cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Debtera Media

ደብተራ ሚዲያ የእውነት ድምጽ! ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!👇 በዩቲዩብ 👉 https://bit.ly/3bMfT8D በፌስቡክ 👉 fb.me/DebteraMedia በቴሌግራም 👉 t.me/DebteraMedia ማንኛውንም ሃሳብ አስተያየት ሆነ መረጃ በ t.me/DebteraMedia_Bot ማድረስ ትችላላችሁ።

Більше
Рекламні дописи
6 136
Підписники
-524 години
-297 днів
-12030 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

09:02
Відео недоступнеДивитись в Telegram
                       †                         🕊 † እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። † በዚሕች ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል እናቱ እግር ሥር ጠበል አፍልቋል::     🕊  †  የጠበል በዓል  †   🕊 [ ለእህታችን የተፈጸመ ድንቅ ተአምር ] በአንጀት ካንሰር በሽታ በጽኑ ታማ ለስምንት ዓመታት በጽናት እግዚአብሔርን ስትማጸን ቆይታ በሸንኮራ ቅዱስ ዮሐንስ ጸበል የተፈወሰችና ተአምር የተፈጸመላት እህታችን ታሪክ [ ክፍል - ፩ - ] † አምላከ ቅዱሳን ከደዌ ሥጋ : ከደዌ ነፍስ በምሕረቱ ይሠውረን:: ከድንግል እመቤታችን በረከትም ያሳትፈን:: †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
Показати все...
11.04 MB
07:16
Відео недоступнеДивитись в Telegram
                       †                         🕊 † እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። † በዚሕች ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል እናቱ እግር ሥር ጠበል አፍልቋል::     🕊  †  የጠበል በዓል  †   🕊 [   ለእህታችን የተፈጸመ ድንቅ ተአምር  ] በአንጀት ካንሰር በሽታ በጽኑ ታማ ለስምንት ዓመታት በጽናት እግዚአብሔርን ስትማጸን ቆይታ በሸንኮራ ቅዱስ ዮሐንስ ጸበል የተፈወሰችና ተአምር የተፈጸመላት እህታችን ታሪክ [ ክፍል - ፪ - ] † አምላከ ቅዱሳን ከደዌ ሥጋ : ከደዌ ነፍስ በምሕረቱ ይሠውረን:: ከድንግል እመቤታችን በረከትም ያሳትፈን:: †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
Показати все...
8.97 MB
Фото недоступнеДивитись в Telegram
                       †                           🕊    †   የጠበል በዓል   †     🕊 🕊 † ዳግመኛ ዕለቱ የጠበል በዓል ተብሎም ይታሠባል:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስለ ጠበል ፈዋሽነት ሁሌ ብታስተምርም በዚህ ቀን ግን ልዩ ትኩረቷ ታደርገዋለች:: እግዚአብሔር በምክንያትም አለምክንያትም መፈወስ ይችላል:: ያለ ምክንያት በቃሉና በወዳጆቹ ቃል አድሮ "ዳን" ይላል:: ወይም ደግሞ በምክንያት በእመት [እምነት] : በጠበል : ቅዱስ ቃሉን በመስማት : በመስቀሉና በመጻሕፍት በመባረክ [በመታሸት] : በቅዱሳን አካል [በልብሳቸው : በበትራቸው : በጥላቸው በአጽማቸው . . .] ይፈውሳል:: እርሱ እግዚአብሔር ነውና በወደደውና በመረጠው አድሮ ያድናል [ይፈውሳል]:: [፪ነገ.፭፥፲ (5:10) , ሐዋ.፫፥፮ (3:6) , ፭፥፲፭ (5:15) , ፲፱፥፲፩ (19:11)] † ዛሬ ግን የጠበል ፈዋሽነት በጉልህ ይነገራል:: [ዮሐ.፭፥፩ (5:1) , ፱፥፯ (9:7) ] † አምላከ ቅዱሳን ከደዌ ሥጋ : ከደዌ ነፍስ በምሕረቱ ይሠውረን:: ከድንግል እመቤታችን በረከትም ያሳትፈን:: †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
Показати все...
👍 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Фото недоступнеДивитись в Telegram
[ + እናመስግነው ፈጣሪያችንን + ] .mp34.53 MB
[ + ታድነኝ ዘንድ + ].mp39.12 MB
Фото недоступнеДивитись в Telegram
                          †                        🕊  💖        ሰ ላ ም ታ        💖  🕊ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሠሮ ለሰጣን ▸ አግዐዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም ❞ 🕊 ❝ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ። ❞ ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [  🕊  እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ !  🕊   ] †                       †                        † 💖                    🕊                     💖 ❝ እግዚኦ መኑ ከማከ ሙታነ አንሣእከ በቃልከ እግዚኦ መኑ ከሚከ ሕይወተ ወሀብከ ሰላመ ለነ ጸጎከ እግዚኦ መኑ ከማከ ንግበር በዓለ ፋሲካ ኵልነ ምስለ ጻድቃኒከ ኅቡረ ፤ ❞ ትርጉም ፦ [ ጌታ ሆይ እንዳንተ ማነው ! ? በቃልህ ሙታንን አነሣህ ፣ ጌታ ሆይ እንዳንተ ማነው ! ? ሕይወትን ሰጠህ ለኛም ሰላም አደልህ ጌታ ሆይ እንዳንተ ማን ነው ! ? የፋሲካን በዐል ከጻድቃንህ ጋር በጋራ በመሆን ሁላችን እናከብራለን። ] [ ድጓ ዘፋሲካ ] †                       †                       † 💖                    🕊                    💖
Показати все...
👍 1
🕊 [ † እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። † ] †  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † † በዓሉ ከሰላሳ ሦስቱ ዓበይት የእመቤታችን በዓላት አንዱ ሲሆን በዚሕች ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል እናቱ እግር ሥር ጠበል አፍልቋል:: †  ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ :- ድንግል ማርያም አምላክ ልጇን አዝላ ስደት ወጥታ ምድረ ግብጽ ትደርሳለች:: በወቅቱ ከደረሱባት ችግሮች አንዱ ደግሞ ረሃብና ጽሙ ነበር:: እንኳን ለስደተኛ በቤቱ ላለም ረሃብና ጥም እንዴት እንደሚከብድ የደረሰበት ያውቀዋል:: † ለዛም ነው ሊቁ በቅዳሴው :- "አዘክሪ ድንግል ረሃበ ወጽምዐ : ምንዳቤ ወኀዘነ : ወኩሎ ዐጸባ ዘበጽሐኪ ምስሌሁ" ያለው:: ታዲያ አንድ ቀን የበርሃው ፀሐይ አቃጥሏቸው ባረፉበት ድንግል እመቤታችን ውኃ ልመና ወጣች:: ብዙ ለመነች : ግን ጥርኝ እንኳ የሚሠጣት አጥታ በሐዘን ተመለሰች:: ስትመለስ ግን ይባስ ብሎ የልጇን ጫማ ሽፍቶች ወስደውት ደረሰች:: ያን ጊዜ ልጇን ታቅፋ "ውኃ ሳላገኝልሕ : ጫማሕንም አሰረቅኩብህ" ብላ ምርር ብላ አልቅሳለች:: "በከየት ወትቤ ማርያም ማዕነቅ:: እምሰብአ ሃገር አልቦ ዘየአምራ ለጽድቅ:: ሰአልክዎሙ ማየ ኢወሀሐቡኒ በሕቅ:: ወአሕጎልኩ ለወልድየ አሳእኖ ዘወርቅ::" እንዳለ ደራሲ:: ይሕንን የተመለከተ ልጇ የቆመችበትን መሬት ቢባርከው ሕይወትነት ያለው ማይ [ጠበል] ፈለቀ:: ጌታችን : እመቤታችን: ዮሴፍና ሰሎሜ ከውኃው ጠጥተዋል:: ሲሔዱ ግን ለእንግዶች ጣፋጭ [መድኃኒት] : ለአካባቢው ሰዎች ግን መራራ ሁኗል:: "ከመ ኢይስተይዋ ሰብአ ሐገር ለይእቲ ማይ አምረራ:: ወለርኁቃንሰ ፈውሰ ወጥዕምተ ገብራ::" እንዳለ መጽሐፍ:: [ሰቆቃወ ድንግል] ከመቶዎች ዓመታት በኋላም ጌታ ጠበል ያፈለቀበት : ድንግል እመቤታችን የቆመችበት ቦታ ላይ በእመ ብርሃን ስም ቤተ ክርስቲያን ታንጿል:: ቅዳሴ ቤቱም ተከብሯል:: ጠበሉም ሲባርክና ሲፈውስ ይኖራል:: † 🕊 የጠበል በዓል 🕊  † † ዳግመኛ ዕለቱ የጠበል በዓል ተብሎም ይታሠባል:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስለ ጠበል ፈዋሽነት ሁሌ ብታስተምርም በዚህ ቀን ግን ልዩ ትኩረቷ ታደርገዋለች:: እግዚአብሔር በምክንያትም አለምክንያትም መፈወስ ይችላል:: ያለ ምክንያት በቃሉና በወዳጆቹ ቃል አድሮ "ዳን" ይላል:: ወይም ደግሞ በምክንያት በእመት [እምነት] : በጠበል : ቅዱስ ቃሉን በመስማት : በመስቀሉና በመጻሕፍት በመባረክ [በመታሸት] : በቅዱሳን አካል [በልብሳቸው : በበትራቸው : በጥላቸው በአጽማቸው . . .] ይፈውሳል:: እርሱ እግዚአብሔር ነውና በወደደውና በመረጠው አድሮ ያድናል [ይፈውሳል]:: [፪ነገ.፭፥፲ (5:10) , ሐዋ.፫፥፮ (3:6) , ፭፥፲፭ (5:15) , ፲፱፥፲፩ (19:11)] † ዛሬ ግን የጠበል ፈዋሽነት በጉልህ ይነገራል:: [ዮሐ.፭፥፩ (5:1) , ፱፥፯ (9:7) ] † አምላከ ቅዱሳን ከደዌ ሥጋ : ከደዌ ነፍስ በምሕረቱ ይሠውረን:: ከድንግል እመቤታችን በረከትም ያሳትፈን:: 🕊 [ † ሰኔ ፰ [ 8 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. የእመቤታችን ድንግል ማርያም ቅዳሴ ቤት ፪. የቅዱስ ውኃ (ጠበል) መታሠቢያ ፫. ቅድስት ትምዳ እናታችን ፬. ቅዱስ አውሎጊስ ፭. አባ አትካሮን [ † ወርኀዊ በዓላት ] ፩. ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት ፪. ኪሩቤል [ አርባዕቱ እንስሳ ] ፫. አባ ብሶይ [ ቢሾይ ] ፬. አቡነ ኪሮስ ፭. አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን ፮. ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ [ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት] † " ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ:: ግርማው በእሥራኤል ላይ: ኃይሉም በደመናት ላይ ነው:: እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው:: የእሥራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን: ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል:: እግዚአብሔርም ይመስገን:: " † [መዝ. ፷፯፥፴፬] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Показати все...
👍 1
[ ስንክሳር ሰኔ - ፰ - ] .mp34.99 MB
👍 1