የጌታ ባሪያ የሲሳይ አበበ ገጽ
Відкрити в Telegram
ይህ የቴሌግራም ቻናል ልዩ ልዩ መልእክቶችን እና ትምህርቶችን ማስተላለፊያ ገፅ ነው፡፡
Показати більше489
Підписники
-124 години
-17 днів
-330 днів
Архів дописів
“...የላካችሁትንም ስጦታ ከአፍሮዲጡ እጅ ተቀብዬ ተሞልቻለሁ፤ ይህም መዐዛው የጣፈጠ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለውና ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ነው።”
(ፊል 4፥18 አመት)
ሰዎች ሊያቀርቡት የሚችሉት ትልቁ መሥዋዕት ሰውነታቸውን ነው፤ “እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ሰውነታችሁን ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕያው መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም እንደ ባለ አእምሮ የምታቀርቡት አምልኳችሁ ነው” (ሮሜ 12፥1)። የጳውሎስ ጥያቄ የተማጽኖ ነው፤ የአምላክን ርኀራኄ የተንተራሠ ተማጽኖ። መሥዋዕቱም (ሰውነት) ተቀባዩን ደስ የሚያሰኝ፣ ቅዱስና ሕያው እንዲሆን ተጠይቋል። ተቀባዩ የሚቀድስ ስለሆነ፣ በሙሉ ፈቃድ የሚቀርብለትን ንፁህ፣ ሕያው የሆነውን ደግሞ ብርቱ ያደርገዋል።
ከሁሉ የሚበልጥ ማነው?
ማቴ18:1-14
አምላክ ሆኖ ሳለ ስለ አባቱ ፈቃድና ለሰው ልጆች ካለው ታላቅ ፍቅር የተነሳ ራሱን ማዋረዱን፣ የሰውን ሥጋ ለብሶ በመካከላቸው መገኘቱን፣ ማንም ከምንም በማይቆጥራቸው ታናናሾች፣ ድሆች፣ ቀራጮች፣ ኃጢተኞች መካከል እንደ ጌታ ሳይሆን እንደ አገልጋይ ሆኖ እያገለገለ መሆኑን ከምንም ግንዛቤ ያልቆጠሩ ደቀ መዛሙርት ጌታን በመንግሥተ ሰማይ ከሁሉ የሚበልጥ ማነው? የሚል ጥያቄ ይጠይቁታል፡፡ ነገር ግን አንዱ ከሌላው በልጦ የመገኘት አባዜ ምድርን የጥልና የጦርነት አውድማ አድርጎአት መገኘቱን አላስተዋሉም፡፡ ያዕቆብ ሲናገር “በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን?” ያዕ4፡1 እንዳለ የምድርን ጣጣ ወደ መንግሥተ ሰማይም ይዘው ለመግባት አሰቡ፡፡ ነገር ግን የሁሉንም አፍ ዝም የሚያሰኝ የመንግሥቱን የትልቅነት ሚስጥር በምሳሌ አስረዳቸው፡፡ በዚህ ክፍልም ትልቅነት ራስን በማዋረድና ለሌላው በመኖር ውስጥ እንደሚገኝ ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ ያአስተማራቸውን እውነት እንመለከታለን፡-
1. ራሱን እንደ ህጻን የሚቆጥር
“እንዲህም አለ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም። እንግዲህ እንደዚህ ሕፃን ራሱን የሚያዋርድ ሁሉ፥ በመንግሥተ ሰማያት የሚበልጥ እርሱ ነው” ማቴ18፡3,4
ይመጣል የተባለው መሲህ እርሱ እንደሆነ ያመኑ እነዚህ ሰዎች የነገዋን ቤተክርስቲያን የሚመሩ ቀዳሚ ሐዋርያ አድርጎ ጌታ ቢሾማቸውም እነርሱ ግን ገና ዳግም ያልተወለዱ መንፈሳውያን ሳይሆኑ ነገር ግን ስጋውያን በመሆናቸው ክርክራቸውና ጥያቄአቸው አንዱ ከሌላው ስለመብለጥ፣ የሥጋ ጥያቄ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች ገና ዳግም ያለመወለዳቸው ዋንኛ ምክንያት በአዲሱ ኪዳን ለኃጢአት ሥርየት የሚሆነው ደም ገና መፍሰስና የመንፈስ ቅዱስ መምጣት ግድ በመሆኑ ነው ዮሐ3፡5፡፡ ስለዚህ ጌታ በመንግሥተ ሰማይ ትልቅ ማን እንደሆነ ለማወቅ ለጓጉ ለነዚህ ሰዎች የመለሰው መልስ ገና ወደ መንግሥቱ ለመግባት ተመልሶ እንደ ህጻን መሆን አስፈላጊ ስለ መሆኑ ነው፡፡ ህጻን ራሱን ከሌላው ጋር የማያበላልጥ፣ በሌላው ላይ ጥገኛ የሆነ፣ በልቡ ምንም የተሰወረ ነገር የሌለው፣ ወላጁ የሚለውን በገርነት የሚቀበል በመሆኑ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባትም ይህንን መስፈርት ይጠይቃል፡፡ አይደለም በመንግሥቱ ትልቅ ትንሽ ለመሆን ገና ዳግመኛ በመወለድ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት እንዲህ አይነቱን ትህትና ጠያቂ ነው፡፡ እንዲህ ትልቅ ማነው ካልን ራሱን ከሌላው ጋር የሚያወዳድር ሳይሆን ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ነው፡፡
2. ለታናናሾች ስፍራ የሚሰጥ
“እንደዚህም ያለውን አንድ ሕፃን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል” ማቴ18፡5
ትልቅነት ራስን ዝቅ በማድረግና ታናሹን ለመቀበል ባለ ፈቃደኝነት ውስጥ ነው፡፡ ዛሬ በምድር ለትልቅነት የምናስቀምጣቸው መስፈርቶች በሙሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ አይሰሩም ምክንያቱም ሁላችን በእግዚአብሔር ፊት አንድ በመሆናችን ነው፡፡ ማንም የመንግሥተ ሰማይን የጽድቅ መስፈርት አሟልቶ ሊገባ የሚችል ሰው በምድር ላይ የለም ነገር ግን በእግዚአብሔር ምህረት እንገባለን ስለዚህ በኛ ዘንድ ትንሽ ብለን ለምንቆጥራቸው ሰዎች ዋጋ የምንሰጥ ከሆንን እኛ ትልቆች ነን፡፡ ስለዚህ ነው ጌታ ለትንሹ፣ ለተናቀው ሰው ዋጋ የሚሰጥ ለእኔ ሰፍራ ያለው ሰው ነው የሚለው፡፡
3. ለማንም መሰናክል የማይሆን
“በእኔም ከሚያምኑ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ፥ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር መስጠም ይሻለው ነበር። ወዮ ለዓለም ስለ ማሰናከያ፤ ማሰናከያ ሳይመጣ አይቀርምና፥ ነገር ግን በእርሱ ጠንቅ ማሰናከያ ለሚመጣበት ለዚያ ሰው ወዮለት” ማቴ18፡6,7
በስጋዊነት ተሞልቶ ታናሹን የሚያሰናክል ሰው መንገዱ ክፉ ይሆንበታል፡፡ ስለዚህ ስለ ራሳችን መብት እንኳ ቢሆን በምንም መንገድ ለሌሎች የመሰናከላቸው ምክንያት መሆን አይገባም፡፡ ጳውሎስ ስለመብቱ እንኳን ሰውን ላለማሰናከል “ስለዚህም መብል ወንድሜን የሚያሰናክለው ከሆነ፥ ወንድሜን እንዳላሰናክለው ለዘላለም ከቶ ሥጋ አልበላም” 1ቆሮ8፡13 በማለት ምን ያህል ጥንቃቄ የተሞላው መንገድ እንደሄደ እንዳለ እንመለከታለን፡፡ የኛ አኗኗር ሰዎች ጌታን እንዲያዩ አሊያም እንዲሰናከሉ የማድረግ አቅም አለው የዕብራዊው ጸሐፊው ሲናገር “ስለዚህ የላሉትን እጆች የሰለሉትንም ጉልበቶች አቅኑ፤ ያነከሰውም እንዲፈወስ እንጂ እንዳይናጋ፥ ለእግራችሁ ቅን መንገድ አድርጉ። ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና” ዕብ12፡12-14 በዚህ መንገድ ካልተራመድን ሰዎች ጌታን ሊያዩ አይችሉም፡፡ ስለዚህ ሌላውን ላለማሰናከል የኛ የሆነውን እጅ፣ እግር፣ ዓይን ማጣት ይቀላል፡፡ እንግዲህ ትልቅ ማነው ከተባለ ለሌላው የሚኖር ሰው ነው፡፡
4. ለነፍሳት የሚጠነቀቅ
“ምን ይመስላችኋል? ለአንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩት ከእነርሱም አንዱ ቢባዝን፥ ዘጠና ዘጠኙን በተራራ ትቶ ሄዶም የባዘነውን አይፈልግምን? ቢያገኘውም፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ካልባዘኑቱ ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ በእርሱ ደስ ይለዋል” ማቴ18፡12,13
እግዚአብሔር የሰራዊት ሁሉ አምላክ ቢሆንም አንድ ሰው በፊቱ አይቀልም፣ አንድ ሰው በፊቱ ዋጋው ትልቅ ነው፡፡ ልክ እንደ አንድ እረኛ በደህንነት ያሉ በጎቹን ትቶ የጠፋበትንና የባዘነውን ሊፈልግ ይወጣል፣ ባገኘውም ጊዜ እጅግ ይደሰታል፡፡ እርሱ እንዲህ ዋጋ የሚሰጠውን ሰው አቃሎ ለመሰናከሉ ምክንያት መሆን ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ለሌላው ዋጋ የሚከፍል፣ የጠፋውን የሚፈልግ እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ትልቅና ዋጋ የሚሰጠው ሰው ነው፡፡
ጸጋ ይብዛላችሁ
ምንጭ mentesnot_kebed
1 ጴጥሮስ 3:8-18
8 በመጨረሻም ሁላችሁ በአንድ ሐሳብ ተስማሙ፤ እርስ በርሳችሁ ተሳሰቡ፤ እንደ ወንድማማቾች ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ።
9 ክፉን በክፉ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ፤ ምክንያቱም እናንተ የተጠራችሁት እንደነዚህ ያሉትን ነገሮች እያደረጋችሁ በረከትን ለመውረስ ነው።
10 ስለዚህ፣
“ሕይወትን የሚወድድ፣
መልካም ቀኖችን ሊያይ የሚፈልግ፣
ምላሱን ከክፉ፣
ከንፈሮቹንም ተንኰል ከመናገር ይከልክል።
11 ከክፉ ይራቅ፤ መልካምንም ያድርግ፤
ሰላምን ይፈልግ፤ ይከተላትም፤
12 ምክንያቱም የጌታ ዐይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉና፤
ጆሮቹም ጸሎታቸውን ለመስማት የተከፈቱ ናቸው፤
የጌታ ፊት ግን በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።”
13 መልካም ነገር ለማድረግ ብትቀኑ የሚጐዳችሁ ማን ነው?
14 ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኳ መከራ ቢደርስባችሁ ብፁዓን ናችሁ፤ “ዛቻቸውን አትፍሩ፤ አትታወኩም።”
15 ክርስቶስን ጌታ አድርጋችሁ በልባችሁ ቀድሱት። እናንተ ስላላችሁ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁልጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን ይህን ሁሉ በትሕትናና በአክብሮት አድርጉት፤
16 በክርስቶስ ያላችሁን መልካም ጠባይ አክፋፍተው የሚናገሩ ሰዎች በሐሜታቸው እንዲያፍሩ በጎ ኅሊና ይኑራችሁ።
17 የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲህ ከሆነ፣ ክፉ ሠርቶ መከራ ከመቀበል ይልቅ መልካም አድርጎ መከራ መቀበል ይሻላል፤
18 እንዲሁም ክርስቶስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለ ኀጢአት ሞቷልና፤ ወደ እግዚአብሔር ያቀርባችሁ ዘንድ ጻድቅ የሆነው እርሱ ስለ ዐመፀኞች ሞተ፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ
1 ጴጥሮስ 3:8-18
8 በመጨረሻም ሁላችሁ በአንድ ሐሳብ ተስማሙ፤ እርስ በርሳችሁ ተሳሰቡ፤ እንደ ወንድማማቾች ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ።
9 ክፉን በክፉ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ፤ ምክንያቱም እናንተ የተጠራችሁት እንደነዚህ ያሉትን ነገሮች እያደረጋችሁ በረከትን ለመውረስ ነው።
10 ስለዚህ፣
“ሕይወትን የሚወድድ፣
መልካም ቀኖችን ሊያይ የሚፈልግ፣
ምላሱን ከክፉ፣
ከንፈሮቹንም ተንኰል ከመናገር ይከልክል።
11 ከክፉ ይራቅ፤ መልካምንም ያድርግ፤
ሰላምን ይፈልግ፤ ይከተላትም፤
12 ምክንያቱም የጌታ ዐይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉና፤
ጆሮቹም ጸሎታቸውን ለመስማት የተከፈቱ ናቸው፤
የጌታ ፊት ግን በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።”
13 መልካም ነገር ለማድረግ ብትቀኑ የሚጐዳችሁ ማን ነው?
14 ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኳ መከራ ቢደርስባችሁ ብፁዓን ናችሁ፤ “ዛቻቸውን አትፍሩ፤ አትታወኩም።”
15 ክርስቶስን ጌታ አድርጋችሁ በልባችሁ ቀድሱት። እናንተ ስላላችሁ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁልጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን ይህን ሁሉ በትሕትናና በአክብሮት አድርጉት፤
16 በክርስቶስ ያላችሁን መልካም ጠባይ አክፋፍተው የሚናገሩ ሰዎች በሐሜታቸው እንዲያፍሩ በጎ ኅሊና ይኑራችሁ።
17 የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲህ ከሆነ፣ ክፉ ሠርቶ መከራ ከመቀበል ይልቅ መልካም አድርጎ መከራ መቀበል ይሻላል፤
18 እንዲሁም ክርስቶስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለ ኀጢአት ሞቷልና፤ ወደ እግዚአብሔር ያቀርባችሁ ዘንድ ጻድቅ የሆነው እርሱ ስለ ዐመፀኞች ሞተ፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፤
https://kedusbible.com
1 ጴጥሮስ 3:1-7
1 ሚስቶች ሆይ፤ እናንተም እንደዚሁ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ አንዳንድ ለቃሉ የማይታዘዙ ቢኖሩ፣ ያለ ቃል በሚስቶቻቸው አኗኗር ተማርከው ይመለሳሉ፤
2 ይህም የሚሆነው ንጹሕና ፍጹም አክብሮት የተሞላውን ኑሯችሁን ሲመለከቱ ነው።
3 ውበታችሁ በውጫዊ ነገሮች በመሽሞንሞን፣ ይኸውም፣ ሹሩባ በመሠራት፣ በወርቅ በማጌጥና በልብስ አይሁን፤
4 ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ፣ ገርና ጭምት መንፈስ ያለበት፣ ምንጊዜም የማይጠፋ የውስጥ ሰውነት ውበት ይሁን፤
5 ተስፋቸውን በእግዚአብሔር ላይ የጣሉ የቀድሞ ቅዱሳን ሴቶች ራሳቸውን ያስዋቡት በዚህ ዐይነት ለባሎቻቸው በመገዛት ነበርና።
6 ሣራም አብርሃምን “ጌታዬ” እያለች ትታዘዘው ነበር፣ እናንተም ምንም ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ የእርሷ ልጆች ናችሁ።
7 ባሎች ሆይ፤ እናንተም ደግሞ ጸሎታችሁ እንዳይደናቀፍ በኑሯችሁ ሁሉ ለሚስቶቻችሁ ዐስቡላቸው፤ ደካሞች ስለሆኑና የሕይወትንም በረከት አብረዋችሁ ስለሚወርሱ አክብሯቸው።
1 ጴጥሮስ 3:1-7
1 ሚስቶች ሆይ፤ እናንተም እንደዚሁ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ አንዳንድ ለቃሉ የማይታዘዙ ቢኖሩ፣ ያለ ቃል በሚስቶቻቸው አኗኗር ተማርከው ይመለሳሉ፤
2 ይህም የሚሆነው ንጹሕና ፍጹም አክብሮት የተሞላውን ኑሯችሁን ሲመለከቱ ነው።
3 ውበታችሁ በውጫዊ ነገሮች በመሽሞንሞን፣ ይኸውም፣ ሹሩባ በመሠራት፣ በወርቅ በማጌጥና በልብስ አይሁን፤
4 ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ፣ ገርና ጭምት መንፈስ ያለበት፣ ምንጊዜም የማይጠፋ የውስጥ ሰውነት ውበት ይሁን፤
5 ተስፋቸውን በእግዚአብሔር ላይ የጣሉ የቀድሞ ቅዱሳን ሴቶች ራሳቸውን ያስዋቡት በዚህ ዐይነት ለባሎቻቸው በመገዛት ነበርና።
6 ሣራም አብርሃምን “ጌታዬ” እያለች ትታዘዘው ነበር፣ እናንተም ምንም ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ የእርሷ ልጆች ናችሁ።
7 ባሎች ሆይ፤ እናንተም ደግሞ ጸሎታችሁ እንዳይደናቀፍ በኑሯችሁ ሁሉ ለሚስቶቻችሁ ዐስቡላቸው፤ ደካሞች ስለሆኑና የሕይወትንም በረከት አብረዋችሁ ስለሚወርሱ አክብሯቸው።
ታማኝነት ለቤተ ክርስቲያን
በመጋቢ ተስፋዬ ገመቹ
መጋቢ የሚለው ቃል ባለ አደራ ማለት ነው። ይህ ስም ከእረኞች ጋር የተያያዘ ብቻ አይደለም። የእግዚአብሔርን ምስጢር ለመግለጥና ለማስተዳደር እንዲሁም ለማገልገል አደራ የተሰጣቸው ናቸው። አደራ የተቀበሉት ሲል አድርጉ የተባሉትን የሚያደርጉ፥ ም መሆን እንደሚጠበቅባቸው ታማኝነት እንደሚጠበቅባቸው ይናገራል። አደራ ክብደቱና ቅለቱ የሚለካው በአደራው ሰጪ ማንነት ነው። አደራውን የሰጠው እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር ለአገልግሎቱ ሾመኝ፥ ይህን ሲያደርግ እግዚአብሔር ጻዲቅ ያልነበርነውን ጻዲቅ አድርጎ ቆጠረን። በሕያው እግዚአብሔር ቤት እርሱ የሰጠን አደራ ታማኝ አድርጎ ስለቆጠረን ነው። እግዚአብሔር አሰራሩ ገራሚ ነው። ያልታመኑ ሰዎች ስንታመናቸው ታማኝነታቸው ይጨምራል። ሾመን፥ አመነን፥ ኃይል ሰጠን። ታማኝ አድርጎ ቆጥሮናልና እግዚአብሔር እንድንታመነው ይፈልጋል። ታማኝነት ማለት ምን ማለት ነው? ለቤተ ክርስቲያንስ መታመን ለምን አስፈለገ?
ታማኝ፥ ሀቀኛ - ቃሉን አክባሪ አደርጋለው ያለውን የሚያደርግ ማለት ነው። ታማኝነት እውነተኛነት፥ ሀቀኝነት፥ እርግጠኝነት ማለት ነው። ሃይማኖቱን እምነቱን የማይክድ ብለው ያብራራሉ ዘርጋው እና ከሳቴ ብርሃን የተባሉ የአማርኛ መዝገበ ቃላት። ለተናገርነው ነገር እውነተኛ መሆን ቃልን መጠበቅ ማለት ነው። የታመኑ ማለት ያመኑ ከማለት ልዩነት የልወም። አንድ ሰው ክርስቲያን ነኝ ካለ ታማኝነት ይጠበቅበታል። ክርስቲያንነት ታማኝነት ነው። አገልግሎት ከክርስትና የሚከተል ነው። ክርስትናን ካልኖርነው ማገልገል አንችልም። አማኝነት ታማኝነት ነውና። ታማኝነት ባህሪይ ነው። ያለመለወጥ ነው። በተናገሩበት በዛው መገኘት፥ መጽናት ቃልን መጠበቅ ነው። ከማንነታችን ጋር የሚሰፋ ነው። አንድ ሰው ለአንድ ዓላማ/ጉዳይ ያለው ቁርጠኝነት ነው። ለአንድ ጭብጥ ወይም ኣላማ ያለን ቁርጠኛ መሰጠታችን ነው። ለቤተ ክርስቲያን እንዲህ ያለ መስጠት ያስፈልጋል። ለቤተ ክርስቲያን ታምኖ መሰጠትን እግዚአብሄር ከእኔና ከእናንተ ይጠብቃል።
ክርስቲያን መታመን ለምን አስፈለገው? እግዚአብሔር የታመነ ስለሆነ ነው። 2ኛ ጤሞ. 2፡13 - 1ኛ ቆሮ. 1፡19
ቤተ ክርስቲያን ጌታ የሚወዳት አካሉና መቅደሱ ማደሪያው ስለሆነች ነው። የሐዋ 9፡4 ለቤተ ክርስቲያን መታመን ለጌታ መታመን ነው። አደራ ከተሰጠው አገልጋይ ታማኝነት ይፈለጋል። ምንም ይሁን ምን እግዚአብሔር ካንተ የሚጠብቀው ታማኝነት ነው። ባለ አደራነት፥ መጋቢነትን እግዚአብሔር ይፈልጋል። እግዚአብሔር አደራ የሰጠው ሁሉ መጋቢ ነው።
ታማኝ መሆን ከጌታ ዘንድ ብድራትን ያስገኛል። ባልታመንን መጠን ኪሳራችን ለራሳችን ነው። የኛ ያለመታመን ቤተ ክርስቲያንን ይጎዳል። የታማኝነት ደስታው፥ በረከቱ፥ ከጌታ ብድራቱ ብዙ ነው። ጌታን ማክበር ማለት የአካል ብልት ከሌላው ጋር ተሰናስሎ /ተቀናጅቶ እግዚአብሔርን አብሮ ያከብራል።አንዱ ሲደክም ሌላው ይደክማል። መታመናችን ለቅዱሳንም ይጠቅማል። ስለዚህም ባልታመንን መጠን ለሌሎችም ችግር የምንሆን ነን። ለራሳችን ስንል ለሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን እንታመን።
ለቤተ ክርስቲያን መታመን ተግዳሮት አለው። በኢትዮጵያ ክርስትና ውስጥ
የግለኝነት ባህል መስፋፋት - ቤ/ክ ሁሉ ነገሯ በጋራ ስለሆነ ከዚህ በተቃራኒው ዓለም እያስፋፋች ያለው ግለኝነትን ስለሆነ ነው። ይሄ ቅዱሳንን እንደ ጉድ እያጠፋ ነው። ክርስትና የኔ የግሌ ጉዳይ አይደለም የጋራ እንጂ። ግለኝነት ሲጫነን እንፍራ፥ ማገልገል የጌታ ጉዳይ መሆኑ ቀርቶ የራስ ስምና መታወቂያ ሆኗል።
የማስ ሚድያና የሶሻል ሚዲያ ተጽዕኖ - ቤተ ክርስቲያንን ቴሌቭዥን አይተካም። እግዚአብሔር በአካል እንድንተያይ እና አብረን እንድንነካካ ይፈልጋል። አጠገቡ ለእርሱ የሚሞቱ ሳይሆኑ በሚዲያ የሚታዩ ሰዎችን ብቻ ያደንቃል፥ ይወዳል።
ቁሳዊነት፥ መንፈሳዊነት መምሰሉ፥ የብልጽግና ወንጌል ትምህርት ተጽዕኖ፥ እኔ ምን ቁሳዊ ጥቅም አገኛለሁ ብሎ መጠየቅ ዋና መርህ መሆኑ፥ ከቁስ ጋር መጣበቅ። በቤተ ክርስቲያን መኖር፥ መገልገልና ማገልገል ግዴታ እንጂ አማራጭ አይደለም።
ሀሰተኛ እምነቶችና ፍልስፍናዎች - ሁሉ ነገር በዚህ ዘመን ቅይጥይጥ ብሏል። ለክርስትና ትምህርቶች ብወአጉ ማወቅ እየተውን ነው ያለው። ልክ ያልሆኑ ትምህርቶች እየተስፋፉ ይገኛሉ።
ስለዚህም መትጋት፥ መታመን እና ስለ ምዕመኑ ታማኝ የክርስቶስ አገልጋይ መሆን ተገቢ ነው። ልናገለግል ብቻ አይደለም ነፍሳችንን ልንሰጣችሁ እንወዳለን ነው ያለው ሐዋሪያው ጳውሎስ። ከምንናገረው በላይ ነው እግዚአብሔር ያለንን ልብ የሚፈትሸው። አገልግሎትን አገልግሎት የሚያደርገው ፍቅር ነው። ወደናቸው እንዘምር፥ ወደናቸው እናገልግላቸው። መረጋጋት፥ ሰላም ማግኘት፥ መልካም ምስክርነት፥ ቤተ ክርስቲያን ጤናማ እድገት ማሳየትና መቻል የአገልጋዮችና ምዕመናን የመታመን ውጤት ነው። ሰዎች ባልታመኑ መጠን እግዚአብሔር አደራን ሊነጥቅ ይቻላል። ለውጤት መብቃት የጋራ ታማኝነትን ይፈልጋል።
