2 301
Подписчики
+724 часа
+827 дней
+34530 дней
Архив постов
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በአጫጭር ስልጠና ማዕቀፍ የአምራች ኢንዱስትሪውን ፍላጎት መለየት የሚያስችል የውይይት መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሄደ::
ከተማችን ድሬደዋ የኢንዱስትሪ ማዕከል ከመሆኗ ጋር ተያይዞ አምራች ኢንዱስትሪው የሚጠይቀውን ብቁና የሰለጠን የሰው ሀይል በአጫጭር ስልጠና ማዕቀፍ አሰልጥኖ ለማቅረብ ታሳቢ ያደረግ የፍላጎት ዳሰሳ ጥናትና የምክክር መድረክ ከኮልጁ የኢንዱስትሪ አድቫይዘሪንግ ቦርድ አካላት ጋር ማካሄድ ተችሏል::
የምክክር መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በንግግራቸው "ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ወጣቶች ከረጅም ጊዜ ስልጠና ይልቅ ወቅቱ ሚጠይቀውን የአጫጭር ሙያ ስልጠናዎች ላይ ትኩረት በማድረጋቸው አምራች ኢንዱስትሪው በሚፈልገው ልክ የበቃ የሰው ሀይል የማቅረብ ውስነት እንዲስተዋል እድርጎታል ያሉ ሲሆን ይህን ክፍተት በዘላቂነት ለመቅረፍ የአምራች ኢንዱስትሪውን የሙያ ፍላጎት መሰረት ያደረገ የአጫጭር ስልጠና ፕሮግራም መቅረፅ አስፈላጊ በመሆኑ ከኢንዱስትሪ አድቫይዘሪግ ቦርድ አባላት ጋር ለመወያየት ይህ መድረክ መዘጋጀቱንም ገልፀዋል::
በEASE ፕሮጀክት ትኩረት ተደርጎባቸው ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል ለኢንዱስትሪው ግብዓት የሚሆኑ ብቁ ባለሙያዎችን የማፍራቱን ሂደት መደገፍ አንደኛው መሆኑን ያስታወሱት የፕሮጀክቱ ኮርዲኔተር ኢ/ር ፋሲል ማዘንጊያ ሲሆኑ የፕሮጀክቱ ባለሙያዎች ከትምህርትና ስልጠና ዘርፉ ጋር በመቀናጀት በሚያዘጋጁት የኢንዱስትሪውን ፍላጎት መሰረት ያደርገ የአጫጭር ስልጠና ፕሮግራም ላይ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግም ገልፀዋል::
የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት አስፈላጊነት ዝርዝር ዓላማ እንዲሁም የአጫጭር ስልጠና ሞጁሉን በማዘጋጀት ሂደት ውስጥ የሚያካተቱ ዝርዝር ተግባራትን በተመለከተ በኮሌጁ ም/ል ዲን እና የትምህርትና ስልጠው ዋና ሀላፊ በሆኑት አቶ ኤሊያስ አህመድ አማካኝነት ለባለ ድርሻ አካላት ግንዛቤ መስጠትም ተችሏል::
በመድረኩ በነበረው ውይይት ኢንዱስትሪውን ወክለው የተገኙ ተስታፊዎች አምራች ኢንዱስትሪዎች ከበቃ የሰው ሀይል አኳያ ያላቸው ፍላጎት ለጥናት ቡድኑ በዝርዝር አቅርበው ሰፊ ውይይት የተካሄደት ሲሆን ለፍላጎት ዳሰሳ ጥናቱ ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦችም የተገኙበት መድረክ ነበር::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
የካቲት 21/6/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
+4
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ዋና ስራ ሂደት በተቋሙ ከሚገኙ አሰልጣኝ መምህራን ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ::
በትምህርትና ስልጠና አካዳሚክ ካላንደሩ መሰረት የስልጠና ዘመኑ የአንደኛ ተርም መጠናቀቁን ተከትሎ በተርሙ የተከናወኑ የትግበራ አፈፃፀም እና የሁለተኛ ተርም ማስጀመሪያ የውይይት መድረክ ተካሂዷል::
የውይይት መድረኩ የመሩት የኮሌጁ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ም/ዲን አቶ ኤሊያስ አህመድ በንግግራቸው እንደግለፁት በአካዳሚክ ካላንደሩ መሰረት የትምህርትና ስልጠናው የመጀመሪያ ተርም ተጠናቆ ሁለተኛውን ተርም ምንጀምርበት ወቅት ላይ እንደመሆናችን የነበሩ ክፍተቶችን በሚገባ ለይቶ መፍትሄ ለማበጀትና በሁለተኛው ተርም ላይ ማስተካከያ ለማድረግ ታልሞ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑንም ገልፀዋል::
በመድረኩ ተሳታፊ ከነበሩት አሰልጣኝ መምህራንም የመጀመርያውን ተርም የትምህርትና ስልጠና ሂደቱን አስመልክቶ የተስተዋሉ ጠንካራና ጎኖችና ያጋጠሙ ትግዳሮቶችን በዝርዝር ያስቀመጡ ሲሆን አያይዘውም የመፍትሄ ሀሳብ ይሆናሉ ያሏቸውንም በመድረኩ አቅርበዋል::
በመጨረሻም ከመድረኩ በተገኙ ግብዓቶችና አጠቃላይ በተነሱ ሀሳቦች ላይ በመወያየት ሰፊ ማብራርያና ምላሽ የተሰጠባቸው ሲሆን በተጨማሪም በቀጣይ በተቋምና አገር አቀፍ ምዘና ሰልጣኝ ተማሪዎችን ማብቃት፣ፕሮጀክት መሰረት ያደረገ ስልጠና፣የትብብር ስልጠና፣ የዲጂታል ስልጠና አገልግሎት እና አሰልጣኝ መ/ራንን በረጅም ጊዜ የማሰልጠን ስነዘዴ ማብቃት ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የጋራ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
የካቲት 19/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የካይዘን ፍልስፍና ስራ ቦታን ምቹ ከማድረግ ባሻገር ምርትና ምርታማነትን በማሻሻሉ ረገድ ፋይዳው የላቀ በመሆኑ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ተገለፀ።
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተቋሙ የካይዘን ማሻሻያ ትግበራ ንቅናቄ ማስጀመሪያ የሆነ የግንዛቤ መስጫ መድረክ ለኮሌጁ አጠቃላይ ሰራተኞች አካሄደ::
የካይዘን ፅንሰ-ሀሳብን ተረድቶ በትኩረት መተግበር ከተቻለ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን መፍቻ ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን የገለፁት የኮሌጁ ም/ል ዲን እና የቴ/ሽ/ኢ/ኤ/አ ዋና ስራ ሂደት ሀላፊ የሆኑት አቶ ተሾመ ሸዋዬ ሲሆኑ የካይዘን ትግበራ ምቹና ፅዱ የሥራ አካባቢን ከመፍጠር ባሻገር የሀብት ብክነትን ከማስወገዱም በተጨማሪ አሰራርን በማዘመን ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መሆኑንም ገልፀዋል::
ም/ል ዲኑ አክለውም በቀጣይ ቀናት በተቋሙ በሚተገበረው የካይዘን ማሻሻያ ትግበራ ወቅት ከትግበራው የሚጠበቀውን ውጤት ለማግኘት ሁሉም የኮሌጁ አመራርና ሰራተኞች ተገቢውን ትኩረትና ተሳትፎ ማድረግ ያስፈልጋልም ብለዋል::
በመድረኩ የካይዘን ትግበራ ማሻሻያ ንቅናቄውን አስመልክቶ ለኮሌጁ ሰራተኞች የተዘጋጀውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና
ከአስተዳደሩ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመት ቢሮ በመጡ ባለሙያ አማካኝነት የተሰጠ ሲሆን በዚህም በተቋም ደረጃ የካይዘን ትግበራ የሚፈጥራቸው ለውጦችና ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን የዳሰሰ የግንዛቤ ስልጠና መስጠት ተችሏል::
በተጨማሪም በኮሌጁ በቀጣይ ቀናት የሚተገበረውን የካይዘን ማሻሻያ ትግበራ መነሻነት የተዘጋጀውን የካይዘን ማስተግበሪያ እና የአፈፃፀም መከታተያ መመሪያ ሠነድ በኮሌጁ የካይዘን ልማት ቡድን መሪ በሆኑት አሰልጣኝ መ/ር አቤል ዘገየ አማካኝነት ለሰራተኛው የቀረበ ሲሆን በዚህም የትግበራውን አካሄድ እና የትግበራ ሂደቱ የሚያካትታቸውን ዝርዝር ጉዳዮች አስመልክቶ በሰፊው ገለፃ ማድረግም ተችሏል::
"ዛሬን እናሻሽል፣ ብክነትን እናስወግድ ፣ ቅልጥፍናን እንጨምር፣ ነገን እንገንባ!"
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
የካቲት 19/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa
ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ለሶስተኛ ዙር የህይወት ክህሎት ስልጠና ላጠናቀቁ ሰልጣኞች የምርቃት እና የማጠቃለያ መድረክ ተካሄደ
" ብቃት ፣ ክህሎት ፣ ስኬት " በሚል መሪ ሀሳብ ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ሶስተኛ ዙር ማጠቃለያ መርሀ ግብር በዛሬው እለት ተካሂዷል።
በዚሁ መርሀ-ግብር ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሮቤል ጌታቸው ፕሮጀክቱ በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታቸውን መቀጠል ያልቻሉ ወጣቶችን ለ 12 ቀናት የህይወት ክህሎት ስልጠና በመስጠት በአስተዳደሩ ባሉ ድርጅቶች ላይ ለስድስት ወራት የስራ ላይ ልምምድ አድርገው በቋሚነት ተቀጣሪ ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል ።
አቶ ሮቤል አክለውም ወጣቶች በተለያዩ ፋብሪካዎች ውስጥ ተቀጥረው ስራቸውን በትጋት እያከናወኑ እንደሚገኙ አስታውቀው የስራ ባህላቸውን የቀየረ ኢንዱስትሪዎችም በዳበረ ተወዳዳሪ የሰው ኃይል እንዲመሩ ማድረግ ያስቻለ ፕሮጀክት መሆኑን ነው አቶ ሮቤል በእለቱ ያስታወቁት ።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ እንዳሉት በብቃት ፕሮጀክት ፕሮግራም እንደ ሀገር 60 ሺህ 399 ወጣቶች ተመዝግበው ከ 54ሺ በላይ እንዳጠናቀቁና ለ 52 ሺህ ወጣቶች ደግሞ ቋሚ የስራ እድል መፈጠሩን ገልፀው በድሬዳዋ አስተዳደርም በሶስት ዓመታት 2 ሺህ 846 ወጣቶች ታቅፈው ከ 2 ሺህ 700 በላይ የሚሆኑት እንደተመረቁና ከነዚም መካከል 60 በመቶ ወጣት ሴቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል ።
©️ DGC የካቲት 7/2018
የቦንጋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮችን ያቀፈ ልዑካን ቡድን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የስራ ልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄደ፡፡
የቦንጋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የEASE ፕሮጀክት ከሚተገበርባቸው 24 የሚሆኑ የሀገሪቱ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች አንደኛው ሲሆን በዚህም የኮሌጁን ዲኖች ጨምሮ የተለያዩ የስራ ሀላፊዎችን ያካተተ የልዑካን ቡድን በኮሌጃችን ያለውን የስራ እንቅስቃሴ ለመመልከት እንዲሁም በEASE ፕሮጀክት ትግበራ ያለውን ተሞክሮ ለመውሰድ የሚያስችላቸውን የስራ ልምድ ልውውጥ በኮልጁ ማካሄድ ችለዋል::
ልዑካን ቡድኑ በኮሌጃችን በነበረው የልምድ ልውውጥ መርሃ-ግብር ወቅትም የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ የEASE ፕሮጀክት ትግበራን ጨምሮ ጠቅላላ በተቋም የተመዘገቡ የአፈፃፀም ውጤቶችን በዝርዝር የተመለከቱ ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ ከምስረታው አንስቶ አሁን እስከደረሰበት ደረጃ የነበረውን ሂደት እና ያከናወናቸውን ዘርፈ ብዙ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አማካኝነት ሰፋ ያለ ገለፃና ማብራሪያም ተደርጎላቸዋል::
ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ በተደረገላቸው አቀባበልና በተመለከቱት የኮሌጁ እንቅስቃሴ መነሻ በማድረግ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ እያከናወናቸው የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የስራ እንቅስቃሴዎች አስደናቂ መሆናቸውን ገልፀው በተለይም ኮሌጁ በEASE ፕሮጀክት ትግበራ ካሳየው የስራ አፈፃፀም ብዙ ልምዶችን መቅሰም መቻላቸውንም ገልፀዋል::
በተጨማሪም ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ የስልጠና ዎርክ ሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በነበራቸው የልምምድ ልውውጥ መርሃ-ግብርም የተሳካ ቆይታን በኮሌጃችን ማድረግ ችለዋል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ጥር 21/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የሀዘን መግለጫ
በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የሆቴልና ቱሪዝም ዲፖርትመንት ሰልጣኝ ተማሪ የነበረችው ወጣት ኤደን ሰለሞን ባደረባት ህመም ጥር 17/2018 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይታናለች።
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅም በሰልጣኝ ተማሪ ኤደን ሰለሞን ህልፈተ ህይወት ጥልቅ ሀዘን የተሰማው መሆኑን እየገለፀ ለቤተሰቦቿ እና ለወዳጅ ዘመዶቿ መጽናናትን ይመኛል።
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
#ዜና | የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቲክኒክ ኮሌጅ በሙያ ደህንነት እና ጤንነት (occupational Safty and Health) ዙሪያ ሲያስለጥናቸው የቆየውን ከአስር ስድስት(16) በላይ የኢንዱስትሪ አንቀሳቃሽ ባለሞያዎችን አስመርቋል::
ኮሌጁ ይህን ስልጠና ሲያከናውን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን ከሽንብሮ ፕላስቲክ ፋብሪካ ጋር በመዋዋል የፋብሪካውን ከአስራ ስድስት (16 ) በላይ የሆኑ ሰራተኞችን አሰልጥኖ ማስመረቁን በወቅቱ ተጠቅሷል ።
በወቅቱ ንግግር ያደረጉት የስራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊና የቴክኒክና ሞያ ኤጀንሲ ዳሬክተር ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ቢሮው በስሩ ዘርፈብዙ ስራዎችን እንደሚሰራ ጠቅሰው ከስራዎቹም መካከል የፋብሪካን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሞያ ክፍተቶችን በመሙላት ደህንነታቸው የተጠበቀ የበቁ ዜጎችን ማብቃት ነው ብለዋል ::
ቢሮው የሞያ ክፍተትን በስልጠና ማጠናከር ብቻ ሳይሆን በሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች በኩል በአስተዳደሩ ለሚገኙ የተለያዩ ፋብሪካዎች መለዋወጫዎችን በማምረት የውጭ ምንዛሬን ከማስቀረት ባሻገር ከውጪ ግብዓቱ የሚመጣበትንም ጊዜ እንዲቆጠብ እያደረገ ይገኛልም በማለት ሀላፊዋ አክለው ተናግረዋል ::
የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በበኩላቸው ይህ የፋብሪካ ውስጥ የሞያ ደህንነትና የጤና አጠባበቅ ስልጠና እንደ ሀገር ያለ ክፍተት መኖሩን ጠቅሰው ኮሌጁ ይህን ችግር ለመቅረፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሽንብሮ ፕላስቲክ ፋብሪካ ጋር በመዋዋል የፋብሪካውን ከአስር ስድስት (16) በላይ ሰራተኞች ማሰልጠናቸውን ተናግረዋል ::
ስልጠናውን ተከታትለው የተመረቁት ስልጣኖች በበኩላቸው የወሰዱት የሞያ ደህንነትና የጤና ስልጠና ከፋብሪካ ውስጥ ስራችን ውጪም የግል ሕይወታችንን ለምን መራበት አካባቢም የሚጠቅመን ነው ብለዋል ::
በምረቃና ማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ላይም ስልጠናቸውን
ላጠናቀቁ ሰልጣኖች የእውቅና ስርተፊኬት ተሰጥቷል ::
#DireTvአማርኛ |ጥር 16 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ
#እንኳን_አደረሳችሁ!!
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሠላም አደረሳችሁ እያልኩ፤ በዓሉ የሠላም፣ የደስታ፣ የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ!!
#መልላም_የጥምቀት_በዓል!!
አቶ ታደለ አሰፋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን
