2 301
Подписчики
+724 часа
+827 дней
+34530 дней
Архив постов
Repost from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
+9
የድሬ የኮሪደር ልማት ምቹ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች፣ የተሻሻለ የአካባቢ ውበትን እና ጥራታቸውን የጠበቁ የማህበረሰብ መሰብሰቢያ ስፍራዎች በድሬ እውን እንዲሆኑ አስችሏል። በኮሪደሩ ለከተማዋ ነዋሪዎች ገቢ ለማስገኘት የሚያስችሉ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጂንግ ስቴሽን፣ ሱቆች፣ ካፍቴሪያዎች እንዲሁም ደረጃቸውን የጠበቁ የፓርኪንግ ቦታዎች እንዲካተቱበት ተደርጓል።
ኢፍጣር በድሬደዋ
የረመዳን ኢፍጣር ከድሬደዋ ነዋሪዎች ጋር።
Iftar in Dire Dawa
Breaking bread with the local community during Ramadan.
#PMOEthiopia
Repost from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
+7
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የምርቶች እና አገልግሎቶች ጥራት የማረጋገጥ ስራ ዓለም አቀፍ አሰራር ስርዓትን መሰረት በማድረግ ለአምራቾች፣ ለአገልግሎት ሰጪዎች፣ ለላኪዎች፣ ለአስመጪዎች፣ ለተቆጣጣሪ መስሪያ ቤቶች፣ ለምርምር ተቋማት እና በአጠቃላይ ለሸማቹ ማህበረሰብ የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎትን የሚሠጥ መንግስታዊ ድርጅት ነው።
በድሬዳዋ አካባቢ ለሚገኙ አምራቾችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ ነፃ የንግድ ቀጣና እንዲሁም የደረቅ ወደብን መሰረት በማድረግ ቀደም ብሎ ይሰጡ ከነበሩ የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎቶች በተጨማሪ በምግብ ዘይት፣ ፔትሮሊዬም ወይም የነዳጅ ምርት፣ የተለያዩ የምግብ ምርቶች፣ የማስዋቢያና የዲተርጀንት ምርቶች፣ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ምርቶችንና ግብዓቶች የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አዲስ የፍተሻ ላቦራቶሪ በማደራጀት አገልግሎቱን ተደራሽ አድርጓል ።
Repost from Fana Media Corporation S.C (FMC)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ያደረጉት ጉብኝት፡-
Repost from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
+6
ድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፤ በውስጡ 10 ተቋማት ይዞ 73 የሚሆኑ አገልግሎቶችን ለዜጎች በመስጠት ላይ ይገኛል። አንድ ማዕከሉ ተገልጋዬችን የሚያስተናግዱ 96 ካውንተሮች እንዲኖሩት ተደርጎ የተደራጀ ነው። ማዕከሉ ስራ ከጀመረበት ስድስት ወራቶች ውስጥ በአጠቃላይ ከ23 ሺ በላይ ተገልጋዮችን አስተናግዷል። ከፍ ብሎ የተጀመረውን የተቀላጠፈ የዲጅታል አገልግሎት ይበልጥ ለማስፋት አቅዶም እየሠራ ነው።
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ EASE ፕሮጀክት በአስተዳደሩ ከሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር በኢንዱስትሪው ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ላይ የምክክር መድረክ አካሄደ::
በመድረኩን በቴክኒክና ሙያ ስልጠና፣ በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ እንዱስትሪውን ከመደገፍ አኳያ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ታልሞ በሚዘጋጀው ጥናት ላይ ከኢንዱስትሪ ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ተካሂዷል::
በEASE ፕሮጀክት ትግበራ ትኩረት ተደርጎባቸው ከሚከናወኑ ቁልፍ ተግባራት መካከል ኢኮኖሚውን የሚያንቀሳቅሱ የአምራች እንዱስትሪዎችን አቅም ማጎልበት አንደኛው መሆኑን የጠቀሱት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ኢ/ር ፋሲል ማዘንጊያ ሲሆኑ በዚህም በሰለጠነ የሰው ሀይል፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ላይ በኢንዱስትሪው ፍላጎት መሰረት በዘላቂነት ድጋፍ ለማድረግ እንዲቻል የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ቡድን በማዋቀር በተቋም ደረጃ ጥናት እያካሄድን እንገኛለንም ብለዋል::
በመድረኩ ለፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ውይይቱ መነሻ የሚሆን ሰንድ በጥናት ቡድኑ አማካኝነት ለባለ ድርሻ አካላቱ ገለፃ የተደረገ ሲሆን በተጨማሪም ኢንዱስትሪዎችን በዘርፍ በመክፈል በቡድን እንዲወያዩ ማድረግ ተችሏል::
በተካሄደው የቡድን ውይይት ወቅትም ኢንዱስትሪዎች በሰለጠነ የሰው ሀይል፣ ተኪ በሆኑ ቴክኖሎጂዎች እና በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ላይ ያሏቸውን ፍላጎቶች ለይተው በዝርዝር ያስቀመጡ ሲሆን በቀጣይ በቅንጅት መስራት በሚቻልበት እግባብ ላይም አመርቂ ውይይቶችን በማድረግ ለጥናቱ አስፈላጊ ግብዓቶች የተገኙበት መድረክም ነበር::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
የካቲት 28/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የተቋሙ የ10 አመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ለባለ ድርሻ አካላት ቀርቦ ውይይት ተካሄደ።
በመድረኩ በዋናነት የኮሌጁ የቀጣይ 10 አመት ስትራቴጂ እቅድ እንዲሁም የተቋሙ የሰው ሀይል ልማት ረቂቅ ሰነድ ለኮሌጁ አድቫይዘሪንግ ቦርድ አባላትና ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት ቀርቦ ውይይቶች ተካሂደዋል::
ኮሌጁን በቀጣይ አመታት ግልፅ በሆነ ስትራቴጂ ለመምራት የሚያስችል አቅም የሚፈጥር የ10 አመት ስትራቴጂክ እቅድ መዘጋጀቱን ያስታወቁት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ሲሆኑ ይህ የ10 አመት ስትራቴጂክ እቅድም ሰፊና ብዙ ጉዳዮችን በውስጡ የያዘ ከመሆኑም በተጨማሪ መጪውን ዘመንም ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ በመሆኑ መሪ እቅዱን ለባለድርሻ አካላት ለማስተዋወቅ ያለመ መድረክ መሆኑንም ገልፀዋል::
የኮሌጁ ዲን አክለውም ከፌደራል በተሰጠን ተልዕኮ መሰረት አዲሱ የቴክኒክና ሙያ ስትራቴጂክ እቅድ ለህብረተሰቡና ለኢንዱስትሪው እንዲወርድ አቅጣጫ መሰጠቱን አስታውሰው የዘርፉን እስትራቴጂ በተቋም ደረጃ ስናወርድ ምን ምን ተግባራት ይከናወናሉ የሚለውንም የሚመልስ እስትራቴጂክ እቅድ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በቀጣይ የዘርፉን እስትራቴጂክ እቅድ ከተቋማችን የ10 ዓመት እስትራቴጂክ እቅድ ጋር የምናስተዋውቅ ይሆናል ብለዋል::
በመድረኩ የኮሌጁን የ10 አመት እስትራቴጂክ እቅድ በኮሌጁ የእቅድና በጀት ዝግጅት ባለሙያ በሆኑት አቶ አለማየሁ ብርሃኑ እማካኝነት ለባለድርሻ አካላት የቀረበ ሲሆን በዚህም ኮሌጁ እንደ አንድ የትምህርትና ስልጠና ተቋም ከተሰጠው ተልዕኮ አንፃር በቀጣይ 10 አመታት በትኩርት የሚያከውናቸውን ቁልፍ ጉዳዮች በዝርዝር ለመድረኩ ተሳታፊዎች ገለፃ ማድረግ ተችሏል::
በቀረቡት ረቂቅ ሰነዶች ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ሀሳብና አስተያየት ተሰጥቶባቸው ሰፋ ያለ ውይይት የተደረገ ሲሆን በዚህም የስትራቴጂክ እቅዱ ከኢንዱስትሪው አኳያ ታሳቢ ያልተደረጉና መካተት ይገባቸዋል ያሉዋቸውን ገንቢ ሀሳቦችም በመድረኩ አንስተዋል::
በቀጣይ የኮሌጁ የ10 አመት ስትራቴጂክ እቅድ ላይ የተገኙ ግብዓችን አካቶ ለኮሌጁ ቦርድ አቅርቦ በማፀደቅ ወደ ትግበራ እንደሚገባም በመድረኩ ተገልፇል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
የካቲት 26/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተቋሙ ለሚገኙ የትምህርትና ስልጠና ክፍሎችና ስራ ሂደቶች የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወር የድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብር ማካሄድ ጀመረ::
በኮሌጁ ዲን በሚመራው በዚህ የድጋፍና ክትትል በድጋፍና ክትትል ቡድኑ በተዘጋጀው ቼክሊስት መሰረት ትምህርትና ስልጠና ክፍሎች፣ ዋና ስራ ሂደቶችና የስራ ክፍሎች በግማሽ አመቱ በእቅድ አፈፃፀም፣ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በስልጠና ጥራት፣ በመረጃ አደረጃጀት፣ በሀብት ማፍራትና ግብዓት አጠቃቀም ላይ ባተኮሩ ነጥቦች መነሻነት ሂደቶችና ክፍሎች ያሉበትን ቁመና የሚገመግም የድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብር መሆኑም ተገልጿል::
የዚህ ድጋፍና ክትትል ዋና አላማ በተቋሙ የሚገኙ ስራ ሂደቶችና ክፍሎች ከተሰጣቸው ተልዕኮ አንፃርና ካስቀመጡት ግብ አኳያ ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ ክትትል ለማድረግና በአፈፃፀም ክፍተት የሚታይባቸውን ተግባራቶች ተለይተው ክፍተቶች እንዲሞሉ ድጋፍ የማድረግ ሲሆን በተጨማሪም የተሻለ አፈፃፀም ለታየባቸው ስራ ሂደቶችና ክፍሎች እውቅና በመስጠት ለሌሎች ሞዴል እንዲሆኑ ማስቻል እንደሆነው ተገልፇል::
በድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብሩ እስካሁን የአውቶሞቲቭ፣ የማኑፋክቸሪንግ፣ የአይ.ሲ.ቲ፣ የውድ ዎርክ እና የኮስትራክሽ ትምህርትና ስልጠና ክፍሎችን ማካሄድ የተቻለ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም በተቀመጠው መርሃ-ግብር መሰረት የድጋፍና ክትትሉ የሚቀጥል መሆኑም ታውቋል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
የካቲት 25/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
