አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ
Ir al canal en Telegram
የአቡ ዩስራ ንጽጽራዊ ሀይማኖት ላይ ያተኮሩ የፁሁፍና የድምጽ ስራዎች ይቀርቡበታል።
Mostrar más4 731
Suscriptores
+724 horas
+647 días
+65030 días
Archivo de publicaciones
Repost from የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
የምሥራች! - "የእባቡን ጭንቅላት ቀጥቅጠነዋል፤ አሁን ጅራቱ ብቻ ይቀረናል!" (ዘፍጥረት 3፡15፣ ሮሜ 16፡20)
አልሐምዱሊላህ! ከሰሞኑ የጀመርነው ታላቅ የምላሽ ሥራ ወደ ፍጻሜው ተቃርቧል። ባለፉት ሳምንታት ረጅም ጊዜና ከፍተኛ ልፋት ወስዶብን በትኩረት ስንሠራው የነበረው "የጽልመቱ ጥላ" የተሰኘው መጽሐፍ የምላሽ ሥራ፣ በአላህ ፈቃድ ፍጻሜው አምሮ ማጠቃለያው ላይ ደርሰናል።
ስለሆነም በቀጣይ ቀናት በአላህ ፍቃድ፦
• በሚቀጥለው ሳምንት፦ ሙሉ የምላሽ መጽሐፉ ለሁሉም አንባቢያን በነጻ በፒዲኤፍ ተለቆ እጃችሁ የሚደርስ ይሆናል፣ ኢንሻአላህ!
• እንደተለመደው፦ ማንኛውም አንባቢ እውነታውን በራሱ ማረጋገጥ እንዲችል፣ ምላሽ የተሰጠበት የመጽሐፉ ሙሉ ክፍል ከምላሻችን ጀርባ አብሮ ይያያዛል።
• በሚቀጥለው ሳምንት ቅዳሜ፦ መጽሐፉን በተመለከተ እና በተዘጋጁት አዳዲስ ምላሾች ዙሪያ እጅግ ደስ የሚልና ልዩ የቲክቶክ ላይቭ ቆይታ ይኖረናል!
(ማሳሰቢያ፦ ዛሬ ምሽት መደበኛው የቲክቶክ ላይቭ ፕሮግራማችን አይኖረንም።)
አልሐምዱሊላህ!
https://t.me/Yahyanuhe
Repost from የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
ሲያጠምቁ "እልልታ"፣ ሲሰልሙ "ተገደው ነው"?! ይህችን ያረጀች ፕሮፓጋንዳ ተዋት!
በምስሎቹ ላይ እንደምትመለከቱት፣ አንደኛው ወገን በገዛ ገጹ "23,199 ነፍሳት ተጠመቁ" እያለ በኩራት ዜና ሲሰራና ሲያጨበጭብ ይታያል። ይህ ለእነሱ "ጻድቅ" እና "ኖርማል" ተግባር ነው፤ ማኅበራዊ ሚዲያቸውም በ"እልልታ" እና "አሜን" ይሞላል። በሌላ በኩል ደግሞ፣ መቶ እንኳን የማይሞሉ ሰዎች በራሳቸው ፍላጎት እስልምናን ሲቀበሉ ምስሉ ላይ እንደምታዩት አይናቸው ይቀላል፤ "ከሚሞቱ ብለው ነው" ወይም "ተገደው ነው" እያሉ የሃሰት ጩኸታቸውን በማህበራዊ ሚዲያ ያቀልጡታል።
ይህ ዓይነቱ የተንሸዋረረ አመለካከትና የለቅሶ ፕሮፓጋንዳ በዋናነት ሁለት ዓላማዎችን ያነገበ ነው፦
1ኛ በዳዕዋ መስክ የገጠማቸውን ትልቅ ሽንፈት በሌላው ላይ ለማላከክና እውነታውን ለመሸሸግ የሚደረግ መፍጨርጨር ነው።
2ኛ እስካሁን ባለው የሙስሊሙ እንቅስቃሴ "ዳዕዋ በሰፊው ተሰርቷል" ተብሎ ባይገመትም እንዲሁም ክፍተቶች ቢኖሩትም፤ በአቅማቸው የሚለፉና የሚታገሉ አካላትን መልካም ድካም ጥላሸት በመቀባት፣ ታጋዮቹን ለማሸማቀቅና ሞራል ለመስበር የታለመ ነው።
እጅግ የሚያሳዝነው የዚህ አስተሳሰብ ባለቤቶች ለራሳቸው ያላቸው የተለጠጠ አመለካከት ነው። ሀገረ ስብከቶቻቸው በየዓመቱ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን "አጠመቅን" እያሉ ዜና ሲሰሩ፣ የሙስሊሙ ትግል ግን እጅግ ይረብሻቸዋል፤ ጥቂት ሰዎች ሲሰልሙም ፈጥነው ፍርጃ ውስጥ ይገባሉ።
በእነሱ እምነት "ሰው መቀበል ያለበት እኛን ብቻ ነው፤ እኛ ጋር ሲመጣ ኖርማል ነው፣ ሌላው ጋር ሲሄድ ግን አእምሮውን ስቶ ወይም ተገዶ ነው" የሚል ያረጀና ያፈጀ ትምክህት ነው። የራሳቸው ሲሆን ጽድቅ፣ የሌላው ሲሆን ወንጀል አድርጎ ስያሜ በመስጠት ሌላውን ለማሸማቀቅ ይሞክራሉ።
ነገር ግን አንድ ሊያውቁት የሚገባ እውነት አለ፤ በእንደዚህ አይነት ርካሽ የ"አስገደዱን" ፕሮፓጋንዳ የሚሸወድ ጅል በዚህ ዘመን የለም! የሰዎችን ንቃተ ህሊና ንቆ የፈጠራ ክስ ከመደርደር ይልቅ፣ እውነታውን ተቀብሎ መኖር ይሻላል።
የዳዕዋ ስራችን ይቀጥላል!
https://t.me/Yahyanuhe
Repost from የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
በቪዲዮው ላይ በካሜራ ፊት ቀርቦ እኛ ያቀረብንለትን በማስረጃ የተደገፈ ምላሽ ሲያጣጥልና ሲዘባበት ታይቷል፦ «ማነው የተጠቀሰው? ኢብኑ ሐጀር አል-አስቀላኒ? ፈትሑል ባሪ? በ15ኛው ክፍለ ዘመን የነበረ ሰውዬ ተረት ተረት ለምን እንቀበላለን?» በማለት ታላቁን የእስልምና ሊቅና የምርምር ሥራቸውን ለማቃለል ሞክሯል።
ነገር ግን እውነታው ሲገለጥ አስደንጋጭ ነው! ግለሰቡ በገዛ እጁ ባሳተመው "የጽልመቱ ጥላ" በተሰኘው መጽሐፉ ገጽ 36 (ማስታወሻ 30) እና ገጽ 214 (ማስታወሻ 138) ላይ ይኸው በካሜራ ፊት ያፌዘበትን ሊቅ «አል-ሓፊዝ ኢብኑ ሐጀር፣ ፈትሑል ባሪ» እያለ በታላቅ ክብር ዋቢ አድርጎ አቅርቦታል!
ለመሆኑ አንድ ጸሐፊ ራሱ በመጽሐፉ ውስጥ ደጋግሞ የተጠቀመውን ዋነኛ ምንጭ በካሜራ ፊት እንዴት ሊረሳውና "ተረት ተረት" ብሎ ሊያንቋሽሸው ይችላል? እውነታው ከሁለት ነጥቦች ሊወጣ አይችልም፦
ወይ መጽሐፉን ራሱ አልጻፈውም፦ በውስጡ ያለውን እንኳን የማያውቅ፣ ከሌሎች ገጾች ኮፒ-ፔስት ተደርጎ የተሰጠውን ጽሑፍ በስሙ ብቻ ያተመ ሰው ነው፤
ወይም ደብል ስታንደርድ የሚጠቀም አጭበርባሪ ነው፦ ለራሱ የሐሰት ትርክትና ጥቃት ሲመቸው "አል-ሓፊዝ" እያለ የሚያከብረውን ሊቅ፣ ሙስሊሞች ስህተቱን ሲያጋልጡበትና ሲያፈርሱበት "ተረት ተረት" ብሎ የሚሸሽ ፍጹም እምነት የማይጣልበት ግለሰብ ነው!
የገዛ መጽሐፉን ገጾችና የራሱን ንግግር እንኳ ማስታረቅ የማይችል አካል፣ እንዴት ሆኖ ነው በዕውቀትና በሐቅ ላይ የተመሠረተ ሞገት አቀረብኩ ሊል የሚችለው?
ህሊና ያለው አስተዋይ አንባቢ ይፍረደው!
https://t.me/Yahyanuhe
Repost from የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
የእፎይ መጽሐፍ የፕሮቴስታንት ነገረ-መለኮትን በኦርቶዶክስ ስም ሲሰብክ... (ከገጽ 353 የተወሰደ)
በምስሉ ላይ እንደሚታየው፣ ጸሐፊው "የጽልመቱ ጥላ" በተሰኘው መጽሐፉ ገጽ 353 ላይ እንዲህ ሲል ይጽፋል፦
“ኢየሱስ የአይሁዶች መድኃኒትና ንጉሥ ነው። ምንም እንኳ በክርስቶስ የማያምኑ አይሁዶች ቢኖሩም ኢየሱስ ግን የአይሁድ ንጉሥ እና መድኃኒት ነው”
ለመሆኑ ይህ አስተምህሮ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነገረ-መለኮት ነውን?
በፍጹም አይደለም!
በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ትምህርት፣ ከክርስቶስ ስቅለትና ትንሣኤ በኋላ "የእግዚአብሔር ሕዝብ" ወይም "እስራኤል ዘነፍስ" የተባለችው በክርስቶስ ያመነችው ቤተ ክርስቲያን እንጂ በሥጋ የተወለዱት አይሁዶች አይደሉም። ጳውሎስ በሮሜ 9፡6-8 እና በገላትያ 3፡28-29 ላይ በግልጽ እንደሚያስተምረው፣ በክርስቶስ የማያምኑ የሥጋ አይሁዶች በሥጋ አብርሃማዊ ስለሆኑ ብቻ ልዩ የቃል ኪዳን ሕዝብ ወይም "ኢየሱስ መድኃኒታቸው የሆነላቸው" ሊባሉ አይችሉም።
ታዲያ እፎይ ይህንን የፕሮቴስታንት ትምህርት እንዴት ወደ መጽሐፉ አስገባው?
መልሱ እጅግ ቀላል ነው! ጸሐፊው የራሱ ቤተ ክርስቲያን የሆነችውን የኦርቶዶክስ ነገረ-መለኮት እንኳን በቅጡ የሚያውቅ ዕውቀት የለውም። ይልቁንም፣ መጽሐፉን ለመጻፍ የተጠቀማቸው ዋና ዋና ምንጮች የምዕራባውያን የኢቫንጀሊካል ወይንም የፕሮቴስታንት ፀረ-እስልምና ድረ-ገጾች ናቸው።
በምዕራቡ ዓለም ያሉ የፕሮቴስታንት "Christian Zionists" ወይንም ዲስፔንሴሽናሊስቶች በክርስቶስ የማያምኑ አይሁዶች አሁንም "ልዩ የአምላክ ሕዝብ ናቸው" የሚል እሳቤ አላቸው። እፎይ ደግሞ የነገረ-መለኮት ዕውቀት ስለሌለው፣ የእነዚያን የፕሮቴስታንት ጸሐፊዎች ጽሑፍ ያለ ምንም ማጣሪያ በቀጥታ ኮፒ-ፔስት በማድረግ፣ የፕሮቴስታንቱን ዶክትሪን እንደ ትክክለኛ ትምህርት አድርጎ አስቀምጦታል።
የገዛ ሃይማኖቱን ነገረ-መለኮት ከሌላ ሃይማኖት መለየት የማይችል አካል፣ እንዴት ሆኖ ነው የሌላውን ሃይማኖት (እስልምናን) ሊሞግት የሚነሳው?
ህሊና ያለው አስተዋይ አንባቢ ይፍረደው!
https://t.me/Yahyanuhe
ዐይን ያወጣ ማጭበርበር በገዛ መጽሐፉ ሲጋለጥ... (ከገጽ 209 የተወሰደ)
በተያያዘው ምስል ላይ እንደምትመለከቱት፣ ጸሐፊው "የጽልመቱ ጥላ" በተሰኘው መጽሐፉ ገጽ 209 ላይ፣ ሱረቱል ፋጢርን (35:1) ሲተረጉም የፈጸመው ዐይን ያወጣ ማጭበርበር እጅግ አስገራሚና እጅ በአፍ የሚያስጭን ነው!
ግለሰቡ የመላእክትን የክንፍ ብዛት በሁለት፣ በሦስትና በአራት ብቻ እንደተገደበ ለማስመሰል እና ከሐዲስ (ሰሒሕ ሙስሊም 174b) ጋር ይጋጫል ለማለት የተጠቀመበት ተንኮል ስለማንነቱና አካሔዱ ብዙ ትምህርት ይሰጠናል። ምስሉ ላይ በግልጽ እንደሚታየው፤ ዐረብኛውን ሙሉ ለሙሉ አስቀምጦ፣ በአማርኛው ትርጉም ላይ ግን ሆን ብሎ በነጠብጣብ (...) ትርጉሙን ቆርጦ አስቀርቶታል።
ለመሆኑ ጸሐፊው በነጠብጣቡ (...) ውስጥ ሆን ብሎ የደበቀው ቃል ምንድን ነው? ከተባለ
ጸሐፊው ሆን ብሎ የደበቀውና የቆረጠው ቀጣዩ የቁርኣን ቃል «በፍጥረቱ ውስጥ የሚሻውን ይጨምራል» (يَزِيدُ فِي الْخَلْقِ مَا يَشَاءُ) የሚለውን ታላቅ መልእክት ነው!
ይህ አንቀጽ አላህ በመላእክት ክንፍ ላይ የፈለገውን ያህል ገደብ የለሽ ጭማሪ እንደሚያደርግ በግልጽ እያሳየ ሳለ፣ እውነታውን ሸሽጎ፣ የቁርኣኑን ሰፊ መልእክት በማጥበብ አንባቢን በሐሰት ለማደናገር መሞከሩ አሳፋሪ ነው።
ጸሐፊው ይህንን ሐቅ ሆን ብሎ በመደበቅ፣ "በግልፅ ቁርኣን ላይ ስለ መላእክት ክንፎች ሲናገር... አራት አራት እንደሆነ ነው" በማለት፣ ቁርኣን ከመላእክት ክንፍ ብዛት ጋር ተያይዞ ጅብሪል 600 ክንፍ እንዳለው ከሚናገረው ሐዲስ ጋር እንደሚጋጭ አድርጎ የፈጠራ ሞኝነቱን አቅርቧል።
አየህ እፎይ... ቃሉን ሳትቆርጥ፣ ማጭበርበርህን ትተህ ሙሉውን ዐረብኛ (በቢጫ ያቀለምኩትን) ፊደል በፊደል ብትተረጉመው ኖሮ፤ አላህ ለጅብሪል 600 ክንፍ የመስጠት ሙሉ ችሎታ ("በፍጥረቱ የሚሻውን ይጨምራልና") እንዳለው፣ በገዛ ራስህ መጽሐፍ ላይ ባሰፈርከው የቁርኣን አንቀጽ ውስጥ መልሱን ታገኘው ነበር! ግን እሱን ከጨመርክ ያመጣሀው አርጊውመንት እርባና ቢስ እንደሚሆን ስላወቅክ ቆርጠህ አስቀራሀት።
ውድ አንባቢዎች (በተለይ ክርስቲያን ወገኖቻችን)... ይህ ሰው የራሱን የጥላቻ ትርክት በቅጥፈት ለመሸጥ ሲል ምን ያህል መረጃን እያጣመመና እየቆረጠ እንደሚያደናግራችሁ ከዚህ በላይ ተግባራዊ ማሳያ የለም። እውነታው ይህ ነው! መመዘኑን ለህሊናችሁ ትተነዋል።
«ይቅርታ» ወይስ የውርደት ሽሽት? - ግመሏን ሰርቆ ጅራቷን ስለተሳሳተው ሰውዬ!
አንድ ሰው የሰፈሩን ግመል ከነጭነቷ በጠራራ ፀሐይ ሰርቆ ሲሮጥ እጅ ከፍንጅ ይያዝና ሸንጎ ይቀርባል። ታዲያ ዳኛው ፊት ሲቆም ዓይኑን በጨው አጥቦ፦ «ክቡር ዳኛ! ሰፈሩ ለወር ያህል ሲፈልግ ቆይቶ ትላንት ማታ አንድ ከባድ ስህተት አግኝቶብኛል፤ የሰረቅኳት ግመል ጅራቷ ላይ ያለው ጸጉር ሦስት ሳይሆን ሁለት ነበር፣ ስለዚህ ሕዝቡን በትህትና ይቅርታ እጠይቃለሁ!» ቢል ምን ይባላል?
ዛሬ «እፎይ» በሚል ስም የተለቀቀችው የ«ይቅርታ» ጽሑፍ ልክ ይህንን አስቂኝ ድራማ ትመስላለች። ግለሰቡ «ለወር በዘለቀው እንከን ፍለጋ ትላንት ማታ አንድ ከባድ ስህተት አግኝተውብኛል» ይልና፣ የተገኘበት ብቸኛ ስህተት ነቢዩ (ﷺ) «ሸፍኑኝ» ያሉትን «ሦስት ጊዜ ሳይሆን ሁለት ጊዜ ነው» የሚለው የቁጥር እርማት ብቻ እንደሆነ አስመስሎ ለማቅረብ ሞክሯል።
ይህ በስነ-ልቦናው ዓለም «ትንሿን ጥፋት አምኖ ትልቁን ወንጀል የመሸፈን» የከሰረ የፕሮፓጋንዳ ስልት ይባላል። ለተከታዮቹ፦ «አያችሁ! ኡስታዞቹ ወር ሙሉ መጽሐፌን ፈትሸው ያገኙብኝ ስህተት ሁለትን ሦስት ማለቴን ብቻ ነው» የሚል የሐሰት መፅናኛ ለመስጠት የተሰራች የጭንቀት ድራማ ናት።
ነገር ግን እውነታው ምንድን ነው? በዚያው በጠቀሰው አንድ ገጽ (ገጽ 17) ላይ ብቻ የተጋለጡበትና በ«ይቅርታ» ጽሑፉ ላይ እንደ እሳት የሸሻቸው ግዙፍ የማጭበርበር ተግባራት የሚከተሉት ነበሩ፦
1/ የሐዲስ ምንጭን በጠራራ ፀሐይ ማጭበርበር፦ በገጽ 17 ላይ «Sahih Muslim 160a» ብሎ በደማቁ ከጻፈ በኋላ፣ በሰሒሕ ሙስሊም ውስጥ ጭራሽ የሌለውንና «ተኝቼ ሳለሁ... ከእንቅልፌ ነቃሁ» የሚለውን የኢብኑ ኢስሐቅን ሰንሰለቱ የተቋረጠ ጽሑፍ በሰሒሕ ሙስሊም ስም አጭበርብሮ ለጥፎታል። ታዲያ ይህንን ግዙፍ የምንጭ ሌብነት ትቶ ስለ «ሁለትና ሦስት» ቁጥር ማውራት ማንን ለማታለል ነው?
2/ በዚያችው የ«ይቅርታ» ጽሑፍ ውስጥ እንኳን የደገመው የፈጠራ ውሸት፦ ይህ ግለሰብ ይቅርታ እጠይቃለሁ ባለበት በዚያችው አጭር ጽሑፍ ውስጥ እንኳን «የከዲጃን ቀሚስ ይዞ... ሸፍኚኝ እንዳላት አስፍሬ ነበር» ብሎ በድጋሚ ዋሽቷል! በየትኛው የሐዲስ ወይም የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ነው «የኸዲጃን ቀሚስ ይዞ አስጥይኝ እያለ ጮኸ» ወይም «እብድ ውሻ እንዳየ እያለከለከ መጣ» የሚል ቃል ያለው? በየትኛውም መጽሐፍ ውስጥ የሌለን የመንደር ስድብ ከራስ ኪስ አውጥቶ በሐዲስ ስም መጻፍ «አሳማኝ ስህተት» አይደለም ወይ?
3/ ከካረን አርምስትሮንግ ልብ-ወለድ እስከ ቡኻሪ 5499 የእንግሊዘኛ ትርጉም ስርቆት፦ በገጽ 8 ላይ የሰሒሕ አል-ቡኻሪን (5499) የእንግሊዘኛ ትርጉም ሆን ብሎ ደብቆ የሌለ የውይይት ትርክት መፍጠሩ፣ በገጽ 26 ላይ የካረን አርምስትሮንግን የእንግሊዘኛ ድርሰት ከሰሒሕ ሙስሊም ጋር ደባልቆ «በዳዴ ተንፏቀቀ» ብሎ መቅጠፉ፣ እንዲሁም በራሱ በቀጥታ ስርጭቱ ላይ «ፈትሑል ባሪ (ኢብኑ ሐጀር) ማነው? እኔ ቡኻሪን እየጠቀስኩ ለምን ፈትሑል ባሪ ትጠቅሳላችሁ?» ብሎ የቡኻሪን ማብራሪያ ከቡኻሪ ጋር ሲያጋጭ ማምሸቱ የት ተረሱ?
ውድ ወገኖች! ሰውዬው አጣብቂኝ ውስጥ ሲገባና በየገጹ የፈጸማቸው የምንጭ ማጭበርበሮች እና የትርጉም ሸፍጦች አንድ በአንድ ሲጋለጡበት፣ ትኩረት ለማስቀየር ሲል «ሁለቴ ያለውን ሦስቴ በማለቴ ይቅርታ!» የሚል የጅል ቀልድ ይዞ ብቅ ብሏል።
በጽሑፉ መጨረሻ ላይ፦ «ውድ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ መጽሐፉን እያነበባችሁ እንዲህ አሳማኝ ስህተት ካገኛችሁ አሳውቁኝ» ብሏል። እኛም በአክብሮት የምንለው፦ ወገናችን! በመጽሐፉ ውስጥ ያሉትን ቅጥፈቶችና የማጣቀሻ ስርቆቶች ለማረም ከፈለግክ፣ «ሁለትና ሦስት» የሚሉ ቁጥሮችን በላጲስ ማጥፋት ሳይሆን መጽሐፉን ከነሙሉ ሽፋኑ ሰብስቦ እንደ አዲስ መጻፍ ወይንም ማስጻፍ ነው የሚጠበቅብህ!
እውነት በማስረጃ ትገለጣለች፤ የጭንቀት ሳይኮሎጂ ግን የፈረሰን ሙግት አያድንም!
- የሕያ ኢብኑ ኑህ
Repost from የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
የላይቭ ፕሮግራማችን ተጀምሯል፦
https://vt.tiktok.com/ZS9yJP9UyqENd-x6eyG/
ከ5 ደቂቃ "ፉከራ" ወደ 2 ሰዓት ልፋት... ዛሬ ምሽት በቲክቶክ ላይቭ እንገናኝ!
ዛሬ ምሽት በአላህ ፈቃድ በወንድማችን ኢብራሂም የቲክቶክ ገጽ ላይ በሳምንት አንድ ቀን የምናቀርበው የላይቭ ፕሮግራም ይኖረናል። በፕሮግራማችንም ቀሪዎቹን የፒዲኤፍ ክፍሎች በሰፊው የምናብራራ ሲሆን፣ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
በዚህ አጋጣሚ፤ ላለፉት ሳምንታት የተለያዩ ሰበቦችን እየደረደረ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቦ የነበረው ግለሰብ፣ ትላንትና ብቅ ብሎ ምላሽ ሰጥቻለሁ ማለቱን ሰምተናል። የሰውየው ፉከራ መጀመሪያ "በ5 ደቂቃ አፈራርሰዋለሁ" ነበር፤ ከዚያ 10 ደቂቃ አለው፤ ትላንት በፖስት ደግሞ 20 ደቂቃ ብሎ የነበረ ቢሆንም ማታ ሙሉ 2 ሰዓት ተቀምጦ፣ በጣም ጥቂት ነጥቦችን ብቻ ለቅሞ በመምረጥ አብዛኛውን ጊዜውን እንደተለመደው በስድብ አባክኖታል።
የትላንቱን ግዙፍ ስህተቶቹን ጨምሮ በርካታ ዝንፈቶችን ዛሬ ምሽት ስናቀርብላችሁ እጅግ ትገረማላችሁ! በዛሬው የላይቭ ፕሮግራማችን፤ በዚህ ሳምንት የለቀቅነውን ሙሉ የፒዲኤፍ ምላሽ አስመልክቶ ሰፊ ትንታኔ የምንሰጥበት ይሆናል። እግረ መንገድ "ምላሽ" በሚል የተናገራቸውን ሀሳቦች እግረ መንገድ የምንቃኛቸው ይሆናል።
ጠብቁን ..
#TikTokLive #የጽልመቱ_ጥላ #ውይይት #ንጽጽር
ሀሳብና አስተያየታችሁን በነጻነት አካፍሉን!
ከሰሞኑ "የጽልመቱ ጥላ" ለተሰኘው መጽሐፍ እየሰጠነው ባለው ተከታታይ ምላሽ ዙሪያ፣ በርካታ ሰዎች ሀሳብና አስተያየታቸውን ማካፈል እንደሚፈልጉ ከኮሜንት ጹሁፎችና በግል ከሚደርሱን አንዳንድ መልዕክቶች መረዳት ችለናል።
በመሆኑም፤ በመጽሐፉም ሆነ በሰጠናቸው ምላሾች ዙሪያ የተሰማችሁን ማንኛውንም ሀሳብ፣ ትችትም ይሁን ግንዛቤ በነጻነት መስጠት እንድትችሉ፣ ክፍት የሆነ የቴሌግራም አስተያየት መቀበያ አዘጋጅተናል።
ሙስሊም ወንድሞች እና እህቶቻችን፣ እንዲሁም ሙስሊም ያልሆናችሁ ወገኖቻችን ያለምንም ገደብ በነጻነት ሀሳባችሁን በዚህ ቦት በኩል ልታጋሩን ትችላላችሁ።
የሁሉንም ሰው አስተያየት መፖሰት ባንችልም፤ ትልቅ ቁምነገር ያዘሉና ሌሎች ሰዎችን ያስተምራሉ ብለን የምናምናቸውን ሚዛናዊ አስተያየቶች በቻናሎቻችን ላይ ሼር በማድረግ፣ ማኅበረሰቡ እንዲማርባቸውና እንዲወያይባቸው የምናመቻች ይሆናል።
ከታች በተቀመጠው የቴሌግራም ሊንክ በመጠቀም አስተያየቶቻችሁን አሁኑኑ አድርሱን፦
➭ https://t.me/Yahyaabuyusrabot
#የጽልመቱ_ጥላ #ውይይት #ሀሳብ_ለማካፈል #እስልምናና_ክርስትና
የምዕራፍ 1 ቀሪ ክፍል እና ሙሉ የምዕራፍ 2 ምላሽ ተለቋል!
"የምናመልከው አምላክ ማነው?" በሚል ርዕስ ከምዕራፍ 1 የተረፈውን ሰፊ ክፍል፣ ዝርዝር በሆነና ራሱን በቻለ መልኩ በማያዳግም ሁኔታ ምላሽ ሰጥተንበታል።
ከዚህ በመቀጠል ደግሞ ስለ 'ወሕይ' ወይንም ራዕይ እና ተያያዥ ጉዳዮች በሰፊው የሚዳስሰውን ሙሉ የምዕራፍ 2 ክፍል፣ አንድም ነጥብ ሳናስቀር እያንዳንዱን ሐሳብ እየነቀስን አጥጋቢ ምላሽ ሰጥተንበታል።
እንደተለመደው አንባቢዎች የእኛን ምላሽ እና የጸሐፊውን ሐሳብ በቀጥታ ማመሳከር እንዲችሉ፣ ምላሽ የሰጠንባቸውን የመጽሐፉን ገጾች ስካን በማድረግ ከፒዲኤፉ ጀርባ አያይዘናል።
ምላሹ በሚገባ የተብራራና ማስረጃዎችን ያካተተ በመሆኑ ሁላችሁም ታነቡት ዘንድ በአክብሮት ጋብዘናል። በፒዲኤፉ ይዘት ዙሪያ ያልተመቻችሁ ወይም መከራከሪያ ማቅረብ የምትፈልጉ ጸሀፊውን ጨምሮ ማንኛችሁም ወገኖች፣ ሐሳባችሁን በነፃነት እንድትገልጹና ምላሽ እንድትሰጡን መድረኩ ክፍት ነው።
ሙስሊም ወንድም እና እህቶቻችን ደግሞ ይህንን የተብራራ እውነታ ለክርስቲያን ወገኖቻችን ሼር በማድረግ እንድታደርሱ ሙሉ ፈቃድ አላችሁ። የመልካም ስራው ተጋሪ ትሆኑ ዘንድም ጥሪያችን ነው።
ቀጣይ ክፍሎችንም ልክ እንደዚሁ በተደራጀ መልኩ በአላህ ፍቃድ ምላሽ መስጠታችንን የምንቀጥል ይሆናል!
ሙሉ ፒዲኤፎችን ለማግኘት ከታች ያለውን የቴሌግራም ሊንክ ይጫኑ፦
https://t.me/Yahyanuhe
https://t.me/Abuyusra3
#የጽልመቱ_ጥላ #አላህ_ማነው #ወሕይ #እስልምናና_ክርስትና #ውይይት
የምዕራፍ 1 ቀሪ ክፍል እና ሙሉ የምዕራፍ 2 ምላሽ ተለቋል!
"የምናመልከው አምላክ ማነው?" በሚል ርዕስ ከምዕራፍ 1 የተረፈውን ሰፊ ክፍል፣ ዝርዝር በሆነና ራሱን በቻለ መልኩ በማያዳግም ሁኔታ ምላሽ ሰጥተንበታል።
ከዚህ በመቀጠል ደግሞ ስለ 'ወሕይ' ወይንም ራዕይ እና ተያያዥ ጉዳዮች በሰፊው የሚዳስሰውን ሙሉ የምዕራፍ 2 ክፍል፣ አንድም ነጥብ ሳናስቀር እያንዳንዱን ሐሳብ እየነቀስን አጥጋቢ ምላሽ ሰጥተንበታል።
እንደተለመደው አንባቢዎች የእኛን ምላሽ እና የጸሐፊውን ሐሳብ በቀጥታ ማመሳከር እንዲችሉ፣ ምላሽ የሰጠንባቸውን የመጽሐፉን ገጾች ስካን በማድረግ ከፒዲኤፉ ጀርባ አያይዘናል።
ምላሹ በሚገባ የተብራራና ማስረጃዎችን ያካተተ በመሆኑ ሁላችሁም ታነቡት ዘንድ በአክብሮት ጋብዘናል። በፒዲኤፉ ይዘት ዙሪያ ያልተመቻችሁ ወይም መከራከሪያ ማቅረብ የምትፈልጉ ጸሀፊውን ጨምሮ ማንኛችሁም ወገኖች፣ ሐሳባችሁን በነፃነት እንድትገልጹና ምላሽ እንድትሰጡን መድረኩ ክፍት ነው።
ሙስሊም ወንድም እና እህቶቻችን ደግሞ ይህንን የተብራራ እውነታ ለክርስቲያን ወገኖቻችን ሼር በማድረግ እንድታደርሱ ሙሉ ፈቃድ አላችሁ። የመልካም ስራው ተጋሪ ትሆኑ ዘንድም ጥሪያችን ነው።
ቀጣይ ክፍሎችንም ልክ እንደዚሁ በተደራጀ መልኩ በአላህ ፍቃድ ምላሽ መስጠታችንን የምንቀጥል ይሆናል!
ሙሉ ፒዲኤፎችን ለማግኘት ከታች ያለውን የቴሌግራም ሊንክ ይጫኑ፦
https://t.me/Yahyanuhe
https://t.me/Abuyusra3
#የጽልመቱ_ጥላ #አላህ_ማነው #ወሕይ #እስልምናና_ክርስትና #ውይይት
የምዕራፍ 1 ቀሪ ክፍል እና ሙሉ የምዕራፍ 2 ምላሽ ተለቋል!
"የምናመልከው አምላክ ማነው?" በሚል ርዕስ ከምዕራፍ 1 የተረፈውን ሰፊ ክፍል፣ ዝርዝር በሆነና ራሱን በቻለ መልኩ በማያዳግም ሁኔታ ምላሽ ሰጥተንበታል።
ከዚህ በመቀጠል ደግሞ ስለ 'ወሕይ' ወይንም ራዕይ እና ተያያዥ ጉዳዮች በሰፊው የሚዳስሰውን ሙሉ የምዕራፍ 2 ክፍል፣ አንድም ነጥብ ሳናስቀር እያንዳንዱን ሐሳብ እየነቀስን አጥጋቢ ምላሽ ሰጥተንበታል።
እንደተለመደው አንባቢዎች የእኛን ምላሽ እና የጸሐፊውን ሐሳብ በቀጥታ ማመሳከር እንዲችሉ፣ ምላሽ የሰጠንባቸውን የመጽሐፉን ገጾች ስካን በማድረግ ከፒዲኤፉ ጀርባ አያይዘናል።
ምላሹ በሚገባ የተብራራና ማስረጃዎችን ያካተተ በመሆኑ ሁላችሁም ታነቡት ዘንድ በአክብሮት ጋብዘናል። በፒዲኤፉ ይዘት ዙሪያ ያልተመቻችሁ ወይም መከራከሪያ ማቅረብ የምትፈልጉ ጸሀፊውን ጨምሮ ማንኛችሁም ወገኖች፣ ሐሳባችሁን በነፃነት እንድትገልጹና ምላሽ እንድትሰጡን መድረኩ ክፍት ነው።
ሙስሊም ወንድም እና እህቶቻችን ደግሞ ይህንን የተብራራ እውነታ ለክርስቲያን ወገኖቻችን ሼር በማድረግ እንድታደርሱ ሙሉ ፈቃድ አላችሁ። የመልካም ስራው ተጋሪ ትሆኑ ዘንድም ጥሪያችን ነው።
ቀጣይ ክፍሎችንም ልክ እንደዚሁ በተደራጀ መልኩ በአላህ ፍቃድ ምላሽ መስጠታችንን የምንቀጥል ይሆናል!
ሙሉ ፒዲኤፎችን ለማግኘት ከታች ያለውን የቴሌግራም ሊንክ ይጫኑ፦
https://t.me/Yahyanuhe
https://t.me/Abuyusra3
#የጽልመቱ_ጥላ #አላህ_ማነው #ወሕይ #እስልምናና_ክርስትና #ውይይት
🎉ልዩ የበጋ ስልጠና በኢሙዳት(የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ዳዕዋና ትምህርት ማህበር)🎉
ኢሙዳት በየአመቱ በጋ ወቅት አጠቃላይ የንፅፅር እውቀት ብልፅግና ላይ የሚያተኩሩ ስልጠናዎችን ያለ ምንም ክፍያ በታዋቂ ኡስታዞች እና አሰልጣኞች በመስጠት ተማሪዎችን እንደሚያስመርቅ ይታወቃል። በመሆኑም በዘንድሮ በጋ ልዩ የሆነ ስልጠና በዋነኝነት በአዲስ አባባ እና ዙርያዋ ለሚገኙ 2ኛ ደረጃ ት/ት ተማሪዎችና ለዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ በተጨማሪም በማንኛውም ዘርፍ ላይ ያሉ በሃይማኖት ንጽጽር ዘርፍ ለኢስላም መስራት የሚፈልጉ ወጣቶችን ለይቶ ስልጠናዎችን ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል።
ስልጠናው የሚያጠነጥነው የንፅፅር እውቀት፣ ኢማንን ማጎልበት፣ የሊደርሽፕ ፣ አርት እና ኢስላማዊ ስልጣኔ፣ የማህበረሰባዊ አይዲዮሎጂዎች እና መሰል የወጣቶችን ንቃተ ሕሊናን የሚያጎለብቱ ጉዳዮች ላይ ሲሆን ስልጠናውም ቅዳሜ እና እሁድ ለግማሽ ቀን ከህዳር እስከ ሰኔ መጨረሻ የሚቆይ ይሆናል
በመሆኑም ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የምታሟሉ ትምህርቱን በቋሚነት መከታተል የምትችሉ ወጣቶች (ወንድ እና ሴት) ይህንን ቅፅ በመሙላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
🏢ኢሙዳት(የኢትዮጵያ ሙስሊም ዳእዋና ትምህርት ማህበር)
🕹ቶታል 3ቁጥር ማዞሪያ ወደ ብስራተ ገብርኤል በሚወስደው መንገድ ገባ ብሎ
⏰ 02:30-06:00LT
ለበለጠ መረጃ ☎️ 0904199399
0960281050
0963262856 ይደውሉ።
✨ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ።
🛑ምዝገባ ህዳር 1 የሚጠናቀቅ ይሆናል።
🙌ማሰራጨት አይርሱ🙌
የመመዝገቢያ Link👇
https://forms.gle/a2ETk8Fm3GG4MCRi6
Repost from የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
አልሐምዱሊላህ! አሁን ደግሞ ወደ ቲክቶክ እናመራለን...
ባለፉት ጥቂት ቀናት በ"እፎይ" ስም ለወጣው መጽሐፍ የሰጠነው የምዕራፍ 1 ምላሽ፣ በፌስቡክ ገጻችን ላይ ሰፊ መነቃቃትና ውይይት መፍጠር ችሏል። አልሐምዱሊላህ! ባለፉት አራት እና አምስት ቀናት ውስጥ ብቻ የለቀቅናቸውን መረጃዎች ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰው የተመለከተው ሲሆን፣ በርካቶችም ሀሳባቸውን በማካፈል በንቃት ተሳትፈውበታል።
በፌስቡክ የጀመርነው ይህ የማብራራትና እውነታውን የማሳየት ስራ፣ አሁን የያዘውን መስመር ጠብቆ በአላህ ፈቃድ የሚቀጥል ይሆናል። በተጓዳኝ ደግሞ፣ ይህንን ዕድል አድማሱን በማስፋት ወደ ቲክቶክ ይዘነው ልንዘልቅ ነው።
በቲክቶክ መንደር ያሉ፣ በተለይም እስካሁን ምላሹን ያልሰሙ፣ እንዲሁም በመጽሐፉ ምክንያት የተሳሳተ ግንዛቤ የተፈጠረባቸው ክርስቲያን ወገኖቻችን የጉዳዩን እውነታ እንዲመዝኑት በሰፊው እንሰራለን። መጽሐፉን ገጽ በገጽ እየገለጥን፣ በላይቭ ፕሮግራም ትክክለኛውን መረጃ፣ ትንታኔና ማብራሪያ በወንድማችን ኢብራሒም ቤት ቅዳሜ ምሽት 3:00 በአላህ ፍቃድ ይዘንላችሁ እንቀርባለን።
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል...
Let's go to TikTok!
#እውነት_ይገለጣል #የጽልመቱ_ጥላ #ንጽጽር #TikTokLive
Repost from የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
እፎይ ሸሸ ወይንስ አፈገፈገ? ገና በማለዳው ሜዳውን ለቀቀሳ!
"የጽልመቱ ጥላ" በሚል ስያሜ በስሙ ለወጣው መጽሐፍ ምላሽ እንደምናዘጋጅ ካሳወቅንበት ቀን ጀምሮ፣ እንቅስቃሴያችንን እየተከታተለ ስማችንን እያነሳ "ምላሽ እሰጣለሁ" ሲል በሙሉ በራስ መተማመን ለተከታታዮቹ ሲፎክር ከርሞ ነበር።
እንዲያውም ፉከራው ጣሪያ ነክቶ፤ "እነሱ መልስ ሰጥተው እኔ ያንን ማፍረስ (ሪፊውት ማድረግ) ከከበደኝ፣ ንጽጽር አቆማለሁ!" እስከማለት ደርሶ በቪዲዮ ሲገዝት ነበር። እኛም ይህን ያህል በራሱ ከተማመነማ፣ ቢያንስ እስከ ግማሽ መጽሐፉ ድረስ ሞገዱን ተቋቁሞ ይዘልቃል ብለን ጠብቀን ነበር።
ነገር ግን፣ ልክ የምዕራፍ 1 ምላሻችን (ፒዲኤፍ) እንደተለቀቀ፣ በሚገርም ሁኔታ ጸጥታ ሰፈነ፤ የበላው ጅብም አልጮህ አለ! ትላንት ደግሞ ተከታዮቹ ግራ ገብቷቸው "ለምን አትመልስላቸውም?" ብለው ሲጠይቁት፣ "ለእነሱ መልስ አልሰጥም!" በማለት የፈሪ ዱላውን ጥሎ ቁርጣቸውን ነግሯቸዋል።
ምነው እፎይ? ገና እኮ መግቢያውን አልፈን ምዕራፍ 1 ላይ ብቻ ነን! ምነው ገና በማለዳው ሩጫውን አቆምከው? "ማፍረስ ከከበደኝ ንጽጽር አቆማለሁ" ያልከው ቃል ኪዳን ገና ዶሮ ሳይጮህ በአንደኛው ምዕራፍ ላይ ጸና ማለት ነው? ቢያንስ የራስህን ፉከራ አክብረህ አቋርጦ ለመውጣት እንኳ ትንሽ አትታገስም ነበር?
ፒዲኤፉን ገልጠህ ስታየው ያሰብከው ዓይነት "ቀላል እራት" ሆኖ ስላላገኘኸው ይሆን እንዲህ በማለዳ ጓዝህን የጠቀለልከው?
ቪዲዮውን ተመልከቱት
- ለማንኛውም የምዕራፍ - 2 ምላሻችን ይቀጥላል ....
ገብርኤልን አምላክ ያደረገው እፎይ!
በቅርቡ "የጽልመቱ ጥላ" በሚል ርዕስ እስልምናን ለመተቸት መጽሐፍ ያሳተመው እፎይ፣ በእስልምና ላይ ክስ ለመደርደር ሲጣደፍ የራሱን የክርስትና እምነት መሠረት ጭምር እስከማፍረስ ደርሷል።
እስኪ ከተያያዘው ምስል ላይ የመጽሐፉን ገጽ 30 ተመልከቱት! ጸሐፊው በድፍረት "ገብርኤል ማለት ትርጉሙ አምላክ ሰው ሆነ... ማለት ስለሆነ" ይለናል!
እስካሁን ሥላሴን በመቃወም ስንደክም ኑረን አሁን ደግሞ ሌላ አራተኛ "አምላክ" ጨምሮ ስራችንን ሊያበዛው ነው።
ከሰሞኑ ሰፊ ማስታወቂያ ሲሰራለት የነበረውና ይዘቱ ግን ከማስታወቂያው ጩኸት ጋር ፈጽሞ የማይመጣጠነው "እፎይ" በተባለ ግለሰብ ስም ለወጣው መጽሐፍ፣ የመጀመሪያ ክፍል ምላሻችንን እነሆ በፒዲኤፍ ተለቋል። ምላሽ የተሰጠባቸው የመጽሀፉ ክፍሎች ስካን ተደርገው ለማመሳከርያነት አብረው ተካተዋል።
በዚህ የመጀመሪያ ክፍል ምላሻችን፤ መጽሐፉ በምዕራፍ አንድ ላይ ካነሳቸው ጉዳዮች ውስጥ ከአንድ ርዕስ በስተቀር፣ እያንዳንዱን ነጥብ አንድም ሐሳብ ሳናስቀር በማስረጃ በጥልቀት አብራርተንበታል። ያንን የተውነውን አንዱን ርዕስ በተመለከተ፣ በቀጣይ በአላህ ፈቃድ ራሱን በቻለ መልኩ የምንመለስበት ይሆናል።
ይህ መጽሐፍ ባለው የተጋነነ ማስታወቂያ ምክንያት በበርካታ ክርስቲያን ወገኖቻችን ዘንድ ስለ እስልምና የተሳሳተ ምስል የፈጠረ በመሆኑ፣ እውነታውንና ትክክለኛውን ምላሽ ያውቁ ዘንድ ይህንን ፖስት ሼር በማድረግ ለሁሉም እንድታደርሱልን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።
ፒዲኤፉን ለማግኘት ከታች ያለውን የቴሌግራም ሊንክ ይጫኑ፦
https://t.me/Yahyanuhe
https://t.me/Abuyusra3
