አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ
前往频道在 Telegram
4 069
订阅者
+124 小时
-147 天
-430 天
帖子存档
በመድኃኒት እና በህክምና መገልገያ መሣሪያዎች አስመጪነት ስራ ላይ ኖዎት? ወይስ አዲስ ማስመጣት አስበዋል? ለስራዎ ስኬት የሚያግዝ አስተማማኝ የማማከር አገልግሎት ከፈለጉ በዚህ አድራሻ ያነጋግሩን።
በተጨማሪም Single Window ላይ የሚሰሩ ስራዎችን በታማኝነት እንሰራለን።
በመድኃኒት እና በህክምና መገልገያ መሣሪያዎች አስመጪነት ስራ ላይ ኖዎት? ወይስ አዲስ ማስመጣት አስበዋል? ለስራዎ ስኬት የሚያግዝ አስተማማኝ የማማከር አገልግሎት ከፈለጉ በዚህ አድራሻ ያነጋግሩን።
በተጨማሪም Single Window ላይ የሚሰሩ ስራዎችን በታማኝነት እንሰራለን።
በመድኃኒት እና በህክምና መገልገያ መሣሪያዎች አስመጪነት ስራ ላይ ኖዎት? ወይስ አዲስ ማስመጣት አስበዋል? ለስራዎ ስኬት የሚያግዝ አስተማማኝ የማማከር አገልግሎት ከፈለጉ በዚህ አድራሻ ያነጋግሩን።
በተጨማሪም Single Window ላይ የሚሰሩ ስራዎችን በታማኝነት እንሰራለን።
Repost from ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል/Hidaya Islamic Center/
የስልጠናው ኦዲዮው አጭር ማብራሪያ፦
ይህ የመጀመሪያው የድምጽ ክፍል ስለ 'ሱና' ምንነት እና የሐዲስ አጠባበቅ ታሪክ ጥልቅ ግንዛቤን የሚያስጨብጥ ነው። ፋይሉን በጉጉት እንድታዳምጡት የሚጋብዙ ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦
• ሱና በቋንቋ እና በሸሪዓዊ አገባቡ (ከነብዩ ንግግር፣ ተግባር እና ማጽደቅ አኳያ) ምን ማለት እንደሆነ በዝርዝር ያብራራል።
• የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲሶች ከመጀመሪያው ጀምሮ እንዴት በአራት ዋና ዋና መንገዶች (በማስታወስ/በመሸምደድ፣ በመጻፍ፣ እርስ በርስ በመማማር እና በተግባር በመተርጎም) ተጠብቀው እንደቆዩ ይተነትናል።
• ገና በሶሓባዎች ዘመን (እንደ አብደላህ ኢብኑ አምር፣ አሊ ኢብኑ አቢ ጧሊብ፣ አቡ ሁረይራ እና አነስ ኢብኑ ማሊክ) የራሳቸው 'ሰሒፋ' (የጽሁፍ ስብስቦች) እንደነበሯቸው ታሪካዊ ማስረጃዎችን ያቀርባል።
• ከሰሒፋዎች በመቀጠል የሐዲስ ስብስቦች እንዴት ወደ 'ሙሰነፍ' (በርዕስ የተከፋፈሉ)፣ 'ሙስነድ' (በሶሓባዎች ስም የተከፋፈሉ) እና 'ሱነን' (በፊቅህ ህግጋት የተከፋፈሉ) መጻሕፍት እንዳደጉ በሰፊው ይዳስሳል።
• የሐዲስን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ በዑለማዎች ስለተዘረጉት ጥብቅ ሳይንሶች (እንደ ዒልሙ ሪጃል፣ ዒልሙል ዒለል የመሳሰሉት) ያስገነዝባል።
© ዳሩል ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል
Repost from ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል/Hidaya Islamic Center/
አዲስ እና ልዩ አጭር ኮርስ ከሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል | #1ኛ ዙር ስልጠና
“ቁርአን ብቻ ይበቃናል” የሚሉ አካላት መነሻቸው ምንድን ነው? የሱና (ሀዲስ) አስፈላጊነትና በኢስላም ውስጥ ያለው ድርሻስ ምን ያህል ነው?
እነዚህን እና ሌሎች ተያያዥ አንገብጋቢ ጥያቄዎችን በሰፊው የሚዳስሰውን 1ኛ ዙር የንፅፅር ትምህርት ኮርስ በማዕከላችን የቴሌግራም ቻናል ይዘንላችሁ ቀርበናል።
• አዘጋጅ፦ ኢልያህ ማሕሙድ
• የሚሰጥበት ቦታ፦ በሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል የቴሌግራም ቻናል
ይህንን ወሳኝ ኮርስ ሙሉ በሙሉ ተከታትለው በመጨረሻም የሚዘጋጀውን ፈተና ለሚወስዱ እና ለሚያልፉ ተሳታፊዎች በሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በኩል የምስክር ወረቀት ይሰጣል።
እውቀትን ከትክክለኛው ምንጭ እንቅሰም! ትምህርቱን ለመጀመር የቴሌግራም ቻናላችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፦
https://t.me/Hidayaic8212
የዚህ ግለሰብ ጓደኛ የሆናቹ
ሰላምታ ከሰጣቹ በሩቅ ይሁን!
ውሃም ሰለማይወድ ቢያንስ በቀኙ እጁ ምን ነካክቶ እንደወጣ አይታወቅም ።
መብቱን አክብሩለት
ህንድ ሀገር የሚኖር አስቸኳይ የተፈለገ መድሀኒት በመግዛት ሊተባበረኝና ሊልክልኝ የሚችል ሰው ካለ በዚህ ያናግረኝ Abu Yusra
Repost from የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
ሀምዛ ዞርትዚስ ከታዋቂው የሞሪታንያ ዓሊም ሸይኽ ዶ/ር ሙስጠፋ አል-ሸይባኒ ጋር ያደረጉትን እጅግ ጠቃሚ ውይይት ተመልክቼ ነበር። በተለይ በዚህ ዲጂታል ዘመን ዳዕዋ ስናደርግ ስለሚገጥሙን እንደ ኢጎ (እኔነት) እና የታዋቂነት ፈተናዎች እንዴት ማለፍ እንደምንችል ያነሱት ሀሳብ ልብ ይነካል። ቪዲዮውን እያየሁ የተወሰነ ማስታወሻ ለመያዝ የሞከርኩ ቢሆንም በመሀል የራሱ AI ሰመራይዝ ያደረገውን ስመለከት ግን ሀሳቤን በጥቅሉ ስለገለጸው እሱን በቡሌት ተርጉሞ ማስቀመጡን መርጫለሁ።
የውይይታቸው ዋና ዋና ነጥቦች እነሆ፡-
• ወደ አደባባይ እና ዲናዊ ስራ ከመውጣታችን በፊት በሌሊት ሶላት (ቂያሙል ለይል) እና በኢኽላስ (ቅንነት) ራሳችንን ማነፅ እና ከአላህ ጋር ያለንን ሚስጥራዊ ግንኙነት ማጠናከር አለብን።
• ቁርኣንን ለበረካ ብቻ ሳይሆን አስተሳሰባችንን ለመቅረፅ እና ራሳችንን ለመለወጥ ልንጠቀምበት ይገባል።
• ለዳዒ ትልቁ ጠላት ታዋቂነት ነው። ከተከታዮቻችን (followers) ቁጥር ይልቅ በዋናው አላማችን ላይ ብቻ ማተኮር አለብን፤ ስኬት ሁሌም ቢሆን የአላህ ስጦታ ነውና።
• ሱረቱ ዩሱፍ እንደሚያስተምረን ውጤታማ ዳዕዋ የረጅም ጊዜ እቅድን፣ ሰዎችን መረዳትን እና ትችትና ውድቀቶችን በትዕግስት ለማለፍ "ትልቅ ልብ" ሊኖረን ይገባል።
• ስኬት ከቤት ይጀምራል፦ የትዳር አጋራችን እና ቤተሰባችን ከውጭ ለሚገጥመንን ጫና መቋቋሚያ ትልቁ "መልህቃችን" ናቸው። ስለዚህ ጠንካራ እና አፍቃሪ የቤተሰብ ግንኙነት መገንባት ለስኬታችን ወሳኝ ነው።
በመጨረሻም ሀምዛ በራሱ ህይወት ተሞክሮ እንዳጠቃለለው፤ ምንም ያህል የተማርን እና የአካዳሚክ እውቀት ቢኖረንም፣ በዳዕዋ ስራችን ላይ ቁርኣን ሁሌም ቀዳሚ፣ ሀይለኛ እና ውጤታማው መመሪያችን ነው።
ሙሉ ውይይቱን በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ።
🎉ልዩ የክረምት ስልጠና በኢሙዳት(የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ዳዕዋና ትምህርት ማህበር)🎉
ኢሙዳት በየአመቱ ክረምት ወቅት አጠቃላይ የንፅፅር እውቀት ብልፅግና ላይ የሚያተኩሩ ስልጠናዎችን ያለ ምንም ክፍያ በታዋቂ ኡስታዞች እና አሰልጣኞች በመስጠት ተማሪዎችን እንደሚያስመርቅ ይታወቃል። በመሆኑም በዘንድሮ ክረምት ልዩ የሆነ ስልጠና በዋነኝነት ክረምታቸውን በአዲስ አባባ ለሚያሳልፉ 2ኛ ደረጃ ት/ት ተማሪዎችና ለዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ በተጨማሪም በማንኛውም ዘርፍ ላይ ያሉ በሃይማኖት ንጽጽር ዘርፍ ለኢስላም መስራት የሚፈልጉ ወጣቶችን ለይቶ ስልጠናዎችን ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል።
ስልጠናው የሚያጠነጥነው የንፅፅር እውቀት፣ ኢማንን ማጎልበት፣ የሊደርሽፕ ፣ አርት እና ኢስላማዊ ስልጣኔ፣ የማህበረሰባዊ አይዲዮሎጂዎች እና መሰል የወጣቶችን ንቃተ ሕሊናን የሚያጎለብቱ ጉዳዮች ላይ ሲሆን ስልጠናውም በሳምንት ለ6 ቀናት የግማሽ ቀን ከሀምሌ 01 እስከ ጷጉሜ 05, 2018 ድረስ የሚቆይ ይሆናል።
በመሆኑም ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የምታሟሉ ትምህርቱን በቋሚነት መከታተል የምትችሉ ወጣቶች (ወንድ እና ሴት) ይህንን ቅፅ በመሙላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
🏢ኢሙዳት(የኢትዮጵያ ሙስሊም ዳእዋና ትምህርት ማህበር)
🕹ቶታል 3ቁጥር ማዞሪያ ወደ ብስራተ ገብርኤል በሚወስደው መንገድ ገባ ብሎ
⏰ 02:30-06:00LT
ለበለጠ መረጃ ☎️ 0904199399
0913242072
0963262856 ይደውሉ።
✨ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ።
🛑ምዝገባ ሰኔ 23 የሚጠናቀቅ ዪሆናል።
🙌ማሰራጨት አይርሱ🙌
የመመዝገቢያ Link👇
https://forms.gle/Gbp1e2kPX74spbLm9
የድርጅትዎን ገጽታ በዲዳት ያድምቁ! ✨
ጥራት ያለው የህትመት እና የማስታወቂያ ስራ ፈልገዋል? ዲዳት ህትመትና ማስታወቂያ የደንበኞቹን አደራ (አማና) በታማኝነት በመጠበቅ ፈጣንና ፕሮፌሽናል አገልግሎት ይሰጣል! ጊዜዎንና ገንዘብዎን በአስተማማኝ ቦታ ላይ በማዋል የንግድዎን ስኬት ያፋጥኑ።
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች፦
• ባነር
• ስቲከር
• ላይት ቦክስ
• የቲሸርት ህትመት
• የደረሰኝ እና የማስታወሻ ደብተር ህትመት
• ማግ (ኩባያ) ህትመት
• የቢዝነስ፣ የመታወቂያ እና የጥሪ ካርዶች ህትመት
ጥራትን ከታማኝነት ጋር አዋህደን እንጠብቅዎታለን!
📍 አድራሻችን፦
ቤቴል፣ አዲሱ ህንፃ፣ 3ኛ ፎቅ
📞 ስልክ፦ 0946-4599-45
Repost from Lingora Language Institute
🔴 🔽ክህሎቶን ያሳድጉ — ሕይወቶን ይለውጡ❗️
በሥራ ዓለምም ሆነ በግል ሕይወት ስኬታማ ለመሆን የቋንቋ እና የኮምፒውተር እውቀት ወሳኝ ናቸው።
ሊንጎራ የቋንቋ እና የኮምፒውተር ማሰልጠኛ ተቋም 💘 ምርጥ አማራጮችን ይዞልዎ ቀርቧል ❗️
✈️🌟 1️⃣. የእንግሊዘኛ ቋንቋ ስልጠና ፦
በራስ መተማመንን ለመጨመር፣ የሥራ ዕድሎችን ለማስፋት እና ማራኪ የንግግር ብቃት ለማዳበር።
🤟👍 🔢. የአረብኛ ቋንቋ ስልጠና ፦
ሰፊ የንግድ ግንኙነቶችን ለመፍጠር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊ ለመሆን።
👨💻👨💻 3⃣. የኮምፒውተር ክህሎት ስልጠና ፦
አሁን ባለንበት ዘመን የኮምፒውተር እውቀት ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው።
የትኛውም የ ኮምፒተር ክህሎት የሚጠይቁ ስራዎችን በብቃት ለመሥራት እና በዲጂታሉ ዓለም ተወዳዳሪ ለመሆን።
✔️ አሁኑኑ ይወስኑ! ቦታዎች ሳይሞሉ ዛሬውኑ ይመዝገቡ። ምርጥ ኢንቨስትመንት በራስ ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት ነው!
📞 ለበለጠ መረጃ እና ምዝገባ
✉️የቴሌግራም አድራሻዎቻችንን በመጫን ያነጋግሩን፦
👉 @LingoraH
👉 @ling_ora
ሊንጎራ የቋንቋ እና የኮምፒውተር ማሰልጠኛ ተቋም
ሰው እንዴት ከዚህ ውስጥ "አንገት አንገታቸውን በሉ " የሚለውን ነጥሎ አውጥቶ የማይገናኘውን ያገናኛል?
እና አበባ ያንጥፉልህ? ወይስ እንደአንተ "ቀኝህን ሲመታህ ግራህን ስጥ" እያለ የፉገራ ጥቅስ ይጥቀስልህ?
ከ ዱባይ እንዲመጣላቹ የምትፈልጉት እቃ እንዲሁም ከኢትዮ ወደ ዱባይ እንዲሄድላቹ የምትፈልጉት ነገር ካለ ከሰር ባለው አካውንት ያናግሩዋቸው።
https://t.me/umishitiandhijab
ለሰለምቴዎች መሰረታዊ የዲን ትምህርት ስልጠና
⚡️ይህ ለሁለት ወራት በአካል የሚሰጥ ነፃ ስልጠና ወደ እስልምና በቅርቡ ለተቀላቀሉ ወንድምና እህቶች የተዘጋጀ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ጦር ኅይሎች አካባቢ ብቁ በሆኑ አሰልጣኞች ጥራቱን በጠበቀ አሰጣጥ የሚከናወን ይሆናል።
ስልጠናውም እነኝህን የዲን ትምህርቶች ያካተተ ነው።
1. ቁርአን አቀራር እና ትርጉም
2. ፊቅህ ( ኢስላማዊ ህግጋት)
3. የኅይማኖቱ መሰረቶች
4. ሲራ (የነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) የህይወት ታሪክ )
5. ሹቡሃት (እስልምና ዙርያ የሚነሱ ጥያቄዎች)
6. ህይወትን በእስልምናና ሌሎችንም ከቅርብ ክትትል (mentorship) ጋር ...
ለመመዝገብ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ
https://forms.gle/ugsXL6MM2QR1T1k99የ"ኢስላሚክ ዳይለማ" ቅዠት እና የቁርኣን ምላሽ!
ክርስቲያን አፖሎጂስቶች "ቁርኣን መጽሐፍ ቅዱስን ያረጋግጣል፤ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ልክ ከሆነ ቁርኣን ስህተት ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዟል ካላችሁ ደግሞ ቁርኣን የተበረዘን መጽሐፍ አረጋግጧል" የሚል፣ የቃላትን ፍቺና የቁርኣንን ይዘት ያልተረዳ የ"ኢስላሚክ ዳይለማ" (Islamic Dilemma) ሙግት ያቀርባሉ።
ነገር ግን ቁርኣን የመጽሐፉ ባለቤቶች (አይሁድና ክርስቲያኖች) በእጃቸው የያዙት መጽሐፍ የተበረዘ፣ እውነት ከሐሰት የተደባለቀበት እና ቁርኣን ከመጣ በኋላ መተው ያለበት መሆኑን በግልጽ ያሳያል። ቁርኣን የመጽሐፉን ሰዎች እንዴት እንደሚሞግታቸው እንመልከት፦
1. የሙግትና የወቀሳ ጥያቄዎች (እውነትን ስለመቀላቀል)
ቁርኣን በእጃቸው ያለው መጽሐፍ ንፁህ ነው አይላቸውም፤ ይልቁንም እንዲህ በማለት ይሞግታቸዋል፦
3:71፦ "የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! እውነትን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ? እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ?"
3:70፦ "የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በአላህ አንቀጾች ለምን ትክዳላችሁ?"
3:65፦ "የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በኢብራሂም ለምን ትከራከራላችሁ?.."
2. ወደ አዲሱ ብርሃን የቀረበ ጥሪ
መጽሐፋቸው መሪ ቢሆን ኖሮ አላህ ወደ አዲስ መልክተኛ እንዲመጡ አይጠራቸውም ነበር፦
5:15፦ "የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ከመጽሐፉ ትደብቁት የነበራችሁትን ብዙ ነገር ለእናንተ የሚገልጽላችሁ መልክተኛችን በእርግጥ መጣላችሁ..."
3:64፦ "የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል እኩል ወደ ኾነች ቃል ኑ..." (ወደ ተውሂድ የቀረበ ጥሪ)
3. ጠንካራ ተግሣጾች እና ክልከላዎች
4:171፦ "የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰን አትለፉ፤ ... መሲሕ ዒሳ የመርየም ልጅ የአላህ መልክተኛ ብቻ ነው..."
5:68፦ "የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ተውራትንና ኢንጂልን ከጌታችሁም ወደ እናንተ የወረደውን (ቁርኣን) እስከምታቆሙ ድረስ በምንም ላይ አይደላችሁም..."
ሲጠቃለል፦
1)የእውነትና የሐሰት መደባለቅ፦ ቁርኣን በእጃቸው ያለው መጽሐፍ ንጹሕ መሆኑን አያረጋግጥም፤ ይልቁንም የመጽሐፉ ባለቤቶች እውነትን ከሐሰት ጋር እንደሚቀላቅሉ በግልጽ ይወቅሳል። ይህ ወቀሳ መጽሐፉ ተበርዟል ለሚለው ሀሳብ ቀጥተኛ ማስረጃ ነው።
2)የመደበቅ ተግባር፦ አይሁዶችና ክርስቲያኖች ከመጽሐፋቸው ውስጥ ብዙዎቹን እውነታዎች እንደሚደብቁና በከፊሉ ብቻ እንደሚጠቀሙ ቁርኣን ይገልጻል። መጽሐፉን "ክፍልፋይ" (6:91) በማድረግ የፈለጉትን ብቻ መግለጣቸው በእጃቸው ያለው ጽሑፍ ሙሉ እንዳልሆነ ያሳያል።
3)ቁርኣን እንደ ሚዛን (ሙሀይሚን)፦ ቁርኣን የቀደሙ መጻሕፍትን "አረጋጋጭ" ብቻ ሳይሆን "ተቆጣጣሪ/ሚዛን" (ሙሀይሚን) ሆኖ ነው የመጣው (5:48)። ይህም ማለት በቀደሙት መጻሕፍት ውስጥ ያለውን መለኮታዊ እውነት ከሰው ድርሰት ለይቶ የሚያወጣ ብቸኛ መመዘኛ ነው ማለት ነው።
4)ወደ አዲሱ መልክተኛ የቀረበ ጥሪ፦ በእጃቸው ያለው መጽሐፍ ለድኅነት በቂ ቢሆን ኖሮ፣ አላህ የመጽሐፉን ባለቤቶች ወደ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ብርሃን እንዲመጡ ባልጠራቸው ነበር። መልክተኛው የመጣው እነርሱ የደበቁትንና ያዛቡትን እውነት ለመግለጥ ነው።
5)የተግባር መስፈርት፦ የመጽሐፉ ባለቤቶች በተውራትና በኢንጂል ውስጥ ያለውን እውነት (ስለ መጨረሻው ነቢይ የተነገሩትን ጨምሮ) እስካላቆሙ ድረስ በምንም ላይ እንዳልሆኑ ቁርኣን ይገልጻል። ይህም በእጃቸው ያለው ጽሑፍ በተግባር ካልተተረጎመና ወደ ቁርኣን ካልመራ ዋጋ እንደሌለው ያረጋግጣል።
