الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ
Открыть в Telegram
الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ
БольшеСтрана не указанаКатегория не указана
2 203
Подписчики
+1824 часа
+617 дней
+46430 дней
Архив постов
⚠️ጀግና ሴት ማለት....⁉️
በስደት ላይ ለሚገኙ፣ በልፋታቸው ዓለምን ለሚቀይሩና ለቤተሰቦቻቸው የጀርባ አጥንት ለሆኑ ብርቱ እህቶቻችን ይድረስልኝ
ጀግና ሴት በሰው ላይ ተስፋ አታደርግም፤ ሙሉ ማንነቷን የምታገኘው ከፈጣሪዋ ከአላህና ከራሷ ከእምነቷ ነው። በስደትም ሆነ በየትኛውም ፈተና ውስጥ ብትሆን፣ ክብሯን ጠብቃ ለገዛ ራሷ ህልም በእውነትና በታማኝነት የምትተጋ ሴት መቼም ቢሆን አትወድቅም!
ጀግና ሴት ማለት ለራሷ ደራሽ፣ ለቤተሰቧ መከታ፣ ለሕልሟ ደግሞ ታማኝ የሆነች የጽናት ተምሳሌት ናት። እሷ በሰው ጫንቃ ላይ ተንተርሳ መኖርን አታውቅም፤ ይልቁንም ሙሉ ማንነቷንና ጥንካሬዋን የምታገኘው ከፈጣሪዋና ለራሷ ካላት ጽኑ እምነት ነው።
ውድ የስደት ጮራዋ እህቴ ሆይ! ስደት መከራ ብቻ አይደለም፤ ስደት አንቺነትሽን የምታገኚበት፣ ብረት እንደ እሳት ተፈትኖ
እንደሚወጣው ሁሉ አንቺም ተፈትነሽ ለትልቅነት የምትበቂበት አውድማ ነው። ለሊቱ ሲረዝምብሽ፣ ናፍቆቱ ሲበዛብሽና
ድካሙ ሲበረታብሽ፤ ያንቺን እጅ የሚጠባበቁትን ወላጆችሽንና ቤተሰቦችሽን አስቢ። አንቺ ለነሱ ተራ ሰራተኛ አይደለሽም፤ አንቺ ለነሱ የቤት አምድ፣ የታናናሾችሽ ተስፋና የወላጆችሽ የኩራት ምንጭ ነሽ።
ክብርሽን ጠብቀሽ፣ ማንነትሽን ሳትዘነጊ፣ በሰው ሀገር ውጣ ውረድ ውስጥ ሆነሽ በታማኝነት የምትተጊው እህቴ ሆይ! ድካምሽ የአሸናፊነትሽ ዋጋ ነው። በዚህ ዓለም ላይ ቀጥ ብለው የሚቆሙት በላባቸው የሚኖሩ፣ በዓላማቸው የጸኑና ለአላህ ውሳኔ እጃቸውን የሰጡ ብርቱዎች ብቻ ናቸው።
አስታውሺ ጀግናዋ! አንቺ የምትገነቢው ቤት ብቻ አይደለም፤ አንቺ የምትገነቢው የነገውን ትልቅ ማንነትሽን ነው። ዛሬ በሰው ሀገር የምታፈስሺው እያንዳንዱ የላብ ጠብታ፣ ነገ ለታላቅ ደስታና ስኬት ዘር ሆኖ ይበቅላል።
ይህ ዓለም የሚገባውና መንገዱን የሚከፍተው "አልችልም" ብሎ ለተሸነፈ ሳይሆን፤ በፈተና መሃል ፈገግ ብላ ለቆመችው፣ እንባዋን ታብሳ ለሰራችውና ተስፋዋን በፈጣሪዋ ላይ ላደረገችው ለጀግናዋ ስደተኛ እህቴ ነው።
አንቺ የአገር ኩራት፣ የወገን መመኪያ ነሽ! አላህ በረካውን በስራሽ፣ ሰላሙን በልብሽ፣ መመለሻሽን ደግሞ በክብርና በደስታ
ያድርግልሽ።
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
እውነተኛ የሆኑ ጓደኞች በሰላም ጊዜ ጌጥ
በችግር ጊዜ አለኝታ ናቸው።🌸
https://t.me/umu_afifah_ami_chanal
🌹 ሰላም ለነዛ ልቦች... 🌹
🌹ሰላም ለነዛ ልቦች... በዚህች ጫጫታና ግርግር በበዛባት ዓለም ውስጥ፣ ረጋ ብለው የስክነትንና የሰላምን ወደብ ለሚፈልጉ።
🌹ሰላም ለነዛ ልቦች... ራሳቸው በቁስል ተሞልተው ሳለ፣ የሌሎችን ስብራት ለመጠገን ለሚተጉ። የራሳቸው ጉዳይ ሳይሳካላቸውና ፍላጎታቸው ሳይሞላላቸው፣ የሌሎችን ደስታ ለማየት በንጹህ ልብ ዱዓ ለሚያደርጉ።
🌹ሰላም ለነዛ ልቦች... ጭንቅ ጥብብ ሲላቸው፣ አማራጭ ሁሉ ሲዘጋባቸውና መውጫ ሲያጡ፤ ሰዎችን ከማማረር ይልቅ በለሊት ጨለማ ውስጥ ተንበርክከው በእንባዋቸው ሰላምን ከጌታቸው ለሚማጸኑ።
🌹 ሰላም ለነዛ ልቦች... በምርጫ መከራ ውስጥ ሆነው፣ የቱ እንደሚሻላቸው ግራ ሲገባቸው፤ በሐሳብ ከመባከን ይልቅ "ኢስቲኻራ"ሰግደው የሕይወታቸውን መሪ ለአላህ አሳልፈው ለሚሰጡና ኸይሩን ነገር ከጌታቸው ለሚጠብቁ።
🌹 ሰላም ለነዛ ልቦች... የውስጥ ስብራታቸው ሳይጠገንላቸው፣ በሐቅ የሚወዳቸውንና የሚከባከባቸውን ሰው ለመቀበል የቆሰለ ልባቸው ገና ባይፈቅድላቸውም፤ አላህ የተሻለውን እንዲሰጣቸውና የልባቸውን መቆለፊያ በረሕመቱ እንዲከፍትላቸው ለሚለምኑ።
🌹 ሰላም ለነዛ ልቦች... በሰው ፊት ፈገግታን ተላብሰው፣ በውስጣቸው ግን ትልቅ የሐዘን ባህር ለተሸከሙ። ፈገግታቸው የደስታ መግለጫ ሳይሆን፣ የአላህን ውሳኔ (ቀድር) የመቀበልና የትዕግስታቸው ምልክት ለሆነ።
🌹 ሰላም ለነዛ ልቦች... "አላህ ለኔ ከመረጠልኝ በላይ ለእኔ የሚበልጥ ምርጫ የለም" ብለው በጸጋ የተቀበሉ፤ ባጡት ነገር ላይ ከማዘን ይልቅ፣ ባላቸው ጥቂት ነገር ላይ "አልሐምዱሊላህ" የሚሉ የሁልጊዜ አመስጋኞች።
💧 አላህ ሆይ! ለነዚህ ልቦች ስክነትን አውርድላቸው። ስብራታቸውን ጠግንላቸው። ጭንቀታቸውን በደስታ፣ ሕመማቸውን በፈውስ፣ ብቸኝነታቸውን ደግሞ ባንተ ቅርበት ለውጥላቸው።
እናንተ የንጹህ ልብ ባለቤቶች... አላህ ሰላሙን በቤታችሁና በልባችሁ ላይ ያውርድላችሁ!
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
اللهم اجعل القرآن ربيع قلوبنا ونور صدورنا.
اللهم مع هذا الصباح، جدد فينا الأمل، وازرع في قلوبنا الطمأنينة، وافتح لنا أبواب رزقك ورضاك. اللهم إنا نسألك خير هذا اليوم، ونوره، ونصره، وبركته، وهداه، ونعوذ بك من شر ما فيه وشر ما بعده.
وَمَا تَدْرِي نَفْسٌ بِأَيِّ أَرْضٍ تَمُوتُ
ነፍስ ሁሉ የት ምድር እደምትሞት አታውቅም
ያአሏህ የኛ ነገር አተ እዘንልኝ ያረብ ሞት እኮ አይቀርም ቀኑም አይታወቅም 1 ቀን እሞታለሁኝ ከናተም በፊት ከሆንኩኝ አሏህ ይዘንላት ብላቹህ ዱዓ እድታረጉልኝ ጓደኝቼ💔💧💧 የኛ ነገር እኮ 1 ደቂቃ ሰተን ብናስተውለው በጣም ገራሚ ነን ግን .........?!
ሀቢቢ 💧 ያረብ በተሻለው እደምጠግነኝ በተስፋ እጠብቃለሁ ኢንሸአሏህ
ሞት አይመርጥም
ለሞት ትልቅም ትንሽም የለወም። ንጉስም ሆነች ድሃ፣ 20 አመትም ሆነ 100 አመት፣ ሁሉን አንድ የሚያደርግ ነው
እሱ ሲመጣ የዕድሜ፣ የገንዘብ፣ የስልጣን ልዩነት አይጠይቅም። በርካታ ጥሩ ሰዎችን ገና በለጋ እድሜው ወስዷል፣ ሌላውን ደግሞ ብዙ ከኖረ በኋላ ይዞት አልፏል
ስለዚህ "ለምንድነው" ብለን እንጠይቃለን፣ መልስ ግን አይሰጠንም
ምክኛቱም ለዘላለም የተፈጠረ የለም ሁሉም በጊዜው ሊያልፍ ሊሸጋገር ነው ወደዚች አለም የመጣው 💧
جهزوا قلوبكم من الآن ليوم عرفة، فشأن القلب عجيب يحتاج ترويض، حتى يلين لذكر الله،
قللوا من المشتتات، ابعدوا عن الضجيج،
اعتزلوا مجالس القيل والقال، اكثروا من الخلوة لله، اكثروا من التكبير والقرآن، اكثروا من الدعاء،
لعل الله يرى صدق عبده ويرحمه ويوفقه لهذا اليوم العظيم.
المعنى باختصار
نصيحة عملية للاستعداد ليوم عرفة: روّض قلبك، ابعد عن المشتتات والضوضاء والقيل والقال، وخلّك مع الله بذكر وخلوة وقرآن ودعاء. لعل الله يرحمك ويوفقك لفضل اليوم.
يوم عرفة من أعظم أيام السنة، والدعاء فيه مستجاب. الله يبلغنا وإياك إياه ويكتب لنا القبول 🌙
https://t.me/umu_afifah_ami_chanal
ጀግናዋ
ጀግናይቱ አንድሴት ነበረች
ድኗንም ተምራ ደግሞም ያስተማረች
የተወሂድ ጀግና የሴቶቹ ልእልት
ደከመኝ የማትል ምትለፋ ሌት ከሌት
ስሞንም ልጥቀሰው እሷ እኮ አሚቲ ነች
➤አሚቲ የእህቶቿ ንግስት
ሰላም ባለሽበት የዓፊፋዬ እናት
ስላንች ላወራ ብዕሬን አዘጋጀሁ
ግን አንችን የሚገልፅ ፍፁም ቃላት አጣሁ
መብሩክ እንበላቸው ለተመራቂወች
እነዛን አበባ የሱና ፍሬዎች
መብሩክ ስል በብዕር በርግጥ ያንሳችኋል
እናንተን የሚገልፅ ቃላትም ጠፍቶኛል
እህቶቼ እናንተ ጀግናዎች እስኪ ልንገራችሁ
ለእናታችሁ ጀግና ለኛ እራእይ ናችሁ
እናማ ስላችሁ እወዳችኋለሁ
ለዛሬ በዝሁ እሰናበታለሁ
🎀🙌መብሩክ በድጋሜ🍓
አውቃ ልታሳውቅ ቆርጣ ተነሳስታ
ለኸይር የቆመች ሸርን ወዳ ትታ
የተውሂድ አርበኛ ቁርአን አኽታሚ
ለኸይር የታዘዘች ሁሉን አስደማሚ
ልቤ የኮራባት ውዷ ጐደኛየ
በጥቂት ስንኞች ይገለጥ ደስታየ
አላህም ሲወዳት አላህ ሲፈቅድላት
ይህ ላቺ ነው ብሎ ቁርአንን ሰጣት
በተሰጣት ፀጋ ኮርታ ያኮራችኝ
የተውሂድ አርበኛ ጐደኛየ አለችኝ
ይመርላትጂ ይሳካ ምኞቷ
በአላህ ቁርአን ይዋብልኝ ቤቷ
በእውቀት የኮራች ሁሉን አስተማሪ
የሱናዋ ቆጆ በይ በራስሽ ኩሪ
የተውሂድ አርበኛ የሁሉም ተምሳሌት
በቀኝ መንገድ መጐዝ ይህ ነው ጐደኝነት
መንገድ እዳትስት የተማርች ፀንታ
ካሉባልታ ቦታ እራሷን አፅድታ
ተግታ የተማርች ሂጃቧን አጥብቃ
በቁርአን መርህ ሁሌምትብቃቃ
እሷናት ጀግናየ የተውሂድ አለቃ
ከሀራም የጠራች ሁሉን አስተማሪ
እሷ ናት ጀግናየ የተውሂድ ተማሪ
ደስታሽን አየሁት ፊትሽ ላይ ሲፈካ
የተማርሽው ሁሉ ይኑርው በርካ
ከእውቀት መአድሽ እደሊ ለሁሉ
መካፈል ነውና የተውሂድ አመሉ
ጨምሮ ጨማምሮ ይስጥሽ ሙሉ ጤና
ዘላለም አትውጪ ከተውሂድ ጐዳና
ውድ አዳማጮቸ አብራችሁ ያለችሁ
በህታችን ደስታ ደስ የተሰኛችሁ
እናተስ በእውቀት ወይስ ታጅባችሁ
አርፈደም ዛሬም ለማወቅ ተነሱ
ካሊፍ ጀምራችሁ ሁሉንም ጨርሱ
ከበደኝ አትበሉ አይከብድም ጠክሩ
ካሊፍ ጀምራችሁ ላኼራ ተማሩ
የዱንያ ኖሮችን ቢበዛም ሽቁሩ
ከሀራም ለመራቅ ቁርአን ተማሩ
አርፍዳል አትበሉ ይደርሳል ቶቶሎ
ስንቱ ሳያውቅ ኖሯል በግዜው ተታሎ
ጊዜችን ከፍቶብን ወስዋሹ ቢበዛ
ሁሉን ነገር ትተን ቶሎ እውቀት እንግዛ
ከእህታችሁ መርየም እሙ ፈውዛን
+1
ከትላንቱ ሙሀደራ የተወሰደ ነው 👇👇
አንድ እያጋጠመን ያለ ነገር አሏህ ይጠብቀንእና
ቁርአን ይቀራል ከዛም ኡለሞች ቦታ ይሰቅላል ዉረድ አልወርድም ተሰቅሎ ይቀራል ።
ቁርአን የእዉቀት መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ አይደለም ።
በኡስታዝ አቡ ዑበይዳ
"رَبَّنَا آتِنَا فِي الدُّنْيَا حَسَنَةً وَفِي الآخِرَةِ حَسَنَةً وَقِنَا عَذَابَ النَّارِ".
+9
አረፍ በሉና እራት ጋብዘናል
ኡስታዞች እና ወድሞች አሏህ ደረጃቹሁን ከፍ ያርግላቹህ ዘራቹህ ይባረክ ፍሬያለው ቅርንጫፍ ያለው ትውልድ አሏህ ይስጣቹህ ልጅ ይውጣላቹህ አሏህ ያክብራቹህ ኑሩልን በአቋማቹህ ላይ አሏሁ ተዓላ ያጠንክራቹህ ከዝንባሌ ይጠብቃቹህ ያረብ እናተ የእምድር ኮኮብ ድምቀቶቻቺን ናቹህ አሏህ ኸይሩን ሁሉ በናተም በቤተሰቦቻቹሁም ላይ ያስፍንባቹህ
ወጀዛኩሙላሁ ኸይረን
ምክራቹህ ሙሀደራቹህ አይጠገብም ወላሂ
+5
አሰላም ዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ በድጋሜ እህቶቸ የኔ ወርቆች እኳን ደስ አላቹህ አልሀምዱ ሊላህ መብሩክ
ዘምዘም እብራሂም👑🌸
ራቢዓ አብዱ👑🌸
እሙ አብዱረህማን👑🌸
መሬም አቢ ሰለምቴዋ ጉብል👑🌸
ፋጡማ ሀሰን👑🌸
መብሩክ ዓለይኩም📚📚💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
አመለጣቹህ እደት የሚጣፍጥ ሙሀደራ ነበረ 💧💧 የኛነገር ግን ገራሚ ነው ሰለፍዬች በሊቭ በፕሮ ግራም ሙሀደራ ሲገቡ ተከታታዬች ጥቂቶች ናቸው ላሀውለውላ መገን የጥመት አጃወች ኢኽዋኖች እና የመሳሰሉት ሊቭ ገባ ካሉ ያለ ጥርቅም ሀቂቃ ኧረ ወገኖቸ ንቁ ንቁ ከየት ከማን መማር እዳለባቺሁ ጠንቅቃቹህ እወቁ
በቲክቶክ ንፅፅር ከተባለ በሚሊዬን በመቶሺ ይቆጠራሉ ሲገቡ ሸር ኮቢ ሊክ ሲያደርጉ በኤሞ በቴሌ በአይ ቦታ 🌶👀 ቆይ በዚህ መተሽ 1 የእውቀት ማዓድ በቀሰምሽ ሀቂቃ ሙሀይም ደደብ ባሎን ነበረ ለማናቸውም ወድም እህቶቸ ልንነቃ ይገባናል ንቁ
