cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

Більше
Рекламні дописи
14 104
Підписники
+3424 години
+437 днів
+8230 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

በአንድ ቀን ፆም የአመት ወንጀል… ——— የዓሹራ ቀን ፆም ትሩፋት! ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- قال النبي صلى الله عليه وسلم: "صِيَامُ يَوْمِ عَرَفَةَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ وَالسَّنَةَ الَّتِي بَعْدَهُ وَصِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ " رواه مسلم “የዐረፋ ቀን ፆም ከፊቱ ያለውን (አንድ) አመት እና ከኋላው ያለውን (አንድ) አመት ወንጀል ያስምራል (ያሰርዛል) ብዬ በአላህ ላይ እገምታለሁ። #የዓሹራ_ፆም_ከፊቱ_የነበረችውን_አመት_ወንጀል_ያስምራል (ያሰርዛል) ብዬ በአላህ ላይ እገምታለሁ።” ሙስሊም 1162 ዘግበውታል። عن أبي قتادة رضي الله عنه – في صفة صوم النبي صلى الله عليه وسلم وهو حديث طويل – قال : وسئل عن صوم يوم عاشوراء فقال : " يكفر السنة الماضية " أخرجه مسلم , والترمذي , وابن ماجه አቢ ቀታዳ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ስለ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ፆም ሁኔታ በረጅም ሀዲስ የሚከተለውን ብሏል:- ነቢዩ ﷺ ስለ ዓሹራ ፆም ተጠይቀው ሲመልሱ “ያለፈውን አንድ አመት ወንጀል ያስምራል (ያሰርዛል)።” ብለዋል። [ሙስሊም፣ ትርሚዚይ፣ እና ኢብን ማጃ ዘግበውታል።] ይህ አላህ ለኛ የዋለው ትልቅ ውለታ ነው!። በአንድ ቀን ፆም ምክንያት የአመት ትናንሽ ወንጀሎች ይሰረዛሉ። በመሆኑ በአላህ ፈቃድ ይህን ፆም የወፈቀው ሰው 9ኛውን ቀን ሰኞ ሙሀረም 9/1446 ዓ.ሂ: እንዲሁም በኢትዮ ሐምሌ 8/2016: በፈረንጆች ደግሞ ጁለይ 15/2024 ስለሆነ ሰኞን ፆሞ ማክሰኞን 10ኛውን ቀን ለመፆም እንዲዘጋጅ ሁላችንም በተቻለን መጠን እናነቃቃ፣ (እናስተውስ)። በመልካም ነገር ላይ በማስታወስ ተጨማሪ አጅር ከአላህ ዘንድ ለማግኘት መሽቀዳደም ነው። ✍🏻ኢብን ሽፋ: ሙሀረም 8/1446 ዓ. ሂ #Join ⤵️ የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
Показати все...
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

የዓሹራ ቀን አጿጿም እና በዕለቱ የሚከሰቱ ቢድዓዎች ————— እንደሚታወቀው የዓሹራ ቀን ፆም ማለትም ሙሀረም 10ኛውን ቀን መፆም ከታላላቅ ሶናዎች ነው። ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- (أَفْضَلُ الصِّيَامِ بَعْدَ رَمَضَانَ شَهْرُ اللَّهِ الْمُحَرَّمُ) رواه مسلم “ከረመዷን በኋላ በላጩ ፆም የሙሀረም ወር ፆም ነው።” [ሙስሊም 1163 ዘግበውታል።] ይህ ፆም የረመዷን ወር ከመደንገጉ በፊት ግዴታ ነበርም ተብሏል። የሚፆምበትን ምክንያት:- በመሰረቱ እንደ ሙስሊም ማንኛውም በቁርኣን እና በሶሂህ ሀዲስ የመጣን መልካም ስራ፣ ትእዛዝም ይሁን ክልከላ ምክንያቱን አወቅነውም አላወቅነውም መተግበርና መቀበል ግዴታችን ነው። በግልፅ ማስረጃ የመጣ ነገር እስከሆነ ድረስ መተግበር ነው። የዓሹራ ፆም ምክንያት አለው። በሚከተለው ሀዲስም ተብራርቷል:- عن ابن عباس ((قَدِمَ النَّبِيُّ -صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ- المَدِينَةَ فَرَأَى الْيَهُودَ تَصُومُ يَوْمَ عَاشُورَاءَ فَقَالَ مَا هَذَا؟ قَالُوا: هَذَا يَوْمٌ صَالِحٌ، هَذَا يَوْمٌ نَجَّى اللَّهُ بَنِي إِسْرَائِيلَ مِنْ عَدُوِّهِمْ فَصَامَهُ مُوسَى، قَالَ فَأَنَا أَحَقُّ بِمُوسَى مِنْكُمْ فَصَامَهُ وَأَمَرَ بِصِيَامِهِ)).  في صحيح البخاري ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ:- “ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደ መዲና በገቡ ጊዜ አይሁዶች የዓሹራን ቀን (ሙሀረም 10ኛውን ቀን) ሲፆሙ አዩዋቸው፣ ነቢዩም ለአይሁዶች ይህ ምትፆሙት ምንድነው? አሉዋቸው፣ ይህ ምርጥ ቀን ነው፣ ይህ ቀን አላህ በኒ ኢስራኢሎችን ከጠላታቸው የገላገለበት ቀን ነው፣ ሙሳ ፆሞታል። አሉ፣ ነቢዩም እኔ ለሙሳ ከናንተ የበለጠ የቀረብኩኝ ነኝ ብለው ፆሙት፣ እንዲፆምም አዘዙ።” [ቡኻሪ ዘግበውታል።] አጿጿሙን በተመለከተ:- ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- (( لَئِنْ بَقِيتُ إِلَى قَابِلٍ لَأَصُومَنَّ التَّاسِعَ )) ، أخرجه مسلم “ወደፊት ከቆየሁ ዘጠነኛውንም (ቀን) እፆማለሁ።” [ሙስሊም ዘግበውታል።] በዚህ መሰረት ዘጠነኛውንና አስረኛውን ቀን እንፆማለን ማለት ነው። ይህም ከምንም አይነት ጭቅጭቅ ነፃ የሆነው አጿጿም ነው። 10ኛው እና 11ኛው??? ዘጠነኛው ቀን ያመለጠው 10ኛውን እና 11ኛውን መፆሙን በተመለከተ ግን የተወሰኑ ጭቅጭቆች አሉበት። እንደ ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) ያሉ ሊቃውንቶች 10 እና 11 መፆም ይቻላል ሲሉ የሚከተለውን ሀዲስ ማስረጃ ያደርጋሉ:- (صُومُوا يَوْمَ عَاشُورَاءَ ، وَخَالِفُوا فِيهِ الْيَهُودَ ، صُومُوا قَبْلَهُ يَوْمًا أَوْ بَعْدَهُ يَوْمًا). رواه أحمد في مسنده “የዓሹራን ቀን ፁሙ፣ አይሁዶችን በመቃራንም ከፊቱ ወይም ከኋላው አንድ ቀን ፁሙ።” ኢማሙ አሕመድ በሙስነዳቸው የዘገቡት ሲሆን አልባኒን ጨምሮ ሌሎችም በርካታ ዓሊሞች ዷዒፍ ነው ብለውታል። የዚህን ሀዲስ ዷዒፍነት ያመኑ ዑለማዎች ሆነው ዘጠነኛው ቀን ያመለጠው ሰው 11ኛውን ለመፆሙ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) "በሚቀጥለው ካደረሰኝ 9ኛውን እፆማለሁ።” ማለታቸው፣ ምክንያቱ ለ11ኛው ቀንም ይሆናል። ይላሉ፣ 9ኛውን ቀን እፆም ነበር ያሉበት ምክንያቱ አይሁዶችን ለመቃረን ነውና። 9ኛውን እና 10ኛውን ቀን ብቻ መፆም ነው፣ 9ኛው ካመለጠ ደግሞ 10ኛውን ብቻ መፆም ነው እንጂ 11ኛው የለም የሚሉት ደግሞ፣ "9ኛውን ቀን እፆም ነበር" ያሉበት ምክንያት አይሁዶችን ለመቃረን ቢሆንም  11ኛውን ለመፆም ማስረጃ አይሆንም ብለዋል። 1ኛ, ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በወቅቱ 10ኛውን ፆመው ነው ያቆሙት እንጂ 11ኛውን አልፆሙም። 2ኛ, በሚቀጥለው ካደረሰኝ 9ኛውን ወይም 11ኛውን እፆማለሁ ሳይሆን ያሉት 9ኛውን ብቻ ነው ከ10ኛው ጨምረው እንደሚፆሙት የተናገሩት። በነዚህ ምክንያቶች አንድ ሰው 9ኛው ካመለጠው 10ኛውን ብቻ ነው የሚፆመው ይላሉ። እንደ ማስረጃው አመዛኝነት ግን ከጭቅጭቁ ለመውጣትም በተቻለ መጠን 9ኛው እንዳያመልጥ ጥረት አድርጎ 9 እና 10 መፆም፣ 9ኛው ካመለጠ ግን ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ንም 9ኛው አምልጧቸው 10ኛውን ብቻ ስለ ፆሙ 10ኛውን ብቻ መፆም ነው። ወላሁ አዕለም!! የዓሹራ ቀን ቢድዓዎች። ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:- “መኳኳልን እና መጋጌጥን፣ በቀኑ ለየት ያለ ሶላትን መስገድም ሆነ ሌሎች ለየት ያሉ ተግባሮችን በላጭነት አስመልክተው የመጡ ሀዲሶች በጠቅላላ ዷዒፍ ናቸው። የዚያን ቀን ከመፆም ውጭ ሌሎችን ነገሮች የሚጠቁም አንድም ትክክለኛ ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የተረጋገጠ ሀዲስ የለም። "የዓሹራ ቀን ባለው አቅም ሰፋ አድርጎ ያመቻቸ ሰው፣ የሌሎችንም አመታት አላህ ሰፋ ያድርግለት።” የሚለው ሀዲስ ኢማሙ አሕመድ ሶሂህ አይደለም ብለውታል። የዚያን ቀን እለቱን አስመልክቶ መኳኳል፣ መቀባባት፣ ሽቶ መጠቀም፣ ውሸታሞች ያስቀመጡትና ሌላውም ተቀብሏቸው ከሀዘን ወደ ደስታ የሽግግር ቀን ብለው መጋጌጫ አድርገው የያዙት ነው። ይህን ያደረጉት ሙብተዲዕና ከአህሉ ሱንና ያፈነገጡ ጭፍሮች ናቸው። አህሉ ሱንናዎች ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ያዘዙበትን የሚፈፅሙና ሸይጧን ያዘዘበትን ቢድዐ የሚጠነቀቁ (የሚርቁ) ናቸው።” [አልመናር አልሙነይፍ ፊ ሶሂሂ ወዷዒፍ 89] የሳዑዲ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴም "ይህን ቀን በመጋጌጥም ሆነ በምግብ ለየት ማድረግ አይፈቀድም። እንዲሁም ሺዓዎች እንደሚያደርጉትም የሀዘን ቀን አድርጎ ራስን በስለት መሰል ነገር መጉዳት አይፈቀድም። በዚያን ቀንም ሆነ በሌሎች ቀኖች ፋጢማን መለመን አይፈቀድም፣ በተውበት እንጂ አላህ ከማይምረው ከትልቁ ሺርክም ነው። ” ብሏል። [ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ ቁ. 22177] ሸይኽ ረቢዕ ቢን ሃዲ ዑመይር አልመድኸሊ (ሀፊዘሁላህ) በዚያ ቀን ለዕለቱ ብሎ ለየት ያለ ምግብ አዘጋጅቶ መብላት ይፈቀዳል ወይ? ተብለው ተጠይቀው፣ ሲመልሱ:- "በዓሹራ ለየት ያለ ነገር መዘጋጀት አለበት፣ ወደ አላህ ያቃርባል የሚል እምነት ኖሯቸው ከሆነ የሰሩት ይህ ቢድዓ ነው። ባረከላሁ ፊኩም።” ብለዋል። በሀገራችን በዚህ ቀን የተለያዩ ቢድዐዎች በተለይ ሱፊዮች ዘንድ ይፈፀማልና በዚህ ቀን ከፆም ውጪ ምንም አይነት ለየት ያለ ተግባር እንደሌለ አውቀን ከተለያዩ ቢድዐዎች ተጠንቅቀን ልናስጠነቅቅ ይገባል!!። ✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) #Join ⤵️  የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
Показати все...
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

Фото недоступнеДивитись в Telegram
الأربعون_المكية_في_التوحيد_والسنة_للحفظ.pdf7.17 KB
ተጀመሯል የኡሱል አስ-ሱንና ሊል ኢማም አሕመድ ኢብኑ ሀንበል (ረሂመሁላህ) ሸርህ (ሉዙም አስ-ሱንነህ) የኩታቡ pdf 👇👇 https://t.me/DarASSunnah1444/7031 በሸይኻችን ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ ኢብኑ ዐብደላህ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ) ቀን:- ጁምዐህ፣ ቅዳሜና እሁድ ሰኣት:- ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ ገባ ገባ በሉ👇👇👇 https://t.me/DarASSunnah1444?livestream=bea2443f610277d234
Показати все...
ዳር አስ-ሱንና Dar As-sunnah Channel

👉 አዲስ ኪታብ pdf عنوان:- لزوم السنة في شرح أصول السنة ሱናን አጥብቆ መያዝ በሚል ርእስ የተዘጋጀ የኢማሙ አሕመድ ኢብኑ ሀንበል (ረሂመሁላህ) ኡሱል አስ-ሱንና ኪታብ ማብራሪያ للشيخ الفاضل الدكتور حسين بن محمد بن عبد الله الإتيوبي السلطي حفظه الله ✍🏻አዘጋጅ:- የታላቁ ዓሊም ሸይኽ ረቢዕ እና የታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ዐሊ ኣደም ተማሪ የሆኑት ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ኢብኑ ሙሀመድ ኢብኑ ዐብደላህ አስ-ስልጢ (ሀፊዘሁላህ) ከሳዑዲ ዐረቢያ መከተ'ል መከረመህ 🔸በዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም ቻናል በonline ጁምዓ፣ ቅዳሜና እሁድ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ በሸይኹ በራሳቸው እየተቀራ ነው በአማርኛ ስለሚብራራ ሁሉም መከታተል ይችላል ቴሌግራም ቻናል ⤵️

https://t.me/HussinAssilty

https://t.me/HussinAssilty

(ዐረቢኛ የምትችሉ pdf ን አውርዳችሁ አንብቡት) የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ

https://t.me/DarASSunnah1444

https://t.me/DarASSunnah1444

Фото недоступнеДивитись в Telegram
🏝 ❝አስደሳች ዜና❞ 📚 አዲስ ኪታብ በተለይ ለኡስታዞችና ለዲን ተማሪዎች 📖 ⚙️ የታላላቅ መሻይኾች ተማሪ የሆነው ዓሊም ሸይኽ ሑሰይን ቢን ሙሀመድ ቢን ዐብደላህ አል-ኢትዮጲ አስ-ስልጢይ (ሀፊዘሁላህ) ከተዘጋጁ ኪታቦች አንዱ የሆነው « እስልምና ዒሳን {ዓለይሂ ሰላም} ማላቁ እና ከእስልምና ሀይማኖት የመካድ ምክንያቶች» በሚል በዐረቢኛ የተዘጋጀ አዲስ ኪታብ በቅርቡ ገበያ ላይ ይውላል ኢንሻ አላህ!!! 📮 📔 تعظيم الإسلام لعيسى عليه السلام وأسباب الارتداد عن دين الإسلام 📝 إعداد وجمع:-             🔑 الشيخ حسين بن محمد بن عبد الله الإتيوبي السلطي 📝  አዘጋጅ:- ሸይኽ ሑሰይን ቢን ሙሀመድ ቢን ዐብደላህ አል-ኢትዮጲ አስ-ሲልጢይ (ሀፊዘሁላህ) የኪታቡን PDF ለማግኘት https://t.me/shakirsultan/1860 📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ 👇👇👇 🌐 https://t.me/shakirsultan
Показати все...
🔹 ኢብኑ ቁዳመህ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:- “እራስህን ከማስተካከልህ በፊት ሌሎችን በሚያስተካክል ነገር ከመወጠር ተጠንቀቅ!። ውስጥህን በማስተካከልና ከሚወገዙ ባህሪያት በማፅዳት ተወጠር!፣ እላይህን ከማስተካከልህ በፊት ለዱኒያ ከመጓጓት፣ ከምቀኝነት፣ ከይዩልኝ፣ በራስ ከመደነቅ ውስጥህን አፅዳ!።” [ሙኽተሶር ሚንሃጁል ቃሲዲን ገፅ 20] #join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
Показати все...
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

ኢብኑ ቁዳመህ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:- “እራስህን ከማስተካከልህ በፊት ሌሎችን በሚያስተካክል ነገር ከመወጠር ተጠንቀቅ!። ውስጥህን በማስተካከልና ከሚወገዙ ባህሪያት በማፅዳት ተወጠር!፣ እላይህን ከማስተካከልህ በፊት ለዱኒያ ከመጓጓት፣ ከምቀኝነት፣ ከይዩልኝ፣ በራስ ከመደነቅ ውስጥህን አፅዳ!።” [ሙኽተሶር ሚንሃጁል ቃሲዲን ገፅ 20] #join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
Показати все...
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

قال ابن قدامة رحمه الله: ((...وإياك أن تشتغل بما يصلح غيرك *قبل إصلاح نفسك*، واشتغل بإصلاح باطنك وتطهيره من الصفات الذميمة، كالحرص، والحسد، والرياء، والعجب، قبل إصلاح ظاهرك)). 📚 مختصر منهاج القاصدين (ص: 20).
Показати все...
ልብ ያለው ልብ ይበል!! ——— የቢድዐህ እና የቡድንተኞችን ሴራ ጠንቅቀው የሚያውቁት አል-ኢማም ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ ዑመይር አል-መድኸሊይ (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ:- “እኔ አሁን እንደምገምተው ከሰለፊዮች ብዙ ሰው ወንድሙ ሲታመም አለያም የሆነ ሙሲባ ሲገጥመው እንደሚደሰት ነው፣ ህመም አይሰማውም፣ ለምን? (መልሱም) ፈተና ስለበዛ፣ በመካከላቸው ስለተንሰራፋና የስሜት ባለ ቤቶች ስላንሰራፉት ነው። እኔ በተደጋጋሚም እላለሁ:- እኛ፣ ሰለፊዮችን በምስራቅም በምእራብም በአንድ መንሀጅ ላይ ሆነው ያለ መለያየት የሚዋደዱ ወንድማማቾች ሆነው ነው ያገኘናቸው፣ የሰለፊያ ደዕዋም በዓለም በምስራቁም በምእራቡም ተሰራጨ። ይህኔ ቆሻሻ ከሆኑት ከአይሁድ፣ ከነሷራና ከሙበሺሮች የጥመት መሪዎች ራፊዷዎችና እነዚያ በሙስሊሞች ላይ ጠላትንና የተለያዩ ለሙስሊሞች አደገኛ የሆኑ ቡድኖችን የሚያስተባብሩ ሱፊዮች ነቅተው ተመለከቱ፣ ወላሂ ከጠላት ጋር ይተባበራሉ፣ በመካከላቸው ስውርና ግልፅ ትስስር አለ፣ ከሰለፊዮች ተቃራኒ በመሆን ይተባበራሉ፣ (ከሰለፊዮች ተቃራኒ በሆነ  ነገር ላይ እንጂ አይተባበሩም)። የሰለፊያ ደዕዋ በምስራቁም በምእራቡም በተሰራጨ ጊዜ በሰለፊዮች መካከል የመለያየትን መርዝ ረጩ፣ ተንኮል የተሞላበትን መበታተንም በታተኗቸው። ይህን ጊዜ ሰለፊያን በአግባቡ የማይረዱ ሰዎች ተከሰቱ (አደጉ)፣ ከነሱም ውስጥ አንዳቸው ሰለፊይ እንደሆነ ይሞግታል፣ ከዚያም የሰለፊያን ገመድ የሚበጣጥስ ሆኖ ትመለከተዋለህ፣ ይህም መጥፎ አካሄድ ስላለው፣ የተሰራጨችውን አላማዋም ሰለፊዮችን መበታተን የሆነችውን መጥፎ መንገድና መንገዶችን ስለ ሚጓዙ ነው። ሠለፊያ የአዕምሮ ባለቤት የሆኑ፣ አዛኝና ጥበበኛ የሆኑ ሰዎች ያስፈልጓታል፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ እንዲህ ያሉ ዓሊሞች ያስፈልጓታል። እነዚህ ነገሮች በሰለፊዮች መካከል ከሌሉ የቱ ጋር ነው ሰለፊይነት?!” [አስኢለቱን ሙሂመህ ሀውለ ሩቂየህ  ወር-ሩቃት] ✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
Показати все...
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.