ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

Открыть в Telegram

ዜና ከምንጩ

Больше

📈 Аналитический обзор Telegram-канала Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

Канал Addis Maleda - አዲስ ማለዳ (@addismaleda) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 33 619 подписчиков, занимая 7 558 место в категории Новости и СМИ и 1 091 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 33 619 подписчиков.

Согласно последним данным от 14 октября, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 458, а за последние 24 часа — 18, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 14.43%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 11.12% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 4 850 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 3 737 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 11.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
“ዜና ከምንጩ”

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 15 октября, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Новости и СМИ.

33 619
Подписчики
+1824 часа
+747 дней
+45830 дней
Архив постов
የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ጋር እንዲወዳደሩ ቢፈለግም በፖሊሲ እና በሌሎች ጉዳዮች ሊሳካላቸው እንዳልተቻለ ገለጹ   ሐሙስ፤ጥቅምት 05 ቀን 2019ዓ.ም (#አዲስ ማለዳ) የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ጋር እንዲወዳደሩ ቢፈለግም በፖሊሲ እና በሌሎች ጉዳዮች ሊሳካላቸው እንዳልተቻለ ገለጹ፤ አዲሱ የዳግም ምዝገባ መስፈርትም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመስፋፋት ይልቅ ለመዘጋት እየዳረጋቸው መሆኑ ተሰማ ይህ የተባለው የግል ከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ማህበር በዛሬው ዕለት ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ጋር የግሉ ዘርፍ በትምህርት ላይ ያለባቸውን ፈተናዎች እና አስተዋጽኦን በተመለከተ በተወያየበት ወቅት ነው። ዳግም ምዝገባን በተመለከተ በርካታ የግል ተቋማት መስፈርቱን ማሟላት ባለመቻለው ስድስት እና አስራ ሁለት ወር ተሰጥቷቸው እንደነበር ተነስቷል። በዚህም ጊዜ ያሟሉ፣ በአንጻሩ መስፈርቱ ያገዳቸው መኖራቸው ተመላክቷል። የማህበሩ ፕሬዝዳንት በበኩላቸው አንዳንድ መስፈርቶችን በተመለከተ “የመንግስት ተቋማት መስፈርቱን አያሟሉም ከተባለ ታዲያ የግል ተቋማት እንዴት ሊያሟሉ ይችላሉ” ሲሉ በጥያቄ አዘል መልኩ ያለውን ችግር አመልክተዋል። አክለውም፤ ማህበሩ ለህገወጥ የትምህርት ተቋማት ጥብቅና እንደማይቆም አንስተው፤ በዚህ ጉዳይም ከመንግስት ጎን በመቆም ህግና ሥርዓትን ተከትሎ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ መንግስት የሚያወጣቸው መስፈርቶች እና ህግጋት የግሉን ዘርፍ ያገናዘበ እና በአስቻይ ሁኔታዎች ላይ የተመረኮዘ መሆን እንዳለበት አጽዕኖት ተሰጥቷል። የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ሞላ ጸጋይ (ዶ/ር) እንደገለጹት ከሆነ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየመጡ ያሉ አዳዲስ አሰራሮች በግሉ ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደሩ ናቸው፡፡ እንዲሁም በመርሐ ግብሩ ላይ ከመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ጋር እንዲወዳደር እንደሚፈለግ በማንሳት፣ ነገር ግን ህጉ እኩል ካልሆነ እንዴት ተወዳዳሪ መሆን ይቻላል የሚል አስተያየት ከተሳታፊዎች ቀርቧል። ትምህርት ሚኒስቴርን በመወከል በመድረኩ የተገኙት ኢባ ሚጀና (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የግሉን ዘርፍ ለማሳደግ የፖሊሲ እና የተለያዩ የህግ ማሻሻያዎች እንዲሁም ጥናት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል። አክለውም የግል ተቋማት ቀጣይነት እንዲኖራቸው ልዩ የሚያደርጋቸውን ጉዳይ መያዝ እንዳለባቸው አንስተዋል። በተጨማሪም በሀገሪቱ ያሉ ተቋማት ተመሳሳይ የትምህርት ዓይነት እንደሚሰጡ አክለዋል። ይህን ጉዳይ ሲገልፁም በሀገሪቱ 47 የመንግስት ዩኒቨርሲቲ መኖሩን ጠቅሰው፣ በሚሰጡት የትምህርት ክፍል ዓይነት ግን “አንድ ዩኒቨርስቲ 47 ካምፓስ” አለን እንደማለት ነው ሲሉ ገልጸዋል። አክለውም ዩኒቨርስቲዎች የተለያዩ ፕሮግራሞችን ማለትም ልዩ የሚያደርጋቸውን መስጠት መጀመር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። ዶክተር ሞላ አክለውም፤ አሁን ላይ ዳግም ምዝገባ ተቋማትን አደጋ ላይ ከመጣሉ በተጨማሪ የሚቀላቀላቸውም ተማሪ እየቀነሰ መሆኑኑን ጠቁመዋል። ይህም በግል ብቻ ሳይሆን በመንግስትም እንደሆን ጠቅሰዋል። በቅርቡ ተግባራዊ የሆነው የሬሜድያል ፕሮግራምን በተመለከተ የግል አስተያየቴ ነው ያሉት ሞላ “ለአንድ ጊዜ ብቻ ነው ተብሎ ይጠበቅ የነበረ ቢሆንም ስርዓት እየመሰለ ነው” በማለት ተናግረዋል። ይህም ጉዳይ መቅረት እንዳለበት እና የማለፊያ ነጥብን በመቀነስ ከዛ በኋላ ያለው ላይ መሰራት እንዳለበት ጠቁመዋል። በተጨማሪም የመውጫ ፈተና ለምን በግሉ የትምህርት ተቋማት የሚያልፉት አነስተኛ እየሆነ መጣ ለሚለው ምላሽ የሰጡት የማህበሩ የቦርድ አባል የሆኑት ዶክተር ተረፈ ፈየራ፤ ሁሉም እንደ አንድ እየተፈረጀ መሆኑን አንስተው፣ ከመንግስት ዩኒቨርስቲ በላይ የሚያሳልፉ መኖራቸውን በመጠቆም ይህ ግን ለምን ሆነ የሚለው ጥልቅ የሆነ ዳሰሳ እና ጥናት ያስፈልጋል ብለዋል። በተለያየ መልኩ መፈተሽ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦ YouTube ➲ t.ly/vSgS Telegram ➲ t.ly/SOXU Facebook ➲ t.ly/flx8 Twitter ➲t.ly/mxA

photo content

የኋይት ሃውስ አዲሷ የፕሬስ ሴክሬታሪ ኬቲ ዛካሪያ ለቦታው አይመጥኑም የሚል የበረታ ትችት እየቀረበባቸው መሆኑ ተሰማ ሐሙስ፤ጥቅምት 05 ቀን 2019ዓ.ም (#አዲስ ማለዳ) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ በካሮይሊና ሊቪት ምትክ የሾሟቸው አዲስ የኋይት ሃውስ የፕሬስ ሴክሬታሪ ኬቲ ዛካሪያ፣ በሕግ አዋቂነት ወይም በጥብቅና ሙያ ፈቃድና የትምህርት ዝግግታቸው ዙሪያ ለተነሱባቸው ጠንካራ ክሶችና ማብራሪያዎች ምላሽ መስጠት ባለመቻላቸው ከፍተኛ የፖለቲካና የሕግ ግፊት እያጋጠማቸው እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡ ኬቲ፤ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው “ሕግ አዋቂ/ጠበቃ” እያሉ ራሳቸውን ስያስተዋውቁ የቆዩ ቢሆንም፣ በአሜሪካ የትኛውም ግዛት ሆነ በቻይና የሕግ አዋቂነት የብቃት ማረጋገጫ ፈተና (ባር ኤግዛም) ማለፋቸውን የሚያስረዳ ምንም ዓይነት ማስረጃ ማቅረብ እንዳልቻሉ አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል። ይህ ጉዳይ ትኩረት ያገኘው ፖፑላር ኢንፎርሜሽን የተሰኘው የምርመራ ድረገጽ ባወጣው ዘገባ መሆኑ ተገልጿል። ዘገባው ይፋ ከሆነ በኋላ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጋዜጠኞች ጥያቄ የቀረበላቸው ቢሆንም፣ መልሱን ለዛካሪያ በመስጠት ራሳቸውን አግልለዋል። ዛካሪያ በሰጡት አጭር ምላሽ “ወደ ቻይና ስጓዝ...” የሚል ያልተጠናቀቀ ሐሳብ የሰነዘሩ ሲሆን፣ ይሁንና የቻይና አገራዊ የሕግ ሙያ ብቃት ፈተና የሚሰጠው ለቻይና ዜጎች ብቻ መሆኑ የጉዳዩን አጠራጣሪነት አጉልቶታል፡፡ የኋይት ሀውስ የመገናኛ ብዙኃን ዳይሬክተር ስቲቨን ቼንግ ባወጡት መግለጫ፣ ዛካሪያ ብቃት ያላትና የትራምፕን አስተዳደር ሥራዎች ለሕዝብ ለማብራራት ዝግጁ የሆነች ምርጥ የፕሬስ ሴክሬታሪ መሆኗን ገልጸው፣ ተከላክለውላቸዋል። ዛካሪያ በበኩላቸው በካሊፎርኒያ በሚገኘው የፔፐርዳይን ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት በ2011 እ.ኤ.አ. በሕግ የተመረቁ መሆኑንና በዓለም አቀፍ የንግድ ሕግ ዘርፍ ተገቢውን አገልግሎት መስጠታቸውን ተናግረዋል። ይሁን እንጂ የካሊፎርኒያ የሕግ ባለሙያዎች ተቆጣጣሪ ተቋም ቃል አቀባይ ሪክ ኮካ ባወጡት ይፋዊ መግለጫ፣ በካሊፎርኒያ ግዛት በኬቲ ዛካሪያ ወይም በወላጅ ስማቸው የተመዘገበ የሕግ ሙያ ፈቃድ አለመኖሩን አረጋግጠዋል። በተመሳሳይ መልኩ በሌሎች 50 ግዛቶችና በዋሽንግተን ዲሲ ተመሳሳይ ፍለጋ ተደርጎ ምንም ዓይነት የሕግ ፈቃድ እንዳልተገኘላቸው ተጠቅሷል። ይህንን ተከትሎ ካምፔን ፎር አካውንታቢሊቲ የተሰኘው የክትትል ተቋም በዛካሪያ ላይ በካሊፎርኒያ ግዛት የሕግ መቆጣጠሪያ ተቋም ዘንድ ይፋዊ አቤቱታ አቅርቧል። የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዳይሬክተር ሚሼል ኩፐርስሚዝ በሰጡት መግለጫ፣ “በካሊፎርኒያ ያለ ሕጋዊ ፈቃድ እራስን 'ጠበቃ' ብሎ መጥራት ወንጀል እንጂ ተራ ማጋነን አይደለም፤ በመሆኑም ተቋሙ በዛካሪያ ላይ አፋጣኝ ምርመራ ሊያካሂድ ይገባል” ሲሉ አሳስበዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዛካሪያን ሲሾሙ “የተከበረች የሕግ ባለሙያና የማጋ(አሜሪካን ዳግም ኃያል ማድረግ) ታማኝ ደጋፊ” ሲሉ የገለጧቸው ቢሆንም፣ የመጀመሪያው የፕሬስ ማብራሪያቸው ከተጠበቀው በታች መሆኑና አሁን ደግሞ የሙያ ፈቃድ ቀውስ መጋጠሙ በኋይት ሃውስ ዙሪያ ያለውን አባብሶታል። ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦ YouTube ➲ t.ly/vSgS Telegram ➲ t.ly/SOXU Facebook ➲ t.ly/flx8 Twitter ➲t.ly/mxA

photo content

ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ ከዞን 6 ወደ ዞን 4 ማረሚያ ቤት ተዛወሩ፤ የኢሕአፓ አባላት ግን እስካሁን ከእስር እንዳልተፈቱ ጠበቃቸው ለአዲስ ማለዳ ገለጹ ሐሙስ፤ጥቅምት 05 ቀን 2019ዓ.ም (#አዲስ ማለዳ) በማረሚያ ቤት ውስጥ ባሉበት የጤና ችግር እየተባባሰባቸው መሆኑን ተከትሎ የቦታ ለውጥ እንዲደረግላቸው ሲጠይቁ የቆዩት ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ፣ ከዞን 6 እስር ቤት ወደ ዞን 4 መዛወራቸውን ጠበቃቸው ሰለሞን ገዛኸኝ ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ። ዶ/ር ወንድወሰን ከቃሊቲ፣ ወደ ዞን 6 ማረሚያ ቤት ከተዛወሩ በኋላ፣ በእስር ቤቱ ውስጥ የረሃብ አድማ መጀመራቸው ይታወሳል። አድማውን የጀመሩት ታስረው የነበሩበት ክፍል ከፍተኛ የጤና ችግር እያስከተለባቸው በመሆኑና ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ማመልከቻ ምላሽ ባለማግኘቱ መሆኑን አዲስ ማለዳ ጠበቃቸውንና የቅርብ ቤተሰባቸውን እማኝ አድርጋ መዘገቧ አይዘነጋም፡፡ በወቅቱ ዶ/ር ወንድወሰን ምግብ ከመመገብ በተጨማሪ የጤና መድኃኒቶችንም እንደማይወስዱ በመግለጽ አድማውን መጀመራቸው ተገልጾ ነበር። ጠበቃቸው ሰለሞን ገዛኸኝ፣ የዶ/ር ወንድወሰን የጤና ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ተከትሎ ከነበሩበት የማረሚያ ቤት ክፍል ወደ ሌላ ቦታ እንዲዛወሩ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ማመልከቻ ማቅረባቸውን ገልጸው ነበር። በዚህም ጉዳይ ላይ ለመስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም. ቀጠሮ መያዙን ጠበቃው ለአዲስ ማለዳ መናገራቸው ይታወሳል። በዚህ መሠረት ዛሬ በዋለው ችሎት፤ ዶ/ር ወንድወሰን ከዞን 6 ወደ ዞን 4፣ ለእሳቸው የተሻለ እንደሚሆን ወደሚታሰብ የማረሚያ ቤት ክፍል እንዲዛወሩ መደረጉን ጠበቃቸው አስረድተዋል። እንደ ጠበቃው ገለጻ፣ ማረሚያ ቤቱም የእስረኛውን ቦታ እንደቀየረ ለፍርድ ቤቱ ምላሽ ሰጥቷል። በሌላ በኩል በእስር ላይየሚገኙት የኢሕአፓ አባላት እስካሁን ከእስር እንዳልተፈቱ ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ገልጸዋል። ጠበቃው እንዳሉት፤ የፌደራል ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ እስካሁን ከእስር ያልተለቀቁበትን ምክንያት እንዲያብራራ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ ቀጠሮ ሰጥቷል። በዚህም ፖሊስ ምላሽ እንዲሰጥ ለመስከረም 6 ቀን 2019 ዓ.ም. ቀጠሮ መያዙን ጠበቃው ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦ YouTube ➲ t.ly/vSgS Telegram ➲ t.ly/SOXU Facebook ➲ t.ly/flx8 Twitter ➲t.ly/mxA

photo content

በጋምቤላ ከተማ የጸጥታ ሁኔታ እየተሻሻለ በመሆኑ ቀያቸውን የለቀቁ ዜጎች በአፋጣኝ እንዲመለሱ ከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቀረበ ሐሙስ፤ጥቅምት 05 ቀን 2019ዓ.ም (#አዲስ ማለዳ)   በጋምቤላ ከተማ በተከሰተው የጸጥታ አለመረጋጋት የሰው ሕይወት በማለፉ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን የገለጸው የከተማው አስተዳደር፤ በአሁኑ ሰዓት የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በሁሉም ቀበሌዎች የማረጋጋት ሥራ እየሠሩ በመሆኑ በስጋት ቀያቸውን የለቀቁ ዜጎች ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ጥሪ አስተላለፈ። የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ዛሬ ጥቅምት 05 ቀን 2019 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ በከተማዋ በተከሰተው የጸጥታ አለመረጋጋትና የዜጎች ሕይወት በማለፉ ከፍተኛ ሐዘን እንደተሰማው ገልጾ ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝቷል።   ከተማ አስተዳደሩ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በሁሉም ቀበሌዎች ሰፊ የማረጋጋት ሥራ እየሠሩ እንደሚገኙና የከተማዋ ጸጥታ እየተሻሻለ በመሆኑ ነዋሪዎች ባሉበት ሆነው እንዲረጋጉ ጠይቋል። በጸጥታ ስጋት ምክንያት አካባቢያቸውን በመልቀቅ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች የጸጥታ አካላት አካባቢውን እያረጋጉ በመሆኑ ባሉበት እንዲቆዩ የጠየቀ ሲሆን፣ ቀያቸውን ለቅቀው የወጡ ዜጎችም ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ ወደ መኖሪያ ቀያቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል።   በተጨማሪም በከተማዋ የሚገኙ የንግድ ተቋማት፣ ሆቴሎች፣ ምግብ ቤቶች፣ የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቆችና ሌሎች የንግድ ድርጅቶች በሙሉ ክፍት በማድረግ የተለመደ አገልግሎታቸውን እንዲሰጡ አስተዳደሩ አሳስቧል። የከተማዋ ነዋሪዎችም ከጸጥታ አካላት ጎን በመቆም ሰላምን ለመመለስ በሚደረገው ጥረት የራሳቸውን ንቁ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ ቀርቧል።   ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በትናንትናው ዕለት የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን በከተማዋ ያለውን ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታና ሰላም ማስከበርን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፣ በሌሊት ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት በተፈጸመ ጥቃት የዜጎች ሕይወት በማለፉ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጾ ነበር። ድርጊቱን የፈጸሙ አካላትን በማጣራት ለሕግ ለማቅረብ ኮሚሽኑ ከፌዴራልና ከክልሉ የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት አጠናክሮ እየሠራ እንደሚገኝ አስታውቋል።   ኮሚሽኑ በመግለጫው ሕዝቡ ሁኔታውን ለግል ዓላማቸው ሊጠቀሙበት ከሚሞክሩ አካላት፣ ከሐሰተኛ መረጃዎችና ከሕገወጥ ቅስቀሳዎች ራሱን እንዲጠብቅ፣ ከታማኝ ምንጮች የሚሰጡ መረጃዎችን ብቻ እንዲከታተል አሳስቧል። የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የሴቶችና የወጣቶች ማኅበራትም ሕዝቡን በማረጋጋት ረገድ ያላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።   ለጸጥታ ሥራው ስኬት ሲባል ከትናንት ምሽት 12፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ነጋታው 12፡00 ሰዓት ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ በጋምቤላ ከተማ የሰዎችና የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ በጥብቅ መከልከሉን ኮሚሽኑ ማስታወቁም አይዘነጋም። እንዲሁም ለጸጥታ ሥራ በሕጋዊ መንገድ ፈቃድ ከተሰጣቸው አካላት ውጪ ማንኛውም አካል የጦር መሣሪያ ይዞ በከተማዋ ውስጥ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑንና እገዳውን ተላልፎ በሚገኝ አካል ላይ አስፈላጊው ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ኮሚሽኑ በጥብቅ አሳስቧል። ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦ YouTube ➲ t.ly/vSgS Telegram ➲ t.ly/SOXU Facebook ➲ t.ly/flx8 Twitter ➲t.ly/mxA

photo content

ዩናይትድ ኪንግደም በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ያለው ውጥረት እንዲረግብ ጥሪ አቀረበች ሐሙስ፤ጥቅምት 05 ቀን 2019ዓ.ም (#አዲስ ማለዳ) በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል እያገረሸ ያለው ውጥረት ከፍተኛ ስጋት እየደቀነ መሆኑን የገለጸችው ዩናይትድ ኪንግደም አፋጣኝ መረጋጋትና ወደ ውይይት እንዲመለሱ ጥሪ ያደረገች ሲሆን፤ በአንጻሩ አሜሪካ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በወቅታዊው የሁለቱ አገራት ግንኙነት ዙሪያ መወያየቷ ተገለጸ። በአፍሪካ ቀንድ እየባባሰ የመጣውን የጸጥታ ሁኔታ አስመልክቶ የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ቃል አቀባይ ዛሬ ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ.ም. መግለጫ አውጥቷል፡፡ ሀገሪቱ በመግለጫዋ፤ ሁሉም አካላት የየቀጣናውን አገራት ሉዓላዊነት፣ ነጻነትና የግዛት አንድነት እንዲያከብሩ አሳስባለች። አንዳቸውም አገራት በጎረቤት ሀገራት ድንበር ጥሰት የሚያደርጉትን ማንኛውንም ድርጊት አጥብቆ እንደሚቃወም የገለጸው የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት፣ ውጥረቱን የሚያባብሱ ማናቸውም እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙና ጉዳዩ በሰላማዊ ውይይት እንዲፈታ ጥሪ አቅርቧል። እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ውጥረቱን ለማርገብ የሚያደርገውን ጥረት ድጋፍ እንደሚሰጡት አስታውሳለች። በሌላ በኩል ደግሞ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ትናንት ጥቅምት 4 ቀን 2019 ዓ.ም. በስልክ መወያየታቸውን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አስታውቋል። ሁለቱ መሪዎች ከኤርትራ ጋር የተፈጠረውን ውጥረት አስመልክቶ ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ ሚኒስትሩ በሁሉም ወገኖች በኩል መረጋጋት እንዲሰፍን ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል። ለአገር ውስጥና ለውጭ ውጥረቶች ብቸኛው ዘላቂ መፍትሔ በ2010 የኢትዮጵያና ኤርትራ የሰላም ማዕቀፍ መሠረት መሆኑንም አጽዕኖት ሰጥተዋል፡፡ የአፍሪካ ቀንድ ተጨማሪ ግጭትን ማስተናገድ እንደማይችል የገለጹት ማርኮ ሩቢዮ፣ በቀጣናው ያሉ ሁሉም ሀገራት የጎረቤቶቻቸውን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ሊያከብሩ እንዲሁም ከድንበር ተሻጋሪ ጥቃቶችና ወረራዎች ሊቆጠቡ እንደሚገባ አሳስበዋል። ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦ YouTube ➲ t.ly/vSgS Telegram ➲ t.ly/SOXU Facebook ➲ t.ly/flx8 Twitter ➲t.ly/mxA

photo content

የሱዳን ብሔራዊ ጦር በምዕራብ ዳርፉር ስትራቴጄካዊዋን የብር ኬለኬል አካባቢ ከፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መቆጣጠሩን አወጀ ሐሙስ፤ጥቅምት 05 ቀን 2019ዓ.ም (#አዲስ ማለዳ) ከሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ኃይል (አር.ኤስ.ኤፍ) ጋር የተካሄደውን ውጊያ ተከትሎ የሱዳን ብሔራዊ ጦርና አጋር ኃይሎች በምዕራብ ዳርፉር ግዛት ከፍተኛ ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ያላትን የብር ኬለኬል አካባቢ በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን የክልሉ ገዢ እና የወታደራዊ ምንጮች አስታወቁ። የምዕራብ ዳርፉር ገዢ ባህር አል-ዲን አዳም ካራማ ባወጡት መግለጫ፤ የሱዳን ብሔራዊ ጦር ከአጋር ቡድኖች ጋር በመሆን በጀበል ሙን፤ ምሥራቃዊ ክፍል በሚገኘው የብር ኬለኬል አካባቢ ጉልህና አወንታዊ ግስጋሴ ማስመዝገባቸውን ገልጸዋል። ገዢው የአካባቢው መያዝ ለሱዳን መንግሥትና ለወታደራዊ ሂደቱ አስፈላጊ ስትራቴጂያዊ ስኬት መሆኑን አብራርተው፣ ቦታው በጀበል ሙን አቅራቢያ በመገኘቱ ለቀጣይ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አስረድተዋል። በምዕራብ ዳርፉር የሚካሄዱ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች በሙሉ ደኅንነትን ለመመለስ፣ የሱዳንን አንድነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ በተቀመጡ የተቀናጁ ዕቅዶች መሠረት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገዥው አክለው ተናግረዋል። ከባለሥልጣኑ መግለጫ ጎን ለጎንም የሱዳን ብሔራዊ ጦር ሠራዊት አባላት በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ ቪዲዮዎችን በመለጠፍ ኃይሎቻቸው የብር ኬለኬልን መቆጣጠራቸውን ይፋ አድርገዋል። ከዚህ ቀደም ጥቅምት 5 ቀን 2026 እ.ኤ.አ. ከአር.ኤስ.ኤፍ ጋር ከተደረገ ውጊያ በኋላ፣ ከብሔራዊ ጦሩ ጎን የተሰለፉት የተባበሩት የታጠቁ ቡድኖች የጋራ ኃይል በዚሁ በምዕራብ ዳርፉር የምትገኘውን ብር ሳሊባን መቆጣጠራቸውን ማስታወቃቸው ቲ.አር.ቲ በዘገባው አስታውሷል፡፡ በሱዳን ከሚገኙት 18 ግዛቶች ውስጥ በሰሜንና ምዕራብ ዳርፉር ከሚገኙ አነስተኛ በብሔራዊ ጦሩ ቁጥጥር ስር ባሉ ቦታዎች በስተቀር፣ ፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ኃይሉ በዳርፉር ቀጣና ያሉትን አምስት ግዛቶች አብዛኛውን ክፍል ተቆጣጥሮ ይገኛል። በአንጻሩ የሱዳን ብሔራዊ ጦር ዋና ከተማዋን ካርቱምን ጨምሮ የሌሎቹን 13 ግዛቶች አብዛኛውን ክፍል በበላይነት እየመራ ይገኛል። ሱዳን እ.ኤ.አ. ከሚያዚያ 2023 ጀምሮ በብሔራዊ ጦሩና በአር.ኤስ.ኤፍ መካከል በተቀሰቀሰወ ጦርነትት ሳቢያ እስካሁን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ሕይወታቸውን ሲያጡ ከ13 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦ YouTube ➲ t.ly/vSgS Telegram ➲ t.ly/SOXU Facebook ➲ t.ly/flx8 Twitter ➲t.ly/mxA

photo content

ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ በማረሚያ ቤት የጀመሩት የረሃብ አድማ አራተኛ ቀን ማስቆጠሩን ጠበቃቸውና አንድ የቤተሰብ አባል ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ ረቡዕ፤ጥቅምት 04 ቀን 2019 ዓ.ም (#አዲስ ማለዳ) ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ ያቀረቡት የዝውውር ጥያቄ ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ የጀመሩትን የረሃብ አድማ ገፍተው እንደቀጠሉበትና አራተኛ ቀን ማስቆጠሩን ጠበቃቸውና አንድ የቅርብ ቤተሰብ ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ፡፡ የመረጃ ምንጮቹ እንደገለጹት፣ ዶ/ር ወንድወሰን በሚገኙበት ማረሚያ ቤት ያለው ሁኔታ ለጤናቸውና ለሕይወታቸው አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል በመግለጽ ወደ ሌላ እስር ቤት እንዲዛወሩ ጠይቀዋል። ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ወደ ዞን 06 እስር ቤት ከተዛወሩ በኋላ ስፍራው እንዲቀየርላቸው ጠይቀዋል፡፡ ይሁንና ከዚያ እስር ቤት ወደ ሌላ ቦታ እንዲዛወሩ ያቀረቡት እስካሁን ድረስ የዝውውር ጥያቄ እንዳልተፈጸመ የገለጹት ጠበቃቸው ሰለሞን ገዛኸኝ፣ ዶ/ር ወንድወሰን በአስቸኳይ ከዞን 06 እስር ቤት ካልተዛወሩ በሕይወታቸው ላይ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል ስጋታቸውን በመጥቀስ አስጠንቅቀዋል። ጠበቃው እንደገለጹት፤ ጉዳዩ በከፍተኛ ፍርድ ቤት የተያዘ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱም ለነገ ሐሙስ ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል። በዚህም የእስር ቤት ዝውውር ጥያቄያቸው በፍርድ ቤት እንደሚታይ ጠበቃቸው ጠቁመዋል። በተመሳሳይ፣ የዶ/ር ወንድወሰን አንድ የቅርብ ቤተሰብ ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣ ዶ/ር ወንደሰን ከፍተኛ የጤና ችግር ውስጥ ይገኛሉ። ከባለፈው እሁድ ዕለት አንስቶም ምግብ መመገብ ማቆማቸውን ገልጸዋል። እኚሁ የመረጃ ምንጭ እንዳሉት፣ የረሃብ አድማውን የጀመሩት በሚገኙበት እስር ቤት ያለው አካባቢ ለጤናቸው አደገኛ ነው በሚል ስጋት ሲሆን፣ ወደ ሌላ እስር ቤት እንዲዛወሩ በመጠየቅ አድማቸውን እያስቀጠሉ ነው። በተለይም በሚታሰሩበት ክፍል ተባዮችና አይጦች እንዳሉ የገለጹት ባለቤታቸው፣ ይህ ሁኔታ ለጤናቸው አስጊ እንደሆነ ገልጸዋል። ዶ/ር ወንድወሰንም ከዚህ አካባቢ መውጣት እንዳለባቸው በመግለጽ የረሃብ አድማውን እንደቀጠሉ አስረድተዋል። ዶ/ር ወንድወሰን ከመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ከቃሊቲ ወደ ዞን 06 እስር ቤት እንደተዛወሩ የገለጹት የቅርብ ቤተሰብ፣ ዝውውሩ ለምን እንደተደረገ በግልጽ እንደማያውቁ ተናግረዋል። በተጨማሪም ወደ አዲሱ የእስር ቤት ክፍል የተዛወሩት እሳቸው ብቻ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ከዚህ በተጨማሪ፣ ዶ/ር ወንድወሰን ከፍተኛ የደም ግፊት እንዳለባቸውና በአሁኑ ወቅት መድኃኒት እየወሰዱ እንዳልሆነም ገልጸዋል። ይህም ቀደም ሲል ካለባቸው የጤና ችግር ጋር ተዳምሮ ለጤናቸውና ለሕይወታቸው ከፍተኛ ስጋት እንደሚፈጥር በመግለጽ፣ በአስቸኳይ ተገቢው የሕክምና እርዳታ እንዲያገኙና የእስር ቤት ዝውውር ጥያቄያቸው መፍትሔ እንዲያገኝ አሳስበዋል። ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦ YouTube ➲ t.ly/vSgS Telegram ➲ t.ly/SOXU Facebook ➲ t.ly/flx8 Twitter ➲t.ly/mxA

photo content

ጌታቸው ረዳ የኤርትራ መንግስት የምትደግፋቸው ኃይሎች ሊቀጡ እንደሚገባ ለአውሮፓ ህብረት ገለጹ ረቡዕ፤ጥቅምት 04 ቀን 2019 ዓ.ም (#አዲስ ማለዳ) የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ የኤርትራ መንግስት እና ድጋፍ የምታደርግላቸው ኃይሎች መቀጣት እንዳለባቸው ለአውሮፓ ህብረት አሳሰቡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ፤ ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ እንዲሁም የቀይ ባህር ቀጣና ልዩ መልእክተኛ  እና በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር  ጋር በወቅታዊ እና የቀጣናዊ ሁኔታዎች ላይ  መምከራቸውን ገልጸው፣ እነዚህ ኃይሎች ላይ እርምጃ አለመውሰድ አስከፊ እንደሚሆን እንደገጹላቸው አስታውቀዋል። ለምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ሰላምና ዘላቂ መረጋጋት እጅግ አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አክለዋል። ጌታቸው፤ በትግራይ፣ በኤርትራ እና በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ግልጸኝነት የተሞላበት የሃሳብ ልውውጥ እንዳደረጉ አንስተዋል። ጌታቸው በአስመራ ያለው አገዛዝ ሲሉ የጠሩትን የኤርትራ መንግስት እና ደጋፊዎቹ ቀጣናውን ለማወክ እያከናወኑት ነው ያሉትን አደገኛ ሚና አጉልተው  እንዳሳዩ አስታውቀዋል። እንዲሁም አሁን ላይ ያለውን አካሄድ በጊዜው ለማስቆም አስፈላጊውን እርምጃ አለመውሰድ የሚያስከትለውን አስከፊ መዘዝ ለህብረቱ ዲፕሎማቶች ማስገንዘባቸውን ተናግረዋል። በሌላ በኩል የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል፤ ብልጽግና ፓርቲን በመውቀስ ባለፉት ዓመታት ብቻ ከ360 በላይ ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎችን ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬትስ እንደገዛ  ለመሳሪያ ግዢም ብዙ እንዳወጣ አንስተው፤ ባለፋት ስምንት ዓመታት ደግሞ ኢትዮጵያ ከ30 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ድጋፍ እንዳገኘች አንስተዋል።   የማነ  አክለውም፤ ኤርትራን የውሸት ክስ ከኢትዮጵያ እየቀረበባት እንደሆነ ቢያነሱም ይህ የመጀመሪያው ውንጀላ አለመሆኑ ይታወሳል። ጌታቸው ከዲፕሎማቶቹ ጋር በነበራቸው ውይይት ውጥረቱ የበለጠ እንዳይባባስ ለመከላከል፣  የመረጃ ልውውጥ አጠናክሮ በመቀጠል በቅንጅት ለመስራት እንደተስማሙ አንስተዋል። ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦ YouTube ➲ t.ly/vSgS Telegram ➲ t.ly/SOXU Facebook ➲ t.ly/flx8 Twitter ➲t.ly/mxA

photo content

ሩሲያ በኪቭ በፈጸመችው የባሊስቲክ ሚሳኤል ጥቃት የኃይል መቋረጥ አጋጠመ ረቡዕ፤ጥቅምት 04 ቀን 2019 ዓ.ም (#አዲስ ማለዳ) በዩክሬን መዲና ኪቭ የሚገኙ  የኃይል ማመንጫ ተቋማት እና መሰረተ ልማቶች ላይ  በሩሲያ በተፈጸመ ከባድ የባሊስቲክ ሚሳኤል እና የአየር ጥቃት ውድመትን ያስከተለ እና የኃይል መቋረጥ እንዳገጠመ ተገለፀ። የከተማዋ ከንቲባ እንደገለፁት ከሆነ፤ በኃይል መሠረተ ልማቶች ላይ በደረሰው ጉዳት ምክንያት በበርካታ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ መቋረጥ በማጋጠሙ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትም ተስተጓጉሏል። በጥቃቱ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉ የተረጋገጠ ሲሆን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ደግሞ ጥቃቱ በዋናነት ሀገሪቱን ከኃይል አቅርቦት ውጪ ለማድረግ ያነጣጠረ መሆኑን ገልጸዋል። ሩሲያ እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 2022 ጀምሮ የዩክሬንን የኃይል ማመንጫዎች እና የኢነርጂ መሠረተ ልማቶችን በስፋት ማጥቃት የጦርነቱ አካል አድርጋው እንደቆየች ይነገራል። በተለይም የክረምት ወቅት ሲቃረብ የሕዝቡን የኤሌክትሪክ፣ የሙቀት እና የውኃ አቅርቦት ለማቋረጥ የሚደረጉት ይህን መሰል ጥቃቶች የዩክሬንን የኃይል ማከፋፈያ አቅም በከፍተኛ ደረጃ እየጎዱት መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል። እንዲሁም በዩክሬን ከተሞች ውስጥ ተደጋጋሚ የኃይል መቋረጥ እንዲከሰት በማድረግ በሕዝቡ ዕለታዊ ሕይወት ላይ ትልቅ ጫና እያሳደሩ ይገኛሉ። በቅርቡ  ሁለቱ ሀገራት የኢነርጂ ተቋማት እንዳይመቱ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ስምምነት መደረጉና ጊዜያዊ የተኩስ ማቆም መታወጁ ቢነገርም፣ ዩክሬን ግን ሩሲያ ስምምነቱን በመጣስ በኃይል መሰረተ ልማቶቿ ላይ ጥቃቷን አጠናክራ  ቀጥላለች በማለት ወቅሳለች። ይሁን እንጂ ይህንን ስምምነት ትራምፕ ቢያሳውቁም ዘለንስኪ ግን በመገናኛ ብዙኃን እንደሰሙት በመጥቀስ ዝርዝሩን እየጠበቁ መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል። ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦ YouTube ➲ t.ly/vSgS Telegram ➲ t.ly/SOXU Facebook ➲ t.ly/flx8 Twitter ➲t.ly/mxA

photo content

#ቃለምልልስ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ አዲስ ማለዳ ከትግራይ ሰላም ኃይል ከፍተኛ አመራር ጋር በዛሬው ዕለት ቃለምልልስ አድርጋለች፡፡ በተለይ ባለፉት ሁለት ቀናት የተከሰቱትን
#ቃለምልልስ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ አዲስ ማለዳ ከትግራይ ሰላም ኃይል ከፍተኛ አመራር ጋር በዛሬው ዕለት ቃለምልልስ አድርጋለች፡፡ በተለይ ባለፉት ሁለት ቀናት የተከሰቱትን አቤይት ጉዳዮች ተከትሎ አመራሩ ለተጠየቋቸው ጥያቄዎች ምላሽ ያሉትንሰጥተዋል፡፡ አድምጡት፡-https://youtu.be/yPwiokviyXo?si=Z5z9utzmgBqFz9Wc

#ቃለምልልስ ግርማ ሰይፉ ከአዲስ ማለዳ ጋር ያደረጉትን የክፍል ሁለት ቆይታ በተከታዩ ማስፈንጠሪያ ያገኙታል፦ ግርማ፤ በቃለምልልሱ ለአምስት መቶ (500) ጡረተኞችና ተማሪዎች “ለውጥና ነውጥ፤ የአትክ
#ቃለምልልስ ግርማ ሰይፉ ከአዲስ ማለዳ ጋር ያደረጉትን የክፍል ሁለት ቆይታ በተከታዩ ማስፈንጠሪያ ያገኙታል፦ ግርማ፤ በቃለምልልሱ ለአምስት መቶ (500) ጡረተኞችና ተማሪዎች “ለውጥና ነውጥ፤ የአትክልተኛው ማስታወሻ” የተሰኘ መጽሐፋቸውን በነጻ ለመስጠት ቃል ገብተዋል። ዝርዝር መረጃዎችን በተረጋገጠ የፌስቡክ ገጻቸው እንደሚገልጹም አስታውቀዋል። https://youtu.be/e3bavy1hAbU?si=Cf8CJ9npG6Q7c28h