
+1057 أيام
+51830 أيام
أرشيف المشاركات
#የወልወል_ጦርነት (ኅዳር 26/1927ዓ.ም.) #ከአድዋ (1888ዓ.ም.) #በኋላ_የጣሊያን_ሁለተኛው_ወረራና_ጦርነት /ከባለፈው ከየካቲት 12 የቀጠለ……/ #ክፍል_፭ #ለየካቲት_12_የሰማዕታት_ቀን_መዳረሻ፥ #ለየካቲት_23_የአድዋ_ድል_መነሻ፥ #ለሚያዝያ_27_የድል_ቀን_ማስታወሻ_ #ሁለተኛው_ወረራና_ጦርነት #የወልወል_ጦርነት #ፋታውራሪ_ዓለማየሁና_107 #ኢትዮጵያውያን የጀግንነት ጀብድ የፈጸሙበት #ኑር_ሑሴንና_ደጃዝማች_ዑመር_ሰመትር #ደጃዝማች_ታደሰ_ይማም_ወንድይራድ (በባንዳነተ ተሰልፈው የነበሩትን 3ት ደጃዝማቾች ድባቅ የመቱ) #ከራስ_ሙሉጌታ_ #በተንቤን፣ #በእንደርታ፣ #በሽሬ፣ #በአሸንጌ፤ ብዙ ኢትዮጵያውያን በቦንብ የተሰዉበት #በማይጨው_ጦርነት፤ ጀግኖች ኢትዮጵያውያን እንደ መነኮራኩር እየተገለባበጡ ጣሊያንንና ባንዳን አፈር ከድሜ ያበሉበት፡፡ #በአምባ_አራዶም፣ #በሽሬና_በተንቤን፤ ብዙ ኢትዮጵያውያን በቦንብ የተሰዉበት ፠ #ሁለተኛው_ጦርነት ከ1929ዓ.ም. – 1933ዓ.ም. የተደረገ ነው፡፡ (ለዚህ ጦርነት ደግሞ መሠረቱ ጣሊያን የቀድሞ ሽንፈቷ ቂም በመያዟ ነው)፡፡ የተጀመረውም በኅዳር 26/1927ዓ.ም. #በወልወል_ (የኢትዮጵያ ሶማሌ ክፍለ ሃገር በኦጋዴን ውስጥ በዋርዴር አውራጃ አካባቢ የምትገኝ ወረዳ ስትሆን ንጹሕ የከርሠ ምድር ውኃ የሚገኝባትም ነች፤ አጼ ዘርዓ ያዕቆብ 350 ጥልቅ የውኃ ጕድጓድ አስቆፍረውላታል) ላይ ሲሆን ጣሊያን ባንዲራዋን በመትከሏና በወቅቱ የሰሜን ሱማሊያ ቅኝ ገዥ ከነበረችዉ ብሪታኒያ የድንበር ማካለል ለማድረግ ኢትዮጵያን አላሳልፍ በማለቷ ነው፡፡ በዚሁም ምክንያት የአውራጃው ገዢ #ፋታውራሪ_ዓለማየሁ ከጣሊያኑ ጦር አዛዥ ካፒቴን ችማሩታ ጋር ጦርነት ገጠመዋል፤ በጦርነቱም ጀግናው ፊታውራሪ ዓለማየሁ በፋሽስታዊ ታንክ ነጂ በገዛ ታንኩ ላይ ላይ ተወርውረው በመውጣት ሰይፈውታል፤ ብዙ የጀግንንት ሥራንም አከናውነዋል፤ ቆይቶ ግን ለሃገራቸው በጀግንነት እየተዋጉ ሣለ ከሌሎች 107 ኢትዮጵያውያን ጋር አርፈዋል፡፡ በዚህ ውጊያ ላይ አብዛኞቹ ሙስሊሞች ባንዳ በመሆን ለሃገራችን ጠላት (ለምሳሌ ሡልጣን ኢብራሂም አሰብን ለሮማ ልዑካን ሸጥኩላቸው የሚለውና፣ የአዳል ባላባት የራሄታ ሡልጣን ሐሰን ሙሐመድ ለሮማ ሚስዮናውያን የኢትዮጵያን ወደቦች እንሸጣለን ብሎ የመከረ) የነበሩ ቢሆኑም፤ ለሃገራቸው ሲሉ የተዋጉ የሙስሊም አርበኞችም ነበሩ፤ ዋነኞቹም #ኑር_ሑሴንና_ደጃዝማች(#ኋላ_ፊታውራሪ)# _ዑመር_ሰመትር ይጠቀሳሉ፡፡ ፠ #ደጃዝማች(#ኋላ_ፊታውራሪ)# _ዑመር_ሰመትር፤ ‹‹ከአገሬ አፈር የሚደባልቅ ቤልጅግ እና ጎራዴ ይዤ እንጂ ጫት ተሸክሜ የምመጣ እንዳይመስልህ!›› በማለት #በኤልቡሬን ጦርነት 6ት ባታሊዮን የጣሊያንን ጦር ከጥቅም ዉጪ ያደረገው፤ #በሸላቦ ጦርነት አይቀጡ ቅጣት የቀጣው፤ በሌሎች ታላላቅ ጦርነቶች (#በቆራሄ፣#በሃነሌ) ላይ ጣልያንን ከአፈር የደባለቀ ፥ ባንዳዎችን አፈር ከድሜ ያበላ ጀግና፡፡ #በገርለጉቤ ጦርነት ላይ በጥይት ተመትቶ ቢቆስልም እስከ መጨረሻው ድረስ በጀግንነት ተዋግቶ ሕክምና ተደርጎለት 9 ዓመታት በሰላም ኖሮ የኢትዮጵያን ነፃነትን አይቶ በመጋቢት 10 ቀን 1936 ዓ.ም. ብክብር ያረፈ የጀግኖች ጀግና ነው፡፡ ይህ እንደ ወንጭፍ እየተወነጨፈ ጣሊያንን ዶግ አመድ ያደረገው፤ እንደ ንብ እየነደፋ ባንዳን ትቢያ ያደረገው ጀግና ስመ አጠራሩ እንዳይዘነጋ፤  በመዲናችን አዲስ አበባ ፥ በመሃል መርካቶ በስሙ ትምህርት ቤት ተሠይሞለታል፡፡  ባላምባራስ አብዶ ሀይድ የተባሉ የትግል አጋራቸው በቀብራቸው ላይም ይህንን ቅኔ ተቀኙላቸው፤ ተገዳይ እወልወል እጠረፉ ዳር፤ ተጋዳይ አፍዱግ ላይ እጠረፉ ዳር፤ ተጋዳይ ቆራሄ እጠረፉ ዳር፤ ተጋዳይ ሀነሌ እጠረፉ ላይ፤ የመትረየሱ ሼክ የለበን መምህር፤ ሞት ጠራህ አንተንም ዑመር ስመጥር!!! ፠ በዚሁም ጣሊያን ‹‹ጅራፍ ረሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል›› እንደሚሉት በደጃዝማች ዑመር ስመተር በተደጋጋሚ ድባቅ በመመታቷ፤ ኢትዮጵያ ዜጎቼን ገድላብኛለችና 200 ሺህ ሊሬ ካሳ ትክፈለን ፤ ደጃች ዑመር ሰመትርም ተላልፎ ይሰጠን ብለው ለመንግሥታቱ ማኅበር ከሰሱ፡፡ ይህን ተከትሎ ኢትዮጵያ በድርድር ያልቃል ብላ ስትጠብቅ በጎን ግን ኢጣሊያ ለጦርነት ስትዘጋጅ ቆየች፤ በኅዳር 1927 ዓ.ም. የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚንስቴር ፒየር ላቫል ኢጣሊያ ከጀርመን ሂትለር ጎን እንዳትሰለፍ በማሰብ ኢትዮጵያን ብትወርር እንደማትቃወም አሳወወቀች፤ ጦርነቱን የተቃመወችው ሩሲያ ብቻ ነበረች፡፡ በመስከረም 22/1928 ዓ.ም. ኢጣሊያ የመረብን ወንዝ ተሻግራ ጦሯን በ3ት መስመር አሰልፋ ወደ ኢትዮጵያ ምድር ገባች፡፡ ፠ ያገኘችውንም እያጠፋች እንትጮንና አዲግራትን በመያዝ ዓድዋ ደረሰች፤ ለዚሁም አስተዋጽዖ ያደረጉላት ለግል ጥቅማቸው ያደሩ የኢትዮጵያ ጠላት የሆኑ ባንዳዎች ነበሩ ለአብነትም ዋነኞቹ (ባንዳ ደጃዝማች ኃይለ ሥላሴ ጉግሳ፣ ባንዳ ደጃዝማች ሀብተ ማርያም፣ ባንዳ ደጃዝማች እጅጉ አያሌው) ናቸው፡፡ ባንዳ ደጃዝማች እጅጉ አያሌው የጎንደርን ሕዝብ አሳምኖ ለኢጣሊያ ተገዢ ለማድረግ መንቀሳቀሱን ጀግናው አርበኛ #ደጃዝማች_ታደሰ_ይማም_ወንድይራድ ሲሰማ ያለበት ድረስ ደርሶ ድባቅ መትቶታል፤ ባንዳው እጅጉ በጣና ሐይቅ በታንኳ ተሻግሮ አምልጦ ወሎ ተደበቀ፤ ይህንንም ታላቁ አርበኛ #ደጃዝማች_ታደሰ ወሎ ድረስ ዘምቶና ከበባ አድርጎ ሃገሩን ለሸጠ ምሕረት አይገባውምና እንደ በግ አርደውታል፡፡ ፠ ጣሊያኖች በባንዳዎች በመታገዝ ጭምር በመርዝ ጋዝ ታግዘው በየካቲት 27 #ከራስ_ሙሉጌታ_ ጋር በተደረገው ውጊያ የራስ ሙሉጌታ ጦርን በመደምሰሳቸው በሐበሾች ዘንድ የሞራል ውደቀት አስከትሏል፡፡ ነገር ግን ጀግኖች አርበኞች እምቢ ለሃገሬ በማለት #በተንቤን፣ #በእንደርታ፣ #በሽሬ፣ #በአሸንጌ ላይ ተዋጉ፡፡ በአሸንጌው ጦርነት ጠላት ጣሊያን ከላይ በአውሮፕላን ጠላት ባንዳ ደግሞ ከታች በመሆን 8ሺህ የሚጠጉ አርበኞቻችን ላይ ጉዳት አደረሱ፡፡ በመጋቢት 24 ለ13 ሰዐታት በተካሄደው #የማይጨው_ጦርነት ላይ ኢትዮጵያውያን ድል አድረገው ጦርነቱ ማብቂያ ላይ የመርዝ ጋዝና የቦንብ ውርጅብኝ ከአውሮፕላን ላይ በማዝነብ ጀግኖች አርበኞቻችን አብዛኞች አለቁ፤ ከማይጨው የተረፉና በአሸንጌ ላይ የነበሩትን ጀግኖች አርበኞችን 150 አውሮፕላን ደርሰው ደብደቡት በመትረየስም ፈጁት፡፡ (ጣሊያኖች በዚሁ ወረራቸው በሰሜን 300፣ በደቡብ 150 አውሮፕላን አዝምተዋል፡፡) ፠ #በአምባ_አራዶም 50 ሺህ፣ #በሽሬና_በተንቤን 15 ሺህ ሰው ሙቶ 200 ሺህ ሰው ቆስሏል፡፡ ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

#ከሰይጣን_ጋር_የተደረገ_ቃለ_ምልልስ (#ተዋስኦተ_ጳውሊ_ምስለ_ሰይጣን_)፤ #ክፍል፪_ #ሰይጣን_ምንጊዜም_ቢሆን_እንደየሰው_ምኞትና_ፍላጎት፥ #እንደ_ጊዜውና_እንደ_ሰዐቱ፥ #እንደ_ዘመኑና_እንደ_ወቅቱ_ተጨባጭ_ሁኔታ_የማሳት_ጥበቡን_እየለዋወጠ_ይጠቀማል፡፡ (ሳኦል የአማሌቃውያንን ምርኮ ባገኘበት ወቅት፣ ሐናንያ ገንዘብ በእጁ በገባበት ወቅት ሰይጣን እንደፈተናቸው ልብ ይሏል /ሐናንያ ሆይ መንፈስ ቅዱስን ታታልል ዘንድ ከመሬቱ ሽያጭ ታስቀር ዘንድ ሰይጣን በልብህ ስለምን ሞላ?፡፡›› ሐዋ. ፭፥፫/ እኛንም እንዲሁ እንደ ዘመናችን ሁኔታ መልኩን እየለዋወጠ ይፈትነናል፡፡ እርሱ የ7511 ዓመታት የመፈተን የሥራ ልምድ ያለው ነውና!!፡፡ ##መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም የመጣውና መጽሐፍ ቅዱስም የተጻፈበት ዐቢይ ጉዳይ ሰይጣን በሰው ልጆች ላይ እያደረሰ ካለው ጉዳትና ጥፋት ለመታደግና ችግሩንም በዝርዝር ለማሳወቅና ሰዎችም የሰይጣንን ክፉ ሥራ ዐውቀው እንዲርቁ ለማድረግ ነው፡፡ /‹‹የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ፡፡›› ፩ዮሐ. ፫፥፰/ ‹‹በእኔም የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር እኔ ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፡፡›› ዮሐ. ፲፪፥፵፮ ***ነገር ግን ጌታችን ወደዚህ ዓለም በመምጣቱ፤ ሰው በመሆኑ ይህ የሕይወት ብርሃን ለዓለም ቢበራም፤ ሁሉም #ሰው ነፃ ፈቃዱን ተጠቅሞ ከዲያብሎስ ሽንገላ ለመላቀቅ ፈቃደኛ አለመሆኑን ተመልክቶ /‹‹ወደ ሕይወት የሚወስደው በር የጠበበ መንገዱም የቀጠነ ነውና የሚገቡትም ጥቂቶች ናቸው፡፡›› ብሏል ማቴ. ፯፥፲፬/ ጌታችን እንዲህ ያለው ሰዎች ነፃ ፈቃዳቸውን ተጠቅመው የሰይጣንን ፈቃድ በመፈጸም በፈቃደ ሥጋቸው ስለሚመሩና የእርሱን ትዕዛዝ ለመፈጸም ደስተኛና ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ለመግለጽ እንጂ ወደ ሕይወት የሚወስደው መንገድ የሚጠብ ሁኖ አይደለም፡፡ ይህ የሕይወት መንገድ የሚሰፋው የራስ ፈቃደኝነት ሲታከልበት ነው፡፡ #ለሰው ልጅ ወደ ሕይወት ለመግባት ወሳኙ ነገር ፈቃደኝነት ነው፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ ቢሆንም የሰውን ልጅ ሲፈጥረው ነጻ ፈቃድ ያለው አድርጎ ስለፈጠረው መልካሙን ነገር ሊያደርግ በሚፈልግበት ጊዜ ፈቃደኝነታቸው ይጠይቃል፡፡ /ድውያንን ሲፈውስ ልትድን ትወዳለህን እያለ የሚጠይቃቸውን ልብ ይሏል፡፡ ዮሐ. ፭፥፮/ #የራስ ፈቃደኝነት ካለ ትእዛዛትን መጠበቅ ቀላል ይሆናል፡፡ /የዘለዓለምን ሕይወት እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ ብሎ ለጠየቀው ሀብታም ጎልማሳ ‹‹ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ትእዛዛትን ጠብቅ … ፍጹም ልትሆን ብትወድ ሂደህ ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፤ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፡፡›› ነገር ግን ሀብታሙ ጎልማሳ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ታላቅ ሐዘን ተሰምቶታል፡፡ ማቴ. ፲፱፥፳፩/ #ጽድቅ፣ ቅድስናና ሰይጣንን ማሸነፍ የሚመጣው በራስ ፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ #አንድ_ሰው_በፍጹም_ትሕትና_ትእዛዛትን_ለመጠበቅ_የራስ_ፈቃደኝነት_ካለውና_ንስሐ_ከገባ__በቀላሉ_ሰይጣንን_የሚያሸንፍበት_ኀይል_ከእግዚአብሔር_ያገኛል፡፡ ሰይጣንም የብዙ ዘመን ልምድ ስላለው ይህን ሁኔታ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ሰዎች፤ ++ሰዎች ትእዛዛትን ለመጠበቅ የራስ ፈቃደኝነት እንዳይኖራቸው የተለያየ ምክንያት በመፍጠር አጥብቆ ይዋጋቸዋል፡፡ ++ሰዎች ትእዛዛትን ሊጠብቁና ንስሐ ሊገቡ ሲያስቡ በታላቅ ፍርሃትና ስጋት እንዲያዙ ያደርጋቸዋል፡፡ ++ሰዎችን ሕግና ትእዛዛትን መፈጸም ከባድና ጭንቅ፥ በሩም የጠበበ፥ ፈጽሞም የማያሳልፍ አድርጎ ያሳያቸዋል፡፡ ++ሰዎች ትእዛዛትን የሚጠብቁና በቁርጠኝነት ንስሐ የሚገቡ ከሆነ በዚህ ምድር ላይ መኖር እንደማይችሉና ታላቅ ጉዳት እንደሚደርስባቸው ደጋግሞ በማሳሰብና በማስፈራራት ያሳምናቸዋል፡፡ … ነገር ግን በፍጹም ትሕትናና በራስ ፈቃደኝነት ትእዛዙን በመጠበቅና ንስሐ በመግባት ከዚህ ሰይጣናዊ ውጊያ ነጻ ይወጣሉ፤ ነጻ ሲወጡም በሰይጣን አሳሳቢነትና ማስፈራርት ከባድ መስሎ ይታያቸው የነበረው ትእዛዛት ለእነርሱ የደስታና የሰላም ምንጭ ይሆንላቸዋል፡፡ /ይህንንም በሐዋርያትና በቅዱሳንና ቅዱሳት ሕይወት ታውቋል ማቴ. ፲፩፥፳፰/ ከእውነተኛ (መንፈሳዊ) ሕይወት ርቀው የሚኖሩ ሰዎች በጥቂት የፈተና ሰዐት ስንኳ መታገሥና መረጋጋትን፥ ሰላማዊነትንና አስተዋንትን አጥተውና ተስፋ ቆርጠው ለከፋ ችግር የሚጋለጡት አስቀድሞ የጠጠጋቸው ሰይጣናዊ መንፈስ ስለሚያስጨንቃቸውና ስለሚያስፈራራቸው ነው፡፡ #የሰው ልጅ በምድር ላይ እስካለ ድረስ በጥንተ ጠላቱ ሰይጣን በየጊዜው መፈተኑ አይቀሬ በመሆኑ /ዘፍ. ፫፥፲፭/ ውጊያውም ከደምና ከሥጋ ጋር ሳይሆን ከጨለማ ዓለም ገዦች፣ ከአለቆችና ከሥልጣናት እንዲሁም ከረቂቃን ሰይጣናት ከዲያብሎስ ሠራዊት ጋር በመሆኑ፤ ፈተናውን ለማለፍ የሰይጣን መግቢያ የሆኑ ቀዳዳዎችን ለመድፈን እንዲያስችለው መንፈሳዊ ዝግጅት ማድረግ አለበት፡፡ ከኃጢአት ንጹሕ ሁኖ ሀብተ መንፈስ ቅዱስን ገንዘብ ያደርግ ዘንድ ስለሰይጣን አስከፊነት በእጅጉ መማርና ማወቅ፥ መረዳትና ማስተዋል ይገባዋል፡፡ +‹‹ከሚመጣው ሁሉ መዳን ትችሉ ዘንድና በሰው ልጅ ፊትም ለመቆም እንድትችሉ ሁል ጊዜ በጸሎት ትጉ፡፡›› ሉቃ. ፳፩፥፮ +‹‹ለጸሎት ትተጉ ዘንድ … ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ ደግሞ አብራችሁ ሁኑ፡፡›› ፩ቆሮ. ፯፥፭ +‹‹የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ፡፡›› ኤፌ. ፮፥፲፩ +‹‹በመጠን ኑሩ፥ ንቁም ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፡፡›› ፩ጴጥ. ፭፥፰ +‹‹በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፤ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት፡፡›› ኤፌ. ፬፥፳፯ #አንድ ሰው ካመነና ከተጠመቀ በኋላ ስለሰይጣን ክፋትና ተንኮል ጥልቅ እውቀት ከሌለውና በመንፈሳዊ ትሩፋት የማይተጋ ከሆነ በቀላሉ ተመልሶ በሰይጣን አገዛዝ ሥር ይወድቃል፡፡ ከዚያ በኋላም ሕይወቱ በእጅጉ የከፋ ይሆንበታል፡፡ /‹‹ርኩስ መንፈስ ከሰው ከወጣ በኋላ ዕረፍት ለማድረግ ፈልጎ ውኃ ወደሌለበት ምድረ በዳ ይዞራል፤ አያገኝም፡፡ ከዚህም በኋላ እንግዲህስ ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ ይላል፡፡ በመጣም ጊዜ ባዶ ሁኖ ተጠርጎና ተጊጦ ያገኘዋል፤ ከዚህም በኋላ ይሄዳል፤ ከእርሱም የሚከፉ ሌሎች ሰባት አጋንንትን ያመጣል፤ ገብተውም በዚያ ይኖራሉ፤ ለዚያም ሰው የኋላ ኑሮው ከፊተኛው የከፋ ይሆናል፡፡›› ማቴ. ፲፪፥፵፫ ‹‹በጌታችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ ዳግመኛ በእርሷ ተጠልፈው ከተሸነፉ ከፊተኛው ኑሯቸው ይልቅ የኋለኛው ኑሯቸው የባሰና የከፋ ይሆንባዋቸዋል፡፡›› ፪ጴጥ. ፪፥፳/፡፡ ሰዎች ዳግመኛ በሰይጣን ሽንገላ ተታለው በዓለም ርኵሰት እንዳይወድቁ የሚረዳ እውቀት ማግኛ የሚሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብና ማወቅ እንዲረዳ መምህረ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ ፲፭፥፬ ላይ .. መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ ይሆንልን ዘንድ አስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፏልና ብሎ እንደተናገረው:: #ቀሲስ_ጳውሊ_ወደ_ጭፈራ_ቤት_የሚሄዱትን_ሰዎች_የሚያስተውን_ሰይጣን_በዙ_ጥያቄዎችን_ሊጠይቀው_እንደገዘተው፤ #ሰይጣን_ሰዎችን_እንዴት_እንደሚፈትንና_ኃይል_እንዴት_እንደሚያገኝ_፤ #ክፍል_፫ _.… #ይቀጥላል_ይጠብቁን_/ #በፌስቡክ_ሊያገኙን_ከፈለጉ_፤ የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔዓለምና ደ/ትጉሃን ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት፡፡ #በቴሌግራም_ሊያገኙን_ከፈለጉ_፤ https://t.me/medihanaelem

#የዐቢይ_ጾም_የሱባኤ_መርሐ_ግብር፡፡ ፠ከሰኞ የካቲት 16 - ዐርብ የካቲት 20/2012 ዓ.ም. *ጠዋት ጠዋት ከ12-1 ሰዐት፤ የማኅበር ጸሎት *ማታ ማታ፤ ከ12፡30-2፡00 ሰዐት መሐረነ አብ ጸሎትና ትምህርት፡፡ ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

በዐቢይ ጾም በተከታታይ ክፍል፤ ሰኞና ኀሙስ፡፡ #ከሰይጣን_ጋር_የተደረገ_ቃለ_ምልልስ (ተዋስኦተ ጳውሊ ምስለ ሰይጣን)፤ #ክፍል_፩ ፠ ‹‹እነሆ በትዕግስት የጸኑትን ብፁዓን እንላቸዋለን፤ ኢዮብ እንደታገሠ ሰምታችኋል፥ ጌታም እንደፈጸመለት አይታችኋል፡፡›› ያዕ. ፭፥፲፩ ሰይጣንን በዘመናቸው ታግሰው ያሸነፉ ሰዎች ልቡናቸው አስተሳሰባቸው አጠቃላይ አኗኗራቸው ንጹሕና ቅዱስ ስለሚሆን ፍጹም ይቅር ባይና ቸሮች ርኅሩኆችና አዛኞች ናቸው፤ ሐዘኔታቸውም ለወዳጆቻቸውም ብቻ ሳይሆን ለጠላቶቻቸው ጭምር ነው (ቅዱስ ዳዊት /፩ኛ ሳሙ. ፳፬፥፲፰/ ና ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን /ሐዋ. ፯፥፰/ ልብ ይሏል) ቅዱሳን ከሰው ልጆች አልፈው ለአራዊት፣ ለአዕዋፍና ለእንስሳ እንዲሁም ለታላቁ ጠላት ለሰይጣን ሳይቀር የሚያዝኑ ናቸው፡፡ (ነቢዩ ሳሙኤል /፩ኛ ሳሙ. ፲፮፥፩/፣ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን /ገድለ ክርስቶስ ሰምራ/ ልብ ይሏል::) ፠ ቅዱሳን ሰዎች እንዲህ ዓይነቱን ጸጋ ሊያገኙ የሚችሉት የሰይጣንን ክፋት ለይተው ተረድተው ሰይጣንን በፍጹም ትዕግስትና ትሕትና ማሸነፍ በመቻላቸውና ከሰይጣን ባርነት ነጻ ወጥተው የእግዚአብሔርን መንፈስ ገንዘብ በማድረጋቸው ነው፡፡ ፠፠ በተቃራኒ ደግሞ በዓለም ላይ ለተፈጠሩትና እየተፈጠሩም ላሉት ችግሮች መንስኤያቸውና ምንጫቸው የሰይጣን ሰለባና ማደሪያ በሆኑ ሰዎች አማካይነት የሚከሠት ነው፡፡ (ቃዔልን /ዘፍ.፬፥፰፣ ሄሮድስን /ማቴ. ፪፥፲፮/፣ አምኖንን /፪ኛ ሳሙ. ፲፫፥፩/፣ ሰዶማውያንን /ዘፍ. ፲፱፥፩፣ ሮሜ. ፳፮፥፳፱፣ ፪ጴጥ. ፪፥፮/ …. ሌሎችንም …. ልብ ይሏል፡፡ ምክንያቱም፤ *ሰይጣን ተዘክሮተ እግዚአብሔርንና መንፈሳዊ ተግባራትን ካስተወ በኋላ በኃጢአት ላይ ኃጢአት እንዲጨምሩ እንጂ *ሰይጣን ኃጢአትን በቃኝ እንዳይሉ ስለሚያደርጋቸው ነው /ዘዳ. ፮፥፲፫/፡፡ *ሰይጣን ኃጢአትንም ተዉ ብሎ በሚመክራቸው ሰው ላይ በጠላትነት እንዲነሳሡ ያደርጋቸዋል፡፡ *ሰይጣን ቀና የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ክፉ አስመስሎ ስለሚያሳያቸው ቅን አሳቢዎችንና ለመልካም ሥራ የተሰለፉትን እንዲጠሉ ያደርጋቸዋል፡፡ *ሰይጣን ቅን አስተሳሰብን መንፈሳዊ ሥራን ሰላምን ፍቅርን ርኅራኄን ከውስጣቸው አሟጦ አውጥቶ የራሱን መንፈስ ስለሚሞላባቸው ማንኛውንም ዓይነት ወንጀል ቢሠሩ ወንጀል የሠሩና ጥፋት ያጠፉ አይመስላቸውም፡፡ እውነተኛ ሕይወት እንደሚኖሩ ያስመስላቸዋልም፡፡ *ሰይጣን ዲያብሎስ የጥፋተኝነት ስሜት እንዳይሰማቸው ስለሚያደርጋቸው ለጥፋታቸው ገደብ የለውም፡፡ ፠ ##መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ከሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም የተወለደው ሰው ሁሉ የሰይጣንን የክፋት ሥራ ተረድቶ ከሰይጣን እንዲሸሽና የእግዚአብሔርን ልጅነት አግኝቶ የዘለዓለም ሕይወት መንግሥተ ሰማያትን እንዲወርስ ለማድረግ ነው፡፡ /‹‹ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፡፡ ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ኃጢአትን ያደርጋልና፤ ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ፡፡ ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔር ተወልዷልና ኃጢአትን ሊያደርግ አይችልም፡፡ የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ የተገለጡ ናቸው፡፡›› ፩ዮሐ.፫፥፰/ /‹‹ክፉ ፍሬ የሚያፈራ መልካም ዛፍ የለምና እንዲሁም መልካም ፍሬ የሚያፈራ ክፉ ዛፍ የለም፡፡ ዛፍ ሁሉ ከፍሬው ይታወቃልና፤ …. መልካም ሰው ከመልካም ልቡ መልካሙን ያወጣል፡፡›› ሉቃስ ፮፥፵፫/ #ማንኛውም ሰው በሚሠራው ሥራ የማን ወገንና የማን ማደሪያ እንደሆነ ለመረዳትና ራሱንም ለመፈተሸ ይችላል፡፡ ፠ ##ጠላት ዲያብሎስ ንስሐ ገብተን መንግሥተ ሰማይትን እንዳንወርስ ማድረግ ብቻ ሳይሆን በሥጋዊ ኑሯችንም ቢሆን በተገቢው ሰዐትና ጊዜ ተምረን ተገቢውን እውቀት ይዘን ሥራችንን በተገቢው ሰዐትና ጊዜ እንዳንሠራ በማድረግ፤ ሠርተንም እንዳንጠቀም ዕንቅፋት በመፍጠር (በስንፍናና በውሸት፤ በዝሙትና በስካር፤ በቃሚነትና በአጫሽነት፤ በጨፋሪነትና በዳንሰኛነት፤ በስርቆትና በአጭበርባሪነት፤ …. በተለያዩ የኃጢአት አሸክላዎች ተብትቦ ይይዘናል፤ እንዲህ ካደረገን በኋላም ሰይጣን በሚያመነጭልን አእምሯዊ ስሜትና ጭፍን አስተሳሰብ እየነዳን መልካም ሥራን ለሚሠሩ ለእውነተኛ ሰዎች እንቅፋት እንድንሆን በመሣሪያነት ይጠቀምብናል፡፡ /‹‹ወደ እናንተ ልንመጣ ወደን ነበር … አንድና ሁለት ጊዜ ሰይጣን አዘገየን፡፡›› ፩ተሰ. ፪፥፲፰/ /አንተ (ኤልማስ የተባለ አስማተኛን/ ተንኮልንና ክፋትንም ሁሉ የሞላብህ የዲያብሎስ ልጅ የጽድቅም ሁሉ ጠላት የቀናውን የጌታን መንገድ ከማጣመም አታርፍምን?›› ሐዋ. ፲፫፥፮/ /እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁን ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ፡፡ እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለሌለ በእውነት አልቆመም፡፡ ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፡፡ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና፡፡›› ዮሐ. ፰፥፵፬/ #ከላይ ባየነው ዓይነት ሕይወት ሰይጣን በእጁ ያደረጋቸውን ሰዎች፤ **ለሕይወታቸው ጠቃሚ ምክርና ትምህርት በሚሰጣቸው ሰዐት ወዲያው እንዲዘነጉትና እንዳይቀበሉት ያደርጋል፡፡ /‹‹ወዲያው እንደሰሙ ሰይጣን መጥቶ በልባቸው የተዘራውን ቃል ይወስዳል፡፡›› ማር. ፬፥፲፭/ **ቢመከሩም ምክርን አይሰሙም አይቀበሉምም፤ /ይሁዳ ሕይወት የሚሆን የጌታን ትምህርት አልሰማ ብሎ ነው ጌታን አሳልፎ የሰጠው፡፡ ማቴ. ፳፮፥፵፱/ /አምኖንም የእኅቱን የትዕማርን ምክር አልሰማ ብሎ ነው አስነዋሪ ጥፋት በእኅቱ ላይ የፈጸመው፡፡ ፪ሳሙ. ፲፭፥፲፱/ /እንዲሁም ደግሞ ሳዖልም የነቢዩ ሳሙኤልን ምክር አልሰማ ብሎ ነው ከአማሌቃውያን ለማረከው ምርኮ በመሣሣት ክፉ መንፈስ ሊያድርበትና በጠላት እጅ ሊወድቅ የቻለው፡፡ ፩ሳሙ. ፲፭፥፲፱/ /#ከሰይጣን_ጋር_የተደረገ_ቃለ_ምልልስ (ተዋስኦተ ጳውሊ ምስለ ሰይጣን)፤ #ክፍል_፪_ #ሰይጣን_ምንጊዜም_ቢሆን_እንደየሰው_ምኞትና_ፍላጎት፥ #እንደ_ጊዜውና_እንደ_ሰዐቱ፥ #እንደ_ዘመኑና_እንደ_ወቅቱ_ተጨባጭ_ሁኔታ_የማሳት_ጥበቡን_እየለዋወጠ_ይጠቀማል፡፡ .… ይቀጥላል ከነገ ወዲያ ይጠብቁን/ #በፌስቡክ_ሊያገኙን_ከፈለጉ_፤ የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔዓለምና ደ/ትጉሃን ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት፡፡ #በቴሌግራም_ሊያገኙን_ከፈለጉ_፤ https://t.me/medihanaelem

እናስተዋውቅዎ፤ ቢከታተሏቸው ይጠቅማሉ የምንላቸው ገጾች እናስተዋውቃችሁ፤ #ዐበይትና_ዐይናማ_መምህራንና_ሊቃውንት_ትምህርት_የሚሰጡበት_ገጽ፤ Kofeda Tube ኮፌዳ ቲዩብ #Kofeda_Tube http
እናስተዋውቅዎ፤ ቢከታተሏቸው ይጠቅማሉ የምንላቸው ገጾች እናስተዋውቃችሁ፤ #ዐበይትና_ዐይናማ_መምህራንና_ሊቃውንት_ትምህርት_የሚሰጡበት_ገጽ፤ Kofeda Tube ኮፌዳ ቲዩብ #Kofeda_Tube https://www.youtube.com/channel/UC55ZqqlOX090QK9X_5L-zMg/featured (እነሆ ለሕዝቡ የሚሆን ታላቅ ደስታ …. ሠለስቱ አዕማድ/ሦስቱ ምሰሶዎች/ ቀጭን ጥያቄ? አጭር መልስ …..) … ሌሎችንም ትምህርቶች ያገኛሉ፡፡ ለሌሎችም ያጋሩ፨

ክብር ለአባቶቻችን አምላክ ይሁን፡፡ የማንቂያ ደወል ከአዲስ አበባ ውጭ ለመጀመሪያ ጊዜ በምሥራቅ ሸዋ ናዝሬት (አደማ) ከተማ ምሥራቀ ፀሐይ ማርያም፤ እልፍ አእላፋት (በመቶ ሺህ የሚቈጠሩ) ክርስቲያኖ
+6
ክብር ለአባቶቻችን አምላክ ይሁን፡፡ የማንቂያ ደወል ከአዲስ አበባ ውጭ ለመጀመሪያ ጊዜ በምሥራቅ ሸዋ ናዝሬት (አደማ) ከተማ ምሥራቀ ፀሐይ ማርያም፤ እልፍ አእላፋት (በመቶ ሺህ የሚቈጠሩ) ክርስቲያኖች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡ የማንቂያ ደወሉ ሰኞ በአዲስ አበባ ይቀጥላል፡፡

#ዘወረደ_መዝሙር፣ #ምንባባት፣ #ምስባክ፣ #ወንጌል መዝሙር ዘወረደ፤ተቀነዩ ለእግዚአብሔር ሃሌ ሉያ ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት በፍርሃት ወተኃሠዩ ሎቱ በረዓድ፤ /መዝ.፪፥፲፩/ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ፤ ባኡ ቅድሜሁ በተጋንዮ ወውስተ አዕጻዲሁ በስብሐት እመንዎ፤ /መዝ.፺፫፥፫-፭/ እስመ … ንጹም ጾመ ወናፈቅር ቢጸነ ፥ ወንትፋቀር በበይናቲነ፤ እስመ … አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ እስመ ሰንበትሰ በእንተ ሰብእ ተፈጥረት፤/ማቴ.፲፪፥፰/ እስመ … ምሕረተ ወፍትሐ አሀሊ ለከ እዜምር ወእሌቡ ፍኖተ ንጹሐ፤ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ አባግዓ መርዔቱ፨ ትርጕም፤ እግዚአብሔርን በመፍራት ተገዙለት፤ለእርሱ መገዛትም ደስ ያሰኛችሁ፡፡ እግዚአብሔር ቸር ምሕረቱም ለዘለዓለም፣ እውነቱም ለልጅ ልጅ ነው፡፡ እኛስ ሕዝቡ የመሰማርያው በጎች ነን፡፡ ወደ ደጁ በመገዛት፤ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፤ ጾምን እንጹም፤ ጓደኞቻችንን እናፍቅር፤ እርስ በርሳችንም እንፋቀር፡፡ ሰንበት ስለሰው ተሠርታለችና፤ ሰንበትን እናክብር፡፡ እውነትንም እንሥራ፤ አቤቱ ምሕረትንና ፍርድን እቀኝልሃለሁ፤ እዘምራለሁ፤ ንጹሕ መንገድንም አስተውላለሁ፡፡ #ምንባባት †ዕብ.13÷7-17፤ ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ለእርሱ እናቅርብ፡፡ /ቊ.7/ †ያዕ.4÷7-17፤ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ፡፡ /ቊ.7/ †የሐዋርያት ሥራ 25፥13-27        #ምስባክ፤ መዝ. ፪÷፲፪ ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት፤ ወተሐሰዩ ሎቱ በረዓድ፤ አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመአዕ እግዚአብሔር፡፡ (ትርጕም፤ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፤ በረዓድም ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር እንዳይቆጣ ጥበብን አጥኗት፡፡)        #ወንጌል፤ ዮሐ. ፫÷፲-፳፭ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን፡፡ /ቊ. ፲፩/)        #ቅዳሴ፤ ቅዳሴ ዘእግዚእነ ꕥꕥꕥ ፨፨፨ ꕥꕥꕥ #ዘወረደ_መዝሙር፣ #ምንባባት፣ #ምስባክ፣ #ወንጌል በድምፅ ከፈለጉ በቴሌግራም አድራሻችን ያገኛሉ፡፡ ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

#ዘወረደ_መዝሙር፣ #ምንባባት፣ #ምስባክ፣ #ወንጌል መዝሙር ዘወረደ፤ተቀነዩ ለእግዚአብሔር ሃሌ ሉያ ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት በፍርሃት ወተኃሠዩ ሎቱ በረዓድ፤ /መዝ.፪፥፲፩/ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ፤ ባኡ ቅድሜሁ በተጋንዮ ወውስተ አዕጻዲሁ በስብሐት እመንዎ፤ /መዝ.፺፫፥፫-፭/ እስመ … ንጹም ጾመ ወናፈቅር ቢጸነ ፥ ወንትፋቀር በበይናቲነ፤ እስመ … አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ እስመ ሰንበትሰ በእንተ ሰብእ ተፈጥረት፤/ማቴ.፲፪፥፰/ እስመ … ምሕረተ ወፍትሐ አሀሊ ለከ እዜምር ወእሌቡ ፍኖተ ንጹሐ፤ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ አባግዓ መርዔቱ፨ ትርጕም፤ እግዚአብሔርን በመፍራት ተገዙለት፤ለእርሱ መገዛትም ደስ ያሰኛችሁ፡፡ እግዚአብሔር ቸር ምሕረቱም ለዘለዓለም፣ እውነቱም ለልጅ ልጅ ነው፡፡ እኛስ ሕዝቡ የመሰማርያው በጎች ነን፡፡ ወደ ደጁ በመገዛት፤ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፤ ጾምን እንጹም፤ ጓደኞቻችንን እናፍቅር፤ እርስ በርሳችንም እንፋቀር፡፡ ሰንበት ስለሰው ተሠርታለችና፤ ሰንበትን እናክብር፡፡ እውነትንም እንሥራ፤ አቤቱ ምሕረትንና ፍርድን እቀኝልሃለሁ፤ እዘምራለሁ፤ ንጹሕ መንገድንም አስተውላለሁ፡፡ ምንባባት †ዕብ.13÷7-17፤ ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ለእርሱ እናቅርብ፡፡ /ቊ.7/ †ያዕ.4÷7-17፤ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ፡፡ /ቊ.7/ †የሐዋርያት ሥራ 25፥13-27        ምስባክ፤ መዝ. ፪÷፲፪ ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት፤ ወተሐሰዩ ሎቱ በረዓድ፤ አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመአዕ እግዚአብሔር፡፡ (ትርጕም፤ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፤ በረዓድም ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር እንዳይቆጣ ጥበብን አጥኗት፡፡)        ወንጌል፤ ዮሐ. ፫÷፲-፳፭