Debtera Media
الذهاب إلى القناة على Telegram
ደብተራ ሚዲያ የእውነት ድምጽ! ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!👇 በዩቲዩብ 👉 https://bit.ly/3bMfT8D በፌስቡክ 👉 fb.me/DebteraMedia በቴሌግራም 👉 t.me/DebteraMedia ማንኛውንም ሃሳብ አስተያየት ሆነ መረጃ በ t.me/DebteraMedia_Bot ማድረስ ትችላላችሁ።
إظهار المزيد3 516
المشتركون
-224 ساعات
-97 أيام
-5530 أيام
أرشيف المشاركات
3 516
🌸 🌸
[ በሦስትነትህ መታመን ይበልጣል ! ]
🌸 🌸
❝ ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ ፦ ከሁሉ ይልቅ በሦስትነትህ መታመን ይበልጣል፡፡ አንተን በወለደችህም በማርያም መማፀን መልካም ዕድል ነው፡፡ ❞ [ መልክአ ኢየሱስ ]
🕊
❝ ነፍሴን መለሳት ፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ። በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም ፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል። ❞ [ መዝ.፳፫፥፩-፮ ]
🌸 🌸
[ ነ ፍ ሴ ን መ ለ ሳ ት ]
💖 ድንቅ ትምህርት 💖
🕊 [ በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ] 🕊
🌸 🌸
†††
✟ 𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y ✟
🕊 💖 🕊
👇
3 516
🕊 💖 🕊
[ 🕊 መድኃኔ ዓለም 🕊 ]
🌸 🌸
† እንኳን ለጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †
🕊 💖 🕊
❝ ሰማይ ደስ ይለዋል ፣ ምድር ፍስሐን ታደርጋለች የምድር መሠረቶችም መለከትን ይነፋሉ ፣ ተራሮችና ኮረብቶችም ይነዋወጣሉ ፣ ሁሉም የበረሃ ዛፎችም [ ይነዋወጣሉ ] በሰማያትም ዛሬ እጅግ ትልቅ ደስታ ይደረጋል፣ ምድርም በክርስቶስ ደም ታጥባ ፋሲካን [ በከርስቶስ ደም በተገኘ ማዕዶት የተገኘ ደስታን ] ታደርጋለች። ] ❞ [ ድጓ ዘፋሲካ ]
🕊 💖 🕊
❝ ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም ዘያበርህ ላዕለ ጻድቃን መርአዊሃ ለቤተ ክርስቲያን ይርዳዕ ዘተኃጕለ ያስተጋብእ ዝርዋነ መጽአ ኀቤነ ፤ ❞
ትርጉም ፦ [ ወደ ዓለም የመጣው ብርሃን በጻድቃን ላይ የሚያበራ ነው ፣ የቤተ ክርስቲያን ሙሽራዋ ነው ፣ የጠፋው ይረዳ ዘንድ የተበተኑትን ይሰበስብ ዘንድ ወደ እኛ መጣ [ ሰው ሆነ ] ] [ ድጓ ዘአስተምህሮ ]
🌸 🌸
†††
✟ 𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y ✟
🕊 💖 🕊
3 516
🕊 🌺 🕊
💛 ♱ መ ድ ኃ ኔ ዓ ለ ም ♱ 💛
🌸 ♱ 🌸
❝ በባሕርዩ ሞት የሌለበት ሲሆን ስለ ሰው ሁሉ ቤዛ ሆኖ ሞተ። በባሕርዩ ሕይወት ትንሣኤ ሲሆን ሰውነቱን ለሞት አሳልፎ ሰጠ ፤ ሥጋን ተዋሕዶ በረቂቅ ሥልጣን ሞትን ድል ይነሣ ዘንድ ፤ ለሙታን የትንሣኤ ዠማሪ ከሙታንም ተለይቶ ለመነሣት መጀመሪያ ይሆን ዘንድ የሰው ባሕርይም ወዶ ዘላለም ሕይወት እንዲወጣ ይመራ ዘንድ። [ዮሐ.፲፪፥፴፪]
አሁንም ስለ ሁሉ ቤዛ ሆኖ ሞተ ፤ በሦስተኛውም ቀን ተነሣ ሲኦልን በዘበዘ ፤ የሙታን ትንሣኤ በዕሩቅ ብእሲ ብቻ የተደረገ አይደለም ፤ እኛ የእግዚአብሔር ቃል ሰው እንደሆነ የሞት ሥልጣንም በእርሱ እንደጠፋ ኋላም አንድ ልጅ ፤ አንድ ገዥ እንደ መሆኑ በእውነት ፈርዶ ዓለምን ያሳልፍ ዘንድ በአባቱ ጌትነት እርሱ እንዲመጣ እናውቃለን እንጂ እንደ ተጻፈ። ❞ [ቅዱስ ቄርሎስ]
🌸 🌸
†††
✟ 𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y ✟
🕊 💖 🕊
3 516
🕊 🌺 🕊
💛 [ መ ድ ኃ ኔ ዓ ለ ም ] 💛
🌸 ♱ 🌸
† እንኳን ለጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †
🌸 ♱ 🌸
❝ ጌታዬና መድሃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ የደረሰበትን ጉስቁልና ሊተካከል የሚችል ጉስቁልና እንደምን ያለ ነው? ቀላያት ፊቱን በተመለከቱ ጊዜ የሚንቀጠቀጡለት ፀሐይ ብርሃኗን የምትከለክልለት : ጨረቃ የምታለቅስለት : ከዋክብት የሚረግፉለት : ክፉዎች አይሁድ ተፉበት : እጃቸውን አክርረው መቱት : ከስድብ ሁሉ የከፋ ስድብ ሰደቡት::
ስድባቸው እንዲሁ የቃላት ብቻ አልነበረምና ምራቅና ቡጢም አለበት እንጂ : ይህ ብቻ አይደለም : - ክርስቶስ ሆይ በጥፊ የመታህ ማን ነው? ትንቢት ተናገርልን ¡ የሚል ስላቅም አለበትና:: ጌታዬና ንጉሴ መከራ ያልደረሰበት አካል አልነበረውም:: ጭንቅላቱ ላይ የእሾኽ አክሊል ደፉበት : ፊቱን በጥፊ መቱት ፡ ትከሻውን መስቀል አሸከሙት : እጁን በችንካር ቸነከሩት : እግሩን በምስማር ቸነከሩት : አፉን ኮምጣጤ አጠጡት : መላ አካልቱን በጅራፍ ገረፉት :: ወዮ ! እንዲህ ያለ መውደድ እንደምን ያለ ፍቅር ነው፡፡ ❞ [ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]
🌸 🌸
†††
✟ 𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y ✟
🕊 💖 🕊
3 516
የተማሩትም ብሉይ ኪዳንን ብቻ ነበር:: በጊዜውም "ክርስቶስ አልተወለደም:: ትክክለኛው እምነት ይሁዲ ነው::" እያሉ ከክርስቲያኖች ጋር ይከራከሩ ነበሩ:: አንድ ቀን ግን ከታላቁ ሊቅና ገዳማዊ አቡነ ዜና ማርቆስ ጋር ተገናኙ:: ጻድቁን ስላልቻሏቸው ተሸንፈው በክርስቶስ አመኑ:: አቡነ ዜና ማርቆስም አስተምረው ክርስትና ሲያነሷቸው [ሲያጠምቁዋቸው] "ጽጌ ድንግል" አሏቸው::
ሲመነኩሱም "ጽጌ ብርሃን" ተብለዋል:: ቀጥለውም በጾምና በጸሎት ሲጋደሉ: እመቤታችንንም ሲለምኑ ምሥጢር ተገለጠላቸው::
የእመ ብርሃንን ስዕለ አድኅኖ በአበባ ተከባ: በብርሃንም ተውጣ ተመለከቱ:: በዚህ ምክንያትም ዛሬ በጣፋጭነቱ የሚታወቀውን ማኅሌተ ጽጌን ፩ መቶ ፶ ዓርኬ አድርገው ደረሱ:: እስከ ዕለተ ዕረፍታቸውም እመቤታችንና ልጇን በገዳማቸው [ወለቃ አካባቢ የሚገኝ] ሲያመሰግኑ ኑረዋል:: በዚህች ቀንም ዐርፈዋል::
አምላከ ቅዱሳን በአማኑኤል ስሙ: በማርያም እሙ: በፈሰሰ ደሙ: በተወጋ ጐኑ: በንጹሐን ቅዱሳኑ ይማረን:: ከመስቀሉና ከቅዱሳኑ በረከትም አይለየን::
† መድኃኔ ዓለም ከወዳጆቹ ጸጋ ክብርን ያድለን::
🕊
[ † መጋቢት ፳፯ [27] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዮሐንስ [ፍቁረ እግዚእ]
፪. ቅዱሳት አንስት [ከእግረ መስቀሉ ያልተለዩ]
፫. ቅዱሳን ባልንጀሮች [በጌታ ስቅለት ጊዜ ከሞት የተነሱ]
፬. ቅዱሳን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ
፭. ታላቁ ቅዱስ መቃርስ [የመነኮሳት አለቃ]
፮. ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት [የኢትዮዽያ ንጉሥ]
፯. ቅዱስ ዕፀ መስቀል
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ
፪. ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
፫. ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
፬. ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
† " የተጠራችሁለት ለዚህ ነው:: ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሏልና:: እርሱም ኃጢአት አላደረገም:: ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም:: ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም:: መከራንም ሲቀበል አልዛተም . . . እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ::" † [፩ጴጥ. ፪፥፳፩-፳፭]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
3 516
🕊
[ † እንኳን ለጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † መድኃኔ ዓለም † 🕊
† ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ በዚሕ ዕለት ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ ፫ ሰዓት [3:00] ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት:: ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል::
ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት:: ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት:: ራሱንም በዘንግ መቱት:: እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ::
በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት:: በሠለስት [ሦስት ሰዓት ላይ] አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ ፮ ሺህ ፮ መቶ ስድሳ ፮ [6,666] ገረፉት:: ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት::
ስድስት ሰዓት ላይ በረዣዥም ብረቶች አምስት ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት:: ሰባት ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ:: ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ ሰባት ቃላትን ተናገረ::
ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በባሕርይ ሥልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ:: በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ:: አሥራ አንድ ሰዓት ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት::
በዚያች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ:: ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ:: [ማቴ.፳፯፥፩ (27:1), ማር.፲፭፥፩ (15:1), ሉቃ.፳፫፥፩ (23:1), ዮሐ.፲፱፥፩ (19:1) ]
ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት ፳፯ [ 27 ] ቀን ቢሆንም በዓሉ ወደ ጥቅምት እንዲመጣ ያደረጉት አበው ሊቃውንት ናቸው:: ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መጋቢት
፳፯ [27] የሚውለው ዓቢይ ጾም ውስጥ በመሆኑና የንግሥ በዓላት በዓቢይ ጾም ስለማይፈቀዱ ነው::
ምንም እንኩዋ በቅርብ ጊዜ በዓቢይ ጾም የሚያነግሡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም አባቶቻችን ግን እንዲህ ያለውን ሥርዓት አላቆዩልንም:: ከበሮና የቸብቸቦ ዝማሬም በወቅቱ የተፈቀደ አይደለም::
በዚህም ምክንያት የበዓለ ስቅለት ንግሡ ወደ ጥቅምት ፳፯ [27] ሲመጣ: የመጋቢት ፭ [5] ገብረ መንፈስ ቅዱስ ንግሥ ወደ ጥቅምት ፭ [5] : የመጋቢት ፲ [10] መስቀል ወደ መስከረም ፲፯ [17] መጥቶ እንዲከበር ሆኗል::
† 🕊 ቅዱስ መቃርስ ብጹዓዊ 🕊 †
በዚህ ስም የሚጠሩ ቅዱሳን ብዙ ናቸው:: "ታላቁ መቃርዮስ": "መቃርስ እስክንድርያዊ": "መቃርስ ባሕታዊ"ን እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል:: ይህኛው ቅዱስ ደግሞ "መቃርስ ኤዺስ ቆዾስ: መቃርስ ብጹዓዊ: መቃርስ ዘሃገረ ቃው" ይባላል:: ሁሉም መጠሪያዎቹ ናቸው::
ቅዱሱ የ፭ኛው መቶ ክ/ዘመን ሰው ሲሆን የቅዱስ ቄርሎስና የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ተከታይ ነው:: ከሕይወቱ ማማርና ከቅድስናው መሥመር የተነሳ አበው አመስግነውት አይይጠግቡም:: ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት "ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል" እንዳለው:: [መዝ.፺፩]
ዳግመኛ "ወይከውን ከመ ዕጽ እንተ ትክልት ኀበ ሙሐዘ ማይ" [መዝ.፩፥፫] እንዳለው ቅዱስ መቃርስ እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን አፍርቷል:: ከሁሉ አስቀድሞ በበርሃ ኗሪ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ስለ ጌታ ፍቅር እንባው እንደ ዥረት እየፈሰሰ:: ራሱን በብረት ዘንግ ይመታ ነበር::
"ቃው" በምትባል ሃገር ዻዻስ ሆኖ በተሾመ ጊዜም ተጋድሎውን አልቀነሰም:: ዻዻስ ቢሆንም የሚለብሰው የበርሃዋን ደበሎ ነው:: ከብቅዓቱ የተነሳ የሕዝቡ ኃጢአት በግንባራቸው ላይ ተጽፎ እየታየው ስለ ወገኖቹ ያለቅስ ነበረ:: በቤተ መቅደስ ውስጥ ቆሞ አንጀቱ ቅጥል እስኪል ድረስም ያለቅስ ነበር::
ሁልጊዜ ሲቀድስ ጌታችንን ከመላእክቱ ጋር ያየው ነበር:: አንድ ቀንም ጌታ ቅዱስ መቃርስን "ዻዻሱ ሆይ ሕዝቡን ገስጻቸው:: ብትገስጻቸውና ባይሰሙህ እዳው በእነርሱ ላይ ነው" አለው:: ቅዱስ መቃርስም ሕዝቡ ከኃጢአታቸው ይመለሱ ዘንድ ይመክራቸው: ይለምንላቸውም ነበር::
ከዚህ ሁሉ በሁዋላ በጉባኤ ኬልቄዶን [ጉባኤ አብዳን] ፮፻፴፮ ዻዻሳት ንጉሡን ፈርተው ሃይማኖታቸውን ሲክዱ ቅዱሳኑ ዲዮስቆሮስና መቃርስ "ተዋሐዶን አንክድም" በማለታቸው ዘበቱባቸው:: ብዙ አሰቃይተውም ወደ ጋግራ ደሴት አሳደዷቸው::
ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ጋግራ ውስጥ ሲሞት ቅዱስ መቃርስ ወደ እስክንድርያ ተመልሶ ሕዝቡን ሲመክር ያዙት:: ከመሬት ላይ ጥለውም እየደጋገሙ ኩላሊቱን ረገጡት:: ከመከራው ብዛትም በዚህች ቀን ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ:: ቅዱሱ ሙታንን ማስነሳትን ጨምሮ ብዙ ተአምራትን ሠርቷል::
አበውም ስለ ቅዱስ መቃርስ ብሎ ጌታ እንዲምራቸው እንዲህ ይጸልዩ ነበር :-
"ሰላም ሰላም ለፈያታዊ ዘቀደሶ::
ሃገረ ጽጌ የአኀዝ ምስለ ጻድቃን በተዋርሶ::
ተዘከረኒ ክርስቶስ አመ ትመጽእ ለተዋቅሶ::
በእንተ መቃርስ ጻድቅ እንተ መጠወ ነፍሶ::
ወበበትረ መስቀል ዘይዘብጥ ርዕሶ::" [አርኬ ዘጥቅምት ፳፯]
† 🕊 አቡነ መብዓ ጽዮን 🕊 †
ሃገራችን ኢትዮዽያ እጅግ በርካታ ቅዱሳንን ስታፈራ አንዳንዶቹ ደግሞ የተለዩ ናቸው:: ጻድቁ አባ መባዓ ጽዮን በ፲፭ኛው መቶ ክ ዘመን በሽዋ [ሻሞ] አካባቢ የተነሱ ጻድቅ ናቸው:: ገና ከልጅነታቸው የእመቤታችንና የጌታችን ፍቅር የሞላባቸው ነበሩ::
በ፫ ዓመታቸው ከእንግዳ የወሰዷት ስዕለ አድኅኖ ተለይታቸው አታውቅም ነበር:: በወጣትነታቸው ጊዜም ብሉያት ሐዲሳትን: ቅኔንም ጨምሮ ተምረው: ከቤተሰባቸው አስፈቅደው በምናኔ ገዳም ገቡ::
ከዚያ በሁዋላ ያለውን ገድላቸውን ማን ችሎ ይዘረዝረዋል!
በተለይ ዐርብ ዐርብ የጌታን ፲፫ ሕማማት ለማዘከር ሲቀበሉት የኖሩት መከራ እጅግ ብዙ ነው:: ድንጋይ ተሸክመው እንባና ላበታቸው እየተንጠፈጠፈ ይሰግዳሉ:: በድንጋይ ደረትና ጀርባቸውን ይደቃሉ:: ራሳቸውን ይገርፋሉ:: በዋንጫ ሐሞት [ኮሶ] ሞልተው ይጠጣሉ::
ከዚህ ሁሉ በሁዋላ ወር በገባ በ፳፯ ስለ መድኃኔ ዓለም ጠላ ጠምቀው: ንፍሮ ነክረው ወደ ገበያ ይወጡና ይዘክሩ ነበር:: ከዝክሩ የነካ ሁሉ ይፈወስ ነበር:: ከእንባ ብዛት ዓይናቸው ቢጠፋ ድንግል ማርያም መጥታ ብርሃናዊ ዓይንን ሰጠቻቸው:: ስለዚህም "ተክለ ማርያም [በትረ ማርያም]" ይባላሉ::
ጌታችንም ስለ ፍቅራቸው በአምሳለ ሕጻን ይገለጽላቸው: እርሳቸውም አቅፈው ይስሙት ነበር:: ጻድቁ ተናግረን የማንጨርሰውን ተጋድሎ ተጋድለው ጌታ በዚህ ቀን ነፍሳትን ከሲዖል እንዲያወጡበት ስልጣንን ሰጣቸው:: አባታችን ቅዱሱና ጻድቁ መብዓ ጽዮን ከብዙ ትሩፋት በሁዋላ ዐርፈዋል::
† 🕊 አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ 🕊 †
ጻድቁ አቡነ ጽጌ ድንግል በ፲፬ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበሩ ሊቅና ገዳማዊ ናቸው:: የዘር ሐረጋቸው ምንም ከቤተ እሥራኤል እንደሚመዘዝ ቢታወቅም ኢትዮዽያዊ ናቸው:: አስቀድመው አይሁዳዊ በመሆናቸው ኢየሱስ ክርስቶስንና ድንግል እናቱን አያምኑም ነበር::
3 516
🕊 🌺 🕊
💛 [ ♱ መ ድ ኃ ኔ ዓ ለ ም ♱ ] 💛
🌸 ♱ 🌸
❝ ለቤተ ክርስቲያን ስትል በአደባባይ በጥፊ የተመታህ ፤ አቤቱ ይህን ማድረግህ እርስዋን በከበረ ደምህ ትቀድሳት ዘንድ ነው፡፡
ለእርስዋ ሲል ታሥሮ መጎተት የቻለ የበደለውም በደል ሳይኖር ፣ ርኩስ ምራቅ ሲተፋበት የታገሠ መድኃኔ ዓለም በእንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ።❞ [ ቅዱስ ቄርሎስ ]
🩵 † 🩵
🕊 ድምጽህንም ሰምቶ ሞት ጠፋ 🕊
❝ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ፣ በመስቀል ላይ የሞትህ ፣ በሞትህም ሞት ድል የተነሣ ፣ አንተ እንደ አባትህ ሕያው ስትሆን በሥጋ ሞትን የምትቀበል ሆነሃልና። ሞትን የምታጠፋው አንተ ነህና ፣ አንተስ መቼም መች አንተ ነህ ፣ አንተም የሕይወት አካል ነህ።
ለሞት ተሳብክ በአንተም ሞት ሞተ [ ጠፋ ] ፣ ሕይወትነትህንም በአሳወቅኸው ጊዜ አይቶህ ሞት ጠፋ ፣ ድምጽህንም ሰምቶ ሞት ጠፋ። ሙታን ባወቁህ ጊዜ ዳኑ፣ ሕያው የሆንህ አንተ የሞትን ልብስ ለብሰህ ሙታን ወዳሉበት ወርደሃልና ፤ ነፍስህ የሕይወትን መዓዛ እፍ ባለችባቸው ጊዜ ዳኑ። ❞ [ ግብረ ሕማማት ]
🌸 🌸
†††
✟ 𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y ✟
🕊 💖 🕊
