uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

Відкрити в Telegram

ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
320
Підписники
+124 години
-47 днів
+5530 днів
Архів дописів
«የሀገራችን ኢኽዋኖች ተከታታይ ፅሁፍ»    √ #ክፍል 02 |• «የሱና ዑለማኦች ስለ ኢኽዋን ምን አሉ?» በክፍል አንድ ባሰማሁት የድምፅ ፋይል ሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን «"ኢኽዋን ከአህለሱና ውጭ ነው የሚለው" ትክክል አይደለም። ያው አህለሱና የሆኑት ሊቃውንቶች ከአህለሱና ውጭ እንዳልሆነ አረጋግጠውለታል።» ማለታቸው ይታወሳል። እናም ዛሬ በአላህ ፍቃድ የሱና ዑለማኦች ስለ ኢኽዋን ምን እንዳሉ እንመልከታለን። ከዚያም ሸይኹ  የተናገሩት እውነት ነው ወይስ በሱና ዑለማኦች ላይ፣ ወይ እየዋሹባቸው ወይ ያለ ዕውቀት አየመሰከሩባቸው የሚለውን እናረጋግጣለን። √| ከዚህ በታች በአላህ ፍቃድና እገዛ ታላላቅ የሱና ዑለማኦች ስለ ኢኽዋን የተናገሩትን ለማቅረብ እሞክራለሁ። 1. ታላቁ ኢማም የዘመናችን ሙሐዲሥ ሸይኽ አል-አልባኒ (ረሒመሁላሁ) እንዲህ ይላሉ፦ |√ «ليس صوابا أن يقال إن الإخوان المسلمين هم من أهل السُنة لأنهم يحاربون السُنة» (من شريط فتوى حول جماعة التبليغ والإخوان من تسجيلات منهاج السنة في الرياض) √| «አልኢኽዋን አል-ሙስሊሙን ከአህሉስ-ሱና ወል-ጀማዓ ናቸው ብሎ መናገር ትክክል አይደለም፤ ምክንያቱም እነርሱ ሱናን ይዋጋሉና።» • ይህንን ሊንክ በመጫን ንግግራቸውን ማድመጥ ይቻላል። 14 years ago የተለጠፈ https://youtu.be/d20Zb6JpAAA?si=KcLPeC_Zn2AQ-Sf0 √|| «لا يجوز أن نقول "الخلاف بيننا وبين الإخوان المسلمين فرعي والإخوان المسلمون من أهل السنة" لا!. هم يحاربون أهل السنة ويقولون دعوتكم الآن تفرق. نحن عاشرناهم في سوريا وهنا.» (من أشرطة سلسلة الهدى والنور، الشريط رقم 356.) √|| «"በእኛና በኢኽዋን አልሙስሊሚን መካከል ያለው ልዩነት በፈርዕ (በቅርንጫፍ ጉዳዮች) ላይ ብቻ ነው፣ ኢኽዋን ሙስሊሚንም ከአህሉስ-ሱና ናቸው።" ብሎ መናገር አይፈቀድም። በጭራሽ! (እንዴውም) እነሱ አህለሰሱናን ይቃወማሉ፤ (እኛንም) "ጥሪያችሁ አሁን ሰዎችን ትከፋፍላለችሁ"ም እያሉ ነው። እኛ በሶሪያም እዚህም ከእነርሱ ጋር አብረን ኖረናል።» • ይህንን ሊንክ በመጫን ንግግራቸውን ማድመጥ ይቻላል። 7 years ago የተለጠፈ https://youtu.be/JDLVfowcQBk?si=-fxNGSlEv0IYvvu6 √ ማሳሰቢያ፦ እንደሚታወቀው ኢኽዋን መልከ ብዙና በሸይኹ የህይወት ዘመን የተስፋፋ አንጃ በመሆኑ ሸይኹል አልባኒ ከህይወታቸው መጀመሪያ እስከ ህይወታቸው ፍጻሜ በኢኽዋኖች ላይ ተመሳሳይና አንድ አቋም አልነበራቸውም። ከእርሳቸው የፈትዋ የድምፅ ቅጅዎች እንደምንረዳውና ታሪካቸውን በቅርበት የሚያቁት ዑለማኦች እንደገለፁት ሸይኹ በአንጃው ሦስት መርሐላዎች (ደረጃዎች) ነበራቸው። 1• በመጀመሪያ ደረጃ ሸይኽ አል-አልባኒ ለኢኽዋን አልሙስሊሚን መልካም ግምት ነበራቸው። ምክንያቱም እነዚህ ኢኽዋኖች ቁርአንና ሱናን መከተልን መፈክራቸው ያደርጉ ነበርና። በዚህም የተነሳ እነርሱን ከሱና ውስጥ እንዳሉ ይቆጥሯቸው ነበር። ነገር ግን የዛኔም ቢሆን ከሱና ባያስወጧቸውም ከእነርሱ ይመለከቱ የነበረውን የዓቂዳ ድክመትና ወደተውሒድ ከመጣራት በላይ ለፖለቲካ የሚሰጡትን ትኩረት ይተቹ ነበር። 2• በሁለተኛው ደረጃ ሸይኽ አል-አልባኒ የኢኽዋን መንጋ ፈር መልቀቅ ግልጽ ይሆንላቸው ጀመር። ከዚያም አንዱ ኢኸዋኒይ የሰለፊያን ደዕዋ መተቸት ሲጀምርና “ሰለፊዮች የሚጨነቁት በውጫዊ  ጉዳዮች ብቻ ነው” ብሎ የፃፈው ሲደርሳቸው የሸይኹ ትችት የበለጠ ጠነከረ። እንዲህም አሉ፦ «ما أعتقد أن سلفيًا عقيدةً وسلوكًا بإمكانه أن يتبنى منهج الإخوان المسلمين وأمثالهم» ትርጉሙም፦ “በዓቂዳውም ሆነ በአካሄዱ ሰለፊይ የሆነ ሰው የኢኽዋን ሙስሊሚንንና እንደነሱ ያሉትን መንገድ ሊይዝ ይችላል ብዬ አላምንም።” እናም ሸይኹ የኢኽዋን መንገድ ሰዎች የተለያዩ ዓቂዳዎች ቢኖራቸውም ሁሉንም በአንድ የፖለቲካ ቡድን ውስጥ ለመሰብሰብና ለማደራጀት የሚሞክር መንገድ መሆኑ ግልጽ እየሆነላቸው መጣ። ሆኖም ግን ሸይኹ ኢኽዋንን ከሌሎች ቡድኖች ይልቅ ወደ ሐቅ የቀረቡ እንደሆኑ ይናገሩ ነበር፦ «الإخوان المسلمون هم أقرب الجماعات إلى الحق، لكنهم ليسوا على الحق.» ትርጉሙም፦ “ኢኽዋን አልሙስሊሚን ከቡድኖች ሁሉ ወደ እውነት የቀረቡ ናቸው፤ ነገር ግን እነርሱ በእውነት ላይ አይደሉም።” 3• በመጨረሻው ደረጃ ሸይኽ አል-አልባኒ የኢኽዋን ሙስሊሚንን አቋም በግልጽ መቃወም ጀመሩ። እነርሱ ከሚያስተካክሉት ይልቅ የሚያበላሹት እንደሚበዛ እና ብዙ መሰረታዊ ስህተቶችን ሲመለከቱ እንዲህ ሲሉ የመጨረሻ አቋማቸውን አወጁ፦ «خلافنا مع الإخوان المسلمين خلافٌ في الأصول لا في الفروع فقط.» “ከኢኽዋን አልሙስሊሚን ጋር ያለን ልዩነት በመሠረታዊ ጉዳዮች ነው፤ በቅርንጫፍ ጉዳዮች ብቻ አይደለም።” እንዲሁም ከላይ እንዳሰፈርኩት፦ «ليس صوابًا أن يقال الإخوان المسلمون من أهل السنة، لأنهم يحاربون السنة.» “ኢኽዋን አልሙስሊሚን ከአህሉስ-ሱና ናቸው ማለት ትክክል አይደለም፤ ምክንያቱም ሱናን ይዋጋሉና።” ሲሉ ኢኽዋን ከአህለሱና አመሆናቸውን አረጋግጠዋል። እናም ሸይኹ መጀመሪያ ላይ እነርሱ ቁርአንና ሱናን እንከተላለን ብለው በሚያሳዩት መፈክር ላይ የተመሠረተ መልካም ግምት ነበራቸው። በኋላ ግን የቡድኑ እውነተኛ መንገድና ተግባራዊ ጥመታቸው ሲገለጥላቸው አቋማቸውን እንደቀየሩ ነው ታሪክ የሚነግረን። ስለዚህ የዑለማዎችን ንግግር በታሪካዊና በጊዜያዊ አውዱ መሠረት መረዳት የፍትሕ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የዕውቀታዊ ታማኝነትም ጉዳይ ነው። አንድን የዓሊም ንግግር ከተናገረበት ደረጃና አውድ ነጥሎ ለሌላ ዓላማ መጠቀም ትክክል አይደለም። በዚህ ረገድ  ሸይኽ አሕመድ ሙሐመድ አስሷዲቁ አንነጃር በ blogpot ገፃቸው «موقف الشيخ الألباني من جماعة الإخوان المسلمين» በሚል ርዕስ የለጠፉትን ያንብቡ፦ http://abuasmaa12.blogspot.com/2025/10/blog-post_20.html የሌሎች ዑለማኦችን ንግግር በቀጣይ ክፍል አቀርባለሁ ኢንሻአላህ። √ #ክፍል 01 t.me/Abu_lmran_Alaseriy/3682 = (አቡ ዒምራን፣ ነሃሴ 11/2018) የቴሌግራም ቻናል t.me/Abu_lmran_Alaseriy t.me/Abu_lmran_Alaseriy

Repost from N/a
ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  ብዙ  የሱና ቻናሎችን add የሚለውን በመጫን ያገኛል ። ጥያቄ 1 💎ተዉሂድ በስንት ይከፈላል?

📚 አድስ ብስራት ለእውቀት ፈላጊዎች ! 🔖 በተለይ በዚህ ጊዜ የተለያዩ ሰለፍያን የሚሞግቱ ብድኖች ከመብዛታቸው ጋ ትክክለኛዋን የሰለፍያ ጎዳና በእውቀት ማወቅ የፈለገ በሱና ኡለማዎች ያዘጋጁቻውን
📚 አድስ ብስራት ለእውቀት ፈላጊዎች ! 🔖 በተለይ በዚህ ጊዜ የተለያዩ ሰለፍያን የሚሞግቱ ብድኖች ከመብዛታቸው ጋ ትክክለኛዋን የሰለፍያ ጎዳና በእውቀት ማወቅ የፈለገ በሱና ኡለማዎች ያዘጋጁቻውን ኪታቦች መማር ያስፈልጋል ። 📚 የሚቀራው ኪታብ ما هي السلفية ؟ لفضيلة الشيخ عبد الله بن عبد الرحيم البخاري 🎤 የሚያስቀራው አስታዝ ተውፊቅ 🗓 የሚቀራበት ቀን በሳምንት አራት ቀን ሰኞ ፣ እሮብ ፣ ጁምዓ ና ቅዳሜ የሙራጀአ ቀን ማክሰኞ ፣ ሀሙስና እሁድ ⏰ ሰዓት ከዒሻ በኃላ በኢትዮ 3:00 ጀምሮ ነገ ሰኞ ወይም እሮብ ይጀመራል ኢንሻ አላህ ሸር በማድረግ የኸይር ተካፋይ ይሁኑ ! የሚተላላፍበት ቻናል t.me/ibnumohammedyimer t.me/ibnumohammedyimer

የሸሪዓ ትምህርት ለምትማሩ ተማሪዎች፦ 1.የምንቀራውን ኪታብ ቃላት ልቅም አድርጎ መያዝ። ከኪታቡ ውስጥ የማናውቀው ቃል ላይኖር። 2.የኪታቡ መልእክት ላይ ትኩረት ማድረግ። መልእክቱን በትክክል መረዳት። ቃላት ለቀማ #ብቻ እንዳይሆን። 3. ማስረጃ ሲጠቀስ ከርእሱ ጋር ያላቸውን ተዛምዶ መለየት። مَحَلَّ الشَّاهِد እና وَجْهُ الاِستِدلال 4. ከደርስ በፊት እና ከደርስ በኋላ ሙራጀዓ ማድረግ። ከጓደኛ ጋር ወይም ለብቻ ሁኖ። ባጭሩ = የተማርነውን ኪታብ ለሌሎች ማስተላለፍ በሚያስችል አቅም መያዝ ያሰፈልጋል። ~ ከኡስታዝ <<ኢብኑ ሙነወር>> ደርሶች ላይ የተወሰደ።

أستغفر الله الذي لا إله إلا هو وأتوب إليه ​የእስቲግፋር ታላቅነትና ጥቅሞች፦ ​እስቲግፋርን ማዘውተር አለብን። እስቲግፋር ከኃጢዓት የሚጠብቀው ከሁለት አቅጣጫ ነው፦ ​አንደኛው፦በነፍስ ውስጥ ለአላህ ያለው ማክበርና ታላቅነቱን ህያው ያደርጋል። ​ሁለተኛው፦ ስህተቶችና ኃጢዓቶችን ያብሳል፣ ፈፅሞ ያጠፋቸዋልም። ​ኢብሊስ እንዲህ ብሏል፦ ​"የአደም ልጆችን በኃጢዓት አጠፋኋቸው፤ እነሱ ደግሞ በእስቲግፋር እና «ላ ኢላሃ ኢልለላህ» (ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም) በማለት አጠፉኝ።" ​የእስቲግፋር ጥቅሞች፦ ​እስቲግፋር እንደሚታወቀው ደረጃው በጣም ታላቅ ነው።ጥቅሞቹም አይቆጠሩም። ​ለሲሳይ በሩ ነው። ​ለስኬት መንገድ ነው። ​ኃጢአትን ለማስማር ምክንያት ነው። ​ ዱዐ እንዲቀበል ለማድረግ መንገድ ነው። ​የእውነተኛ ተሞክሮ ታሪክ ​አንድ ሰው እንዲህ ይላል፦ ​*"ስለ እስቲግፋር ታላቅነትና ፍሬዎች ሰማሁ፤ ከዚያም በቀን 30,000 ጊዜ ምህረት መጠየቅ (እስቲግፋር ማድረግ) ጀመርኩ። ​ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ በሌለው ጌታ እምላለሁ! እስቲግፋር ማዘውተር ከጀመርኩ በኋላ አላህን የለመንኩት ማንኛውም ዱዐ እንደ ጧት ብርሃን ግልፅ ሆኖ ተቀባይነት አገኘ። ​እንዲያውም አላህ ዱዐየን አብዝቶ ስለተቀበለኝ እስከማፍር ደረስኩ። እስቲግፋርን ማዘውተር ከጀመርኩ በኋላ አላህ ያልተቀበለኝ አንድም ዱዐ የለም። እንዲሁም በሲሳይ በኩል እንደዚሁ አላህ ባረከኝ።

🛡️ጥቂትም ቢሆን በጎ ስራህ ነው ለነገ ዋስትናህ! ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿ما مِنْكُمْ مِنْ أَحَدٍ إِلَّا وَسَيُكَلِّمُهُ اللَّهُ يَوْمَ القِيَامَ
🛡️ጥቂትም ቢሆን በጎ ስራህ ነው ለነገ ዋስትናህ! ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿ما مِنْكُمْ مِنْ أَحَدٍ إِلَّا وَسَيُكَلِّمُهُ اللَّهُ يَوْمَ القِيَامَةِ، لَيْسَ بَيْنَ اللَّهِ وَبَيْنَهُ تُرْجُمَانٌ، ثُمَّ يَنْظُرُ أَيْمنَ مِنْهُ فَلَا يَرَى إِلَّا مَا قَدَّمَ، وَيَنْظُرُ أشْأَمَ مِنْهُ فَلَا يَرَى إِلَّا مَا قَدَّمَ، وَيَنْظُرُ بَيْنَ يَدَيْهِ فَتَسْتَقْبِلُهُ النَّارُ، فَمَنِ اسْتَطَاعَ مِنْكُمْ أَنْ يَتَّقِيَ النَّارَ وَلَوْ بِشِقِّ تَمْرَةٍ﴾ “ከእናንተ መካከል በቂያማ (በትንሣኤ) ቀን አላህ በእሱና በእሱ መካከል ምንም ዓይነት አስተርጓሚ ሳይኖር የሚያነጋግረው እንጂ ማንም የለም። ከዚያም ወደ ቀኙ ይመለከታል ያስቀደመውን (መልካም) ሥራውን እንጂ ሌላ አያይም፤ ወደ ግራውም ይመለከታል ያስቀደመውን (መጥፎ) ሥራውን እንጂ ሌላ አያይም፤ ወደ ፊቱ ሲመለከትም እሳት ከፊቱ ትጠብቀዋለች። ስለዚህ ከእናንተ መካከል የቴምር (ክፋይ) እንኳን ቢሆን ሰደቃ በመስጠት እሳትን መከላከል (ከሱ መጠበቅ) የቻለ ሰው ይህንን ያድርግ።” 📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 6539 ➖➖➖➖➖➖➖ 🔸 በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦ 📱 Telegeram 📱 Whatsup 📱 Facebook  📱 Instagram 📱 X 📱 Youtube 📱 Tik tok

«የሀገራችን ኢኽዋኖች ተከታታይ ፅሁፍ»    √ #ክፍል 01 እውን «"ኢኽዋን ከአህለሱና ውጭ ነው የሚለው" ትክክል አይደለምን!?» ሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን ማለት የኢኽዋንን አስተሳሰብ በሀገራችን ሀበሻ ከመሰረቱትና ካስፋፉት ታላላቅ የኢኽዋን መሻኢኾች አንዱና ግንባር ቀደሙ ናቸው። በል እንዴውም የእርሳቸውን መንሃጃዊ ጉዞ፣ ለራሳቸውና ለወደዱት ሸይኽ የሚሰጡትን ቦታ፣ በሐሰኑል በንና እና በሰይድ ቁጥብ ያለባቸውን ቦዘቲቭነት፣ እነርሱን ለሚቃረኗቸው የሱና ዑለማኦች ያላቸውን ምልከታና ለሰለፊዮች ያላቸውን ጥላቻና ንቀት ስትመለከት ሀበሻዊዩ ሙሐመድ ሱሩር መሆናቸውን ነው የምታረጋግጠው። ባያያዝኩት የድምፅ ፋይል ሸይኹ ይጠየቃሉ። ጠያቂ፦ «ኢኽዋን ተብሎ መጠራት ይቻላል ወይ? ካልተቻለ ኢኽዋን የሚለውን ስያሜ የተሰጣቸው ሰዎች ሰለፍ (ሰለፊይ ማለቱ ይመስላል) መባልን ለምን ጠሉ። "አላህ ሙስሊሞች ብሎ ጠርቶናል ይበቃናል" ይላሉ። ዓሊሞችንም ይሰድባሉ ይባላል። በተላይ ሸይኽ ረቢዕን እውነት ነው ወይ?» የሸይኹ መልስ፦ «ጥያቄው ብዙ ጥያቄ ነው አንድ ጥያቄ አይደለም። ኢኽዋን ተብሎ መጠራት ይቻላል ወይ? የስያሜ ጉዳይ ነገሮችን አይለውጥም። ስያሜው ስላማረ ሰውየው አምሯል ማለት አይደለም። ስያሜው ችግር ስላለበትም ደግሞ ሰውየው ችግር አለበት ማለትን አያስይዝም። "ኢኽዋን" የሚለው ቃል ወንድም ማለት ነው። ሌላ ምንም የለውም። ኢኽዋን አልሙስሊሚን አንድ ጀመዓ አለ በግብጽ ሀገር የተመሰረተ። አቅሙ የፈቀደለትን፣ ራሱ እችላለሁ ባለው ኢስላምን ለማገልገል ሞክሯል። "ኢኽዋን ከአህለሱና ውጭ ነው የሚለው" ትክክል አይደለም። ያው አህለሱና የሆኑት ሊቃውንቶች ከአህለሱና ውጭ እንዳልሆነ አረጋግጠውለታል። መፅሃፎችን እያነበብን የምንመለስበት ይሆናል።» √| በቅድሚያ ጠያቂው በጥያቄው ያነሳቸው ነጥቦች ከንግግሩ አውድ እንደምንረዳው ተጨባጩን ያዋጁ ሁለት ቁም ነገሮች ናቸው። አንደኛው "ሱፊይ ሰለፊይ የሚባል ነገር የለም። አላህ ሙስሊሞች ብሎ ነው የጠራን ,,," የሚለውን የኢኽዋን ኡስታዞች የረጩትን ብዥታ መልስ እዲሰጥበት ሲሆን። ሁለተኛው ደግሞ አንዳንድ የኢኽዋን ወጠጤዎች የሱና ዓሊሞች ላይ በተላይ ሸይኽ ረቢዕ ላይ የሚላገጉትን ሀግ እንዲሉ ነበር። ነበር ብቻ!  ضَعُفَ ٱلطَّالِبُ وَٱلۡمَطۡلُوبُ √| ሸይኹ ግን ለጥያቄው ግልፅና ቀጥተኛ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ዙሪያ ጥምጥሙን መዞርን ነበር የመረጡት። እንዲህ ሲሉም መልስ ጀመሩ፦ «ጥያቄው ብዙ ጥያቄ ነው አንድ ጥያቄ አይደለም። ኢኽዋን ተብሎ መጠራት ይቻላል ወይ? የስያሜ ጉዳይ ነገሮችን አይለውጥም።» አዎ ንግግሩ ልክ ነው። ነገር ግን "ኢኽዋን" እና "ሰለፊይ" እንዲሁ ተራ ስያሜ ብቻ ነው ወይ? ለምን ጉዳዮን ያለባብሱታል። ጉዳዮኮ እንደ አንድ የዘመናችን ዓሊም የሚጠበቀው ጠንከር ያለ ማስረጃዊ ምላሽ የሚሻ ነበር። √| «ስያሜው ስላማረ ሰውየው አምሯል ማለት አይደለም።» በዚህ ቦታ ይህን ማለታቸው መልዕክቱ ግልፅ ነው። "ሰለፊይ" ነን የሚሉትን አካሎች መጎሽመጣቸው ነው። በአንፃሩ «ስያሜው ችግር ስላለበትም ደግሞ ሰውየው ችግር አለበት ማለትን አያስይዝም።» የሚለውም መልዕክቱ ግልፅ ነው። "እኛን ኢኽዋን ይሉናል እንጅ ትክክለኞቹ ሰለፊዮች እኛ ነን" ነው ነገሩ። ይህን ስል ከጥያቄና መልሱ አውድ በመነሳት ነው። "ልባቸውን ሰነጠቅከው? አናታቸውን ቀደድከው?" እንዳትል ማለቴ ነው ሙሪዱ። √| ሸይኹም በመቀጠል እንዲህ ይላሉ፦ «"ኢኽዋን" የሚለው ቃል ወንድም ማለት ነው። ሌላ ምንም የለውም።» ወላሂ! በሉ እስኪ! ለምን ግን በዚህ ልክ በሰዎች ጭንቅላት ትጫወታላቹህ!? ሰውየውኮ ቋንቋዊ ፍች አልነበረም ጥያቄው። ቀጥለውም፦ «ኢኽዋን አልሙስሊሚን አንድ ጀመዓ አለ በግብጽ ሀገር የተመሰረተ።» ሰሒሕ ልክ ብለዋል። «አቅሙ የፈቀደለትን፣ ራሱ እችላለሁ ባለው ኢስላምን ለማገልገል ሞክሯል።» እ? "ለማገልገል" የሚለውን "ለማፍረስ" ብትሉ አይሻልም ነበር!? አሁን In the 21st century. የሚኖር ዓሊም ቀርቶ ተራ ሰው ኢኽዋንን በዚህ በልኩ ይገልፃል!? √| በመጨረሻም፦ ولله الحمد «"ኢኽዋን ከአህለሱና ውጭ ነው የሚለው" ትክክል አይደለም።» በማለት ለብዙዎቻችን ተደብቆ የነበረውን ማንነታቸውን አፍርጠውታል። አላህን ያመሰገንኩት ማንነታቸውን ስለገለፁ እንጅ፣ ጥመትን በመምረጣቸው አይደለም። "እንዴት በሰዎች ጥመት ይደሰታል!?" እንዳትል ማለቴ ነው። ቀጥለውም «ያው አህለሱና የሆኑት ሊቃውንቶች ከአህለሱና ውጭ እንዳልሆነ አረጋግጠውለታል። መፅሃፎችን እያነበብን የምንመለስበት ይሆናል።» ይላሉ። • «"ኢኽዋን ከአህለሱና ውጭ ነው የሚለው" ትክክል አይደለም።» የሚለው የሸይኹ ንግግር ይሰመርበት። ስለ ኢኽዋን ዑለማኦች ምን እንዳሉ እመለስበታለሁ።  ሸይኹ ይህን ሲሉ ከሁለት ሁኔታዎች አይወጡም። አንደኛው፦ ሸይኹ የኢኽዋን ቢድዓዊ መሰረቶችን እያወቁና አምነውበት ነው ይህንን ያሉት። ሁለተኛው፦ ሸይኹ ኢኽዋን ስለሚባለው አንጃ የሚያቁት ነገር የለም ማለት ነው። መቸም ሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን ይቅርና ገ’ጠር የሚቀራ፣ ሱናን የሚሞግት ተራ ጧሊበል ዒልም እንኳ ስለኢኽዋን አያውቅም ማለት እራስን መሸወድ ነው። √|• ለማንኛውም «"ኢኽዋን ከአህለሱና ውጭ ነው የሚለው" ትክክል አይደለም። ያው አህለሱና የሆኑት ሊቃውንቶች ከአህለሱና ውጭ እንዳልሆነ አረጋግጠውለታል።»  የሚለው የሸይኹ ንግግር ከእውነት የራቀና ፍንትው ያለ ውሸት መሆኑን፣ እንዴውም በተቃራኒው ኢኽዋን ከአህለሱና ውጭ መሆኑ የተረጋገጠ መሆኑን ከዘመኑ የሱና ሊቃውንቶች ንግግር በማጣቀስ በቀጣይ ክፍል የምመለስበት ይሆናል ኢንሻአላህ። ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ እንዲህ ይላሉ፦ «وَمِثْلُ أَئِمَّةِ الْبِدَعِ مِنْ أَهْلِ الْمَقَالَاتِ الْمُخَالِفَةِ لِلْكِتَابِ وَالسُّنَّةِ أَوْ الْعِبَادَاتِ الْمُخَالِفَةِ لِلْكِتَابِ وَالسُّنَّةِ؛ فَإِنَّ بَيَانَ حَالِهِمْ وَتَحْذِيرَ الْأُمَّةِ مِنْهُمْ وَاجِبٌ بِاتِّفَاقِ الْمُسْلِمِينَ» [مجموع الفتاوى ٢٨/ ٢٣١ ـ ٢٣٢] «ከቁርአንና ከሱና ጋር የሚቃረኑ አመለካከቶችን የሚያስተምሩ የቢድዓ መሪዎችን ወይም ከቁርአንና ከሱና ጋር የሚቃረኑ የአምልኮ መንገዶችን የሚያስፋፉ ሰዎችን ሁኔታቸውን ማብራራትና ሙስሊሞችን ከእነርሱ ማስጠንቀቅ በሙስሊሞች ሁሉ ስምምነት ግዴታ ነው።» [መጅሙዑል ፈታዋ 28/231–232] = (አቡ ዒምራን፣ ነሃሴ 10/2018) የቴሌግራም ቻናል t.me/Abu_lmran_Alaseriy t.me/Abu_lmran_Alaseriy

ወንድሜ ሆይ! ስሜት እና እልህህን ዋጥ አድርገው። ሀቅን እንድትገፋ፣ ባጢልን እንድታነግስ እንዳያደርግህ። ነገ የምትቆጭበት ውሳኔ እንዳያስወስንህም ተጠንቀቅ። መስለሃ እና መፍሰዳን መለየት እንዳትችል እንዳያደርግህ አስተውል። https://t.me/tdarna_islam https://t.me/tdarna_islam

🎙توجيهاتٌ سديدة، ونصائح غالية، ألقاها على مسامعنا ليلة البارحة فضيلة الشيخ الوالد العلامة: عبد الله بن مرعي بن بريك العدني (حفظه الله تعالى ورعاه، وبارك في عُمره وعلمه) 📜في رسالةٍ أبويةٍ حانية، خُصَّ بها طلبةُ العلم في بلاد الحبشة عبر البث المباشر 📌تـنـبـيـه:--المحاضرة متبوعة بترجمة فورية إلى اللغة الأمهرية في ختامها، لتعميم النفع لجميع المستمعين የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ሳምንታዊ የደርስ ፕሮግራም ~ * ቦታ፦ ሑዘይፋ መስጂድ * ጊዜ፦ ዘወትር እሁድ ከረፋዱ 4:00 ጀምሮ ኪታቦች 1. منھج السالكين 2. كن سلفيا على الجادة 3. من أصول عقيدة أهل السنة فوزان ሼር በማድረግ አግዙን ባረከላሁ ፊኩም።

Repost from Ibnu Muhammedzeyn
አጫጭር መልእክቶች በኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ 👇📱📱📱📱👇 https://t.me/ISLAMICBOOKSANDAPPS/211853

حين بكى سفيان.. ‏« ولقد بكى سفيان الثوري ليلةً إلى الصباح، فلما أصبح قيل له: كلُّ هذا خوفًا من الذنوب؟ فأخذ تِبْنةً من الأرض، وقال: الذنوب أهون من هذا، وإنّما أبكي من خوف الخاتمة ».
- ابن القيم | الداء و الدواء صـ (٣٩٠).📚

ነጠላ ሰረዝ ታውቃለህ አይደል? ፅሁፍ ላይ አስፈላጊ ነው። ቃላትን ትለይበታለህ፣ ዝርዝር ሃሳብህን ትጠቅስበታለህ። ነገር ግን በድምፅ አታነበውም፣ ትፅፈዋለህጂ። እናልህ፤ ህይወትህ ላይ አንዳንድ ሰዎች አሉ፤ ክፉ ደጉን ትለይባቸዋለህ። ትምህርትህ ናቸው። ግን “ምን አሉ?” ብለህ አትጮህም። “በምን አሙኝ?” ብለህ ዋይታህን አታሰማም። ይፃፋሉ፤ ግን አይነበቡም !! t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman

إنْ كانَ تابعُ أحمدٍ مُتوَهّباً، فليشهدِ الثّقلان أنّني وهّابي አሕመድን(ሙሐመድን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) መከተል #ወሃቢይ ካስባለ የሰው ልጆችም ጅኖችም በጠቅላላ ወሃቢይ መሆኔን ይመስክሩ!

❌መውሊድ❌ አንተ,የመልክተኛውን ልደት የምታከብረው (መውሊድ )‼️ የአላህ መልክተኛን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከነዚህ ይበልጥ ትወዳለህ❓ ከአቡበክር ረዲየላሁ ዐንህ ከዑመር ረዲየላሁ ዐንህ ከኡስማን ረዲየላሁ ዐንህ ከአልይ ረዲየላሁ ዐንህ ከሰሀቦች ሊቆች ከሰሀቦች በአጠቃላይ ከነሱም በኋላ ከተከተሉዐቸው ታብዕዮች። ሼር አድርጉት

➨ንገሯቸው ዛሬም ሐቅ ላይ ነን።   «ክብራችን ይብቃችሁ» -------------------------- 👉 አልሀምዱ ሊላሒ ምስጋና ይገባው፡ 👉እንዳይፈርስ አድርጎ ሐቅን ለገነባው፡ 👉ውብ ሰለፍዮችን በፍትህ ላተባው፡ 👉ከመረጃ ጂረት ከምንጩ ላጠባው፡ 👉የአለማት ጌታ ምስጋና ይገባው፡ 👉ጭብጨባና አጀባ ወከባ አንፈልግም፡ 👉ሐቅ አውቀን ይዘናል አናፈገፍግም፡ 👉ወላሒ ሰው ሁሉ ጥሎን ቢከረበት፡ 👉የኔ ወንጀል በዝቶ ነውሬም ቢበዛበት፡ 👉መንሀጁ ሐቅ ነው እንከንም የለበት፡ 👉በስሜት አይደለም ይህንን የምለው፡ 👉በአላህ ይሁንብኝ መንሀጄ ገብቶኝ ነው፡ 👉ይከፋኛልና ሳስበው ትናንቴን፡ 👉አይቸዋለሁኝ ድክመቴን ውድቀቴን፡ 👉ጌታዬ አደራውን በሐቅ አርገው ሞቴን፡ 👉ስንት ግፍ አይተን ነው ከስንቱ ተፋልመን፡ 👉ስንት ፀብ አፍርተን ስንት ዘመን ታመን፡ 👉ሰለፍይ ለመሆን ብዙ ጉድ አይተን ነው፡ 👉በአቅማችን አውቀን ነው ወደን የጨበጥነው፡ 👉ከኛ ላይ ውረዱ ከናንተ አንፈልግም፡ 👉ወላሒ ከሐቁ አናፈገፍግም፡ 👉የምናምፀውን አላህ ይምረናል፡ 👉አሁን የያዝነውን መንገዱን ወደናል፡ 👉እሱ ሲነካብን እጂግ ይከፋናል፡ 👉መንሀጁን አትንኩት ክብራችን ይብቃችሁ፡ 👉ትንሽ የሚያስታውስ አዕምሮ ካላችሁ‼️ 👉የማንም መከርበት አያስጨንቀንም፡ 👉ቤተሰብ ስንለይ ያኔ አላማተርንም፡ 👉ከአባት ጋር ስንሞግት አላፈርንም ያኔ፡ 👉ዛሬ ማንም ቢሸሽ አልፈራም ወገኔ‼️ 👉ኪታብ አገላብጦ ታሪክ ያነበበ፡ 👉በማስተዋል ሆኖ በሁጃ ያበበ፡ 👉በንፁህ ህሌና ሐቅን ለቀረበ፡ 👉ሀያዕና ፍትህ ሰላም ለደረበ፡ 👉ለሰው ልጅ በሙሉ ሰላምን ላሰበ፡ 👉አድናቂ አዳማቂ ቂል ላልሰበሰበ፡ 👉እውነታው ግልፅ ነው ደፍሮ ላልጀዘበ፡ 👉ህይወቱን ለሰዋ ሐላል ለከሰበ፡         አስተዋይ የሆነ! 👉ሰለፍያን መንሀጅ በፍፁም አይ'ከዳም፡ 👉ለውሸት ውንጀላ እጁን አይከነዳም፡ 👉ደደግሞምን ቢናገር ማንንም አይጎዳም፡ 👉የዥዋዥዌ ሰው መቼሜ አይ'ረዳም፡ 👉ጀግና ሐቅን ሲይዝ ሁሌም ይከበራል፡ 👉የታሪክ መዛግብት ይህን ይናገራል፡ 👉ማን ምን እንደሆነ በግልፅ ያስተምራል፡ 👉ታዲያ ማንስ በማን ለምን ይሸበራል!? 👉እውነት ያው እውነት ነው እያደር ይበራል፡፡ 👉ስንት እየተባሉ ጀግና አባቶቻችን፡ 👉ስማቸው አድፎ ውብ ሞደሎቻችን፡ 👉ነብዩም ሳይቀሩ ውሸታም ተብለው፡ 👉ጠንቋይ ድግምተኛ እያሏቸው ችለው፡ 👉የሰላም ሰው ሆነው ስም አብቅለው ሌላ፡ 👉ስንት ነገር አልፈው ስንት የወጥመድ ኬላ፡ 👉ብዙ ግፍ ነበረ ታሪክ ሲመረመር፡ 👉ያለ ዋጋ አይደለም ዲናችን ሲጀመር፡ 👉ስንቱን ተጋፍጠዋል አቡ-በክርም ዑመር፡ 👉የዑስማን የአልይ ትግላቸው ይደንቃል፡ 👉ስንቱ ስንት ሆኗል ግን ይህን ማን ያውቃል!! 👉ምንም ሳንቸኩል ፍፁም ሳንጀረጂር፡ አሏህን ተማምነው ጠብቀው ውብ አጂር፡ 👉ስንት ግፍ አይተዋል አንሷርም ሙሀጂር፡ 👉ለኛ አድርሰውናል የተውሒዱን ጉዳይ፡ 👉አጥብቀን እንጨብጥ ይህን ንፁህ ሙዳይ፡ 👉ጠላት ስሙን ያውጣ ያርዳ ለቀባሪ፡ 👉#አህባሽም ውሀብይ ካ*ፊር አሸባሪ፡ 👉ይበለን ማንም ሰው ስም ይስጠን በገባው፡ 👉የመንጋ ፍርደኛው ጫት ቃሚ ገሪባው፡ 👉ብቻ ሰለፍያን አይስደቧት የትም፡ 👉መንሀጁ ሐቅ ነው ስህተት የለበትም፡ 👉ለማንኛውም ግን ጥንትም የሐቅ ሰው፡ 👉እውነት ወዳለበት ነው እንጂ እሚነፍሰው፡ 👉ከሒዝብዮች ተርታ ምን አልከሰከሰው⁉️ 👉ከልብህ ንገረኝ እስኪ ልጠይቅህ!? 👉እንዲህ ነበርክ እንዴ ያኔም እኔ ሳውቅህ!? 👉በዚህ ልክ አድርጎ ከመንሀጅ ያሶጣህ⁉️ 👉ከመንሀጀ-ሰለፍ እውነት ግን ምን አጣህ⁉️ 👉እስኪ በል ተጠየቅ እስኪ ምን አገኘህ!? 👉አስረዳን ንገረን እንደት ያን ተመኘህ!? 👉የሆኑ ባህሪዎች እንዳሉብህ ባውቅም፡ 👉ካንተ ግን ወዳጄ ይህን አልጠብቅም፡ 👉ማንም ሔደ መጣ ለማይጨነቁት፡ 👉የትም ቢቀመጡ እውነቱን ለሚያውቁት፡ 👉ሰውን በመጠኑ ወደው ለሚያልቁት፡ 👉በማስመሰል ጥበብ ለማያሳብቁት፡ 👉ጌታቸውን ፈርተው በሰው ለማይስቁት፡ 👉ሰው ስህተትን ሲመርጥ ዋ ነፍሴ ለሚሉ፡ 👉ማስተዋል ጥበብ ጋር ሁሌ ለታደሉ፡ 👉ከሐቅ መንሐጅ ላይ ለተደላደሉ፡ 👉ከልጅ እስከ አዋቂ ዛሬም ጀግኖች አሉ፡ 👉መረጃ ነው ሁሌም የሱንዮች አቅም፡ 👉በመንጋ ለሚጎርፍ ለመንጋ ጥርቅም፡ 👉ስሜት ለሚያላምጥ ወይም ጫት ለሚቅም፡ 👉ወላሒ የምሬን ተጨንቀን አናውቅም። 👉የግለሰብ ፍቅር እጂግ ያሰከረው፡ 👉በመንጋ ዳኝነት እልህ የወረረው፡ 👉ፍትሀዊ መሆን ሁሌ እሚያስቸግረው፡ 👉እንወያይ ሲባል መረጃ እማይደፍረው፡ ከእውነቱ ይልቅ፤ ለቡዲን ስሜቱ የሚቆረቆረው፡ ክፋት ምቀኝነት፤ ጥላቻና ሴራ እጂጉን ያወረው፡ በምን ሞራሉ ነው፤ የሱና ሰዎችን ደፍሮ እሚናገረው⁉️ ----------------------------- 👉በመንጋቸው መሐል ፍትህ የማያውቁ፡ 👉የመሰላቸውን በጂምላ እሚያደንቁ፡ 👉መረጃና ሁጃ ሐቅ የማይጠይቁ፡ 👉በግርጭርጭ ፀባይ የሚተዋወቁ፡ 👉እናውቃቸዋለን ሀፍረት የላቸውም፡ 👉ዛሬ ምንም ቢሉ እኛ አንሰማቸውም፡ 👉የስሜት አለቃ የጥላቻ ምንቸት፡ 👉የሱና ሰዎችን አይችልም መተቸት፡ 👉ሰለፍይ ወጣቶች ሀቅ ያስቀድማሉ፡ 👉በየደረሱበት ሽርክ ይፋለማሉ፡ 👉አህባሽ ሱፍይ ላይ ሁጃ ያቆማሉ፡ 👉አሁንም በቻሉት አቋም አልቀየሩም፡ 👉ብሩህ ነው ልባቸው ከሐቅ አልታወሩም፡ 👉ሐቅን መስበክ እንጂ፤ ጎትቶ የማምጣት የለብንም ግዳጅ፡ 👉ውብ ነው መንሀጃችን፤ ከውጭም ከውስጥም እጂጉን ተወዳጅ፡ 👉የተውሒድ የሱና የመንሀጅ ልሳኖች፡ 👉በመረጃ ሞጋች የምድር ድሮኖች፡ 👉አልሀምዱ ሊላሒ ዛሬም አሉን ጀግኖች፡ 👉ማንም ስለመጣ እኛ አናጋንንም፡ 👉የማንም ሰው መሔድ አወ አይቀንሰንም፡ 👉ማን ምን እንደሚያደርግ አውቀናል ሁሉንም፡ 👉እኛን ችግር የለም ስማችንን አጥፉት፡ 👉አብሽሩ ግደለም በየትም ለጥፉት፡ 👉ሰው አይደሉም በሉ ቲፎዞው ያጨብጭብ፡ 👉ያም ከዚህ ይህ ከዚያ ቁራጭ ቃል ይቀንጭብ፡ 👉ለክብራችን ብለን አንከራከርም፡ 👉በናንተም ላይ ቢሆን ውሸትን አንደፍርም፡ 👉አንድ ቃል ብቻ ግን እኔ የምላችሁ፡ 👉ትንሽ የሚያስተውል ህሌና ካላቸው፡ 👉የጎመን-ዘር ታክል ፍትህ ካሰባችሁ፡ 👉መንሀጁን አትንኩት ክብራችን ይብቃችሁ‼️ በኑረዲን አል-አረብ

+2
▪ስለ መውሊድ ሰፋ ያለ ዳሰሳ! ➡️ ክፍል አንድ 🎙በአብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን t.me/MuhaderahChannel

በነገራችን ላይ አሁን አሁን በአንዳንድ ወንድሞች እና እህቶች ላይ የሚታየዉ መንሐጃዊ መዘናጋት የቢድዓ ሰዎችን ማወደስ ተመዩዝ የለለበት የተደበላለቀ አካሄድ የዱዓቶች እና አሳቲዛዎች በዚህ ርዕሶች ላይ መዘናጋት የቢድዓ ሰዎችን ማደንደን እና በደዕዋዉ ላይ ብዙ መፋሲዶች ስለሚያመጣ በዚህ ጉዳይ ላይ ያለዉ መቀዛቀዝ ላቅ ያለ ትኩረት ይሻል አስተማሪዎች «መንሐጃዊ ዱሩሶች እና ዳዕዋዎች ላይ መበርታት» ይጠበቅባቸዋል።

👉የኔ ቤጤ «ልበ-ቢሶች» አንብቧትማ‼️ «ተጣላሁህ ልቤ» ------------------- ተው ብዬ መከርኩህ ሽማግሌ ልኬ፡ ለመንኩህ በለቅሶ ቆሜም ተንበርክኬ፡ መረር በል ብዬም ፀለይኩ ወደ አምላኬ፡ አንተ ግን ብታገል ብለፋ ብደክም፡ አሁንም እዛው ነህ መመከር አልቻልክም፡ ወደት ይዠህ ልሒድ ከማን ጋር ላሳክም!? ምንድነው ትርፍ ያለህ ምንህን ልከርክም፡ ወደ አሏህ የጮህኩት ዱዓዬ አልተሰማም!? ለትንሽ ቀን እንኳን ተሽዬ አልታማም!? ምን ሆነህ ነው ልቤ የምትበቀለኝ፡ ለምንስ ነው ስቀህ የምታስገድለኝ፡ ...እርግጥ ነው.....!! ወርቅ ሆነን ሳለ ብትቆጥሩን ከጠጠር፡ ከመካከላችን መናናቅ ቢፈጠር፡ ለምን ሆነ ብለን አንወቅስም እናንተን፡ መርከሳችን ሳይሆን፤ ቦታ አለማወቅ ነው እኛን ያስገመተን፡ ከእንግድህ ዋጋችን ይታወቃል ገኖ፡ ማን ነበር የቆየው በማን ተከሽኖ፡ ማንስ ነው ደጋግሞ የሚነካው ማኖ፡ .....ልቤ ግን አድምጠኝ.... ስንቴ ጎንበስ አልን ስንቱን ሰው ሸኝተን፡ ስንቴ ባይተዋር ሆን እኔና አንተ ቀርተን፡ አምነን የሄድን ለት ስንቱ ጥሎን ገደል፡ በእኛ ተረማምዶ ስንቱ ሲደላደል፡ አንተ ግን አሁንም እርም አታውቅም አይደል⁉️ ....ይሔ ሁሉ ሲሆን ለምን አጠይቅም፡ ..ሞኝነቱ ለምን ለምን እርም አታውቅም!? ለምን ከሌሎች ጋር አትተዋወቅም⁉️ ከዚያ ግፍ በኋላ ዛሬ ምን አሞኘህ ? ለምን ተስፋ አትቆርጥም አሁን ምን አሰኘህ ? ድጋሜ ረበሽከኝ ደግሞ ምን አገኘህ⁉️ ....ንገረኝ....⁉️ በስንቱ ስብራት ስንት መንገድ መተህ፡ ከጌታህ ጋ አልቅሰህ እልፍ ስለት ገብተህ፡ ከተደበቅክበት #አሏህ ስላነሳህ፡ ያን የገባኸውን ቃልህን እረሳህ ⁉️ ....እንደት⁉️ በሚስጥር ቃል-ኪዳን ምለን ተማምለን፡ አልስቅም ብለኸኝ እኛን ለበደለን፡ መሀላህን በላህ ውሉን አፈረስከው፡ እስኪ ልጠይቅህ ምንድነው የሆንከው⁉️ አምርሬ ነግሬህ የሳቀ እንዳይረታህ!! ለምን ትንሽ ሳትቆይ ለማፍቀር በረታህ⁉️ ምድብክን ንገረኝ ከነማን ነው ተርታህ⁉️ ...ንገረኝ...⁉️ ማመንህ ሳይከፍልህ ሳያንስ ያደከምከኝ ልክ እንደ ታች አምናው ዘንድሮም ደገምከኝ ??? እንኳንም ጨክነህ እሰይ ደግ አረከኝ‼️ የውስጤን የአንጀቴን ነግሬህ ቀርቤ፡ ከሰዎች ሽሽ ብየህ የማምነው ተርቤ፡ መሀላህን በላህ ደፈረሰ ቀልቤ፡ ዳግም ላንታረቅ ተጣላሁህ ልቤ . . .‼️ ....በኑረዲን አል-ዓረብ...✍️ t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

ከቤተሰብ ርቆ መኖር የሚያስተምሩን ነገሮች፦ 1.ራስን መቻል ምርጫ ሳይሆን ግዴታ እንደሆነ ፦ ማንም ሊደርስልህ በማይችልበት ቅፅበት ራስህን ማዳን ትማራለህ ። 2.ደህና ነኝ የሚል ቃል ብዙ ሚስጥር እንደሚሸፍን ፦ ላለማስጨነቅ ስትል ህመምህን በሳቅ መደበቅን ትማራለህ ። 3.ግዜ የማይመለስ ሀብት መሆኑ ፦ በስልክ ላይ የሚልፉ ግዚያት በስራ ላይ አለማዋላቸው ፀፀት እንደሚያተርፍ ትረዳለህ ። 4.ብቸኝነት አስተማሪም ጨካኝም እንደሆነ ፦ ለብቻህ ማልቀስ ለብቻህ መነሳት በትልቁ ትለምዳለህ። 5.የቤት ምግብ ጣዕም ምግብ ብቻ  እንዳልሆነ ናፍቆትም እንደሆነ ፦ ቤተሰቦቻችን የሚሰሩት ምግብ ብቻ እንዳልሆነ እና በስስት እንድትበላ የሚፈልጉት ብቻኛ ሰዎች እንደሆኑ ትረዳለህ ። 6.የቱንም ያክል ገንዘብ ቢኖር ፍቅርን ሊተካ አለመቻሉን ታውቃለህ ፦ የቱንም ያክል ገንዘብ ቢኖርህ የምትወደውን  የልብህን ሰው  ካልሆነ በገንዘብ ብዛት አታፈቅረውም ። 7.ቤተሰብ ጋር ያለው ትንሽ ነገር ትርጉም እንዳለው ፦ የቤተሰብ ድምፅ ብቻ  በራሱ  የሚገርም ደስታ እንዳለው ትረዳለህ።