የቀጠናው ተመልካች
Відкрити в Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
4 321
Підписники
+824 години
-47 днів
-7130 днів
Архів дописів
4 330
🇩🇪🇾🇪🇸🇦⚡️ — የጀርመኑ ቻንስለር ፍሬድሪክ መርዝ በየመን፡
ሁቲዎች አሁን በባብ አል ማንዳብ ዙሪያ ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን ተቆጣጥረዋል። በሳውዲ ዓረቢያ የኃይል ማመንጫዎችን እያጠቁ ነው። ይህ ሁኔታ በኃይል ገበያው ላይ ያለውን ሁኔታ የበለጠ እያባባሰው ሲሆን ጀርመንም ተፅዕኖው እየተሰማት ነው። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁቲዎች ቀይ ባህርን እንዲቀጥሉ መፍቀድ አይችልም።
4 330
🇩🇪🇮🇷⚡️ — የጀርመኑ ቻንስለር ፍሬድሪክ መርዝ በኢራን ላይ፡
ኢራን በመጨረሻ ይህንን የሆርሙዝ እገዳ ማቆም አለባት። ከምንም በላይ ወታደራዊ የኒውክሌር ፕሮግራሟን ማቆም አለባት። ቴህራን በመላው ቀጣናው ለፕሮክሲዎች የምታደርገው ድጋፍ መቆም አለበት። ውጤቱን በየቀኑ እያየን ነው። በተጨማሪም ኢራን ግጭቱን ወደ ኢራቅ እንዳትወስድ እንጠይቃለን።
4 330
🇸🇦🇪🇺⚡️ — ሳዑዲ ዓረቢያ በሴፕቴምበር ላይ ድፍድፍ ዘይት ለመጫን ከአውሮፓ ነዳጅ ማጣሪያዎች ወስዳ የነበረውን ትእዛዝ መሰረዟን ገለጸች። ይህን ያለችው፣ በድሮን ጥቃቶች የምስራቅ-ምዕራብ የቧንቧ መስመር ላይ ያሉ ሦስት የፓምፕ ጣቢያዎች ከጥቅም ውጭ ከሆኑ በኋላ ነው።
ኤክስፐርቶች፣ የወደመውን ቧንቧ መስመር ለመጠገን ወራቶች ሊወስድ እንደሚችል አሳስበው፣ በዓለም ገበያ ሊፈጠር ለሚችለው እጥረት ሀገራት ከወዲሁ መጠባበቂያቸው እንዲያዘጋጁ መክረዋል።
4 330
🇮🇷/🇺🇸/🇷🇺/🇺🇦 ፕሬዝደንት ትራምፕ ለመገናኛ ብዙኃን ከተናገሩት በተቃራኒ፣ የናፍጣ ነዳጅ ዋጋ የጨመረው የዩክሬን ጥቃት በሩሲያ ኢነርጂ ተቋማት ላይ ስለተደረገ አይደለም።
የናፍጣ ዋጋ ጣሪያ የደረሰው በኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ላይ ከተደረገው ጦርነት በኋላ ነው --- The Washington Post
*-*-*-
ናፍጣ፣ ከጋዝ የሚለይ ሲሆን ከባባድ የፋብሪካ ማሽነሪዎች፣ ከባባድ መኪኖች፣ የእርሻ መሳሪያዎች እና በዋናነት ፔትሮኬሚካል ፋብሪካዎች በግብአትነት የሚጠቀሙበት raw material ነው። ፕላስቲክ የሚሰራው ከናፍጣ ነው። እንዲሁም ጋዝ ጋር ተደባልቆ የተጣራ የሚያደርገው ናፍጣ ነው።
የዋጋው መናር፣ አሜሪካ ውስጥ በአሁኑ ሰዓት፣ በተለይ ገበሬውን እና ከባባድ የጭነት መኪና ባለቤቶችን፣ ያስጨነቀ ጉዳይ ነው።
4 330
🚨 🇸🇦⚡️🇾🇪 ሰበር ዜና: በሳዑዲ አረቢያ ያንቡ፣ ጅዳ፣ ጣኢፍ፣ አብሃ፣ አል-ኡላ እና ኻሚስ ሙሻይት ላይ፣ ከፍተኛ የሆነ የየመን የሚሳኤል ጥቃቶች በመደረግ ላይ ናቸው።
በብዙ የሳዑዲ ግዛቶች ትምህርት ቤቶች፣ አየር ማረፊያዎች እና የመንግሥት ተቋማት ተዘግተዋል።
የባላስቲክ ሚሳኤል እና የድሮን ጥቃቱ እንደቀጠለ ነው።
*-*-*-
4 330
🇸🇦⚡️ሳዑዲ የመን ላይ የሙጥኝ ያለችው ለምንድነው? በየመን እንዲህ የምትንገበገበው ምን ስላለ ነው? ምን ፈልጋ ነው?
ለምን የመንን አትተዋትም እና መሠረተ-ልማቶቿን ከውድመት አትታደግም?
4 330
🇾🇪❌🇸🇦 — የአንሷረላህ (ሁቲ) የፖለቲካ ቢሮ አባል እና የሹራ ምክር ቤት ሰብሳቢ፣ ሀዛም አል አሳድ፡
ያፋፋመው ላይ አፋፍምበት! የጀመረው የበለጠ ኢፍትሃዊው ነው።
4 330
🇺🇸🇮🇷⚡️ — የአሜሪካ የነዳጅ ዘይት ሥራ አስፈፃሚዎች፣ የንግድ ምርቶች እየቀነሱ እና ስትራቴጂካዊ ክምችቶች ወደ ገደባቸው በመቃረባቸው በሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት ምክንያት የተነበዩት ዓለም አቀፍ የነዳጅ ቀውስ፣ አሁን መድረሱን እያስጠነቀቁ መሆኑን WSJ ዘግቧል።
የቼቭሮን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማይክ ዊርት እንዳለው፣ መጀመሪያ ላይ በኢራን ጦርነት ምክኒያት ገበያዎች እንዳይወድቁ ይከላከሉ የነበሩ ብዙ መጠባበቀቂያዎቻችን፣ አሁን ተጠናቀዋል፣ ብሏል።
ሲፈራ የነበረው ቀውስም፣ ደጃፍ ላይ እንደደረሰ ጨምሮ ተናግሯል።
ከየመን የተነሱ የድሮን ጥቃቶች የሳውዲ ዓረቢያ የምስራቅ-ምዕራብ የቧንቧ መስመርን በአብዛኛው ከመስመር ውጭ ካደረጉ በኋላ፣ ሁኔታው ተባብሷል፣ ያለው ሌላው ሥራ አስፈፃሚ፣ ይህም ቀድሞውኑ ውስን ከሆነው ገበያ ላይ በቀን በግምት 3.5 ሚሊዮን በርሜል አስወግዷል፣ ሲል ተናግሯል።
የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር በበኩሉ፣ ሊፈጠር ጫፍ የደረሰው ቀውስ "ጊዜያዊ" መሆኑን በመግለጽ፣ የቬንዙዌላን ምርት ለማሳደግ እና የዩናይትድ ስቴትስን የማጣራት አቅም ለማስፋፋት እየሞከረ መሆኑን ተናግሯል።
4 330
🇸🇦⚡️🇾🇪 ከጥቂት ሰዓታት በፊት ሳዑዲ ዓረቢያ በአብሃ፣ ኻሚስ ሙሻይት እና በሌሎች በርካታ የአገሪቱ አካባቢዎች የትምህርት እንቅስቃሴዎችን ማቋረጧን አስታወቀች።
የተጠቀሰው ምክንያት፣ "ዝናብ ስለሚጥል" የሚል ነው (በዓለም ላይ አነስተኛ ዝናብ ያለበት ሀገር፣ በዚህ ሰዓት ቅልጥ ያለ ዝናብ ሊያስተናግድ)።
በሳውዲ ዓረቢያ በቀጣዮቹ 24 ሰዓታት ዝናብ የመውረድ ዕድሉ ዜሮ (0%) መሆኑን ልብ ይበሉ እና አካባቢዎቹ በአሁኑ ጊዜ በሮኬት ጥቃት ከሚሰነዘርባቸው ጋር የሚዛመዱ ናቸው።
*-*-*
4 330
+1
🇺🇦❌🇷🇺 — የዩክሬን ድሮኖች በሩሲያ ሲዝራን፣ ግዙፉን የነዳጅ ማጣሪያ መትተዋል። በማጣሪያው ውስጥ በርካታ እሳቶች ይታያሉ።
*-*-*-
ሳይውል ሳያድር
4 330
🇸🇦🇹🇷🇵🇰 ሳውዲ ዓረቢያ፣ ፓኪስታን እና ቱርክ አንድ ላይ ተሰባስበዋል።
ኤርዶጋን፣ የመካ ስምምነትን "አዲስ እርምጃ" ሲል አወድሶታል።
"ለእስላማዊው ዓለም ግልፅ መልዕክት መላክ እንፈልጋለን፣ እነዚህ አዎንታዊ እድገቶች ናቸው... ... አላህ ቢሻ በእርግጥ እናሸንፋለን" ብሏል።
*-*-
በካራቴ ነው የምንጠርባችሁ ነው የሚለው፣ ግን የታል በተግባር? ሳዑዲን ታዲያ ለምን ሳትረዷት እንደዛ እየለመነቻችሁ …? ቅር አሰኝታችሁኛል!
4 330
⚡️🇺🇸🇺🇦 ትራምፕ፡ ዩክሬን የሩስያ ኢነርጂ ኢላማዎችን ላለመምታት ተስማምታለች። ሩሲያም እንዲሁ ለማድረግ ተስማምታለች! የዓለም የናፍጣ የዋጋ ጭማሪ በአብዛኛው የተከሰተው በኢራን ሳይሆን በሩሲያ/ዩክሬን ጦርነት ነው።
*-*-*-
አይመስለኝም የተከበሩ ፕሬዝዳንት!
አውሮፓዊያን፣ በተለይ ጀርመን፣ እንግሊዝ እና ፈረንሳይ፣ እስካሉና በንግድ ልውውጥ ወይም በኔቶ ፈንዲንግ እስካልተቆነጠጡ ድረስ፣ ዩክሬን መዋጋቷን አታቆምም!
እንዲያውም በአሁኑ ሰዓት፣ አሜሪካ ከኔቶ ራሷን ስታስወጣ ብቻ ነው፣ ጦርነቱ ያለማወላወል ሊቆም የሚችለው።
የአውሮፓዊያን የሁልጊዜም ትጋት፣ የአሜሪካን ጦርነቱን የመቋጨት ፍላጎትን በማምከን፣ ለዓመታት ማስቀጠል ነው።
በሩሲያ፣ ምስጋና ለፑቲን ድክመት ይሁንና፣ ክፍተት አይተዋል።
4 330
🇸🇦/🇪🇬/🇾🇪 የሳውዲ አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሰልማን የግብጡን ፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አል ሲሲን ነገ በካይሮ ይገናኛል።
ሳዑዲ አረቢያ ግብጥን ሁቲዎችን ለመጋፈጥ እርዳታ ትጠይቃለች ተብሏል።
*-*-*-*-
ግብጥም ተጠየቀች
4 330
🇬🇧🇸🇦🇾🇪⚡️ — የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዲ በርንሃም በየመን ቀይ ባህር ዳርቻ የሁቲ (አንሷሩላህ) ጥቃቶች እና ግስጋሴዎች እየተባባሱ በመምጣታቸው ለሳውዲ ዓረቢያ ድጋፍ እያሰበ ነው ሲል ብሉምበርግ ዘግቧል።
ሪያድ ስትራቴጂክ ባብ ኤል-ማንደብ ወሽመጥ አቅራቢያ ያሉትን ሁቲዎች ለመቋቋም እና የሳውዲ የነዳጅ መሠረተ ልማትን ከጥቃት ለመከላከል የተግባር ድጋፍን ጨምሮ ዲፕሎማሲያዊ እና ወታደራዊ እርዳታን ከእንግሊዝ ጠይቃለች።
በርንሃም፣ የብሪታንያ የጦር አማካሪዎችን ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ለማሰማራት ተስማምቷል፣ ምንም እንኳን የሪያድ ሌሎች ጥያቄዎችን ማጽደቁ ባይታወቅም።
*-*-*-
ልመና ሱስ ነው! አንዴ ለማኝ ከሆንክ፣ ራስህን በራስህ ለመቻል አትችልም።
ሳዑዲን የምታክል ግብዳ ሀገር፣ ሽርጥ ያገለደሙና ጫት የወጠራቸው፣ ባለ ሸበጥ ጫማ ጦር ሰራዊቶችን ብቻዋን አቅቷት… ድመት ስትሆን… ሀብት ንብረቷ እያየችው ሲወድምባት ……
🇹🇷🇵🇰 ባለፈው ሳምንት ፓኪስታንን እና ቱርክን ጠየቁ፣ እምቢ ተባሉ።
🇺🇸 አሜሪካኖችን ጠየቁ፣ አግዙን ብለው፣ እምቢ ተባሉ።
🇮🇱 ትናንት እስራኤልን መጠየቋ ተሰማ፣ እምቢ ተባለች።
🇬🇧 ዛሬ ደግሞ እንግሊዝን …
መጀመሪያ ከዚሁ ሁሉ በፊት ወደ ፈጣሪ ቢጠይቁ ኖሮ፣ ውጤት ያዩ ነበር። እሱ ላይ የሉበትም።
4 330
🇮🇷🇺🇸⚡️የኢራን ጦርነት ለባሕረ ሰላጤው ሀገራት አንድ ነገር ግልፅ አድርጓል፡- 'የአሜሪካ የፀጥታ ዣንጥላ ከአሁን በኋላ የሚታመን አይደለም። 'የባሕረ ሰላጤው ሀገራት ያለ ማስጠንቀቂያ፣ ምክክር እና ጥበቃ ነው ወደ ቀጠናዊ ጦርነት ተጎትተው የገቡት። ጦርነቱንም እንደሚታየው ዋሽንግተን ለማስተዳደር ወይም ለማሸነፍ 'አልቻለችም ወይም አልፈለገችም።' --- TIME
