cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

ዳዕዋ ሰለፍያ በአርባ ምንጭ AMUጫሞ ካምፓስ ሃቅን ፍለጋ ከቁርዓንንና ከትክክለኛ ሃድስ በነዚያ ደጋግ ቀደምቶች ( በሰለፉነ–ሷሊሂን) አረዳድ ! "ከሃቅ በሗላ ጥሜት እንጅ ምን አለ! ? " ስለዚህ ሃቅን ብቻ ተከተል ! ማሳሰቢያ: –ለማንኛውም አስተያየትዎ ከታች ባለው ቦት ያስቀምጡልን ጀዛኩሙላህ ኸይር @JemalEndroAbuMeryem

Больше
Рекламные посты
2 366
Подписчики
Нет данных24 часа
-27 дней
-2030 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

የፈለጋችሁትን የስልክ አይነት ፣ ኤርፎን ፣ ፍላሾች ፣ ቻርጀሮች ፣ የፈለጋችሁት አይነት የስልክ አክሰሰሪዎች ፣ እስፒከሮች  ካላችሁበት ሆናችሁ ማዘዝ ትችላላችሁ ኢንሻ አላህ በታማኝነት ያላችሁበት ድረስ  እናደርስላቹሀለን   Phone 📲 0947778381                   Muhammed fedlu             ወይም በቴሌግራም አድራሻችን           👉@AbuNuhibnufedlu ማዘዝ ትችላላችሁ   ወደ ግሩፓችን ጆይን በማለት ጎራ በሉ👇    ፦  t.me/MohammedOnlineBisness
Показать все...
ማስታወቂያ ~ የክረምት ተመላላሽ ኮርስ ለልጆችዎ! እድሜያቸው ከ 7 አመት በላይ ለሆኑ ወንድ እና ሴቶች *) ከሰኞ እስከ ሀሙስ ከ 2:30 እስከ 10:00 *) ቅዳሜ ከ 2:30 እስከ 6:30 የሚሰጡት ትምህርቶች *)ቁርኣን *) አቂዳ *) ተርቢያ *) ሀዲስ አካባቢያቸው ጦርሃይሎች፣ የሺ ደበሌ፣ ቀራኒዬ፣ አንፎ፣ አለም ባንክ፣ ቤተል የሆኑ ይበልጥ ይጠቀማሉ። አድራሻ = ቀራኒዮ፣ ሑዘይፋ መስጂድ ምዝገባ:- ስልክ ቁጥር  0912898155 telegram User name  @Huzeyfaibnulyeman
Показать все...
ማስታወቂያ ~ መርከዘ ተውሒድ ኢንሻ አላህ በዚህ አመት ክረምት ለሴቶች ቁርኣንን ጨምሮ የመሰረታዊ ትምህርት በአዳሪ ፕሮግራም አዘጋጅቷል። እድሜያቸው ከ 13 በላይ የሆኑ ልጆች ማስመዝገብ የምትሹ በዚህ ቁጥር ልታናግሩን ትችላላችሁ :- 096 046 1624 ከአላህ በታች የሚገባውን ጥንቃቄ እና ሀላፍትና እንወስዳለን። ወንድሞቻችሁ ሳዳት ከማል እና ኢብኑ ሙነወር በቴሌግራም መልእክት ለመላክ https://t.me/SadatAbuIbrahim
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
🚫ለእህቶች ጥንቃቄ የሚሻ ወሳኝ ማሰጠንቀቂያ! ረሱል (▫️) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿لَا تُبَاشِرِ الْمَرْأَةُ الْمَرْأَةَ فَتَنْعَتَهَا لِزَوْجِهَا كَأَنَّهُ يَنْظُرُ إِلَيْهَا﴾ “አንዲት ሴት የሌላኛውን ሴት ሰውነት አትንካ (አትዳብስ) በመንካቷ ምክንያት የተመለከተችውን ውበትም ለባሏ አትንገር። ወደሷ ሊመለከት ይችላልና።” 📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 5240 📌ጥቂት ማብራሪያ፦ ሴትን ሴት አትንካ ሲባል መከለያ በሌለበት ወደ ሁሉ ሰውነቷ አትመልከት፣ አካላቷንም አትዳብስ፣ በሷ ላይ የተመለከተችውንም ማራኪ የሆነ የሰውነት ውበት ለባሏ አትግለፅ፤ ይሄ በሚሆን ግዜ ባልየው ልቡ ይሸፍታል እሷን ለማየትም በውስጡ ፍላጎት ያሳዳራል ለማለት ነው። አላሁ አዕለም!! ✅በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦ ✉️፦ https://bit.ly/4ayf0xJ 📞፦ https://bit.ly/486xnrS ✉️፦ https://bit.ly/41zEZkk 📷፦ https://bit.ly/4arMbTx ❌፦ https://bit.ly/41tIUPv 📹፦ https://bit.ly/3UTTSwh
Показать все...
የማንቂያ ደወል ! 🚠🚷❌ 🚫  እህቶችን መሰረት ያደረገ የሿሿ ጥቃት       ሿሿ ማለት የሚታወቀው በአንድ ሚኒ ባስ ታክሲ ላይ ከስብእና የወጡ ሴቶች የሽማግሌ ቀላሎችና ወሮበላ ወጣቶች ተሰባስበው የሶስት ሰው ቦታ ከፊት ከመሀልና ኋላ ክፍት አድርገው ከተሳፋሪ ውስጥ የሚፈልጉትን ሲያገኙ አንድ ሰው ብቻ ብለው ያስገባሉ ። በክብር ቦታ የተለቀቀለት በማስመሰል የሚፈልጉት ቦታ እንዲቀመጥ ይደረጋል ። ያ ቦታ ማለት የተዋጣለት ፈታሽ የተዘጋጀበት ቦታ ነው ። ፈታሹ ስራውን ሲጀምር ውስጥ ያለው የውርጋጦች ስብስብ ረብሻ ይፈጥራል ። ሹፌሩ መኪናውን የሚገለብጠው ይመስላል ። በዚህ መሀል ግራ በመጋባት ምን እንደተፈጠረ ሳይገባው በፍተሻው የተራቆተው እንግዳ ተሳፋሪ እንዲወርድ ይደረጋል ። ወደራሱ ሳይመለስ ግራ እንደተጋባ ቆሞ ታክሲውን ያያል ። ታክሲው ትቶት ይፈተለካል ።   ወደራሱ ሲመለስና ኪሱን ሲፈትሽ ተራቁቷል ። ለመደወል ስልክ የለም ለመሳፈር ሳንቲም የለም ። የዚህን ጊዜ ነው የድራማው ሚስጢር የሚገባው ። ይህ ነው ከዚህ በፊት በሿሿ የሚታወቀው ።      የአሁኑ ሿሿ የረቀቀና ከውጭ የመጡ ወይም የውጭ ሀገር እድል ያገኙ እህቶችን መሰረት ያደረገ ነው ። በአብዛኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አካባቢና እንዲሁም ኤምባሲዎች አካባቢ ነው የወጥመዱ አካባቢዮች ።     ይህን በድራማ መልኩ የሚሰራ ትእይንተ ዘረፋ የሚያካሄዱ ዋልጌዎች በተቀናጀ መልኩ ስፍራ ስፍራቸውን ይይዛሉ ። በቅርብ ርቀት ቦታና የስራ ድርሻ ይመዳደባሉ ። የተንጣለለ ጊቢ ተከራይተው ለእኩይ ተግባራቸው ያዘጋጃሉ ።      በአብዛኛው ሒጃብ የለበሱ ሴቶችና ፂም ያስረዘሙ ሱሪ ያሳጠሩ ኮፍያ ያጠለቁ የሙስሊም ገፀባህሪ ተደርገው የተዘጋጁ የድራማው ተሳታፊ ይሆናሉ ። በዚህም በቀላሉ የሙስሊም እህቶችን ዐይን ይስባሉ ።      ከቀረጥ ነፃ ወረቀት ውክልና ሰጥተው ለማረጋገጥ ወደ ውጪ ጉዳይ የሚሄዱ , የጋብቻ ወይም የልደት አሊያም የትምህርት ማስረጃ ለማረጋገጥም ወደዚያ የሚያመሩ እህቶች በተለይ ከተማውን የማያውቁ ከሆኑ ቶሎ ይታወቃሉ ። ወዲያው በእነዚያ በተዘረጋ ሰንሰለት አቀባበል ይደረግላቸዋል ።       ሙስሊሞች ከሆኑ በባለ ሒጃቧ ወዴት ነው ?  ተብለው ይጠየቃሉ ያለ ምንም መጠራጠር ለምን ጉዳይ ወዴት መሄድ እንደሚፈልጉ ይናገራሉ ። እኔም ወደዛው ነኝ አብረን እንሄዳለን ይባላሉ ።  ጉዞ ይጀመራል ። ከደቂቃ በኋላ መኪና ይዞ የቆመ የሰንሰለቱ ተዋናይ ጋር ይደርሳሉ ።  ባለ ሂጃቧ ውጪ ጉዳይ በየት በኩል ነበር የሚያስገባው ?  ብላ ትጠይቃለች ። ተዋናዩም ግቡ ላድርሳችሁ ይላል ። ወደ ትወናው ቢሮ ጊቢ አድርሶ ያው ብሎ አውርዶ ይሄዳል ። በድራማው የተመለመሉ የወንድና ሴት ጥበቃዎች የት ነበር ብለው ይጠይቃሉ ይነገራቸዋል ።      እዚህ ጋር የሚሰራውን ድራማ ለመረዳት ወደ ተለያዩ በጣም ጥብቅ የሆኑ የመንግስት ተቋማት ሲገባ ያለውን ሁኔታ ላስታውሳችሁ ።      እንደ ሰላም ሚኒስቴር ፣ ደህንነትና መረጃ ፣ ኤር ፖርትና የመሳሰሉ ቦታዎች ሲገባ አንድ ሰው ወንድም ይሁን ሴት ወደ ውስጥ ለማለፍ ፍተሻ አልፎ ነው የሚገባው ። ፍተሻው ጋር ኤክስሬ ማሽን አለ ። ማንም ሰው በእጁም በኪሱም የያዘውን ማንኛውንም ብረት ነክ ነገር እንደ ሰአት ፣ ቁልፍ ጌጣጌጥ ፣ ቀበቶም ጭምር አውጥቶ በማሽኑ እንዲያልፍ አድርጎ ራሱም በሌላ ፈታሽ ማሽን አልፎ ይሄድና ያ በማሽን እንዲያልፍ ያደረገውን ንብረቱን ይወስዳል ። ከዚህ በኋላ ወደ መስሪያ ቤቱ ቢሮ ያመራል ።      ይህ ታዲያ እነዚህ ድራማ ሰሪዮች እንዴት እንደሚጠቀሙበት እንይ : – ይህች ድራማ የሚሰራባት ምስኪን እህት በእነዚህ ተልእኮ በተሰጣቸው ሴት ፈታሾች ምንም ብረት ነክ ነገር ይዞ መግባት አይፈቀድም ስለዚህ ሰአት ፣ ሞባይል ፣ ጌጣ ጌጦችን በሙሉ አውጥተሽ በቦርሳሽ ውስጥ አድርጊ ትባላለች ። ምስኪኗ እህትም የተባሉትን በሙሉ በቦርሳው ውስጥ ያለውን ብርም ጭምር ታስረክባለች ። ምናልባት ፓስፖርትና የሚረጋገጠው ወረቀት ቦርሳው ውስጥ ካለ በፓስፖርቱ ውስጥ መቶ ብር ተደርጎ ይሰጣታል ። ወደ ተባለው ቢሮ ስትገባ ማንም የለም ትንሽ ቆዪ ይመጣሉ ትባላለች ። ይሁን እንጂ የሚመጣ የለም ለመጠየቅ ስትወጣ ዘበኛው ተቀይሮ ሌላ ነው ።  ስትጠይቀው ቢሮ ገና ሰው ያልገባበት ባዶ ነው ። የምን የውጪ ጉዳይ ነው እንዲህ የሚብል ነገር አላቅም ይላል ። ‼      ኤምባሲ ከሆነ ድራማ ሰሪዮቹ በታክሲ ወደ ኤንባሲ የመጡ እህቶችን አዛኝ መስለው ኤምባሲው ከዚህ ለቋል ተብለን ነው ኑ ወደ አዲሱ ቢሮ አብረን እንሄዳለን በማለት የተለመደውን ድራማ ይሰራሉ ። ሴቶችን መሰረት ያደረገው ሿሿ ይህን ይመስላልና እህቶች ራሳችሁን ጠብቁ ።     ወጪ ለመቀነስ ብላችሁ በታክሲ ከመሳፈር በሚታወቁ ታማኝ ራይዶች ሄዳችሁ ጉዳያችሁን ፈፅማችሁ በሰላም ተመልሳችሁ ተመጣጣኝ ዋጋ ብትከፍሉ ከአስደንጋጭ ዘረፋ ትድናላችሁና ለማንኛውም ተጠንቀቁ ።           copy!
Показать все...
👍 3
ወቅታዊ ሙሓደራ ርዕስ አያመተሽሪቅ የመብል እና የመጠጥ አላህን የማስታወሻ ጊዜ❜ 🎙በኡስታዝ አቡ ሓቲም ኸድር አሕመድ አል-ኸሚሴ «ሐፊዘሁሏህ» ⌲ T.me/Ustaz_Kedir_ahmed_2
Показать все...
ሙሓደራ_156_አያመተ1.47 MB
መኖርህ እዳ አይሁን! ላንተ ነው! “ቀለም ለገባህ”! ~~ 1. አንተ ልዩ አይደለህም ሙስሊሙ፤ እንደ ማህበረሰብ ሰቅዘው የያዙት ብዙ አይይነት ችግሮች እንዳሉበት ግልፅ ነው። በኛ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አለማት ኢኮኖሚው የደቀቀ፣ ማህበራዊ ህይወቱ የተናጋ፣ ፖለቲካዊ ስርኣቱና ሚናው የወረደ፣... ብዙ ሙስሊም ማህበረሰብ አለ። ችግሩን ‘ፍሬም’ በማድረግና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ላይ ሃሳቦች ሊለያዩ ቢችሉም ይህን እውነታ በመረዳት አንተ ብቸኛ አይደለህም። እራስህን ከማህበረሰቡ አንዱ እንጂ ልዩ አድርገህ አትሳል። ሙስሊሙ ኡማ ውስጥ የተማረው የቀለለ ከመሆኑ ጋር የተማርከውን የተማሩ፣ የምትረዳውን የሚረዱ ብዙ እንዳሉ አትዘንጋ። ይህንን እውነት ለነፍስህ ሹክ በላት። “ብርቅየ አይደለሽም” በላት። ያኔ እብጠቷ ይተነፍሳል። መንጠራራቷ ይቀንሳል። 2. የደዕዋው ዘርፍ የመፍትሄዎቻችን ሁሉ እናት ነው ቀዳዳዎቻችን ብዙ ናቸው። በዚያው መጠን ዘርፈ ብዙ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ያስፈልጉናል። በሆነች ዘርፍ ላይ ትንሽ አስተዋፅኦ ስለኖረችህ ለሌሎች በተለይም ለደዕዋው ዘርፍ ያለህ እይታ አይንሸዋረር። ለደዕዋው ዘርፍ ያለህ አክብሮት ለኢስላምህ ያለህ አክብሮት ነው። የደዕዋውን ዘርፍ ሳታከብር ለኢስላም አክብሮት ሊኖርህ አይቻልም። ኢስላም ያለ ደዕዋ ምንም ነው። አዎ በደዕዋው ዘርፍ ላይ ብዙ ችግሮች አሉ። ግና “ችግሩ የሚፈታው በማነው?” ብለህ እራስህን ጠይቅ። አንተ ለዚህ ብቃቱ አለህ? የተማርከው ትምህርት ለዚህ የሚያበቃህ ነው? የእውነት አካደሚ ስለተማርክ ብቻ ያለውን መሰረታዊ ችግር የምታውቀው ይመስልሃል? እንዴት ሆኖ?! 3. አንጃዎችን መኮነን ከአንጃ ውጭ አያደርግህም ብዙ የተማሩ ወንድሞች አንጃዎችን ስላወገዙ ብቻ ገለልተኛ የሚሆኑ ይመስላቸዋል። ነገሮችን በዚህ መጠን መረዳት ሲበዛ ግልብነት ነው። በቅድሚያ ገለልተኝነትህ ከሐቅም ሊሆን ስለሚችል ጉዳዩን ከልብ መርምር። ጉዳዩን ቀርበው ሳይመረምሩ ሁሉንም በጭፍንና በጅምላ ማውገዝ በስንፍና ውስጥ ማድፈጥ እንጂ ልዩነትን መፀየፍ አይደለም። ይህንን ለማድረግ አቅምና ፍላጎቱ ከሌለህ ዝምታን ማን ያዘብህ? ምላስህንም ብእርህንም ከንዲህ አይነቱ ጉዳይ ሰብስበህ በምትችለው ሙያ ወገንህን አገልግል። በአደብህ ተከበር። የማትችለውን ገብቼ አቦካለሁ ስትል፣ በምትችለው ዘርፍ ልታበረክተው የምትችለውን አስተዋፅኦ ታመነምነዋለህ። ልንገርህ ወዳጄ! የሆኑ የሚፋጩ አካላትን ስላየህ፣ የሚወረወሯቸውን ቃላት ስለሰማህ ብቻ ስለጉዳዩ ያለህን መረዳት በዚያ መጠን አቅልለህ አትመልከት። እንዲህ አይነቱ ጥራዝ ነጠቅ ድምዳሜ ነው አንዳንዶችን በመሰረታዊ የኢስላም ክፍል ላይ እንዲሳለቁ እየገፋቸው ያለው። ሳይረዱ እንደተረዱ ማሰብ። እንዲያውም የአንዳንዶቹ ገለልተኝነት ከማስመሰል የዘለለ አይደለም። ክስተቶችን እየጠበቁ ለይተው ሲያጠቁ፣ ለይተው ደግሞ ሲያደንቁ ታገኛቸዋለህ። “የአይነላህ ተቆርቋሪዎች” እያለ በነብዩ ﷺ ሐዲሥ ላይ የሚያሾፍ ሰው፣ “ተው” እና “ሂድ” እያለ በተውሒድ ላይ የሚሳለቅ ሰው በየትኛው ሞራሉ ነው ስለ ገለልተኝነት የሚያደነቁረን? ለኡማው መትረፉ ቀርቶ እራሱን ባዳነ! 4. ይልቅ ለኡማው ሸክም አትሁን! እራስህን ብቻ ሁን! ሁለት እግር አለኝ ብሎ ሁለት ዛፍ ላይ አይወጣም። ማኔጅመንት ወይም ፖለቲካ ተምረህ የደዕዋ ስልጠና ካልሰጠሁ አትበል። በዱዓት ላይ መዘባነንህን አቁም። ፖለቲካ ብትደሰኩርም፣ ታሪክ ብትተርክም፣ መድረክ ብታደምቅም ዋጋ የሚኖረው ለተውሒድ በሚኖርህ ክብር ነው። አክብሮቱ ቀርቶ ሸክም የምትሆን ከሆነ የትኛውም ያንተ አበርክቶ ገለባ ነው። ተውሒድና ሺርክን የማትለይ፣ በተውሒድ ላይ እየተሳለቅክ ለቀብር አምልኮ የምትወግን ከሆነ፣ ወይም ደግሞ በገለልተኝነት ስም ተውሒድንም ሺርክንም እኩል የምታወግዝ ከሆነ እውነቴን ነው የምልህ ከመኖርህ አለመኖርህ የሚሻል ለመባል እንኳን አትመጥንም። እንዲያውም ለሙስሊሙ ኡማ ከጠላት የከፋ እዳ ነህ። 5. ከ“ንቃትህ” ንቃ! መንቃት ማለት እንግሊዝኛ እየቀላቀሉ ማውራት አይደለም። መንቃት ማለት በግምት የታጨቀ የሴራ ፖለቲካ መፈትፈት አይደለም። መንቃት ማለት የራስን እያናናቁ በፈረንጅ ፍልስፍና ላይ መራቀቅ አይደለም። መንቃት እራስን ማወቅ ነው። መንቃት የማህበረሰብን መሰረታዊ ችግር መለየት ነው። ተውሒድና ሺርክን የማትለይ፣ የወገንህ የሙታን አምልኮ ላይ መነከር የማይቆጠቁጥህ ከሆነ እንኳን ለሰው ልትተርፍ ለራስህ አንቂ ያስፈልግሃል። ደግሞም እወቅ! ይሄ ሌሎችን ማናናቅና እራስን መቆለል የጀርባ መንሴው ለዘመናዊ ትምህርት ያለህን የተንሸዋረረ እይታ ነው የሚያጋልጠው። ትምህርቱ አስፈላጊ እንደሆነ የሚያከራክር አይደለም። ህዝበ ሙስሊሙ ባለመማሩ የደረሰብት ውስብስብ ችግር እንዳለ የሚዘነጋ አይደለም። ቢሆንም በልክ አድርገው። የቀለም ትምህርት ከዲን ትምህርት፣ እንግሊዝኛ ከዐረብኛ፣ የነ ዑመር፣ የነ ሙዓዊያ ታሪክ፣ ከነ ሶቅራጠስ ሊነፃፀር አይችልም። በቅድሚያ እራስህን ከአስተሳሰብ ተፅእኖ ነፃ አውጣ! እነ ፍሮይድና ማስሎውን እያደነቅክ ዑለማዎችን የምትንቅ ከሆነ ብሽቅነትህን ብቻ ነው የምታሳየው። “የፋርስና የሮማ ፈላስፎች ጥበብ ላይ የሚያተኩር ለኢስላማዊ ጥበብና ስርኣት ልቡ ውስጥ ቦታ አይኖርም” ይላሉ ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ። [አልኢቅቲዷእ፡ 217] 6. ሚናህን ለይ! ዱዓት መሃል ብዙ ችግሮች እንዳሉ የሚታወቅ ነው። የምታየው ቢያምህ ሰውኛ ስሜት ነው። ሃሳብ ካለህ ዲኑ ያንተም ነውና እርምትና ሃሳብ መስጠት ያባት ነው። ችግር የሚመጣው ያልገባህን እያወራህ የእብድ ገላጋይ ስትሆን ነው። ወይ ዲንህን ተማር! ወይ ሃሳብህ የተመጠነ ይሁን። ባቅምህ ልክ ብቻ አውራ። ቀይ መስመር አትለፍ። ማኔጅመንት ተምረህ ቀዶ ጥገና ህክምና ካላደረግኩ ትላለህ እንዴ? ሳይኮሎጂ ላይ እድሜህን ፈጅተህ ተፍሲር ካላስተማርኩ ይባላል ወይ? ልክ ሃያ ሰላሳ አመት እድሜህን የቀለም ትምህርት ላይ ስለፈጀህ ብቻ ይሄ ነው የሚባል ትኩረት ባልሰጠኸው እምነት ላይ ፈራጅ ቀዳጅ ካልሆንኩ አይባልም። በቃ አቅምህንና ተሰጥኦህን ለይ! የግድ ስለ ሁሉም ማውራት አይጠበቅብህም። 7. ስለ ዲንህ ተማር በቀለም ትምህርት ላይ መራቀቅ እንደምትሻው ሁሉ ለዲናዊ ትምህርትም ጊዜ ስጥ። ከምንም በላይ የዚያኛውን አለም ስንቅ ታዘጋጅበታለህ። በመተጓዳኝ የራስህን ጨምሮ የወገንህን ችግርና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ትለይበታለህ። በርግጠኝነት ነገሮችን የምትመለከትበት መነፅርም ይቀየራል። በተለይም ደግሞ መሰረታዊ የእምነትህን ክፍል ተውሒድን ተማር። አካደሚ ስለተማክ ብቻ ከሺርክ የምትርቅ ከመሰለህ ሞኝ ነህ ወላህ! በአለም ላይ ቁራጥራጭ እንጨቶችን፣ ያሸበረቁ ስዕሎችን፣ ላሞችን፣ አይጦችን፣ በሰው ልጅ ብልት አምሳል የተቀረፁ ሀውልቶችን የሚያመልኩ ህልቆ መሳፍርት ዶክተሮች፣ ፕሮፌሰሮች አሉ። የተማሩት ትምህርት፣ የሚቀናጡበት ቴክኖሎጂ፣ የተቆናጠጡት ስልጣን፣ የሚያጋብሱት ሀብት ግኡዛንና እንስሳትን ከማምለክ አላወጣቸውም። ብልህ በሌሎች ይማራል። ሞኝ በራሱ ላይ በሚደርሰው ይማራል። አንተ ከሁለቱም ተራ ወጥተህ ሳይማሩ የተማሩ ከሚመስላቸው አትሁን።
Показать все...
ደግሞም ልንገርህ! አካደሚ እውቀት ቀርቶ ሌሎች የሸሪዐ ዘርፎች እንኳ ዋጋ ይኖራቸው ዘንድ ተውሒድ ላይ የተንጠለጠሉ ናቸው። ሸምሰዲን አሰፋሪኒ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ “ሌሎች የእውቀት ዘርፎች ለተውሒድ እውቀት ቅርንጫፎች ናቸው። ምክንያቱም እሱ ከአምልኮቶች ሁሉ የላቀው፣ ከትእዛዛት ሁሉ በላጩ እንዲሁም እያንዳንዱ አምልኮትና ትእዛዝ፣ ጤናማ ይሆን ዘንድ ብሎም ዋጋ ይኖረው ዘንድ መስፈርቱ ነውና። የክብርና የልቅና ባለቤት የሆነው (ጌታ ምንነት) የሚታወቅበትም ነውና።” [ለዋሚዑል አንዋሪል በሂያ፡ 1/57] ስለዚህ በቅድሚያ ለራስህ ሁን! ለራስህ ሳትሆን ለህዝብ አትሆንም። ያለበለዚያ አስር ገንብተህ ሺ ታፈርሳለህ። ምንም ላይ ሳትሆን ትልቅ ነገር ላይ ያለህ ይመስልሃል። በተውሒድ የምትሳለቅ፣ ለቀብር አምልኮ የምትወግን ከሆንክ የታሪክም ሆነ የፖለቲካ አስተዋፆህ የዜሮ ብዜት ነው የሚሆነው። አልዓስ ብኑ ዋኢል በጃሂሊያ መቶ ግመል ሊያርድ ስለት ተስሎ ነበር። ስለቱን ሳይፈፅም ስለሞተ ልጁ ሂሻም ሃምሳ ግመል አረደለት። ሌላኛው ልጅ ዓምር ግን የድርሻውን ከማረዱ በፊት የአላህ መልእክተኛን ﷺ ስለ ጉዳዩ ቢጠይቅ {አባትህማ ተውሒድን ቢቀበል ኖሮ ብትፆምለት ብትሰድቅለት ይጠቅመው ነበር} ነው ያሉት። [አሶሒሐህ፡ 1/180] ሰላም!! ~ ~ https://t.me/IbnuMunewor
Показать все...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

የዘመኑ ሰዉስ፦ እፍፍ ቢሉት ንፋስ       ቢደገፉት ድርምስ    ቢከፋፈት ፍስስ          ቢከዳደን ቸሰስ    ቢለቁት ትርምስምስ    ቢጨብጡት ቅንስ   የዘመኑ ሰዉስ             ስትቀርበዉ ቀልበስ ስትርቀዉ ምልስ          ነፍሲያዉን ዉድስ    ስራዎቹን ቅድስ            የዘንድሮ ሰዉስ ሰፍሰፍ ስትወደስ          ክስስ ስትወቀስ ስትወደዉ ለምን       ስትርቀዉ ልምን       ስትረዳዉ ልቅም       ስትረሳዉ እርግም   ችላ ስትል ድርግም    ስትመክረዉ ግግም ሲሞላልህ ሞልቶ ወንድም ስትቼገር የለም አንድም ሲሳካልህ ፈገግ         ስትከስር ጨፍገግ ስልጣን ሲኖር ዉድድ  ስልጣን ሲያጣ ዉርድ ስትወደድ ስግድ         ስትጠላ ሽዉድ 🎙𝐀𝐛𝐝𝐮 𝐒𝐡𝐢𝐤𝐮𝐫 𝐀𝐛𝐮 𝐅𝐞𝐰𝐳𝐚𝐧 t.me/abu_fewzan_abdu_shikur t.me/abu_fewzan_abdu_shikur
Показать все...
Abdu shikur abu fewzan

በአብዱ ሽኩር አቡ ፈዉዛን የሚሰጡ የተለያዩ የኪታቦች እና ዳእዋዎች የሚለቀቅበት ቻናል ነዉ፡፡ ቻናላችንን ይቀላቀሉ ተጠቃሚም ይሁኑ! አስተያየትና ገንቢ ምክር ካለዎት በዚህ ያቀብሉን @Abu_fewzan_bot

السلام عليكم ورحمتله وبركاته ውድ የአላህ ባሮች እንኳን ለዚህ ለተከበረው ኢደል አድሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ኢድ ሙባረክ عيد مبارك تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال እንኳን በሰላም ለዒደ አል አድሃ አደረሳችሁ ------------------ @✍🎙ወንድማችሁ ጀማል እንድሮ ከወሎ–ወረኢሉ 🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.