قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
Відкрити в Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
898
Підписники
-224 години
-167 днів
+2730 днів
Архів дописів
ታላቁ ታቢዒይ ሙሓሪብ ኢብኑ ዲሳር አላህን በሚያወድሱበትና ዱዓእ በሚያደርጉበት ጊዜ እንዲህ ይሉ ነበር፡-
√ አላህ ሆይ! እኔ አንተ ያሳደግከኝ ያ ትንሽ ባሪያህ ነኝ፤
ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን!
√ እኔ አንተ ያበረታኸኝ ያ ደካማ ባሪያህ ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን!
√ እኔ አንተ ያብቃቃኸኝ (ያከበርከኝ) ያ ድሃ ባሪያህ ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን!
√ እኔ አንተ ሀብት የለገስከኝ ያ ሚስኪን ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን!
√ እኔ አንተ ትዳር የሰጠኸኝ ያ ላጤ ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን!
√ እኔ አንተ ያጠገብከኝ ያ የተራብኩ ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን!
√ እኔ አንተ ያለበስከኝ ያ የተራቆትኩ ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን!
√ እኔ አንተ አብረኸኝ የሆንክ (የጠበቅከኝ) ያ ተጓዥ ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን!
√ እኔ አንተ በሰላም የመለስከኝ ያ ርቄ የነበርኩ ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን!
√ እኔ አንተ መጓጓዣ የሰጠኸኝ (ያሳፈርከኝ) ያ እግረኛ ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን!
√ እኔ አንተ የፈወስከኝ ያ በሽተኛ ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን!
√ እኔ አንተ የለገስከኝ ያ ጠያቂ ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን!
√ እኔ አንተ ጥሪውን የተቀበልከው ያ ዱዓእ አድራጊ ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን!
🤲ጌታችን ሆይ! ምስጋና ሁሉ ለአንተ የተገባ ነው... ጌታችን ሆይ! በምስጋና ላይ የተደራረበ ምስጋና ለአንተ ይሁን!
📚(ምንጭ፦ "አት-ተሀጁድ ወቂያሙል ለይል" — በኢብኑ አቢ አድ-ዱንያ፡ 45)
https://t.me/alruqyehsheriyeh
https://t.me/alruqyehsheriyeh
Repost from فتاوى شرعية لفضيلة الشيخ محمد بن حزام البعداني
بسم اللــــه الرحمـــــــــن الرحيم.
📩 الســــــــــــؤال:-
يقول الســـــائل: ما هي كفارة اليمين؟
📝 الإجـــــــــابة :-
كفارة اليمين مذكورة في قوله تعالى {لايُؤَاخِذُكُمُ اللَّهُ بِاللَّغْوِ فِي أَيْمَانِكُمْ وَلَٰكِن يُؤَاخِذُكُم بِمَا عَقَّدتُّمُ الْأَيْمَانَ ۖ فَكَفَّارَتُهُ إِطْعَامُ عَشَرَةِ مَسَاكِينَ مِنْ أَوْسَطِ مَا تُطْعِمُونَ أَهْلِيكُمْ أَوْ كِسْوَتُهُمْ أَوْ تَحْرِيرُ رَقَبَةٍ ۖ فَمَن لَّمْ يَجِدْ فَصِيَامُ ثَلَاثَةِ أَيَّامٍ ۚ ذَٰلِكَ كَفَّارَةُ أَيْمَانِكُمْ إِذَا حَلَفْتُمْ ۚ وَاحْفَظُوا أَيْمَانَكُمْ ۚ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمْ آيَاتِهِ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ} [المائدة:٨٩] .
فهذه الآية فيها بيان كفارة اليمين، وقد ذكر الله عز وجل فيها وبيَّن أن المسلم مخير بين ثلاثة أمور فإن لم يقدر عليها ينتقل إلى صيام ثلاثة أيام، وهي إطعام عشرة مساكين من أوسط ما تطعمون أهليكم أي المعتدل ليس بالرديء ولا بالجيد، أي لا يلزمه من أجود الجيد، ولا يجزئه من الرديء.
أو كسوتهم، إذا اخترت كسوة المساكين فلك ذلك، عشرة مساكين يشترط أن يكونوا عشرة في الإطعام وفي الكسوة.
أو تحرير رقبة، فمن لم يجد فصيام ثلاثة أيام ، فإن لم يقدر على الثلاثة الأمور الأولى انتقل إلى الصيام.
ويخطئ بعض الناس فينتقل إلى الصيام، وهو قادر على الإطعام ولا يجزئ ذلك، ومن فعل ذلك فصومه نافلة له، ولا يجزئه عن الكفارة، وعليه أن يرجع إلى الإطعام أو الكسوة أو العتق.
إطعام عشرة مساكين يشترط فيهم العدد أن يكونوا عشرة وأن يكون طعامًا ليس برديء {وَلَا تَيَمَّمُوا الْخَبِيثَ مِنْهُ تُنفِقُونَ وَلَسْتُم بِآخِذِيهِ إِلَّا أَن تُغْمِضُوا فِيهِ ۚ } [ البقرة:٢٦٧].
ولم يشترط أحد من العلماء أن تكون وجبة جاهزة مطبوخة، بل إذا دفعت إليه الدقيق أو البر أو الأرز فيجزئ عند جميع العلماء.
ولا يشترط في الإطعام أيضًا أنه يأكله وجبة واحدة أعني إذا أعطيته الحب، له أن يأكل بعضه اليوم وبعضه في الغد وله أن يهدي منه قد أطعمته بمعنى أعطيته الطعام، ثم هو إن بدا له أن يهدي لغيره أهدى وإن أكل منه أكل وإن أشرك معه غيره فلا بأس، وأقل الإطعام مدٌّ لأنه أقل ما ورد في الإطعام بالشرع .
واستدل العلماء بحديث الرجل المعسر الذي واقع امرأته في نهار رمضان، أن النبي صلى الله عليه وسلم أتي بمكتل فيه خمسة عشر صاعًا، فقال: خذ هذا فأطعم به المساكين.
قال العلماء: هذا أقل ما ورد في الإطعام، خمسة العشر صاعا إذا وزعت على ستين مسكينًا يصيب كل مسكين ربع صاع يعني مدا، الصاع أربعة أمداد، وعلى التقدير في هذهِ الأيام النصف الكيلو يجزئ ، أقل ما يجزئ هو نصف كيلو من الدقيق أو البر أو العدس أو الأرز أو نحو ذلك.
وما يتعلق بالكسوة اختلف العلماء في تقدير كسوة المسكين والصحيح في هذه المسألة أن كل ما يطلق عليه كسوة يجزئه سواء كساه قميصاً أو جبة أو سراويل أو عمامة، كلها كسوة على الصحيح، وهو اختيار الإمام الشافعي رحمه الله.
واختار بعض العلماء أنه يكسوه ما تصح به الصلاة يعني إزارًا أو رداءًا أو قميصاً أو نحو ذلك، وهذا هو الأحوط.
الأحوط أن يعطيه ما تصح به الصلاة، أي ما يستطيع أن يصلي بها ، ولكن لا نستطيع أن نجعل ذلك شرطًا، وإنما ما يطلق عليه كسوة تجزئ ولو كساه عمامة.
وعتق الرقبة معلوم وهو عتق العبيد سواء كان ذكرًا أو أنثى.
وصيام الثلاثة الأيام إذا لم يقدر على الثلاثة الأمور فينتقل إلى الصيام والصحيح أنه لا يشترط فيه التتابع، لأن القرآن بلغنا بالإطلاق (فصيام ثلاثة أيام) وما جاء في قراءة ابن مسعود وأبي بن كعب (فصيام ثلاثة أيام متتابعات) فهي قراءة منسوخة نسخت بالعرضة الأخيرة التي نزلت بدون التقييد (متتابعات) ،فدل على أن الحكم على الإطلاق لأن الله سبحانه وتعالى أبقى لنا في القرآن المطلق، ونسخ المقيد وعلى هذا فلا يشترط التتابع.
وما يتعلق بالإطعام إن أطعم نصف صاع فهو أحوط وأولى لاسيما إن كان موسرا، لأن النبي صلى الله عليه وسلم في فدية الحاج أمر من ارتكب المحظور أن يفدي بإطعام ستة مساكين لكل مسكين نصف صاع، ولذلك نختار لمن كان قادرا أن يزيد على المد، نختار له أن يطعم نصف صاع لكل مسكين، ويساوي نحو كيلو من البر والأرز، نسأل الله الهدى والسداد.
#فتاوى_الفقه
#فتاوى_في_الأيمان_والنذور
----------------‐-------------------
للاشتراك في فتاوى فضيلة الشيخ محمد بن حزام عبر التيلجرام:- https://t.me/ibnhezam
وباللغة الإنجليزية:- http://t.me/ibnhezamen
وعبر الواتساب :- https://chat.whatsapp.com/20UEwOUrfsVJ1h5rmK1sHx
Repost from 🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹
_የሱና እህቶቸ___
አልሀምዱሊላሂ ይመስገን ጌታችን
በማይቆጠረው ኒዕማው ላመቻቸን
የነብዩ ኡመት አድርጎን በእዝነቱ
በሱናቸው ግርጌ አስውቦን ሙሚቱ
በጅልባብ በኒቃብ ደምቀን ልንራመድ
ትዛዝ አመጣልን መጠጊያችን ሶመድ
የነብያት መሪ ኢማሙል ቃኢሚን
አሏህ ነገራቸው ተሸፈኑ እንዲሉን
ውበት ነው ማረግ ነው ለሱና መመረጥ
በተውሂድ ተውቦ በአንድነት ማጌጥ
የሱናዋ እህቴ የመንሀጇ ንግስት
ሁሌ ወድሻለሁ እያየሁ በስስት
አገናኘንና የመንሀጅ የአቂዳ ረመጥ
አለያየንና ያገር አቀማመጥ
በሙሀባሽ ግርጌ ሁሌ ስትናፍቂኝ
አለሁ ዛሬም ድረስ ልቤን ስትደልቂኝ
በርቀት ከንፌ ደስታሽን ስሰማ
ዳዕዋ ወጥነሻል በጠንካራው ማማ
አምልኩት በማለት አረሂሙ ሯህማ
በቂርአት ደምቀሽ ኢልምን ስትሾፍሪ
ከማዳም ቤት ሁነሽ ድካምን ሳትፈሪ
በአንድ እጅሽ ስትሞጥይ በአንዱ ስትሰሪ
እጅጉን ደስ አለኝ የብርታትሽ ድግሪ
የመንሀጅ እህቴ የሱናዋ ኮከብ
በአንድነት ደምቀን በመሀባው መርከብ
እንድንዘያየር ያሳካልን ያ ረብ
ወደድኩሽ ምን ላድርግ እንዴት ይሻለኛል
በድንገት ስትጠፊ ድብርት ይጫነኛል
የማረከኝ ወኔሽ የጥንካሬሽ አውድ
ትምርት ሁኖኛል ጀግና ነሽ የኔ ውድ
በአረብ በረሀ በሚንቀለቀለው
በብርዱ ታፍነሽ በሚቆራጠመው
ቁመሽ ተገትረሽ በአረቦች ስራ
ሳይበግርሽ ቅንጣት የምሽቱ ዳራ
ሳትንገዳገጂ ልንክ እንደተራራ
ትቀስሚያለሽ እውቀት ኢልምሽ እንዲያፈራ
የአንችን ገድል ታሪክ የወኔሽን ማጀት
አይዘልቀውምና የቃላት ቅንጅት
አሏህ ይጠብቅሽ ልበልሽ ጠቅልየ
የአኼራ እህቴ ውስጤ ነሽ እምዬ
ሀገርም ያላችሁ ባህር ወዳ ማዶ
በናንተ ሰቀቀን በናፍቆት ማገዶ
ልባችን ሊያልቅ ነው ተንዶ ተንዶ
እስገምንገናኝ ጀልባው ተሰርጉዶ
የተጋረደብን ሂጃቡ ተቀዶ
አትራቁን በጭራሽ በተቻለ መጠን
እንወዳችኋለን ባህሩን አቋርጠን
በመንሀጃችሁ ላይ_ ሳትንሸራተቱ
በተውሂድ ደምቃችሁ _ሽርክ ሳትወዝቱ
ሱንዩን አቅፋችሁ _ቃሚ ሳትገዝቱ
አድሩስ ሳታጨሱ _ ዱቤ ሳትገትቱ
በሱና ደምቃችሁ ኒቃብ ሳታወልቁ
በኢስላም መርህ ላይ ከፈሩ ሳትወልቁ
ከፀና አቋማችሁ ሳትነቃነቁ
ጠብቁኝ አልቀርም በናፍቆት ሰስቸ
በርቱ የኔ ጀግኖች ውድ ንግስቶቸ
ደግሞም ታምራለችሁ የሱና እህቶቸ
🔷ከምወዳችሁ እህታችሁ ኡሙ ሓቲም
https://t.me/+o7ZrQFQjILVhNDVk
https://t.me/+o7ZrQFQjILVhNDVk
ሰውየው መንሃጅ ብቻ ሳይሆን ቁጥርም ይምታታበት ጀመር ማለት ነው! ሚስኪን!
ቆይ አልገባኝም ሀራ እኛ የምናቀው ከወልደያ በታች ያለው ነው? ወይስ ሌላ ክልል ያለ ሀራ ነው? አረ አደናገራቹህን ጎበዝ!
ለነገሩ ፊቱንም ውሸት መገለጫህ ስለነበርና አሁን ደግሞ የተላተምክበት ጀማዓ የውሸት ማሽን ስለሆነ በዚህ ልክ መቀደድህ ብዙም አይደንቅም። የቤቱ አባዎራዎች እነአብዱል ሀሚድ ውሸት ጌጣቸው ከሆነ የልጆቹ በዚህ ልክ መሆን አያስደነግጥም። እንደ አባባል
"መምህሩ ከፈሳ ተማሪው ይቀዝናን ይባላን"
ገጣሚው እንዲህ ይላል፦
إذا كان رب البيت بالدف ضاربا
فشيمة أهل البيت كلهم الرقص
የቤቱ ባለቤት ከሆነ ዲቢ ወጋሪ፣
ቤተሰቡ ሁሉ ይሆናል ጨፋሪ፣
አሁን እንደዚህ አይነት ፈጣጣ ውሽት ለምን አስፈለገ? ይህችን ቦግ እልም የምትለውን ጀምዓችሁን በውሸት ለመጠበቅ? እኛ እንደዚህ ብዙ ነን ጧሊበል ኢልሙን ሁሉ ይዘነዋል አብሽሩ ሁሉም ከኛ ጋር ነው እያለ በውሸት ነጋሪት ከታች ላለው ጀሌ ሞራል ለመስጠት? ይሄኮ ያረጅ ፋሽን ነው።
ወይስ የለተምያ እውቅና የተሰጠው ሰው አንድ በአስር ነው የሚባዛው!?
أَلَيْسَ مِنْكُمْ رَجُلٌ رَشِيدٌ
=
t.me/Multeka_Selefiyin
t.me/Multeka_Selefiyin
Repost from 𝗗𝗮𝗿𝘂𝗹 𝗜𝗹𝗺 𝗠𝗲𝗿𝗸𝗲𝘇 - ዳሩል ዒልም መርከዝ
📢 አስደሳች ዜና!
ከዳሩል ዒልም የቁርአን ሒፍዝ
እና የተርቢያ መዕከል
💎 ዳሩል ዒልም መርከዝ ለመጪዉ ክረምትና በጋ በአዳሪ መርሃግብር ተማሪዎችን ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቆ በምዝገባ ላይ ይገኛል።
☑️ የመመዝገቢያ መስፈርቶች፦
📍ጾታ፦ ለወንዶች ብቻ (አዳሪ)
📍 እድሜ፦ ከ10 - 20 ዓመት
📍 ጤንነት፦ ከማንኛውም በሽታ ነፃ የሆነ
📍 ስነ-ምግባር፦ለመርከዙ ህግና ደንቦች ተገዢ የሆነ
📍 ፍላጎት፦ ለመቅራት ከፍተኛ ፍላጎት ያለው
📍ክፍያ፦ ወርሃዊ ክፍያን መክፈል የሚችል
☑️ የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች፦
📌 የቁርአን ሒፍዝ (በቃል መያዝ)
📌 የቁርአን ነዘር (ንባብ) እና ሙራጀዓ (ክለሳ)
📌 ቃዒደቱን ኑራኒያ እና የተጅዊድ ትምህርቶች
📌 የተለያዩ የዲን ኪታቦች
☎️ ለምዝገባ እና ለበለጠ መረጃ፡
+251911171786 | +251910034682
+251947224231 | +251970092357
በቴሌግራም ለመመዝገብ ይህን ይጫኑ👈
በዋትስ አፕ ለመመዝገብ ይህን ይጫኑ👈
የቴሌግራም አድራሻ፡
🔗https://t.me/darulilmmerkezofficial
🔗https://t.me/darulilmmerkezofficial
🏢 አድራሻ: አንፎ 105 ከዘቢዳር ሆቴል ጀርባ
Repost from የኡስታዝ አቡ ሓቲም ኸድር አህመድ«አል ኸሚሴ» የፈታዋ ቻናል
#ጥያቄ_እና_መልስ ክፍል 4
33- ዑመር ኮምቦልቻ: “ውሃብዮች ከሚያመልኩት ጌታ ሙፍቲን የሚያመልክ ይሻላል” ብሏል። ሙስጦፋ ዐብደላህ ደግሞ: “እሱን ሙስሊም ነው ያለ ሁሉ ካፊር ነው፣ ዑዝር ቢል ጀህል ይሰጠዋል ያለ አካል ካፊር ነው” አለ። “ዑዝር ቢል ጀህል የለም” ያሉ ዑለሞች እንደዚህ ብለዋልን? (0:18)
34- ሙስጦፋ ዐብደላህ ከሱና ሰው ይመደባልን? (12:31)
35- በሃገራችን በዳዒ ደረጃ ያሉ ዋና ዋና ኢኽዋኖች እነማን ናቸው? ከሱና መርሆዎች ውስጥ የኻለፉትንም ቢጠቅሱልን? (17:15)
36- አንድ ሰው ሰለፊይ ነህ ወይ ሲባል አዎ ብሎ ይመልሳል። ነገር ግን ከሁኔታው ሰለፍዮችን የሚገልፅ ነገር አያንፀባርቅም። እኛ ሌላ ነገር እንድንጠረጥር አደረገን። መጠራጠራችን ወንጀለኛ ያደርገናል ወይ? (25:18)
37- ከኢኽዋኖች መስጂድ ደዕዋ ተጋብዘን ደዕዋ ብናደርግ ችግር አለው ወይ (28:38)
38- ዑዝር ቢል ጀህልን በተመለከተ ሸይኽ ፈውዛን ሁለት አቋም አላቸው። የሙስጦፋ ጀማዓዎች የሚመስላቸውን ነው የያዙት። ይሄን በተመለከተ ምክር ብትለግሰን (32:18)
39- መርሳ አካባቢ ስላሉ ኢኽዋኖች ቢነገር። ወጣቶችን ዐቂዳ ከመቅራት አዘናግተዋልና ወደፊት የነሱን አቋም እንደሚከተሉ ግልጽ ነው። (36:56)
40- ቁርኣን በተጅዊድ አልቀራሁም። የዐቂዳና የመንሃጅ ኩቱቦችን ቀርቻለሁ። መድረሳ ላይ ባስተምር ችግር ይኖረዋልን? (38:40)
41- ሙስጦፋ: ዑዝር ቢል ጀህል አለ ከሚል ሰው ጋር መስጂድ መስራት አይቻልም ይላል። ስለዚህ ነገር ምን ትለናለህ? (39:45)
42- እኔ ሙስጦፋን ነበር የምከታተለው። ባለቤቴ በዛ እንዳትገቢ ብሎ ከለከለኝ። እኔም ትንሽ ተጨቃጨቅኩትና መጨረሻ ላይ እሽ አልኩት። ይሄ እንዴት ይታያል? (41:00)
t.me/Ustaz_Kedir_ahmed_2
Repost from የኡስታዝ አቡ ሓቲም ኸድር አህመድ«አል ኸሚሴ» የፈታዋ ቻናል
5️⃣ ጥያቄ እና መልሶች 🤏➊.ሰለ ኡዝር ቢልጀህል አብራሩልኝ❔ ❷.የሱና ሰዎችን የሚያከፍር አካልን መውረስ ይቻላልን❔ ❸.ጥያቄዎ ረጅም ሰለሆነ መልሱን ያዳምጡ ..🤝 ❹.አንድ ሰው ጠንቋይ ዘንድ ሄደ ከዚያም ጠየቀው የአርባ ሌሊት ሶላት ተቀባይነት የለውም ሲባል እንደት ነው❔ ❺.በገጠሩ አካባቢ ስለዲናቸዉ ሳይማሩ በጂህልና ጊዜያቸዉን ያሳለፉ ሰዎች ከዛም ከአመታቶች በሗላ በልጆቻቸዉ ሰበብ ሽርክንም ተዉ ሰላት መስገድ ጀመሩ ሶላትን ሲሰግዱ ግን አህካሙን እና ሸርጡን አሟልተዉ አይደለም ከሞላ ጎደል ነዉ አሏሁሙስተዓን አላህ ይዘንላቸዉ እና እነርሱ ያረዱት ሀላል ይሆናልን እርዲን መሃለል ይችላሉ❔
👤በኡስታዝ አቡ ሓቲም ኸድር አህመድ📱 t.me/Ustaz_Kedir_ahmed_2
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
ሸይኽ ሙሐመድ ሸይኽ
-------------------------
👉ታዋቂው ኢትዮጵያዊው ዓሊም ነሕዊይ ኡሱሊ አቡ-ዓብደልጀሊል ሙሐመድ ኢብን ዓሊ ቢን አደም ቢን ሙሳ አል-ሐበሺይ (ረሒመሁሏህ) ሀገራቸው ላይ ባሉ በአንዳንድ ወዳጆቻቸው ሸይኽ ሙሐመድ ሸይኽ በመባል ይታወቃሉ
◆ትወልድና ትምህርት
✅ሸይኹ ረሒመሁሏህ የተወለዱት በሐገራችን በሰሜኑ ክፍል በቀድሞው የወሎ ክፍለ ሀገር ወረሂመኑ አውራጃ በ1366 ዓ.ሂ አቅራቢያ ነበር። የዲን ዕውቀትን 'አሊፍ' ብለው አባታቸው ላይ ቁርኣን በመቅራት በመጀመሪያ ሸይኽ ሙሐመድ ገዩ (ረሂመሁሏህ) ዘንድ አክትመዋል። በመቀጠልም ከአባታቸው ሸይኽ አሊ አደም ሙሳ (ረሂመሁሏህ) እና ከሌሎችም ታዋቂ መሻይኾች እንደ ነሕው፣ ሶርፍ፣ በላጋ፣ ኡሱል፣ መንጢቅ፣ ሐዲስ፣ ፊቅህ እና ሌሎችም ዘርፎች ላይ የጠለቀ ዕውቀትን በጊዜው አሉ ከሚባሉ የሀገራችን መሻይኾች ተምረዋል።
✅ሸይኹ በሀገራችን ኢትዮጵያ ሳሉ ቁርአንን ከመሀፈዛቸው በተጨማሪ እንደ አልፊየቱ ኢብን ማሊክ እና አልፊያ አስ-ሱዩጢ ያሉ መትኖችንና ግጥሞችን በቃላቸው ሸምድደዋል። እንዲሁም ከበርካታ መሻይኾቻቸው ለብቁነታቸው ምስክርነት/ሸሀዳ ተችሯቸዋል።
◆ስደት
✅ከዚህም በዃላ ሸይኽ ሙሐመድ ዓሊ አደም (ረሂመሁሏህ) በወቅቱ የነበረውን የኮሚኒስት መንግጊ(ደርግ) በመሸሽ ወደ መካ-ሳዑዲ ዓረቢያ ተሰደዱ። ይሁንና በጉዟቸው ወቅት በከፊል መሻይኾቻቸው የተሰጣቸውን ሸሀዳ በእጃቸው ባለመያዛቸው ምክንያት በተማሪነት መልኩ መካ ውስጥ በሚገኝ መድረሳ የተወሰነ ጊዜ ቆይታ አድርገዋል። በመቀጠልም በወቅቱ በሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ ኢብኑ ባዝ ወደሚመራው ዳረል ሐዲስ አቅንተው ለመማር ፈተና ቢወስዱም ያስመዘገቡት ውጤት በሰዓቱ የነበሩ የዳረል ሐዲስ አመራሮችን አስደምሞ እኒህን ለመማር የመጡ ድንቅ ሸይኽ መምህር እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።ከዛን ስዓት ጀምሮ ህይወታቸው እስካለፈችበት ጊዜ ድረስ በዳረል ሐዲስ እና በመስጂድ አለ-ሐረም ለበርካታ ዓመታት ራሳቸውን ለዒልም እና ለፈላጊዎቹ ተሰጥተው አስተምረዋል።
◆ከአሽዓሪያ ወደ አህሉ-ሱና
✅ሸይኹ (ረሂመሁሏህ) በተለያዩ ድምፆቻቸው ከልጅነታቸው ጀምሮ ለሐዲስ ትልቅ ፍቅር እንዳላቸው ከመግለፃቸውም ባሻገር በደረስነት ጊዜያቸውም እንደ ሌሎች ሰዎች ባደጉበት የሐነፊያ መዝሀብ ከመገደብ ይልቅ መረጃ (ቁርዐን ሐዲስ) የሚደግፈውን አካሄድ ይመርጡ እንደነበር ይናገራሉ። ሸይኹ ወደ መካ ከተሰደዱ እና ዳሩል ሐዲስ ከገቡ በዃላ የነ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ፣ ኢብኑል ቀይም አልጀውዚይ እና ሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲልወሀብ ኪታቦችን ሲያገላብጡ በሐገራቸዉ ሳሉ ከተማሯቸው የዐቂዳ ትምህርቶች ጋር የሚጋጩ ነገሮች እንዳገኙ ይናገራሉ። እናም ቀድሞም ያደርጉት እንደነበረው ሁሉ ትክክለኛ መረጃ ያለውን ሲፈትሹ አሁን ያነበቧቸው ኪታቦች ትክክል ሆነው ማግኘታቸውን ይናገራሉ።
✅ሸይኹ ወደ መካ ከመጡ በዃላ የተለያዩ ታላላቅ ዓሊሞችን ኪታብ አገላብጠው አንብበው የያዙትን አቋም ሲናገሩ ... “በሀገሬ ሳለሁ ከአሽዓሪያ መሸይኾቼ የተማርኩትንና አምንበት የነበረውን ዓቂዳ በመተው ራቅኩት” ይላሉ።
✅ሸይኽ ሙሐመድ አሊይ አደም (ረሂመሁሏህ) አስከትለውም “አባቴን ለመጠየቅ ወደ ሀገሬ በሄድኩ ጊዜ አንድ ሰው 'አንተ ዉሀቢይ ሆነሃል' አለኝ። 'የለም፣ እኔ መረጃውን ነው የምከተለው ፤ እንደምታውቀው ወደ መካ ከመሄዴም በፊት ትክክለኛውን መረጃ ነበር የምከተለው አልኩት። 'አዎ እሱን አውቃለሁ ማጥበቅ ላይ ጨምረኻል' አለኝ። እኔም ምነው ኢማሙ ሻፊዒ በዒራቅ እና ሒጃዝ ሳሉ አንድ መዝሀብ (አቋም) እንደነበራቸውና ወደ ግብፅ ሄደው ብዙ ማስረጃነን ያገኙ ጊዜ የቀድሞውን መዝሀባቸውን እንደተው አና አዲስ መዝሀብ እንደመሰረቱ አታውቅም እንዴ? ልክ እንደዚሁ እኔም ከሀገሬ ሰዎች የተሰወረን ማስረጃ ያገኘሁ ጊዜ ተከተልኩት ፤የሚያስይዘውንም ሰራሁበት፤ ይህ እድሜ ልኬን የምሄድበት አካሄድ ነው ኢንሻአላህ' አልኩት”ሲሉ ይናገራሉ።
◆ስራዎቻቸው
✅ሸይኽ ሙሐመድ አሊይ አደም አል-ሐበሺይ በተለያዩ የሸሪዓ እውቀት ዘርፎች በርካታ ኪታቦችን ፅፈዋል።በተለይ በሐዲስ ዘርፍ ያበረከቷቸው ኪታቦች ጎልተው ይወጣሉ። ከነዚህም መካከል የሶሒሕ ሙስሊም ሸርሕ የሆነውን البحر المحيط الثجاج شرح صحيح مسلم بن الحجاج በሃምሳ ሙጀለድ/ቅፅ ሲያዘጋጁት ፣ የሱነን አነሳዒ ሸርሕን زخيرة العقبى في شرح المجتبى በአርባ ሁለቱ ሙጀለድ ፅፈውታል።እነኚህ ሸርሖች የሸይኹን የዒልም ምጥቀት ለዓለም ያሳዩ ህያው ምስክሮች ሁነው ይታያሉ።
✅እንዲሁም በሀዲስ እና በሌሎችም ዘርፎች ከ30 በላይ በርካታ ኪታቦችን አሳትመዋል
◆የዑለማኦች አድናቅቶ
✅ታዋቂው ሙሐዲስ (የሐዲስ ሊቅ) ሸይኽ ናሲሩ-ዲን አል-አልባኒይ (ረሂመሁሏህ) ስለ ነሳዒ ሸርሕ ዘኺረቱል ዑቅባ ሲናገሩ “ይህን የመሰለ የነሳዒ ሸርሕ አላውቀውም” ብለዋል።
✅ከሸውካኒ በመቀጠል የየመኑ ሙሐዲስ በመባል የሚታወቁት ዓሊም ሸይኽ ሙቅቢል አል-ዋድዒይ (ረሂመሁሏህ) ስለ ዘኺረቱል ዑቅባ “ይህ ኪታብ የሐፊዝ ኢብን ሐጀር 'ፈትሑል ባሪ' አይነት ነው ...ጧሊበል ዒልሞች ይህ ታላቅ ኪታብ ለማግኘት እንድጥሩ እመክራለሁ። በዚህ ዘመን ያለ ሙሐዲስ ሁሉም ይህን የመሰለ ሸርህ እንዲያመጣ እጠይቃለሁ” ብለው ነበር።
✅የዚህ ዘመን የጀርሕ እና የተዕዲል ኢማም የሆኑት ታላቁ ዐሊም ሸይኽ ረቢዕ ቢን ሓዲ አል-መድኸሊይ (ረሒመሁሏህ) ደግሞ ሸይኽ ሙሐመድ አሊ አደም 'በሁሉም ዘርፍ ዐሊም ናቸው ሲሉ መስክረውላቸዋል።
✅ሸይኹን ከእነዚህም ውጭ ያሉ በርካታ ዑለሞች አወድሰዋቸዋል ለምሳሌ ሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛን፣ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሒዛም፣ ሸይኽ ሷሊህ አል-ዑሶይሚ እና ሌሎችም...
ሸይኹ እንዲህም ተገጥሞላቸዋል .
يـا سائلي عن عالم الأحابشي .....
اسمع مقالي سمع ذي إنعاشي
فـالـولـوي إمـام أهـل زمـانـهـم....
من غير ما شك ولا إغباش
جـمـع الـعـلـوم أصـولـهـا وفـروعـهـا....
مع نظمها في غاية الإدهاش
بـحـر بـعـيـد غـوره ونـطـاقـه....
قد عم كل السهل والأحراش
👉ሸይኽ ሙሐመድ ዐሊይ አደም አላህ ይዘንላቸውና የበርካታ መሻይኾች ሸይኽ የሆኑ የዒልም ባህር ናቸው።
والشيخ رحمه الله .. توفي الخميس21 صفر 1442 الموافق لـ 8 أكتوبر 2020 .. ودفن في مقبرة شهداء الحرم في حي الشرائع بمكة. رحمه الله تعالى واعلى درجته في عليين
Repost from 💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
እውነተኛ የሴት ልጅ ነፃነትና ጥበቃ ሊረጋገጥ የሚችለው ክብሯን ከፍ ባደረገው፣ ከውርደትና ከብልሽትም ጠብቆ በማኅበረሰቧ ውስጥ የተከበረችና ውድ ዕንቁ እንድትሆን ባደረጋት የኢስላም ሸሪዓ ጥላ ስር ብቻ ነው።
📌 قـ✑ــال العلامــة صـالح الفــوزان حفظــہ اللـہ تعـالـﮯ :
☜ المــرأة لا تڪـون حــرة إلا بالتــزام الأحڪـام الشــرعية
⇦ الشــر؏ حــررها مـن الهــوان حــررها مـن الفســاد حــررها مـن ڪـل رذيلـة
❀ ◄ ضبطها
✿ ◄ ڪرمها
❀ ◄ عززهـا
✿ ◄ صانهـا
📑 شـرح ڪـتاب الفتـن والحـوادث [ صـ 34 ]
"አንዲት ሴት ነፃ ልትሆን የምትችለው የሸሪዓዊ ድንጋጌዎችን (አህካሞችን) ሙጥኝ ብላ ስትይዝ ብቻ ነው።
⇦ ሸሪዓ ከውርደት ነፃ አውጥቷታል፣ ከብልሽት ነፃ አውጥቷታል፣ ከማንኛውም መጥፎ ምግባር (ርኩሰት) ነፃ አውጥቷታል።
❀ ◄ ስነ-ስርዓት አስይዟታል
✿ ◄ አክብሯታል
❀ ◄ ልዕልናን ሰጥቷታል
✿ ◄ ጠብቋታል
ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን
📑 [ሸርሕ ኪታብ አል-ፊተን ወል-ሐዋዲሥ — ገጽ 34]
t.me/durusuabihizam
t.me/durusuabihizam
حُبُ أهل التوحيد، وبغض أهل الشّرك:
👉አላህን በብቸኝነት የሚያመልኩ ሰዎችን መውደድ እና የሺርክ ሰዎችን መጥላት፦
👉ይህ አል-ወላዕ ወል-በራዕ (ለአላህ ሲሉ መወዳጀትና መጥላት) ማለት ነው። እርሱም የተውሒድ ሰዎችን መውደድ እና የሺርክ ሰዎችን መጥላት ሲሆን፤ ለአላህ ሲል ይወዳጃል፣ ለአላህ ሲል ይጣላል። ኢብራሂም (ዐለይሂ አስ-ሰላቱ ወስ-ሰላም) ለአባቱና ለሕዝቦቹ እንዳለው፦
{إِنَّا بُرَآءُ مِنْكُمْ وَمِمَّا تَعْبُدُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ كَفَرْنَا بِكُمْ وَبَدَا بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ الْعَدَاوَةُ وَالْبَغْضَاءُ}
«እኛ ከእናንተ ከአላህም ሌላ ከምትገዙት ሁሉ የጠራን ነን፤ በእናንተ ካድን፤ በእኛና በእናንተ መካከልም ጠላትነትና ጥላቻ ተገለጠ።»
{وَإِذْ قَالَ إْبْرَاهِيمُ لأَبِيهِ وَقَوْمِهِ إِنَّنِي بَرَاءٌ مِمَّا تَعْبُدُونَ}
«ኢብራሂምም ለአባቱና ለሕዝቦቹ፡- እኔ ከምትገዙት ሁሉ የጠራሁ ነኝ ባለ ጊዜ (አስታውስ)።»
ይህ የኢብራሂም ንግግር ነው፦ {{إِنَّنِي بَرَاءٌ مِمَّا تَعْبُدُونَ}} (እኔ ከምትገዙት የጠራሁ ነኝ)፤ ማለትም፦ ከጣዖታት፣ ከዛፎችና ከድንጋዮች ከምታመልኳቸው ነገሮች ሁሉ የጠራሁ ነኝ ማለት ነው።
{{إِلاَّ الَّذِي فَطَرَنِي}}
«ያ የፈጠረኝ ሲቀር»
እርሱም አላህ (ሱብሐነሁ ወተዓላ) ነው፤ ይህ የ "ላ ኢላሀ ኢልለላህ" (ከአላህ በስተቀር #በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም) ትርጉም ነው፦
{{إِنَّنِي بَرَاءٌ} (እኔ የጠራሁ ነኝ) የሚለው የ "ላ ኢላሀ" (ምንም እውነተኛ አምላክ የለም) ትርጉም ሲሆን፣
{{إِلاَّ الَّذِي فَطَرَنِي}} (የፈጠረኝ ሲቀር) የሚለው ደግሞ የ "ኢልለላህ" (ከአላህ በስተቀር) ትርጉም ነው።
حُبُ أهل التوحيد، وبغض أهل الشَّرك، وهى أوثقْ عُرى الإيمان
የተውሒድ ሰዎችን መውደድ እና የሺርክ ሰዎችን መጥላት፣ ይህ ነገር ከኢማን ማሰሪያዎች ሁሉ ይበልጥ አስተማማኙ ገመድ ነው።
የአላህ መልክተኛ (ሰልለላሁ ዐለይሂ ወሰልለም) እንዲህ ብለዋል፦
« أَوْثَقُ عُرَى الْإِيمَانِ الْحُبُّ فِي اللَّهِ، وَالْبُغْضُ فِي اللَّهِ»
«ከኢማን ማሰሪያዎች ሁሉ ይበልጥ አስተማማኝዋ ለአላህ ብሎ መውደድና ለአላህ ብሎ መጥላት ነው።
« ثَلاثٌ مَنْ كُنَّ فِيهِ وَجَدَ حَلاوَةَ الإِيمَانِ: أَنْ يَكُونَ اللَّهُ وَرَسُولُهُ أَحَبَّ إِلَيْهِ مِمَّا سِوَاهُمَا، وَأَنْ يُحِبَّ الْعَبْدَ لا يُحِبُّهُ إِلا لِلَّهِ -عَزَّ وَجَلَّ -، وَأَنْ يَكْرَهَ أَنْ يَرْجِعَ فِي الْكُفْرِ بَعْدَ إِذْ أَنْقَذَهُ اللَّهُ مِنْهُ كَمَا يَكْرَهُ أَنْ يُلْقَى فِي النَّارِ»
«ሦስት ነገሮች በእርሱ ውስጥ የተገኙ ሰው የኢማንን ጣዕም አግኝቷል፦ አላህና መልክተኛው ከሌላው ነገር ሁሉ ይበልጥ በእርሱ ዘንድ ተወዳጅ መሆን የለባቸው፣ አንድን ባሪያ ለአላህ (ዐዘ ወጀል) ሲል እንጂ ሌላ ለምንም ሳይሆን መውደዱ፣ እና አላህ ከክህደት ካዳነው በኋላ ወደ ክህደት መመለስን ልክ ወደ እሳት ውስጥ መጣልን
እንደሚጠላው አድርጎ መጥላቱ።»
እነዚህ አላህን፣ መልክተኛውን፣ ዲኑን (ሃይማኖቱን) እና ወዳጆቹን የመውደድ ምልክቶች ናቸው። አላህ (ጀልለ ወዐላ) እንዲህ ይላል፦
{{إِنَّمَا وَلِيُّكُمْ اللَّهُ وَرَسُولُهُ وَالَّذِينَ آمَنُوا الَّذِينَ يُقِيمُونَ الصَّلاةَ وَيُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَهُمْ رَاكِعُونَ}}
«ረዳታችሁና ወዳጃችሁ አላህ፣ መልክተኛውና እነዚያ የሰገዱ ሆነው ሶላትን የሚሰግዱ፣ ዘካንም የሚሰጡ ምዕመናን ብቻ ናቸው።»
{{وَمَنْ يَتَوَلَّ اللَّهَ وَرَسُولَهُ وَالَّذِينَ آمَنُوا فَإِنَّ حِزْبَ اللَّهِ هُمْ الْغَالِبُونَ}}
«አላህንና መልክተኛውን እነዚያን ያመኑትንም ወዳጅ የሚያደርግ ሰው (የአላህ ጭፍራ ነው)፤ የአላህም ጭፍራዎች እነሱ አሸናፊዎች ናቸው።» (የአላህን ወዳጅ ማድረግ ማለት አላህን መውደድ ማለት ነው)።
ለአላህ ብሎ መውደድና ለአላህ ብሎ መጥላት ማለት ይህ ነው። ነገር ግን ሰውን ሁሉ የሚወድ ከሆነ፣ ወይም ደግሞ ለእርሱ መልካም ለዋለለት ሰው ብቻ ውዴታን አሳይቶ፣ የበደለውን ሰው ሙእሚን (አማኝ) ቢሆን እንኳ የሚጠላ ከሆነ፤ ይህ ሰው (ፍፁም) አማኝ አይደለም።
ምንጭ፦ «ከላ ኢላሀ ኢልለላህ» ትርጉም መልእክት በኢማም ሙሐመድ ቢን ዓብደል ወሃብ
አብራሪው፦ ታላቁ የፊቅህ ሊቅ ዐላማህ ሸይኽ / ሷሊህ ቢን ፈውዛን አል-ፈውዛን (አላህ ይጠብቃቸው)
Repost from قَناةُ وفَوا ئِد أبي فَوزان الْحَبَشِيِّ
🎙በድምፅ እንደምሰሙት ባህር ዳር ከተማ በ08 ቡኻሪ መስጂድ ኢማሙ ከግድያ በአላህ ፍቃድ አመለጡ ።
እረተው እንጠንቀቅ በቻልነው አቅም ኢማሞች በዬ ቦታው እየታደኑነው።
በያስ ሼርኳን እያደ ርጋችሁ ለሁሉም ይድረስ እባካችሁ።
🔷👉https://t.me/abujemila25
🔷👉https://t.me/abujemila25
ለሁሉም አድርሱልኝ።
🔷 የሰለፎች መንሀጅ በማጥበቅ እና በማላላት መካከል ያለ የፍትህ፣ የሚዛን እና የጥበብ መንገድ ነው!!!
አላህ ይችን ዑማ የመካከለኛነት ኡማ አድርጎ መርጧታል። እንዲህም ይለናል፦
﴿وَكَذَٰلِكَ جَعَلْنَاكُمْ أُمَّةً وَسَطًا﴾
“እንዲሁም መካከለኛ ሕዝብ አድርገን አደረግናችሁ።” (አል-በቀራህ 2፥143)
ይህ “ወሰጥ” የሚለው ቃል በሰለፎች ግንዛቤ ፍትህን፣ ሚዛንን፣ ከጫፎች መራቅን እና እያንዳንዱን ነገር በሚገባው ቦታ ማስቀመጥን ያመለክታል። ስለዚህ የሰለፎች መንሀጅ የስሜት መንገድ አይደለም፣ የወገንተኝነት መንገድ አይደለም፣ የተከታዮችን ብዛት የሚለካ መንገድም አይደለም፤ ይልቁንም የማስረጃ፣ የፍትህ፣ የእውቀት እና የጥበብ መንገድ ነው።
የሰለፎች መንገድ ከሁለት ጫፎች የጸዳ ነው። ከአንዱ በኩል ያለቦታው ተጥቢቅና ጉሉው፣ ከሌላው በኩል ደግሞ ያለቦታው ማላላትና ተፍሪጥ ነው።
አላህ እንዲህ ይለናል፦
﴿يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لَا تَغْلُوا فِي دِينِكُمْ﴾
“የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በዲናችሁ ውስጥ ከመጠን አትለፉ።” (አን-ኒሳእ 4፥171)
እንዲሁም ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«إِيَّاكُمْ وَالْغُلُوَّ فِي الدِّينِ، فَإِنَّمَا أَهْلَكَ مَنْ كَانَ قَبْلَكُمُ الْغُلُوُّ فِي الدِّينِ»
“በዲን ውስጥ #ከመጠን ማለፍን ተጠንቀቁ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ያጠፋቸው በዲን ውስጥ ከመጠን ማለፋቸው ነበር።”
ከዚህ የተነሳ ያለቦታው ማጥበቅ የሰለፎች መንገድ አይደለም። #አንዳንዶች የራሳቸውን ፍርድ የሰዎች መመዘኛ ያደርጋሉ። በስሜት በቁጣ እና ሞቅ ሲላቸው ቸኩለው በሰው ላይ #ፍርድ የሚሰጡ አካላቶች እንድሁም የግለሰቦችን ወይም የቡድኖችን ጉዳይ በራሳቸው ግምት በመወሰን ሌሎች ሰዎች ያንኑ ፍርድ ካልተከተሉ ወይም ካልተስማሙ በተመሳሳይ መፈረጅ ይጀምራሉ።
አንዳንድ ጊዜ #ኢልዛምን የወላዕና በራዕ መለኪያ ያደርጋሉ።ሰዎችን በቁርአንና በሱና ማስረጃ ሳይሆን #በግለሰብ ውሳኔ ይመዝናሉ። የሰለፎች መንገድ ግን ይህ አይደለም። የሰለፎች መንገድ ሰዎችን በማስረጃ፣በፍትህ እና በእውቀት ይመዝናል።
በማጥበቅ ጫፍ የወደቁ #አንዳንድ አካላት #ግለሰቦችን ወይም #ቡድኖችን በመፈረጅ ላይ ከልክ ያልፋሉ። አንድ ሰው በአንድ ጉዳይ ላይ የሰጡትን ፍርድ ካልተከተለ ወይም ተመሳሳይ ውሳኔ ካልደረሰበት በቀላሉ በተመሳሳይ ስም ለመፈረጅ ይቸኩላሉ። እኔ ሙብተድዕ ያልኩትን ካላልክ #ሙብተድዕ ነህ። እኔ ሙሽሪክ ያልኩትን ካላልክ #ሙሽሪክ ነህ የሚሉ አካላቶች እንደዚህ ያለውን የግዴታ ተከታታይነት (الإلزام) የሰው ታማኝነት ወይም የመንሀጅ መለኪያ ማድረግ ግን ከሰለፎች የፍትህ መንገድ አይደለም።
አላህ እንዲህ ይለናል፦
﴿يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ بِالْقِسْطِ شُهَدَاءَ لِلَّهِ وَلَوْ عَلَى أَنْفُسِكُمْ﴾
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ምስክሮች ሆናችሁ በፍትህ ጽኑ፤ ምንም እንኳ በራሳችሁ ላይ ቢሆንም።” (አን-ኒሳእ 4፥135)
እንዲሁም፦
﴿وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَى أَلَّا تَعْدِلُوا ۚ اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَى﴾
➜ “የአንድ ሕዝብ ጥላቻ ፍትህን እንዳትተዉ አያድርጋችሁ። ፍትህን አድርጉ፤ እርሱ ለተቅዋ ይበልጥ ቅርብ ነው።” (አል-ማኢዳህ 5፥8)
በሌላ በኩል ደግሞ ያለቦታው #የሚያላሉና #የሚያግራሩ አካላት አሉ። እነርሱ አንዳንድ ጊዜ ለጥቅም፣ ለስም፣ ለተከታይ ብዛት፣ ለዝና ወይም ለሌሎች ዓለማዊ ግቦች ሲሉ ሀቅን ከመናገር ይቆጠባሉ። ስህተትን በስሙ ለመጥራት ይፈራሉ፣ ባጢልን በባጢልነቱ ለመግለጽ ይዘገያሉ፣ እናም አንድነትን ከሀቅ በላይ ያስቀድማሉ።
ነገር ግን አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿وَلَا تَلْبِسُوا الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُوا الْحَقَّ وَأَنْتُمْ تَعْلَمُونَ﴾
“ሀቅን ከባጢል ጋር አትቀላቅሉ። እናንተም እያወቃችሁ ሀቅን አትደብቁ።” (አል-በቀራህ 2፥42)
እንዲሁም ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«الدِّينُ النَّصِيحَةُ»
“ዲን መመካከር ነው።”
ስለዚህ ሀቅን መግለጽ ከዲን አካል ነው። ➜ ነገር ግን ሀቅን መግለጽ ማለት #ፍትህን መተው ማለት አይደለም።እንዲሁም ፍትህን መጠበቅ ማለት ሀቅን መደበቅ ማለት አይደለም።
የሰለፎች መንሀጅ ሀቅን በእውቀት ላይ ሁነው እንድናገሩ ያዛል። እንደዝሁም ከስህተትም በእውቀትና በፍትህ ያስጠነቅቃሉ።
አብደላህ ኢብኑ መስኡድ እንዲህ ብለዋል፦
«الجماعة ما وافق الحق وإن كنت وحدك»
“ጀማዓ ማለት ከሀቅ ጋር መሆን ነው፤ ምንም እንኳ አንተ ብቻህን ብትሆንም።”
እንዲሁም ሱፍያን አሶውሪ እንዲህ ብለዋል፦
«إذا رأيت الرجل يعمل العمل الذي اختلف فيه وأنت ترى غيره فلا تنهه»
“አንድ ሰው በዑለማዎች መካከል የተለያየበትን ጉዳይ ሲሠራ ብታይ አትከልክለው።”
ይህም የሰለፎች ፍትህና ሚዛን ነበር፤ ሰዎችን በአንድ ጉዳይ ላይ በችኮላ አይፈርዱባቸውም ነበር፣ እንዲሁም ሀቅን በሰዎች ፍላጎት ምክንያት አይተዉም ነበር።
ስለዚህ የሰለፎች መንሀጅ ከጉሉውና ከተፍሪጥ፣ ከማጥበቅና ከማላላት፣ ከችኮላ ፍርድና ከዝምታ፣ ከጭካኔና ከመለሳለስ መካከል የቆመ የፍትህ፣ የሚዛን፣ የእውቀት እና የጥበብ መንገድ ነው። ይህ ነው የአህሉ ሱና ውበት፤ ይህ ነው የሰለፎች ጓዳ፤ ይህ ነው ከሁለቱ ጫፎች መካከል ያለው ቀጥተኛ መንገድ።
አላህ እኛን በዚህ የፍትህ እና የሚዛን መንገድ ላይ እንዲያጸናን፣ ከጉሉውና ከተፍሪጥ፣ ከማጥበቅና ከማላላት እንዲጠብቀን፣ ሀቅን በእውቀት እና በጥበብ እንድንናገር እና ፍትህን በሁሉም ሁኔታ እንድንጠብቅ እንለምነዋለን።
Repost from Ansuar Muhammed {አንሷር ሙሐመድ} Official Channel
🟢 በመጨረሻም ይህ በዝርዝር ያቀረብኩት ወሎ ላይ ያለውን ደውራ በተመለከተ ሲሆን ጅማዎች እና ቡታጅራዎች ከምለው በላይ ደስ አሰኚታችሁናል ። አላህ ይጠብቃችሁ።ሸይኽ ልናመጣ ነው ስንላችሁ እንደ እኛ ተዘጋጁ ስንላችሁ መርሀባ ዝግጁ ነን በማለት ላሳያችሁን የዲን እና የሱና ውደታ ምስጋናችን ከልብ ነው ።
ኢን ሻ አላህ የአላህ ፍቃዱ ከሆነ ሀገር አቀፍ ደውራ አዘጋጅተን የትውውቅ ፕሮግራም በአንድኛችን የምናደርግ ያድርገን ።
ከላይ ስማችሁ ያልተጠቀሰ ግን ለዚህ ፕሮግራም መሳካት ብዙ የለፋችሁና የደከማችሁ መሻይኾች፣ኡስታዞች እና ጀማዓዎች ትኖራላችሁ አላህ መልካሙን ሁሉ ይግጠማችሁ ።ልፋታቹሁ መልካም ስራችሁ ሚዛን ላይ የሚጨመር አላህ ያድርገው።
አንሷር ሙሐመድ🔗🔗🔗https://t.me/ansuar_muhammed_0088
Repost from Ansuar Muhammed {አንሷር ሙሐመድ} Official Channel
ምስጋናችን ከልብ ነው።በመጀመሪያ ደረጃ ይህንን ታላቅ የደውራ ፕሮግራም በሰላም፣ በስኬት እና በደመቀ ሁኔታ እንድንጨርስ የረዳንን ኃያሉን አላህ (سبحانه وتعلى) እናመሰግነዋለን። በመቀጠልም፣ ይህ ፕሮግራም ካለ ምንም እንከን ግቡን እንዲመታ እና ለብዙሃን እህትና ወንድሞቻችን የብርሃንና የእውቀት ምንጭ እንዲሆን በገንዘባችሁ፣ በዕውቀታችሁ፣ በጉልበታችሁ እንዲሁም በሃሳባችሁ ከጎናችን በመቆም ይህ የደውራ ፕሮግራም እንዲሳካ ላደረጋችሁ በሙሉ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን። በተለይም ደግሞ ለተከበሩ ሸይኽ አልዩ አር ራዚሒ ወደ ሀበሻ (ኢትዮጵያ) ለመምጣት መጀመሪያ ከሳዑዲ ወደ ግብፅ ከዚያም ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ አዲስ አበባ ላይ በመስጂዶች ላይ ደዕዋ፣ኹጥባ እንድሁም ኮርስ ለአህለ ሱናዎች ከሰጡ በኋላ ወደ ወሎዋ ምድር ኮንቦልቻ በመምጣት ኮንቦልቻ ላይ ከተለያየ ቦታ የመጡ ከ1300 በላይ ለሆኑ መሻይኾች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች ፣ዒልም ፈላጊ ወንድሞች እና እህቶች ለአምስት ቀን በሚያምር እና በቆንጆ አገላለፅ በመንሀጅ ዙሪያ ፣አንድ ኪታብ በአስማኡ ወሲፋት ዙሪያ ፣አንድ ኪታብ በሙስጦላሁ አል"ሀዲስ ዙሪያ እና አንድ ኪታብ በፊቂህ ዙሪያ በማስተማር ሲደክሙና ሲለፉ ካሳለፉ በኋላ በየመሃሉ ላይ የፈተዋ ፕሮግራም ሲሰጡን ነበር።ሸይኽ አላህ ጀዛቸውን ይክፈላቸው ና የኮንቦልቻውን ፕሮግራም ከጨረሱ በኋላ በደሴ ከተማ ከዝሁር ሶላት በኋላ በአረብ ገንዳ እና ከአስር ሶላት በኋላ በመስጂደ አስ"ሱና በሚያምር አገላለፅ ሁሉንም ባቦች በመዳሰስ የደዕዋ ፕሮግራም በማድረግ የወሎዉን ደውራ በዚሁ ጨረሱ።ከወሎ ወደ አዲስ አበባ የደዕዋና የኮርስ ፕሮግራም በድጋሜ አድርገዋል።የአዲስ አበባውን ፕሮግራም ከጨረሱ በኋላ ወደ ቡታጅራ የተላያዩ ኪታቦችን በኮርስ መልኩ ለብዙ መሻይኾችና ኡስታዞች ወሎ ላይ ባስተማሩት መልኩ አስተምረዋል። ከቡታጅራ ከተመለሱ በኋላ ወደ ጂማ ዞን በሁለት ከተማዎች ላይ ወሎ ላይ ባስተማሩት መልኩ አስተምረዋል። ሸይኽ ኢትዮጵያ ላይ በዚህ መልኩ ሲያስተምሩ ከቆዩ በኋላ ወደ የመን መዕበር አቅንተዋል።የመን መዕበር በሰላም መድረሳቸውንም ለዶ/ር ሰዒድ ሙሳ በላኩት ድምፅ አረጋግጠናል። አልሀምዱሊላህ ሸይኽ ይህን ሁሉ ውጣ ውረድ ደከመኝ ሰለቼኝ ሳይሉ በዛ ስሙኝ ስሙኝ በሚልና ከምግብ እና ከመጠጥ በላይ በሚጣፍጥ አገላለፅ ሲያስተምሩን ስለቆዩ ለሸይኽ አልይ ምስጋናችን ከልብ ነው።ሸይኹን አላህ መልካም ስራቸውን እጥፍ ድርብ አድርጎ ይቀበላቸው። አሚን ይሄን ፕሮግራም እዚህ እንዲደርስ ሲወጡና ሲደክሙ የነበሩ ወንድሞች ለአብነት ያክል:– 1⃣ ወንድም አብዱልፈታህ (ኢብኑ ሙሐመድ ዘይን) ይሄን ሀሳብ ለወንድሞች በማማከር እና ሸይኽ አልዩ አር"ራዚሒ ቅርብ የሆኑ ወንድሞች ጋር በማውራት የዚህን ፕሮግራም እውን ይሆን ዘንድ ከመጀመሪያዎቹ አወለ ሶፍ ሊሰለፉ ከሚችሉ ወንድሞች ውስጥ ቀዳሚው ነው።አላህ ይቀበልህ ወንድሜ በአካል ባላውቅህም ከልቤ ነው የምወድህ ፣የማከብርህ፣የምሳሳልህ አላህ ይጠብቅህ ። 2⃣ ወንድም ሙሳ (ስሙን እርግጠኛ አይደለሁም) የሸይኽ አልዩ አር"ራዚሒ ቅርብ የሆነና ለዚህ ፕሮግራም መሳከት መሀል ላይ እንደ ሞተር ሆኖ የለፋና የደከመ ወንድም ነው። ወንድማቸን ሙሳ ከወንድም አብዱል ፈታህ እና ከሸይኽ አልይ ጋር መልዕክቶችን በመለዋወጥ ይህ እቅድ ወደ መሬት ይወርድ ዘንድ በሰፊው የለፋና የደከመ ወንድም ነው። አላህ የአንተን መሰል ወንድሞችን ያብዛልን። 3⃣ ወንድም አህመድ ኑር (አቡ ሻኪራ) ይህ ፕሮግራም ይሳካ ዘንድ የመን ያሉትን ወንድሞች (ከወንድም አብዱል ፈታህ እና ወንድም ሙሳ) እና ሀበሻ ያሉ ወንድሞች ጋር ጊዜውን እና ገንዘቡን መስዋት በማድረግ በተለያየ ሰዓት ሹራ በማድረግ የአንበሳውን ድርሻ የተወጣ ነፍስ ያለው ወንድማችን ነው። ይህ ወንድማችን ለደውራው የሚያስፈልጉ ኪታቦችን አህለል ኸይር በማፈላለግ ከ 154,000 ብር አውጥቶ ደውራው ላይ በነፃ ኪታቦቹ እንዲታደሉ ያደረገ ወንድም ነው። አላህ ይጠብቀው ብዙ ሀጃዎች አሉት ዱዓ አድርጉለት ከአይን ይጠብቅህ ወንድሜ አህመድ ኑር ! 4⃣ ዶክተር ሰዒድ ሙሳ ይህ ፕሮግራም ከታሰበበት ሰዓት አንስቶ ሸይኹ ወደ የመን እስኪመለሱ ድረስ የለፋ ፣የደከመ፣ለዚህ ፕሮግራም ሲል 23 ቀን ሙሉ ልጆቹን፣ቤቱን ፣ስራውን በመተው ከሸይኹ ጋር አብሮ በሄዱበት ሁሉ ጭርታ እንደይሰማቸው ያደረገ እና የሸይኹን ሙሉ ወጭ የሸፈነልን ውድ ኡስታዛችን ነው። ኡስታዙና ዱክቱር አላህ መልካም ስራህን ይቀበልህ ።በመልካሙ ሁሉ ጀሊሉ ይጠግንህ።ሀጃህንም ይሙላልህ። ሷሊህ ፣ ለኡማው ጠቃሚ፣ ፍሬ የሚያፈሩ እና የአይን ማረፊያ የሆኑ መልካም ፍሬዎችን ይለግስህ። እነ ቡኻሪ ሰዒድንም ሱና ላይ አንበሳ ለሱና የሚለፉና የሚደክሙ ፣ ለቢድዓ ደግሞ መጋዝ ጀባሩ ያድርጋቸው የአንተ አይነት መሰሎችን ያብዛልን ! 5⃣ የጀዕፈር ኢብኑ አቢ ጧሊብ የደዕዋና የቂርዓት ማዕከል ሀላፊዎች ፕሮግራሙ እንደይሳካ ጥረት ያደረጉ አካላቶችን እኛ ፍቃድ ያለን አካል ነን ።ፕሮግራሙ የእኛ ነው ሙሉ ሀላፊነት እንወሰዳለን በማለት ምንም እንቅፋት እንደይኖር ቀድመው በማመቻቸት ለዚህ ፕሮግራም የአንበሳውን ድርሻ የተወጣ ማዕከል ነው።ለሀላፊዎቹ ጀዛቸውን አላህ ይክፈላቸው። 6⃣ አቡ ሒበቲላህ፣አቡ አዩብ፣አቡ ማሂ፣አቡ ዒምራን ፣አቡ ሁዘይፋ፣አቡ ረያን ፣አቡ ሹራ፣አቡ ሀፍሷ ፣አቡ ሀሳን ፣አቡ ዑበይዳ፣ኑረዲን አል ዓረቢ እና ሌሎችም አሁን ላስታውሳቸው የማልችለው ወንድሞች ለዚህ ፕሮግራም የሚሆነውን ወጪ በማስላት ከራሳቸውም ከሌሎችም በማስተባበር የፋይናንሱን ወጭ የሸፈኑ ወንድሞች ናቸው። አላህ መልካሙን ሁሉ ያግራላቸሁ ❗️❗️ 7⃣ የኮንቦልቻ የአንሷር መስጂድ ጀማኣዎች: –የአንሷር ጀማኣዎች በጣም የሚያስቀኑና ቅንጅታቸው ልብን የሚያረጥብ ፣ክድሜያቸው በጣም ቆንጆ የሆኑ ወድ እና የተከበሩ ወንድሞች ናቸው። እኚህ ወንድሞች ሙሉ ከኢትዮጵያ ተጠራርተው የመጡ ወንድሞቻቸውን ደከመኝ፣ሰለቸኝ ሳይሉ፣ቤት፣ ንብረታቸውን እና ስራቸውን ትተው አምስት ቀን ሙሉ ምንም አይነት ክፍተት ሳይኖር እንግዶቻቸውን ተንከባክበው የሸኙ የወሎዎች አይን ማረፊያ ጀማዓዎች ናቸው። ጀማዓቸውን እና መስጂዳቸውን ከተንኮለኞች ሴራ አላህ ይጠብቅልን። 8⃣ ከተለያየ ቦታ የመጣችሁ መሻይኾች፣ኡስታዞች እና ወንድሞች በሙሉ የቦታው መራቅ ሳይገድባችሁ ጥሪያችንን አክብራችሁ፣ በሰዓቱ ተገኝታችሁ፣ በስነ-ስርዓትና በትዕግስት ፕሮግራሙን ስለተከታተላችሁ እንድሁም ድምቀታችን ስለሆናችሁ፤ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን። ሁላችሁንንም አላህ በሱና ላይ ያፅናንን። 9⃣ በወንድሞች ጥቆማ መሰረት ጉዳዩ የኛም ነው ብላችሁ ያላችሁን በመዘርጋት ፕሮግራሙ ያለምንም የፋይናንስና የቁሳቁስ እጥረት እንዳይከሰት ላደረጋችሁት ያልተቆጠበ ልግስና እና ድጋፍ ምስጋናችን ከልብ ነው ። አላህ ገንዘባችሁን በረካ ያድርግላችሁ። 1⃣0⃣ ለሶሻል ሚድያ ተጠቃሚ ወንድሞች ሲካሄዱ የነበሩ ፕሮግራሞችን በድምፅ በመቅዳት ጥራቱን ጠብቆ ፕሮግራሙ ላይ ላልተሳተፉ ወንድሞች እንዲደርስ እና ፕሮግራሙን በቀጥታ ስርጭት በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ለአለም ህዝብ ተደራሽ ስላደረጋችሁ ምስጋናችን ከልብ ነው።
