uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Kanalga Telegram’da o‘tish

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
899
Obunachilar
-224 soatlar
-167 kun
+2730 kun
Postlar arxiv
Repost from N/a
#— Backend Development Course (LayTech Solution) Coming Soon 🚀 Backend Developer ልትሆን ትፈልጋለህ/ጊያለሽ? ከዜሮ ጀምረህ Production-Ready Backend Developer ለመሆን የሚያስፈልጉህን ሁሉንም ክህሎቶች የምንሸፍንበት ኮርስ ! 💻🔥 📚 የምንማራቸው Technologies: 🟢 Node.js & Express.js — Scalable REST API መገንባት 🟢 PostgreSQL & Prisma ORM — Relational Database Design & Queries 🟢 MongoDB & Mongoose — NoSQL Database Modeling 🟢 Zod — Schema Validation ለ Type-Safe APIs 🟢 RabbitMQ — Message Queue & Microservices Communication 🟢 Authentication, Authorization, Error Handling, Deployment... እና ሌሎችም! 👨‍💻 ኮርሱ ለማን ነው? - Frontend developer የነበራችሁ Backend ውስጥ ጠልቃችሁ መግባት ለምትፈልጉ - Junior developers ወደ Job-ready ደረጃ መድረስ ለምትፈልጉ - Real-world project experience የምትፈልጉ ሁሉ 🎯 የምታገኙት: ✅ Real-world Projects (Portfolio-ready) ✅ Hands-on coding, ደረጃ በደረጃ ✅ Industry best practices ✅ Certificate of Completion ✅ Community & Support ከ mentors ጋር 📍 ቦታ: Online | 🕒 Flexible Schedule 🔗 ለበለጠ መረጃ : @laytechsolutions 🔁 ጓደኛህን አትርሳ — Share/Forward አድርግለት! #BackendDevelopment #NodeJS #ExpressJS #PostgreSQL #MongoDB #Prisma #RabbitMQ #LayTechSolution #EthioTech #ስራ_ፈላጊ #ኮደር

ግልፅ ውይይት በ ቀጥታ ስርጭት በ ኡስታዝ ኸድር አህመድ እና በሼይኽ አቡዘር መካከል። ብዙ ጠቃሚ አንገብጋቢ ርዕሶች አሉበት ይደመጥ ። ሙሉውን ለማዳመጥ ገብተው መከታተል ይችላል 👇 https://t.me/+IgpLkgtISs40ZDQ0 1: 028

መርህ አልባ የሆነ ግንኙነት ዉጤቱ መጨረሻዉ መባላት ነዉ ሚሆነዉ:: [አንድ ነን ብለዉ በቡጢ እንደተለያዩት ሰዎች] 🎙ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር አላህ ይጠብቀው "ሰዎች በበደልና በወንጀል ሲተባበሩ ሲረዳዱ ከፊላቸዉ ከፊሉን ይጠላል" ኢብኑ ተይሚያ https://t.me/NABAWITUBE

የታመመ ቤተሰብ ሲኖር ከሚደረጉ ሰበቦች 1. ዱዓእ፣ 2. ሩቃ፣ 3. ሶደቃ እና 4. ህክምና እነዚህ ሰበቦች በአላህ ፈቃድ ለህመምተኛው ይጠቅማሉ። በዚህ ላይ የምንችለውን እናድርግ። ነገር ግን ሰው ዱንያ ላይ ዘላለማዊ አይደለም። እና ሁሉንም ሰበቦች አድርሰንም አይቀሬውን የምንጋፈጥበት ቀን እንዳለ በቁርጥ እናውቃለን። ያኔ ላይድን/ ላትድን ይህን ሁሉ ገንዘብ ለህክምና ማውጣቴ የሚል ቁጭት ፈፅሞ ሊሰማን አይገባም። ዋናው ነገር በአላህ ላይ ተወክለን ሰበብ ማድረስ ነው። አላህ መዳንን ከወፈቀልን አልሐምዱ ሊላህ። አይቀሬው ከመጣም አልሐምዱ ሊላህ። የሙስሊም አደቡ ይሄ ነው። ደግሞም በእርግጠኝነት ያደረስነው ሰበብ ለኛ ባይታወቀንም በከንቱ የሚቀር አይደለም። ወይ በዱንያ ወይ ለአኺራ። አላህ የታመሙትን ያድንልን። የሞቱትን ይማርልን። የተጨነቁትን ይገላግልልን። ኣሚን። = የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/IbnuMunewor t.me/IbnuMunewor

• ህሊናህ ከሀብት ይበልጣል፤ ባህሪህ ከውበት ይበልጣል፤ ኢማንህ ከሁሉም ሀብት የላቀ ነው። እነዚህን ጠብቅ፣ የቀረውን አላህ ያስተካክላል። 𝐓𝐞» t.me/Ibnu_Teymya_Ye_Ewket_Maed
• ህሊናህ ከሀብት ይበልጣል፤ ባህሪህ ከውበት ይበልጣል፤ ኢማንህ ከሁሉም ሀብት የላቀ ነው። እነዚህን ጠብቅ፣ የቀረውን አላህ ያስተካክላል። 𝐓𝐞» t.me/Ibnu_Teymya_Ye_Ewket_Maed

👉 ኢላሂ ባልተስተካከለ ማንነቴ ለምትሰጠኝ አፊያ,ሪዝቅ,ድስታ እና ሰላም ለሁሉም ነገር ምስጋና ለአንተ የተገባ ነው!

​የሸሪዓ ዓላማዎች (መቃሲድ አል-ሸሪዓ) ​የእስልምና ሸሪዓ ዓላማዎችን (መቃሲድን) የተረዳ ሰው በርካታ ህጋዊ ጉዳዮችን ይረዳል፣ እንዲሁም የእነሱን ሳይንሳዊ እሴት ይገነዘባል። ​የሸሪዓ ዓላማዎች በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላሉ፦ 👉​አስገዳጅ/አስፈላጊ ዓላማዎች (ዶሩሪያት) 👉​አስፈላጊነታቸው መካከለኛ የሆኑ ዓላማዎች (ሐጂያት) 👉​የማስዋቢያ/የማሟያ ዓላማዎች (ተሕሲኒያት) ​1ኛ.አስገዳጅ/አስፈላጊ ዓላማዎች (ዶሩሪያት) ​እነዚህ በዲን (በሃይማኖት) እና በዱንያ (በዚህች ዓለም) ህይወት ውስጥ መረጋጋትን ለመፍጠር ፍጹም አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮች ናቸው። ሁሉም መለኮታዊ ህጎች (ሸሪዓዎች) እንዲጠበቁ የተስማሙባቸውን አምስቱን መሰረታዊ አስፈላጊ ነገሮች (አል-ዶሩሪያት አል-ኸምስ) ያጠቃልላል። እነሱም፦ 👉ሃይማኖትን መጠበቅ (ሒፍዙድ-ዲን) 👉​ነፍስን መጠበቅ (ሒፍዙን-ነፍስ) 👉​አእምሮን መጠበቅ (ሒፍዙል-አቅል) 👉​ንብረትን መጠበቅ (ሒፍዙል-ማል) 👉​ትውልድን/ዘርን መጠበቅ (ሒፍዙን-ነስል) ​1. ሃይማኖትን መጠበቅ (ሒፍዙድ-ዲን) ​ሸሪዓ ሃይማኖትን ለመጠበቅ በርካታ መንገዶችን ደንግጓል፦ ​አንደኛ መንገድ፦ ወደ ሃይማኖት ጥሪ ማድረግን (ዳዕዋን) ደንግጓል። ​ሁለተኛ መንገድ፦ በኢስላም እና በኢማንአርካኖች (ማዕዘናት) ማመንን ግዴታ አድርጓል፣ እንዲሁም የተውሒድ (የአላህ አንድነት) እና የኢሕሳን ትዕዛዛት መጥተዋል። ​ሦስተኛ መንገድ፦ ሃይማኖት እንዳይስፋፋ እንቅፋት በሆኑት ላይ ጂሃድን ደንግጓል። ​አራተኛ መንገድ፦ ሃይማኖቱን የቀየረን (ከእስልምና የወጣን/ሙርተድን) መግደልን ግዴታ አድርጓል... ወዘተ። ​አምስተኛ መንገድ፦ ሃይማኖትን የሚያጠናክሩ ተጨማሪ (ነዋፊል) አምልኮቶችንና መልካም ስራዎችን ለመስራት አበረታቷል። ​ስድስተኛ መንገድ፦ በሃይማኖት ግዴታዎች ላይ ጉድለት ለሚያሳይ ማንኛውም ሰው አስተማሪ ቅጣቶችን (ተዕዚራት) ደንግጓል... ወዘተ። ​ሰባተኛ መንገድ፦ ሃይማኖትን መከላከል፣ የባጠል (የሃሰት) ሰዎችን ብዥታ ማብራራት፣ ወሰን አላፊዎችንና አዛቢዎችን ማጋለጥ። ​2. ነፍስን መጠበቅ (ሒፍዙን-ነፍስ) ​ሸሪዓ የሰውን ነፍስ ለመጠበቅ በሚከተሉት መንገዶች መጥቷል፦ ​አንደኛ መንገድ፦ ሰውን መግደልን እርም (ሐራም) አድርጓል፤ ሆን ብሎ በደል በፈጸመ ላይ ቂያስ (የደም መመለስን) ወይም ዲያን (የደም ካሳን) ግዴታ አድርጓል። ሌላው ቀርቶ ጥበቃ በተደረገላት ነፍስ ላይ በጦር መሣሪያ መጠቆምን እንኳ ከልክሏል። ​ሁለተኛ መንገድ፦ ሆን ተብሎ ባልሆነ (ከፊል ሆን ተብሎ) እና በስህተት ለተገደለች ነፍስ የደም ካሳን (ዲያን) ግዴታ አድርጓል። ​ሦስተኛ መንገድ፦ ከፊል ሆን ተብሎ ወይም በስህተት ለተገደለች ነፍስ ከባድ ማስተሰረያ (ከፋራ) መክፈልን ግዴታ አድርጓል... ወዘተ። ​አራተኛ መንገድ፦ ጥበቃ የተደረገላትን የሙስሊም ያልሆነን ሰው ነፍስ (ለምሳሌ፡ በስምምነት፣ በፈቃድ ወይም በአደራ የሚኖሩ የውጭ ዜጎችን ነፍስ) ማጥቃትን እርም አድርጓል፣ እነሱን መግደልም የደም ካሳና ማስተሰረያን ያስከትላል። ​አምስተኛ መንገድ፦ ከነፍስ በታች ባሉ የአካል ክፍሎች ላይ የሚፈጸምን ጥቃት (ማጉደልን) እርም አድርጓል። ​3. አእምሮን መጠበቅ (ሒፍዙል-አቅል) ​ሸሪዓ አእምሮን ለመጠበቅ በሚከተሉት መንገዶች መጥቷል፦ ​አንደኛ መንገድ፦ አእምሮን የሚያስቱና የሚያደነዝዙ ነገሮችን (አልኮልና እፅዋትን) በሙሉ እርም አድርጓል። ​ሁለተኛ መንገድ፦ አስካሪ ነገር የጠጣን ሰው መቅጣትን ግዴታ አድርጓል። ​ሦስተኛ መንገድ፦ በሌላው ሰው አእምሮ ላይ ጉዳት ባደረሰ (አእምሮውን ባሳጣው) ላይ ሙሉ የደም ካሳ (ዲያ) እንዲከፍል ግዴታ አድርጓል... ወዘተ። ​አራተኛ መንገድ፦ አእምሮን የሚያሳድጉ የሃሳብ፣ የንፅፅር እና የጥልቀት ማስተንተን ተግባራትን አበረታቷል... ወዘተ። ​4. ንብረትን መጠበቅ (ሒፍዙል-ማል) ​ሸሪዓ ንብረትን ለመጠበቅ በሚከተሉት መንገዶች መጥቷል፦ ​አንደኛ መንገድ፦ በተፈቀዱ (ሐላል) መንገዶች ገንዘብ ለማግኘት መስራትን ደንግጓል። ​ሁለተኛ መንገድ፦ ማባከን እና ያለአግባብ ማውጣትን (ኢስራፍ እና ተብዚር) እርም አድርጓል። ​ሦስተኛ መንገድ፦ የሰውን ንብረት በሰረቀ ላይ የስርቆት ቅጣትን (ሀድ) ግዴታ አድርጓል። ​አራተኛ መንገድ፦ የሌላውን ሰው ንብረት ያጠፋ ሰው፣ ያንን ንብረት የመተካት/የመካስ ግዴታ አለበት። ​አምስተኛ መንገድ፦ የሰዎችን ገንዘብ ያለአግባብ መብላትን ወይም መበደልን የሚያስከትሉ መንገዶችን በሙሉ እርም አድርጓል፤ ለምሳሌ፡ አራጣ (ሪባ)፣ ቁማር (መይሲር)፣ ማጭበርበር (ገረር) እና ጉቦ።

ታላቁ ታቢዒይ ሙሓሪብ ኢብኑ ዲሳር አላህን በሚያወድሱበትና ዱዓእ በሚያደርጉበት ጊዜ እንዲህ ይሉ ነበር፡- √ አላህ ሆይ! እኔ አንተ ያሳደግከኝ ያ ትንሽ ባሪያህ ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን! √
ታላቁ ታቢዒይ ሙሓሪብ ኢብኑ ዲሳር አላህን በሚያወድሱበትና ዱዓእ በሚያደርጉበት ጊዜ እንዲህ ይሉ ነበር፡- √ አላህ ሆይ! እኔ አንተ ያሳደግከኝ ያ ትንሽ ባሪያህ ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን! √ እኔ አንተ ያበረታኸኝ ያ ደካማ ባሪያህ ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን! √ እኔ አንተ ያብቃቃኸኝ (ያከበርከኝ) ያ ድሃ ባሪያህ ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን! √ እኔ አንተ ሀብት የለገስከኝ ያ ሚስኪን ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን! √ እኔ አንተ ትዳር የሰጠኸኝ ያ ላጤ ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን! √ እኔ አንተ ያጠገብከኝ ያ የተራብኩ ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን! √ እኔ አንተ ያለበስከኝ ያ የተራቆትኩ ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን! √ እኔ አንተ አብረኸኝ የሆንክ (የጠበቅከኝ) ያ ተጓዥ ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን! √ እኔ አንተ በሰላም የመለስከኝ ያ ርቄ የነበርኩ ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን! √ እኔ አንተ መጓጓዣ የሰጠኸኝ (ያሳፈርከኝ) ያ እግረኛ ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን! √ እኔ አንተ የፈወስከኝ ያ በሽተኛ ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን! √ እኔ አንተ የለገስከኝ ያ ጠያቂ ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን! √ እኔ አንተ ጥሪውን የተቀበልከው ያ ዱዓእ አድራጊ ነኝ፤ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይሁን! 🤲ጌታችን ሆይ! ምስጋና ሁሉ ለአንተ የተገባ ነው... ጌታችን ሆይ! በምስጋና ላይ የተደራረበ ምስጋና ለአንተ ይሁን! 📚(ምንጭ፦ "አት-ተሀጁድ ወቂያሙል ለይል" — በኢብኑ አቢ አድ-ዱንያ፡ 45) https://t.me/alruqyehsheriyeh https://t.me/alruqyehsheriyeh

بسم اللــــه الرحمـــــــــن الرحيم. 📩 الســــــــــــؤال:- يقول الســـــائل: ما هي كفارة اليمين؟ 📝 الإجـــــــــابة :- كفارة اليمين مذكورة في قوله تعالى {لايُؤَاخِذُكُمُ اللَّهُ بِاللَّغْوِ فِي أَيْمَانِكُمْ وَلَٰكِن يُؤَاخِذُكُم بِمَا عَقَّدتُّمُ الْأَيْمَانَ ۖ فَكَفَّارَتُهُ إِطْعَامُ عَشَرَةِ مَسَاكِينَ مِنْ أَوْسَطِ مَا تُطْعِمُونَ أَهْلِيكُمْ أَوْ كِسْوَتُهُمْ أَوْ تَحْرِيرُ رَقَبَةٍ ۖ فَمَن لَّمْ يَجِدْ فَصِيَامُ ثَلَاثَةِ أَيَّامٍ ۚ ذَٰلِكَ كَفَّارَةُ أَيْمَانِكُمْ إِذَا حَلَفْتُمْ ۚ وَاحْفَظُوا أَيْمَانَكُمْ ۚ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمْ آيَاتِهِ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ} [المائدة:٨٩] . فهذه الآية فيها بيان كفارة اليمين، وقد ذكر الله عز وجل فيها وبيَّن أن المسلم مخير بين ثلاثة أمور فإن لم يقدر عليها ينتقل إلى صيام ثلاثة أيام، وهي إطعام عشرة مساكين من أوسط ما تطعمون أهليكم أي المعتدل ليس بالرديء ولا بالجيد، أي لا يلزمه من أجود الجيد، ولا يجزئه من الرديء. أو كسوتهم، إذا اخترت كسوة المساكين فلك ذلك، عشرة مساكين يشترط أن يكونوا عشرة في الإطعام وفي الكسوة. أو تحرير رقبة، فمن لم يجد فصيام ثلاثة أيام ، فإن لم يقدر على الثلاثة الأمور الأولى انتقل إلى الصيام. ويخطئ  بعض  الناس فينتقل إلى الصيام، وهو قادر على الإطعام ولا يجزئ ذلك، ومن فعل ذلك فصومه نافلة له، ولا يجزئه عن الكفارة، وعليه أن يرجع إلى الإطعام أو الكسوة أو العتق. إطعام عشرة مساكين يشترط فيهم العدد أن يكونوا عشرة وأن يكون طعامًا ليس برديء {وَلَا تَيَمَّمُوا الْخَبِيثَ مِنْهُ تُنفِقُونَ وَلَسْتُم بِآخِذِيهِ إِلَّا أَن تُغْمِضُوا فِيهِ ۚ } [ البقرة:٢٦٧]. ولم يشترط أحد من العلماء أن تكون وجبة جاهزة مطبوخة، بل إذا دفعت إليه الدقيق أو البر أو الأرز فيجزئ عند جميع العلماء. ولا يشترط في الإطعام أيضًا أنه يأكله وجبة واحدة أعني إذا أعطيته الحب، له أن يأكل بعضه اليوم وبعضه في الغد وله أن يهدي منه قد أطعمته بمعنى أعطيته الطعام، ثم هو إن بدا له أن يهدي لغيره أهدى وإن أكل منه أكل وإن أشرك معه غيره فلا بأس، وأقل الإطعام مدٌّ لأنه أقل ما ورد في الإطعام بالشرع . واستدل العلماء بحديث الرجل المعسر الذي واقع امرأته في نهار رمضان، أن النبي صلى الله عليه وسلم أتي بمكتل فيه خمسة عشر صاعًا، فقال: خذ هذا فأطعم به المساكين. قال العلماء: هذا أقل ما ورد في الإطعام، خمسة العشر صاعا إذا وزعت على ستين مسكينًا يصيب كل مسكين ربع صاع يعني مدا، الصاع أربعة أمداد، وعلى التقدير في هذهِ الأيام النصف الكيلو يجزئ ، أقل ما يجزئ هو نصف كيلو من الدقيق أو البر أو العدس أو الأرز أو نحو ذلك. وما يتعلق بالكسوة اختلف العلماء في تقدير كسوة المسكين والصحيح في هذه المسألة أن كل ما يطلق عليه كسوة يجزئه سواء كساه قميصاً أو جبة أو سراويل أو عمامة، كلها كسوة على الصحيح، وهو اختيار الإمام الشافعي رحمه الله. واختار بعض العلماء أنه يكسوه ما تصح به الصلاة يعني إزارًا أو رداءًا أو قميصاً أو نحو ذلك، وهذا هو الأحوط. الأحوط أن يعطيه ما تصح به الصلاة، أي ما يستطيع أن يصلي بها ،  ولكن لا نستطيع أن نجعل ذلك شرطًا، وإنما ما يطلق عليه كسوة تجزئ ولو كساه عمامة. وعتق الرقبة معلوم وهو عتق العبيد سواء كان ذكرًا أو أنثى. وصيام الثلاثة الأيام إذا لم يقدر على الثلاثة الأمور فينتقل إلى الصيام والصحيح أنه لا يشترط فيه التتابع، لأن القرآن بلغنا بالإطلاق (فصيام ثلاثة أيام) وما جاء في قراءة ابن مسعود وأبي بن كعب (فصيام ثلاثة أيام متتابعات) فهي قراءة منسوخة نسخت بالعرضة الأخيرة التي نزلت بدون التقييد (متتابعات) ،فدل على أن الحكم على الإطلاق لأن الله سبحانه وتعالى أبقى لنا في القرآن المطلق، ونسخ المقيد وعلى هذا فلا يشترط التتابع. وما يتعلق بالإطعام إن أطعم نصف صاع فهو أحوط وأولى لاسيما إن كان موسرا، لأن النبي صلى الله عليه وسلم في فدية الحاج أمر من ارتكب المحظور أن يفدي بإطعام ستة مساكين لكل مسكين نصف صاع، ولذلك نختار لمن كان قادرا أن يزيد على المد، نختار له أن يطعم نصف صاع لكل مسكين، ويساوي نحو كيلو من البر والأرز، نسأل الله الهدى والسداد. #فتاوى_الفقه #فتاوى_في_الأيمان_والنذور ----------------‐------------------- للاشتراك في فتاوى فضيلة الشيخ محمد بن حزام عبر التيلجرام:-       https://t.me/ibnhezam وباللغة الإنجليزية:- http://t.me/ibnhezamen وعبر الواتساب :-  https://chat.whatsapp.com/20UEwOUrfsVJ1h5rmK1sHx

_የሱና እህቶቸ___ አልሀምዱሊላሂ ይመስገን ጌታችን በማይቆጠረው ኒዕማው ላመቻቸን የነብዩ ኡመት አድርጎን በእዝነቱ በሱናቸው ግርጌ አስውቦን ሙሚቱ በጅልባብ በኒቃብ ደምቀን  ልንራመድ ትዛዝ አመጣልን  መጠጊያችን ሶመድ የነብያት መሪ ኢማሙል ቃኢሚን አሏህ ነገራቸው ተሸፈኑ እንዲሉን ውበት ነው ማረግ ነው ለሱና መመረጥ በተውሂድ ተውቦ በአንድነት ማጌጥ የሱናዋ እህቴ  የመንሀጇ ንግስት ሁሌ ወድሻለሁ እያየሁ በስስት አገናኘንና የመንሀጅ የአቂዳ ረመጥ አለያየንና ያገር አቀማመጥ በሙሀባሽ ግርጌ ሁሌ ስትናፍቂኝ አለሁ ዛሬም ድረስ ልቤን ስትደልቂኝ በርቀት ከንፌ ደስታሽን ስሰማ ዳዕዋ ወጥነሻል  በጠንካራው ማማ አምልኩት በማለት አረሂሙ ሯህማ በቂርአት ደምቀሽ ኢልምን ስትሾፍሪ ከማዳም ቤት ሁነሽ ድካምን ሳትፈሪ በአንድ እጅሽ ስትሞጥይ በአንዱ ስትሰሪ እጅጉን ደስ አለኝ የብርታትሽ ድግሪ የመንሀጅ እህቴ የሱናዋ ኮከብ በአንድነት ደምቀን በመሀባው መርከብ እንድንዘያየር ያሳካልን ያ ረብ ወደድኩሽ ምን ላድርግ እንዴት ይሻለኛል በድንገት ስትጠፊ ድብርት  ይጫነኛል የማረከኝ ወኔሽ የጥንካሬሽ አውድ ትምርት ሁኖኛል ጀግና ነሽ የኔ ውድ በአረብ በረሀ  በሚንቀለቀለው በብርዱ ታፍነሽ በሚቆራጠመው ቁመሽ ተገትረሽ በአረቦች ስራ ሳይበግርሽ ቅንጣት የምሽቱ ዳራ ሳትንገዳገጂ ልንክ እንደተራራ ትቀስሚያለሽ እውቀት ኢልምሽ እንዲያፈራ የአንችን ገድል ታሪክ የወኔሽን ማጀት አይዘልቀውምና የቃላት ቅንጅት አሏህ ይጠብቅሽ ልበልሽ ጠቅልየ የአኼራ እህቴ ውስጤ ነሽ እምዬ ሀገርም ያላችሁ ባህር ወዳ ማዶ በናንተ ሰቀቀን በናፍቆት ማገዶ ልባችን ሊያልቅ ነው ተንዶ ተንዶ እስገምንገናኝ  ጀልባው ተሰርጉዶ የተጋረደብን ሂጃቡ ተቀዶ አትራቁን በጭራሽ በተቻለ መጠን እንወዳችኋለን ባህሩን አቋርጠን በመንሀጃችሁ ላይ_ ሳትንሸራተቱ በተውሂድ ደምቃችሁ _ሽርክ ሳትወዝቱ ሱንዩን አቅፋችሁ _ቃሚ ሳትገዝቱ አድሩስ ሳታጨሱ _ ዱቤ ሳትገትቱ በሱና ደምቃችሁ ኒቃብ ሳታወልቁ በኢስላም መርህ ላይ ከፈሩ ሳትወልቁ ከፀና አቋማችሁ ሳትነቃነቁ ጠብቁኝ አልቀርም በናፍቆት ሰስቸ በርቱ የኔ ጀግኖች ውድ ንግስቶቸ ደግሞም ታምራለችሁ የሱና እህቶቸ 🔷ከምወዳችሁ እህታችሁ ኡሙ ሓቲም https://t.me/+o7ZrQFQjILVhNDVk https://t.me/+o7ZrQFQjILVhNDVk

ሰውየው መንሃጅ ብቻ ሳይሆን ቁጥርም ይምታታበት ጀመር ማለት ነው! ሚስኪን!

ቆይ አልገባኝም ሀራ እኛ የምናቀው ከወልደያ በታች ያለው ነው? ወይስ ሌላ ክልል ያለ ሀራ ነው? አረ አደናገራቹህን ጎበዝ! ለነገሩ ፊቱንም ውሸት መገለጫህ ስለነበርና አሁን ደግሞ የተላተምክበት ጀማዓ
ቆይ አልገባኝም ሀራ እኛ የምናቀው ከወልደያ በታች ያለው ነው? ወይስ ሌላ ክልል ያለ ሀራ ነው? አረ አደናገራቹህን ጎበዝ! ለነገሩ ፊቱንም ውሸት መገለጫህ ስለነበርና አሁን ደግሞ የተላተምክበት ጀማዓ የውሸት ማሽን ስለሆነ በዚህ ልክ መቀደድህ ብዙም አይደንቅም። የቤቱ አባዎራዎች እነአብዱል ሀሚድ ውሸት ጌጣቸው ከሆነ የልጆቹ በዚህ ልክ መሆን አያስደነግጥም። እንደ አባባል "መምህሩ ከፈሳ ተማሪው ይቀዝናን ይባላን" ገጣሚው እንዲህ ይላል፦ إذا كان رب البيت بالدف ضاربا فشيمة أهل البيت كلهم الرقص የቤቱ ባለቤት ከሆነ ዲቢ ወጋሪ፣ ቤተሰቡ  ሁሉ   ይሆናል  ጨፋሪ፣ አሁን እንደዚህ አይነት ፈጣጣ ውሽት ለምን አስፈለገ? ይህችን ቦግ እልም የምትለውን ጀምዓችሁን በውሸት ለመጠበቅ? እኛ እንደዚህ ብዙ ነን ጧሊበል ኢልሙን ሁሉ ይዘነዋል አብሽሩ ሁሉም ከኛ ጋር ነው እያለ በውሸት ነጋሪት ከታች ላለው ጀሌ ሞራል ለመስጠት? ይሄኮ ያረጅ ፋሽን ነው። ወይስ የለተምያ እውቅና የተሰጠው ሰው አንድ በአስር ነው የሚባዛው!? أَلَيْسَ مِنْكُمْ رَجُلٌ رَشِيدٌ = t.me/Multeka_Selefiyin t.me/Multeka_Selefiyin

📢 አስደሳች ዜና! ከዳሩል ዒልም የቁርአን ሒፍዝ እና የተርቢያ መዕከል 💎 ዳሩል ዒልም መርከዝ ለመጪዉ ክረምትና በጋ በአዳሪ መርሃግብር ተማሪዎችን ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቆ በምዝገባ ላይ ይገኛ
📢 አስደሳች ዜና! ከዳሩል ዒልም የቁርአን ሒፍዝ እና የተርቢያ መዕከል 💎 ዳሩል ዒልም መርከዝ ለመጪዉ ክረምትና በጋ በአዳሪ መርሃግብር ተማሪዎችን ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቆ በምዝገባ ላይ ይገኛል። ☑️ የመመዝገቢያ መስፈርቶች፦ 📍ጾታ፦ ለወንዶች ብቻ (አዳሪ) 📍 እድሜ፦ ከ10 - 20 ዓመት 📍 ጤንነት፦ ከማንኛውም በሽታ ነፃ የሆነ 📍 ስነ-ምግባር፦ለመርከዙ ህግና ደንቦች ተገዢ የሆነ 📍 ፍላጎት፦ ለመቅራት ከፍተኛ ፍላጎት ያለው 📍ክፍያ፦ ወርሃዊ ክፍያን መክፈል የሚችል ☑️ የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች፦ 📌 የቁርአን ሒፍዝ (በቃል መያዝ) 📌 የቁርአን ነዘር (ንባብ) እና ሙራጀዓ (ክለሳ) 📌 ቃዒደቱን ኑራኒያ እና የተጅዊድ ትምህርቶች 📌 የተለያዩ የዲን ኪታቦች ☎️ ለምዝገባ እና ለበለጠ መረጃ፡ +251911171786 | +251910034682 +251947224231 | +251970092357 በቴሌግራም ለመመዝገብ ይህን ይጫኑ👈 በዋትስ አፕ  ለመመዝገብ ይህን ይጫኑ👈          የቴሌግራም አድራሻ፡ 🔗https://t.me/darulilmmerkezofficial 🔗https://t.me/darulilmmerkezofficial 🏢 አድራሻ: አንፎ 105 ከዘቢዳር ሆቴል ጀርባ

#ጥያቄ_እና_መልስ ክፍል 4 33- ዑመር ኮምቦልቻ: “ውሃብዮች ከሚያመልኩት ጌታ ሙፍቲን የሚያመልክ ይሻላል” ብሏል። ሙስጦፋ ዐብደላህ ደግሞ: “እሱን ሙስሊም ነው ያለ ሁሉ ካፊር ነው፣ ዑዝር ቢል ጀህል ይሰጠዋል ያለ አካል ካፊር ነው” አለ። “ዑዝር ቢል ጀህል የለም” ያሉ ዑለሞች እንደዚህ ብለዋልን? (0:18) 34- ሙስጦፋ ዐብደላህ ከሱና ሰው ይመደባልን? (12:31) 35- በሃገራችን በዳዒ ደረጃ ያሉ ዋና ዋና ኢኽዋኖች እነማን ናቸው? ከሱና መርሆዎች ውስጥ የኻለፉትንም ቢጠቅሱልን? (17:15) 36- አንድ ሰው ሰለፊይ ነህ ወይ ሲባል አዎ ብሎ ይመልሳል። ነገር ግን ከሁኔታው ሰለፍዮችን የሚገልፅ ነገር አያንፀባርቅም። እኛ ሌላ ነገር እንድንጠረጥር አደረገን። መጠራጠራችን ወንጀለኛ ያደርገናል ወይ? (25:18) 37- ከኢኽዋኖች መስጂድ ደዕዋ ተጋብዘን ደዕዋ ብናደርግ ችግር አለው ወይ (28:38) 38- ዑዝር ቢል ጀህልን በተመለከተ ሸይኽ ፈውዛን ሁለት አቋም አላቸው። የሙስጦፋ ጀማዓዎች የሚመስላቸውን ነው የያዙት። ይሄን በተመለከተ ምክር ብትለግሰን (32:18) 39- መርሳ አካባቢ ስላሉ ኢኽዋኖች ቢነገር። ወጣቶችን ዐቂዳ ከመቅራት አዘናግተዋልና ወደፊት የነሱን አቋም እንደሚከተሉ ግልጽ ነው። (36:56) 40- ቁርኣን በተጅዊድ አልቀራሁም። የዐቂዳና የመንሃጅ ኩቱቦችን ቀርቻለሁ። መድረሳ ላይ ባስተምር ችግር ይኖረዋልን? (38:40) 41- ሙስጦፋ: ዑዝር ቢል ጀህል አለ ከሚል ሰው ጋር መስጂድ መስራት አይቻልም ይላል። ስለዚህ ነገር ምን ትለናለህ? (39:45) 42- እኔ ሙስጦፋን ነበር የምከታተለው። ባለቤቴ በዛ እንዳትገቢ ብሎ ከለከለኝ። እኔም ትንሽ ተጨቃጨቅኩትና መጨረሻ ላይ እሽ አልኩት። ይሄ እንዴት ይታያል? (41:00) t.me/Ustaz_Kedir_ahmed_2

5️⃣ ጥያቄ እና መልሶች 🤏
➊.ሰለ ኡዝር ቢልጀህል አብራሩልኝ❔ ❷.የሱና ሰዎችን የሚያከፍር አካልን መውረስ ይቻላልን❔ ❸.ጥያቄዎ ረጅም ሰለሆነ መልሱን ያዳምጡ ..🤝 ❹.አንድ ሰው ጠንቋይ ዘንድ ሄደ ከዚያም ጠየቀው የአርባ ሌሊት ሶላት ተቀባይነት የለውም ሲባል እንደት ነው❔ ❺.በገጠሩ  አካባቢ ስለዲናቸዉ ሳይማሩ በጂህልና ጊዜያቸዉን ያሳለፉ ሰዎች ከዛም ከአመታቶች በሗላ በልጆቻቸዉ ሰበብ ሽርክንም ተዉ ሰላት መስገድ ጀመሩ ሶላትን ሲሰግዱ ግን አህካሙን እና ሸርጡን አሟልተዉ አይደለም  ከሞላ ጎደል ነዉ አሏሁሙስተዓን አላህ ይዘንላቸዉ እና እነርሱ ያረዱት ሀላል ይሆናልን እርዲን መሃለል ይችላሉ❔
👤በኡስታዝ አቡ ሓቲም ኸድር አህመድ
📱 t.me/Ustaz_Kedir_ahmed_2

ሸይኽ ሙሐመድ ሸይኽ ------------------------- 👉ታዋቂው ኢትዮጵያዊው ዓሊም ነሕዊይ ኡሱሊ አቡ-ዓብደልጀሊል ሙሐመድ ኢብን ዓሊ ቢን አደም ቢን ሙሳ አል-ሐበሺይ (ረሒመሁሏህ) ሀገራቸው ላይ ባሉ በአንዳንድ ወዳጆቻቸው ሸይኽ ሙሐመድ ሸይኽ በመባል ይታወቃሉ ◆ትወልድና ትምህርት ✅ሸይኹ ረሒመሁሏህ የተወለዱት በሐገራችን በሰሜኑ ክፍል በቀድሞው የወሎ ክፍለ ሀገር ወረሂመኑ አውራጃ በ1366 ዓ.ሂ አቅራቢያ ነበር። የዲን ዕውቀትን 'አሊፍ' ብለው አባታቸው ላይ ቁርኣን በመቅራት በመጀመሪያ ሸይኽ ሙሐመድ ገዩ (ረሂመሁሏህ) ዘንድ አክትመዋል። በመቀጠልም ከአባታቸው ሸይኽ አሊ አደም ሙሳ (ረሂመሁሏህ) እና ከሌሎችም ታዋቂ መሻይኾች እንደ ነሕው፣ ሶርፍ፣ በላጋ፣ ኡሱል፣ መንጢቅ፣ ሐዲስ፣ ፊቅህ እና ሌሎችም ዘርፎች ላይ የጠለቀ ዕውቀትን በጊዜው አሉ ከሚባሉ የሀገራችን መሻይኾች ተምረዋል። ✅ሸይኹ በሀገራችን ኢትዮጵያ ሳሉ ቁርአንን ከመሀፈዛቸው በተጨማሪ እንደ አልፊየቱ ኢብን ማሊክ እና አልፊያ አስ-ሱዩጢ ያሉ መትኖችንና ግጥሞችን በቃላቸው ሸምድደዋል። እንዲሁም ከበርካታ መሻይኾቻቸው ለብቁነታቸው ምስክርነት/ሸሀዳ ተችሯቸዋል። ◆ስደት ✅ከዚህም በዃላ ሸይኽ ሙሐመድ ዓሊ አደም (ረሂመሁሏህ) በወቅቱ የነበረውን የኮሚኒስት መንግጊ(ደርግ) በመሸሽ ወደ መካ-ሳዑዲ ዓረቢያ ተሰደዱ። ይሁንና በጉዟቸው ወቅት በከፊል መሻይኾቻቸው የተሰጣቸውን ሸሀዳ በእጃቸው ባለመያዛቸው ምክንያት በተማሪነት መልኩ መካ ውስጥ በሚገኝ መድረሳ የተወሰነ ጊዜ ቆይታ አድርገዋል። በመቀጠልም በወቅቱ በሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ ኢብኑ ባዝ ወደሚመራው ዳረል ሐዲስ አቅንተው ለመማር ፈተና ቢወስዱም ያስመዘገቡት ውጤት በሰዓቱ የነበሩ የዳረል ሐዲስ አመራሮችን አስደምሞ እኒህን ለመማር የመጡ ድንቅ ሸይኽ መምህር እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።ከዛን ስዓት ጀምሮ ህይወታቸው እስካለፈችበት ጊዜ ድረስ በዳረል ሐዲስ እና በመስጂድ አለ-ሐረም ለበርካታ ዓመታት ራሳቸውን ለዒልም እና ለፈላጊዎቹ ተሰጥተው አስተምረዋል። ◆ከአሽዓሪያ ወደ አህሉ-ሱና ✅ሸይኹ (ረሂመሁሏህ) በተለያዩ ድምፆቻቸው ከልጅነታቸው ጀምሮ ለሐዲስ ትልቅ ፍቅር እንዳላቸው ከመግለፃቸውም ባሻገር በደረስነት ጊዜያቸውም እንደ ሌሎች ሰዎች ባደጉበት የሐነፊያ መዝሀብ ከመገደብ ይልቅ መረጃ (ቁርዐን ሐዲስ) የሚደግፈውን አካሄድ ይመርጡ እንደነበር ይናገራሉ። ሸይኹ ወደ መካ ከተሰደዱ እና ዳሩል ሐዲስ ከገቡ በዃላ የነ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ፣ ኢብኑል ቀይም አልጀውዚይ እና ሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲልወሀብ ኪታቦችን ሲያገላብጡ በሐገራቸዉ ሳሉ ከተማሯቸው የዐቂዳ ትምህርቶች ጋር የሚጋጩ ነገሮች እንዳገኙ ይናገራሉ። እናም ቀድሞም ያደርጉት እንደነበረው ሁሉ ትክክለኛ መረጃ ያለውን ሲፈትሹ አሁን ያነበቧቸው ኪታቦች ትክክል ሆነው ማግኘታቸውን ይናገራሉ። ✅ሸይኹ ወደ መካ ከመጡ በዃላ የተለያዩ ታላላቅ ዓሊሞችን ኪታብ አገላብጠው አንብበው የያዙትን አቋም ሲናገሩ ... “በሀገሬ ሳለሁ ከአሽዓሪያ መሸይኾቼ የተማርኩትንና አምንበት የነበረውን ዓቂዳ በመተው ራቅኩት” ይላሉ። ✅ሸይኽ ሙሐመድ አሊይ አደም (ረሂመሁሏህ) አስከትለውም “አባቴን ለመጠየቅ ወደ ሀገሬ በሄድኩ ጊዜ አንድ ሰው 'አንተ ዉሀቢይ ሆነሃል' አለኝ። 'የለም፣ እኔ መረጃውን ነው የምከተለው ፤ እንደምታውቀው ወደ መካ ከመሄዴም በፊት ትክክለኛውን መረጃ ነበር የምከተለው አልኩት። 'አዎ እሱን አውቃለሁ ማጥበቅ ላይ ጨምረኻል' አለኝ። እኔም ምነው ኢማሙ ሻፊዒ በዒራቅ እና ሒጃዝ ሳሉ አንድ መዝሀብ (አቋም) እንደነበራቸውና ወደ ግብፅ ሄደው ብዙ ማስረጃነን ያገኙ ጊዜ የቀድሞውን መዝሀባቸውን እንደተው አና አዲስ መዝሀብ እንደመሰረቱ አታውቅም እንዴ? ልክ እንደዚሁ እኔም ከሀገሬ ሰዎች የተሰወረን ማስረጃ ያገኘሁ ጊዜ ተከተልኩት ፤የሚያስይዘውንም ሰራሁበት፤ ይህ እድሜ ልኬን የምሄድበት አካሄድ ነው ኢንሻአላህ' አልኩት”ሲሉ ይናገራሉ። ◆ስራዎቻቸው ✅ሸይኽ ሙሐመድ አሊይ አደም አል-ሐበሺይ በተለያዩ የሸሪዓ እውቀት ዘርፎች በርካታ ኪታቦችን ፅፈዋል።በተለይ በሐዲስ ዘርፍ ያበረከቷቸው ኪታቦች ጎልተው ይወጣሉ። ከነዚህም መካከል የሶሒሕ ሙስሊም ሸርሕ የሆነውን البحر المحيط الثجاج شرح صحيح مسلم بن الحجاج በሃምሳ ሙጀለድ/ቅፅ ሲያዘጋጁት ፣ የሱነን አነሳዒ ሸርሕን زخيرة العقبى في شرح المجتبى በአርባ ሁለቱ ሙጀለድ ፅፈውታል።እነኚህ ሸርሖች የሸይኹን የዒልም ምጥቀት ለዓለም ያሳዩ ህያው ምስክሮች ሁነው ይታያሉ። ✅እንዲሁም በሀዲስ እና በሌሎችም ዘርፎች ከ30 በላይ በርካታ ኪታቦችን አሳትመዋል ◆የዑለማኦች አድናቅቶ ✅ታዋቂው ሙሐዲስ (የሐዲስ ሊቅ) ሸይኽ ናሲሩ-ዲን አል-አልባኒይ (ረሂመሁሏህ) ስለ ነሳዒ ሸርሕ ዘኺረቱል ዑቅባ ሲናገሩ “ይህን የመሰለ የነሳዒ ሸርሕ አላውቀውም” ብለዋል። ✅ከሸውካኒ በመቀጠል የየመኑ ሙሐዲስ በመባል የሚታወቁት ዓሊም ሸይኽ ሙቅቢል አል-ዋድዒይ (ረሂመሁሏህ) ስለ ዘኺረቱል ዑቅባ “ይህ ኪታብ የሐፊዝ ኢብን ሐጀር 'ፈትሑል ባሪ' አይነት ነው ...ጧሊበል ዒልሞች ይህ ታላቅ ኪታብ ለማግኘት እንድጥሩ እመክራለሁ። በዚህ ዘመን ያለ ሙሐዲስ ሁሉም ይህን የመሰለ ሸርህ እንዲያመጣ እጠይቃለሁ” ብለው ነበር። ✅የዚህ ዘመን የጀርሕ እና የተዕዲል ኢማም የሆኑት ታላቁ ዐሊም ሸይኽ ረቢዕ ቢን ሓዲ አል-መድኸሊይ (ረሒመሁሏህ) ደግሞ ሸይኽ ሙሐመድ አሊ አደም 'በሁሉም ዘርፍ ዐሊም ናቸው ሲሉ መስክረውላቸዋል። ✅ሸይኹን ከእነዚህም ውጭ ያሉ በርካታ ዑለሞች አወድሰዋቸዋል ለምሳሌ ሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛን፣ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሒዛም፣ ሸይኽ ሷሊህ አል-ዑሶይሚ እና ሌሎችም... ሸይኹ እንዲህም ተገጥሞላቸዋል . يـا سائلي عن عالم الأحابشي ..... اسمع مقالي سمع ذي إنعاشي فـالـولـوي إمـام أهـل زمـانـهـم.... من غير ما شك ولا إغباش جـمـع الـعـلـوم أصـولـهـا وفـروعـهـا.... مع نظمها في غاية الإدهاش بـحـر بـعـيـد غـوره ونـطـاقـه.... قد عم كل السهل والأحراش 👉ሸይኽ ሙሐመድ ዐሊይ አደም አላህ ይዘንላቸውና የበርካታ መሻይኾች ሸይኽ የሆኑ የዒልም ባህር ናቸው። والشيخ رحمه الله .. توفي الخميس21 صفر 1442 الموافق لـ 8 أكتوبر 2020 .. ودفن في مقبرة شهداء الحرم في حي الشرائع بمكة. رحمه الله تعالى واعلى درجته في عليين

እውነተኛ የሴት ልጅ ነፃነትና ጥበቃ ሊረጋገጥ የሚችለው ክብሯን ከፍ ባደረገው፣ ከውርደትና ከብልሽትም ጠብቆ በማኅበረሰቧ ውስጥ የተከበረችና ውድ ዕንቁ እንድትሆን ባደረጋት የኢስላም ሸሪዓ ጥላ ስር ብቻ ነው። 📌 قـ✑ــال العلامــة صـالح الفــوزان حفظــہ اللـہ تعـالـﮯ : ☜ المــرأة لا تڪـون حــرة إلا بالتــزام الأحڪـام الشــرعية ⇦ الشــر؏ حــررها مـن الهــوان حــررها مـن الفســاد حــررها مـن ڪـل رذيلـة ❀ ◄ ضبطها ✿ ◄ ڪرمها ❀ ◄ عززهـا ✿ ◄ صانهـا 📑 شـرح ڪـتاب الفتـن والحـوادث [ صـ 34 ] "አንዲት ሴት ነፃ ልትሆን የምትችለው የሸሪዓዊ ድንጋጌዎችን (አህካሞችን) ሙጥኝ ብላ ስትይዝ ብቻ ነው። ​⇦ ሸሪዓ ከውርደት ነፃ አውጥቷታል፣ ከብልሽት ነፃ አውጥቷታል፣ ከማንኛውም መጥፎ ምግባር (ርኩሰት) ነፃ አውጥቷታል። ​❀ ◄ ስነ-ስርዓት አስይዟታል ✿ ◄ አክብሯታል ❀ ◄ ልዕልናን ሰጥቷታል ✿ ◄ ጠብቋታል ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን ​📑 [ሸርሕ ኪታብ አል-ፊተን ወል-ሐዋዲሥ — ገጽ 34] t.me/durusuabihizam t.me/durusuabihizam