ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Открыть в Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
906
Подписчики
-124 часа
-127 дней
+4430 дней
Архив постов
ሰው መሳይ በሸንጎ ~ ከውጭ ትጥቅ አሳማሪ ብንሆንም፣ ውስጣችን ክፋት፣ ቅናት፣ ምቀኝነት ያረገዘ ከሆነ ራሳችንን እየሸወድን ነው። ለአላህ እንደሆነ የሚሰወረው ነገር የለም። የውስጣችንም እንደ ውጫችን
ሰው መሳይ በሸንጎ ~ ከውጭ ትጥቅ አሳማሪ ብንሆንም፣ ውስጣችን ክፋት፣ ቅናት፣ ምቀኝነት ያረገዘ ከሆነ ራሳችንን እየሸወድን ነው። ለአላህ እንደሆነ የሚሰወረው ነገር የለም። የውስጣችንም እንደ ውጫችን ግልፅ ነው። ለሰዎች ጥሩ መስሎ ለመታየት ከመልፋት ይልቅ የእውነት ጥሩ ሆኖ መገኘት ነው ትርጉም ያለው። መቼስ መሆንና መምሰል የተለያዩ ነገሮች እንደሆኑ ግልፅ ነው። ከሰው ፊት ጤነኛ፣ ኸይረኛ፣ አላህን ፈሪ የምንመስል ከሰው እይታ ገለል ስንል ሰቅጣጭ ወንጀሎችን የምናጨማልቅ ብዙ ሰዎች አለን። አውዛዒይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ "በአደባባይ የአላህ ወሊይ፣ በድብቅ ግን ጠላቱ አትሁን።" [አዝ-ዙህድ፣ ኢማም አሕመድ] በዚህ ዘመን እንደ ልብ ትኩረት ያጣ ነገር የለም። ለውጫዊ ገፅታችን የምንጨነቀውን ሩብ ታክል እንኳ ለልባችን እያሰብን አይደለም። ልብ ካልተገራ እና አላህን ከመፍራት ከተራቆተ ደግሞ ሌላው ሰውነት ቀፎ ነው፣ ቢከፍቱት ተልባ! ብዙዎቻችን ሰው ሰው እንሸታለን እንጂ ሰውነት አጥተናል። እንደ ሰው እንተውናለን እንጂ ባህሪያችን ከአው^ሬ የከፋ ሆኗል። በልብስና በምላስ የተሸፈነው አው^ሬነታችን በተለያዩ ክስተቶች ጥፍሩን ቀስሮ፣ ጥርሱን አግጥጦ ሲወጣ እየታየ ነው። ሁላችንም ሰባኪ ሆነናል። በምናውቃት መስራት ላይ ግን የለንም። እንዲሁ ወሬ ብቻ! ኢላ መታ?! (ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 03/2015) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

Repost from N/a
https://t.me/+2tj_97-rQqFkOGNk አሰላሙ አለይኩም ያጀማአ challenge ተሰጠኝ እናም chalengu join ባደረገ ስለ ሆነ ከላይ ባለው link ገብታችሁ join በሉልኝ በ አላህ 👆👆👆

Repost from N/a
التحذير_من_البدع_ومنها_بدعة_المولد_النبوي_خطبة_جمعة_للشيخ_عبدالله.docx0.49 KB

♦️የገጠር ትዝታ !!! ይህች የፍቅር ጎጆ__!!. የሀገሬ ሽታ ሜዳው ሸንተረሩ፡ የማለዳው ጮራ የፀሀይ ጨረሩ፡ ሜዳና ተራራው ኮረብታው ጠጠሩ፡ ትዝታው መጣብኝ ናፈቀኝ ገጠሩ። ያለምንም ሀፍረት ያለመመሳጠር፡ በንፁህ ህሌና ያለመጠራጠር፡ ፍቅር ከሞላበት መወለድስ ገጠር፡ ከተማ ቪላ ቤት አያስደንቀኝም፡ ባንች ውስጥ ያለውን ፍቅር አላገኝም፡ አውቃለሁ ሔጃለሁ አዝየሽ በልቤ፡ ዛሬም በትዝታሽ አንች ነሽ ቀለቤ፡ አስታውስሻለሁ ራሴን ሰብስቤ፡ ምንም በሸምበቆ ታስራ ብትወደር፡ ባጧ በሰንበሌጥ ቢታታ ቢሰደር፡ የፍቅር ጓዳ ነች የገጠሯ መንደር፡ ምንም ሀብታም ሆነው ቢላ ቤት ቢሰሩም፡ በሊፍት እየወጡ ከፎቅ ላይ ቢኖሩም፡ ፍቅር ከሌላቸው አይደምቁም አያምሩም፡ በደስታ በሀሴት ህይወትን አይመሩም፡ የጭራሮዋን ቤት ያችን የገጠሯን፡ የየዋህነት ምንጭ የፍቅር መንደሯን፡ የጥበብ መፍለቂያ የስነ-መግባሯን።ለ የእውነቷን ምድር ያችን የገጠሯን!! ጠባብ ነች ይሏታል ውስጧ መች ጠበበ፡ እውነተኛ ፍቅር ካፈራ እያበበ፡ እርሱ ወጣ ብሎ ሀላል ከከሰበ፡ እርሷ ተቅዋ ካላት ውስጧ ከተዋበ፡ በደስታ ከኖሩ ሰው ከተሳሰበ፡ ደስታ ካለበት ቤት ፍቅር ያሰፋዋል፡ ምን ውብ ህንፃ ቢሆን ክፋት ያጠበዋል፡ አንተ ትብስ አንች በሚሉት አባባል፡ እንኳን ለሁለት ሰው ለሚስትና ለባል፡ በርካታ ቢሆኑስ ቤት እንደት ይጠባል? ቤተሰብ ቢሆኑ ብዙ ልጆች ወልደው፡ እየተማከሩ በፍቅር ተጋምደው፡ መልካም እየሰሩ አርሰውም ነግደው፡ ይህች ዶርም አትጠብም ከኖሩ ተዋደው፡ በሩቅ ሲያስተውሏት መልኳ ባይማርክም፡ ምንም ብትከፋ ጥላቻን አትሰብክም፡ የገጠሯ ጎጆ ፍቅር አታሾልክም፡ ለዕይታ ብትመስልም ውጯ የኮሰሰ፡ ክዳኗ ሳር ቢሆን ቅጠል የለበሰ፡ ውስጧ ውሀም ቢሆን ዝናብ ያፈሰሰ፡ የፍቅር አዝመራ ምርት ከታፈሰ፡ ምንም ጌጥ ባይኖራት ምንም ባትመችም፡ ጥላቻን አትሰብክም ፍቅር አትሰለችም፡ ከስራ ጋር እንጂ ከፀብ ጋር የለችም፡ ...ገጠርኮ... ሰላም አለው ቤቱ ፍቅር ነው ማደሪያው፡ ጠይቁት ይናገር ግድግዳና ጣሪያው፡ ሰው ገራገር ነው ጎጆው የገዘፈ፡ ማር ነው የሚበላው እየተቀዘፈ፡ በፈገግታ ስቦ ልብ እየዘረፈ፡ ኑሮ ቢከብደውም ፍቅር እየሸረፈ፡ ሰላም አስተምሮ እልፍ እያተረፈ፡ በስንቱ አረመኔ እየተፈረፈ፡ ለበር የታሰበው ሽንቁር ኾኖ ዐረፈ፡ .....ገጠሬ ይችላል...‼️ ሊያጠፉት ሞከሩ ባህልና ወጉን፡ ደጋግመው ፈተኑት ያንን ህዝብ ደጉን፡ ዘግናኝ የሆነ ግፍ ቢፈፅሙበትም፡ አለ በደግነት ክፉ አላረጉትም፡ በገጠሯ መንደር ዘር አይታወቅም፡ ማንም የማንንም ማንነት አይሸርቅም፡ እንብላ እንጠጣ ነው ባህልና ወጉ፡ የገጠሩ ዑመት ፍቅር ነው ማዕረጉ፡ ማንም ዘሩ ታይቶ ከሰው አይለይም፡ እንግዳ ክቡር ነው በቁጣ አይታይም፡ ደሳሳ ብትሆንም ስትታይ ጎጇችን፡ እልፍ ያስተናግዳል ሰፊ ነው ልባችን፡ ኩራት ጋሻችን ነው ገጠሬነታችን፡ እኔን ያሳደገች አስጠልላ እንደ እናት፡ የጭራሮዋ ቤት የገጠር ጎጆ ናት፡ የደስታ የስኬት ከሆነች ኮረጆ፡ አትጠብም ሰፊ ነች ይህች የፍቅር ጎጆ፡ ✍️ኑረዲን አል አረቢ!! t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

ትንሽ ምክር ቢጤ ለዛ ለሙስጦፋ፤ ስሜት በመከተል የወጣው በይፋ፤ በእውቀት አይናገር የያዘው ዘለፋ፤ የመንሀጅ አቋሙ የሆነው ሸፋፋ፤ ቀን በቀን አድስ ነው አቋሙ በድን ላይ፤ ሰውን የሚሳደብ ጃሂሉን #አታላይ፤ ውሸት የሚቀጥፍ በአሊሞቻችን ላይ፤ መረጃ አይቀበል ኪታቦችን አያይ፤ ተው እንጅ ሙስጦፋ አደብንም ተማር፤ ሸይኽ መባል ሸወደህ አየንህ በተግባር፤ #ጀምዕያ ስትል ሳታውቅ በዝርዝር አሁን ደግሞ ጀመርክ ➜ሙስሊሞችን #ማክፈር ምነው ሸይኽ ሙስጦፋ አፍህ ገደብ አጣ፤ ኡለሞቻችን ላይ ድንበርን በማለፍ ፊትህ የገረጣ፤
ተው ባይ የለህም ወይስ አማካሪ፤ በሙስሊም ኡማ ላይ የሆንከው ተክፊሪ፤ አይሰማ የለም ከሙስጦፋ ጉድ፤ በሸይኽ ረቢዕ ላይ ጀመረኮ ንግድ፤ ሸይኽ ረቢዕን መስሎህ ማዋረድ፤ በለመደው አፍህ ጀመርክ መቅደድ፤ አልሰማህምደ ..! እከተላለሁኝ ያልካቸው ኡለሞች፤ በአለም ላይ ያሉ የሱና ኡለሞች፤
ስለ ሸይኽ ረቢዕ የመሰከሩ፤ የቢዳዓ ሰወችን አንገት የሰበሩ፤ የሰለፍያ ረዳት ሙጃሂድ ነበሩ፤ መሰከሩላቸው የሱና ኡለሞች! ኢብኑ ባዝም አሉ ናቸው አህለል ሱና፤ እውቀትም አላቸው አሉ በጥሞና፤ የተከበሩ ናቸው ካሉትም መድና፤ የጀርህ የተዕድል ዶክተርም ነበሩ፤ እስኪ ዝቅ በሉና ኪታቡን ተማሩ፤ ረቢዕ ኢብኑ ሀድ ጀግናችን ነበሩ፤ ከነብያቶች ጋር ያርጋቸው ጀባሩ፤ አላህ ይዘንላቸው! እባክህ ሙስጦፋ ተመለስ ወደ ሀቅ፤ አላህን በመፍራት ነገ ከመጨነቅ፤ ስሜት አትከተል አትሽሽም ከሀቅ፤ ጀነት አትገኝም እንድህ በመቦርቀቅ። ✍  አቡ ማሒራህ

የማለዳ መልእክት (47) ~ ልጅ ትልቅ ሃብት ነው። እንዲያውም ከልጅ በላይ ሀብት የለም። ህንፃ ቢደረደር፣ ሃብት ቢትረፈረፍ ያለ ልጅ ጣእም የለውም። የልጅን ኒዕማ የሚያቃልለው ወይ ህይወት ያለ ልጅ ምን ያክል ባዶ እንደሆነች የሚረዳበት የእድሜ ክልል ላይ ያልደረሰ ነው። ወይ ደግሞ አእምሮው በሌሎች መጥፎ አስተሳሰብ የተበከለ አካል ነው። እንጂ በተትረፈረፈ ሃብት ውስጥ ብትሆን እንኳ ያለ ልጅ ህይወት ጣእም አልባ ናት። የአላህ ነብይ ዘከሪያ የነበራቸውን ስሜት እና የሰጣቸውን ፈረጃ አላህ እንዲህ ሲል ይገልፀዋል:- { وَزَكَرِیَّاۤ إِذۡ نَادَىٰ رَبَّهُۥ رَبِّ لَا تَذَرۡنِی فَرۡدࣰا وَأَنتَ خَیۡرُ ٱلۡوَ ٰ⁠رِثِینَ (89) "ዘከሪያንም፡ 'ጌታዬ ሆይ! ብቻዬን አትተወኝ፡፡ አንተም ከወራሾች ሁሉ በላጭ ነህ' ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡'' فَٱسۡتَجَبۡنَا لَهُۥ وَوَهَبۡنَا لَهُۥ یَحۡیَىٰ وَأَصۡلَحۡنَا لَهُۥ زَوۡجَهُۥۤۚ إِنَّهُمۡ كَانُوا۟ یُسَـٰرِعُونَ فِی ٱلۡخَیۡرَ ٰ⁠تِ وَیَدۡعُونَنَا رَغَبࣰا وَرَهَبࣰاۖ وَكَانُوا۟ لَنَا خَـٰشِعِینَ (90) } "ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ የሕያንም ሰጠነው፡፡ ለእርሱም ሚስቱን አበጀንለት፡፡ እነርሱ በበጎ ሥራዎች የሚቻኮሉ ከጃዮችና ፈሪዎች ሆነው የሚለምኑንም ነበሩ፡፡ ለእኛ ተዋራጆችም ነበሩ፡፡" [አልአንቢያእ፡ 89-90] በርግጥ ትልቁ ነገር እንዲሁ ልጅ መኖሩ ብቻ አይደለም፣ አስተዳደጉ ሲያምር ነው ልጅ የዓይን ማረፊያ፣ የዱንያ ምርኩዝ፣ የኣኺራ ስንቅ የሚሆነው። ስለዚህ ልጆቻችን ከየትኛውም ሃብት በላይ ናቸውና አጥብቀን እንድከምላቸው። ውለዱ፣ ክበዱ። አስተዳደጋቸው ላይ ትኩረት ስጡ። የሌላችሁ አላህ ልጅ ይስጣችሁ። ያልተሰካላችሁ አላህ ስብራታችሁን ጠግኖ በኣኺራ ይካሳችሁ። (ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል አወል 05/1448) = የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

«አብሽር!» 『የሸይኽ ሙሐመድ ሰዒድ ረስላን』   「ሐፊዘሁላህ」 ድንቅ ንግግር፦ «እልሃለሁ፦ "እውነታኛዋ ጥሪ 【ደዕወቱ ሰለፊያ】 ምን ቢዘመትባትም እንኳ ድል የምትቀዳጀው እርሷ ነች። አብሽር! በአላህ እምላለሁ! ይህች የሐቅ ጥሪ ከግድግዳ በስተጀርባ ብትሆን፣ አኸ በጠንካራ ደረቅ ድንጋይ ውስጥም ብትሆን፣ ሰማይንም ሆነ ውሃን የማትመለከት፣ አየርም የማይገባባት ብትሆን፤ የዓለማት ጌታ አላህ የእርሷን መድረስ ከሚፈልገው ደረጃ ድረስ፤ በክቡር ሰው ክብርና በውርደተኛ ሰው ውርደት ያደርሳታል። ከአህለስ-ሱናዎች የሚያደርሰው አላህ ነውና። ታዲያ ሐቅ በባጢል ይዋጋልን?! የሐቅ ሰዎች በሐቅ እንዳይናገሩ መብታቸው ይጨቆናልን?! ወይስ ከተራ ሕዝብ እንዲርቁና ከሰዎች እንዲገለሉ ይደረጋሉን?! «عامي» የሚለው ቃልም ከ‘ዕውርነት’ የተወሰደ ነው። እርሱ እንደማትናገር እንስሳ ነው፤ ነጂዋን እየተከተለች ትሄዳለች፣ ወይም መሪዋን ትከተላለች፤ ወደየት እንደሚሄድም ይሁን የት መሄድ እንደሚሻ አትጠይቅም። ስለዚህ ሐቅን በባጢል አይዋጉትም፤ መረጃና ማስረጃም በማስረጃ እንጂ በሌላ ነገር  መዋጋት አይቻልም። ሰዎችን ከማስረጃ ለማራቅ፣ በማስፈራራት ወይም በማስጠላት ማስረጃን መዋጋት አይቻልም። በመሠረቱ ሐቅን አይዋጉትም፤ ማስረጃም በማስረጃ እንጂ በሌላ አይዋጉትም፤ በመረጃ እንጂ በሌላም አይፋለሙትም። ሐቅን የሚናገርን ሰው መግደል፣ ማባረር፣ ዝም ማሰኘት፣ ንግግሩን ማስቆም፣ ማስፈራራት፣ ማሸበር፣ ወይም ሰዎች ከእርሱ እንዲርቁ ሕዝቡን ማስፈራራት፤ በአላህ እምላለሁ! ይህ ሐቅን መሸፈንና መደበቅ አይችልም። አላህ ከፈለገ በችሎታውና በእዝነቱ የሐቅን ጥሪ በእርግጥም ያስፋፋዋል። እንዲሁም ቃል ገብቷል፦ 《 وَلَیَنصُرَنَّ ٱللَّهُ مَن یَنصُرُهُۥۤۚ 》[سُورَةُ الحَجِّ: ٤٠] «አላህም በእርግጥ እርሱን የሚረዳውን ይረዳዋል።» አላህን ዲኑን በማቆም፣ ወደ መንገዱ በመጥራት፣ መንገዱንና መመሪያውን በመጠበቅ፣ የመልእክተኛውንምﷺ ቀጥተኛ መንገድ በመከተል የሚረዳውን አላህ የረዳዋል። አላህ የረዳውን ማን ሊያሸንፈው ይችላል?! አላህ ያከበረውን ማን ሊያዋርደው ይችላል?! አላህ ከፍ ያደረገውን ማን ሊያወርደው ይችላል?! አላህ ያላቀውን ማን ሊያዋርደው ይችላል?! አላህ መጨረሻችንን እንዲያሳምርልን እንለምነዋለን። = የቴሌግራም ቻናል t.me/Abu_lmran_Alaseriy t.me/Abu_lmran_Alaseriy

‏مات ﺳﻌﻴﺪ ﺑﻦ اﻟﻤﺴﻴﺐ ﻣﻘﺘﻮﻻً.. وﻣﺎت ﺳﻌﻴﺪ ﺑﻦ ﺟﺒﻴﺮ ﻣﻘﻄﻮﻉ ﺍﻟﺮأس.. وﻣﺎت الاﻣﺎﻡ ﺍﻟﺸﺎﻓﻌﻲ ﺑﺴﺒﺐ اﻟﻀﺮب الـعنيف ﺑﺎﻟﻬﺮاوات.. وﻣﺎت ﺳﻔﻴﺎﻥ ﺍﻟﺜﻮﺭﻱ فاراً.. وﻣﺎﺕ ﺍﻟﻄﺒﺮﻱ ﻣﺤﺎﺻﺮاً.. ومات البخاري مهجوراً.. وﻣﺎﺕ ﺍﻟﻨﺴﺎﺋﻲ ﻣﻘﺘﻮﻻً.. وﻣﺎﺕ ﺍﺑﻦ ﺣﺰﻡ ﻣﻄﺎرداً.. وﻣﺎﺕ ﻋﻴﺎﺽ ﻣﺴﻤﻮﻣﺎً.. وﻣﺎت ﺷﻴﺦ ﺍﻹﺳﻼﻡ اﺑﻦ ﺗﻴﻤﻴﻪ ﻣﺴﺠﻮﻧﺎً.. ومات نعيم بن حماد مقيدا، وجر فى قيده، وألقي في حفره، ولم يغسل ولم يصلى عليه.. . هذا ﻫﻮ ﺣﺎﻝ ﺍﻟﻌﻠﻤﺎﺀ! ﻳﺪﻓﻌﻮﻥ أعمارهم ﻣﻦ أﺟﻞ إﻳﺼﺎﻝ ﻛﻠﻤﺔ ﺍﻟﺤﻖ ﻭﺭﺳﺎﻻت اﻟﻠﻪ.. إن الموت في سبيل الحق، لهو عين البقاء.. فماذا قدمت أنت في هذا الطريق؟ . قال الله تعالى : {الم ۝ أَحَسِبَ النَّاسُ أَن يُتْرَكُوا أَن يَقُولُوا آمَنَّا وَهُمْ لَا يُفْتَنُونَ ۝ وَلَقَدْ فَتَنَّا الَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ فَلَيَعْلَمَنَّ اللَّهُ الَّذِينَ صَدَقُوا وَلَيَعْلَمَنَّ الْكَاذِبِينَ ۝ أَمْ حَسِبَ الَّذِينَ يَعْمَلُونَ السَّيِّئَاتِ أَن يَسْبِقُونَا سَاء مَا يَحْكُمُونَ} [العنكبوت].

እጀን አጥብቀህ ያዝክ።አምኘህ ተደገፍኩ። ቁስሌን እረስቸ አዲስ ጉዞ ጀመርኩ። ሁሉን ላንተ ተውኩኝ ሰጠውህ ራሴን። አንተን #ማፍቀር ጀመርኩ ተውኩትና ራሴን።

ወዳጄ_ሆይ! 👉 ሰው ሁሉ ምንም ያህል #ቢክደው የውስጥ ሕመም አለው።እያንዳንዱ ልብ ምንም ያህል #ቢደብቀው የውስጥ ስብራት አለው። ገጽታዎች አያታሉህ። ነገሮች እንደሚመስሉት አይደሉም። በረጋ መንፈሱ የምትቀናበት ያ ሰው፣ በልቡ ውስጥ አላህ እንጂ ማንም የማያውቀው እሳት #እየነደደ ሊሆን ይችላል። ጭስ አለመውጣቱ ሰውየው እየነደደ አይደለም ማለት አይደለም። ወንጀለኛው በወንጀሉ ሰላም የለውም። አላህን የሚፈራውም ያንን ጽናቱን በቀላሉ አላገኘውም። እንዳያጣው ጥርሱን ነክሶ የያዘው አፍቃሪም ሰላም የለውም።በልቡ ውስጥ ያለውን ክፍተት ገና ያልሞላውም ሰላም የለውም። እንደሚባለው"መጽሐፉን በሽፋኑ አትመዝነው!"

➤አንድን ሰው ስለወደድከው ሊወድህ አይችልም! ስለፈለከውም ብቻ ሊፈልግህ አይችልም! ልብህ ንፁህ ያደረክለት ሰው ሁሉ ልቡን ንፁህ ሊያደርግልህ አይችልም! አል-ኢማም ሻፍዒይ ረሂመሁላህ
➤አንድን ሰው ስለወደድከው ሊወድህ አይችልም! ስለፈለከውም ብቻ ሊፈልግህ አይችልም! ልብህ ንፁህ ያደረክለት ሰው ሁሉ ልቡን ንፁህ ሊያደርግልህ አይችልም!                         አል-ኢማም ሻፍዒይ ረሂመሁላህ

«የሀገራችን ኢኽዋኖች ተከታታይ ፅሁፍ»    √ #ክፍል 02 |• «የሱና ዑለማኦች ስለ ኢኽዋን ምን አሉ?» በክፍል አንድ ባሰማሁት የድምፅ ፋይል ሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን «"ኢኽዋን ከአህለሱና ውጭ ነው የሚለው" ትክክል አይደለም። ያው አህለሱና የሆኑት ሊቃውንቶች ከአህለሱና ውጭ እንዳልሆነ አረጋግጠውለታል።» ማለታቸው ይታወሳል። እናም ዛሬ በአላህ ፍቃድ የሱና ዑለማኦች ስለ ኢኽዋን ምን እንዳሉ እንመልከታለን። ከዚያም ሸይኹ  የተናገሩት እውነት ነው ወይስ በሱና ዑለማኦች ላይ፣ ወይ እየዋሹባቸው ወይ ያለ ዕውቀት አየመሰከሩባቸው የሚለውን እናረጋግጣለን። √| ከዚህ በታች በአላህ ፍቃድና እገዛ ታላላቅ የሱና ዑለማኦች ስለ ኢኽዋን የተናገሩትን ለማቅረብ እሞክራለሁ። 1. ታላቁ ኢማም የዘመናችን ሙሐዲሥ ሸይኽ አል-አልባኒ (ረሒመሁላሁ) እንዲህ ይላሉ፦ |√ «ليس صوابا أن يقال إن الإخوان المسلمين هم من أهل السُنة لأنهم يحاربون السُنة» (من شريط فتوى حول جماعة التبليغ والإخوان من تسجيلات منهاج السنة في الرياض) √| «አልኢኽዋን አል-ሙስሊሙን ከአህሉስ-ሱና ወል-ጀማዓ ናቸው ብሎ መናገር ትክክል አይደለም፤ ምክንያቱም እነርሱ ሱናን ይዋጋሉና።» • ይህንን ሊንክ በመጫን ንግግራቸውን ማድመጥ ይቻላል። 14 years ago የተለጠፈ https://youtu.be/d20Zb6JpAAA?si=KcLPeC_Zn2AQ-Sf0 √|| «لا يجوز أن نقول "الخلاف بيننا وبين الإخوان المسلمين فرعي والإخوان المسلمون من أهل السنة" لا!. هم يحاربون أهل السنة ويقولون دعوتكم الآن تفرق. نحن عاشرناهم في سوريا وهنا.» (من أشرطة سلسلة الهدى والنور، الشريط رقم 356.) √|| «"በእኛና በኢኽዋን አልሙስሊሚን መካከል ያለው ልዩነት በፈርዕ (በቅርንጫፍ ጉዳዮች) ላይ ብቻ ነው፣ ኢኽዋን ሙስሊሚንም ከአህሉስ-ሱና ናቸው።" ብሎ መናገር አይፈቀድም። በጭራሽ! (እንዴውም) እነሱ አህለሰሱናን ይቃወማሉ፤ (እኛንም) "ጥሪያችሁ አሁን ሰዎችን ትከፋፍላለችሁ"ም እያሉ ነው። እኛ በሶሪያም እዚህም ከእነርሱ ጋር አብረን ኖረናል።» • ይህንን ሊንክ በመጫን ንግግራቸውን ማድመጥ ይቻላል። 7 years ago የተለጠፈ https://youtu.be/JDLVfowcQBk?si=-fxNGSlEv0IYvvu6 √ ማሳሰቢያ፦ እንደሚታወቀው ኢኽዋን መልከ ብዙና በሸይኹ የህይወት ዘመን የተስፋፋ አንጃ በመሆኑ ሸይኹል አልባኒ ከህይወታቸው መጀመሪያ እስከ ህይወታቸው ፍጻሜ በኢኽዋኖች ላይ ተመሳሳይና አንድ አቋም አልነበራቸውም። ከእርሳቸው የፈትዋ የድምፅ ቅጅዎች እንደምንረዳውና ታሪካቸውን በቅርበት የሚያቁት ዑለማኦች እንደገለፁት ሸይኹ በአንጃው ሦስት መርሐላዎች (ደረጃዎች) ነበራቸው። 1• በመጀመሪያ ደረጃ ሸይኽ አል-አልባኒ ለኢኽዋን አልሙስሊሚን መልካም ግምት ነበራቸው። ምክንያቱም እነዚህ ኢኽዋኖች ቁርአንና ሱናን መከተልን መፈክራቸው ያደርጉ ነበርና። በዚህም የተነሳ እነርሱን ከሱና ውስጥ እንዳሉ ይቆጥሯቸው ነበር። ነገር ግን የዛኔም ቢሆን ከሱና ባያስወጧቸውም ከእነርሱ ይመለከቱ የነበረውን የዓቂዳ ድክመትና ወደተውሒድ ከመጣራት በላይ ለፖለቲካ የሚሰጡትን ትኩረት ይተቹ ነበር። 2• በሁለተኛው ደረጃ ሸይኽ አል-አልባኒ የኢኽዋን መንጋ ፈር መልቀቅ ግልጽ ይሆንላቸው ጀመር። ከዚያም አንዱ ኢኸዋኒይ የሰለፊያን ደዕዋ መተቸት ሲጀምርና “ሰለፊዮች የሚጨነቁት በውጫዊ  ጉዳዮች ብቻ ነው” ብሎ የፃፈው ሲደርሳቸው የሸይኹ ትችት የበለጠ ጠነከረ። እንዲህም አሉ፦ «ما أعتقد أن سلفيًا عقيدةً وسلوكًا بإمكانه أن يتبنى منهج الإخوان المسلمين وأمثالهم» ትርጉሙም፦ “በዓቂዳውም ሆነ በአካሄዱ ሰለፊይ የሆነ ሰው የኢኽዋን ሙስሊሚንንና እንደነሱ ያሉትን መንገድ ሊይዝ ይችላል ብዬ አላምንም።” እናም ሸይኹ የኢኽዋን መንገድ ሰዎች የተለያዩ ዓቂዳዎች ቢኖራቸውም ሁሉንም በአንድ የፖለቲካ ቡድን ውስጥ ለመሰብሰብና ለማደራጀት የሚሞክር መንገድ መሆኑ ግልጽ እየሆነላቸው መጣ። ሆኖም ግን ሸይኹ ኢኽዋንን ከሌሎች ቡድኖች ይልቅ ወደ ሐቅ የቀረቡ እንደሆኑ ይናገሩ ነበር፦ «الإخوان المسلمون هم أقرب الجماعات إلى الحق، لكنهم ليسوا على الحق.» ትርጉሙም፦ “ኢኽዋን አልሙስሊሚን ከቡድኖች ሁሉ ወደ እውነት የቀረቡ ናቸው፤ ነገር ግን እነርሱ በእውነት ላይ አይደሉም።” 3• በመጨረሻው ደረጃ ሸይኽ አል-አልባኒ የኢኽዋን ሙስሊሚንን አቋም በግልጽ መቃወም ጀመሩ። እነርሱ ከሚያስተካክሉት ይልቅ የሚያበላሹት እንደሚበዛ እና ብዙ መሰረታዊ ስህተቶችን ሲመለከቱ እንዲህ ሲሉ የመጨረሻ አቋማቸውን አወጁ፦ «خلافنا مع الإخوان المسلمين خلافٌ في الأصول لا في الفروع فقط.» “ከኢኽዋን አልሙስሊሚን ጋር ያለን ልዩነት በመሠረታዊ ጉዳዮች ነው፤ በቅርንጫፍ ጉዳዮች ብቻ አይደለም።” እንዲሁም ከላይ እንዳሰፈርኩት፦ «ليس صوابًا أن يقال الإخوان المسلمون من أهل السنة، لأنهم يحاربون السنة.» “ኢኽዋን አልሙስሊሚን ከአህሉስ-ሱና ናቸው ማለት ትክክል አይደለም፤ ምክንያቱም ሱናን ይዋጋሉና።” ሲሉ ኢኽዋን ከአህለሱና አመሆናቸውን አረጋግጠዋል። እናም ሸይኹ መጀመሪያ ላይ እነርሱ ቁርአንና ሱናን እንከተላለን ብለው በሚያሳዩት መፈክር ላይ የተመሠረተ መልካም ግምት ነበራቸው። በኋላ ግን የቡድኑ እውነተኛ መንገድና ተግባራዊ ጥመታቸው ሲገለጥላቸው አቋማቸውን እንደቀየሩ ነው ታሪክ የሚነግረን። ስለዚህ የዑለማዎችን ንግግር በታሪካዊና በጊዜያዊ አውዱ መሠረት መረዳት የፍትሕ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የዕውቀታዊ ታማኝነትም ጉዳይ ነው። አንድን የዓሊም ንግግር ከተናገረበት ደረጃና አውድ ነጥሎ ለሌላ ዓላማ መጠቀም ትክክል አይደለም። በዚህ ረገድ  ሸይኽ አሕመድ ሙሐመድ አስሷዲቁ አንነጃር በ blogpot ገፃቸው «موقف الشيخ الأباني من جماعة الإخوان المسلمين» በሚል ርዕስ የለጠፉትን ያንብቡ፦ http://abuasmaa12.blogspot.com/2025/10/blog-post_20.html የሌሎች ዑለማኦችን ንግግር በቀጣይ ክፍል አቀርባለሁ ኢንሻአላህ። √ #ክፍል 01 t.me/Abu_lmran_Alaseriy/3682 = (አቡ ዒምራን፣ ነሃሴ 11/2018) የቴሌግራም ቻናል t.me/Abu_lmran_Alaseriy t.me/Abu_lmran_Alaseriy

ፂሙን በማሳደግ ረሱልንﷺ መከተልና እርሳቸውን መምሰል የተሳነው ሴታሴት የሆነ ፂሙን የሚጋጥጥ የአሕባሽ መንጋ «መውሊድን የማከብረው ነቢዩንﷺ ስለምወዳቸው ነው።» የሚልበትን ሞራል የት እንደሚያገኘው ግን በጣም ይደንቀኛል። ሰው በዚህ ልክ ሀፍረቱን ይሸጣል!? ሱብሓነላህ! = የቴሌግራም ቻናል t.me/Abu_lmran_Alaseriy t.me/Abu_lmran_Alaseriy

ኢህዋንን_በተመለከተ_ኡለማወች_ምን_አሉ_በኡስታዝ_ኸድር.amr4.40 MB

. 🔴 «تأكيد قطبية الدكتور عبدالله الجربوع» ❗️ 🎙 د. عبدالعزيز بن ريس الريس 🔊 [https://youtu.be/BFe3ulZhsms] ═══ ¤❁✿❁¤ ═══ 🔸 ردود سابقــــة 👇 📌 [الجربوع القطبي] https://youtu.be/nSqTKwm2ugM 📌 [التبيين في غلو الجربوع في تكفير المسلمين] https://youtu.be/Hmoz2DAdcj0 . . . . . . .

عدم_تكفير_السلف_للمعين_إلا_بعد_إقامة_الحجة_خلافًا_للحدادية.pdf5.53 KB

...የሚፃፍና የሚነገር ለሚያታልላችሁ የዋሆች... 👅 ....በምላስ ነው ለካ....👅 የመኖርን ጥበብ ጠፍቶ የሚነግረኝ፡ ዙሪያው ገደል ሆኖ ሲያደነጋግረኝ፡ ህይወት የሚቀናው በእጅ መስሎኝ አጉል፡ መዳፌ እስኪመለጥ ሳርም ስጎለጉል፡ መንገድ እየዘጋሁ ስንቱን ሳስተጓጉል፡ ድካም ሆነ ትርፌ ቀረሁኝ ባጓጉል፡ አልደፈን ብሎኝ የኑሮ ቀዳዳ፡ አምሽቼ ስተኛ ስነሳ ማለዳ፡ ስዋትት ስቃትት ላቤ እስከሚቀዳ፡ ስንት ረጂም እቅድ ሳስብ ስከነዳ፡ ተወልጀ አድጌ #ወሎ እሚባል ሀገር፡ መቸም ቀጥታ እንጂ ቶሎ አይገባኝ ነገር፡ ለካ በምላስ ነው እንጀራ እሚጋገር፡ ለተጠጋኝ ሁሉ ስጫዎት ስቀልድ፡ ወንድም ላለኝ ሁሉ ስኳትን ስማልድ፡ ከተደሱ እያልኩኝ ስጋግር ሳቦካ፡ ሁሉንም በኔ ልክ ስመዝን ስለካ፡ ሰው የሚያታልሉት በምላስ ነው ለካ!!👅 የሚወራ ሁሉ አይታመንም ተግባርን እመኑ!! ....ኑር....✍️ t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi