uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

Debtera Media

Debtera Media

Відкрити в Telegram

ደብተራ ሚዲያ የእውነት ድምጽ! ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!👇 በዩቲዩብ 👉 https://bit.ly/3bMfT8D በፌስቡክ 👉 fb.me/DebteraMedia በቴሌግራም 👉 t.me/DebteraMedia ማንኛውንም ሃሳብ አስተያየት ሆነ መረጃ በ t.me/DebteraMedia_Bot ማድረስ ትችላላችሁ።

Показати більше
3 513
Підписники
-224 години
-97 днів
-5530 днів
Архів дописів
photo content

+1
[ + ገሊላ እትዊ + ] .mp37.28 MB

🕊 🌺 🕊 [ 🕊 ድንግል ሆይ 🕊 ] 🕊 🌺 🕊 🌹 ተፈጸመ ናሁ ማሕሌተ ጽጌ 🌹 ❝ የሚያብረቀርቅ ቀይና ነጭ ቀለም ያለው አርአያው የብር ዝንጒርጒር ጠቃጠቆ የኾነ ንጹሕ ተአምርሽ በወርቅ
🕊                        🌺                       🕊        [    🕊 ድንግል ሆይ  🕊    ] 🕊                        🌺                       🕊 🌹    ተፈጸመ ናሁ ማሕሌተ ጽጌ     🌹 ❝ የሚያብረቀርቅ ቀይና ነጭ ቀለም ያለው አርአያው የብር ዝንጒርጒር ጠቃጠቆ የኾነ ንጹሕ ተአምርሽ በወርቅ አምሳል የተሠራ ነው ፤ እነሆ የተወደደ [ መልካም ] ማሕሌተ ጽጌ ደረሰ ተፈጸመ ፤ የሰማይና የምድር ንግሥት ማርያም ሆይ የተወደደ ልጅሽ በጒያሽ [ በዕቅፍሽ ] እንዲጠጋ [ እንዲደገፍ ፣ እንዲንተራስ ] በርሱ ዐማጽኚ፡፡ ❞ [ አባ ጽጌ ድንግል] 🌸        🌸 ❝ እመቤቴ ማርያም ሆይ በመገዛት አመሰግንሻለሁ:: በመማጸንም አገንሻለሁ። አንቺ የሊቀ ካህናቱ መሠውያ ሁነሻልና ልጅሽም በእውነት ለሚመገበው የሕይወት ምግብ ነው:: ሕፃንሽ ከልብ ለሚያዳምጠው ምክሩ ጣፋጭ ነው። ቁጣ የሌለብሽ ርኅሩኅ ሆይ ወደ አንቺ እጸልያለሁ ፤ በመማለድም ወደ አንቺ እለምናለሁ:: በኵርሽ /ልጅሽ ክርስቶስ/ አካሔዴን ወደ ጽድቅ መንገድ ያቅና ስምሽን በማስታወስ በጠራሁት ጊዜም በእውነት ይነጋግረኝ። አንቺም ለዚህ ለአገልጋይ የሚጠቅመውን ስጠው በሥልጣንህ እርዳው ፤ በእጅህም አጽናው ፤ ከሚያስፈራው የሕይወት ጠላቱም መፈራትን አጐናጽፈው በይው:: ለዘለዓለሙ አሜን:: ❞ ❝ ሱላማጢስ ሆይ ተመለሺ ! ❞ [መሓ. ፯:፩] 🌹                                                    🌹                            †††                ✟𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y✟ 🕊                         💖                        🕊

photo content

[ ስንክሳር ጥቅምት - ፳፱ - ] .mp38.42 MB

" በእሸቅድምድም ሥፍራ የሚሮጡት ሁሉ እንዲሮጡ: ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ:: የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል:: እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው:: እኛ ግን የማይጠፋውን::" [፩ቆሮ.፱፥፳፬] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖

🕊 † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ † [  እንኩዋን ለአበው ቅዱሳን "ሳሙኤል ዘወገግ": "ጸቃውዐ ድንግል" እና "ድሜጥሮስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።   ] 🕊  † አባ ሳሙኤል ዘወገግ  †  🕊 ሃገራችን ኢትዮዽያ ማኅደረ ቅዱሳን [ምዕራፈ ቅዱሳን] እንደ መሆኗ ፍሬ ክብር: ፍሬ ትሩፋት ያፈሩ ብዙ አባቶችና እናቶችን አፍርታለች:: ብርሃን ሁነው ካበሩላት ቅዱሳን መካከል አንዱ ደግሞ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ ናቸው:: በእኛው ሃገር ብቻ ብዙ "ሳሙኤል" የሚባሉ ቅዱሳን በመኖራቸው ስንጠራቸው "ዘእንትን" እያልን ነው:: ለምሳሌም: - ሳሙኤል ዘዋሊ - ሳሙኤል ዘወገግ [የዛሬው] - ሳሙኤል ዘጣሬጣ - ሳሙኤል ዘቆየጻ - ሳሙኤል ዘሃሌ ሉያና - ሳሙኤል ዘግሺን መጥቀስ እንችላለን:: ሁሉም የመካከለኛው ዘመን ሐዋርያዊ አባቶች ናቸው:: ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ የተወለዱት በ፲፫ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ሃገረ ሙላዳቸው የብዙ ቅዱሳን ቤት የሆነችው ሽዋ ናት:: መንደራቸውም ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ብዙም አይርቅም:: የጻድቁ ወላጆች እንድርያስና አርሶንያ የሚባሉ ሲሆን ደጐች ነበሩ:: ጻድቁ በተወለደ ጊዜ የቤታቸው ምሰሶ ለምልሞ ተገኝቷል:: አቡነ ሳሙኤል ከልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው በጉብዝናቸው ወራት ይህችን ዓለም ንቀዋል:: የታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ደቀ መዝሙር ሆነው በደብረ ሊባኖስ መንነዋል:: ከ፲፪ቱ ኅሩያን [ምርጦች] አርድእት አንዱ ነበሩና በክህነታቸው ደብረ ሊባኖስን ተግተው ያጥኑ ነበር:: በዚያውም በንጹሕ ልቡና በጾምና ጸሎት ይተጉ ነበር:: አቡነ ተክለ ሃይማኖት ካረፉ በሁዋላ በደጉ ዻዻስ በአቡነ ያዕቆብ ዘመን ፲፪ቱ ንቡራነ እድ ተመረጡ:: እነዚህ አባቶች በወንጌል አገልግሎት: በተለይ ደቡብና ምሥራቁን የሃገራችን ክፍል ያበሩ ናቸው:: ቅዱሳኑ ሲመረጡም ከአቡነ ፊልዾስ ቀጥለው በ፪ኛ ደረጃ የተመረጡ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ ናቸው:: ሃገረ ስብከታቸውም ሐረርና ሱማሌ ነበር:: ጻድቁ በሃገረ ስብከታቸው ወርደው በሐረርና ሱማሌ አካባቢ ለዘመናት የወንጌልን ዘር ዘርተው እልፍ ፍሬን አፍርተዋል:: አካባቢውንም መካነ ቅዱሳን አድርገውታል:: ቀጥለው ገዳማዊ ሕይወትን ያጸኑ ዘንድ በምሥራቁ የሃገራችን ክፍል በአፋር ሱባኤ ገቡ:: ቦታውም ደብር ሐዘሎ ነበር:: በቦታው ለ፻፶፭ ቀናት ከቆሙ ሳያርፉ: ከዘረጉ ሳያጥፉ: እህል ውሃ ሳይቀምሱ ጸለዩ:: በሱባኤያቸው ፍጻሜ ግን ቅዱስ መልአክ መጥቶ "ሳሙኤል ወደዚያ ተራራ ሒድ:: የስምህ መጠሪያ እርሱ ነውና:: ይህ ግን የሌላ ሰው [የአባ አንበስ ዘሐዘሎ] ርስት ነው" አላቸው:: ጻድቁም ወዳላቸው ተራራ ሒደው ቢጸልዩ ከሰማይ ብርሃን ወረደላቸው:: በመንፈቀ ሌሊት የበራው ብርሃን እስከ ጐረቤት መንደር ሁሉ በመድረሱ የአካባቢው ሰው "ወገግ አለኮ-ነጋ" ብለውዋል:: በዚህ ምክንያት ዛሬም "ደብረ ወገግ" ይባላል:: ይህ ቦታ ዛሬም ድረስ ንጹሕ ልብ ላላቸው አበው በብርሃን ተከቦ ይታያል:: ጻድቁ የወለዷቸው ብዙ ሥውራንም በሥፍራው ይገኛሉ:: ቦታው የአንበሶች መኖሪያ በመሆኑ ጠላት መናንያኑን ማጥቃት አይችልም:: ሳሙኤል ዘወገግም የሚጸልዩት በአናብስት ተከበው ነበር:: በቦታው አንዳንዴም አንበሶች ሲሰግዱ ይታያል ይባላል:: ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ግን እንዲህ በቅድስና ተመላልሰው በ፲፬ኛው መቶ ክ/ዘመን ሱማሌ ክልል ውስጥ በዚህች ቀን ዐርፈዋል:: የጻድቁ ልደት ሐምሌ ፱ : ፍልሠታቸው ደግሞ ግንቦት ፳፯ ነው:: 🕊 † አባ ጸቃውዐ ድንግል † 🕊 እኒህ ጻድቅም ኢትዮዽያዊ ናቸው:: የስማቸው ትርጉም "የድንግል ማርያም ወለላ ማር" ማለት ሲሆን ዜና ሕይወታቸው እንደ ስማቸው ጣፋጭ ነው:: የእኒህ ጻድቅ አባታቸው የተመሰከረላቸው ሊቅና የገዳም መምሕር ናቸው:: ምክንያቱም ጸቃውዐ ድንግልን ከወለዱ በሁዋላ መንነዋልና:: አባት የደብረ ዘኸኝ መምሕር ሳሉ ልጃቸው ጸቃውዓ ድንግልን ወደ ገዳሙ ወስደው አሳደጉዋቸው:: በዚያውም ጾምና ጸሎትን: ትዕግስትና ትሕርምትን አስተማሯቸው:: ቅዱሳት መጻሕፍትንም በወጉ አስጠኗቸው:: አባ ጸቃውዐ ድንከግልም በጐውን የምናኔ ጐዳና ከተማሩ በሁዋላ መዓርገ ምንኩስናን ተቀበሉ:: ፵ ዓመት ሲሞላቸው ግን አባታቸው ዐረፉ:: መነኮሳት አበውም ተሰብስበው "ከአንተ የተሻለ የለም" ሲሉ ጸቃውዐ ድንግልን የደብረ ዘኸኝ መምሕር አድርገው ሾሟቸው:: ጻድቁም ቀን ቀን ሲያስተምሩ ይውሉና ሌሊት ባሕር ውስጥ ሰጥመው ሲጸልዩ ያድሩ ነበር:: በሌሊትም ከባሕሩ ወጥተው የአካላቸው ርጥበት ደርቆ ላበታቸው እስኪንጠፈጠፍ ድረስ ይሰግዱ ነበር:: በዚህ መንገድም ራሳቸውን ገዝተው: መነኮሳትንም ገርተው ያዙ:: እግዚአብሔርም ክብራቸውን ይገልጽ ዘንድ ብዙ ተአምራትን በእጃቸው አሳይቷል:: አንድ ቀን አባ ጸቃውዐ ድንግል መንገድ ሲሔዱ ሁለመናው በቁስል የተመታ አንድ መጻጉዕ ነዳይ ወድቆ አዩ:: ወደ እርሱ ሲደርሱ ምጽዋትን ለመናቸው:: ጻድቁ ግን "የምሰጥህ ነገር የለኝም:: ግን የፈጣሪየን ስጦታ እሰጥሃለሁ" ብለው: በውሃ ላይ ጸልየው ረጩት:: ያ መጻጉዕም አካሉ ታድሶ: እንደ እንቦሳ ዘሎ ተነሳ:: ደስ እያለው: ፈጣሪውንም እያከበረ ወደ ቤቱ ሔዷል:: አባ ጸቃውዐ ድንግልም በዚህች ቀን ዐርፈው በገዳማቸው ተቀብረዋል:: 🕊 † ቅዱስ ድሜጥሮስ ሰማዕት † 🕊 ይህ ቅዱስ በዘመነ ሰማዕታት: በ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከነበሩ ክርስቲያኖች አንዱ ነው:: ቅዱስ ድሜጥሮስ ስቅጣር ከሚባል ደግ ባልንጀራው ጋር በበጐው ጐዳና ሲኖሩ የመከራው ዘመን ደረሰ:: መወሰን ነበረባቸውና ፈጣሪያቸውን ከሚክዱ ሞትን መረጡ:: አስቀድሞም ሲያስተምር በመገኘቱ ቅዱስ ድሜጥሮስ በንጉሡ እጅ ወደቀ:: ንጉሡ መክስምያኖስም እሥራትን አዘዘበት:: በዚያ ወራት ደግሞ የንጉሡ ወታደር የሆነና በጣዖት የሚመካ አንድ ጉልበተኛ ነበር:: ማንም በትግል አሸንፎት ስለማያውቅ ጣዖታዊው ንጉሥ ይመካበት ነበር:: አንድ ቀን ግን አንድ ክርስቲያን ወደ እሥር ቤት ገብቶ ቅዱስ ድሜጥሮስን "ባርከኝና ያንን ጣዖታዊ ጉልበተኛ እጥለዋለሁ" አለው:: የቅዱሱን ጸሎትና በረከት ተቀብሎም በንጉሡ አደባባይ ታግሎ ጣለው:: ንጉሡና የጣዖቱ ካህናትም በእጅጉ አፈሩ:: በሁዋላ ግን ይህንን ያደረገው ቅዱስ ድሜጥሮስ መሆኑ በመታወቁ ከባልንጀራው ቅዱስ ስቅጣር ጋር በዚህች ቀን ገድለዋቸዋል:: አምላከ አበው ቅዱሳን ጸጋ ክብራቸውን ያብዛልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: 🕊 [ † ጥቅምት ፳፱ [ 29 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. አቡነ ሳሙኤል ጻድቅ [ዘደብረ ወገግ] ፪. አባ ጸቃውዐ ድንግል [ዘደብረ ዘኸኝ] ፫. ቅዱስ ድሜጥሮስ ሰማዕት ፬. ቅዱስ ስቅጣር ሰማዕት [ † ወርኀዊ በዓላት ] ፩. የፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ፪. ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት ፫. ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ ፬. ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት ፭. ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ ፮. ቅድስት አርሴማ ድንግል

photo content

[ + እንሂድ ተነሺ + ] .mp37.38 MB

🌺 🌺 🌷 [ 🕊 የግፉዓን መጠጊያ ! 🕊 ] 🌷 🌸 🌸 ❝ ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን ፤ ​ኢየሱስ ግፉዕ ምስካዮሙ ለግፉዓን ፤ እግዚአብሔር ማኅደር ዘአልቦ ከመ ነዳያን ፤ ኢየሱስ ነግ
🌺                                                  🌺    🌷  [   🕊  የግፉዓን    መጠጊያ ! 🕊  ] 🌷 🌸                                                  🌸  ❝ ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን ፤ ​ኢየሱስ ግፉዕ ምስካዮሙ ለግፉዓን ፤ እግዚአብሔር ማኅደር ዘአልቦ ከመ ነዳያን ፤ ኢየሱስ ነግድ ወፈላሲ እንዘ ውእቱ ሕጻን ፤ ወልደ አብ ፍቁር በኀበ ሰብእ ምኑን ፤ መኃልየ ብካይ ኮነኒ ዘእሙ ኃዘን። ❞ 🌷      🕊                               🕊     🌷 ትርጉም ፦ [ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመሰደዱ የስደተኞች ተስፋ በመገፋቱ የግፉዓን መጠጊያ ኾነ። የዓለማት ፈጣሪ የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጁ እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን በለበሰበት የሕፃንነቱ ወራት እንደ ነዳያን ቤት ስንኳ የሌለው ስደተኛና መጻተኛ ኾኖ በሰዎች ዘንድ እንደምን ተናቀ እያልኹ የእናቱ ድንግል ማርያም ኀዘን ለእኔ የልቅሶ ዜማ ኾነብኝ። ] [ ሰቆቃወ ድንግል ] 🌸                                                    🌸                            †††                ✟𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y✟ 🕊                         💖                        🕊

photo content

[ የወጣቶች ሕይወት - ፭ - ] .mp37.83 MB

🕊 💖 🕊 [ 🕊 ድምፀ ተዋሕዶ 🕊 ] 🍒 🍒 [ ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ። ] [ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]
🕊                        💖                       🕊           [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]   🍒                                                    🍒 [  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]         [   ሳምንታዊ መርሐ-ግብር   ] 🌸                         ♱                       🌸 [ ሕይወተ ወራዙት [ የወጣቶች ሕይወት ! ]               [   ክፍል አምስት   ]           💛   ድንቅ ትምህርት  💛 [ በመምህራችን ቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ] 🍒                                                    🍒 ❝ የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ] 🌸                                                  🌸                            †††                ✟ 𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y ✟ 🕊                        💖                        🕊                              👇

photo content

6! ሰዓሊ ለነ.mp36.12 MB

🕊 🌺 🕊 💛 [ † ቅዱስ አቡነ ይምአታ † ] 💛 🕊 🌺 🕊 ❝ † ሰላም ለአባ ይምአታ ዘከለሎ እግዚአብሔር ወልታ † ❞ [ ጋሻ እግዚአብሔር የጋረደው ለኾነ ለአባ ይምአታ ሰላምታ ይገባል።
🕊                        🌺                       🕊 💛   [   † ቅዱስ  አቡነ ይምአታ  †  ]  💛     🕊                        🌺                       🕊 ❝ †  ሰላም ለአባ ይምአታ ዘከለሎ እግዚአብሔር ወልታ  † ❞ [ ጋሻ እግዚአብሔር የጋረደው ለኾነ ለአባ ይምአታ ሰላምታ ይገባል። ] [ ተአምኆ ቅዱሳን ] 🌸                         ♱                       🌸 አባ ይምአታ ቁጥራቸው ከዘጠኙ ቅዱሳን ሲኾን የመጡት እስያ ሀገር ሲኾን ገርአልታ በተራራው ላይ ገዳምን ገድመዋል ፤ በዓላቸውም ዛሬ ጥቅምት ፳፰ ቀን ነው። 💛                                                 💛 ሊቁም እንዲህ በማለት ቅዱስ አባታችንን አመስግኗቸዋል ፦ ❝ † በከሃሊ አምላክ ፈቃድ ወንዝን ለኹለት የከፈለ ፤ ሥርዐትን ከሹና ሕግንም ከጠበቁ ሽማግሎች ጋር የተባበረ ለኾነ ለአባ ይምአታ ሰላምታ ይገባል ፤ የሥጋው በድን ግን ወደ ተራራ ላይ በወጣ ጊዜ የግንዘቱ ምልክት በዐለት ላይ ለምልክት ቀረ።  † ❞ [ ተአምኆ ቅዱሳን ] 🕊                        💖                     🕊 [  † የቅዱስ አባታችን የአባ ይምአታ ጸሎት ከዘላለም እሳት ያድነን። በረከታቸው ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን። †  ] 🌸                                                    🌸                            †††                ✟𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y✟ 🕊                         💖                        🕊

photo content

[ ስንክሳር ጥቅምት - ፳፰ - ] .mp34.99 MB

🕊 [  † እንኳን ለጻድቁ አቡነ ይምዓታ እና ለአበው ቅዱሳን መርትያኖስ ወመርቆሬዎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ] † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † †  🕊   አባ ይምዓታ ጻድቅ  🕊  † † ጻድቁ ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ቢሆንም ሃገረ ሙላዳቸው የጥንቱ የሮም ግዛት የሆነችው ታናሽ እስያ ናት:: አባ ይምዓታ ከዘጠኙ [ተስዓቱ] ቅዱሳን አንዱ ናቸው:: ዘጠኙ ቅዱሳን ተወልደው ያደጉት ምንም በአንድ የሮም ግዛት ሥር ቢሆንም መነሻ ቦታቸው ግን የተለያየ ነው:: ሁሉንም አንድ ያደረጋቸው መንፈስ ቅዱስ በኪነ ጥበቡ ነው:: በምክንያት ደረጃ እንግለጸው ከተባለ ደግሞ የአንድነታቸው ምሥጢር :- ፩. የቀናች ሃይማኖታቸው ተዋሕዶ:: ፪. ዓላማ [የእግዚአብሔር መንግስት] እና ፫. ገዳማዊ ሕይወት ነው:: አባ ይምዓታን ጨምሮ ሁሉም ቅዱሳን ዘራቸው ከቤተ መንግስት ነው:: እነርሱ ግን ምድራዊውን ክብር ንቀው ሰማያዊውን ክብር ገንዘብ ማድረግን መርጠዋል:: አስቀድመው ቅዱሳት መጻሕፍትን ያጠኑት አበው በተለያየ ጊዜ እየመነኑ ከሮም ግዛት ወደ ግብጽ በርሃዎች ወርደዋል:: በምናኔ ቅድሚያውን አባ ዸንጠሌዎንና አቡነ አረጋዊ ይይዛሉ:: ዘመኑ የተዋሕዶ አማኞች የሚሰደዱበት ፭ኛው መቶ ክ/ዘመን ነበርና እምነትን ላለመለወጥ ዘጠኙ ቅዱሳን ስደትን መረጡ:: በወቅቱ ደግሞ ለስደት መጠለያ የምትሆንና ከኢትዮዽያ የተሻለች ሃገር አልነበረችም:: ስለዚህም በ፬፻፸ዎቹ ዓ/ም አልዓሜዳ በኢትዮዽያ ነግሦ ሳለ ቅዱሳኑ በአረጋዊ መሪነት መጡ:: ንጉሡም ሲጀመር የእግዚአብሔር እንግዳ ስለሆኑ: ሲቀጥል ደግሞ ቅድስናቸውን ተመልክቶ መልካም አቀባበልን አደረገላቸው:: ማረፊያ ትሆናቸውም ዘንድ አክሱም ውስጥ አንዲት ቦታን ወስኖ ሰጣቸው:: ይህች ቦታ "ቤተ ቀጢን" ትባላለች:: አባ ይምዓታና ፰ቱ ቅዱሳን ወደ ሃገራችን እንደ ገቡ የመጀመሪያ ሥራቸው ቋንቋን መማር ነበር:: ልሳነ ግዕዝን በወጉ ተምረው እዛው አክሱም አካባቢ ሥራቸውን አንድ አሉ:: በወቅቱ በአቡነ ሰላማ: በአብርሃ ወአጽብሐና በአቡነ ሙሴ ቀዳማዊ የተቀጣጠለው ክርስትና በተወሰነ መንገድ ተቀዛቅዞ ነበርና እነ አባ ይምዓታ እንደ ገና አቀጣጠሉት:: ሕዝቡን በራሱ ልሳን ለክርስትና ይነቃቃ ዘንድ ሰበኩት:: የካደውን እየመለሱ: የቀዘቀዘውን እያሟሟቁ ለዓመታት ወንጌልን ሰበኩ:: ቀጣዩ ሥራቸው ደግሞ መጻሕፍትን መተርጐም ሆነ:: ከሃገራቸው ያመጧቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት ተከፋፍለው ወደ ግዕዝ ልሳን ተረጐሟቸው:: በዚህም ለሃገራችን ትልቁን ውለታ ዋሉ:: ይህ ሁሉ ሲሆን እነ አባ ይምዓታ የሚመገቡትም ሆነ የሚጸልዩት በማሕበር ነበር:: በመካከላቸውም ፍጹም ፍቅር ነበር:: ጸጋ እግዚአብሔር አልተለያቸውም:: የነ አባ ይምዓታ ቀጣዩ ተግባራቸው ደግሞ ገዳማዊ ሕይወትን ማስፋፋት ሆነ:: ይህንን ለማድረግ ግን የግድ መለያየት አስፈለጋቸው:: እያንዳንዱም መንፈስ ቅዱስ ወደ መራው ቦታ ሔደ:: - ዸንጠሌዎን በጾማዕት:: - ገሪማ በመደራ:: - ሊቃኖስ በቆናጽል:: - አረጋዊ በዳሞ:: - ጽሕማ በጸድያ:: - ሌሎችም በሌላ ቦታ ገዳማትን መሠረቱ:: - አባ ይምዓታ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ምርጫቸው ገርዓልታ [እዛው ትግራይ] ሆነ:: ጻድቁ ወደ ቦታው ሲሔዱ ወንዝ [ባሕር] ተከፍሎላቸዋል:: ወደ ቦታው ደርሰውም ገዳም አንጸዋል:: በቦታውም ብዙ ተአምራትን ሠርተው በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፍርተዋል:: የአቡነ ይምዓታ ገዳም ገርዓልታ [በፎቶው ላይ እንደምናየው] እጅግ ድንቅና ማራኪ ነው:: ነገር ግን እዛው ድረስ ሒዶ ለማየት ብርታትን ይጠይቃል:: በተራሮች መካከል ከመቀመጡ ባሻገር የአባቶቻችንን ጽናት የሚያሳይ ድንቅ ቦታ ነው:: ጻድቁ በዚሁ በፎቶው ላይ በምናየው ገዳም ለዘመናት ተጋድለው በዚህች ቀን ዐርፈዋል:: †  🕊 ቅዱሳን መርትያኖስና መርቆሬዎስ 🕊  †  † እነዚህ ቅዱሳን የቁስጥንጥንያ ሰዎች ሲሆኑ የወቅቱ ፓትርያርክ አባ ዻውሎስም ደቀ መዛሙርት ናቸው:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ አካባቢ በአርዮሳውያን ምክንያት ስደት በሆነ ጊዜ አባ ዻውሎስ: ቅዱስ አትናቴዎስ: ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስና ቅዱስ ሊዋርዮስ ከመንበራቸው ተፈናቀሉ:: በስደቱ ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ ሲያርፍ ቅዱሳኑ አትናቴዎስና ሊዋርዮስ ተመለሱ:: አባ ዻውሎስን ግን በእሥር ቤት ውስጥ ሳለ በንጉሡ ትዕዛዝ አርዮሳውያን አንቀው ገደሉት:: ይህንን ያወቁት 2ቱ ደቀ መዛሙርቱ [መርቆሬዎስና መርትያኖስ] ቅዱስ አባታቸውን ቀብረው ንጉሡን ረገሙት:: አርዮሳዊው ታናሹ ቆስጠንጢኖስም ይህንን በሰማ ጊዜ ፪ቱንም አስመጥቶ በአደባባይ በሰይፍ አስመታቸው:: ይህ ከተከናወነ ከ፶ ዓመታት በሁዋላም ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ ሆኖ በመምጣቱ ሥጋቸውን አፈለሠ:: ቤተ ክርስቲያንንም አንጾ ቀድሶላቸዋል:: † አምላከ አበው ቅዱሳን በምልጃቸው ይማረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: 🕊 [   † ጥቅምት ፳፰ [ 28 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ] ፩. አባ ይምዓታ ጻድቅ [ከተስዓቱ ቅዱሳን] ፪. ቅዱሳን መርትያኖስ ወመርቆሬዎስ [ሰማዕታት] ፫. አባታችን ያፌት [የኖኅ ልጅ] [   †  ወርኀዊ በዓላት    ] ፩. አማኑኤል ቸር አምላካችን ፪. ቅዱሳን አበው [አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ] ፫. ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ ፬. ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ ፭. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ [ሰማዕት] ፮. ቅዱስ አባዲርና ቅድስት ኢራኢ † " በጐንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው? ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኩዋ መከራን ብትቀበሉ ብጹዓን ናችሁ:: ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ: አትናወጡም:: ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስን በልባችሁ ቀድሱት:: " † [፩ዼጥ.፫፥፲፫] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖

photo content