cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student | Teacher |

Больше
Рекламные сообщения
13 211Подписчики
+624 часа
+377 дней
+33630 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

👍 19
የእስራኤላውያን ቆይታና ዝብርቅርቁ ታሪክ እስራኤላውያን በግብጽና ከነአን ምድር የቆዩበትን ዘመን በተመለከተ መጽሀፍ ቅዱስ በኦሪት ዘጸአት ላይ የጊዜ መጠኑን እንደሚከተለው ገልጾ እናገኛለን፦
“የእስራኤልም ልጆች በግብፅ ምድር የተቀመጡት ዘመን አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ነው።”   — ዘጸአት 12፥40
ይህ አንቀጽ እስራኤላውያን በግብጽ ምድር ብቻ የቆዩበትን ጊዜ ጠቅሶ 430 አመት እንደሆነ ሲናገር አዲሱ መደበኛ ትርጉምም በተመሳሳይ 430 አመት አድርጎ ያስቀምጠዋል። ነገር ግን በሳምራዊያን ኦሪትና በሰብአ ሊቃናት ትርጉም ግን 430 አመት በግብጽ ብቻ የቆዩበት ዘመን ሳይሆን በከነአንም ጭምር የኖሩበት ዘመን እንደሆነ ይገልጻል። አዲሱ መደበኛ ትርጉምም በህዳጉ ይህንኑ ልዩነት ይገልጻል። በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የታተመው የሚሊኒየም ትርጉምም ከዚህ ቀደም ከነበረው ለየት በሚል መልኩ ከነአንን ጨምሮ ይጠቅሳል፦
"የእስራኤልም ልጆች በግብፅ ምድርና በከነዓን ምድር እነርሱና አባቶቻቸው የተቀመጡት ዘመን አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ነው።" ኦሪት ዘጸአት 12፥40 (የ2000 ትርጉም)
የእንግሊዝኛ ትርጉሞችም አንቀጹን አስመልክቶ የተለያየ አይነት ትርጉም የያዙ ሲሆን የንጉስ ጀምስ ቅጅ ግብጽን ብቻ ሲጠቅስ የኮንሰርቫቲቭና የአፖስትል ትርጉሞች ደግሞ የሰብአ ሊቃናትን ትርጉም በመያዝ ከነአንንም ይጨምራሉ። ከታች ለአብነት የተወሰኑት ተያይዘዋል፦
“Now the sojourning of the children of Israel, who dwelled in Egypt, was four hundred and thirty years.”   — Exo 12:40 (AKJV)
“Now the time that the sons of Israel dwelt in the land of Egypt and the land of Canaan (LXX) was four hundred and thirty years.”   — Exo 12:40 (ACV)
“And the sojourning of the children of Israel, while they sojourned in the land of Egypt and the land of Canaan, was four hundred and thirty years.”   — Exo 12:40 (ABC)
እነዚህ ሁሉ ልዩነቶች/Variants/ የተለያየ የመጽሀፍ ቅዱስ አንቀጽ ጋር የሚገኙና እርስበርስ የሚጋጩ ሳይሆን አንድ አንቀጽ ላይ የሚገኙና ሊቃውንቱ በይዘታቸው ዙሪያ ያልተስማሙባቸው ሁነው በተለያየ መጽሀፍ ቅዱስ ላይ የተለያየ ዘገባ የያዙ ናቸው። © የሕያ ኢብኑ ኑህ በዚህ ዙሪያ በቪዲዮ የተሰጠውን ትምህርት ለመከታተል የሚከተለውን ሊንክ ይከተሉ፦ https://vm.tiktok.com/ZMMgWm61s/
Показать все...
👍 20 2
ይህንን ነጻ ኮንፈረንስ ተሳተፉ..! በተለይም ኦንላይን በብዛት ለመቆየት ምቹ ሁኔታ ያላችሁና የተለያየ ተሰጥኦ ያላችሁ ክፍያ ያላቸው የኦንላይን ስራዎችን እንዴት መስራት እንደምትችሉ ለማወቅ ይጠቅማችኃል። ማስታወቂያው ከዚህ በታች እንደሚከተለው ነው፦ ** ከቤትዎ ሆነው ኦንላይን መስራት ይችላሉ የሚል ማስታወቂያ ገጥሞዎት ያውቃል? ወይም ግብዣ ተልኮልዎት ያውቃል?በዚህ ዘመን የትኛው ትክክል የትኛው ደግሞ የማጭበርበርያ መንገድ መሆኑን መለየት እየከበደ መጥቷል። ነገር ግን በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅናን ያገኙና ለረዥም አመታት ለበርካታ ስራ ፈጣሪዎች እስከ ሚልዮን ዶላሮች ገቢ ማስገኘት የቻሉ online freelance platformኦችና የስራ አይነቶችን መተዋወቅ ይፈልጋሉ? በኦንላይን በሚሰሯቸው ስራዎች የሚያገኟቸውን አለም አቀፍ ክፍያዎች እንዴት መሰብሰብ እንደሚችሉስ ማወቅ ይፈልጋሉ? ... 1ኛውን የቲጃራ Bizpreneur conference በመሳተፍ በዘርፉ እውቀትና ልምድ ካላቸው ባለሙያዎች የዘመኑን ኢንደስትሪ ይቀላቀ። 1ኛውን የቲጃራ Bizpreneur conference ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ በመጫን የሚመጣላችሁን የጎግል ፎርም በመሙላት መመዝገብ ትችላላችሁ፦ https://forms.gle/W5mGSSipD3TAfHfXA በተጨማሪም በሚከተለው ስልክ ቁጥር (0922615555) ስም፣ እድሜ ፣ የትምህርት ደረጃ፣ እየሰሩት ያለበት የስራ ዘርፍ (ሊሰማሩበት የሚፈልጉት የስራ ዘርፍ) በአጭር የፅሁፍ መልዕክት በዋትስአፕ ወይም በቴሌግራም በመላክ መመዝገብ ትችላላችሁ ◾️ ይህንን ነፃ ኮፍረንስ ያለ ምዝገባ መሳተፍ አይቻልም። 1ኛው የቲጃራ Bizpreneur conference #ቲጃራ #TBC
Показать все...
👍 29
የአፋሩ ወንድማችን ወንድም ሳዲቅ በድሩ እዚህው ፌስቡክ ሜዳ ላይ ከተዋወቅኳቸው ቅን ወንድሞች መካከል ነው። በተለያዩ የዳዕዋ ጉዳዮች አፋር ላይ ሀጃ ካለን ለትብብር ቀድሜ የምሄደው ወደርሱ ነበር። ከወራት በፊት ምክንያቱን በማላውቀው ጉዳይ የክልሉ መንግስት እንዳሰረው ሰማሁ። ዛሬ ደግሞ በእስር ቤት ከፍተኛ ህመም እንደገጠመው በዚሁ ሜዳ ተመለከትኩ፣ ወንድማችንን ሳናጣው በፊት የማሳከም ኃላፊነቱን በህግ ከለላ ስር ያደረጉት አካላት ከነሱ ይጠበቃል። አሏህ አፍያውን እንዲመልስለት በዱዓ አትርሱት..! ___ https://t.me/Yahyanuhe
Показать все...
😢 55👍 27 11🤩 2
የሸይኽ ሙሐመድ ዑስማን ማራኪ ቲላዋ ነው፣ አድምጡት https://t.me/Qurantilawas
Показать все...
🥰 31👍 11 2
"ጎንደር ላይ 500 ሚሊየን ብር የሚፈጅ አውዳሚ ዩራኒየም ቦንብ ከሙስሊሞች ይዘናል" ብለው የጎንደሩን ጭፍጨፋ ሲያጋፍሩ ከነበሩ ቀጣፊ ግለሰቦች መካከል ነበሩ፥ ሊቀ ኅሩያን አባ ዮሴፍ ደስታ..! በወቅቱ በፈጸሙት ግዙፍ ውሸት ምክንያት ሀፍረታቸውን ለመሸሸግ ሲኖዶሱ ከቦታው ዘወር አድርጎ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አምጥቷቸው የነበረ ቢሆንም አሁን ጉዳዩ የተረሳሳ ሲመስል በአቡነ አብርሀም የድጋፍ ደብዳቤ አማካኝነት ወደ ማዕከላዊ ጎንደር የቀድሞ "ስራቸው" ተመልሰዋል። https://t.me/Yahyanuhe
Показать все...
ማርያም በእቅፏ የነበረው ልጇ "ሰማያትና ምደርን ያስገኘው የአለማት ፈጣሪ" ነው ብላ ታምን ነበርን? ___ https://t.me/Yahyanuhe
Показать все...
👍 46😢 13🤷‍♂ 2 2🙉 2🤩 1
አንዳንድ ጉዳዮችን በዝርዝር ከመጻፍ አጠር አድርጎ በሜሜ ማቅረብ የተሻለ ሀሳቡን ሊያብራራ ይችላል..! ___ https://t.me/Yahyanuhe
Показать все...
👍 122🤩 7🙉 5😱 2🙊 1
በውጭ ሀገር ያሉ ሙስሊም ነበርን እያሉ የሚዋሹ ሰዎች ደግሞ ሲጠየቁ የሚመልሱት መልስ በሳቅ ድክም ነው የሚያደርገው። አንዱን በእንግሊዝኛ እየጠየቁት "እርግጠኛ ሙስሊም ከነበርክ ከየትኛው ጀመዓ ነበርክ?ከሳንቡሳ ወይንስ ከመንዲ ጀመዓ ነበርክ?እርግጠኛ ነን ከመንዲ ጀመዓ ነበርክ እነሱ ናቸው ከሀቅ ያፈነገጡት" ሲሉት እሱም ተቀብሎ "ኧረ በፍጹም እኔ ከሳንቡሳ ጀመዓ ነበርኩ" ብሎ የምሩን መለሰ፤ በእርግጥ እንደኔ የመንዲ ጀመዓ ይሻለው ነበር 🙌
Показать все...
🤩 120👍 30🙊 24🙉 15🥰 3🍓 3😱 2 1🔥 1