ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
Відкрити в Telegram
ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
321
Підписники
+124 години
-77 днів
+5830 днів
Архів дописів
📍 ብሶትሽን ለአሏህ ብቻ ተናገሪ::
አንዳንድ ቀን በውስጥሽ ያለው ጭንቀትና ድካም ከብዶሽ ለቅርብ ጓደኞችሽ አውጥተሽ በመተንፈስ ቀለል እንዲልሽ ትፈልጊ ይሆናል። ነገር ግን ሰዎች የቱንም ያህል ቢወዱሽ ሁሌ ስለ ችግርሽና ስለ ብሶትሽ መስማት ሊሰለቻቸው ይችላል።መሰልቸታቸውን በቃላት ባይነግሩሽም ከሁኔታቸውና ከዝምታቸው መረዳት ትችያለሽ::
እህቴ ሰዎች ይሰለቻሉ አላህ ግን አይሰለችም
ሰዎችን በብሶትሽ ደጋግመሽ ካስቸገርሻቸው ከአንቺ መራቅን ይመርጣሉ። አላህ ግን በለመንሽውና ወደ እርሱ በተመላለሽ ቁጥር ይበልጥ ይቀርብሻል። እርሱ ለቅሶሽን የማይሰለች ብሶትሽን የማይንቅና ለጭንቀትሽ እውነተኛ መፍትሔ ያለው ብቸኛ ጌታ ነው።
ችግርሽን ለአላህ ብቻ ንገሪው
ነቢዩ ያዕቆብ (አለይሂ ሰላም) ታላቅ ጭንቀት በደረሰባቸው ጊዜ እንዲህ ነበር ያሉት፦
﴿إِنَّمَا أَشْكُو بَثِّي وَحُزْنِي إِلَى اللَّهِ﴾
"ጭንቀቴንና ሐዘኔን የማሰሙተው ወደ አላህ ብቻ ነው (ዩሱፍ፡ 86)
ሰዎች ብሶትሽን ቢሰሙ አይዞሽ ከማለት ባለፈ ሊያደርጉልሽ የሚችሉት ነገር የለም:: አሏህ ግን ብሶትሽን ሰምቶ መፍትሄን ይሰጥሻል::
ሰውን አታስቸግሪ ለራስሽ ስትይ ጠካራ ሁኚ
ሁሌ ስለ ራስሽ ድካም የምታወሪ ከሆነ በሰዎች ዘንድ ያለሽ ግርማ ሞገስ ይቀንሳል። ሰዎች ሲያዩሽ የችግርና የጭንቀት ምልክት ብቻ እንዳትሆኝ ተጠንቀቂ። በሰዎች ፊት ጠንካራና ታጋሽ ሁኝ በጌታሽ ፊት ግን ደካማና ተናናሽ ሁኚ።
ሱጁድ ትልቁ መተንፈሻሽ ይሁን
የውስጥሽ ጩኸት ሲበዛ ማንም ሊሰማሽ ያልፈለገ ሲመስልሽ መስገጃሽን ዘርጊና ወደ ጌታሽ አልቅሺ። በዝምታ የምታፈስሽው እምባ በአላህ ዘንድ ትልቅ ዋጋ አለው። እርሱ ምላሽ የሚሰጥሽ ልብሽን የሚያረጋጋና ካሰብሽው በላይ መውጫ መንገድን የሚያዘጋጅልሽ ጌታ ነው።
♦️♦️በሰዎች መካከል ብቻህን
📌ወላሂ፣ ለራሱ ብቻ ከሚያስብ፣ የራሱን ምቾት ብቻ ከሚፈልግ፣ የአንተን ስሜት ለመረዳት የማይሞክር ሰው ጋር ከመኖር፣ ብቸኝነት እጅግ ይሻላል።
📍ከሰው ጋር መኖር ማለት አንድ ቤት ውስጥ ብቻ መኖር አይደለም፤ አንድ ልብ መሸከም፣ በደስታ አብሮ መደሰት፣ በሐዘን ጊዜ ከጎን መቆም፣ ሳትናገር ስትሰቃይ የልብህን ህመም መረዳት ነው።
📍አንዳንድ ጊዜ ከጎንህ የሚቀመጥ ሰው፣ ከሩቅ ካለ ሰው ይልቅ ልብህን የበለጠ ሊያሳዝን ይችላል። አንድ ቤት ውስጥ ሆነህ ማንም እንደሌለ መሰማት፣ አንድ ሰው ከጎንህ እያለ የልብህን ህመም ለማንም መናገር አለመቻል—ይህ እጅግ ከባድ የሆነ ብቸኝነት ነው።
📍ሰው ሁልጊዜ ብዙ ሰዎች አያስፈልገውም፤ አንድ በቂ ነው። አንድ ሰው—ስትደክም የሚያሳርፍህ፣ ስታዝን የሚያዝንልህ፣ ስትወድቅ የሚያነሳህ፣ እና ምንም ሳትናገር የልብህን ሁኔታ የሚረዳህ።
📍ነገር ግን ሁልጊዜ “እኔ” ብቻ የሚል፣ “አንተስ?” ብሎ የማይጠይቅ፣ “እንዴት ነህ?” ብሎ የማይጨነቅ፣ በህመምህ ጊዜ ከጎንህ የማይቆም ሰው ከሆነ፣ ከእንዲህ ያለ ሰው ጋር ከመኖር ብቻህን መኖር ይሻላል።
📍ምክንያቱም ብቸኝነት ሰውን አንድ ጊዜ ሊያሳዝነው ይችላል፤ ነገር ግን ከማይረዳህ፣ ከማያዝንልህ እና የልብህን ህመም ከማይሰማ ሰው ጋር መኖር በየቀኑ በዝምታ ሊሰብርህ ይችላል።
📍ስለዚህ ከሰዎች መካከል መኖር ብቻ አንፈልግ፤ በልብ የሚያኖረንን፣ የሚረዳንን፣ የሚያከብረንን እና በችግራችን ጊዜ ከጎናችን የሚቆምን ሰው እንፈልግ።
📍ከጎናችን ያለ ሰው ሁሉ ከእኛ ጋር አይደለም፤ አንዳንዶች በአጠገባችን ናቸው፣ ግን በልባችን ውስጥ ብቻችንን እንሆናለን።
አላህ የሚተሳሰብ፣ የሚዋደድ፣ የሚተጋገዝ፣ ለሌላውም እንደራሱ የሚያስብ ሰው ያድርገን። ልባችንን ለሌሎች ርኅራኄ ያድርግ፤ ለራሳችን ብቻ እንዳንኖር ከራስ ወዳድነት ይጠብቀን። አሚን።
ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ
https://telegram.me/abutoiba
https://telegram.me/abutoiba
Repost from ስለ ቀልባችን
➔ በሃላል መተያየት፣
➔ ከዚያም እጮኝነት፣
➔ ከዚያም ኒካህ፣
➔ ከዚያም ሰርግ።
ይህ ነው ትክክለኛው መንገድ፤ የእውነት የሚወድሽ ከሆነ መንገዱ ይሄው ነው፣ ከዚህ ውጭ ሌላ አማራጭ የለም።
+4
👉ውበት ተመልከቱ እስኪ #አላህ ይጠብቃቸው ያረብ! አልሐምዱሊላህ ዛሬም #ሰለፍዮች ወደፊትም በአላ ፈቃድ ሰለፍዮች ነን ወሊላሂል ሀምድ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Abulabas1444
https://t.me/Abulabas1444.
+9
{{ قُلْ مُوتُوا۟ بِغَیۡظِكُمۡۗ }}
فيزيد ويتزايد إن شاء الله،
لأن الله تعالى يقول: {{ أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَاۤءِ مَاۤءࣰ فَسَالَتۡ أَوۡدِیَةُۢ بِقَدَرِهَا فَٱحۡتَمَلَ ٱلسَّیۡلُ زَبَدࣰا رَّابِیࣰاۖ وَمِمَّا یُوقِدُونَ عَلَیۡهِ فِی ٱلنَّارِ ٱبۡتِغَاۤءَ حِلۡیَةٍ أَوۡ مَتَـٰعࣲ زَبَدࣱ مِّثۡلُهُۥۚ كَذَ ٰلِكَ یَضۡرِبُ ٱللَّهُ ٱلۡحَقَّ وَٱلۡبَـٰطِلَۚ فَأَمَّا ٱلزَّبَدُ فَیَذۡهَبُ جُفَاۤءࣰۖ وَأَمَّا مَا یَنفَعُ ٱلنَّاسَ فَیَمۡكُثُ فِی ٱلۡأَرۡضِۚ كَذَ ٰلِكَ یَضۡرِبُ ٱللَّهُ ٱلۡأَمۡثَالَ }} [سُورَةُ الرَّعۡدِ: ١٧]
https://t.me/Abulabas1444
https://t.me/Abulabas1444.
♦️ለነዚያ ለታሪክ አተላወች
♦️ለነዚያ የራፊዷ ገረዶች
♦️ለመጁሳ ቅጥረኞች አድርሱልኝ⁉️
ሲሰድቡሽ ቢውሉ ከሽዓ ወግነው፡
የተውሒድን መርህ ስለማያውቁ ነው፡
ለአህባሽ፣ለኢኽዋን ደግሞም ለሱፍያ፡
ግልፅ ነው ይጠላል ደዕዋ ሰለፍያ፡
🎙በኑረዲን አል-ዓረቢ
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
Repost from Werabe university muslim students union
ወደ ዩኒቨርሲቲ ለምትገቡ አዲስ ተማሪዎች፦
ከላይ የተቀመጠው መረጃ የየዩኒቨርሲቲ ጀመዓዎችን መረጃ የያዘ ሲሆን በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች በመደወል ስለ ዩኒቨርስቲዎቹ፤ ጀመዓዎች እንዲሁም ሌሎች መረጃዎች መጠየቅ ትችላላችሁ።
አላህ ለስኬት መሠረት የሆነን ቆይታ ያድላችሁ።
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ዛሬ ጁሙዓ ነዉ የጁሙዓ ሱናዎችን እንተግብር
➖➖➖➖➖➖➖
↩️💎 سنن يوم الجمعة🌿🌿🌿
➊ 💎الغسل
➋💎 الطيب
➌ 💎السواك
➍💎 لبس الجميل
➎💎 قراءة سورة الكهف
➏💎 التبكير لصلاة الجمعة
➐💎الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
➊ 🌺መታጠብ
➋ 🌺ሽቶ መቀባት
➌🌺 ሲዋክ መጠቀም
➍ 🌺ጥሩ ልብስ መልበስ
➎ 🌺ሱረቱል ካህፍን መቅራት ከቻልን
➏ 🌺ለጁመዓ ሶላት በግዜ መጣድ
➐ 🌺በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማብዛት
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿〰
«اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ،
كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ،
اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ،
كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ
🌺በሰለዋት በዚክር ያውለን ያረብ
ﷺ 🌹 .................🌹
ﷺ ﷺ🌹 ..................🌹 ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ ﷺ🌹🔹🔹🌹
ﷺ ﷺ ﷺ 🌹🔹🔹🌹
በነብዩ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ !!
https://t.me/Abulabas1444
https://t.me/Abulabas1444.
🌿 የሙስሊሞችን ጉዳይ ችግር ማቃለል ማስወገድ የመልካምነት ታላቅ በር ነው።
አላህ ሱበሀነሁ ወተዓላ እንዲህ ብሎናል፦
﴿وَافْعَلُوا الْخَيْرَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ﴾
«መልካምን ሥሩ፤ ምናልባትም ልትድኑና ነጃ ልትወጡ ትችላላችሁ።»
🤍 የሰውን ጉዳይ ማስተናገድ ትንሽ ሥራ አይደለም…
አንድ ሰው በችግር ውስጥ ሆኖ ሲመጣብህ፣ ምናልባት በእጅህ ያለው ነገር ትንሽ ይመስልህ ይሆናል፤ አንተ ግን ለእሱ ያደረግከው ነገር በሕይወቱ ትልቅ ቦታ ሊኖረው ይችላል።
አንድ ሰው በጭንቀት ላይ እያለ በአንድ ቃል ማጽናናት፣
●አንድ ሰው ጉዳዩን ማስፈጸም፣
●የሚያስፈልገውን ሰው ማገዝ፣
●በችግሩ ጊዜ ከጎኑ መቆም፣
●የሚያውቀውን መረጃ መንገር፣
●አንድ የተዘጋ በር እንዲከፈትለት ምክንያት መሆን…
●እነዚህ ሁሉ የሙስሊም ወንድማማችነት ምልክቶች ናቸው።
ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«المُسْلِمُ أَخُو المُسْلِمِ، لَا يَظْلِمُهُ وَلَا يُسْلِمُهُ، وَمَنْ كَانَ فِي حَاجَةِ أَخِيهِ كَانَ اللهُ فِي حَاجَتِهِ، وَمَنْ فَرَّجَ عَنْ مُسْلِمٍ كُرْبَةً فَرَّجَ اللهُ عَنْهُ بِهَا كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ يَوْمِ القِيَامَةِ، وَمَنْ سَتَرَ مُسْلِمًا سَتَرَهُ اللهُ يَوْمَ القِيَامَةِ.»
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
🌿 “የወንድሙን ፍላጎት ለማሟላት የሚጥር ሰው አላህ ፍላጎቱን ያሟላለታል”
ይህ ቃል ልብን የሚነካ ታላቅ ተስፋ ነው።
እኛ የሰውን ጉዳይ ስናስተናግድ እንዲህ እንበል፦
“ይህን ሰው ለማገዝ አላህ ምክንያት አድርጎኛል።”ከዚያ የምናገኘው ክብር ወይም ምስጋና ሳይሆን፣ የአላህ ውዴታ ይሁን የምንፈልገው። ሰዎች አመስግነውን ይሆናል፤ አላመሰገኑንም ይሆናል። ሰዎች አስታውሰውን ይሆናል፤ ረስተውንም ይሆናል። አላህ ግን የሠራነውን መልካም ሥራ አይረሳም።
● አንድ ሰው የእኛን እርዳታ ሲፈልግ አንተ የምታየው ችግሩን ብቻ ነው፤ አላህ ግን የሚያየው የአንተን አቋም ነው።
ለዚህ ነው አንዳንድ ጊዜ ትንሽ የምናደርገው ነገር በአላህ ዘንድ ታላቅ የሚሆነው።
●አንድ ሰው እንባውን እንዲያብስ ምክንያት ሆነህ ሊሆን ይችላል።
●አንድ ቤተሰብ ችግሩን እንዲያልፍ ምክንያት ሆነህ ሊሆን ይችላል።
●አንድ ወንድም ተስፋ እንዳይቆርጥ አንተ ምክንያት ሆነህ ሊሆን ይችላል።
እነዚህን መልካም ስራዎች አታቃልል።
ምክንያቱም ነብዩ ﷺ እንዳስተማሩን፣ የሰውን ጭንቀት ማስወገድ እንኳን በቂያማ ቀን ከጭንቀቶች አንዱን እንዲያስወግድልን ምክንያት ይሆናል።
● ወንድማማችነት የሚታየው በደስታ ጊዜ ብቻ አይደለም…
ሰው ሲደሰት ከእሱ ጋር መደሰት ቀላል ነው። ነገር ግን ሲወድቅ እጁን መያዝ፣ ሲጨነቅ ማጽናናት፣ ሲደክም መደገፍ ነው እውነተኛ ወንድማማችነት።
ሰዎች በሚያስፈልጉን ጊዜ ብቻ አንቅረባቸው፤ እኛም ሌሎችን በሚያስፈልጋቸው ጊዜ እንቅረብ።
የሙስሊም ወንድምህ ጉዳይ ካለው፣ “እኔ ምን አገባኝ?” ከማለት በፊት “ምን ላግዘው እችላለሁ?” ብለህ አስብ።
🌿 ምናልባት ያ ትንሽ እገዛህ በአላህ ዘንድ የተቀበለች ትሆናለች።
🌿 ምናልባት ያ የሰጠኸው ጊዜ ነገ አንተ በችግር ላይ ስትሆን የምትፈልገው ምሕረት ይሆናል።
🌿 ምናልባት የሰውን ጭንቀት ያስወገድክበት ቀን አንተም ከቂያማ ቀን ጭንቀት እንድትወጣ ምክንያት ይሆናል።
● እንግዲህ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን በቻልነው አቅም እንርዳ…
● ጉዳያቸውን እናስፈጽል፣
● ችግራቸውን እናቅልል፣
● እንባቸውን እናብስ፣
● ምስጢራቸውን እንጠብቅ፣
● ነውራቸውን እንሸፍን፣
● በችግራቸውም ጊዜ ከጎናቸው እንቁም።
ምናልባት ነገ እኛ የምንፈልገው እርዳታ ዛሬ ለሌላ ሰው የሰጠነው እርዳታ ትሆናለች።
⚠️ አላህ ሆይ! የሙስሊሞችን ጭንቀት አስወግድ፣ ጉዳያቸውን አስተካክል፣ እኛንም የተጨነቁትን ከሚያጽናኑ፣ የተቸገሩትን ከሚረዱ፣ የወደቁትን ከሚያነሱ ባሮችህ አድርገን። እኛ የሰዎችን ፍላጎት ለማሟላት ስንሮጥ፣ አላህ የእኛን ፍላጎት የሚያሟላልን ጌታ ነው።
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy«تُكفى همك، ويُغفر ذنبك»
يقول ابن باز رحمه الله:
إذا جعل الإنسان وقتًا يصلي فيه على النَّبي ﷺ كثيرًا، فالله -جلَّ وعلا- يأجره على ذلك، والحسنة بعشر أمثالها، إلى ما لا يحصى من الفضل، وإذا صرف ذلك الوقت كله في الصلاة على النبي ﷺ؛ حصل له هذا الفضل: «تُكفى همّك» يعني: يكفيك الله همك «ويُغفر ذنبك».
اللهم صلِّ وسلم على نبينا محمد، وعلى آله وصحبه أجمعين.
በውድም በግድም
አንድ ደግ ሰው «የወደድከውን ያክል ውደድ ከወደድከው መለየትህ አይቀርም፤ የኖርከውን ያክል ኑር ከሕይወት በሞት መሰናበትህ አይቀርም!» አለ አሉ። እውነትም ነገሩ እንዲህ ነው፣ በውድም በግድም ከሰው ሕይወት መውጣትህ አይቀርም።
በውድ፣ አንዳንዴ ገፍተህ፤ በግድ ደግሞ ተገፍተህ ቆምጠጥ ሲል ደግሞ በሞት ትለያያለህ። ሞት ግን የዋሁ ከሰው ጋር የምንለያይበት መንገድ መሰለኝ።
ታዲያ ሰዎችን ስትለያቸው፣ የሕይወታችሁ የጋራ መጽሐፍ የመጨረሻው ምዕራፍ የቂም ምዕራፍ አይሁን፣ የጭካኔ ምዕራፍ አይሁን፣ የበደል ምዕራፍ አይሁን፣ የእብሪትና ትዕቢት ምዕራፍ አይሁን።
ሰዎችን ስትለያቸው ግድ የለህም የመጨረሻው የሕይወት ገጻቸው ላይ የምትጽፈው፣ ይቅርታን ይሁን፣ እዝነትን ይሁን፣ እራስን ዝቅ ማድረግ ይሁን፣ እነርሱን ላለማጣት ሁሉንም ነገር መሞከር ይሁን።
የመጨረሻው ገጽ ወሳኝ ነው። አንተን የሚያወሱህም በእርሱ ነው። «ከመሄዳቸው አካሄዳቸው ያማል» ሲባል አልሰማህም?!—እና አካሄድህን አሳምር። አታካብድ መሞትህ ካልቀረ አካሄድህ ቢያምር ምናለ?
قال الإمام بن القيم رحمه الله
أغبى الناس من ضل في أخر سفره وفد قارب المنزل
ከሰዎች ይበልጥ ሞኝ ማለት (ጉዞ ወቶ) በጉዞዉ መጨረሻ ላይ ወደ መዳረሻዉ ከቀረበ በኋላ መንገድ የሳተ ግለሰብ ነዉ ::
አል ኢማም ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንላቸዉ
الفوائد ١٠٧
አሏህ የመንገዳችንን መጨረሻ ያሳምረዉ
.
ልክ ማለት ምን እንደሆነ ሲገባህ ልክ ማለፍ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ትረዳለህ‼️
🎤 በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር حفظه الله
https://t.me/Umu_Reyan_channel_No1
ስለ ተውሂድ የተደረጉ በውድ እና በሱና ኡስታዞች ሙሓደራወች ስብሰብ በቀላሉ ለማገኘት👇👇👇👇👇👇
የተለያዩ መሳጭ ዳእዋወች ርዕሶቹ ከዚህ በታች ናቸው ርዕሱን አንዲ ብቻ በመካት ማዳመጥ ይችላሉ ➍🥉አከባቢ ሙሓደራወች❶ ተውሂድ ➋ ተውሂድ እና አህባሽ ❸ ተውሂድ እና ሽርክ እና ተቅዋ ➍ ተውሂድ እና ኢትዮጵያ ➎ ቅድሚያ ለተውሂድ ➏ ተውሂድ እና ላኢላሀኢለሏህ ➐ ተውሂድ እና ሽርክ ➑ ተውሂድ እና አሳሳቢነናቱ ❾ ተውሂድ አፍራሾች ❿ ስለ ተውሂድ ❶❶ ተውሂድ እናትሩፋት ❶➋ ለምን ተፈጠርን ❶❸ ስለ ተውሂድ አስፈላጊነት ❶➍ ተውሂድ እና ነብዩ ኢብራሂም ❶➎ ተውሂድ የመጀመሪያ ግደታ ነው ❶➏ ቅድሚያ ለተውሂድ ❶ ➐ ስለ ተውሂድ አንገብጋቢነት ❶➑ ተውሂድን አደራ አደራ አደራ ❶❾ ተውሂድ እና ሽርክ ➋0 ተውሂድ ሩብብያ ➋❶ ተውሂድ ወሳኝ ርዕሰ ነወ ➋➋ ተውሂድ እና ሽርክ ➋❸ ታላቁ አደራ ተውሂድ ➋➍ ተውሂድ የጀነት ቁልፍ ነወ ➋➎ ተውሂድ አሳሳቢነት እና ሽርክ አስከፊነት ➋➏ ተውሂድ ስትጣራ ቅጥል ይሰጥሃል ➋➐ ተውሂድ በአጭሩ ➋➑ የአማናወች አማና ተውሂድ ➋❾ ተውሂድ አሳሳቢነት ❸0 ቅድሚያ ለተውሂድ ❸❶ ተውሂድ የነብያቶች ሁሉ ጥሪ ነው ❸➋ ተውሂድ ሁሌም አድስ ሲያወሩት የሚጣፍጥ ❸❸ ተውሂድ ምንነት ❸➍ አሁንም ቅድሚያ ለተውሂድ ❸➎ ተውሂድ ከሁሉም እደሚቀደም ❸➏ ተውሂድ ቢያወሩት የማይጠገብ ❸➐ ተውሂድ እና የሀገራችን ❸➑ ዛሬም ነገም ቅድሚያ ለተውሂድ ❸❾ ለምን ቅድሚያ ለተውሂድ ➍0 ቅድሚያ ለአቂዳ ➍❶ ቅድሚያ ለተውሂድ ➍➋ ቅድሚያለተውሂድ ከሁሉም ነገር በፊት ➍🥉ለምን ቅድሚያ ለተውሂድ እንላለን ❓
Repost from ትዳር እና ኢስላም 🌷🌹🥀
«የጣፋጮችን ሁሉ ጣዕም ቀመስኩ፤ ከጤናና ከሰላም የሚበልጥ ጣዕም አላገኘሁም። የመራራዎችን ሁሉ መራርነት ቀመስኩ፤ ከሰው እጅ የመጠበቅን ያህል መራር አላገኘሁም። ድንጋይንና ብረትን ተሸከምኩ፤ ከዕዳና ከብድር የሚከብድ የከበደ ሸክም አላገኘሁም።»
http://t.me/ibrahim_furii
🤲 ዱዓ እናብዛ ❗️
እህት ወንድሞቼ እናት አባቶቼ ሆይ፣ ለተበዳዩ የየመን ሕዝብ ዱዓ አብዙ፤ ለነዚያ በሁቲዮች ለተጨቆኑት፣ ለተበደሉት፣ ሃይማኖታቸውን፣ ደኅንነታቸውንና ሀገራቸውን ለመጠበቅ ለሚጥሩት ከወንበዴው ቡድን ጋር ለሚፋለሙት ከልባችሁ ዱዓ አድርጉላቸው።
በየመን የሚካሄደውን ጦርነት በሚዲያ እንደሚራገበው በፖለቲካዊ ግጭት ወይም በውስጣዊ ጦርነት ብቻ አትገድቡት። በጉዳዩ ውስጥ የሃይማኖት፣ የዐቂዳና የህልውና ጉዳዮች ተደባልቀው አሉ። የኢራን ተላላኪ የሆነው የሁቲ ቡድን ሰሐቦችን رضي الله عنهم መስድብና በህፃናት ላይ ሳይቀር የሰሐቦችን ጥላቻ ማስረፅ ዋና አላማው ነው።
ሰሓቦች رضي الله عنهم የአላህን ዲን የተሸከሙና የአላህ መልእክተኛ ﷺ ሱናን ለእኛ ያስተላለፉ የሚወደዱ ሰዎች ናቸው። እነርሱን መውደድ ዲንን መውደድ ነው፤ ክብራቸውን መጠበቅና በጎነታቸውን ማብራራትም እውነትን መደገፍ ነው።
ስለዚህ የአላህ ባሮች ሆይ፣ ወንድሞቻችሁን በዱዓችሁ አትርሱ። በሱጁድ፣ በሌሊት መጨረሻ፣ በአዛንና በኢቃማ መካከል ዱዓ አድርጉላቸው። አላህ የየመንን ሕዝብ ክብርና ደማቸውን እንዲጠብቅ ከጭቆናና ከፈተና እንዲያድናቸው ለምኑት።
አላህ ሆይ፣ የየመንን ሕዝብ ጠብቅ። አላህ ሆይ፣ ከመከራና ከፈተና አላቅቃቸው ደኅንነታቸውን፣ ክብራቸውንና ንብረታቸውን ጠብቅ። የቆሰሉትን ፈውስ፣ የሞቱትን ማር፣ ችግራቸውንም ፍታላቸው።
አላህ ሆይ፣ የሱና ሰዎችን በእውነት ላይ አጽና፣ ዐቂዳቸውን ጠብቅ፣ በእውነት ላይ አንድ አድርጋቸው፣ ከግልፅም ድብቅም ከሆነው ፈተና ሁሉ ጠብቃቸው።
ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ፣ ለእነርሱ በእውነትና በቅንነት ዱዓ አድርጉ፤ ዱዓ አድርጉ፤ ዱዓ አድርጉ። ምክንያቱም ሙእሚን ወንድሞቹን አይረሳም፤ ከእርሱ ሀገር ሩቅ ቢሆኑም መከራቸውን ቀላል አድርጎ አይመለከትም።
የሁቲ ራፊዷዎች ዋና አላማ እስልምናን ማውደም ነው ወደኋላ ዞር ብሎ ታሪካቸውን ያጠና ይህንን እውነታ በደንብ ይገነዘባል። በሚዲያ እንደምንሰማው መካ ላይ ጥቃት ለመሰንዘርም ይዝታል። አላህ ያውድማቸው አላህ አስደናቂ ሀይሉን በነርሱ ላይ ያሳየን አላህ ሳውዲንም ከነቅዱሳን ከተሞቿ ይጠብቃት።
👌የኢኽዋን መንጋ አፍንጫው መሬት ቢልስም እኛ ለሳውዲ ዱዓ ከማድረግ ኢራንና ሁቲዎችን እንዲቀጣልንና ከሸራቸው እንዲበቃን ከመለመን አንቦዝንም ኢንሻአላህ
✍ አቡ አብድልመናን
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ሙስሊም መሪን በተመለከተ የሸይኽ ረቢዕ አልመድኸሊይ አቋም ቁርኣንና ሐዲሥ ላይ የተመሰረተ ነው። ኢኽዋኖችና የነሱ ፍልፍሎች እንደሚቀጥፉባቸው ሸሪዐ በማይፈቅደው መልኩ መሪዎችን በመታዘዝ ላይ የሚሰብኩ አልነበሩም። ከብዙ ንግግሮቻቸው ውስጥ አንድ ማስረጃ ላቅርብ፦
"እኛ፣ በአላህ እንምላለን፤ ሰይፎች በአንገታችን ላይ ቢደገኑ እንኳን፣ ውሸትን ወይም የተሳሳተ ነገርን መናገር ፈጽሞ የምንፈቅድ አይደለንም።
የምንለው፦ “መሪዎችን አላህን መታዘዝ ባለበት ጉዳይ ላይ ታዘዝ፤ አላህን ማመፅ ባለበት ጉዳይ ግን አትታዘዛቸው” ነው።
“መሪዎችን አላህን መታዘዝ ባለበት ነገር ታዘዙ፤ አላህን በማመፅ ባለበት ነገር ግን አትታዘዟቸው።” ይህ ኢስላማዊ መርህ ነው ወይስ እስላማዊ መርህ አይደለም?
እኔ ይህንን እውነት ነው ለወጣቶች የማቀርበው፣ እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነውን መብትና በላዩ ያለውን ግዴታ እንዲያውቅ ነው። እንዲሁም የነቢዩ ﷺ ትምህርት ያሰመሩበትን መንገድ፣ እንደነገርኳችሁ፣ በትክክል እንዲያውቁ እገልጻለሁ።
እኛ የእውነትን ቃል በድፍረት እንናገራለን፤ በአላህ ጉዳይም የሚወቅሰንን ሰው ምንም አንፈራም፤ ይህም በገዢውም ሆነ በተገዢው ላይ ነው።
ስለዚህ አላህ በማመፅ በሆነ ነገር ላይ ማንኛውንም ገዢ አትታዘዙ፤ አላህን በመታዘዝ ባሉበት ነገር ግን ታዘዟቸው። ይህ ግዴታ ነው።"
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
♦️♦️♦️እህቴ ሆይ…አቤት ብለሽ ማንበብ እንደጀመርሽ ተስፋ አደርጋለሁ
📌መልካም የሆነን ባል ለረጅም ጊዜ ስትጠብቂ ቆይተሻልን?
ብዙ ጊዜ በሌሊት እጆችሽን ወደ ሰማይ አንስተሽ፣ በእንባ ዓይኖችሽን ሞልተሽ፣
“ያ አላህ! የእኔ ተራ መቼ ነው? በሩን አንኳክቶ ወደ ሕይወቴ የሚገባው ሰው መቼ ነው?” ብለሽ ይሆናል።
📍ጓደኞችሽ አንድ በአንድ ሲዳሩ አይተሽ ይሆናል። አንቺ ግን አሁንም ትጠብቂያለሽ።
🔷ሰዎችም ልብሽን በሚያሳምሙ ቃላት፦
“መቼ ነው የምትዳሪው?”
“ለምን እስካሁን ዘገየ?”
ብለው ይጠይቁሽ ይሆናል።
ነገር ግን እህቴ ሆይ፣ ማንም ሰው ሊያውቀው የማይችለውን አንድ እውነት አስታውሺ፦
አላህ አልረሳሽም!
እንባሽን ያውቃል።
የልብሽን ህመም ያውቃል።
የምስጢር ዱዓሽን ይሰማል።
ማንም ሰው የማያውቀውን ያንቺን ልብ ያውቃል።
አንቺ ገና ያላወቅሽውን ሰው እንኳን አላህ ያውቀዋል።
ስለዚህ የትዳርሽ መዘግየት እንዲሰብርሽ አትፍቀጂ።
ይልቁንም ወደ አላህ የሚያቀርብሽ ይሁን።
📍ሌሊት ሰዎች በተኙበት ጊዜ ተነሺ። ሁሉም ዝም ባለበት ጊዜ ከአላህ ጋር ተነጋገሪ።
እጆችሽን አንስተሽ እንዲህ በይ፦
“ያ አላህ! ማንኛውንም ወንድ አልፈልግም። አንተ ለእኔ የመረጥከውን ሰው እፈልጋለሁ።
ያ አላህ! አንተን የሚፈራ፣ ሶላቱን የሚጠብቅ፣ ቁርአንን የሚወድ፣ በእኔ ላይ የሚራራ፣ የሚያከብረኝ እንጂ የማያዋርደኝ፣ ስሳሳት በርኅራኄ የሚመክረኝ፣ ስደክም የሚያግዘኝ፣ በአንተ መታዘዝ ላይ የሚረዳኝን ባል ስጠኝ።”
ከዚያም የነበዩ ሙሳን عليه السلام ዱዓ አስታውሺ፦
﴿رَبِّ إِنِّي لِمَا أَنْزَلْتَ إِلَيَّ مِنْ خَيْرٍ فَقِيرٌ﴾
“ጌታዬ ሆይ! ከአንተ ወደ እኔ ለምታወርደው ማንኛውም መልካም ነገር በጣም ተፈላጊ ነኝ።”
እህቴ ሆይ…
ምናልባት ዛሬ በመዘግየቱ ታለቅሺ ይሆናል፤ ነገ ግን ወደ ኋላ ተመልሰሽ፦
“ያ አላህ! ያኔ ያንን ሰው ለምን አልሰጠኸኝም ብዬ ነበር፤ አሁን ግን ለምን ከእሱ እንደጠበቅኸኝ ገባኝ። አልሐምዱሊላህ!” ትዪ ይሆናል።
ምናልባት የምትፈልጊው ሰው አላህ ላንቺ የማይስማማ መሆኑን ያውቃል።
ምናልባት እሱ የልብ ሰባሪሽ ይሆን ነበር።
ምናልባት ዲንሽን ያዳክም ነበር።
ምናልባት ልጆችሽ የማይገባቸውን ነገር እንዲያዩ ምክንያት ይሆን ነበር።
አንቺ ግን አታውቂም፤ አላህ ያውቃል።
ስለዚህ አንድ በር ሲዘጋ አታልቅሺ፤ ምናልባት ከኋላው ያለውን ጉዳት አላህ እያራቀልሽ ይሆናል።
አደራ አደራ ......
በትዳር መዘግየት ምክንያት የማይመችሽን ሰው አትቀበዪ።
የትዳር ጉዳይ የአንድ ቀን ደስታ ብቻ አይደለም።
ትዳር ዕድሜ ነው።
ትዳር ቤተሰብ ነው።
ትዳር ልጆች ናቸው።
ትዳር ዲን ነው።
ትዳር የወደፊት ሕይወት ነው።
ስለዚህ ከገንዘብ፣ ከውበትና ከማዕረግ በፊት ዲንና መልካም ሥነ-ምግባር ተመልከቺ።
ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«إذا جاءكم من ترضون دينه وخلقه فزوجوه»
“ዲኑንና ሥነ-ምግባሩን የምትወዱት ሰው ወደናንተ ከመጣ አጋቡት።”
እህቴ ሆይ…እያነበብሽ ነዋ
አላህ የጻፈልሽ ነገር በፍጹም አያመልጥሽም።
ሰዎች ቢያግዱት ይመጣል።
ሩቅ ቢሆን አላህ ያቀርበዋል።
ጊዜው ቢዘገይ ጊዜው ሲደርስ ይመጣል።
አላህ ያልጻፈልሽ ነገር ግን ሰዎች ሁሉ ቢሰበሰቡ ሊያገኙልሽ አይችሉም።
ስለዚህ እንዲህ በይ፦
“ያ ረቢ! እኔ በአንተ እተማመናለሁ። ለእኔ ምረጥልኝ፤ እኔ ለራሴ የማላውቀውን አንተ ታውቃለህ። ለእኔ የሚሆነውን አንተ ምረጥ።”
ከዚያም ልብሽን አሳርፊ።
አትጨነቂ።
አትቸኩዪ።
ተስፋ አትቁረጪ።
የአላህን ምሕረት አትጠራጠሪ።
ምክንያቱም…
እንባሽን ያየ አላህ አለ።
ዱዓሽን የሰማ አላህ አለ።
ልብሽን የሚያውቅ አላህ አለ።
ዕጣሽንም በእጁ የያዘ አላህ አለ።
በመጨረሻም
አላህ ሆይ! በሙስሊም ሴቶች ልብ ውስጥ ያለውን፣ አንተ ብቻ የምታውቃቸውን ምኞቶች ፈጽምላቸው።
አላህ ሆይ! ለእነርሱም ሳሊህ ባሎችን ስጣቸው፤ በዲናቸው ላይ የሚረዷቸውን፣ የሚያከብሯቸውን፣ የሚወዷቸውንና በእነርሱ ጉዳይ አንተን የሚፈሩትን ስጣቸው።
አላህ ሆይ! የተሰበረ ልብ ካለ አጽናው። ብቸኛ ልብ ካለ አጽናናው። የሚጠብቅ ልብ ካለ በመልካም ነገር አስደስተው።
አላህ ሆይ! ከእያንዳንዱ መጠበቅ እፎይታን፣ ከእያንዳንዱ ዱዓ መልስን፣ ከእያንዳንዱ ሐዘን ደስታን ስጣቸው።
አላህ ሆይ! ባል የሌላት አንዲትም ሴት አትተው፤ ለእሷ የሚሆን ሳሊህ ባል ስጣት። የተሰበረ ልብ አትተው፤ ጽናትና ደስታ ስጠው።
አላህ ሆይ! በኢማን፣ በፍቅር፣ በምሕረትና በሰላም የተሞሉ ቤቶችን ስጣቸው።
አሚን ያ ረብ
ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ
https://telegram.me/abutoiba
https://telegram.me/abutoiba
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የማለዳ መልእክት (49)
~
ልጆቻችን አካዳሚ ትምህርት መማራቸው እና በዚህ ላይ መጎበዛቸው ይበል የሚያሰኝ ነው። በዚህ ላይ ማገዝና ሞራል መስጠትም ተገቢ ነው። ይሄ የሚሆነው በዲናዊ ትምህርት ሂሳብ ከሆነ ግን ትርፍ ሳይሆን ኪሳራ ነው።
* ልጆቻችን ሶላት ይሰግዳሉ ወይ? ቁርኣን እና ሌሎችም ኢስላማዊ ትምህርቶችን ይማራሉ ወይ? በዚህ በኩል ከሌሉ በአካደሚ ትምህርት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸው ትርጉም የለውም። እንዲያውም ሊጎዳቸው ይችላል። ዲናቸውን ካላወቁ በየትምህርት ዓይነቶቹ ውስጥ የተሰነቀሩ ብልሹ አስተሳበቦችን ሳያመዛዝኑ ይውጣሉ። የዲንን ዋጋ እና የአለማመንን አደጋ በቅጡ ስለማይለዩ እንደዋዛ ከኢስላም ሊወጡ ይችላሉ። ስማቸው የሙስሊም የሆኑ ግን ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን በየዩኒቨርሲቲው ውስጥ አሉ። የአካደሚ ትምህርት ደረጃቸው የሚያላብሳቸው ትእቢት ስላለ ምክር ለመስማትም ዝግጁ አይደሉም። (አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ስማቸው የሙስሊም የሆኑ፣ ግን ከነ ጭራሹ እስልምና ውስጥ የሌሉ፣ ሰው ግን ሙስሊም አድርጎ የሚያስባቸው ሁለት ዶክተሮችን አውቃለሁ።)
* በሃገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ልጆችን ማበረታታትና መሸለም ጥሩ ሆኖ ሳለ መነጋገሪያ ያደርግንበት መንገድ ግን በጣም የተጋነነ ነው። ቁርኣን ሒፍዝ የጨረሱ፣ በተለያዩ ሃገራት ለአመታት ተንከራተው ጥሩ የዒልም ደረጃ ላይ የደረሱ ደረሶችን ግን ዞሮም የሚያያቸው የለም። ከስር እየመጡ ላሉት ተተኪዎች ምንድነው እያስተላለፍን ያለነው? ይህንን የተራራቀ አቀራረባችንን እያዩ ለዲናቸው ትኩረት ይሰጣሉ ወይ?
* የዲን ትምህርት ለምን የትርፍ ጊዜ ትምህርት ይሆናል? ክረምት ብቻ፣ ቅዳሜና እሁድ ብቻ፣ ... እየሆነ ነው። ለአካደሚው ግን ሁለ ነገራችንን እየሰጠን ነው። በግል ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለን እናስተምራለን። መጥፎ ነገር የማያዩበት የተሻለ ድባብ ያለበት ግቢ መምረጣችን ይሁን። ለቁርአን ትምህርት ግን የዚያን ግማሽ እንኳን ከፍለን ማስተማር አንፈልግም። ለአካደሚ ትምህርቱ ተጨማሪ ከፍለን አስጠኚ እናደርጋለን። ለቁርኣንና ኪታብ ትምህርቶች ግን የረባ ቦታም የለንም።
እነዚህ ነገሮች ከጊዜያዊ ትኩረታችን መራራቅ ባለፈ በልጆቹ አእምሮ ላይ እያስቀመጥነው ያለው ነገር ይበልጥ አደገኛ ነው፡፡ የዲን ትምህርት መማር ያን ያህል አንገብጋቢ እንዳልሆነ በተግባር እያሰርፅንባቸው ነው። በዚህ ላይ ሶላት አለመስገድ ሲጨመርበት፣ ክፍተታቸው የበዙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚማሩ ከሆነ፣ በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ አፍላ እድሜ ላይ ሲደርሱ ለመግለፅ የሚሰቀጥጥ ኪሳራ ይደርሳል። ስለዚህ ሳይቃጠል በቅጠል።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል ኣኺር 05/1448)
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from ስለ ቀልባችን
❝ድንግል ስላልሆንኩ ትዳርን እፈራለሁ ላለች እህት የተላከ መልእክት!❞
~
ውድ እህቴ ሆይ!
ሰው ነሽና ተሳስተሻል፤ አማኝ ነሽና ተፀፅተሽ ወደ ጌታሽ ሮጠሻል። አላህ ደግሞ ተውበት አድራጊዎችንና ወደ እርሱ የሚመለሱትን
እጅግ ይወዳል። ታዲያ ይቅር ባዩ ጌታሽ በራሕመቱ የሸፈነልሽን ስህተት ይዘሽ፣ ዛሬም ድረስ ራስሽን የምትወቅሺውና የሐላሉን የትዳር በር በራስሽ ላይ የምትቆልፊው እስከ መቼ ነው?
እውነተኛው ንፅህና የተውበት እንባ ያጠበው የልብ ንፅህና ነው። ረሱል (ﷺ) «ከወንጀሉ የተመለሰ ሰው ልክ ምንም ወንጀል
እንዳልነበረው ነው» ብለውናል።
ሸይጣን ሁለት ጊዜ ያጠቃሻል፦
1. በመጀመሪያው ወቅት ወደ ወንጀል እንድትገቢ አታሎሻል፤
2. ዛሬ ደግሞ «አንቺ ድንግል አይደለሽም፣ ስለዚህ ለትዳር ብቁ አይደለሽም፣ ነገ ትዋረጃለሽ» እያለ በተስፋ መቁረጥ እና በብቸኝነት ወጥመድ ውስጥ እንድትኖሪ ይፈልጋል።
● ጥያቄ 1፡ «ቢክራ ሳልሆን እንዴት አገባለሁ? ለማግባት ብቁ ነኝ?»
- ምላሽ፡- አዎን፣ ሙሉ በሙሉ ብቁ ነሽ! ትዳር በኢስላም ለድንግሎች ብቻ የተፈቀደ ሸቀጥ አይደለም። የነቢያችን ﷺ ሚስቶች ከእናት አዒሻህ በስተቀር ሁላቸውም ቀደም ሲል ያገቡ (ቢክራ ያልነበሩ) ናቸው።
በሸሪዓው ሚዛን የሴት ልጅ ትልቁ ክብር የሚለካው በዲኗ፣ በስነ-ምግባሯና አላህን በመፍራቷ እንጂ በአንድ የአካል ሽፋን ብቻ አይደለም።
● ጥያቄ 2፡ «ለሚጠይቀኝ ሰው ያለፈውን ህይወቴን መንገር አለብኝ?»
- ምላሽ፡- ፈጽሞ የለብሽም! ኢስላም ያለፈን ወንጀል መዘርዘርን ያወግዛል። አላህ በምህረቱ የሸፈነልሽን ነውር ለሰው መግለጥ «ሙጃሀራህ» (ወንጀልን ይፋ ማድረግ) ስለሚሆን ይከለከላል። ማንም ሰው መርማሪ ፖሊስ ሆኖ የቀደሞ ህይወትሽን ሊመረምር አይፈቀድለትም፤ አንቺም የመናገር ምንም ዓይነት ሸሪዓዊ ግዴታ የለብሽም።
● ጥያቄ 3፡ «ወንዱ 'ቢክራ መሆን አለባት' ብሎ በግልፅ ቢያስቀምጥስ?»
- ምላሽ፡- አንድ ወንድ ድንግልናን ጥብቅ መስፈርት አድርጎ ካስቀመጠ፣ መዋሸት አያስፈልግሽም፤ በዚያው ልክ ደግሞ «እኔ እኮ እንዲህ ሆኜ ነው ያጣሁት…» ብለሽ ራስሽን አትግለጪ።
አጭሩ መልስ፦ «እኔና አንተ በመስፈርት አንጣጣምም፤ አላህ የተሻለውን ይስጥህ» በማለት ጥያቄውን ውድቅ አድርጊው።
● ጥያቄ 4፡ «ወንዱ ስለ ድንግልና ምንም ካላነሳስ?»
- ምላሽ፡- ወንዱ ስለ ቢክራ ምንም ካላነሳና ትኩረቱ ስነ-ምግባርሽ፣ ዲንሽና አብሮ መኖር ላይ ከሆነ፤ ጉዳዩን ፈጽሞ ማንሳት አያስፈልግሽም። ጥያቄውን በደስታ ተቀብለሽ ወደ ኒካህና ወደ ትዳርሽ መሻገር ሙሉ በሙሉ ይፈቀድልሻል።
ስለዚህ ይህንን ጉዳይ ለጓደኛ፣ ለቤተሰብም ሆነ ለማንም ሰው አትናገሪ። በአንቺና በአላህ መካከል የቀረ ሚስጥር ይሁን።
ከአሁን በኋላ የሚመጡትን የትዳር ጥያቄዎች «ቢክራ ስላልሆንኩኝ» በሚል ሰበብ ብቻ ውድቅ አታድርጊ። ወንዱ ቅድመ-ሁኔታ እስካላደረገው ድረስ፣ እንደማንኛውም ሴት ኢስቲኻራህ አድርገሽ ተቀበይ።
«ያ አላህ! በምህረትህ ሸፍነኸኛልና በትዳሬም ውስጥ ነውሬን ሸፍንልኝ፤ የሚያከብረኝንና ወደ አንተ የሚያቀርበኝን ሷሊሕ ባል ወፍቀኝ» በማለት ዘወትር ዱዓ አድርጊ። አብሽሪ!
---
t.me/Sle_qelbachn1
t.me/Sle_qelbachn1
