cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

በፌስቡክ ያግኙን፤ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool በድኅረ ገጽ ያግኙን፤ http://www.finotehiwotsundayschool.com

Більше
Рекламні дописи
11 192
Підписники
+224 години
+507 днів
+25730 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

#ሰኔ_21 ሰኔ ጎልጐታ ወሕንፀተ ቤተክርስቲያን እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለቅድስተ ቅዱሳን ለድንግል ማርያም ሰኔ ጐልጐታና ሕንፀተ ቤተ ክርስቲያን (ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ለታነጸበት) ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ፡፡ ✤✤ ሰኔ ጎልጐታ ፤ ‹‹ ሰኔ ጎልጐታ ችግር የምትፈታታ፡፡›› ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም በዚህች ቀን (ሰኔ 21) ልጇን ወዳጇን ጐልጐታ በሚባል ቦታ ላይ እንባዋ እንደ ጅረት እስኪፈስ ድረስ ለኃጥአን ምሕረትን ለምናዋለች:: ጌታችንም ‹‹ስምሽን የጠራውን፤ በቃል ኪዳንሽ ያመነውን ሁሉ እምርልሻለሁ፡፡›› ብሎ ቃል ኪዳን ሰጥቷታል፡፡ ሰኔ ጐልጐታን ተመልከት ✤✤ ሕንፀተ ቤተ ክርስቲያን፤ ሰኔ 21 ከእመቤታችን #33ቱ በዓላት አንዱ ሲኾን፤ ሕንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል፡፡ በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን በአምላክ እናት ስም የታነጸችው በዚሁ እለት በሰኔ 20 ቀን ነው፡፡ አናጺውም ደግሞ እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፤ ቦታው በፊልጵስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው፤ ጥንተ ነገሩስ (ታሪኩ) እንደምን ነው ቢሉ፤ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና አምላካችን መደኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ‹‹ሑሩ ወመሐሩ ኵሎ አሕዛበ፤ አሕዛብን ሁሉ ሒዱና አስተምሩ፡፡›› /ማቴ. 28፥19/ ባላቸው ቃል መሠረት ሐዋርያት በወንጌል ያርሷት ዘንድ በዕጣ ተካፍለዋታል:: የሰው ልጅ ድኅነቱ የሚፈጸመው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበል ነውና (ዮሐ. 6፥ 56) አበው ሐዋርያት ቊርባንን በተመረጡ ሰዎች ቤት እያዘጋጁ ቀድሰው ያቆርቡ ነበር:: በመጀመሪያ በጽርሐ ጽዮን፣ቀጥሎም በተለያዩ ሰዎች ቤት እንዲህ ይከናወን ነበር፡፡ ለጸሎት ሥራ ደግሞ አንዳንዴ ምኵራበ አይሁድን ይጠቀሙ ነበር:: እየቆየ ሲሔድ ግን ከአሕዛብ ያመኑ ሰዎች ቊጥር እጅጉን በመብዛቱ /በተለይ ቅዱስ ዻውሎስ ያሳመናቸው ለጸሎት እያሉ ወደ ጣዖት ቤት መግባት አመጡ::/ በዚህ ምክንያት መምህራን ሕዝቡን ‹‹ካመናችሁ በኋላ እንዴት ወደ ጣዖት ቤት ትገባላችሁ?›› ቢሏቸው ‹‹እኛ ምን እናድርግ! የምንጸልይበት ቤት የለን››ሲሉ መለሱላቸው:: ነገሩ ሲያያዝ ከደጋጉ ሐዋርያት ዻውሎስና በርናባስ ደረሰ:: ወዲያውኑ አንዳንድ ወንድሞች ቤት ‹‹ለምን አናንጽም?›› ብለው ነበር:: ቅዱስ ዻውሎስ ግን ‹‹ሊቀ ሐዋርያቱ ሳይፈቅድ አይሆንም›› አለ:: (ለዚህ ነው ዛሬም ሊቀ ዻዻስ ካልፈቀደ ቤተክርስቲያን የማይታነጸው፡፡) ከዚያ ቅዱሳን ዻውሎስና በርናባስ ሐዋርያቱ ወዳሉበት ሔደው ነገሩን ለቅዱስ ዼጥሮስ አስረዱ:: ሊቀ ሐዋርያቱ ቅዱስ #ዼጥሮስም ‹‹የጌታችን ፈቃዱመኾኑን እናውቅ ዘንድ ተያይዘን ሱባዔ እንግባ›› ብሎ አዋጅ ነገረ:: በዓለም ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድ ልብ ሱባዔ ገቡ:: በሱባዔያቸው መጨረሻም ክብር ይግባውና ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መላአክትን አስከትሎ በግርማ ወደ እነርሱ ወረደ፤እመቤታችን በቀኙ ነበረች፡፡ ኹሉንም ሐዋርያት በሩቅም በቅርብም ያሉትን ደቀ መዛሙርቱን በደመና ጠቅሶ ፊልጵስዩስ በሚባል ሃገር ሰበሰባቸው፡፡ ከዚያም በስተምሥራቅ ከከተማ ወጣ ወዳለ ሥፍራ ወሰዳቸው፡፡ በዚያም ተራርቀው የነበሩ 3 ደንጊያዎች ነበሩ፡፡ 3ቱንም ድንጋዮችን በተአምራት አቀራርቦ አንሥቶ ጎተታቸው፡፡ ድንጋዮቹም እንደሰም ተለጠጡ፣ እንደ ግድግዳም ሆኑ፡፡ ቁመቱን ወርዱን መጥኖ ለሐዋርያቱ ሰጣቸው፡፡ እነርሱም እሳት እንዳየው ሰም በእጃቸው እየለመለሙ (እየሳቡ) ቁመቱን 24፥ ወርዱን 12 ክንድ አድርገው ዕጽብት፥ ግርምት የምትኾን 3 ክፍል ያላትን የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን በ52 ዓ/ም ሰኔ 20 ቀን አነጹ፡፡ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ፤ ጌታችንም በሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም አምሳያ አድርጎ አነጻት፤ ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ለሐዋርያቱ ‹‹እንግዲህ እናንተም እንዲህ አድርጋችሁ ሥሩ፡፡›› ብሏቸው ዐረገ፡፡ ✜ በማግስቱ ሰኔ 21 ዕለት ደግሞ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላእክትን፣ ሰማያውያን ቅዱሳንን እና እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን ይዞ ወረደ:: ሐዋርያቱ አብዛኞቹ እዛው ሲጸልዩ አድረው ነበርና ጌታችን ከቅዳሴው በፊት 2 ነገሮችን አሳየ፤ አስቀድሞ ቤተክርስቲያኗን በድንግል እናቱ ስም አክብሮ ሥርዐተ ቤተክርስቲያንን አሳየ:: ቀጥሎ ደግሞ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስን ከመካከል አቁሞ ‹‹አርሳይሮስ›› ሲል ሾመው:: ይኼውም የዓለም ሁሉ ሊቀ ዻዻሳት (ፓትርያርክ) ማለት ነው:: በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ‹ ‹‹አክስዮስ››(አክዮስ)እያሉ 3 ጊዜ አሰምተው ጮሁ:: አክዮስ ማለት በግዕዙ ‹‹ይደልዎ›› በአማርኛው ደግሞ ‹‹ይገባዋል፤ ያስምርለት›› እንደ ማለት ነው:: ጌታችን ይህን ከከወነ በኋላ ይቀድስ ዘንድ ጀመረ:: አማናዊት ማኅደሩን ድንግል ማርያምን መንበር አድርጎ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ ተራዳኢ ካህን ቆሞ፣ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሠራኢ ዲያቆን ኾኖ፣ ሐዋርያት ድንግልን ከበው፣ መላእክተ ብርሃን በክብራቸው ቆመው ጌታችን ቀድሶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወዳጆቹ አቀበለ:: በዚያች ዕለት በፍጡር አንደበት ተከናውኖ ሊነገር የማይችል ደስታ ተደረገ:: ከቅዳሴ በኋላ ጌታችን ሐዋርያትን አዘዛቸው:: ‹‹ከዚህ ቀን ጀምሮ በመላው ዓለም በእናቴ በማርያም ስም አብያተ ክርስቲያናትን አንጹ፤ ይህችን እለት የሚያከብራትን አከብረዋለሁ::›› ብሏቸው ከድንግል እናቱና ከመላእክቱ ጋር ዐረገ:: ✤✤ ሥርዐተ ማኅሌቱ እንደየደብራችሁ ይትበሃል ትጠቀሙበበት ዘንድ አስቀምጠንላችኋል፤ ✼ የድንግል እመቤታችን ልመናዋ ክብሯ፣ ጣዕመ ፍቅሯና በረከቷ በሁላችን ላይ ይደርብን:: አሜን! /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ :: ꔰ #share Contact: https://t.me/finotehiwot1927 .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .Telegram... https://t.me/finotehiwott http://tiktok.com/@finotehiwot .YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w www.finotehiwotsundayschool.com ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት . Telegram (https://t.me/finotehiwot1927)
Показати все...
ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .

የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት

👍 12 3
የጉዞ ቀን ወደ ሰኔ 30 መዘዋወሩን በትኅትና እንገልጻልን፡፡
Показати все...
👍 3
የሰንበት ት/ቤታችን የቅድስት ኪዳነ ምህረት የዝክር ማህበር 28ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አካባበር ምን ይመስል ነበር በፎቶ
Показати все...
#ጾመ_ሐዋርያት  ‹‹ይኽ ጾም በአላዋቂዎችን እና በቤተክርስቲያን ጠላቶች የሽማሌዎች ጾም እየተባለ ምዕመናን እንዳይጾሙት ብዙ ተለፍቷል..›› በየዓመቱ በዕለተ ሰኑይ የሚዠምሩ ሶስት አጽዋማት ብቻ አሉ ፡፡ ከእነርሱ መሀከል አንዱ ጾመ ሐዋርያት ነው ፡፡ ቅበላው በዕለተ እሑድ ይሆንና ጾሙ ሰኞ ይውላል ፡፡ የ2016 ዓ.ም ጾመ ሐዋርያት ሰኔ 17 ይገባል ፡፡ ይህ ጾም እራሱ ጌታቸን ኢየሱስ ክርቶስ ትንቢት የተናገረለት ጾም ነው፡፡ ይኽ ታላቅ ጾም የዛሬ 1902 ዓመት በፊት በራሳቸው  በቅዱሳን ሐዋርያት የተጀመረ ጾም ነው ፡፡ ከሰባቱ አጽዋማት መሀከልም አንዱ ነው ፡፡ ፈሪሳውያ ጌታችንን ደቀ መዛሙርትህ አይጾሙም ብለው በጠየቁት ጊዜ እርሱም ‹‹ ሚዜዎች ሙሽራ ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን ? ነገር ግን መሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል ፤ በዚያ ጊዜም ይጾማሉ ፡፡ በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ   የሚያኖር የለም ፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና ፤ መቀደዱም የባሰ ይሆናል ፡፡ በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም ፤ ቢደረግ ግን አቁማዳው ይፈነዳል የወይን ጠጁም ይፈሳል ፡፡አቁማዳው ይጠፋል ፡፡ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል ሁለቱም ይጠባበቃሉ ፡፡›› ማቴ 9 ፥ 14-17  አላቸው ፡፡ይኽ ቃለ እራሱ  ጌታችን መድኀኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ስለ ጾመ ሐዋርያት የተናገረው ትንቢት ነው ፡፡ ‹‹#መሽራው_ከተወሰደ በኃላ››  ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ካረገ በኃላ ማለት ሲኾን ይኽን ጾም ከዕረገት በኋላ የምንዠምረው ፤ ይኽን ምሳሌ በማድረግ ነው ፡፡ ዐሥር ቀን ዘግይቶ መዠመሩም የሐዋርያት ሰውነት ለጾሙ መዘጋጀት ነበረበትና  ነው ፡፡ የዚኽን ማብራርያ በቀጣይ ጽሑፋችን እንመለስበታልን፡፡ ይኽ ጾም በአላዋቂዎችን እና በቤተክርስቲያን ጠላቶች የሽማሌዎች ጾም እየተባለ ምዕመናን እንዳይጾሙት ብዙ ተለፍቷል ልናውቅ የሚገባው ነገር ግን ሐዋርያት ዓለምን ዞረው ከማስተማራቸው በፊት ይህን ጾም  ጾመዋል ፡፡ በዚህም ጌታችን የተናረው ተንቢት ተፈጽሟል፡፡  ከሰባቱ አጽዋማትን አንዱ ነው ፡፡ በዚህ  ምክንያት ይህን ጾም ታላቅ እና ልዩ ያስብለዋል ፡፡ ይኽንን አውቀን ሁላችንም በሕግ በሥርዓት ልንጾመው ይገባል ፡፡   #share Contact: https://t.me/finotehiwot1927 .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .Telegram...  https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot  .YouTube    https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w                    www.finotehiwotsundayschool.com ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .
Показати все...
ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .

የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት

👍 22 12
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.