cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ድብቁ ህሊና ለስኬት ፕሮግራም ማድረግ!!!

የዚህ ቻናል አላማ ሰዎች በመልካም አስተሳሰባቸው የሚፈልጉትን ህልም እንዴት ማሳካት እንደሚችሉ ፣ የአሸናፊነት ልማድ እንዴት እንደሚገነባ እንዲሁም የአእምሯችንን ሚስጥራዊ አሰራር የምናውቅበት እና የስኬታማ ሰዎች ተሞክሮም እናቀርባለን። ዘለቄታዊ የሆነ ለውጥ ለማምጣት ደግሞ በነፃ የማማከር አገልግሎትም እንሰጣለን (0912098256 )። ስልጠናዎችን በኦዲዮ ፣ በቪድዮ እንዲሁም በፁሁፍም ይቀርባሉ።

Більше
Рекламні дописи
3 627
Підписники
+324 години
+357 днів
+25330 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

03:30
Відео недоступнеДивитись в Telegram
87.76 MB
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ከምክንያት ወደ ውጤት! ስላላችሁበት ሁኔታ ምክንያት እየሰጣችሁ ባላችሁበት ከመርገጥ ይልቅ ለውጤት ወደመስራት አለፋችሁ እንድትሄዱ . . . 1. በዚህ አመት የሚሰራ ስራ ካጣችሁ በአንድ ዘርፍ ላይ ያተኮረን ክህሎት ያለማዳበራችሁን ጉዳይ አስቡብ፡፡ በተቃራኒው፣ መስራት የምታስቡት ነገር በዝቶባችሁ ከየትኛው እንደምትጀምሩ ግራ ከገባችሁ የትኩረት ችግር አለባችሁና እሱ ላይ ስሩ፡፡ 2. በዚህ አመት ጊዜያችሁን የምታሳልፉበት ነገር ካጣችሁ ራእይና ዓላማ እንደሌላችሁ ጠቋሚ ነውና እሱ ላይ ስሩ፡፡ በተቃራኒው፣ የማሕበራዊው ግንኙነትና የስራው ብዛት ጊዜ ካሳጣችሁ ነገሮችን ቅደም-ተከተል የማስያዝ ብቃተችሁን አስቡበት፡፡ 3. በዚህ አመት ጓደኛ ካጣችሁና ብቸኝነት ከተሰማችሁ የባህሪያችሁን ጉዳይ በሚገባ አስቡበት፡፡ በተቃራኒው፣ ጓደኛ በዝቶ ለራሳችሁ ጊዜ እስከማጣት ድረስ ከደረሳችሁ እንደዚህ የሚያጦዛችሁ የብቸኝነት ስሜት እንዳይሆን ሁኔታውን ለማጤን ሞክሩ፡፡ 4. በዚህ አመት ገንዘብ ካጣችሁ የሰዎችን ችግር የመፍታት ብቃታችሁን አስቡበት፤ ገንዘብ የምናገኘው ለፈታነው የሰዎች ችግር ስለሆነ ማለት ነው፡፡ በተቃራኒው ገንዘብ በዝቶ በምን ላይ እንደምታውሉት አጠቃቀሙን ግራ ከገባችሁ የፈጠራ ብቃታችሁ ላይ ስሩ፡፡ ዝም ብላችሁ የመጣውን እየተቀበላችሁ፣ የሚሄደውን ደግሞ እየሸኛችሁ አትኑሩ! አስቡ! ጠይቁ! መልስ እስከምታገኙ አትረፉ! ሞክሩ! ተንቀሳቀሱ!
Показати все...
ስሙ Sylvester Stallone ይባላል። አንጋፋ እና በጣም ታዋቂ ከሆኑት የአሜሪካ የፊልም ኮከቦች አንዱ ነው፡፡ በአንድ ወቅት እጅግ በጣም ችግር ውስጥ ከመሆኑ የተነሳ ቤት አልባ የነበረ ሲሆን በኒውዮርክ አውቶቡስ ጣቢያ ለ 3 ቀናት ተኝቷል፡፡ ኪራይ ለመክፈል ወይም ምግብ ለመግዛት አቅም ስላልነበረው እጅግ የሚወደው ውሻውን በ50 ዶላር ብቻ ሸጠው፡፡ በአጋጠመው ችግር ምክንያት ውሻውን ከሸጠ ከሁለት ሳምንት በኋላ ግን የህይወቱን አቅጣጫ የቀየረ አንድ ክስተት ተከሰተ። በMohammed Ali እና Chuck Wepner መካከል የቦክስ ውድድርን ይመለከታል። ይህ ግጥሚያም ROCKY በመባል የሚታወቀውን ታዋቂ የፊልም ስክሪፕቱን ለመጻፍ መነሳሳትን ሰጠው፡፡ የፊልም እስክሪፕቱንም የጻፈው በ20 ሰዓታት ውስጥ ነበር! ይህን ስክሪፕትም በ 35,000 ዶላር ሲሸጠው በእሱ ጥያቄ መሠረትም በፊልሙ ውስጥ እሱ ራሱ Rockyን ሆኖ ዋና ተዋናይ ለመሆን ቻለ፡፡ ይህ ፊልምም በታዋቂው የኦስካር ሽልማት ውድድር ምርጥ የምስል ፣ ምርጥ የዳይሬክቲንግ እና ምርጥ የፊልም ኤዲቲንግ አሸነፈ፡፡ በምርጥ ተዋንያንነትም ታጭቷል! ፊልሙ Rocky በአሜሪካ ብሔራዊ ፊልም መዝገብ ውስጥ ከመቼውም ጊዜ ታላላቅ ፊልሞች መካከል አንዱ ሆኖ ተመዝግቧል! በመጨረሻም፤ ከእስክሪፕት ሽያጭ ባገኘው የ35,000 ዶላር የገዛውን የመጀመሪያውን ነገር ታውቃለህ? የሸጠውን ውሻ ነበር መልሶ የገዛው። አዎ Stallone በመቸገሩ ምክንያት ብቻ የሸጠውን ውሻውን በጣም ስለሚወደው የሸጠለትን ሰው እየጠበቀ ለ 3 ቀናት በሸጠበት ቦታ ላይ ቆሞ ነበር፡፡ በመጨረሻም ሰውዬውን ከውሻው ጋር አገኘው። በ 50 ዶላር ብቻ የሸጠውን ያው ውሻ 3,000 ዶላር በመክፈል ማስመለስ ቻለ! ሌላው ታሪክ ነው! ወዳጄ ያለ ትግል ምንም ነገር አታገኝም! በህይወትህ ውስጥ የተለያዩ ችግሮች ሊከሰቱ ይችላሉ ነገር ግን ችግሮችህን መቀረፍ እንደማይችሉ ድክመትህ ከወሰድካቸው በጭራሽ ሊሳካልህ አይችልም። እናም ችግሮችህን ጥንካሬህን የምታወጣባቸው እድሎች ካደረካቸው በህይወት ውስጥ ምንም ልታገኘው የማትችለው ነገር የለም። የላቀ እይታ
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሐምሌ የልምላሜ ወር 🌿☘🍀🌿☘🍀🌴🌴🌴🌴 የቦነስ ልምላሜ    BOOOOOOOM 🌳🌴🌳🌴🌳🌴🌳🌴🌳🌴 የራንክ ልምላሜ    BOOOOOOOM 🌿☘🍀🌳🌴🌿☘🍀🌳🌴 የሽያጭ ልምላሜ  BOOOOOOOM 🌿☘🍀🌳🌴🌿☘🍀🪴💐 የመትረፍረፍ ልምላሜ  BOOOOOOM 💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐 ለኔ ሁለተኛ፣መኪና ፡ IBB : 5000,000 ETB ልምላሜ ነው!!!!  ላንተስ ???? ላንቺስ ???? ፃፉልን 🌝🌝🌝🌝🌝🌝🌝🌝🌝🌝 🙈🙈🙈🙈🙈🙈🙈🙈🙈🙈 👑👑👑👑👑👑👑👑👑👑
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሐምሌ የልምላሜ ወር 🌿☘🍀🌿☘🍀🌴🌴🌴🌴 የቦነስ ልምላሜ BOOOOOOOM 🌳🌴🌳🌴🌳🌴🌳🌴🌳🌴 የራንክ ልምላሜ BOOOOOOOM 🌿☘🍀🌳🌴🌿☘🍀🌳🌴 የሽያጭ ልምላሜ BOOOOOOOM 🌿☘🍀🌳🌴🌿☘🍀🪴💐 የመትረፍረፍ ልምላሜ BOOOOOOM 💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐 ለኔ መኪና ፡ IBB : 5000,000 ETB ልምላሜ ነው!!!! ላንተስ ???? ላንቺስ ???? ፃፉልን 🌝🌝🌝🌝🌝🌝🌝🌝🌝🌝 🙈🙈🙈🙈🙈🙈🙈🙈🙈🙈 👑👑👑👑👑👑👑👑👑👑
Показати все...
00:13
Відео недоступнеДивитись в Telegram
Показати все...
3.94 MB
ወሬ...😏 ችግር የሚቀረፈው በስራ ነው! በወሬ የሚቀረፍ ችግር የለም። ችግራችሁን እየዞራችሁ ለሰው ማውራቱ ጥቅም የለውም ሁሉም ሰው ችግር አለው በህይወቱ ፈተና የሌለበት ችግር ያላጋጠመው ሰው በዚህ ምድር የለም። ማውራታችሁን ትታችሁ Action❗️ ድርጊት ውሰዱ። ስለ ችግራችሁ ከምትወዱስ ሰው ጋር በየቀኑ እየተገናኛችሁ 1 ወር ብታወሩ በ30ኛው ቀን ምን እንደሚፈጠር ታውቃላችሁ? ምንም!🤷 ድርጊት ለመውሰድ የሚፈራና ቆራጥ ያልሆነ ሰው ችግሩን ከመቅረፍ ይልቅ ችግሩን ለሁሉም በማውራት ለትንሽ ጊዜ ቀለል እንዲለው ይመኛል። Stop! እስካሁን ያወራችሁት ይበቃል ከዚህ በኋላ ስለችግራችሁ ለሰው አታውሩ። አሁን ጀምራችሁ መፍትሄው ላይ አተኩሩ ድርጊት ውሰዱ! ቻይኖች ምን ይላሉ..
Talk 🗣️ doesn't cook Rice🍚
"ወሬ ሩዝ አያበስልም!" እንደማለት ነው። ማውራት አቁም! ማድረግ ጀምር! ............
Показати все...
ዘመኑ መረጃ ሞልቶ የተትረፈረፈበት፤ ዕውቀት እንደጎርፍ የሚጎርፍበት ጊዜ ነው ብንል አልተሳሳትንም፡፡ ጊዜው ራሱ የእውቀት ዘመን (Knowledge Era) አይደለ የሚባለው፡፡ የሆነው ሆኖ መረጃው በየቦታው ቢንፎለፎልም፤ ዕውቀት በየጥጋጥጉ ቢበቅልም የሰው ልጅ የሚፈልገውን የእርካታና የሰላም፤ የደስታና የፍቅር ሕይወት መምራት አልቻለም፡፡ መንፈሳዊ እሴቶቻችን ማለትም የአዕምሮ ሰላም፣ የልብ ፍቅር፣ የነፍስ ደስታ፣ እውነተኛ እርካታ ቋሚ ያልሆኑት መሆን ስለማይችሉ ሳይሆን የዘመኑ ሰው ከቁሳቁስ መረጃውና ከዓለማዊው እውቀቱ ባሻገር ሰዋዊ የሆነውን መንፈሳዊውን ጥበብ መጨበጥ ስላልቻለ ነው፡፡ ብዙ ሰው በዘመን አመጣሹ መረጃ ተወስዷል፡፡ ጎርፉ ቀላል አይደለም፤ ብዙዎቻችን የመረጃው ጎርፍ፣ የዕውቀቱ ደራሽ አደጋ እንዳያስከትልና ጥቅም ላይ እንዲውል ቦይ ሰርቶ፣ መስኖ አበጅቶ ከመጠቀም ይልቅ ሁላችንንም ጠራርጎ እንዲወስደን ተመቻችተንለታል፡፡ ቦታ አልያዝንም፡፡ የመጣው ወጀብ እያስተናገደን ነው፡፡ መደገፊያም ሆነ ጎርፉን ማቆሚያ ታኮ ሃሳብ አላዘጋጀንም፡፡ ፍሬን መያዝ የለም፤ ነዳጅ መርገጥ ብቻ!! ረጋ ብሎ ማሰብ ጠፍቷል፡፡ ለምን፣ እንዴት ብሎ መጠየቅ አልተለመደም፡፡ ዞር ብሎ ማሰብ የፋራ ሆኗል፡፡ ከመገንዘብ ይልቅ ገንዘብን ማስቀደም ባህላችን አድርገነዋል፡፡ መረጃውን ዕውቀት የሚያደርግ፤ ዕውቀቱን ወደጥበብ የሚለውጥ ብልህ ትውልድ ተመናምኗል፡፡ በስሜት የሚነጉድ፣ በደመነፍስ የሚወነጨፍ፣ በስማ-በለው የሚነጉድ፣ በመንጋ የሚያስብ ትውልድ ቦታውን እየተረከበ ነው፡፡ ሰውን መከተል እንጂ እውነትን መከተል ኋላቀር እየሆነ ነው፡፡ ጓዶች ጉድ ሆነናል! መረጃ ስለአንድ ጉዳይ ወይም ስለሆነ ነገር ያለን ተያያዥና ትርጉም የሚሰጥ የጥሬ ሃቆች ስብስብ ነው፡፡ ዕውቀት ያንን መረጃ ለመጠቀም ወይም በተግባር ወደመሬት ለማውረድ የሚያስችል የአዕምሮ ብቃት ነው፡፡ ጥበብ ደግሞ ዕውቀቱን አስፍቶ ለአንድ ወገን ብቻ ሳይሆን ለሰው ልጅ በሙሉ እንዲውል ለበጎ ነገር ብቻ የመጠቀም የቀናነት፣ የመልካምነትና የመንፈሳዊነት አቅም ነው፡፡ ጥበብ የሌለው ዕውቀት ዓለምን ይጎዳል እንጂ አይጠቅምም፡፡ ዕውቀትን ሰዋዊ ስሜት እንዲሰጥ፣ ለብዙሃኑ መጥቀም እንዲችል የሚያደርገው ጥበብ ነው፡፡ እንግሊዛዊው ሙዚቀኛ ማይልስ ኪንግተን ስለእውቀትና ስለጥበብ ልዩነት ሲናገር፡- ‹‹ዕውቀት ማለት ቲማቲም ፍራፍሬ ስለመሆኑ ማወቅ ነው፡፡ ጥበብ ማለት ደግሞ ቲማቲሙን ከሰላጣ ጋር አብሮ አለማስቀመጥ ነው፡፡ (“Knowledge is knowing that a tomato is a fruit. Wisdom is not putting it in a fruit salad”)›› ይላል አዎ! ዕውቀትህን ምን ላይ እንደምታውለውና መቼ እንደምትተገብረው ካላወቅክ ጥበብ የለህም ማለት ነው፡፡ ዛሬ ብዙ ሰዎች እውቀት አላቸው፡፡ ነገር ግን ዕውቀታቸው ውስጥ ቀናነት የለም፡፡ የብዙዎቹ ዘመነኞች ዕውቀት ውስጡ ሌሎችን የሚጎዳ የስግብግብ ፖለቲካ መርዝ ሞልቶታል፡፡ ይሄ ዕውቀት ጥበብ ስለሌለው ዓላማው ክፋት ነው፡፡ ለሆዳቸው ያደሩ ከርሳም አዋቂዎች ለነሱ ጥቅም ብቻ የሚውል ግማሽ እውቀት ይሰራሉ፡፡ በክፋት ዕውቀት የተሞሉ ሊቅ ተብዬዎች ሳይንሱን ያሳንሱታል፡፡ ፍልስፍናውን ይልፈሰፈሱበታል፤ ህጉን ፍርደገምድል ያደርጉታል፡፡ ሃይማኖቱን ያምታቱበታል፡፡ እውነተኛ ጥበብ ከውጫዊው ሕይወት የበለጠ ውስጣዊውን ሕይወት ውብ ያደርጋል፡፡ ብዙዎቻችን ለውጫዊው ሕይወታችን ስለምንሮጥ ውስጣችንን ማስዋብ አልቻልንም፡፡ ሰው መንፈሱን ሳይገዛ ቁሳቁስ ሊገዛ የሚችል ገንዘብ ቢያከማች የዓይን አምሮቱን እንጂ ነፍሱን አያስደስትም፡፡ የዓይን አምሮት ውጫዊ ነው፤ የነፍስ አምሮት ግን ውስጣዊ ነው፡፡ በጥበብ እንድትበለፅግ፣ ሕይወትህ እንዲያምር፤ አዕምሮህ የሰላም ባለቤት እንዲሆን ለውስጣዊው ሐብትም ሩጥ! የእንጀራ ዕውቀት ብቻ የትም አያደርስህም!! ጥበበኛ መሆን ማለት መንፈሱን ያበረታ፣ ስሜቱን የገዛ፣ ደመነፍሱን የተቆጣጠረ ቀና አዋቂ ሰው መሆን ማለት ነውና! ወዳጄ ሆይ... ሩሚ ‹‹ትናንት ጎበዝ ስለነበርኩ ዓለምን ለመለወጥ እፈልግ ነበር፡፡ ዛሬ ግን ብልህ ስለሆንኩ ራሴን እየለወጥኩ ነው፡፡›› የሚለው ወዶ አይምሰልህ፡፡ ሩሚ ይሄን ያለው ዓለምን ለመለወጥ ራስን መለወጥ ቀዳሚ ስራ መሆኑን ሲያሰምርበት ነው፡፡ ውስጣዊ ለውጥህ ውጫዊው ሕይወትህንም ይለውጣል እያለህ ነው፡፡ ለውጥህ ደግሞ ሊሳካ የሚችለው ባለህ ዕውቀት ሳይሆን በጥበብህ ነው፡፡ ዕውቀትህን በጥበብ ከያዝከው ከራስህ አልፈህ ዓለሙን ትለውጣለህ፡፡ ጥበብ በዕውቀት፣ በልምምድ፣ በማሰብ ሃይል እውን የሚሆን ስለሆነ በሰፊው መንፈሳዊ ጥበብ ለመስፋት ተጋደል እንጂ በዓለማዊው ዕውቀት ብቻ ጠብበህ በአጭር አትቅር! ብልጥ ሳይሆን ብልህ ሁን! አርባአራት ነጥብ! ቸር ጥበብ! ደግ ዕውቀት! ይህን ፅሁፍ አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ Share.. መልካም ቀን ይሁንላቹ
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.