en
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Open in Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
4 330
Subscribers
-924 hours
-407 days
-8130 days
Posts Archive
🇷🇺🇺🇦⚡️በይ ቻይው ሩሲያ እንግዲህ፣ ዛሬ ሌሊትም መጡብሽ እነዚህ ሰዎች። ዩክሬን፣ ከ400 በላይ የድሮን መንጋዎችን ምሽቱን ወደ ሩሲያ ግዛቶች ልካለች።
🇷🇺🇺🇦⚡️በይ ቻይው ሩሲያ እንግዲህ፣ ዛሬ ሌሊትም መጡብሽ እነዚህ ሰዎች። ዩክሬን፣ ከ400 በላይ የድሮን መንጋዎችን ምሽቱን ወደ ሩሲያ ግዛቶች ልካለች።

🇷🇺‼️ ፑቲን ለመሸነፍ አላሰበም፣ ለማቆምም እቅድ የለውም፣ ጦርነቱ ለዓመታት ይቆያል — The NewYork Times ክሬምሊን ይህንን ስትራቴጂ ተግባራዊ በማድረግ ረዘም ባለ ጦርነት የምዕራቡ ዓለ
🇷🇺‼️ ፑቲን ለመሸነፍ አላሰበም፣ ለማቆምም እቅድ የለውም፣ ጦርነቱ ለዓመታት ይቆያል — The NewYork Times ክሬምሊን ይህንን ስትራቴጂ ተግባራዊ በማድረግ ረዘም ባለ ጦርነት የምዕራቡ ዓለም መዳከም ላይ ተስፋውን ጥሏል። በአርሜኒያ፣ በካዛኪስታን እና በሶሪያ የሩሲያ አቋም ቢደክምም፣ ሞስኮ ምዕራቡን በማዛል ለማሸነፍ ተስፋ ታደርጋለች። አሁንም ሩሲያን የሚደግፉ ወይም ገለልተኛ የሆኑ ብዙ ሀገራት አሉ። ክሬምሊን በዩክሬን የሚደረገው ጦርነት ውጤት፣ የሀገሪቱን ዓለም አቀፍ መልካም ስም የሚወስን እንደሆነ ስለሚያምን፣ የምዕራቡ ዓለም ወጪዎች እና እርምጃዎች ምንም ይሁኑ ምን፣ ጦርነቱን ይቀጥላል።"

🇾🇪🇸🇦 ሳዑዲ በየመን ላይ፣ "ቀልድ ጨርሻለሁ" እያለች ነው።

🇸🇦⚡️🇾🇪 የሚገርማችሁ፣ እየሆነ ባለው በዚህ ሁሉ ውስጥ፣ በግሌ፣ አስደንጋጭ ሆኖ ያገኘሁት እና ሳይታወቅ እየተለመደ የመጣው ነገር፣ የአረቦች እርስ በእርስ መዋጋት ነው። በሀገር እና በመንግሥ
🇸🇦⚡️🇾🇪 የሚገርማችሁ፣ እየሆነ ባለው በዚህ ሁሉ ውስጥ፣ በግሌ፣ አስደንጋጭ ሆኖ ያገኘሁት እና ሳይታወቅ እየተለመደ የመጣው ነገር፣ የአረቦች እርስ በእርስ መዋጋት ነው። በሀገር እና በመንግሥታት ደረጃ። ይሄ ፍፁም አዲስ ነገር ነው። አንዱ የአረብ መንግሥት/ሀገር፣ ከሌላኛው የአረብ መንግሥት/ሀገር ጋር ዓለም ይወቅልኝ ብሎ በግልፅ መዋጋት፣ የሚያስገርም ለውጥ ነው። አዎ፣ በእርግጥ አንዱ አንዱን መምታት ወይም ማስመታት፣ ሴራ መተብተብ ወይም ከኋላ መውጋት አዲሳቸው አይደለም ለአረቦች። በግልፁ እንዲህ ወጥተው እርስ በእርሳቸው መመታታት መልመዳቸው ግን፣ የተለ ነገር ነው። ምን ሆኑ?

🇾🇪🚫🇸🇦⚡የየመን ኃይሎች በቀይ ባሕር ውስጥ በሚጓዝበት ጊዜ የሳውዲ መርከብ NCC MASAን ዒላማ አድርገውታል። በቀይ ባሕር ውስጥ ዒላማ የተደረገው የሳዑዲ መርከብ ጉዳት ደርሶበታል። በአሁኑ ሰዓት በተመሳሳይ፣ በየመን የወደብ ከተማ በሆነችው በሁደይዳ ላይ፣ እየተካሄደ ስላለ የሳውዲ አየር ጥቃቶች ዘገባዎች በመውጣት ላይ ናቸው ።

🇺🇸🇮🇷⚡️— ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስለ ኢራን፦ አሁን እያወራናቸው ነው። ቀናት እያለፉ ሲሄዱ እየበረታ እየሄደ ያለ ይመስለኛል። ስምምነቱን የበለጠ ብልህ መንገድ አድርጌ እቆጥረዋለሁ፣ ነገር ግን
🇺🇸🇮🇷⚡️— ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስለ ኢራን፦
አሁን እያወራናቸው ነው። ቀናት እያለፉ ሲሄዱ እየበረታ እየሄደ ያለ ይመስለኛል። ስምምነቱን የበለጠ ብልህ መንገድ አድርጌ እቆጥረዋለሁ፣ ነገር ግን እየሠራነው ያለውን (ድብደባ) መሥራት እና ቀላሉ መንገድ ነው። ከፈለግን ያንን ወደ እጅግ ከፍተኛ ደረጃ ማድረስ እንችላለን። እኛ ተዘጋጅተናል፣ ዝናራችንን ታጥቀናል፣ እጃችን ምላጩ ላይ ነው እና ለመሄድ ዝግጁ ነን።

🇺🇸🇸🇦🇮🇱⚡️— ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሳውዲ የኒውክሊየር ስምምነት ላይ፦ "የሆነ ጊዜ ላይ፣ ሳዑዲዎች በአብርሃም ጎጆ ሥር (Abraham Accord) ከእስራኤል ጋር መደመራቸው አይቀርም። ስምምነቶችን ይቀላቀላሉ። የዛኔ ብቻ፣ የሲቪል የኒውክሊየር ፕሮግራማቸውን እንዲጀምሩ እፈቅዳለሁ። ማበልጸግ የለም። *-*-*- ሰድቁ፣ ዱዓ አድርጉ፣ በሬ አርዳችሁ እስራኤልን በዋይት ሃውስ አብሉ፣ ከዚያ ጠባያችሁ ተመርምሮ ሊፈቀድላችሁ ይችላል።

🇷🇺🇺🇦 ሩሲያ ዛሬ 210 የዩክሬን ድሮኖችን መትታ መጣሏን አስታወቀች። በምስሉ የሚታየው፣ በሴይንት ፒተርስበርግ ከተማ፣ በግዙፍ የሎጀስቲክ ተቋም ላይ ሊወድቅ ሰከንዶች የቀሩት ድሮን፣ በሩሲያ ኃይሎች ተመትቶ ሲወድቅ ነው።

🇺🇦🇷🇺 ዘሌንስኪ፦ ሩሲያውያን በዩክሬን ላይ ለአዲስ ግዙፍ ጥቃት ሚሳይሎችን እንዳዘጋጁ ከደኀንነት እና ከአጋሮቻችን እናውቃለን። ይህ ጥቃት ዛሬ ሊከሰት ይችላል፦ የመጀመሪያ መረጃ በ48 ሰዓታት
🇺🇦🇷🇺 ዘሌንስኪ፦ ሩሲያውያን በዩክሬን ላይ ለአዲስ ግዙፍ ጥቃት ሚሳይሎችን እንዳዘጋጁ ከደኀንነት እና ከአጋሮቻችን እናውቃለን። ይህ ጥቃት ዛሬ ሊከሰት ይችላል፦ የመጀመሪያ መረጃ በ48 ሰዓታት ውስጥ እንደሚሆን ይጠቁማል። አሜሪካ ከዩክሬን ጋር መሆኗን እንደምትቀጥል እና ይህንን ጦርነት በተገቢ ሰላም ማቆም እንደምንችል ተስፋ አደርጋለሁ። ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት እና ከቡድኑ ጋር ለሚደረግ ስብሰባ እየተዘጋጀን ነው። ሩሲያ ለመኽር አዲስ የክተ ማዕበል እያዘጋጀች እንደሆነ ግልጽ የሆነ የስለላ መረጃ አለን፣ በጣም ጉልህ ጉዳይ ነው።

🇷🇺⚡️ከሩሲያ እየወጡ ያሉ ምስሎች አስደናቂ ናቸው። ዩክሬን በድጋሜ ሩሲያን ስታደማት አድራለች። አሁንም ንጋቱን፣ በተለያዩ የሩሲያ ክፍለ ሀገሮች ጥቃቶች እና ፍንዳታዎች እንደቀጠሉ ናቸው። የጥቃቱ
+5
🇷🇺⚡️ከሩሲያ እየወጡ ያሉ ምስሎች አስደናቂ ናቸው። ዩክሬን በድጋሜ ሩሲያን ስታደማት አድራለች። አሁንም ንጋቱን፣ በተለያዩ የሩሲያ ክፍለ ሀገሮች ጥቃቶች እና ፍንዳታዎች እንደቀጠሉ ናቸው። የጥቃቱ ሰለባዎች ግዙፍ መሠረተ ልማቶች ናቸው። ምናቸውን እንዴት አድርገው በምን፣ እየመቷቸው እንደሆነ አይታወቅም። ድሮኖች በዚህ መጠን ፍንዳታዎችን ያደርሳሉ ለማለት ከባድ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ፣ የሩሲያን የኃይል መሠረተ ልማት 40 በመቶውን ያወደሙት እነዚሁ ድሮኖች ናቸው። እስካሁን ድረስ ከፑቲን ሩሲያ መልስ የለም። የደነዘዙ ይመስላሉ። የጭሱ መተለቅ እና መጠቅጠቅ፣ ምቱን፣ የቮልካኖ ፍንዳታ ውጤት አስመስሎታል ።

https://www.naturalnews.com/2026-07-23-the-persian-gulf-is-never-coming-back.html ብትችሉና ይህን ጽሑፍ ብታነቡት ደስ ይለኛል። ቀስ ብላችሁ አንብቡት፣ በደንብ ትረዱታላችሁ።

+5
🇷🇺🇺🇦 እንደተጠበቀው ፑቲን ሩሲያ በዩክሬን ድሮኖች ስትነድ አድራለች። ንጋቱንም በመመታት ላይ ናት። በዋና ከተማዋ ሞስኮ ዙሪያ ጨምሮ፣ በተለያዩ ግዛቶቿ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሚመስሉ እሳቶች እና ጭሶች እየነደዱ ናቸው። ሩሲያ ሳይደክማት አልቀረችም፣ እስካሁንም መልስ የላትም። *-*-*- "ሩሲያ እየተቀጠቀጠች ነው" ብሎ መፃፍ እኮ ራሩ ከባድ ነገር ነው፣ አይደለም እንዴ? አሜሪካ ዋና ዋና ከተሞቿን፣ ሜክሲኮ ወይም ካናዳ ገብተው ቀንም ሌትም ሲመቷቸው ማለት እኮ ነው። የሚሆን ነው? እንዲያ የሚሆነው ምናልባት የትንሳኤ ቀን ነው፣ ተብሎ ነው የሚታሰበው። እዚያ ድረስ ነው። አሜሪካ ምን ያህል ብትልፈሰፈስ ነው? አመራሮቿ ምን ያህል ቢደነዝዙ ነው? ምን ያህል ባንዳ? ምን ያህል አንጎለ-ቢስ? ምን ያህል ጦሯ አመድ ቢሆን ነው? ተብሎ ይጠየቅ ነበር። በዋሽንግተን ዙሪያ ጦርነት፣ በዋይት ሃውስ ዙሪያ ጦርነት፣ ኒውዮርክ፣ ሎስ አንጀለስ በጠላት ድሮኖች፣ ሚሳዬሎች፣ በየቀኑ ሲመቱ፣ ሲታረሱ … ሳሉት እስኪ። "የማይሆን ነገር ለሚስትህ አትንገር" ተብሎ ይተረት ነበር። ሩሲያ በገሃዱ በዩክሬን ዛሬ እየሆነች ያለችው እንደዚያ ነው። ትልቅ ናት፣ ግዙፍ ናት ተብላ ትታሰብ ነበር። ነገር ግን፣ በወሳኝ ሰዓት፣ አጣብቂኝ በገባችበት፣ መሪ ስለሌላት፣ በሥልጣን የጀፈጀፈው ስለያዛት፣ ድመት አክላ እያየናት ነው።

+3
🇮🇷⚡️🇺🇸🇯🇴 ሌሊት ጀምሮ እስከ ንጋት ድረስ በቀጠለው የኢራን ጥቃት፣ ሚሳዬሎች በዮርዳኖስ ሰማይ ላይ በነፃነት ሲንሸራሸሩ ታይተዋል። የዮርዳኖስን ሰማይ ኢራን የምታዝበት እስኪመስል፣ ሚሳዬሎች ያለ መቃወሚያ እየሄዱ ታይተዋል። በዮርዳኖስ የአሜሪካ የጦር ሰፈር፣ ሙወፊቅ አል-ሱልቲ፣ ቀጥታ በወረደበት በርካታ ሚሳዬሎች ፍንዳታዎችን አስተናግዷል። ዮርዳኖሳዊያን፣ የአሜሪካ አየር መቃወሚያዎች የት ገብተዋል? ሲሉ እየጠየቁ ነው።

🇺🇦🇷🇺⚡️ምሽቱን ዩክሬን 575 ገደማ የድሮን መንጋዎችን፣ ወደ ምዕራብ ሩሲያ ግዛቶች እና ወደ ክራይሚያ ክልል ልካለች። ነገ እንግዲህ ብዙ እሳቶች በሩሲያ ይኖራሉ።
🇺🇦🇷🇺⚡️ምሽቱን ዩክሬን 575 ገደማ የድሮን መንጋዎችን፣ ወደ ምዕራብ ሩሲያ ግዛቶች እና ወደ ክራይሚያ ክልል ልካለች። ነገ እንግዲህ ብዙ እሳቶች በሩሲያ ይኖራሉ።

🇮🇷🇺🇸⚡️ፕሬዝዳንት ትራምፕ፡ ከአሁን በኋላ በመርከብ ላይ፣ በጭነቶች ላይ ወይም በሌላ ተያያዥ ንብረቶች ላይ፣ ኢራን ምንም ዓይነት ጉዳት የምታደርስ ከሆነ፣ እኛ ጋር ካላት ብር ለኪሳራው እየተ
🇮🇷🇺🇸⚡️ፕሬዝዳንት ትራምፕ፡ ከአሁን በኋላ በመርከብ ላይ፣ በጭነቶች ላይ ወይም በሌላ ተያያዥ ንብረቶች ላይ፣ ኢራን ምንም ዓይነት ጉዳት የምታደርስ ከሆነ፣ እኛ ጋር ካላት ብር ለኪሳራው እየተመዠረጠ እንደሚከፈል እንድታውቅ ይሁን። ቀልድ ጨርሰናል!

🇺🇦 በወደብ መሠረተ ልማት ላይ በሩሲያ ጥቃት ምክንያት ዩክሬን በቅርቡ የምግብ እጥረት ቀውስን ትጋፈጣለች። የቀድሞው የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኩሌባ፣ ግጭቱ ወደ ሰፊ ግጭት ደረጃ እየገባ መሆኑን፣ በዚህም ሁለቱም ወገኖች የእያንዳንዳቸውን ኢኮኖሚ ለማጥፋት እንደሚሞክሩ ገልጿል። በጥቃቶቹ ምክንያት፣ በሎጂስቲክስ እና በአቅርቦት ላይ ከባድ ችግሮች ሊፈጠሩ ይችላሉ፣ ይህም የምግብ አቅርቦትን ሊጎዳ ይችላል። ቀደም ሲል፣ የሩሲያ ጦር ሰራዊት በዩክሬን የወደብ መሠረተ ልማት እና AFUን በሚደግፉ የሎጂስቲክስ ተቋማት ላይ ተከታታይ ጥቃቶችን አካሂዷል። ከትናንት ጀምሮ፣ የዩክሬን የባሕር ሎጂስቲክስ ሙሉ በሙሉ ሽባ ሆኗል።

የሳዑዲ የ"ሲቪሊያን" ኒውክሊየር ፍላጎት እክል ገጥሞታል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ፍቃድ መስጠቱን፣ ሳዑዲ ለእስራኤል እውቅና ከመስጠት ጋር አያይዞታል -- The NewYork Times ሳዑዲ ለእስራኤል እ
የሳዑዲ የ"ሲቪሊያን" ኒውክሊየር ፍላጎት እክል ገጥሞታል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ፍቃድ መስጠቱን፣ ሳዑዲ ለእስራኤል እውቅና ከመስጠት ጋር አያይዞታል -- The NewYork Times ሳዑዲ ለእስራኤል እውቅና ትስጥ፣ ከዚያ እህሉም ፍራፍሬውም ይሰጣታል።

🇺🇸🇮🇱🇵🇸⚡️— በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሃካቢ፦
ቤንጃሚን ኔታንያሁ የዘር ጭፍጨፋ ፈጽሟል፣ ጥፋተኛ ነው፣ እስራኤል የዘር ጭፍጨፋ ፈጽማለች ብለው ሲናገሩ፣ ወይም ማምዳኒ ሲናገር፣ በግልጽ ሲታይ፣ ያን መናገር እራሱ ሞኝነት ነው። ለምን? ምክንያቱም የዘር ማጥፋት ወንጀል ስትፈጽም፣ ለማጥፋት ትሞክራለህ፣ እና አንድን ሕዝብ በሙሉ ለማጥፋት አስበህ ነው። ከኦክቶበር 7 ጀምሮ የጋዛ ህዝብ በየዓመቱ በ4% ገደማ እየጨመረ መሆኑን ያውቃል ማምዳኒ?


🇮🇷⚡️IRGC በለቀቀው የሳተላይ ምስል፡ "የኢራን ጦር በባሕሬን የአማዞንን ዳታ ሴንተር አውድሟል" ብሏል። *-*-*- ዳታ ሴንተር ማለት 'ነርቭ' ማለት ነው። ለጦርነቱ እነዚህ ዳታ ሴንተሮች፣ በሰውነት ውስጥ እንዳሉ ነርቮች ናቸው። በመካከለኛው ምሥራቅ ትልቁን እና በኤሜሬት የሚገኘውን የአማዞንን ዳታ ሴንተር፣ ኢራኖች መትተው ከጥቅም ውጭ በማድረግ እንዲዘጋ ያደረጉት በጦርነቱ ጅማሮ ሳምንታት ላይ ነበር። ይሄኛው ሌላው ዳታ ሴንተር መሆኑ ነው። የኤሜሬቱን ዳታ ሴንተር ለመገንባት የፈጀው ወጪ $16 ቢሊዮን ዶላር ነበር።

❗️🇺🇸/🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ፦ 'ኢራናውያን ታምመዋል። እነሱ ሙሉ በሙሉ እብድ የሆኑ ሰዎች ናቸው። በጭንቅላታቸው ውስጥ በጣም የተሳሳተ ነገር አለ።'