قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
Открыть в Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
БольшеСтрана не указанаКатегория не указана
906
Подписчики
-124 часа
-127 дней
+4430 дней
Архив постов
Repost from N/a
🚨ፈጥኖ ማን ይመልስ ‼️🏃➡️🏃➡️
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው ብዙ ጠቃሚ ኢስላማዊ ቻናሎችን add የሚለውን በመጫን ያገኛል ።
Free promoter👉 @selluhi
👉ጥያቄ፦ ቁርዓን ስንት ምዕራፍ አለው⁉
ኢብራሒም_ኢብኑ_አድሀም ረሒመሁሏህ እንዲህ ብለዋል፦
«እረፍትን የፈለገ ፍጡራንን ከቀልቡ ያውጣ የዛኔ ያርፋል።»
📚 ۞【سيــر السلـف الصالــح【477】۞
Repost from قناة ابن محمد الولوي (abu abdirehman)
📚 አድስ ብስራት ለእውቀት ፈላጊዎች !
🔖 በተለይ በዚህ ጊዜ የተለያዩ ሰለፍያን የሚሞግቱ ብድኖች ከመብዛታቸው ጋ ትክክለኛዋን የሰለፍያ ጎዳና በእውቀት ማወቅ የፈለገ በሱና ኡለማዎች ያዘጋጁቻውን ኪታቦች መማር ያስፈልጋል ።
📚 የሚቀራው ኪታብ
ما هي السلفية ؟
لفضيلة الشيخ عبد الله بن عبد الرحيم البخاري
🎤 የሚያስቀራው አስታዝ ተውፊቅ
🗓 የሚቀራበት ቀን በሳምንት አራት ቀን
ሰኞ ፣ እሮብ ፣ ጁምዓ ና ቅዳሜ
የሙራጀአ ቀን ማክሰኞ ፣ ሀሙስና እሁድ
⏰ ሰዓት ከዒሻ በኃላ በኢትዮ 3:00 ጀምሮ
ነገ ሰኞ ወይም እሮብ ይጀመራል ኢንሻ አላህ
ሸር በማድረግ የኸይር ተካፋይ ይሁኑ !
የሚተላላፍበት ቻናል
t.me/ibnumohammedyimer
t.me/ibnumohammedyimer
Repost from N/a
🧩ብዙ ሙስሊም ወንድምና እህቶች
የሚገኙበት
🪞ልብ የሚነኩ ዲናዊ ምክሮች🥹
◌ ልዩ የሆኑ ዳዓዋዎችን
◍ ቁርዓን እና ሀዲስ የምታገኙበት
◌ ምርጥና ተወዳጅ ቻናል ተጋበዙልኝ🎉
🎈ሙስሊም አይዋሽም ተቀላቀሉ🎈
Repost from N/a
🕌 ቁርአን መቅራትን መልመድ አሳስቦዎታል ⁉️
✨ያለ ማንም አጋዥ እራስዎ ችለው በብቃት እንዲቀሩ ልንረዳዎ ዝግጁ ነን💯
ይህ ታልቅ እድል ሳያመልጥዎ ይመዝገቡ 📥
Repost from ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
የሸሪዓ ትምህርት ለምትማሩ ተማሪዎች፦
1.የምንቀራውን ኪታብ ቃላት ልቅም አድርጎ መያዝ። ከኪታቡ ውስጥ የማናውቀው ቃል ላይኖር።
2.የኪታቡ መልእክት ላይ ትኩረት ማድረግ። መልእክቱን በትክክል መረዳት። ቃላት ለቀማ #ብቻ እንዳይሆን።
3. ማስረጃ ሲጠቀስ ከርእሱ ጋር ያላቸውን ተዛምዶ መለየት። مَحَلَّ الشَّاهِد እና وَجْهُ الاِستِدلال
4. ከደርስ በፊት እና ከደርስ በኋላ ሙራጀዓ ማድረግ። ከጓደኛ ጋር ወይም ለብቻ ሁኖ።
ባጭሩ = የተማርነውን ኪታብ ለሌሎች ማስተላለፍ በሚያስችል አቅም መያዝ ያሰፈልጋል።
~
ከኡስታዝ <<ኢብኑ ሙነወር>> ደርሶች ላይ የተወሰደ።
Repost from ኢስላማዊ ጥያቄ እና መልስ™
♦️♦️♦️ስለመውሊድ ያሉ ሙሓዶራዎች ♦️♦️♦️
◆መውሊድን የተመለከቱ በሡና ኡለማዎች የተደረጉ ሙሓዶራዎችን ለማግኘት ከታች በኩል ይቀላቀሉ
➥የቻናል ባለቤቶች ሸርር አድርጉት ለሁሉም ይድረስ
https://t.me/yedaewachannel/7065
https://t.me/yedaewachannel/7065
Repost from ትዳር እና ኢስላም 🌷🌹🥀
ወንድሜ ሆይ!
ስሜት እና እልህህን ዋጥ አድርገው። ሀቅን እንድትገፋ፣ ባጢልን እንድታነግስ እንዳያደርግህ። ነገ የምትቆጭበት ውሳኔ እንዳያስወስንህም ተጠንቀቅ። መስለሃ እና መፍሰዳን መለየት እንዳትችል እንዳያደርግህ አስተውል።
https://t.me/tdarna_islam
https://t.me/tdarna_islam
➠ላኩላቸው ለእነዚያ
ምንም ያክል ጥሩ ብትሆን በሌላ እንደሚተኩህ አትዘንጋ!
በህይወት ጉዞ ውስጥ ብዙዎቻችን የምንሸወድበት አንድ ትልቅ እውነት አለ፦ «እኔ ከሌለሁ ይህ ነገር አይካሄድም» ወይም «እኔን ማንም ሊተካኝ አይችልም» ብሎ ማሰብ። ነገር ግን እውነታው ጨካኝና ግልጽ ነው፤ በስራ ቦታህ፣ በማህበራዊ ህይወትህ፣ ወይም በየትኛውም መስክ ምንም ያህል ብቁ፣ ታማኝ እና ለየት ያለ ሰው ብትሆንም—አንድ ቀን በሌላ ሰው መተካትህ የማይቀር እውነት ነው።
ይህንን እውነት መረዳት ተስፋ ለመቁረጥ ሳይሆን፣ ህይወትን በትክክለኛው መንገድ ለመምራትና ሚዛንን ለመጠበቅ የሚረዱ በርካታ አስተማሪ ነጥቦችን ይሰጠናል።
1. እራስህን ከአቅም በላይ አታስጨንቅ
ለስራህ ወይም ለሰዎች የምትሰጠው ዋጋ ከፍተኛ ይሁን፤ ነገር ግን ጤናህን፣ ሰላምህንና ደስታህን አሳልፈህ እስከመስጠት ድረስ አትልፋ። ዛሬ ተጨንቀህ ብትታመም ወይም ህይወትህ በፍጹም ብታልፍ፣ ስራህ በሚቀጥለው ሳምንት በሌላ ሰው ይተካል፤ ቤተሰብህና የቅርብ ወዳጆችህ ግን ትክክለኛውን ያንተን ቦታ የሚያካክስ ሰው አያገኙም።
2. ትህትናን ተማርበት
ምንም ያህል ጎበዝ ብትሆን አለም በአንተ ዙሪያ ብቻ አትዞርም። ከአንተ በላይ የሚያውቁ፣ የሚችሉና የሚተኩ ብዙ ሰዎች አሉ። ይህንን ማወቅ በትዕቢት ከመወጠር ያድናል፤ ሁልጊዜም ለመማርና እራስን ለማሻሻል ዝግጁ ያደርጋል።
3. ዋጋህን በሰዎች እውቅና ላይ አታስቀምጥ
ሰዎች ዛሬ ሊያደንቁህና ሊያከብሩህ ይችላሉ፤ ነገ ግን ፍላጎታቸው ወይም ሁኔታዎች ሲቀየሩ በቀላሉ ሊረሱህ ይችላሉ። ስለዚህ የምታደርገውን መልካም ነገር ሁሉ ለአላማህ፣ ለህሊናህና ለፈጣሪህ ብለህ አድርገው እንጂ ከሰዎች ዘላቂ ምስጋናን አትጠብቅ።
4. ለራስህና ለሚወዱህ ሰዎች ቦታ ስጥ
በጣም አስፈላጊው ነገር በስራህ ወይም በሰው ዘንድ የሚኖርህ ቦታ ሳይሆን፣ ከእውነተኛ የህይወት አጋሮችህ፣ ከቤተሰብህና ከራሴህ ጋር የምታሳልፈው ጊዜ ነው። እነዚህ ነገሮች በምንም ሊተኩ የማይችሉ እውነተኛ የህይወት ሀብቶችህ ናቸው።
በማንኛውም ቦታ ያለህን አቅም ሙሉ በሙሉ ተጠቀም፣ መልካም ስራን ስራ፣ አሻራህንም አኑር፤ ነገር ግን ቦታህ ለዘላለም የተጠበቀ እንዳልሆነ በመገንዘብ ለራስህ፣ ለጤናህና ለእውነተኛ የህይወት እሴቶችህ ቅድሚያ መስጠትን አትዘንጋ!
`
https://t.me/BerhanFelega
https://t.me/BerhanFelegaRepost from ስለ ቀልባችን
🎙ቀጥታ ስርጭት ተጀመረ!
● ወንጀል ላደከማት ነፍስ!
https://t.me/Sle_qelbachn1?livestream=1ae6e66a0eee342f69
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
«የሀገራችን ኢኽዋኖች»
በአላህ ፍቃድና እገዛ ከነገ ጀምሮ «የሀገራችን ኢኽዋኖች» በሚል ርዕስ በድምፅ ማስረጃ የታገዘ ተከታታይ ፅሁፍ ይዠ እመጣለሁ ኢንሻአላህ።
=
የቴሌግራም ቻናል
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
➨ንገሯቸው ዛሬም ሐቅ ላይ ነን።
«ክብራችን ይብቃችሁ»
--------------------------
👉 አልሀምዱ ሊላሒ ምስጋና ይገባው፡
👉እንዳይፈርስ አድርጎ ሐቅን ለገነባው፡
👉ውብ ሰለፍዮችን በፍትህ ላተባው፡
👉ከመረጃ ጂረት ከምንጩ ላጠባው፡
👉የአለማት ጌታ ምስጋና ይገባው፡
👉ጭብጨባና አጀባ ወከባ አንፈልግም፡
👉ሐቅ አውቀን ይዘናል አናፈገፍግም፡
👉ወላሒ ሰው ሁሉ ጥሎን ቢከረበት፡
👉የኔ ወንጀል በዝቶ ነውሬም ቢበዛበት፡
👉መንሀጁ ሐቅ ነው እንከንም የለበት፡
👉በስሜት አይደለም ይህንን የምለው፡
👉በአላህ ይሁንብኝ መንሀጄ ገብቶኝ ነው፡
👉ይከፋኛልና ሳስበው ትናንቴን፡
👉አይቸዋለሁኝ ድክመቴን ውድቀቴን፡
👉ጌታዬ አደራውን በሐቅ አርገው ሞቴን፡
👉ስንት ግፍ አይተን ነው ከስንቱ ተፋልመን፡
👉ስንት ፀብ አፍርተን ስንት ዘመን ታመን፡
👉ሰለፍይ ለመሆን ብዙ ጉድ አይተን ነው፡
👉በአቅማችን አውቀን ነው ወደን የጨበጥነው፡
👉ከኛ ላይ ውረዱ ከናንተ አንፈልግም፡
👉ወላሒ ከሐቁ አናፈገፍግም፡
👉የምናምፀውን አላህ ይምረናል፡
👉አሁን የያዝነውን መንገዱን ወደናል፡
👉እሱ ሲነካብን እጂግ ይከፋናል፡
👉መንሀጁን አትንኩት ክብራችን ይብቃችሁ፡
👉ትንሽ የሚያስታውስ አዕምሮ ካላችሁ‼️
👉የማንም መከርበት አያስጨንቀንም፡
👉ቤተሰብ ስንለይ ያኔ አላማተርንም፡
👉ከአባት ጋር ስንሞግት አላፈርንም ያኔ፡
👉ዛሬ ማንም ቢሸሽ አልፈራም ወገኔ‼️
👉ኪታብ አገላብጦ ታሪክ ያነበበ፡
👉በማስተዋል ሆኖ በሁጃ ያበበ፡
👉በንፁህ ህሌና ሐቅን ለቀረበ፡
👉ሀያዕና ፍትህ ሰላም ለደረበ፡
👉ለሰው ልጅ በሙሉ ሰላምን ላሰበ፡
👉አድናቂ አዳማቂ ቂል ላልሰበሰበ፡
👉እውነታው ግልፅ ነው ደፍሮ ላልጀዘበ፡
👉ህይወቱን ለሰዋ ሐላል ለከሰበ፡
አስተዋይ የሆነ!
👉ሰለፍያን መንሀጅ በፍፁም አይ'ከዳም፡
👉ለውሸት ውንጀላ እጁን አይከነዳም፡
👉ደደግሞምን ቢናገር ማንንም አይጎዳም፡
👉የዥዋዥዌ ሰው መቼሜ አይ'ረዳም፡
👉ጀግና ሐቅን ሲይዝ ሁሌም ይከበራል፡
👉የታሪክ መዛግብት ይህን ይናገራል፡
👉ማን ምን እንደሆነ በግልፅ ያስተምራል፡
👉ታዲያ ማንስ በማን ለምን ይሸበራል!?
👉እውነት ያው እውነት ነው እያደር ይበራል፡፡
👉ስንት እየተባሉ ጀግና አባቶቻችን፡
👉ስማቸው አድፎ ውብ ሞደሎቻችን፡
👉ነብዩም ሳይቀሩ ውሸታም ተብለው፡
👉ጠንቋይ ድግምተኛ እያሏቸው ችለው፡
👉የሰላም ሰው ሆነው ስም አብቅለው ሌላ፡
👉ስንት ነገር አልፈው ስንት የወጥመድ ኬላ፡
👉ብዙ ግፍ ነበረ ታሪክ ሲመረመር፡
👉ያለ ዋጋ አይደለም ዲናችን ሲጀመር፡
👉ስንቱን ተጋፍጠዋል አቡ-በክርም ዑመር፡
👉የዑስማን የአልይ ትግላቸው ይደንቃል፡
👉ስንቱ ስንት ሆኗል ግን ይህን ማን ያውቃል!!
👉ምንም ሳንቸኩል ፍፁም ሳንጀረጂር፡
አሏህን ተማምነው ጠብቀው ውብ አጂር፡
👉ስንት ግፍ አይተዋል አንሷርም ሙሀጂር፡
👉ለኛ አድርሰውናል የተውሒዱን ጉዳይ፡
👉አጥብቀን እንጨብጥ ይህን ንፁህ ሙዳይ፡
👉ጠላት ስሙን ያውጣ ያርዳ ለቀባሪ፡
👉#አህባሽም ውሀብይ ካ*ፊር አሸባሪ፡
👉ይበለን ማንም ሰው ስም ይስጠን በገባው፡
👉የመንጋ ፍርደኛው ጫት ቃሚ ገሪባው፡
👉ብቻ ሰለፍያን አይስደቧት የትም፡
👉መንሀጁ ሐቅ ነው ስህተት የለበትም፡
👉ለማንኛውም ግን ጥንትም የሐቅ ሰው፡
👉እውነት ወዳለበት ነው እንጂ እሚነፍሰው፡
👉ከሒዝብዮች ተርታ ምን አልከሰከሰው⁉️
👉ከልብህ ንገረኝ እስኪ ልጠይቅህ!?
👉እንዲህ ነበርክ እንዴ ያኔም እኔ ሳውቅህ!?
👉በዚህ ልክ አድርጎ ከመንሀጅ ያሶጣህ⁉️
👉ከመንሀጀ-ሰለፍ እውነት ግን ምን አጣህ⁉️
👉እስኪ በል ተጠየቅ እስኪ ምን አገኘህ!?
👉አስረዳን ንገረን እንደት ያን ተመኘህ!?
👉የሆኑ ባህሪዎች እንዳሉብህ ባውቅም፡
👉ካንተ ግን ወዳጄ ይህን አልጠብቅም፡
👉ማንም ሔደ መጣ ለማይጨነቁት፡
👉የትም ቢቀመጡ እውነቱን ለሚያውቁት፡
👉ሰውን በመጠኑ ወደው ለሚያልቁት፡
👉በማስመሰል ጥበብ ለማያሳብቁት፡
👉ጌታቸውን ፈርተው በሰው ለማይስቁት፡
👉ሰው ስህተትን ሲመርጥ ዋ ነፍሴ ለሚሉ፡
👉ማስተዋል ጥበብ ጋር ሁሌ ለታደሉ፡
👉ከሐቅ መንሐጅ ላይ ለተደላደሉ፡
👉ከልጅ እስከ አዋቂ ዛሬም ጀግኖች አሉ፡
👉መረጃ ነው ሁሌም የሱንዮች አቅም፡
👉በመንጋ ለሚጎርፍ ለመንጋ ጥርቅም፡
👉ስሜት ለሚያላምጥ ወይም ጫት ለሚቅም፡
👉ወላሒ የምሬን ተጨንቀን አናውቅም።
👉የግለሰብ ፍቅር እጂግ ያሰከረው፡
👉በመንጋ ዳኝነት እልህ የወረረው፡
👉ፍትሀዊ መሆን ሁሌ እሚያስቸግረው፡
👉እንወያይ ሲባል መረጃ እማይደፍረው፡
ከእውነቱ ይልቅ፤
ለቡዲን ስሜቱ የሚቆረቆረው፡
ክፋት ምቀኝነት፤
ጥላቻና ሴራ እጂጉን ያወረው፡
በምን ሞራሉ ነው፤
የሱና ሰዎችን ደፍሮ እሚናገረው⁉️
-----------------------------
👉በመንጋቸው መሐል ፍትህ የማያውቁ፡
👉የመሰላቸውን በጂምላ እሚያደንቁ፡
👉መረጃና ሁጃ ሐቅ የማይጠይቁ፡
👉በግርጭርጭ ፀባይ የሚተዋወቁ፡
👉እናውቃቸዋለን ሀፍረት የላቸውም፡
👉ዛሬ ምንም ቢሉ እኛ አንሰማቸውም፡
👉የስሜት አለቃ የጥላቻ ምንቸት፡
👉የሱና ሰዎችን አይችልም መተቸት፡
👉ሰለፍይ ወጣቶች ሀቅ ያስቀድማሉ፡
👉በየደረሱበት ሽርክ ይፋለማሉ፡
👉አህባሽ ሱፍይ ላይ ሁጃ ያቆማሉ፡
👉አሁንም በቻሉት አቋም አልቀየሩም፡
👉ብሩህ ነው ልባቸው ከሐቅ አልታወሩም፡
👉ሐቅን መስበክ እንጂ፤
ጎትቶ የማምጣት የለብንም ግዳጅ፡
👉ውብ ነው መንሀጃችን፤
ከውጭም ከውስጥም እጂጉን ተወዳጅ፡
👉የተውሒድ የሱና የመንሀጅ ልሳኖች፡
👉በመረጃ ሞጋች የምድር ድሮኖች፡
👉አልሀምዱ ሊላሒ ዛሬም አሉን ጀግኖች፡
👉ማንም ስለመጣ እኛ አናጋንንም፡
👉የማንም ሰው መሔድ አወ አይቀንሰንም፡
👉ማን ምን እንደሚያደርግ አውቀናል ሁሉንም፡
👉እኛን ችግር የለም ስማችንን አጥፉት፡
👉አብሽሩ ግደለም በየትም ለጥፉት፡
👉ሰው አይደሉም በሉ ቲፎዞው ያጨብጭብ፡
👉ያም ከዚህ ይህ ከዚያ ቁራጭ ቃል ይቀንጭብ፡
👉ለክብራችን ብለን አንከራከርም፡
👉በናንተም ላይ ቢሆን ውሸትን አንደፍርም፡
👉አንድ ቃል ብቻ ግን እኔ የምላችሁ፡
👉ትንሽ የሚያስተውል ህሌና ካላቸሁ፡
👉የጎመን-ዘር ታክል ፍትህ ካሰባችሁ፡
👉መንሀጁን አትንኩት ክብራችን ይብቃችሁ‼️
በኑረዲን አል-አረብ
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
👉የሰለፍይ ዑለሞች ታዋቂ ንግግሮች‼️
🩸أشهر كلمة قالها الشيخ الجامي رحمه الله:
🔹«السلفية تبقىٰ»
🩸أشهر كلمة قالها الشيخ مقبل رحمه الله:
🔹الحزبية نار حمراء.
🩸أشهر كلمة قالها الشيخ ربيع رحمه الله:
🔹نتحدىٰ أهل البدع والأهواء.
🩸أشهر كلمة قالها الألباني رحمه الله:
🔹من السياسة ترك السياسة.
🩸أشهر كلمة قالها الشيخ الفوزان حفظه الله:
🔹خُذ النصوص واترك آراء الناس، لكن ستصبح غريباً بين الناس.. فاصبر.
🩸أشهر كلمة قالها الشيخ رسلان حفظه الله:
🔹دعوة الحق مهما حُورِبَتْ فهي منصورة.
من يزيد؟
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
Repost from NABAWI TUBE [ነበዊ ቲዩብ]
«ኢብኑል ጀውዚይ፡- የሱፊያ ክፍሎችን ተግባር አንስተው ባወገዙበት እንዲህ ብለዋል:–
“በየምግቡ ላይ ይቀመጣሉ፡፡ ሲጠግቡ ጊዜ ይደንሳሉ፡፡ … ከመዐቶቻቸው ሁሉ የከፋው መዐት ግን ይህንን (ጭፈራ) መቃረቢያ (ዒባዳ) አድርገው መሞገታቸው ነው፡፡ ዳንስን ወደ ላቀው አላህ መቃረቢያ ነው ብሎ የሞገተ ሰው እንደሚከፍር በርግጥም የዑለማዎች ኢጅማዕ ተቋጥሯል፡፡”
[ሰይዱል ኻጢር፡ 168]
ኢላሂ ምኑን አቅመውት ነው ግን
t.me/NABAWITUBE
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
መውሊድ - በፉክክር የተጀመረ በዓል ነው!
~
መውሊድ ቀደምት የኢስላም ትውልዶች ዘንድ የማይታወቅ መጤ ፈጠራ መሆኑን ራሳቸው የመውሊድ አክባሪ የሆኑ አካላት የመሰከሩትን አሳልፌያለሁ። እነዚሁ አካላት መውሊድ ከክርስቲያኖቹ ገና ተኮርጆ በፉክክር እንደሚከበር የተናገሩቱን ደግሞ እናያለን። ዘግይተው የመጡ አንዳንድ ሱፍዮች ግን “መውሊድ በሀይማኖታችን መረጃዎች መሰረት የተፈቀደ በመሆኑ ላይ ከተግባባን ከክርስቲያን ወይም ከሂንዱ እምነት ጋር ባጋጣሚ ተመሳስሎ ቢገኝ ችግር የለውም” ይላሉ። በሀይማኖታችን መሰረት ቢኖረውማ እነ ኢብኑ ሐጀር “የመውሊድ ተግባር መሰረቱ ቢድዐ ነው። በሶስቱ ክፍለ ዘመናት ከነበሩት መልካም ቀደምቶች ከአንድም አልተላለፈም” አይሉም ነበር።
እያከበሩ ያሉት ሌላ መልክ ያለው ገና ነው። ገና (chrismas) ማለት ልደት ማለት ነው። ልደት ማለት ደግሞ በዐረብኛው መውሊድ ማለት ነው። ስለዚህ የሚከበረው ማንነት እንጂ የተለየው የሚያከብሩት ገናን ነው።
የክርስቲያኖች ገና = የሱፍዮች መውሊድ!
የክርስቲያኖች መውሊድ = የሱፍዮች ገና!
እንዲያውም መውሊድን የሚያከብሩት ከክርስቲያኖች ጋር ለመፎካከር ብለው ነው። የፉክክር ዒባዳ ማለት ነው! ይህንን ሐቅ በኪታብ ሳይቀር ያሰፈሩት አሉ። መረጃ እጠቅሳለሁ፡-
1. አስ-ሰኻዊይ ምን እንደሚል ተመልከቱ፡- “ባለ መስቀሎቹ (ክርስቲያኖች) የነብያቸውን ልደት ትልቁ ዒዳቸው አድርገው የሚይዙ ከሆነ ሙስሊሞችም (ነብያቸውን) በማክበርና በማላቅ ይበልጥ የተገቡ ናቸው።” [አት-ቲብሩል መስቡክ፡ 14]
2. ከጀዘሪም ቃል በቃል ተላልፏል።
3. አቡል ዐባስ አል-አዘፊይ (መውሊድን ለምዕራቡ ዐረቢያ ያስተዋወቀ ነው)፡- በክርስቲያን በዓላት ላይ የሚሳተፉ ወጣቶችን ለመመለስ ሲል እንደጀመረው በግልፅ ተናግሯል።
4. ዐብዱላህ አልሀረሪይ (የአሕባሾቹ መሪ):- ንጉስ ሙዞፈር መውሊድን የጀመረው ክርስቲያኖች የመሲሕ ልደትን በዓል ሲያከብሩ ተመልክቶ ነው። በዚህም ሳቢያ ሰይዳችንን ሙሐመድን ﷺ ስላወጣልን አላህን ለማመስገን ሲል መውሊድን ጀመረ ይላል። [ኢዝሃሩል ዐቂደቲ ሱንኒያህ፡ 240]
ስለዚህ የመውሊድ ቢድዐን በፉክክር የተለከፉ ሰዎች የፈጠሩት መጤ ፈሊጥ ነው ማለት ነው። በዚህ መልኩ በሌሎች መመሳሰል ደግሞ የተወገዘ እንደሆነ ነብያችን ﷺ አጥብቀው አሳስበዋል።
* ማስረጃ አንድ፦
مَنْ تَشَبَّهَ بِقَوْمٍ فَهُوَ مِنْهُمْ
"አንድን ሕዝብ የተመሳሰለ (የተከተለ) ከእነርሱ ነው (እንደነርሱ ይቆጠራል)።" [አቡ ዳውድ ፡ 4031]
* ማስረጃ ሁለት፦
በሌላም ሐዲሥ ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
لتتَّبعنَّ سَننَ من كانَ قبلَكم حذو القُذَّةِ بالقُذَّةِ حتَّى لو دخلوا جحرَ ضبٍّ لدخلتُموه. قالوا: اليَهودُ والنَّصارى؟ قالَ: فمَن
“በርግጥ ከናንተ በፊት የነበሩ ሰዎችን ፈለጎች ስንዝር በስንዝር ክንድ በክንድ ትከተላላችሁ። የወከሎ ጉድጓድ ቢገቡ እንኳን በርግጥም ትገቡታላችሁ!” ሲሉ “አይሁድና ክርስቲያኖችን ነው (ትከተላላችሁ) የምትለን?” ብለው ቢጠይቁ “ታዲያ ማንን ነው?!” አሉ። [ቡኻሪይ፡ 7320]
የተናገሩት በትክክል ተፈፀመ። ለብዙ ጥፋቶች የሚያጋልጠው በዓል ከክርስቲያኖች ተኮርጆ በ"ፋጢሚያ" ሺዐዎች ተጠንስሶ፣ በሱፍዮች ተዛምቶ ብዙ ሙስሊም ሊዘፈቅበት በቅቷል።
የሚያሳፍረው “ክርስቲያኖቹ የነብያቸውን ልደት እያከበሩ የኛ ነብይ ከማን ያንሳሉ?” የሚሉት ነገር ነው። ሱብሓነላህ! ለመሆኑ ዒሳ የኢስላም ነብይ አይደሉም እንዴ?! ታዲያ ይሄ ምን የሚሉት አፀያፊ ሎጂክ ነው? ደግሞ ምንም ሳያፍሩ መውሊድን የሚቃወሙ ሙስሊሞችን “የነቢ ጠላቶች ናቸው!” እያሉ ከባድ ክስ ይከሳሉ። የነብዩን ﷺ መውሊድ አለማክበር እሳቸውን መጥላት ከሆነ እናንተም የክርስቲያኖቹን ገና (chrismasን) ባለማክበራችሁ የዒሳ ጠላቶች ናችሁ ማለት ነው። መውሊድን ማክበር ነብዩን ﷺ ማክበር ከሆነ የሌሎቹን ነብያት ልደቶች ስለማታከብሩ ለሌሎች ነብያት በሙሉ ክብር የሌላችሁ የነብያት ጠላቶች ናችሁ ማለት ነው። ከአንደበታችሁ በቀጥታ ባይወጣም አመክኗችሁ የሚሰጠው ይህንን ነው።
አንዳንዶች "ገናን የማናከብረው የዒሳን ልደት ስለማናውቅ ነው" ይላሉ። የነብያችንም ﷺ የውልደት በየትኛው የረቢዕ ቀን ላይ እንደሆነ የሚያሳይ ሶሒሕ ማስረጃ የለም። በ12ኛው ቀን ነው የሚለው የሰነድ መቆረጥ እንዳለበት ኢብኑ ከሢር ገልፀዋል። [አልቢዳያ ወንኒሃያ፡ 3/109]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
