ru
Feedback
الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ

الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ

Открыть в Telegram

​الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ ​እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
2 203
Подписчики
+1824 часа
+617 дней
+46430 дней
Архив постов
✍ 👇👇👇👇👇 يا ايها الذين امنوا لما تقولون ما لا تفعلون كبر مقتا عند الله ان تقولوا ما لا تفعلون እነዚያ ያመናችሁ ሆይ የማትሰሩትን የማታደር
✍ 👇👇👇👇👇   يا ايها الذين امنوا لما تقولون ما لا تفعلون كبر مقتا عند الله ان تقولوا ما لا تفعلون እነዚያ ያመናችሁ ሆይ የማትሰሩትን የማታደርጉትን ነገር ለምን ትናገራላችሁ? የማይሰሩትን ነገር መናገር አላህ ዘንድ መቆጣቱ ጥላቻው ታላቅ ሆነ ​ አጠር ያለ ማብራሪያና ምክር ​ከዚህ አንቀፅ  የምንማራቸው ዋና ዋና ቁምነገሮች የሚከተሉት ናቸው ​የንግግርና የተግባር መጣጣም፦ አንድ ሙስሊም በአፉ የሚናገረው መልካም ነገር፣ የሚሰጠው ምክር ወይም የገባው ቃል ከተግባሩ ጋር እኩል መሆን አለበት። ሰዎችን ወደ መልካም ነገር እየጠሩ ራስን መርሳት አላህ ዘንድ እጅግ የተጠላ ተግባር ነው ​የቃል ኪዳን ክብደት፦ ለአላህም ሆነ ለሰዎች ቃል ስንገባ፣ ወይም «ይህንን መልካም ስራ እሰራለሁ» ብለን ስንናገር መፈጸም እንዳለብን ያስገነዝበናል​ከንቅናቄ (ሙናፊቅነት) ባህሪ መራቅ፦ ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንደተናገሩት ከሙናፊቆች ምልክቶች አንዱ «ቃል ሲገባ ማፍረስ» ነው። ይህ አንቀጽ አማኞችን ከዚህ መጥፎ ባህሪ ይጠብቃቸዋል​ ማጠቃለያ ይህ አያህ ሁልጊዜ ራሳችንን እንድንመረምር ያሳስበናል። ዎችን «ታገሱ» ስንል እኛ መጀመሪያ ታጋሽ መሆን፣ «ስገዱ» ስንል እኛ መጀመሪያ ሰጋጅ መሆን፣ «አትዋሹ» ስንል እኛ መጀመሪያ እውነተኛ መሆን እንዳለብን ያስገነዝበናል። አላህ ከተናጋሪና ከተግባሪዎች ያድርገን https://t.me/umu_afifah_ami_chanal

حياك الله اخواتي واخواني في الله👆👆👆👍👍👍 ቢል ዓፊያ ዓለይኩም 👌👌👌
+4
حياك الله اخواتي واخواني في الله👆👆👆👍👍👍 ቢል ዓፊያ ዓለይኩም 👌👌👌

ቤተሰብ እደት ነው ኢዱ አይዞን አይዞን በሉ ጠጣጡ ምሳ ይድረስ ደቢሀም አርደናል እስከዛው ሻይ ጋህዋ በሉ ክክ🌸🌸🌸👌 الحمدلله على التمام الحمدلله الذي بنعمته تتم ال
ቤተሰብ እደት ነው ኢዱ አይዞን አይዞን በሉ ጠጣጡ ምሳ ይድረስ ደቢሀም አርደናል እስከዛው ሻይ ጋህዋ በሉ ክክ🌸🌸🌸👌 الحمدلله على التمام الحمدلله الذي بنعمته تتم الصالحات الحمدلله الذي بلغنا عشر ذي الحجة وبلغنا صيام عرفة أسأل الله الحي القيوم أن يتقبل منا ومنكم ويتجاوز عنا تقصيرنا. ورحل يوم عرفة ... حاملاً معه كل دعواتنا التي نرجو من الله تحقيقها .. ربِ اجعلني وأحبتي ممن غفرت ذنبه وقبِـلتَ أعماله ، وأجبت دُعاءَه. 🌸وكل عام وأنتم بخير 🌸 اللهم في أول أيام عيد الأضحى، اكتب لنا فرحة لا تزول، ورزقًا لا ينقطع، ودعاءً مستجابًا، وقلوبًا مطمئنة، وأيامًا مملوءة بالسعادة والرضا.اللهم اجعل عيدنا هذا عيد خير وبركة، وتقبل منا صالح الأعمال، واغفر لنا ولوالدينا ولمن نحب.

ትክክል ናቹህ ከፎቶው ላይ ኢደል ፊጥር ነው 💧💧👍👍ኢደል አድሀ ነበር ረስቸው ነው ኢድ እና አረፋ ሲሆን ሁሌ በሰው ቤት ስለሚከፋን የምንጫጪራቸውን ራሱ አናስተውልም 💧💧💧ያረብ የዘድሮውን ብቸኝነት የመጨረሻ ያርግልን ኢንሸአሏህ በሰው ቤትኮ ከባድ ነው አልሀምዱ ሊላህ

🌹በስደት ለሚገኙ፣ የናፍቆትና የብቸኝነት ስሜት ለሚፈታተናቸው ጀግና እህቶቻችን የኢድ መልዕክቴ🌹 👑 የኔ ጀግና... የፅናትና የፍቅር ተምሳሌት የሆንሽው ስደተኛዋ ሰለፊዮ እህቴ! 👑 ኢድ ሲመጣ የሀገር ሽታ፣ የእናት ምርቃት፣ የአባት እቅፍና የወንድም እህት ሳቅ ይበልጥ እንደሚናፍቅና ልብን እንደሚከብድ አውቃለሁ። አዎ... በሰው ሀገር ላይ በዓል እንደ በዓል ላይሰማሽ ይችላል። ሌሎች ቤተሰቦቻቸውን አቅፈው ሲደሰቱ፣ አንቺ በብቸኝነትና በናፍቆት ማዕበል መሀል ሆነሽ በስልክ ስክሪን ላይ በሚታይ ምስል ትዝታሽን ልታክሚ ትሞክሪ ይሆናል። ግን ውድ እህቴ ሆይ... ለአፍታ ቆም ብለሽ እራስሽን ተመልከቺ! አንቺ እኮ ተራ ስደተኛ አይደለሽም፤ አንቺ ለአገርሽ ኩራት፣ ለቤተሰብሽ የጀርባ አጥንት፣ ለቤተሰቦችሽ የደስታቸው ምንጭ ነሽ ለታናናሾችሽ የተስፋ ጮራ ነሽ። ዛሬ በሰው ሀገር የምታፈስሺው እያንዳንዱ የላብ ጠብታና በብቸኝነት የምታፈሽው እያንዳንዱ የናፍቆት እንባ አላህ ዘንድ ትልቅ ዋጋ አለው። በዓላትን ከቤተሰብሽ ርቀሽ የምታሳልፊው እራስ ወዳድ ስለሆንሽ ሳይሆን፣ እነሱን ለማስደሰትና የነገ ሕይወታቸውን ብሩህ ለማድረግ ደስታቸው የተሟላ እንዲሆን ምንም እንዳይጎድልባች ራስሽን መስዋዕት ስላደረግሽ ነው። የኔ ጀግና እህት ! ዛሬ ልብሽ በናፍቆት ቢደማም፣ ከዚህ በስተጀርባ ግን የሚያምርና ብሩህ የሆነ የአላህ ራህመት እንዳለ በፍጹም አትዘንጊ። ዛሬ አንቺ በሩቅ ሆነሽ የምትልኪው ስጦታ በቤተሰቦችሽ ውስጥ ትልቅ ደስታን እንደሚፈጥር ሁሉ፣ አላህም በስደት ሀገር ባለሽበት ቦታ ላይ ሰላሙንና በረካውን ያውርድልሽ። ጀግናዬ ይሄም ቀን ያልፋል! ነገ በሀገርሽ፣ በገዛ ቤትሽ፣ ከወላጆችሽ ምርቃትና ከምትወጃቸው ሰዎች እቅፍ ጋር በደስታና በሳቅ የምታከብሪበት ጊዜ በእርግጥ ይመጣል። ያኔ የዛሬው ትግልሽ ለጣፋጭ ትዝታ ይበቃል። የዛሬው ድካምሽ ነገ በሀገርሽ ላይ በኩራት እንድትቆሚ ያደርግሻል። ጀግናዬ ዛሬ የደስታ ቀን ነው! የጌታሽ ስጦታ ነውና ራስሽን አታሳዝኚ። ፈገግ በይ፣ የኢድን ልብስሽን ልበሺ፣ ልብሽን በምስጋና ሙሊው። ከቻልሽ ከውድ ሰለፊይ እህቶችሽ ጋር ተገናኝተሽ ከነሱ ጋር አላህን በማያስቆጣ መልኩ ኢድን ደስተኛ ሁነሽ አሳልፊ አብሽሪ አላህ ደስተኛ ያድርግሽ ።አንቺ ኮ ለኛም ሆነ ለቤተሰቦችሽ እውነተኛ ልዕልትና የቁም ጀግና ነሽ! 🌹 ኢድ ሙባረክ! ውዷና ብርቱዋ ስደተኛዋ እህቴ!🌹 አላህ ዕድሜሽን በበረካ፣ በጤናና በደስታ ያርዝመው። የሚመጣው ዓመት በሀገርሽ፣ በናፈቅሽው ቅጥር ጊቢ ውስጥ ከቤተሰቦችሽ ጋር የምታከብሪው ያድርግሽ። ከወንድማችሁ አቡ ሒበቲላህ ሁሰይን t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

عيدكن مبارك أخواتي واخواني في الله أتمنى أن يكون هذا العيد سببا لمغفرة الله وسببا للتألف بيننا وتوطأة إلى الجنة عرضها السموات والأرض. በአላህ ያመናችሁ እህቶቼ፤  ወድሞች ይህ በዓል ለአላህ ምህረት፣ በመካከላችን ላለው መተሳሰብ፣ እንዲሁም ስፋቷ እንደ ሰማያትና ምድር ወደሆነችው ጀነት ለመግቢያ ምክንያት እንዲሆንልን እመኛለሁኝ። ​መልካም የዒድ በዓል ይሁንላችሁ! ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩነ! ኢድ ሲመጣ ብዙ ነገሮች እናስታዉሳለን በሰዉ ሀገር ስንኖር 1እናት እና አባቶቻችን 2 ባል ሚስቱን ይበልጥ ያስታዉሳል ሚስት ባሏን 3 ልጆቹ በጣም ትዝ ይሉታል ጎረቤቶቹን ያስታዉሳል ጓደኞቹን ያስታዉሳል እኒህን ማገኘት ምንኛ ያስደስት ነበርኮ አልሀምዱሊላህ

ነገ እኮኢድ ነው አልሀምዱ ሊሏህ🌸 ​ውድ እና የተከበርሽ ጓደኛዬ እንኳን ለተከበረው የኢድ አድሀ _ በዓል በሰላም አደረሰሽ ​ይህ በዓል ላንቺ የደስታ የሰላም የጤና እና የበረከት በዓል እንዲሆንልሽ
+1
ነገ እኮኢድ ነው አልሀምዱ ሊሏህ🌸 ​ውድ እና የተከበርሽ ጓደኛዬ እንኳን ለተከበረው የኢድ አድሀ _ በዓል በሰላም አደረሰሽ ​ይህ በዓል ላንቺ የደስታ የሰላም የጤና እና የበረከት በዓል እንዲሆንልሽ ከልቤ እመኛለሁ ​ካንቺ ጋር ያለኝ እውነተኛ ጓደኝነት በሕይወቴ ውስጥ ትልቅ ቦታ ካላቸው ውብ ስጦታዎች አንዱ ነው ​በደስታሽ ሰዓት አብሬሽ መሆን ባልችልም ልቤ እና ዱዓዬ ሁልጊዜም ካንቺው ጋር ናቸው ​አላህ መልካም ስራሽን ሁሉ ተቀብሎ ያሰብሽበትና የፈለግሽበት የደስታ ጥግ ላይ እንዲያደርስሽ እማጸናለሁ ​በዓሉ በቤትሽ ላይ ፍቅርን በልብሽ ላይ እርካታን በፊቱሽ ላይ ደግሞ ፈገግታን ብቻ ይሙላው ​መልካም በዓል ይሁንልሽ ከነቤተሰቦችሽ ጋር በደስታ አሳልፊው ከልብ እወድሻለሁ🎀💐🎈

ኢላሒ...! ጭንቀቴ ለአንተ ቀላል ነው! "የኔ አላህዬ... ለእኔ እንደ ተራራ የከበደኝና እንቅልፍ የነሳኝ ትልቁ ጭንቀቴ... በአንተ ዘንድ እጅግ በጣም ቀላልና በአንድ ቃል 'ሁን' (ኩን) ሲባል የሚፈታ ነው። በልቤ የታመቀውን ምኞቴን ሁሉ አንተ ታውቀዋለህና፤ ካሰብኩት በላይ አድርገህ ስጠኝ። ወዳጆቼ...! አንዳንዴ ሕይወት ትከብደናለች። በትከሻችን ላይ ዓለምን የተሸከምን ያህል ይሰማናል። በሐሳብ ማዕበል እንዋጣለን፣ ሌሊቱ ይረዝምብናል፣ እንቅልፍ ከዓይናችን ይሸሻል። ያ የያዝነው ጭንቀት መውጫ የሌለው ተራራ ሆኖ ይታየናል። ነገር ግን... አንድ ትልቅ እውነት እናስታውስ! ያ ለእኛ እንደ ተራራ የከበደን ጉዳይ፣ ሰማያትና ምድርን ያለ አንዳች ድካም ለፈጠረው ጌታ እጅግ በጣም "ቀላል" ነው። እኛ በሰበቦችና በምክንያቶች ዓለም ውስጥ ስንባክን፣ እርሱ ግን በምክንያቶች ላይ የበላይ ነው። አላህ (ሱበሀነሁ ወተዓላ) በቁርአኑ እንዲህ ይላል፦ "ነገሩን (ሊሆን) በሻ ጊዜ ትእዛዙ ለእርሱ 'ሁን' ማለት ብቻ ነው፤ ወዲያውም ይሆናል።" (ያሲን 82) አዎን! ያ አንተን ያስለቀሰህ፣ ያ አንቺን ተስፋ ያስቆረጠሽ ጉዳይ በአላህ ዘንድ በአንድ ቃል የሚፈታ "ቀላል" ነገር ነው። ጌታችን ሰጪነቱ እንደ እኛ ስስት የለበትም። እኛ "ይህ ቢሆንልኝ" ብለን በጠበበ አእምሯችን ስንመኝ፣ እርሱ ግን ካሰብነውና ከገመትነው በላይ አትረፍርፎ የመስጠት ችሎታና ቸርነት አለው። በልብህ የታመቀውን ሚስጥር ያውቀዋል! ለሰው መናገር የከበደህን፣ በቃላት መግለጽ ያቃተህን የልብህን ትርታና ምኞት እርሱ ያውቀዋል። ገና ሳይወጣ የታፈነውን እንባህን ያያል። ስለዚህ ለሰዎች ከማማረር ይልቅ፣ ጉዳዩን ወደ ባለቤቱ አቅርብ። "ያ አላህ! አቅሜ ደክሟል፣ አንተ ግን ጠንካራ ነህ። እኔ መውጫውን አላውቅም፣ አንተ ግን መላሽ ነህ። ጭንቀቴን በአንተ ራህመት አቅልልልኝ፤ የልቤን መሻት ካሰብኩት በላይ አሳካልኝ" ብለህ ተማጸነው። ያኔ ተራራው ሜዳ ሲሆን፣ እንቅልፍ የነሳህ ጭንቀት የሰላም እንቅልፍ ሲሆን ታየዋለህ። አላህ ሆይ! የሁላችንንም የልብ መሻት በቸርነትህ ካሰብነው በላይ አድርገህ ስጠን! t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

اللهم لا تجعل شمس يوم عرفة تغيب إلا وقد جعلتنا ممن عفوت عنهم ورضيت عنهم وغفرت لهم واستجبت لهم وتقبلت منهم💧 اللهم لا تجعل هذا
اللهم لا تجعل شمس يوم عرفة تغيب إلا وقد جعلتنا ممن عفوت عنهم ورضيت عنهم وغفرت لهم واستجبت لهم وتقبلت منهم💧 اللهم لا تجعل هذا اليوم يمضي إلا وقد أعطيت كل منا مراده، ورويت قلوبنا بفيض كرمك وعفوك وغفرانك🤲 يا رب في يوم عرفة، بشرني بأمنيات كانت ولا زالت أول دعائي🤲 اللهم إني أسألك من الخير ما سألك به عبادك الصالحون في يوم عرفة، وأسألك من الرحمة ما يليق بجلال وجهك وعظيم سلطانك، أن تغفر لنا ذنوبنا، وتصلح أحوالنا، وتحقق لنا ما نتمنى، وتكتب لنا من الأقدار أجملها، ومن السعادة أكملها، ولا تردنا خائبين يا أرحم الراحمين.🤲 ማሳሰቢያ እነዚህ ዱዓዎች በዱዓ ተቀባይነቱ በሚታወቀው የዓረፋ ቀን ላይ ለማለት በጣም ውብ እና ሙሉ የሆኑ የዱንያንም የአኼራንም ስኬት የሚያስገኙ ልመናዎች ናቸው አላህ ዱዓሽን ይቀበልሽ የልብሽን መሻት ሁሉ ያሳካልሽ https://t.me/umu_afifah_ami_chanal

لا إله إلا الله وحده لا شريك له، له الملك وله الحمد، وهو على كل شيء قدير..

4 ከባባድ የሆኑ የዐረፋ ቀን ደረጃ... الشيخ عبد الرزاق البدر حفظه الله👉

+2
أسأل الله أن يتقبل منكم دعاءكم، ويكتب لكم الأجر والقبول. الله أكبر، الله أكبر، الله أكبر. لا إله إلا الله، الله أكبر، الله أكبر، ولله الحمد.

መልካም ስነ-ምግባር (አህላቅ) የአንድ ሙስሊም የህይወት መሰረት እና የኢማኑ መገለጫ ነው ​እራስን በዕውቀት ማነፅና ወደ አላህ መጠጋት 👌
መልካም ስነ-ምግባር (አህላቅ) የአንድ ሙስሊም የህይወት መሰረት እና የኢማኑ መገለጫ ነው ​እራስን በዕውቀት ማነፅና ወደ አላህ መጠጋት 👌

በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው። ​ስለ አዱንያ (የምድር ሕይወት) ተፈጥሮ ጠንቅቆ ማወቅ እና ትኩረትን በአኼራ (በመጨረሻው ዓለም) ላይ ማድረግ፣ በዱንያ ላይ ለሚገጥሙን መከራዎችና ፈተናዎች ትልቁ ማስታገሻና መጽናኛ ነው። አላህና መልክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በዚህ ዙሪያ ያስቀመጡልንን ግልጽ የቁርአን አንቀጾች (አያቶች) እና ሐዲሶች ትርጉማቸውን ጨምሮ እንደሚከተለው በዝርዝር እንመልከት። ​1. የዱንያ ሕይወት ጊዜያዊና የፈተና ቦታ መሆኑን ማወቅ ​በመጀመሪያ ደረጃ፣ ዱንያ የደስታና የዘላለም ማረፊያ ሳትሆን የፈተና አዳራሽ መሆኗን መረዳት መከራን ለመቻል የመጀመሪያው እርምጃ ነው። ​ከቁርአን፦ አላህ በሱረቱ አል-በቀራህ አንቀጽ 155-156 ላይ እንዲህ ይላል፦
​وَلَنَبْلُوَنَّكُم بِشَيْءٍ مِّنَ الْخَوْفِ وَالْجُوعِ وَنَقْصٍ مِّنَ الْأَمْوَالِ وَالْأَنفُسِ وَالثَّمَرَاتِ ۗ وَبَشِّرِ الصَّابِرِينَ ۞ الَّذِينَ إِذَا أَصَابَتْهُم مُّصِيبَةٌ قَالُوا إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ ​ትርጉም፦ «ከፍርሃትና ከራብም፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍሬዎችም በማጉደል በእርግጥ እንፈትሻችኋለን፤ ታጋሾችንም አብስራ። እነዚያን መከራ በገጠማቸው ጊዜ «እኛ ለአላህ ነን፤ እኛም ወደ እርሱ ተመላሾች ነን» የሚሉትን (አብስራቸው)።»
​ከሐዲስ፦ ታላቁ ሰሃባ አብዱላህ ኢብኑ ዑመር (ረዲየልላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል፦ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ትከሻዬን ያዙኝና እንዲህ አሉኝ፦
​"كُنْ فِي الدُّنْيَا كَأَنَّك غَرِيبٌ أَوْ عَابِرُ سَبِيلٍ" (رواه البخاري) ​ትርጉም፦ «በዱንያ ላይ ልክ እንደ እንግዳ ወይም መንገድ አቋራጭ መንገደኛ ሆነህ ኑር።» (ቡኻሪ ዘግበውታል)
​የምክር ጭብጥ፦ እንግዳ ሰው በሰው አገር ላይ በሚገጥመው እንግልት ብዙ እንደማይበሳጭና ዋናው ሃሳቡ ወደ ሀገሩ (ወደ አኼራ) በሰላም መመለስ እንደሆነ ሁሉ፣ አንተም በዱንያ መከራ አትደንግጥ፤ መድረሻህ አኼራ ነው። ​2. መከራ ወንጀልን እንደሚያብስና ደረጃን እንደሚያወጣ ማመን ​በአላህ መንገድ ላይ እያለህ የሚገጥምህ ማንኛውም አይነት ችግር፣ ህመምም ሆነ ጭንቀት ዝም ብሎ የሚጠፋ ሳይሆን ወንጀልህን የሚያራግፍልህ መሆኑን ስታውቅ መከራው ይቀልሃል። ​ከቁርአን፦ አላህ በሱረቱ አሊ-ዒምራን አንቀጽ 142 ላይ እንዲህ ይላል፦
​أَمْ حَسِبْتُمْ أَن تَدْخُلُوا الْجَنَّةَ وَلَمَّا يَعْلَمِ اللَّهُ الَّذِينَ جَاهَدُوا مِنكُمْ وَيَعْلَمَ الصَّابِرِينَ ​ትርጉም፦ «እነዚያ ከእናንተ ውስጥ የታገሉትን ሳያውቅ (ሳይለይ) እና ታጋሾቹንም ሳይለይ ጀነትን ልትገቡ አሰባችሁን?»
​ከሐዲስ፦ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
​"مَا يُصِيبُ الْمُسْلِمَ مِنْ نَصَبٍ وَلاَ وَصَبٍ وَلاَ هَمٍّ وَلاَ حُزْنٍ وَلاَ أَذًى وَلاَ غَمٍّ حَتَّى الشَّوْكَةِ يُشَاكُهَا إِلاَّ كَفَّرَ اللَّهُ بِهَا مِنْ خَطَايَاهُ" (متفق عليه) ​ትርጉም፦ «አንድን ሙስሊም ድካም፣ ህመም፣ ሃሳብ፣ ትካዜ፣ ችግር ወይም ጭንቀት አይገጥመውም—እንኳን የሾህ መውጋት ቢሆን—አላህ በእሱ ወንጀሎቹን ያበሰለት ቢሆን እንጂ።» (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
​3. ከችግር በኋላ ምቾት መኖሩንና የአላህን እገዛ መጠበቅ ​ሙስሊም በማንኛውም መከራ ውስጥ ተስፋ አይቆርጥም፤ ምክንያቱም ከእያንዳንዱ መከራ ጀርባ የአላህ እገዛና ሰፊ እዝነት እንዳለ ቃል ተገብቶለታል። ​ከቁርአን፦ አላህ በሱረቱ አል-ኢንሺራህ አንቀጽ 5-6 ላይ እንዲህ ይላል፦
​فَإِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا ۞ إِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا ​ትርጉም፦ «ከችግርም ጋር በእርግጥ ምቾት አለ። ከችግር ጋር ምቾት አለ።»
​ከሐዲስ፦ ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ለኢብኑ ዐባስ (ረዲየልላሁ ዐንሁማ) በሰጡት ታላቅ ምክር ላይ እንዲህ ብለዋል፦
​"وَأَعْلَمْ أنَّ النَّصْرَ مَعَ الصَّبْرِ، وَأَنَّ الفَرَجَ مَعَ الكَرْبِ، وَأَنَّ مَعَ العُسْرِ يُسْراً" (رواه الترمذي) ​ትርጉም፦ «እወቅ! ድል (እገዛ) ከትዕግስት ጋር ነው፤ መገላገልም ከጭንቀት ጋር ነው፤ ከችግርም ጋር ምቾት አለ።» (ቲርሚዚ ዘግበውታል)
​📌 ወሳኝ የአኗኗር ማጠቃለያ ምክር፦ ​በሰብርና በሶላት ታገዝ፦ መከራ ሲበዛብህ ውዱእ አድርገህ ወደ ሶላት ሩጥ። የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ነገር በጠነከረባቸው ጊዜ ወደ ሶላት ይፈጥኑ ነበር። ​ከአንተ በታች ያሉትን እይ፦ በዱንያ ጉዳይ (በሀብት፣ በጤና) ከአንተ በታች ያሉትን ተመልከት፤ አላህ የሰጠህን ጸጋ እንድታመሰግን ይረዳሃል። በአኼራ ስራ ግን ከአንተ በላይ ያሉትን (ደጋግ ሰዎችን) አርአያ አድርግ። ​ዱዓህን አታቋርጥ፦ ሁልጊዜ የዱንያንም የአኼራንም መልካም ነገር በአንድ ላይ የያዘውን የቁርአን ዱዓእ አዘውትር፦ «ረበና ኣቲና ፊዱንያ ሐሰነተን ወፊል ኣኺረቲ ሐሰነተን ወቂና ዐዛበን-ናር» (ጌታችን ሆይ! በዱንያም በአኼራም መልካሙን ስጠን፣ ከእሳት ቅጣትም ጠብቀን)። ​አላህ በዱንያ ላይ በትዕግስት አልፈው በአኼራ የጀነት ወራሾች ከሚሆኑት ደጋግ ባሮቹ ያድርገን https://t.me/umu_afifah_ami_chanal

የዛሬው ፕሮ ግራም ያሰላም ይለያል 👌👌👌 ግን ላጤወች ላይ ሚሳኤል ነው የወረወሩት ክክክክ ሆ አይዞቹህህ ላጤወች 💧💧💧 ህዕ ላጤ በየሄደበት በሽጉጥ እያሉ ይደፉታል እህህ ከሰው መደባለቅ በቃን እስከሚሉ ድረስ ሀሀሀሀሀ

እዚቤት መደረግ የያዘው  ሙሀደራ   ያሱበሀን አሏህ   ትልቅ  ትንሽ  ሳይል   መስማት    መደመጥ  ያለበት    ሙሀደራ ነው      ኑኑኑኑኑኑኑኑኑ👆📢📢📢📢👌  🔴በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ፕሮግራም   ተ         ጀ             መ                   ረ 🔉🎴 ፕሮግራም  1⃣ 🎙በኡስታዝ አቡ አብዲ ረህማን 🔰ርዕስ የትዳር አንገብጋቢነት https://t.me/Multeka_Selefiyin?videochat=f9fe331d511c1a03e7

وَٱتَّقُواْ يَوۡمٗا لَّا تَجۡزِي نَفۡسٌ عَن نَّفۡسٖ شَيۡـٔٗا وَلَا يُقۡبَلُ مِنۡهَا عَدۡلٞ وَلَا تَنفَعُهَا شَفَٰعَةٞ وَلَا ه
+1
وَٱتَّقُواْ يَوۡمٗا لَّا تَجۡزِي نَفۡسٌ عَن نَّفۡسٖ شَيۡـٔٗا وَلَا يُقۡبَلُ مِنۡهَا عَدۡلٞ وَلَا تَنفَعُهَا شَفَٰعَةٞ وَلَا هُمۡ يُنصَرُون አንድት ነፍስ ለሌላኛዋ ምንንም የማትጠቅምበትን ከርሷም ቤዛ የማይወሰድበትን ምልጃም ለርሷ የማትጠቅምበትን እነርሱም የማይረዱበትን ቀን ተጠንቀቁ ፍሩም
https://t.me/umu_afifah_ami_chanal

​በህይወትሽ ውስጥ በሚያጋጥሙሽ ውጣ ውረዶች ተስፋ አትቁረጪ ​ጊዜሽን በአግባቡ ተጠቀሚበት እያንዳንዱ ቀን ውድ ነው ​ለራስሽ ታማኝ ሁኚ የራስሽን ደስታ ቀድሚ ​የሰዎችን መልካምነት ተመልከች ግን ደግ
+2
​በህይወትሽ   ውስጥ በሚያጋጥሙሽ ውጣ ውረዶች ተስፋ አትቁረጪ ​ጊዜሽን  በአግባቡ  ተጠቀሚበት እያንዳንዱ  ቀን ውድ ነው ​ለራስሽ ታማኝ  ሁኚ የራስሽን  ደስታ  ቀድሚ ​የሰዎችን መልካምነት ተመልከች ግን ደግሞ ጥንቁቅ ሁኚ ​በመጨረሻም    ሁሌም ፈገግታ አይለይሽ ጓደኝነት እንደ አበባ ያብባል በመካከላችን ፍቅርና መተሳሰብ ያኖረዋል በልባችን በርቺልኝ ጓደኛ

الْحَجُّ أَشْهُرٌ مَّعْلُومَاتٌ ۚ فَمَن فَرَضَ فِيهِنَّ الْحَجَّ فَلَا رَفَثَ وَلَا فُسُوقَ وَلَا جِدَالَ فِي الْحَجِّ ۗ وَمَا تَفْعَلُوا مِنْ خَيْرٍ يَعْلَمْهُ اللَّـهُ ۗ وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ የሐጅ ጊዜያቱ የታወቁ ወሮች ናቸው   በእነርሱም ውስጥ ሐጅን  እንዲሠራ  ነፍሱን ያስገደደ ሰው በሐጅ ውስጥ ሴትን መገናኘት ማመጽም ክርክርም የለም  ከበጎም ሥራ የምትሠሩትን ሁሉ አላህ ያውቀዋል  ተሰነቁም  ከስንቅም  ሁሉ በላጩ  ጥንቃቄ አላህን መፍራት ነው  የአእምሮዎችም ባለቤቶች ሆይ! ፍሩኝ https://t.me/umu_afifah_ami_chanal