ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Открыть в Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
912
Подписчики
-224 часа
-127 дней
+5130 дней
Архив постов
አሁን ላይ ስለ ማንም የምጨነቅበት ጊዜ ላይ አይደለሁም፤ ማን መጣ፣ ማን ሄደ፣ ማን ራቀ የሚለው አያሳስበኝም። ትልቁ ትኩረቴ ከጌታዬ ጋር ያለኝን ትስስር አሳምሬ በዱንያም በአኼራም እውነተኛውን ስኬት ማግኘት ብቻ ነው።

​📍 ብሶትሽን ለአሏህ ብቻ ተናገሪ:: ​አንዳንድ ቀን በውስጥሽ ያለው ጭንቀትና ድካም ከብዶሽ ለቅርብ ጓደኞችሽ አውጥተሽ በመተንፈስ ቀለል እንዲልሽ ትፈልጊ ይሆናል። ነገር ግን ሰዎች የቱንም ያህል
​📍 ብሶትሽን ለአሏህ ብቻ ተናገሪ:: ​አንዳንድ ቀን በውስጥሽ ያለው ጭንቀትና ድካም ከብዶሽ ለቅርብ ጓደኞችሽ አውጥተሽ በመተንፈስ ቀለል እንዲልሽ ትፈልጊ ይሆናል። ነገር ግን ሰዎች የቱንም ያህል ቢወዱሽ ሁሌ ስለ ችግርሽና ስለ ብሶትሽ መስማት ሊሰለቻቸው ይችላል።መሰልቸታቸውን  በቃላት ባይነግሩሽም  ከሁኔታቸውና ከዝምታቸው መረዳት ትችያለሽ:: ​ እህቴ ሰዎች ይሰለቻሉ አላህ ግን አይሰለችም ሰዎችን በብሶትሽ ደጋግመሽ ካስቸገርሻቸው ከአንቺ መራቅን ይመርጣሉ። አላህ ግን በለመንሽውና ወደ እርሱ በተመላለሽ ቁጥር ይበልጥ ይቀርብሻል። እርሱ ለቅሶሽን የማይሰለች ብሶትሽን የማይንቅና ለጭንቀትሽ እውነተኛ መፍትሔ ያለው ብቸኛ ጌታ ነው። ​ ችግርሽን ለአላህ ብቻ ንገሪው ነቢዩ ያዕቆብ (አለይሂ ሰላም) ታላቅ ጭንቀት በደረሰባቸው ጊዜ እንዲህ ነበር ያሉት፦ ​﴿إِنَّمَا أَشْكُو بَثِّي وَحُزْنِي إِلَى اللَّهِ﴾ "ጭንቀቴንና ሐዘኔን የማሰሙተው ወደ አላህ ብቻ ነው (ዩሱፍ፡ 86) ​ ሰዎች ብሶትሽን ቢሰሙ አይዞሽ ከማለት ባለፈ ሊያደርጉልሽ የሚችሉት ነገር የለም:: አሏህ ግን ብሶትሽን ሰምቶ መፍትሄን ይሰጥሻል:: ሰውን አታስቸግሪ ለራስሽ ስትይ ጠካራ ሁኚ ሁሌ ስለ ራስሽ ድካም የምታወሪ ከሆነ በሰዎች ዘንድ ያለሽ ግርማ ሞገስ ይቀንሳል። ሰዎች ሲያዩሽ የችግርና የጭንቀት ምልክት ብቻ እንዳትሆኝ ተጠንቀቂ። በሰዎች ፊት ጠንካራና ታጋሽ ሁኝ  በጌታሽ ፊት ግን ደካማና ተናናሽ  ሁኚ። ሱጁድ ትልቁ መተንፈሻሽ ይሁን የውስጥሽ ጩኸት ሲበዛ ማንም ሊሰማሽ ያልፈለገ ሲመስልሽ መስገጃሽን ዘርጊና ወደ ጌታሽ አልቅሺ። በዝምታ የምታፈስሽው እምባ በአላህ ዘንድ ትልቅ ዋጋ አለው። እርሱ ምላሽ የሚሰጥሽ ልብሽን የሚያረጋጋና ካሰብሽው በላይ መውጫ መንገድን የሚያዘጋጅልሽ ጌታ ነው።

قال الشيخ ربيع بن هد المدخلي رحمه الله : الحوثيين يؤمنون بعقائد الخُميني وأسلافه ومَنهجهم القائِم على الكُفر والتقية القائمة على الكذب والكفر وعندهم مِن الحِقد على الصحابة والمسلمين ما لا يوجد عند اليهود والنصارى والهندوس وذلك انطلاقاً مِن تكفيرهم للصحابة الكرام وسائر المسلمين فعلى المسلمين في اليمن وغيرها أن يعرفوا حقيقة دين الروافض وشدة عداوتهم للإسلام والمسلمين ولا ينخدعوا بأكاذيبهم وتلبيساتهم القائمة على عقائدهم الكفرية ومنها التقية. دين الروافض قائم على الكفر والزندقة (7) ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ሀዲ አል-መድኸሊይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ፦ ሁቲዎች በኹመይኒ እና በቀደምቶቹ እምነቶች፣ እንዲሁም በክህደት  እና በውሸትና በክህደት ላይ በተገነባው የማስመሰል መንገዳቸው ያምናሉ። ለሶሃባዎች እና ለሙስሊሞች ያላቸው #ጥላቻ አይሁዶች፣ ክርስቲያኖች እና ሂንዱዎች ዘንድ እንኳን የማይገኝ ነው። ይህም የሚመነጨው የተከበሩ ሶሃባዎችን እና ቀሪውን ሙስሊም ማህበረሰብ ከማክፈራቸው ከእስልምና ውጭ ናቸው ብለው ከመፈረጃቸው ነው። ስለዚህ በየመንም ሆነ በሌሎች ቦታዎች ያሉ ሙስሊሞች የራፊዷዎችን  ሃይማኖት እውነታ፣ እንዲሁም ለእስልምና እና ለሙስሊሞች ያላቸውን የጠነከረ ጠላትነት በሚገባ ማወቅ አለባቸው። ተቂያን ጨምሮ በክህደት እምነቶቻቸው ላይ በተመሰረቱት ውሸቶቻቸው እና ማደናገሪያዎቻቸው ሊታለሉ አይገባም። የራፊዷዎች ሃይማኖት በክህደት እና በሙናፊቅነት ከእስልምና በማፈንገጥ ላይ የተገነባ ነው።(7). = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Abulabas1444 https://t.me/Abulabas1444.

➔ በሃላል መተያየት፣ ➔ ከዚያም እጮኝነት፣ ➔ ከዚያም ኒካህ፣ ➔ ከዚያም ሰርግ። ይህ ነው ትክክለኛው መንገድ፤ የእውነት የሚወድሽ ከሆነ መንገዱ ይሄው ነው፣ ከዚህ ውጭ ሌላ አማራጭ የለም።
➔ በሃላል መተያየት፣ ➔ ከዚያም እጮኝነት፣ ➔ ከዚያም ኒካህ፣ ➔ ከዚያም ሰርግ። ይህ ነው ትክክለኛው መንገድ፤ የእውነት የሚወድሽ ከሆነ መንገዱ ይሄው ነው፣ ከዚህ ውጭ ሌላ አማራጭ የለም።

አስቸጋሪ የሚሆነው ምን መሰለህ? …  እንደክፍት መፅሃፍ መሆን። የቀረበህ ሁሉ ፣ አላፊ አግዳሚው ሁሉ የሚያነብህ አይነት ሰው መሆን።  አንዳንዱ አየር ላይ አንብቦህ ቦታ አይሰጥህም፣  አንዳንዱ በተሳሳተ መንገድ ይረዳዋል…     እና የህይወትህን  አንድ ፊደል እንኳን ማንበብ የማይገባቸውም ሰዎች ሀሳብ ሊሰጡብህ ይመጣሉ። … እና  ክፍት መሆን ጥሩ አይመስለኝም። t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman

👉ውበት ተመልከቱ እስኪ #አላህ ይጠብቃቸው ያረብ! አልሐምዱሊላህ ዛሬም #ሰለፍዮች ወደፊትም በአላ ፈቃድ ሰለፍዮች ነን ወሊላሂል ሀምድ። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Abulabas144
+4
👉ውበት ተመልከቱ እስኪ #አላህ ይጠብቃቸው ያረብ! አልሐምዱሊላህ  ዛሬም #ሰለፍዮች ወደፊትም በአላ ፈቃድ ሰለፍዮች ነን ወሊላሂል ሀምድ። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Abulabas1444 https://t.me/Abulabas1444.

{{ قُلْ مُوتُوا۟ بِغَیۡظِكُمۡۗ }} فيزيد ويتزايد إن شاء الله، لأن الله تعالى يقول: {{ أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَاۤءِ مَاۤءࣰ فَسَالَت
+9
{{ قُلْ مُوتُوا۟ بِغَیۡظِكُمۡۗ }} فيزيد ويتزايد إن شاء الله، لأن الله تعالى يقول: {{ أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَاۤءِ مَاۤءࣰ فَسَالَتۡ أَوۡدِیَةُۢ بِقَدَرِهَا فَٱحۡتَمَلَ ٱلسَّیۡلُ زَبَدࣰا رَّابِیࣰاۖ وَمِمَّا یُوقِدُونَ عَلَیۡهِ فِی ٱلنَّارِ ٱبۡتِغَاۤءَ حِلۡیَةٍ أَوۡ مَتَـٰعࣲ زَبَدࣱ مِّثۡلُهُۥۚ كَذَ ٰ⁠لِكَ یَضۡرِبُ ٱللَّهُ ٱلۡحَقَّ وَٱلۡبَـٰطِلَۚ فَأَمَّا ٱلزَّبَدُ فَیَذۡهَبُ جُفَاۤءࣰۖ وَأَمَّا مَا یَنفَعُ ٱلنَّاسَ فَیَمۡكُثُ فِی ٱلۡأَرۡضِۚ كَذَ ٰ⁠لِكَ یَضۡرِبُ ٱللَّهُ ٱلۡأَمۡثَالَ }} [سُورَةُ الرَّعۡدِ: ١٧] https://t.me/Abulabas1444 https://t.me/Abulabas1444.

ወንጀልህ የቱንም ያህል ቢበዛ፣ በሰራኸው ጥፋት ልብህ በፀፀትና በጭንቀት ቢሰበርም… አላህ ግን «ላ ተቅነጡ — ከእዝነቴ ተስፋ አትቁረጡ!» ይልሃል። ይህች እህት በቀጥታ ስርጭት ላይ በዕንባ ታንቃ፣ የወንጀሏ ክብደት አስፈርቷት ልቧ ሲጨነቅ የሸይኹ መልስ ግን ለሁላችንም ትልቅ ማስተንፈሻና የተስፋ ብርሃን ነበር። እሱ ራሱ ጌታችን «ተስፋ አትቁረጡ» እያለን እኛ በምን አቅማችን ተስፋ እንቆርጣለን?! የሰራነው ወንጀል ዚናም ይሁን ምንም፣ ተራራ ያህል ቢገዝፍም እንኳ… የአላህ እዝነት ከወንጀላችን ሁሉ በላይ እጅግ የሰፋ ነው። እውነተኛ ፀፀት ይዘን «ማረኝ» ብለን ወደ እርሱ ከተመለስን አላህ ሁሉንም ወንጀል ይቅር ይላል። t.me/AbuSufiyan_Albenan t.me/AbuSufiyan_Albenan

ትምህርት ቅንጦት አይደለም ~ ያ ኡመተል ኢስላም! ልጆችህን ትምህርት አስተምር። ካልሆነ ግን በገዛ ምድርህ ባይተዋር ትሆናለህ። ካልሆነ ግን ሌላው በተቋም እና በመዋቅር ሲዋጋህ አንተ በለቅሶ ነው የምትከላከለው። ካልሆነ ግን በገዛ ቀየህ ላይ "የእስላም አገሩ መካ፣ የአሞራ አገሩ ዋርካ" ይተረትብሃል። ካልሆነ ግን ግብር የምትከፍልበት ተቋም የምትወገርበት ዱላ ይሆናል። ካልሆነ ግን ለሚደርስብህ መድሎና መገለል ምላሽህ ለቅሶ ብቻ ይሆናል። ካልሆነ ግን መብትህን የምታገኘው ሌሎች ሰፍረው ለክተው በሚሰጡህ መጠን ብቻ ይሆናል። ካልሆነ ግን በአስተማሪነት፣ በሰራተኝነት በሚመጡ አካላት በገዛ ቀየህ ላይ የባህል ወረራ ይፈፀምብሃል። ማንነትህ ይደባለቃል። አለመማር አንድምታው ብዙ ነው። አላስተምርም ካልክ ሚሽነሪ ገብቶ ልጆችህን በትምህርትና በጤና አገልግሎት ስም ይወስድልሃል። እነ ላጲሶ የሚሸነሪ ሰለባዎች ናቸው። አላስተምርም ካልክ ሴረኛ ፖሊሲዎችና ደንቦች እየተረቀቁ ከንግዱ ሴክተር ሳይቀር በካልቾ ትባረራለህ። አላስተምርም ካልክ ታሪክህን እያወላገደ፣ እምነትህን እያንጋደደ ለሚያጠለሽ አካል ቦታውን ትለቃለህ። አለመማር በጤናው፣ በፀጥታው፣ በአስተዳደሩ፣ ... ሴክተር የሚኖረው ክፍተት ከምናስበው በጣም የራቀ ነው። በዚህ ዘመን በስልኩ የተላከለትን መልእክት የማያነብ፣ የሰፈሩ አጥር ላይ የተለጠፈን ማሳሰቢያ የማያውቅ፣ ባንክ ቤት ገብቶ ስሙን መፃፍ አቅቶት ሰው የሚጠብቅ ወጣት ማፍራት እጅግ አደገኛ ነገር ነው። አስተምር ልጆችህን። በትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ ችግሮችን ልጆችህን በማራቅ አትፈታቸውም። አንተ ራስህን ካራቅክላቸው በኋላ ላንተ በመቆርቆር ምቹ ከባቢ አደላድለው ይጠሩኛል ብለህ እንዳትጠብቅ። ይልቁንም እየተማርክ፣ እያስተማርክ ታገል። ጎን በጎን ክፍተቶችን በራስህ በቤትህ ወይም ተደራጅተህ ሙላ። ብታስተምር ይሻልሃል! ልጆችህን አስተምር። በተለያዩ የዓለም ጫፎች የምንሰማቸው ሙስሊሞች ላይ የሚደርሱ ግፎች አንዱ ምክንያታቸው የተራቀቁ ቴክኖሎጂዎችን እና ጠላትን መገዳደር የሚያስችሉ ዘመኑን የዋጁ የጦር መሳሪያዎችን ማምረት ላይ ስለሌለን ነው። እነዚህ ቴክኖሎጂዎችና የተራቀቁ የጦር መሳሪያዎች ደግሞ የዘመናዊ ትምህርት ውጤቶች ናቸው። ጠላት እጅግ አውዳሚና ጅምላ ጨራሽ፣ አህጉር አቋራጭ መሳሪያ እስከ አፍንጫው ታጥቆ ሳለ አንተ በኮንትሮባንድ ያገኘኸውን ጥቂት ክላሽንኮቭ ይዘህ እንገጅ እንገጅ ብትል ውጤቱ የትም የማይደርስ ሰሞንኛ መፈራገጥ ብቻ ነው የሚሆነው። ባጭሩ ስለ ትምህርት ሲወራ ስለ ቅጥር እንጀራ ብቻ አናስብ። የመማር ትርጉሙ ከዚያ ያለፈ ነው። ስለ ትምህርት ሲወራ ከአንድ ከሁለት አቅጣጫ ብቻ መመልከት አይገባም። መማርም፣ አለመማርም ተጽእኗቸው መልኩም አይነቱም ብዙ ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ አካባቢያችን፣ ወገናችን ከሌሎች በትምህርት ወደ ኋላ እንዳይቀር እንዴት የተሻለ ስራ እንስራ በሚል ልንመካከር በሚገባን ጊዜ ከፊሉ ገና የመማርን አስፈላጊነትና ያለመማርን አደጋ ለመረዳት ማገዶ እየፈጀ ነው ያለው። (ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 10/2017) (ትንሽ ተነካክቶ በድጋሜ የተለጠፈ) = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

📢 አስደሳች ዜና! ከዳሩል ዒልም የቁርአን ሒፍዝ እና የተርቢያ ማዕከል 💎 ዳሩል ዒልም የቁርአን ሒፍዝ እና የተርቢያ ማዕከል ለ2019 ዓ. ል የትምህርት ዘመን በአዳሪ መርሃግብር ተማሪዎችን ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቆ በምዝገባ ላይ ይገኛል። ☑️ የመመዝገቢያ መስፈርቶች፦ 📍ጾታ፦ ለወንዶች ብቻ (አዳሪ) 📍 እድሜ፦ ከ10 - 20 ዓመት 📍 ጤንነት፦ ከማንኛውም በሽታ ነፃ የሆነ 📍 ስነ-ምግባር፦ለመርከዙ ህግና ደንቦች ተገዢ የሆነ 📍 ፍላጎት፦ ለመቅራት ከፍተኛ ፍላጎት ያለው 📍ክፍያ፦ ወርሃዊ ክፍያን መክፈል የሚችል ☑️ የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች፦ 📌 የቁርአን ሒፍዝ (በቃል መያዝ) 📌 የቁርአን ነዘር (ንባብ) እና ሙራጀዓ (ክለሳ) 📌 ቃዒደቱን ኑራኒያ እና የተጅዊድ ትምህርቶች 📌 የተለያዩ የዲን ኪታቦች ☎️ ለምዝገባ እና ለበለጠ መረጃ፡ +251911171786 | +251910034682 በቴሌግራም ለመመዝገብ ይህን ይጫኑ👈 በዋትስ አፕ  ለመመዝገብ ይህን ይጫኑ👈          የቴሌግራም አድራሻ፡ 🔗https://t.me/darulilmmerkezofficial 🔗https://t.me/darulilmmerkezofficial 🏢 አድራሻ: አንፎ 105 ከዘቢዳር ሆቴል ጀርባ

የጁሙዐህ ኹጥባ ርዕስ፦ የዒልም ደረጃ (በላጭነት) 🏙በደሴ ጂብሪል ጎራ መስጂድ 🎙አቡ ዑሠይሚን ዒዙዲን የቴሌግራም ቻናል፦ ¤t.me/Ezedin_Ibnu_Shafi

📌محاضرة :-الثبات على الدين                          በዲን ላይ ጽናት 🎙አቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba

●ምረጪው ጀግናውን ያን ሰለፍይ ወጣት ●ጎስቋላ ቢሆንም ቢጎዳውም ማጣት ●ሰለፍዩን ወጣት ምረጪው ያን ጀግና ●የነብያት ወራሽ የኢስላም ናሙና ●ያንን የሱና ሰው ጀግናውን ምረጪው ●በኒቃብ ተውበሽ ያንቺ ይሁን አምጪው ●በይ ምረጪው ውዴ ምንም አታመንቺ ● በቃ ይሁንልሽ አባወራሽ ላንቺ ። 🫵በቃ ምረጪው ✍️

♦️ለነዚያ ለታሪክ አተላወች ♦️ለነዚያ የራፊዷ ገረዶች ♦️ለመጁሳ ቅጥረኞች አድርሱልኝ⁉️ ሲሰድቡሽ ቢውሉ ከሽዓ ወግነው፡ የተውሒድን መርህ ስለማያውቁ ነው፡ ለአህባሽ፣ለኢኽዋን ደግሞም ለሱፍያ፡ ግልፅ ነው ይጠላል ደዕዋ ሰለፍያ፡ 🎙በኑረዲን አል-ዓረቢ http://t.me/nuredinal_arebi http://t.me/nuredinal_arebi

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ረድ የሸይኽ ሙሀመድ ሀሚድን ስህተቶች وَلَا تَلْبِسُوا الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُوا الْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ እውነቱንም በውሸት አትቀላቅሉ፡፡ እናንተም የምታውቁ ስትሆኑ እውነትን አትደብቁ፡፡ 🇸🇦የቴሌግራም ቻናል https://t.me/KedmiyaLetewhid9

﴿رَبِّ إِنّي لِما أَنزَلتَ إِلَيَّ مِن خَيرٍ فَقيرٌ﴾ القارئ : عبدالعزيز الغامدي 🩶.

ወደ ዩኒቨርሲቲ ለምትገቡ አዲስ ተማሪዎች፦ ከላይ የተቀመጠው መረጃ የየዩኒቨርሲቲ ጀመዓዎችን መረጃ የያዘ ሲሆን በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች በመደወል ስለ ዩኒቨርስቲዎቹ፤ ጀመዓዎች እንዲሁም ሌሎች መረጃዎ
ወደ  ዩኒቨርሲቲ ለምትገቡ አዲስ ተማሪዎች፦     ከላይ የተቀመጠው መረጃ የየዩኒቨርሲቲ ጀመዓዎችን መረጃ የያዘ ሲሆን በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች በመደወል ስለ ዩኒቨርስቲዎቹ፤ ጀመዓዎች እንዲሁም ሌሎች መረጃዎች መጠየቅ ትችላላችሁ።    አላህ ለስኬት መሠረት የሆነን ቆይታ ያድላችሁ።

♦️♦️♦️በፈገግታ ተገናኝተን በጥላቻ ለምን እንለያያለን? 📌ግን ለምንድነው የሰው ልጅ ሲገናኝ በፈገግታ፣ በደስታና በፍቅር የሚቀራርበው፤ ሲለያይ ግን ለመጠላላት ምክንያት፣ ለመከፋፈል ሰበብ፣ የተቃውሞ ቃል እና የቁርሾ ምክንያት ፈልጎ የሚሄደው? 📍ሲገናኝ እያንዳንዱ ሰው የሌላውን መልካምነት ይመለከታል፤ ፈገግታውን ያያል፣ መልካም ቃሉን ይሰማል፣ ውብ ጎኖቹን ያደንቃል። ጊዜ ሲያልፍ ግን የሰውን ጉድለት ማየት ይጀምራል፤ ከዚያም አንድ ትንሽ ስህተት ትልቅ ሆኖ ይታየዋል። የብዙ ዓመታት መልካምነት በአንድ ቅጽበት ይረሳል። አሳዛኙ ነገር ግን መለያየቱ አይደለም፤ እንደ ጠላት መለያየቱ ነው። 📌አንድ ቀን በፍቅር የተገናኛችሁ ሰዎች ለምን በጥላቻ መለያየት አለባችሁን? አንድ ቀን የተዋደዳችሁትን ሰው ዛሬ ስለተለያያችሁት ለምን መጥፎ ሰው ማድረግ ያስፈልጋል? 📍አንዳንድ ሰዎች ከሕይወታችን ሊወጡ ይችላሉ፤ ነገር ግን ከሕይወታችን መውጣታቸው በልባችን ውስጥ ጠላት ሆነው እንዲቀሩ አያስገድደንም። መንገዳችሁ ቢለያይ፣ ልባችሁ አይለያይ። መገናኘታችሁ ቢያበቃ፣ ክብራችሁን አትጨርሱ። 👌ሰውን በመልካምነት ማግኘት ብቻ ትልቅ ነገር አይደለም፤ በመልካምነት መሰናበትም የሰውነት ትልቅነት ነው። 📍እናም ከአንድ ሰው ስትለያዩ፣ ምክንያት ፈልጋችሁ እንዳትጠሉት፤ ያሳለፋችሁትን መልካም ጊዜ አስቡ። ያደረገላችሁን መልካም ነገር አስቡ። ካልቻላችሁም ቢያንስ ዝም ብላችሁ በሰላም ተለያዩ። 🗳ምክንያቱም መለያየት የግድ ጥላቻን አይፈልግም፤ አንዳንድ ጊዜ መለያየት ብቻ በቂ ነው። ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba