uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ

Відкрити в Telegram

Every one comment us about the informations that we are uploading. you are also very wellcommed to give us nominations which helps us to improve our capability with regard to the concerns of the organization.

Показати більше
1 579
Підписники
+124 години
+57 днів
+2430 днів
Архів дописів
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በአረንጓዴ አሻራ የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብና ለፅድቀት የማብቃት ንቅናቄ ተጀመረ። ***** ጥቅምት 7/2019 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብና ለፅድቀት የማብቃት ሥራ በይፋ ተጀምሯል። የዚሁ ንቅናቄ አካል በሆነው መርሐ- ግብር በክፍለ ከተማው በሚገኘው ግዙፉ የኢሬቻ ፓርክ ውስጥ የተተከሉ ከአንድ ሺሕ በላይ የጥላ፣ የውበትና የፍራፍሬ ችግኞች የእንክብካቤ ሥራ ተከናውኗል። በተጠናቀቀው የክረምት ወቅት በክፍለ ከተማው ደረጃ ከ248 ሺሕ በላይ የተለያዩ የውበት፣ የጥላና የፍራፍሬ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን እነዚህን ሀብቶች ተንከባክቦ የማሳደጉ ሥራ በአሥሩም ወረዳዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል። ችግኝ መትከል የመጀመሪያው ምዕራፍ እንጂ የመጨረሻው ግብ ባለመሆኑ የተተከሉት ችግኞች ተንከባካቢና ጠባቂ አግኝተው ለፅድቀት እንዲበቁ ማድረግ የተጀመረውን ዘላቂ የአካባቢ ጥበቃና የከተማ ውበት ለማረጋገጥ ወሳኝ ድርሻ እንዳለው ተመላክቷል። ችግኞችን በወቅቱ ማረም፣ ኮትኩቶ ውሃ ማጠጣትና መንከባከብና መጠበቅ የፅድቀት መጠናቸውን ከፍ ለማድረግ መሰረታዊ ጉዳይ ነው። ልክ እንደ ህፃናት ልዩ ፍቅርና ክትትል የሚሹትን እነዚህን ችግኞች በጥንቃቄ ማሳደግ የከተማዋን የአየር ንብረት ለማስተካከል፣ የአፈር መሸርሸርን ለመከላከልና ንጹሕ የመኖሪያ አካባቢን ለመፍጠር እንደሚያስችል በመገንዘብ በተለይም የፍራፍሬ ችግኞችን ለፍሬ ማብቃት ለምግብ ዋስትና እና ለኢኮኖሚ ጥሪት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው በመሆኑ የእንክብካቤ ሥራው የረጅም ጊዜ ዘላቂ ጥቅም የሚያረጋግጥ ተግባር እንደሆነ ተገልጿል። በዚህ የእንክብካቤ ማስጀመመያ መርሐ -ግብር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ዘይዳ ሻሚል፣ የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሮ መዓዛ መንግሥቱ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አርቲስቶች፣ ኮሜዲያኖች፣ ወጣቶች፣ ሴቶችና በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች በመርሀ-ግብሩ ተገኝተዋል።

የመማክርት ጉባኤው በከተማው በሚከናወኑ የአረንጓዴ መሠረተ ልማት ስራዎች ትልቅ አጋዥ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ የሚያከናውናቸውን የልማት ስራዎችና የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች
የመማክርት ጉባኤው በከተማው በሚከናወኑ የአረንጓዴ መሠረተ ልማት ስራዎች ትልቅ አጋዥ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ የሚያከናውናቸውን የልማት ስራዎችና የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ይበልጥ ለማሳለጥ፣ በቢሮውና በህዝቡ መካከል እንደ ድልድይ ሆኖ እንዲያገለግል የተቋቋመው መማክርት ጉባኤ ለቢሮው ውጤታማነት ትልቅ አጋዥ እየሆነ መምጣቱ ተገልጿል። ይህ የተገለጸው መማክርት ጉባኤው ባለፉት ሶስት ወራት ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት የሪፖርት አፈጻጸም ባቀረበበት መድረክ ላይ ነው። በዚህ የግምገማ መድረክ ላይ የቢሮውና የዘርፉ የክፍለ ከተማ አመራሮች እንዲሁም የአረንጓዴ አምባሳደሮች ተገኝተዋል። በወቅቱ የሪፖርት ማጠቃለያውን ያቀረቡት የመማክርት ጉባኤው ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ፀሐይ እንደገለጹት፤ ጉባኤው ባለፉት ሶስት ወራት ስራዎችን በስርአት ለመምራት የሚያስችል የአሰራር ማኑዋል አዘጋጅቷል። ከዚህም በተጨማሪ ልዩ ትኩረት የሚሹ የአረንጓዴ መሰረተ ልማቶችን የመለየት፣ በመስክ ጉብኝት ተግባራዊ ግንዛቤዎችን የማግኘት እንዲሁም የአመራርና የተቋማት የውይይት መድረኮችን የመፍጠር አመርቂ ተግባራት መከናወናቸውን አመላክተዋል። ሰብሳቢው አክለውም በተደረጉት የመስክ ምልከታዎች ወቅት የተስተዋሉና ሊስተካከሉ የሚገቡ ክፍተቶችን የጠቆሙ ሲሆን፣ በቀጣይ ትኩረት ሊደረግባቸው በሚገቡ ዘርፎች ላይ ለቢሮው ስራ ስኬት ግብዓት የሚሆኑ ጠቃሚ ምክረ ሃሳቦችን በዝርዝር አቅርበዋል። በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ዚያዳ ሻሚል ባስተላለፉት መልዕክት፤ መማክርት ጉባኤው ለቢሮው የልማት እንቅስቃሴ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን አምነውበታል። በቀጣይም ለጉባኤው የሚጠበቀው አስፈላጊው ድጋፍ ሁሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ይበልጥ ውጤታማ የሆነ የጋራ ስራ እንደሚሰራም አስገንዝበዋል።

የአረንጓዴ መሰረተ ልማትን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተቀናጀ አሰራርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ፡፡ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ከተለያዩ ባለድርሻና ተጠሪ ተቋማት ጋር  የሩብ ዓመቱን ዕቅድ አፈፃፀም ገመገመ። የአረንጓዴ ልማት አምባሳደሮች፣ የዘርፉ የክ/ከተማ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች የተለያዩ ከከተማ አስተዳደሩ የተዉጣጡ ባለድርሻ ተቋማት እንዲሁም የቢሮውን የመማክርት ጉባኤ  በዕቅድ አፈፃፀሙ መድረክ ላይ ተሳትፈዋል። በግምገማ መድረኩ ላይ በመዲናዋ እየተከናወኑ ያሉ የአረንጓዴ መሰረተ ልማቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፉና የከተማዋን ገጽታ እየቀየሩ መምጣታቸው ተገልጿል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ህብረተሰቡ በልማቱ ላይ ያለው አመለካከትና ተሳትፎ እያደገ መምጣቱ ተመላክቷል። የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዚያዳ ሻሚል በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ የከተማዋን የአረንጓዴ መሰረተ ልማት ቀጣይነት ለማረጋገጥ የቅንጅት ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል። የአረንጓዴ አምባሳደሮችም የከተማዋን የአረንጓዴ መሰረተ ልማቶች ከቢሮው ጋር በተቀናጀ መልኩ ለማልማትና ቀጣይነቱን በባለቤትነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩም ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የመድረኩ አካል የነበሩት የአረንጓዴ አምባሳደሮች በበኩላቸው፤ የከተማዋን አረንጓዴ መሰረተ ልማት ለማስፋፋትም ሆነ ለማስቀጠል ሁልጊዜም ቢሆን ከቢሮው ጎን መሆናቸውን በድጋሚ አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል በግምገማው ወቅት በዘላቂ ማረፊያ ቦታዎች ላይ ጥሩ ስራዎች መሰራታቸው የተጠቀሰ ቢሆንም፣ በስራዎቹ ላይ ወጥነትና እጥረት መኖሩ እንደ ክፍተት ተነስቷል። በተጨማሪም የንፅህና መጠበቂያ ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥ፣ በአረንጓዴ ቦታዎች ላይ የሚስተዋለው ወረራ፣ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ አወጣጥ መዘግየት እንዲሁም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ የመስራት ውስንነቶች በዋናነት የተስተዋሉ ክፍተቶች ተደርገው በዝርዝር ቀርበዋል። በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ከተሳታፊዎች ለቀረቡ ገንቢ ምክረ ሃሳቦችና ጥያቄዎች፤ የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ዚያዳ ሻሚል፣ የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ዳይሬክተር ኢንጂነር ጉተማ ሞረዳ እና የቢሮው መማክርት ጉባኤ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ፀሐይ ሰፊ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። ወ/ሮ ዚያዳ ሻሚል በቀረበው ሪፖርትና በውይይቱ ወቅት እንደ ክፍተት የተነሱትን ጉዳዮች በልዩ ትኩረት በመያዝ፣ በቀጥታ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት ፈጣን እልባት እንደሚሰጠው አስረግጠው ተናግረዋል።

የአረንጓዴ መሰረተ ልማትን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተቀናጀ አሰራርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ፡፡ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ከተለያዩ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር የሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ገምግሟል። የአዲስ አበባ አረንጓዴ ልማት አምባሳደሮች፣ የዘርፉ የክፍለ ከተማ ፅ/ቤት ኃላፊዎችና የተለያዩ የከተማ አስተዳደሩ ባለድርሻ ተቋማት እንዲሁም የቢሮውን የመማክርት ጉባኤ የተቋሙን ሩብ ዓመ ዕቅድ አፈፃፀም በጋራ ገምግመዋል። በግምገማ መድረኩ ላይ በመዲናዋ እየተከናወኑ ያሉ የአረንጓዴ መሰረተ ልማቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፉና የከተማዋን ገጽታ እየቀየሩ መምጣታቸው ተገልጿል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ህብረተሰቡ በልማቱ ላይ ያለው አመለካከትና ተሳትፎ እያደገ መምጣቱ ተመላክቷል። የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዚያዳ ሻሚል በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ የከተማዋን የአረንጓዴ መሰረተ ልማት ቀጣይነት ለማረጋገጥ የቅንጅት ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል። የአረንጓዴ አምባሳደሮችም የከተማዋን የአረንጓዴ መሰረተ ልማቶች ከቢሮው ጋር በተቀናጀ መልኩ ለማልማትና ቀጣይነቱን በባለቤትነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩም ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የመድረኩ አካል የነበሩት የአረንጓዴ አምባሳደሮች በበኩላቸው፤ የከተማዋን አረንጓዴ መሰረተ ልማት ለማስፋፋትም ሆነ ለማስቀጠል ሁልጊዜም ቢሆን ከቢሮው ጎን መሆናቸውን በድጋሚ አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል በግምገማው ወቅት በዘላቂ ማረፊያ ቦታዎች ላይ ጥሩ ስራዎች መሰራታቸው የተጠቀሰ ቢሆንም፣ በስራዎቹ ላይ ወጥነትና እጥረት መኖሩ እንደ ክፍተት ተነስቷል። በተጨማሪም የንፅህና መጠበቂያ ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥ፣ በአረንጓዴ ቦታዎች ላይ የሚስተዋለው ወረራ፣ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ አወጣጥ መዘግየት እንዲሁም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ የመስራት ውስንነቶች በዋናነት የተስተዋሉ ክፍተቶች ተደርገው በዝርዝር ቀርበዋል። በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ከተሳታፊዎች ለቀረቡ ገንቢ ምክረ ሃሳቦችና ጥያቄዎች፤ የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ዚያዳ ሻሚል፣ የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ዳይሬክተር ኢንጂነር ጉተማ ሞረዳ እና የቢሮው መማክርት ጉባኤ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ፀሐይ ሰፊ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። ወ/ሮ ዚያዳ ሻሚል በቀረበው ሪፖርትና በውይይቱ ወቅት እንደ ክፍተት የተነሱትን ጉዳዮች በልዩ ትኩረት በመያዝ፣ በቀጥታ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት ፈጣን እልባት እንደሚሰጠው አስረግጠው ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ የተገነቡ ዘመናዊ የንፅህና መጠበቂያ ቤቶች የከተማዋን ውበትና ንፅህና እያሻሻሉ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ በመዲናዋ ልዩ ልዩ መዳረሻዎች የገነባቸ
በአዲስ አበባ የተገነቡ ዘመናዊ የንፅህና መጠበቂያ ቤቶች የከተማዋን ውበትና ንፅህና እያሻሻሉ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ በመዲናዋ ልዩ ልዩ መዳረሻዎች የገነባቸው ዘመናዊ የንፅህና መጠበቂያ ቤቶች ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ተከትሎ የከተማዋ ንፅህና ከጊዜ ወደ ጊዜ ተጨባጭና ከፍተኛ መሻሻል እያሳየ መምጣቱ ተገልጿል። የተቀናጀ ዘላቂ ማረፊያ ልማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አጃኢብ ኩምሳ እንደገለጹት በአሁኑ ጊዜ በመዲናዋ ከ400 በላይ የንፅህና መጠበቂያ ቤቶች ተገንብተው አገልግሎት መስጠት ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ማዕከላት በቀንም ሆነ በምሽት ክፍት ሆነው ተደራሽ አገልግሎት የሚሰጡ በመሆናቸው ህብረተሰቡ ባልተገቡ ቦታዎች ከመጸዳዳት ተቆጥቦ እነዚህን ዘመናዊ አማራጮች የመጠቀም አዎንታዊ የአመለካከት ለውጥ እያሳየ ይገኛል። ከእነዚህ መደበኛ የንፅህና መጠበቂያ ቤቶች በተጨማሪ ከዚህ ቀደም የአደባባይ በዓላት ሲከበሩ ይፈጠር የነበረውን የመጸዳጃ ቤት እጥረት በዘላቂነት ለመቅረፍ አዳዲስና ፈጠራ የታከለባቸው አሰራሮች ተዘርግተዋል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ ተንቀሳቃሽ የንፅህና መጠበቂያ ቤቶች ተሰርተው በዋና ዋና አደባባዮች ላይ እንዲቀመጡና አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል። በዚህም መሰረት በቅርቡ በተከበሩት የአደባባይ በዓላት ላይ 64 የሚሆኑ ተንቀሳቃሽ መጸዳጃ ቤቶች ቀርበዉ ለበዓላቱ ታዳሚዎች በቂና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠታቸዉን አቶ አጃኢብ አክለው ገልጸዋል። የንፅህና መጠበቂያ ቤቶችን በአግባቡና በስልጣኔ አግባብ መጠቀም ተገቢ መሆኑን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ ህብረተሰቡ እነዚህን የንፅህና መጠበቂያ ቤቶች ለመፀዳጃነት በመጠቀም ለመዲናዋ ንፅህናና ውበት መጠበቅ የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የቆሸሸ ዉሃን መልሶ በማጣራት የመዲናዋን የአረንጓዴ መሰረተ ልማት ዉሃ ፍጆታ ሙሉ በሙሉ መሸፈን መቻሉ ተገለጸ፡፡ በዋና ከተማዋ የተገነቡና በመልማት ላይ ያሉ የአረንጓዴ መሰረተ ልማቶች እየገባ ያለው
+1
የቆሸሸ ዉሃን መልሶ በማጣራት የመዲናዋን የአረንጓዴ መሰረተ ልማት ዉሃ ፍጆታ ሙሉ በሙሉ መሸፈን መቻሉ ተገለጸ፡፡ በዋና ከተማዋ የተገነቡና በመልማት ላይ ያሉ የአረንጓዴ መሰረተ ልማቶች እየገባ ያለውን የበጋ ወቅት ተከትሎ ሊከሰት የሚችለውን ደረቅ አየር መቋቋም እንዲችሉ፣ አስተማማኝና በቂ የውሃ አቅርቦት ዝግጅት መደረጉ ታውቋል። ለእነዚህ የልማት ስራዎች የሚሆን የውሃ አቅርቦትን በበቂ ሁኔታ ተደራሽ ለማድረግ በትሪትመንት (የውሃ ማጣሪያ) ቦታዎችና በተለያዩ የከተማዋ መዳረሻዎች የውሃ አቅርቦትን የማስፋት ስራ በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል። ይህ የማስፋፊያ ስራ መልክዓ-ምድራዊ ስርጭቱን ተደራሽ በማድረግ እፅዋቱና መናፈሻዎቹ በደረቁ ወቅት እንዳይጠወልጉ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል። በተጨማሪም በወንዞች አካባቢ የሚገኙ የአረንጓዴ መሰረተ ልማቶችን በዘላቂነት ለመንከባከብ አዲስ አሰራር ተዘርግቷል። የወንዝ ውሃን በፓምፕ ቴክኖሎጂ በመጠቀም አካባቢዎቹን በበቂ ሁኔታ ማጠጣት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፈጠሩ የተገለጸ ሲሆን ይህም የከተማዋን ውበትና የአረንጓዴነት ጉዞ በበጋው ወቅትም ሳይስተጓጎል ለማስቀጠል እንደሚያስችል ተመልክቷል።

የችግኝ እንክብካቤ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ተካሄደ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተተከሉ ችግኞችን በአግባቡ በመንከባከብ ለዘላቂ የአረንጓዴ ልማት እና ለአካባቢ ጥበቃ እውን መሆን
+9
የችግኝ እንክብካቤ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ተካሄደ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተተከሉ ችግኞችን በአግባቡ በመንከባከብ ለዘላቂ የአረንጓዴ ልማት እና ለአካባቢ ጥበቃ እውን መሆን የሚያበረክተውን ሚና ለማጠናከር የችግኝ እንክብካቤ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ። በመርሐ ግብሩ ላይ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን የተተከሉ ችግኞችን በየጊዜው በመንከባከብ እስኪጸድቁና ለውጤት እስኪበቁ ድረስ ተገቢውን ክትትል ማድረግ የሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነት መሆኑን ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ፀሐይ ጌታሁን በበኩላቸው የከተማዋን ውበት ለማስጠበቅ፣ አረንጓዴ አካባቢን ለማስፋፋትና ለቀጣይ ትውልድ ምቹ የአካባቢ ሁኔታን ለማስረከብ የችግኝ እንክብካቤ ሥራው በትኩረት መከናወን እንዳለበት አሳስበዋል።

በቀጣይ ክፍተት በታየባቸዉ አፈፃፀሞች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ያስፈልጋል፡፡ ወ/ሮ ዚያዳ ሻሚል የከተማ ዉበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ ቢሮዉ የሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ገመገመ፡፡ የከተማ ዉበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ የ2019 ዓ.ም ሩብ ዓመት አበይት ተግባራትን መሰረት ባደረገ መልኩ የቢሮዉ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት ዕቅድ አፈፃፀሙን ገምግሟል፡፡ በሩብ ዓመቱ አበረታች ክነዉን ከታየባቸዉ መካከል የኢንሼቲቭ ስራዎች፤የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ስራዎች፤የእንክብካቤ ስራዎች፤የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር፤የቀዳማይ ልጅነት፤የዉበት ስራዎች፤የህብረተሰብና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ይገኙበታል፡፡ በሌላ በኩል ከይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ማዉጣት ፤ከአረንጓዴ ቦታዎች ወረራ፤ ከዘላቂ ማረፊያ ልማት፤ከወንዝ ዳርቻ ልማት፤ከአረንጓዴ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ ጋር ተያይዞ ያሉ ጉዳዮች በልዩ ሁኔታ ሊሰራባቸዉ እንደሚገባ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡ ሁሉም ሰራተኛ የቢሮዉ አምባሳደር  እንደሆነ የገለፁት የቢሮዉ ኃላፊዋ  ወ/ሮ ዚያዳ ሻሚል የአረንጓዴ መሰረተ ልማት ላይ የሚደርሰዉን ማንኛዉንም ጉዳት የመከላከል፤የመጠበቅና የማሳወቅ ሃላፊነት አለበት ያሉ ሲሆን በቀጣይ ዝቅተኛ አፈፃፀም የታየባቸዉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተደርጎ መሰራት እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡ የቢሮዉ ም/ኃላፊ  ወ/ሮ ፀሐይ ጌታሁን በበኩላቸዉ ትልቁ ስራችን እንክብካቤ እና የችግኝ ዝግጅት ነዉ ያሉ ሲሆን ዘርፉ በቀጥታ የሚመለከታቸዉ የስራ ክፍሎች በልዩ ትኩረት እንዲሰሩበት ጥብቅ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡