ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ

Открыть в Telegram

የአቡ ዩስራ ንጽጽራዊ ሀይማኖት ላይ ያተኮሩ የፁሁፍና የድምጽ ስራዎች ይቀርቡበታል።

Больше
4 301
Подписчики
Нет данных24 часа
+1647 дней
+16230 дней
Архив постов
እፎይ ሸሸ ወይንስ አፈገፈገ? ገና በማለዳው ሜዳውን ለቀቀሳ! "የጽልመቱ ጥላ" በሚል ስያሜ በስሙ ለወጣው መጽሐፍ ምላሽ እንደምናዘጋጅ ካሳወቅንበት ቀን ጀምሮ፣ እንቅስቃሴያችንን እየተከታተለ ስማችንን እያነሳ "ምላሽ እሰጣለሁ" ሲል በሙሉ በራስ መተማመን ለተከታታዮቹ ሲፎክር ከርሞ ነበር። እንዲያውም ፉከራው ጣሪያ ነክቶ፤ "እነሱ መልስ ሰጥተው እኔ ያንን ማፍረስ (ሪፊውት ማድረግ) ከከበደኝ፣ ንጽጽር አቆማለሁ!" እስከማለት ደርሶ በቪዲዮ ሲገዝት ነበር። እኛም ይህን ያህል በራሱ ከተማመነማ፣ ቢያንስ እስከ ግማሽ መጽሐፉ ድረስ ሞገዱን ተቋቁሞ ይዘልቃል ብለን ጠብቀን ነበር። ነገር ግን፣ ልክ የምዕራፍ 1 ምላሻችን (ፒዲኤፍ) እንደተለቀቀ፣ በሚገርም ሁኔታ ጸጥታ ሰፈነ፤ የበላው ጅብም አልጮህ አለ! ትላንት ደግሞ ተከታዮቹ ግራ ገብቷቸው "ለምን አትመልስላቸውም?" ብለው ሲጠይቁት፣ "ለእነሱ መልስ አልሰጥም!" በማለት የፈሪ ዱላውን ጥሎ ቁርጣቸውን ነግሯቸዋል። ምነው እፎይ? ገና እኮ መግቢያውን አልፈን ምዕራፍ 1 ላይ ብቻ ነን! ምነው ገና በማለዳው ሩጫውን አቆምከው? "ማፍረስ ከከበደኝ ንጽጽር አቆማለሁ" ያልከው ቃል ኪዳን ገና ዶሮ ሳይጮህ በአንደኛው ምዕራፍ ላይ ጸና ማለት ነው? ቢያንስ የራስህን ፉከራ አክብረህ አቋርጦ ለመውጣት እንኳ ትንሽ አትታገስም ነበር? ፒዲኤፉን ገልጠህ ስታየው ያሰብከው ዓይነት "ቀላል እራት" ሆኖ ስላላገኘኸው ይሆን እንዲህ በማለዳ ጓዝህን የጠቀለልከው? ቪዲዮውን ተመልከቱት - ለማንኛውም የምዕራፍ - 2 ምላሻችን ይቀጥላል ....

ገብርኤልን አምላክ ያደረገው እፎይ! ​በቅርቡ "የጽልመቱ ጥላ" በሚል ርዕስ እስልምናን ለመተቸት መጽሐፍ ያሳተመው እፎይ፣ በእስልምና ላይ ክስ ለመደርደር ሲጣደፍ የራሱን የክርስትና እምነት መሠረት ጭ
ገብርኤልን አምላክ ያደረገው እፎይ! ​በቅርቡ "የጽልመቱ ጥላ" በሚል ርዕስ እስልምናን ለመተቸት መጽሐፍ ያሳተመው እፎይ፣ በእስልምና ላይ ክስ ለመደርደር ሲጣደፍ የራሱን የክርስትና እምነት መሠረት ጭምር እስከማፍረስ ደርሷል። ​እስኪ ከተያያዘው ምስል ላይ የመጽሐፉን ገጽ 30 ተመልከቱት! ጸሐፊው በድፍረት "ገብርኤል ማለት ትርጉሙ አምላክ ሰው ሆነ... ማለት ስለሆነ" ይለናል! እስካሁን ሥላሴን በመቃወም ስንደክም ኑረን አሁን ደግሞ ሌላ አራተኛ "አምላክ" ጨምሮ ስራችንን ሊያበዛው ነው።

​ከሰሞኑ ሰፊ ማስታወቂያ ሲሰራለት የነበረውና ይዘቱ ግን ከማስታወቂያው ጩኸት ጋር ፈጽሞ የማይመጣጠነው "እፎይ" በተባለ ግለሰብ ስም ለወጣው መጽሐፍ፣ የመጀመሪያ ክፍል ምላሻችንን እነሆ በፒዲኤፍ ተለቋል። ምላሽ የተሰጠባቸው የመጽሀፉ ክፍሎች ስካን ተደርገው ለማመሳከርያነት አብረው ተካተዋል። ​በዚህ የመጀመሪያ ክፍል ምላሻችን፤ መጽሐፉ በምዕራፍ አንድ ላይ ካነሳቸው ጉዳዮች ውስጥ ከአንድ ርዕስ በስተቀር፣ እያንዳንዱን ነጥብ አንድም ሐሳብ ሳናስቀር በማስረጃ በጥልቀት አብራርተንበታል። ያንን የተውነውን አንዱን ርዕስ በተመለከተ፣ በቀጣይ በአላህ ፈቃድ ራሱን በቻለ መልኩ የምንመለስበት ይሆናል። ​ይህ መጽሐፍ ባለው የተጋነነ ማስታወቂያ ምክንያት በበርካታ ክርስቲያን ወገኖቻችን ዘንድ ስለ እስልምና የተሳሳተ ምስል የፈጠረ በመሆኑ፣ እውነታውንና ትክክለኛውን ምላሽ ያውቁ ዘንድ ይህንን ፖስት ሼር በማድረግ ለሁሉም እንድታደርሱልን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን። ​ፒዲኤፉን ለማግኘት ከታች ያለውን የቴሌግራም ሊንክ ይጫኑ፦ https://t.me/Yahyanuhe https://t.me/Abuyusra3

Post 1 | መውዱዕ ምን እንደሆነ የማያውቀው "እፎይ" - የመጽሀፉ መግቢያ (የመረጃ ማጣቀሻ) ተዳሷል! በመጽሐፉ መግቢያ ላይ ጸሐፊው እንዲህ ይላል፦ "ሐዲስ ሳሂህ፣ ሐሰን፣ ዳዒፍ፣ መኡዱ ... የሚባሉ ደረጃዎች አሉት፡፡ ... መውዱ ስንሰለቱ የተቆረጠ ወይም ነቢዩና ሰሀቦቹ ጋር ማይደርስ ሲሆን ነው፡፡ እኔ የተጠቀምኩት ሳሂህና ሐሰን ደረጃ ያላቸውን ሐዲሳት ነው፡፡" ይህ የጸሐፊው ሀሳብ ትክክል እንዳልሆነ በሚከተሉት ነጥቦች ማሳየት ይቻላል፦ ◆ ጸሐፊው እስልምናን ለመተቸት ብዕር ከማንሳቱ በፊት ስለሚተቸው ሃይማኖት መሰረታዊ የትምህርት ዘርፎች በቂ ግንዛቤ እንደሌለው ገና በመግቢያው ላይ ራሱን አጋልጧል። የሐዲስን መረጃዎች ሲያብራራ መውዱዕ (መኡዱ ብሎ የጻፈውን አስቂኝ ስህተት አስተካክለነው እንቀጥል) ማለት ሰንሰለቱ የተቆረጠ ወይም ነቢዩና ሰሀቦቹ ጋር የማይደርስ በማለት የሰጠው ብያኔ የፍጹም ስህተት እና እውቀት አጠርነቱን ማሳያ ነው። በኢስላማዊ የሐዲስ ጥናት መሠረት «መውዱዕ» ማለት በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሆን ተብሎ የተቀጠፈ እና የተፈበረከ ውሸት ማለትን እንጂ (¹) ሰንሰለቱ መቆረጥን አያመለክትም። ሰንሰለቱ የተቆረጠ ሐዲስ በዑለሞች ዘንድ «ሙንቀጢዕ» ወይም «ሙርሰል» በመባል ይታወቃል እንጂ መውዱዕ ተብሎ አይጠራም። ጸሐፊው እነዚህን መሠረታዊ የቃላት ፍቺዎች ሳያውቅ "ሰሂህ እና ሐሰን ሐዲሶችን ብቻ ተጠቀምኩ" ማለቱ የዕውቀቱን ውስንነት ያሳያል። ቀጥሎም ጸሐፊው እንዲህ ይላል፦ "ደረጃ ያልተሰጣቸው አንዳንድ የታሪክ መጽሐፍቶቻቸውን የተጠቀምኳቸው በሐዲስና በቁርኣን የተደገፉና የተረጋገጡ ስለሆነ ነው፡፡" ይህ የጸሐፊው ሀሳብ ትክክል እንዳልሆነም በሚከተለው ነጥብ ማሳየት ይቻላል፦ ◆ የታሪክ መጽሐፍትን "ደረጃ ያልተሰጣቸው" በማለት መግለጹ የታሪክ አዘጋገብ ስልትን ካለመረዳት የመነጨ ነው። የታላላቅ ሙስሊም የታሪክ ሊቃውንት መጻሕፍት የራሳቸው የሰንሰለት ማጣሪያ እና ርቀት ያላቸው መሆኑ ሲታወቅ፣ ጸሐፊው ግን ከዚህ እውቀት በመራቁ የራሱን አረዳድ ለማጽደቅ ሞክሯል። ቀጥሎም ጸሐፊው እንዲህ ይላል፦ "ሰዎች በማቀርበው ማስረጃ ላይ ምንም አይነት ቅሬታ ወይም መጠራጠር እንዳይኖርባቸው ለማሰብ ላነሳሁት እያንዳንዱ ነጥብ ብዙ ማስረጃዎችን ተጠቅሜያለሁ... ተቀጥፎብናል ወይም የሐሰት ማስረጃ ተለጥፎብናል የሚል ካለ ማንኛውንም ትችት ወይም ሂስ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ፡፡" ይህ የጸሐፊው ሀሳብ አሁንም ትክክል እንዳልሆነ በሚከተለው ነጥብ ማሳየት ይቻላል፦ ◆ ጸሐፊው ማስረጃዎችን አቅርቤአለሁ በማለት የተሟላ እምነት ለማሳየት ቢሞክርም፣ ገና ከመግቢያው ላይ በሰጣቸው የተሳሳቱ ትርጓሜዎች መሰረት የገነባቸው ሀሳቦች በሙሉ የምርምር ክፍተት እንዳለባቸው ያሳያል። የህዳግ ማስታወሻ (1) ኢብኑ ሀጀር አል-አስቀላኒ፣ "ኑኽበቱል ፊክር ፊ ሙስጦለህ አህሊል አሰር"  ላይ መውዱዕን ሲገልጹት፦ "ውሸት የሆነና በነቢዩ ላይ የተቀጠፈ" በማለት ነው። ይቀጥላል © የሕያ ኢብኑ ኑህ © አቡ ዩስራ

እስላማዊው ዓለም ወንጀለኞችን በህግ አግባብ የሚቀጣበትን ስርኣት "ዘግናኝ" እና "ኋላቀር" እያለ የሰብዓዊ መብት ስብከት ሲሰጥ የኖረው የምዕራቡ ዓለም፣ ዛሬ የገዛ "ስልጣኔውን" እርቃን እያወጣው ይ
እስላማዊው ዓለም ወንጀለኞችን በህግ አግባብ የሚቀጣበትን ስርኣት "ዘግናኝ" እና "ኋላቀር" እያለ የሰብዓዊ መብት ስብከት ሲሰጥ የኖረው የምዕራቡ ዓለም፣ ዛሬ የገዛ "ስልጣኔውን" እርቃን እያወጣው ይገኛል። "የዲሞክራሲ፣ የእኩልነትና የፍትህ ማማ ነኝ" የምትለው አሜሪካ፣ በተለያዩ ምክንያቶች 13 የአሜሪካ ወታደሮችን በመግደል ወንጀል በተፈረደበት አንድ የቀድሞ የአሜሪካ ጦር ሜጀር ላይ የሚፈጸመውን የጥይት ድብደባግድ*ያ በመንግስት ደረጃ በ'ላይቭ' ለዓለም ህዝብ ልታሳይ ቀጠሮ መያዟ አስገራሚ የግብዝነት ጥግ ነው። ለዘመናት የሞት ቅጣትን በአደባባይ መፈጸም "የመካከለኛው ዘመን የጨለማ ታሪክ ነው" ሲሉን የነበሩት ራሳቸው፣ ዛሬ የሰውን ልጅ በጥይት ተደብድቦ ህይወቱ ሲያልፍ የሚያሳይ ክስተት ለህዝብ ክፍት አድርገናል እያሉ ነው። ይህንን ድርጊት አሜሪካ ሳይሆን ሌላ ምስራቃዊ ወይም የሙስሊም ሀገር አድርጎት ቢሆን ኖሮ፣ ምዕራባውያን ሚዲያዎች እምነቱን በማጥላላት ምን ዓይነት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ይከፍቱበት እንደነበር መገመት አያዳግትም። "ጨካኝ፣ ጸረ-ሰብዓዊ፣ እና የጭቆና ስርዓት" የሚሉ የውግዘት ናዳዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ይዘንቡበት ነበር። ነገር ግን አድራጊዋ አሜሪካ በመሆኗ፣ ይህንኑ አሰቃቂ ድርጊት እንደ ግልጽነትእና እንደ ተራ የህግ ማስከበር ሂደት ለማቅረብ ሲሞከር ይታያል። ይህ ደብል ስታንደርድ ሚያስተምረን ትልቅ እውነት ቢኖር፤ የምዕራቡ ዓለም የሰብዓዊ መብት ጩኸት ለሌሎች ሀገራት ማሸማቀቂያ የሚጠቀሙበት የፖለቲካ ዱላ እንጂ፣ ከእውነተኛ የሞራል ልዕልና የመነጨ አለመሆኑን ነው! የሕያ ኢብኑ ኑህ

የስራ ማስታወቂያ በፋርማሲ ድግሪ ያለው/ያላት ስራ ቦታ ጀሞ ሚካኤል አከባቢ ደሞዝ በስምምነት በዚህ አድራሻ ያናግሩን

ኢየሱስ ተሰቅሏል አይተናል ያሉትም እኮ እንዲሁ ነው😊

ከጥቂት ወራት በፊት አንድ ወንድሜ በግርምት አንድ ጥያቄ አነሳልኝ፦ "ምንድነው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተፈጠረ ያለው? አንድ ሙስሊም በምንም ዙሪያ ይሁን ብቻ የሆነ ጉዳይ በለጠፈ ቁጥር፣ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ነን የሚሉ አካላት ጽሑፉን በእስልምና ጥላቻ እና በስድብ ያጥለቀልቁታል። ኮሜንት አድራጊው የሰው ልጅ ሳይሆን ፕሮግራም የተደረገ 'ቦት' እስኪመስል ድረስ ስድቡና ጥላቻው ይገርማል። ያውም በብልግናቸው ላይ ያላቸው ድፍረትና መተማመን እጅግ ያስደነግጣል፤ ምክንያቱ ምንድን ነው?" የሚል ነበር። የዚህ ችግር መነሻ ሩቅ አይደለም። በተለይ በፌስቡክ፣ ቲክቶክ እና መሰል የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ መረን የለቀቁ፣ ከሃይማኖት ስነ-ምግባር ይልቅ የብልግና አምባሳደር የሆኑ ሰዎችን የመከተል እና ለእነሱ የተጋነነ መድረክ የመስጠት አዝማሚያ የፈጠረው ቀውስ ነው። ስድብና ጥላቻ እንደ ጀግንነት የሚቆጠርበት አሳዛኝ የሞራል ኪሳራ ውስጥ ገብተናል። ታዲያ ለዚህ ምላሻችን ምን ሊሆን ይገባል? የዚህን የብልግና መንጋ ጩኸት ለማስተጋባት፣ እኛም እንደነሱ ተመሳሳይ ባለጌዎችን አሰልጥነን ማሰማራት እንችላለን? በጭራሽ! ብልግናን በብልግና መመለስም የእነሱን የውድቀት ደረጃ ማጽደቅና እነሱ ወዳሉበት አዘቅት መውረድ ነው። ነገር ግን፣ ይህ ማለት በዝምታ እናልፈዋለን ወይም የጥላቻ ዶፍ ሲወርድብን እጃችንን አጣጥፈን እንቀመጣለን ማለት አይደለም። በተለይ በእስልምና እና በነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ የሚሰነዘሩ ጸያፍ አገላለጾችን እና የጥላቻ ትርክቶችን ዝም ብሎ ማየት ፈጽሞ አይቻልም። እስካሁን ድረስ በግል የስራ ሁኔታዎች አለመመቻቸት ምክንያት፣ ለዚህ አሳሳቢ ጉዳይ የሚገባውን ትኩረት መስጠት ተስኖን ቆይቷል። እንደምናውቀው ቲክቶክ ላይ ረጅም ሰዓታት በ'ላይቭ' ተቀምጦ መከራከር ከሚፈልገው ጊዜ አንጻር አሁንም ቢሆን በእጅጉ ይከብደናል። ሆኖም ይህን እንደ ምክንያት አቅርበን ዳር ቆመን መመልከቱን ግን ማቆም የሚኖርብን ሰአት ይመስለኛል። ስለዚህ፣ ኢንሻአላህ አላህ ፈቃዱ ከሆነ ከአንድ ወንድሜ ጋር በመሆን፣ በዚህ በፌስቡክ መንደር ጠንከር ያሉ የጽሑፍ Counter ስራዎችን በቻልነው ልክ በተጠና መልኩ በአላህ ፍቃድ ከዚህ በኃላ እንሰራለን። መሠል ነገርም ዝምብሎ በማለፍ ብቻ ሳይሆን በመታገልም ጭምር ማምከን አስፈላጊ ነው። እንደ ሙስሊም የሚሰነዝርብንን የጥላቻ መልዕክት የምንመክተው የእነሱን ጸያፍ ቋንቋ በመዋስ ሳይሆን፣ አጀንዳቸውን ከስሩ በሚያመክንና እውነታውን ገልጦ በሚያሳይ የማያቋርጥ የጽሑፍ ትግል ነው። ዛሬ ላይ አንድም ሆነን ሁለት፣ ኢንሻአላህ ይህንን ስራ እንጀምረዋለን። ሀቅን የሚወዱና ቁጭቱ ያለባቸው የሙስሊም ወንድም እህቶቼ ጋር፣ ቀስ እያልን እንደምንበዛ፣ ሀሳብ ለሀሳብ ተሳስረን ድምጻችንን እንደምናጎላም ጽኑ ተስፋ አለኝ። በባዶ አሸዋ ላይ የተገነባው ጸያፍ አንደበትና ሀሰት ላይ የተመሠረተው የራስ መተማመንም ቢሆን እውነት ፊት መትነኑ አይቀርም። ❝ በእርግጥ እውነትን በውሸት ላይ እንጥላለን፡፡ አንጎሉን ያፈርሰዋልም፡፡ ወዲያውም እርሱ ጠፊ ነው፡፡ ለእናንተም ከዚያ (ሚስትና ልጅ አለው በማለት) ከምትመጥኑት ነገር ብርቱ ቅጣት አላችሁ፤ (ወዮላችሁ)፡፡❞ — አል አንቢያ (21:18) በፌስቡክ ለመከታተል

ክርስቲያኖች ቁርኣን (3፡178) በመጥቀስ፡- "የእስልምናው አምላክ ለሰው ልጆች መዳን አይጨነቅም፤ ሰዎች እንዲድኑም እድል አይሰጥም። ይልቁንም አዘናግቶ በማቆየትና ኃጢአት እንዲጨምሩ በማድረግ፣ የንስሐ ጊዜ አሳጥቶ ለገሃነም ይዳርጋቸዋል። የኛ አምላክ ግን ማንም እንዳይጠፋ ይታገሳል" የሚል ክስ ያቀርባሉ። "እነዚያ የካዱት ሰዎች እነርሱን ማዘግየታችንን ለነፍሶቻቸው ደግ ነገር ነው ብለው አያስቡ፡፡ እነርሱን የምናዘገያቸው ኃጢኣትን እንዲጨምሩ ብቻ ነው፡፡ ለነሱም አዋራጅ ስቃይ አላቸው፡፡" ( አል-ዒምራን 3፡178) መልስ፡ 1)የቁርኣኑ አንቀጽ እየተናገረ ያለው መልእክቱ በግልጽ ደርሷቸው፣ እውነታውን በልቦናቸው እያወቁ፣ ሐቁን ላለመቀበል "አሻፈረኝ" ብለው በእልከኝነት በክህደታቸው ስለሚዘወትሩ ሰዎች ብቻ ነው።ይህ ባይሆንና አንቀጹ እስልምናን ባልተቀበሉ ሰዎች ሁሉ ላይ የሚሰራ አጠቃላይ ሕግ ቢሆን ኖሮ፣ ማንም ሰው ተመልሶ ወደ እስልምና አይመጣም ነበር። ምክንያቱም የተሰጣቸው ጊዜ እንዲጠፉ እንጂ እንዲድኑ ካልሆነ፣ መጀመሪያ ካመኑት ሰዎች ውጪ አዲስ የሚድን (የሚሰልም) ሰው አይኖርም ነበር። በተግባር ግን እያየን ያለነው ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ብዙዎች የተሰጣቸውን ጊዜ ተጠቅመው እውነቱን ሲረዱ ወደ እስልምና ሲመጡ ነው። ስለዚህ አንቀጹን ሁሉንም ከሃዲ እንደሚመለከት አድርጎ ማቅረብ ፈጽሞ የተሳሳተ አረዳድ ነው። አንቀፁ በጭራሽ ሁሉንም ከሃዲ አይመለከትም። የሚሰራው እውነቱ እንደ ፀሀይ አብርቶላቸው፣ ልባቸው እያወቀው በስልጣን፣ በኩራት ወይም በእልህ "አንቀበልም" ብለው በሚያምፁት (በዘመኑ እንደነበሩት አቡ ጃህል ወይም እንደ ፈርዖን ባሉ) እልከኞች ላይ ብቻ ነው። አላህ እነዚህን ሰዎች በራሳቸው ምርጫ ይተዋቸዋል። እውነቱን ለማወቅ ለሚፈልገው፣ ቅን ልቦና ላለው ወይም ባለማወቅ ለተሳሳተው አብዛኛው ሰው ግን፣ የሚሰጠው ተጨማሪ ጊዜ የንስሐ (የተውባ) እና ወደ ቀጥተኛው መንገድ የመመለሻ ትልቅ መለኮታዊ እድል ነው። 2) አላህ የሰው ልጆች እንዲድኑ ስለሚፈልግ ንስሐ የሚባል እድል ሰጥቶናል፤ ይህን እድል መጠቀም ወይም አለመጠቀም ደግሞ የኛ ምርጫ ነው። በተደጋጋሚ "አሻፈረኝ" ስንል ግን ባለንበት መስመር ይተወናል (ጊዜ ይሰጠናል)። በዚያም ወንጀላችን እየበዛ ልክ እንደ ፈርዖን ልባችን ይደነድናል፤ አምላክን እያመፅን ሲደላን ደግሞ ያላወቀብን፣ ያላየንና ምንም ነገር የማያደርገን ይመስለናል። ቀኑ ሲደርስ ግን መመለሻ አናገኝም፤ ምክንያቱም አውቀን ያጠፋን ነንና።አላህ አዛኝነቱን እና መሐሪነቱን ከሚያሳይባቸው ነገሮች አንዱ፣ ባጠፋን ቁጥር ወዲያውኑ መቅጣት እየቻለ ማለፉ ነው። ቁርኣን 35፡45፦ "አላህም ሰዎችን በሠሩት ኃጢአት ቢቀጣ ኖሮ፣ በምድር ጀርባ ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ ባልተወም ነበር፡፡ ግን እስከ ተወሰነ ጊዜ ያቆያቸዋል..." ቁርኣን 18፡58፦ "ጌታህም መሐሪ የእዝነት ባለቤት ነው፡፡ በሠሩት ኃጢአት ቢቀጣቸው ኖሮ ቅጣትን ለእነሱ ባስቸኮለ ነበር፡፡ ግን ለእነሱ የተቀጠረ ጊዜ አላቸው..." ዝም ይለናል፤ የሱን ዝምታ ግን እኛ የምንረዳበት መንገድ ወሳኝ ነው። "ምንም አይመጣብኝም" የምንል ከሆነ በዝምታው ጊዜ ይሰጠናል ፣ ባይወደውም በራሳችን ላይ ወንጀል እያከማቸን እንቆያለን፤ የንስሐ በር ይዘጋብናል፣ ድንገትም ሞት መጥቶ ይወስደናል። "ተመቸኝ፣ ዝም አለኝ፣ ትክክል ባልሆን እኮ ዝም አይለኝም ነበር " ብላችሁ በኃጢአት ላይ አትዘውትሩ፤ "ለነፍሶቻቸው ደግ ነገር ነው ብለው አያስቡ" የተባለውም ለዚህ ነው። 3) መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች እውነትን በተደጋጋሚ ሲክዱ፣ ፈጣሪ በገዛ ፍላጎታቸው እንደሚተዋቸውና ልባቸውን እንደሚያደነድን ያሳያል። የፈርዖን ልብ መደንደን ዋነኛው ማሳያ ነው። ፈርዖን ተአምራትን አይቶ እውነት መሆኑን ከተረዳ በኋላም በተደጋጋሚ እምቢተኛ በመሆኑ፣ እግዚአብሔር ልቡን አደነደነው። ዘጸአት 9፡12፦ "እግዚአብሔርም የፈርዖንን ልብ አደነደነ፥ እግዚአብሔርም ለሙሴ እንደ ተናገረው አልሰማቸውም።" ​ዘጸአት 10፡20፦ "እግዚአብሔር ግን የፈርዖንን ልብ አደነደነ፥ የእስራኤልንም ልጆች አልለቀቀም።" ​ዘጸአት 10፡27፦ "እግዚአብሔር ግን የፈርዖንን ልብ አደነደነ፥ ሊለቃቸውም አልወደደም።" ​ዘጸአት 11፡10፦ "...እግዚአብሔርም የፈርዖንን ልብ አደነደነ፤ የእስራኤልንም ልጆች ከምድሩ አልለቀቀም።" ሮሜ 1፡28፦ "እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው።" ​ኢሳይያስ 6፡10፦ "በዓይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳይፈወሱ የዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን..."

በመድኃኒት እና በህክምና መገልገያ መሣሪያዎች አስመጪነት ስራ ላይ ኖዎት? ወይስ አዲስ ማስመጣት አስበዋል? ለስራዎ ስኬት  የሚያግዝ አስተማማኝ የማማከር አገልግሎት ከፈለጉ በዚህ አድራሻ ያነጋግሩን። በተጨማሪም Single Window ላይ የሚሰሩ ስራዎችን በታማኝነት እንሰራለን።

በመድኃኒት እና በህክምና መገልገያ መሣሪያዎች አስመጪነት ስራ ላይ ኖዎት? ወይስ አዲስ ማስመጣት አስበዋል? ለስራዎ ስኬት  የሚያግዝ አስተማማኝ የማማከር አገልግሎት ከፈለጉ በዚህ አድራሻ   ያነጋግሩን። በተጨማሪም Single Window ላይ የሚሰሩ ስራዎችን በታማኝነት እንሰራለን።

በመድኃኒት እና በህክምና መገልገያ መሣሪያዎች አስመጪነት ስራ ላይ ኖዎት? ወይስ አዲስ ማስመጣት አስበዋል? ለስራዎ ስኬት  የሚያግዝ አስተማማኝ የማማከር አገልግሎት ከፈለጉ በዚህ አድራሻ ያነጋግሩን። በተጨማሪም Single Window ላይ የሚሰሩ ስራዎችን በታማኝነት እንሰራለን።

የስልጠናው ኦዲዮው አጭር ማብራሪያ፦ ይህ የመጀመሪያው የድምጽ ክፍል ስለ 'ሱና' ምንነት እና የሐዲስ አጠባበቅ ታሪክ ጥልቅ ግንዛቤን የሚያስጨብጥ ነው። ፋይሉን በጉጉት እንድታዳምጡት የሚጋብዙ ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦ • ሱና በቋንቋ እና በሸሪዓዊ አገባቡ (ከነብዩ ንግግር፣ ተግባር እና ማጽደቅ አኳያ) ምን ማለት እንደሆነ በዝርዝር ያብራራል። • የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲሶች ከመጀመሪያው ጀምሮ እንዴት በአራት ዋና ዋና መንገዶች (በማስታወስ/በመሸምደድ፣ በመጻፍ፣ እርስ በርስ በመማማር እና በተግባር በመተርጎም) ተጠብቀው እንደቆዩ ይተነትናል። • ገና በሶሓባዎች ዘመን (እንደ አብደላህ ኢብኑ አምር፣ አሊ ኢብኑ አቢ ጧሊብ፣ አቡ ሁረይራ እና አነስ ኢብኑ ማሊክ) የራሳቸው 'ሰሒፋ' (የጽሁፍ ስብስቦች) እንደነበሯቸው ታሪካዊ ማስረጃዎችን ያቀርባል። • ከሰሒፋዎች በመቀጠል የሐዲስ ስብስቦች እንዴት ወደ 'ሙሰነፍ' (በርዕስ የተከፋፈሉ)፣ 'ሙስነድ' (በሶሓባዎች ስም የተከፋፈሉ) እና 'ሱነን' (በፊቅህ ህግጋት የተከፋፈሉ) መጻሕፍት እንዳደጉ በሰፊው ይዳስሳል። • የሐዲስን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ በዑለማዎች ስለተዘረጉት ጥብቅ ሳይንሶች (እንደ ዒልሙ ሪጃል፣ ዒልሙል ዒለል የመሳሰሉት) ያስገነዝባል። © ዳሩል ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

አዲስ እና ልዩ አጭር ኮርስ ከሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል | #1ኛ ዙር ስልጠና ​“ቁርአን ብቻ ይበቃናል” የሚሉ አካላት መነሻቸው ምንድን ነው? የሱና (ሀዲስ) አስፈላጊነትና በኢስላም ውስጥ ያለው ድርሻ
አዲስ እና ልዩ አጭር ኮርስ ከሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል | #1ኛ ዙር ስልጠና ​“ቁርአን ብቻ ይበቃናል” የሚሉ አካላት መነሻቸው ምንድን ነው? የሱና (ሀዲስ) አስፈላጊነትና በኢስላም ውስጥ ያለው ድርሻስ ምን ያህል ነው? ​እነዚህን እና ሌሎች ተያያዥ አንገብጋቢ ጥያቄዎችን በሰፊው የሚዳስሰውን 1ኛ ዙር የንፅፅር ትምህርት ኮርስ በማዕከላችን የቴሌግራም ቻናል ይዘንላችሁ ቀርበናል። • ​አዘጋጅ፦ ኢልያህ ማሕሙድ • ​የሚሰጥበት ቦታ፦ በሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል የቴሌግራም ቻናል ​ይህንን ወሳኝ ኮርስ ሙሉ በሙሉ ተከታትለው በመጨረሻም የሚዘጋጀውን ፈተና ለሚወስዱ እና ለሚያልፉ ተሳታፊዎች በሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በኩል የምስክር ወረቀት ይሰጣል። ​እውቀትን ከትክክለኛው ምንጭ እንቅሰም! ትምህርቱን ለመጀመር የቴሌግራም ቻናላችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፦ https://t.me/Hidayaic8212

የዚህ ግለሰብ ጓደኛ የሆናቹ ሰላምታ ከሰጣቹ በሩቅ ይሁን! ውሃም ሰለማይወድ ቢያንስ በቀኙ እጁ ምን ነካክቶ እንደወጣ አይታወቅም ። መብቱን አክብሩለት

ህንድ ሀገር የሚኖር አስቸኳይ የተፈለገ መድሀኒት በመግዛት ሊተባበረኝና ሊልክልኝ የሚችል ሰው ካለ በዚህ ያናግረኝ Abu Yusra

ሀምዛ ዞርትዚስ ከታዋቂው የሞሪታንያ ዓሊም ሸይኽ ዶ/ር ሙስጠፋ አል-ሸይባኒ ጋር ያደረጉትን እጅግ ጠቃሚ ውይይት ተመልክቼ ነበር። በተለይ በዚህ ዲጂታል ዘመን ዳዕዋ ስናደርግ ስለሚገጥሙን እንደ ኢጎ (እኔነት) እና የታዋቂነት ፈተናዎች እንዴት ማለፍ እንደምንችል ያነሱት ሀሳብ ልብ ይነካል። ቪዲዮውን እያየሁ የተወሰነ ማስታወሻ ለመያዝ የሞከርኩ ቢሆንም በመሀል የራሱ AI ሰመራይዝ ያደረገውን ስመለከት ግን ሀሳቤን በጥቅሉ ስለገለጸው እሱን በቡሌት ተርጉሞ ማስቀመጡን መርጫለሁ። የውይይታቸው ​ዋና ዋና ነጥቦች እነሆ፡- • ​ወደ አደባባይ እና ዲናዊ ስራ ከመውጣታችን በፊት በሌሊት ሶላት (ቂያሙል ለይል) እና በኢኽላስ (ቅንነት) ራሳችንን ማነፅ እና ከአላህ ጋር ያለንን ሚስጥራዊ ግንኙነት ማጠናከር አለብን። • ​ ቁርኣንን ለበረካ ብቻ ሳይሆን አስተሳሰባችንን ለመቅረፅ እና ራሳችንን ለመለወጥ ልንጠቀምበት ይገባል። • ​ ለዳዒ ትልቁ ጠላት ታዋቂነት ነው። ከተከታዮቻችን (followers) ቁጥር ይልቅ በዋናው አላማችን ላይ ብቻ ማተኮር አለብን፤ ስኬት ሁሌም ቢሆን የአላህ ስጦታ ነውና። • ​ሱረቱ ዩሱፍ እንደሚያስተምረን ውጤታማ ዳዕዋ የረጅም ጊዜ እቅድን፣ ሰዎችን መረዳትን እና ትችትና ውድቀቶችን በትዕግስት ለማለፍ "ትልቅ ልብ" ሊኖረን ይገባል። • ​ስኬት ከቤት ይጀምራል፦ የትዳር አጋራችን እና ቤተሰባችን ከውጭ ለሚገጥመንን ጫና መቋቋሚያ ትልቁ "መልህቃችን" ናቸው። ስለዚህ ጠንካራ እና አፍቃሪ የቤተሰብ ግንኙነት መገንባት ለስኬታችን ወሳኝ ነው። ​በመጨረሻም ሀምዛ በራሱ ህይወት ተሞክሮ እንዳጠቃለለው፤ ምንም ያህል የተማርን እና የአካዳሚክ እውቀት ቢኖረንም፣ በዳዕዋ ስራችን ላይ ቁርኣን ሁሌም ቀዳሚ፣ ሀይለኛ እና ውጤታማው መመሪያችን ነው። ሙሉ ውይይቱን በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ።