uk
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Відкрити в Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
4 330
Підписники
+2824 години
+307 днів
-4230 днів
Архів дописів
🇬🇧🇷🇺🇦⚡️ - የቀድሞ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጀንሰን፣ አመለጠ ስለተባለው የድሮን ጥቃት እና ስለ ቭላድሚር ፑቲን፡
ይህ ሰው በፍፁም እየተሸነፈ ያለ ሰው ነው። በግንባር ላይ ብዙ ጦሩን እያጣ ነው፣ እና በዩክሬን  ጀግኖች ሰራተኞች እና ተሳፋሪዎች ላይ የሽብር ጥቃት እየፈፀመ ነው።

🇩🇪 መርዝ፡ ምናልባትም የአህጉራችንን ነፃነት እና ሠላም ለመጠበቅ በጣም ወሳኝ ጊዜዎችን - ምናልባትም ሳምንታት ወይም ወራትን - እያየን ነው። ሩሲያ ከተሳካላት፣ ይህ ጀርመንን ጨምሮ ለሁላችንም የማይገመት እና ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ውጤት ይኖረዋል። ለዚህም ነው እኔ እዚህ ቆሜ በጣም ጽኑ ፣ በጣም ግልፅ ፣ እና አንድ ሴንቲ ሜትር ወደ ኋላ ለመመለስ ፈቃደኛ ያልሆንኩት። *-*-*- 78 በመቶ የጀርመን ሕዝብ፣ ፍሬድሪክ መርዝ በአስቸኳይ ሥልጣኑን እንዲለቅ ይፈልጋል። ቻንስለሩ በጀርመን የመሪነት ቅቡልነቱ እጅግ የወረደ ሆኗል፣ በዋናነት በኢኮኖሚው እና ለሩሲያ ባለው ጠላትነቱ የተነሳ።

🇸🇦⚡️🇾🇪 አንሷሩላህ (ሁቲ) በሳውዲ ዓረቢያ የምስራቅ-ምዕራብ (መዲና- ቀይ ባሕር) የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ላይ ያደረሰው ውድመት፣ ሲባል ከነበረው በላይ ነው። ምስሉ፣ ከሳተላይት የተወሰደ 'የበፊትና የበኋላ' ምስል ነው። -*-*- ከስሏል እኮ፣ ምንም የቀረ የለም!

🇾🇪🇸🇦⚡ - በሳውዲ ዓረቢያ ደቡባዊ ክፍል በርካታ ቦታዎች ላይ፣ ፍንዳታዎች ተሰምተዋል።

🇾🇪❌️🇸🇦 ምሽቱን የየመን ሚሳኤሎችን ቀጥተኛ ጥቃት ተከትሎ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ፡ ምንም አይነት መሰባሰብ እና ፎቶግራፍ ማንሳትን ክልክል ነው!ይህን ሕግ ሲጥስ የተገኘ ወየውለት፣ ጨዋታ አቁመናል!
🇾🇪❌️🇸🇦 ምሽቱን የየመን ሚሳኤሎችን ቀጥተኛ ጥቃት ተከትሎ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ፡
ምንም አይነት መሰባሰብ እና ፎቶግራፍ ማንሳትን ክልክል ነው!ይህን ሕግ ሲጥስ የተገኘ ወየውለት፣ ጨዋታ አቁመናል!

🇸🇦⚡️የሳዑዲ ምንጭ፡- አሁን በደቡብ ሳውዲ አረቢያ እየሆነ ያለው ነገር ጀሃነም እና ቅዠት ይመስላል፣ በመንግሥቱ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነገር ነው።

🇸🇦⚡️በአሁኑ ሰዓት በሳውዲ አረቢያ ደቡባዊ አካባቢዎች በሚገኙ ቁልፍ ቦታዎች ላይ፣ ድሮኖች በጅምላ ጥቃት እየሰነዘሩ ናቸው። 

🇸🇦⚡️በሳውዲ አረቢያ ናጅራን ከተማ በሚገኝ የነዳጅ ማምረቻ ፋብሪካ ላይ የተከሰተ ከፍተኛ የእሳት አደጋ ተመዝግቧል።
🇸🇦⚡️በሳውዲ አረቢያ ናጅራን ከተማ በሚገኝ የነዳጅ ማምረቻ ፋብሪካ ላይ የተከሰተ ከፍተኛ የእሳት አደጋ ተመዝግቧል።

🇾🇪🇮🇶🇸🇦⚡️- በሳዑዲ ዓረቢያ የምሥራቅ-ምዕራብ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ላይ የደረሰውን ውድመት ለመጠገን፣ ከአንድ ወር በላይ ጊዜ ያስፈልጋል፣ በዚህም ምክኒያት በዓለም አቀፍ ነዳጅ ገበያ ውዥንብር ተፈጥሯል- ሮይተርስ

🇾🇪🇸🇦⚡- የሳውዲ ዓረቢያ ዋና የነዳጅ ቧንቧ መስመር ጥገና ተደርጎለት በቀናት ውስጥ እንደገና ወደ ሥራ ካልገባ፣ ለውጭ የሚሆነው የነዳጅ ክምችት ያልቃል፣ ይህም እስከ 4% የሚደርስ እጥረት የዓለም አቅርቦት ላይ ያስከትላል፣ ሲሉ የሳውዲ ነዳጅ ገዢዎች እና ነጋዴዎች ለሮይተርስ ተናግረዋል።

🇾🇪🇸🇦⚡- የሳውዲ ዓረቢያ ዋና የነዳጅ ቧንቧ መስመር ጥገና ተደርጎለት በቀናት ውስጥ እንደገና ወደ ሥራ ካልገባ፣ ለውጭ የሚሆነው የነዳጅ ክምችት ያልቃል፣ ይህም እስከ 4% የሚደርስ እጥረት የዓለም አቅርቦት ላይ ያስከትላል፣ ሲሉ የሳውዲ ነዳጅ ገዢዎች እና ነጋዴዎች ለሮይተርስ ተናግረዋል።

🇸🇦🇮🇱⚡️🇾🇪 የሳዑዲው ቢን ሰልማን የመንን ለመጋፈጥ ከጽዮናውያን ጋር አብሯል -- የሁቲ ቃል አቀባይ። የዕብራይስጥ ጋዜጣ፣ ኢዝራኤል ሁም፣ መሐመድ ቢን ሰልማን በዩናይትድ ስቴትስ በኩል ለእስራኤል መልእክት እንደላከ እና በቀይ ባሕር እና በባብ አል-ማንደብ ውጥረት እንዳይባባስ እርዳታ እንደጠየቀ ዘግቧል። ጋዜጣው አክሎም፣ ሳዑዲ አረቢያ ለእስራኤል በተዘዋዋሪ መልእክት፦ “በሁቲዎች ላይ በሚደረገው ጦርነት እርዱን” ብላለች። ጋዜጣው በማጠቃለያው አንድ የእስራኤል ከፍተኛ የደህንነት ባለስልጣንን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው፣ እስራኤል ቀጥተኛ ጥቃት ካልደረሰባት በስተቀር በአሁኑ ግጭት ውስጥ በየመን ጣልቃ ለመግባት ፍላጎት እንደሌላት ተናግሯል።

🇺🇦🇬🇷 ዩክሬን፣ ግሪክ ያላትን የፔትሪዮት ሚሳይሎችን ያለ ቅድመ ሁኔታ እና ያለ ማንገራገር እንድትሰጣት ጠይቃለች — የዩክሬን ፓርላማ አባል ጎርቤንኮ። *-*-*- በአውሮፓ ሕብረት በአሁኑ ሰዓት ፔትሪዮት ሚሳዬል ያላቸው ግሪክና ስፔን ናቸው። ሌሎቹ ሁሉም ጨርሰው ቁጭ ብለዋል፣ አሜሪካም አልሰጣችሁም ብላቸዋለች። ሕብረቱ ዩክሬንን ለማገዝ በሚል ሁለቱን ሀገሮች ከባለፈው ወር ጀምሮ ሚሳዬሎቻቸውን ለዩክሬን እንዲያስረክቡ ጫና ሲያደርግባቸው ነበር። ሁለቱም እምቢ ብለዋል። ግሪክ፣ ከቱርክ ጋር ውጥረት ውስጥ ነኝ፣ ለራሴው ያስፈልገኛል፣ ብላ እምቢ ብላለች። ስፔን፣ በሩሲያና በዩክሬን ገለልተኝነቴን እመርጣለሁ ብላ እምቢ ብላለች። ዘለንስኪ በሁለቱም ላይ ጥርሱን ቢነክስም፣ ሊያደርግ የሚችለው ምንም አልነበረም፣ እስከ ቅርብ ሳምንታት ድረስ። አሁን የዩክሬን ድሮኖች 'የሩሲያን መርከቦች' በመምታት ሰበብ፣ የግሪክን መምታት ጀምረዋል። በዚህም ግሪክ ሽንቷን መሽናት ጀምራለች። ዛሬ እየወጣ እንዳለው ዘገባ፣ ግሪክ ዩክሬንን 'መርከቦቼን አትምችብኝ፣ የምትፈልጊውን ፔትሪዮት በምላሹ እሰጥሻለሁ' እንዳለቻ ተሰምቷል።

🇺🇦🇷🇺⚡️የሩሲያ ኃይሎችን እና አጋሮችን ለማጥቃት ዩክሬን የድሮን ኦፕሬተሮችን ወደ ማሊ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ሱዳን ሊቢያ እና ቢያንስ ወደ አምስት የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት ልካለች። ሩሲያ ባለችባቸው የአፍሪካ ሀገሮች፣ በየ ጊዜው ከሚነሱ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎች ጀርባ፣ ዩክሬን ትገኛለች ተብሎ ይገመታል፣ በሩሲያ ኃይሎች እና አጋሮች ላይም ጥቃት በመሰንዘር እገዛቸው አለ-- CNN

🇸🇦 ሳዑዲ አረቢያ አሁን እያደገ በሚሄድ አደገኛ ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ ውስጥ ትገኛለች። የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ ከተዘጋ በኋላ የነበረው የአብቃይቅ-ያንቡ ቧንቧ መስመር (ምዕራብ-ምሥራቅ - ከመዲ
🇸🇦 ሳዑዲ አረቢያ አሁን እያደገ በሚሄድ አደገኛ ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ ውስጥ ትገኛለች። የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ ከተዘጋ በኋላ የነበረው የአብቃይቅ-ያንቡ ቧንቧ መስመር (ምዕራብ-ምሥራቅ - ከመዲና ቀይ ባሕር)፣ ሳዑዲ ነዳጅ ወደ ውጭ የምትልክበት የመጨረሻው መስመሯ ነበር። ሆኖም፣ ባሳለፍነው ሳምንት በሁቲዎች በደረሰበት ከፍተኛ ጥቃት ከአገልግሎት ውጭ ሆኗል። በዚህም፣ ሳዑዲ አረቢያ አሁን የነዳጅ ላኪነቷ በከፍተኛ ሁኔታ የመስተጓጎል አደጋ ተጋርጦባታል። በተመሳሳይ ጊዜ፣ የንግዱ ሁኔታ መባባሱን ስለቀጠለ፣ መንግሥቱ ከዓለም ባንክ ትልቅ ብድር እንደጠየቀ ተዘግቧል። የባብ አል-ማንዳብ የባሕር መተላለፊያ በሁቲ እጅ መውደቁ ለሪያድ ሌላ አደጋን ይወክላል፣ በተለይም የሳዑዲ መርከቦች በቀይ ባሕር ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶች እና መስተጓጎሎች ከደረሱባቸው በኋላ። ሳዑዲዎች አሁን ውስጥ ከገቡበት ስልታዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉድጓድ እንዴት ለመውጣት እንዳሰቡ ማየት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከበደ ነው። የመካ ስምምነት ዋጋ የለውም ተብሎ ተረጋግጧል፣ አሜሪካውያን ሁቲዎችን በቀጥታ ለመጋፈጥ ፈቃደኛ ያልሆኑ ይመስላሉ፣ እና ሌሎች ሁሉ ጣልቃ ላለመግባት እየሞከሩ ነው። 

🇮🇷🇦🇪⚡️ — የኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን እና የአቡ ዳቢ የዘውድ ወራሽ ሼክ ካሊድ ቢን ሙሐመድ ቢን ዛይድ በኒው ዴሊ በተካሄደው የBRICS ጉባኤ ላይ አዎንታዊ ውይይት ካደረጉ በኋላ፣ ኢራን እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ያለፉ ክርክሮችን ትተው ለጋራ የወደፊት ሁኔታ ለመሥራት ተስማምተዋል። *-*-*- ለአረቦች ከዚህ ውጭ ምርጫ የለም! አዲሱን፣ መሬት የረገጠውን ቀጠናዊ የጂኦፖለቲካ እውነታ፣ ከመቀበል እና ከኢራን ጋር ከመሥራት ውጭ፣ አረቦች ምርጫ የላቸውም። 1. በራሳቸው መዋጋት አይችሉም፣ አቅም የላቸውም። 2. ሌሎችም ተዋግተውላቸው አልቻሉም፣ አቅም አላገኙም። 3. ጊዜ በረዘመ ቁጥር ከመድቀቅ ውጭ ሌላ የተሻለ አይመጣም። ስለዚህ … ሪያሊቲውን ተቀብሎ፣ ለመቀጠል መሞከር ነው። በአካባቢው ከሞላ ጎደል የድሮው ሥርዓት አብቅቶለታል።

+1
🇷🇺⚡️🇺🇦 ሰበር ዜና፡ የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቦሪስ ጆንሰን፣ የጀርመን ጠቅላይ ሚኒስትር መርዝ ከፍተኛ የደህንነት አማካሪ እና ከእንግሊዝ፣ ከፈረንሳይ እና ከጣሊያን የመጡ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪዎች፣ በኪየቭ ያካሄዱትን ስብሰባ ጨርሰው በመመለስ ላይ ሳሉ፣ የተሳፈሩበት ባቡር ፖላንድ ድንበር አቅራቢያ፣ በሩሲያ ሸሂድ ድሮን መመታቱ ታወቀ።   ከአውሮፓ ሀገራት የተውጣጡ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪዎች፣ የጀርመን ቡንደስታግ አባላት፣ ዲፕሎማቶች እና ምሁራን በባቡሩ ውስጥ ነበሩ። ሁሉም በአሁኑ ሰዓት ከባቡር እንዲወጡ እንደተደረገ ተገልጿል። ክስተቱ ትኩስ እንደመሆኑ፣ ተጨማሪ መረጃ ይጠበቃል።

🇺🇸❗️🇺🇦 ትራምፕ፦ ዜለንስኪ አንድ ነገር ማድረግ አለበት። በሩሲያ ውስጥ የናፍጣ ነዳጅ መምታት ማቆም አለበት። የናፍጣ እጥረት እያስከተለ ነው። ይህ በመካከለኛው ምሥራቅ የተደረገ አይደለም። ይህ የሚደረገው በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል በሚከሰተው ነገር ነው።