قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
Открыть в Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
БольшеСтрана не указанаКатегория не указана
906
Подписчики
-124 часа
-127 дней
+4430 дней
Архив постов
Repost from ዳዕዋ ሰለፍያ በአልብኮ ወረዳ ሶባ እና ጀብል ቀበሌ(አሸዋዉ) ✈
🪴ኢስቲቃማን እንዴት እናምጣ?
በእስልምና ኢስቲቃማ (الاستقامة) ማለት በአላህ ትእዛዝ ላይ ጸንቶ መቆም፣ ከኃጢአት መራቅና በመልካም ሥራ ላይ መቀጠል ነው። በነገራችን ላይ ኢስቲቃማ ማምጣት በተለይ በችግር ጊዜ ትልቅ መፍትሔ ነው።
💎ነገር ግን ኢስቲቃማ ማለት ችግር ፈጽሞ አይመጣም ማለት አይደለም፤ ችግር ሲመጣ በአላህ ላይ ተማምኖ፣ በትዕግሥትና በትክክለኛ መንገድ መቆም ነው።
ኢስቲቃማን እንዴት እናምጣ?
1. እምነትን ማስተካከል – ተውሂድን ማጠናከርና ልብን ከአላህ ጋር ማያያዝ።
2. ግዴታዎችን መጠበቅ – በተለይ አምስቱን ሶላቶች በጊዜያቸው መስገድ።
3. ኃጢአትን መተው – ትንሽ ነው ብሎ ኃጢአትን አለመናቅ።
4. በቁርአንና በሱና ላይ መጠንከር።
5. ዱዓን ማብዛት። ነቢዩ ﷺ በብዛት ይሉ ነበር፦
«يا مقلب القلوب ثبت قلبي على دينك»
“የልቦች ቀያሪ ሆይ! ልቤን በዲንህ ላይ አጽናው።”
6. መልካም ጓደኞችን መምረጥ – ሰው በሚያደርገው አካባቢና ጓደኛ በጣም ይጎዳል ወይም ይጠቀማል።
7. ትንሽ ትንሽ ቢሆንም በመልካም ሥራ መቀጠል። ዋናው ነገር ብዙ ጀምሮ ቶሎ መተው ሳይሆን በቀጣይነት መሥራት ነው።
አላህ ሲል፦
> ﴿إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا تَتَنَزَّلُ عَلَيْهِمُ الْمَلَائِكَةُ أَلَّا تَخَافُوا وَلَا تَحْزَنُوا﴾
“ጌታችን አላህ ነው ካሉ በኋላም ጸኑ፣ መላእክት በእነርሱ ላይ ይወርዳሉ፤ ‘አትፍሩ፣ አትዘኑም’ ይሏቸዋል።” (ፉሲለት 41፥30)
ስለዚህ ኢስቲቃማ በችግር ላይ የሚሰጠን መፍትሔ ነው፣ ነገር ግን ችግሩን በአንድ ጊዜ የሚያጠፋ ፈጣን መፍትሔ አይደለም። ችግሩን እንዴት እንደምንጋፈጠው የሚያስተካክል የልብ ጥንካሬና የሕይወት መንገድ ነው።
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ለሶስቱ "ዝሆኖች"!
~
ትግራዋይ ነኝ ታታሪ - ስራዬን ብቻ የምሰራ
ትብታባችሁ የማይገባኝ - ለፍቶ አዳሪ ነኝ አማራ
ይሁንታችሁ የማያሻኝ - ኦሮሞ ነኝ ዋዠራ
የለት ጉርሴን የማሳድድ - እሩቅ ነኝ ከናንተ ሴራ
ፍጥጫችሁ ማይጥመኝ - ሁሌ የሚሆንብኝ ግራ
ከጫካው አውሬ በላይ - ፍረጃችሁን የምፈራ
አንዱ እንዳይገድለኝ በጨለማ - አንዱ እንዳያስረኝ በጠራራ
ልርቃችሁ የሚከብደኝ - ልቀርባችሁ የምፈራ
ከዝርፊያችሁ የሌለሁኝ - ብጣሽ ያላየሁ ሰባራ
ከፌሽታችሁ ያልታደምኩኝ - ከጭፈራው ከዳንኪራ
ጦሳችሁ ግን የሚተርፈኝ - ባልዋልኩበት የምጠራ
ፍቅራችሁ ለይቶ አግላይ - ጥላችሁ ሁለት ግራ
ምቾት ድሎታችሁ የግል - ሰቀቀናችን የጋራ
የግጭት ጅምላ አቅራቢ - የብሶት የመከራ
ደም መጣጭ እንደ መዥገር - እንብላው ባይ በየተራ
እስቲ አርፋችሁ አሳርፉን - ለሰላም ቁሙ በጋራ።
* አብዛኛው ያገሪቱ ችግር መነሻ የሶስቱ ብሄር #ፖለቲከኞች ስግብግብ ፖለቲካ ነው። ሶስቱም የራሳቸውን ጥለው ወደ ሌላው ጣት ይቀስራሉ። እነሱ ባልተግባቡበት የሃገሪቱ ሰላም የራቀ ነው። በነሱ ጦስ ፍዳቸውን የሚያዩት ከየብሄሮቹ የወጡት ምስኪኖች ናቸው። አላህ ሁሉንም ልቦና ይስጣቸው።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ህዳር 01/2014)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
አልሓሪሥ ብኑ ሐቢብ ስምንት ልጆቹን በሞት አጣ። በዚህ መሀል አንድ በጉ በተኩላ የተበላችበት ሰው አዝኖ ሲያለቅስ አየ። በዚህን ጊዜ አልሓሪሥ ለሰውየው አንዲት ግመል ሰጠውና፦ "ይህችን በበግህ ምትክ ውሰድ፤ ማልቀስን ግን ለሚገባው (እውነተኛ ሐዘን ላለበት) ሰው ተወው" አለው።
📚 ዑዩኑል አኽባር — ኢብኑ ቁተይባህ
"እናቱ የሞተችበትና ገበያ የሄደችበት እኩል ያለቅሳል" ይላል ያገራችን ብሂል። ሆድ የባሰው ሁሉ የከፋ ሁኔታ የገጠማቸውን ቢያስብ አርፎ ይቀመጥ ነበር።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from ዳእዋ ብቻ الدعوة فقط
ስለ ኢኽዋነል ሙፍሲድን የተደረጉ በውድ እና በሱና ኡስታዞች ሙሓደራወች ስብሰብ በቀላሉ ለማገኘት👇👇👇👇👇👇
የተለያዩ መሳጭ ዳእዋወች ርዕሶቹ ከዚህ በታች ናቸው ርዕሱን አንዲ ብቻ በመካት ማዳመጥ ይችላሉ 42 አከባቢ ሙሓደራወችኢኽዋነል ሙስሊሚን እና ፓለቲካ ኢኽዋን እነማን ናቸው ኢኽዋን እና ሀድስ ኢኽዋን ይገለሀል ኢኽዋን እና ችግራቸው ኢኽዋን ሙፍሲድን ኢኽዋነል ሙፍሲድ ኢኽዋነል ሙስሊሚን እና አቂዳ ኢኽዋን እና ቡድተኝነት የሀገራችን ኢኽዋኖች ለምንድነው ኢኽዋኖች ኢኽዋን እና ስልጣን ኢኽዋን እና ኡዙር ኢኽዋን እና ኢሀድግ ኢኽዋን እና ኢብኑ ባዝ ኢኽዋን እና ሙብተድእ ኢኽዋን እና ዱአ የኢኽዋን ዱአቶች ኢኽዋኖች እነማን ናቸው ኢኽዋኖች ለምን ተበጣበጡ የኢኽዋኖች መገለጫ ኢኽዋኖች ከተስማሙ ከሸይጣንም ጋር ይሰራሉ ኢኽዋን እና ኡስማን ሰሀባው የኢኽዋን 2ቱ መስራቾች ኢኽዋን እና መውሊድ ኢኽዋን እና ድሞክራሲ ኢኽዋን ሱሩሪያ ኢኽዋን እና ሱፍያ ኢኽዋን ድሮ እና ዘንድሮ ኢኽዋንን ሳታቅ ኢኽዋን ባጭሩ ኢኽዋን እና መሪዎቻቸው ኢኽዋንን ተጠንቀቋቸው ኢኽዋን እና ስልክ ምልልስ ኢኽዋን እና ፖለቲካ ኢኽዋን እና ሽርክ ኢኽዋን ጎጂወች የኢኽዋን ድፍረት ኢኽዋን ጠላቶቻችን ናቸው የኢኽዋኖች ጥመት
من دعاء الإمام أحمد بن حنبل - رحمه الله تعالى :
( اللهم مَن كان مِن هذه الأمة على غير الحق وهو يظن أنه على الحق ، فرُدَّه إلى الحق ؛ ليكونَ من أهل الحق ).
📕 [البداية والنهاية (٣٢٩/١٠)].
Repost from የለተሞ መንጋን በመረጃ ማፈራረስ
የለተሞ ጀመዓ መረጃ አወሳሰድ ከዝንቧ ታሪክ ጋር ይመሳሰልብኛል
የለተሞ ጀመዓዎች መረጃን አጣሞ የመውሰድ፣ አውዱን ሳያገናዝቡ ለማይገናኝ ነገር አያያዞ ሰዎችን ከሱና የመግፋትና በቢድዓ የመፈረጅ አካሄድ፤ ሼኽ ረስላን ከተናገሩት አንድ አስገራሚ የተክፊሪዮች ታሪክ ጋር ተመሳስሎ ይገኛል።
ታሪኩ እንዲህ ነው፦
" ሁለት ጓደኛሞች አብረው ተቀምጠው ሳለ አንዲት ዝንብ መጥታ አዛ ታደርጋቸዋለች (ታስቸግራቸዋለች)።
ከሁለቱ አንደኛው፦ "እቺ ዝንብ እኮ ከፍራለች (ከእስልምና ወጥታለች)" ይላል።
ጓደኛውም በመገረም፦ "እንዴት ዝንብ ትከፍራለች?" ብሎ ሲጠይቀው፤
የመጀመሪያውም፦ "ምክንያቱም እቺ ዝንብ ምእመናንን አዛ አድርጋለች (አስቸግራለች)፤ አላህ ደግሞ በቁርኣን እንዲህ ብሏል፦
> وَالَّذِينَ يُؤْذُونَ الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ بِغَيْرِ مَا اكْتَسَبُوا فَقَدِ احْتَمَلُوا بُهْتَانًا وَإِثْمًا مُّبِينًا
> ( እነዚያም ምእመናንን እና ምእመናትን ባላደረጉት ጥፋት የሚያስቸግሩ በእውነት ታላቅ ቅጥፈትንና ግልጽ ወንጀልን ተሸክመዋል)
ስለዚህ ምእመንን ያስቸገረች ከፍራለች!" ሲል ድምዳሜ ላይ ይደርሳል።
ጓደኛውም አሁንም አልተዋጠለትምና፦ "ኧረ ዝንብ በሸሪዓ አትከፍርም!" ብሎ ሲከራከረው፤
ተክፊሪዩ ወዲያው ፊቱን ወደ ጓደኛው አዙሮ፦ "አንተም እኮ አሁን ከፍረሃል!" ይለዋል።
ጓደኛው ደንግጦ፦ "እኔ ደግሞ እንዴት ከፈርኩ?" ሲለው፤
"ካፊርን ካፊር ያላለ አካል ራሱ ካፊር ነው
(من لم يكفر كافراً فهو كافر)"
ብሎ እርሱንም ከእስልምና አስወጣው ይባላል።
የለተሚዮችና የታሪኩ ተመሳሳይነት፦
ይህ አያያዥ የለተሞ ጀመዓዎችን ትክክለኛ ምስል ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፦
አውድ አልባ ትስስር፦ ለተሚዮችም በዲኑ ውስጥ ያላትን ቦታና አውድ ሳያገናዝቡ፣ ለማይገናኝ ነገር ቁርኣንና ሐዲስን እየመዘዙ፣ የራሳቸውን ስሜትና አተረጓጎም በመጨመር ሰዎችን ከሱና ያባርራሉ።
የፍረጃ ሰንሰለት፦ ልክ እንደ ታሪኩ ሰውዬ "እኔ የፈረጅኩትን ካልፈረጅክ አንተም ከሱና ወጥተሃል" በሚል የጅልነትና የድንበር አላፊነት መረብ ውስጥ ህዝቡን ሲያታግሉ ይኖራሉ።
በአጠቃላይ፣ የለተሞ ጀመዓዎች የዒልም ጥልቀት የሌላቸው፣ የመረጃ አወሳሰዳቸው የተዛባና ሰዎችን በከንቱ ምክንያት ከሱና አጥር ለማስወጣት የሚቸኩሉ ድንበር አላፊዎች መሆናቸውን ይህ ታሪክ ያመላክታል።
https://t.me/Menhaje_Selef/
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
የአካል ጉዳት ሊደርስ የሚችልበት፣ ከዚህም አልፎ ህይወት የመጥፋት አደጋ ያለበት ስፖርት በኢስላም የተከለከለ ለመሆኑ የቁርኣንና የሐዲሥ ማስረጃዎች እና አጠቃላይ የሸሪዐ መርሆዎች አጉልተው ያሳያሉ። እንዲህ አይነት ስፖርታዊ ውድድር እንደማይፈቅድ የሚገልፁ የዑለማእ ፈትዋዎችንም ማየት እንችላለን። ይሄ እውነታ በተለያዩ አካላት ሲገለፅ ስለነበር ከሞላ ጎደል ግልፅ ይመስለኛል። ስፖርቱ የሚታወቅባቸው አላስፈላጊ ስድድቦች፣ ጉራዎች፣ ውሸቶች ሲጨመሩ ደግሞ ጥፋቱ ከፍ ይላል። ተወዳዳሪዎቹ ሴቶች ሲሆኑ ደግሞ የበለጠ ይብሳል።
እዚህ ድረስ ያለው ሐቅ ለአብዛኛው ሙስሊም የሚሰወር ባይሆንም እጅግ ብዙ ወገን በተለያዩ መንገዶች ለግርግሩ ድምቀት እየሰጠ ነው። ቀላል የማይባል አካል ደግሞ ተሳታፊዎቹ ባልተፈቀደ ተግባር ላይ የተሰማሩ ሳይሆን ትልቅ ገድል የፈፀሙ ያክል ሃይማኖታዊ ውግንና እያሳየ ነው። አንድ ነገር በኢስላም የማይፈቀድ ከሆነ በሃይማኖትም፣ በሃገርም፣ በብሄርም፣ በአካባቢም ፣ በፆታም መነፀር እየተመለከትን ልንወግን አይገባም። የማይፈቀድ ከሆነ በቃ አይፈቀድም።
ያልተፈቀደን ነገር ለመመልከት ገንዘብ ማውጣት፣ ያልተፈቀደን ነገር በሚያበረታታ መልኩ ድርጅቶችን ማስተዋወቅ አብሮ የማይፈቀድ ተግባር ነው። ሌላው ጊዜያችንን፣ ገንዘባችንን፣ ትኩረታችንን የምንሰጠው ምሳሌ ለሚሆነንና ከኛ የሚሻል ጉዳይ ላይ ለሚሰማራ አካል ነው።
በተረፈ ጤናን ለመጠበቅ እና ከራስ ላይ ለመከላከል አካልን ብቁ የሚያደርጉ የ"ስፖርት" አይነቶችን መሰልጠን ጥሩ ነው። ይሄኛው ቀደም ብዬ ከገለፅኩት የሚለይ ነው።
በመጨረሻም በቦክስና መሰል ስፖርታዊ ውድድሮች ላይ የደረሱ የነፍስ መጥፋቶችና ቋሚ ጉዳቶችን መጥቀስ ፈልጌ ጄሚናይን ጠይቄ ነበር። ያገኘሁት እንደወረደ የሚከተለውን ይመስላል:-
በቦክስና በሌሎች መሰል ከባድ የውጊያ ስፖርቶች (እንደ MMA/Mixed Martial Arts ያሉ) ላይ በውድድር እና በልምምድ ወቅት የሚደርሱ የነፍስ ማለፍና ከፍተኛ ቋሚ የአካል/የአእምሮ ጉዳቶች አሉ።
የነፍስ መጥፋት (ሞት)
* በቦክስ፡ በቦክስ ታሪክ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተወዳዳሪዎች በጨዋታ ወቅት ወይም ከጨዋታ በኋላ በተከሰተ የጭንቅላት ጉዳት ሕይወታቸውን አጥተዋል። ለምሳሌ ያህል፡
* ዱክ ኩ-ኪም (Duk Koo Kim - 1982)፦ የደቡብ ኮሪያው ቦክሰኛ ሬይ ማንሲኒን በተጋጠመበት ጨዋታ ላይ በደረሰበት የጭንቅላት ደም መፍሰስ ምክንያት ሕይወቱ አልፏል። ይህ አደጋ ዓለም አቀፉ የቦክስ ማህበር የዙር ብዛትን ከ15 ወደ 12 እንዲቀንስ ትልቅ ምክንያት ሆኗል።
* ፓትሪክ ዴይ (Patrick Day - 2019)፦ አሜሪካዊው ቦክሰኛ በውድድር ወቅት ባጋጠመው ከባድ የጭንቅላት ጉዳት (Traumatic Brain Injury) ምክንያት ሕይወቱ አልፏል።
* በሌሎች ስፖርቶች፦ በኤምኤምኤ (MMA)፣ በሙአይ ታይ (Muay Thai) እና በባዶ እጅ ውጊያዎች (Bare-knuckle boxing) ላይም ተመሳሳይ የነፍስ ማለፍ አደጋዎች ተመዝግበዋል።
ቋሚ እና የረጅም ጊዜ ጉዳቶች
* የአእምሮ እና የነርቭ ጉዳት (Chronic Traumatic Encephalopathy - CTE)፦ በየጊዜው በጭንቅላት ላይ በሚያርፉ ጠንካራ ምቶች ምክንያት የሚከሰት የረጅም ጊዜ የአእምሮ ጉዳት ነው። ይህም የማስታወስ ችሎታ ማጣት፣ ድብርት፣ የባህሪ ለውጥ እና የነርቭ መታወክ ያመጣል።
* ቦክሰኛ ዲሜንሽያ (Punch-Drunk Syndrome / Dementia Pugilistica)፦ በብዙ የቦክስ ተወዳዳሪዎች ላይ የሚታይ ሲሆን፣ የመናገር ችግርን፣ የእጅ መንቀጥቀጥን (እንደ ፓርኪንሰን በሽታ) እና የእንቅስቃሴ መዛባትን ያስከትላል።
* የዓይን እና የአካል ጉዳቶች፦
* የዓይን ሌንስ መንሸራተት ወይም የሬቲና መቀደድ (Retinal Detachment) እስከ ሙሉ እይታ ማጣት የሚያደርስ ቋሚ ጉዳት ያስከትላል።
* የፊት አጥንቶች ስብራት፣ የጆሮ ቅርጽ መበላሸት (Cauliflower Ear) እና የቋሚ መንጋጋ ጉዳቶች።
* የውስጥ አካላት (እንደ ኩላሊት እና ጉበት) ደም መፍሰስ እና ስብራት።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
በጣም ብዙ ምክሮች ተካትተውበታል
ከ26ኛው - 29ኛው ደቂቃ በሱሪ ፣ ጀምዕያና ቪድዮ ዙሪያ ተናግሯል በጥሩ ልብ ስሙት በተለይ ጀምዕዮች እያላችሁ የምታላዝኑ ሰወች ሊትማሩበት ይገባል ሸኽየውን ታውቁታላችሁ ፈቂህ እንደሆነም ትመሰክራላችሁ አሁን ካልተገለበጣችሁ በስተቀር
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
«እናውቃለን»
-------------------
ህይወት ዑደት ውስጥ በመኖር ጎዳና፡
በሰው መሆን አለም ስርዓትና ዳና፡
እጂግ ብዙ ነገር እያየነው ሆኗል፡
የስንት ወጣት እቅድ ስንት ቦታ ባክኗል፡
በሰፊው ጎዳና ጉዞ እየጀመሩ፡
ስኬት ላይ ለመድረስ መስመር ያሰመሩ፡
በፍቅር ጥላ ስር ሰላም የቀመሩ፡
መንገድ ለያይቷቸው ሜዳ ላይ የቀሩ፡
ከባድ ስርቻ ስር የተቀረቀሩ፡
በልብ አዳራሽ ላይ ፍቅር እንደሰሩ፡
እናውቃለን ጥንዶች ለትርፍ የከሰሩ፡
ዛሬ ተለያይተው ይነፋፈቃሉ፡
አልጠፋም ህያው ነው የትዝታው ቃሉ፡
ህይወት እንደዚህ ነች ብለው ይስቃሉ፡
የአሏህ ውሳኔ በዚህ ተፈፅሟል፡
እንደዚህ ነች ዱንያ ሆኖ ተደምድሟል፡
በትዝታ ፀዳል ሁሉም ልቡን ታሟል፡
ግና ተለያዩ የአሏህ ቀደር ቀድሟል፡
.....እንጂማ......!!
ተዋደው ተላምደው ሊጋቡ ቀጥረው፡
ፕላን አዘጋጅተው ቀን ሰዓቱን ቆጥረው፡
በሞት የተለዩ ስንቶችን አይተናል፡
አሏህ ያለው ሆነ ብለን እንላለን፡
መመኪያ ነውና በሱ እንፅናናለን፡
ያልጠበቅነው ሆኗል ይህን እናውቃለን፡
.....ኑር...✍️
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
Repost from ስለ ቀልባችን
ወዐለይኩም ሰላም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ
ውድ ወንድሜ፣ እንዲሁም በውጤቱ ምክንያት ልባችሁ ለተሰበረ፣ ግራ ለገባችሁ ውድ እህትና ወንድሞቼ በሙሉ፤
በመጀመሪያ ደረጃ ጭንቀታችሁ ይገባኛል። ለወራት ደክማችሁ፣ እንቅልፍ አጥታችሁ ያሰባችሁት ውጤት ሳይሳካ ሲቀር መከፋት ተፈጥሯዊ ነው። ነገር ግን እባካችሁ ተረጋጉ፤ ረጋ ብላችሁ አስተውሉ!
💡 የኢንትራንስ ፈተና ውጤት ያላሰባችሁት መሆን ማለት የዱኒያ ስኬታችሁ ተቋረጠ ማለት በፍፁም አይደለም! አላህ ለአንድ ባሪያው አንድን በር ሲዘጋበት ከዚያ የተሻለ ሰፊ በር ሳይከፍትለት አይቀርም።
አላህ ለእናንተ ያሰበው መልካም ነገር እናንተ ዛሬ ከምታስቡትና ከምትመኙት እጅግ የላቀ ነው። እኛ በጠባቡ እይታችን «ይህ ካልሆነ ጠፋሁ» እንላለን፤ አላህ ግን በሰፊው እውቀቱ የተሻለውን መንገድ ያዘጋጅልናል። ስለዚህ በአላህ ውሳኔ ላይ እመኑ፤ «አልሐምዱሊላህ አላ ኩሊ ሐል» በሉ።
✏️ሌላው...በዚህ ዘመን ስለተማሩና ዲግሪ ስለያዙ ብቻ ስኬታማ ይሆናል ማለት አይደለም። በተቃራኒው ዛሬ ላይ በቢዝነሱ፣ በቴክኖሎጂውና በተለያዩ ዘርፎች ትልቅ ደረጃ የደረሱ በርካታ ሰዎች መደበኛውን የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ያላጠናቀቁ ወይም ፈፅሞ ያልተማሩ ናቸው።
ይገርማችኃል...እኔ በኮምፒውተር ሳይንስ ተመርቄ ዛሬ የምሰራው በኮንስትራክሽን ዘርፍ ነው። ይህ የሚያሳየው ዩኒቨርሲቲ ገብተህ በተማርክበት ትምህርት ትሰራለህ የሚል ምንም ዓይነት ዋስትና እንደሌለ ነው። የሕይወት ሜዳ ሰፊና ያልተገመተ ነው። ትልቁ ነገር የትምህርት ዲግሪ መያዝ ሳይሆን ራስን ለገበያውና ለዘመኑ ብቁ አድርጎ ማዘጋጀት ነው።
✏️ሐቢቢ ዘመኑ የሙያ እና የ Skill እንጂ የዲግሪ ብቻ አይደለም! ብልህ ሰው ዛሬ ባጣው ነገር ላይ ቁጭ ብሎ አያለቅስም፤ ነገን ለመለወጥ ይነሳል! ዘመኑ የቴክኖሎጂ ዘመን ነው።
✔️አጫጭርና ጠቃሚ ኮርሶችን በመውሰድ በቤት ውስጥ ሆናችሁ በኢንተርኔት ገቢ የምታገኙባቸውን ሙያዎች ተማሩ።
- Web Development
- Graphic Design
- Video Editing
- ዲጂታል ማርኬቲንግ እና መሰል ዘመናዊ ክህሎቶች ተማሩ።
ወዳጆቼ...ዛሬውኑ ጭንቀቱንና ራስን መውቀሱን አቁሙ። ዛሬ ያጋጠማችሁ ነገር ውድቀት ሳይሆን አቅጣጫ መቀየሪያ
ነው። ወድቆ መቅረት እንጂ መውደቅ ራሱ ውድቀት አይደለም!
አላህ ላይ ተወኩል አድርጉ፣ ወገባችሁን ታጥቃችሁ አዳዲስ ክህሎቶችን ለመማር ተነሱ። ዛሬ የተዘጋባችሁ በር ነገ ለሚከፈተው ትልቅ የስኬት በር መነሻ ሊሆን ይችላል።
አላህ ልባችሁን ያረጋጋላችሁ፣ የተሻለውን መንገድ ይምራችሁ፣ በዱኒያም በአኼራም ስኬታማ ያድርጋችሁ!
🪶ወንድምህ አቡ ሱፍያን
Repost from محاضرات وخطب دار الحديث السلفية بإب
بسم اللــــه الرحمـــــــــن الرحيم
بمشيئة الله تعالى ستكون محاضرة في دار الحديث السلفية بإب يوم غد الجمعة الموافق ١٤ ربيع الأول بين مغرب وعشاء.
Repost from Fewaz tv ( ፈዋዝ ቲቪ )
አላህ ከልብህ የተደበቀውንም ያውቃል ሰለዚህ በሰው ፊት ማስረዳት ባትችልም በሱጁድ ላይ ንገረው 🧎♀
🔎 t.me/qelbun_selim
➦አስደሳች ዜና ለእውቀት ፈላጊዎች
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
አሠላሙ አለይኩም ወራህመቱላሒ ወበረካትሁ ለሚመጡት ተከታታይ ወራቶች የሚደረግ የመጀመሪያ ዙር የኪታብ ትምህርት ፕሮግራም ምዝገባ ተጀመረ
በዚህ ትምህርት ላይ ታላላቅ መሻኢኾች እና ኡስታዞች የሚገኙበት ነው
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
የመጀመሪያው ትምህርትም ሰኞ ምሽት
🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺
♦️በሳኡዲ10:00
♦️በኢትዮ4:00
♦️ በዱባይ 11:00
ኸዛ በኋላ ያለው ሰዓት በምክክር ይሆናል
ትምህርቱን የሚሠጡት መሻኢኾችና ኡስታዞች 👇👇👇👇👇👇👇
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
👉◀◀1. ሸይኽ ጀማል አዝ-ዘሀቢ▶▶ቀዋዒዱል ሙስላን
◀◀2.ሸይኽ ሙሐመድ غዛል ▶▶አቂደቱል ዋሲጥያ
◀◀3.ሸይኽ ሙሐመድ ሰዒድ ▶▶ ዶላለቱል አህባሽ
◀◀4.ሸይኽ ሙሐመድ መኪን▶▶ ኡሡሉ ሠላሳ
◀◀5.ሸይኽ ሙሐመድ አሚን▶▶ቀዋዒዱል አርበዕ
◀◀6.ሸይኽ አህመድ አወቀ ▶▶አርበዒን ሐዲስ
◀◀7.ዱክተር ሰዒድ ሙሳ▶▶ሚን ኡሡል አቂደቲ አህሊ ሡነቲ ወል ጀመዓ
◀◀8.ኡስታዝ አቡ አመቲ ረህማን▶▶ማሒየ ሠለፍያ ወይንም አሠሩ ተመሡኩ ቢሡና
◀◀9.ኡስታዝ ሙርሠል ሰዒድ ጨፌ▶▶አዱሩሡል ሙሐማ
◀◀10.ኡስታዝ አቡ ጁለይቢብ ▶▶አል ዑዝር ቢል ጀህል በይነል ጉሉዊ ወል ጀፋ
◀◀11.ኡስታዝ አቡ ሒበቲላህ ▶▶ሪሳለቱል ሒጃብ
◀◀11.ኡስታዝ አቡ ረያን▶▶ ነዋቂضል ኢስላም
◀◀12.ኡስታዝ አብደል መሊከ▶▶ኑሩ ተውሒድ
ከዛም በመቀጠል በሁለተኛ ደረጃ የተለያዩ ኪታቦችን በሌሎች መሻኢኾችና ኡስታዞች የሚቀጥል ይሆናል
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
ይሔን ተከታታይ የሆነ ኮርስ በቋሚነት ለመከታተል የምትፈልጉ ከታች ባሉት ዩዘር ኔሞች መመዝገብ ይቻላል
ክፍያ የለውም ነፃ ነው በቋሚነት መከታተል ብቻ ነው የሚያስፈልገው
♦️♦️የሚያስፈልገው 👉👉
ሙሉ ስም_
አድራሻ _ ብቻ ነው
እነዚህን መሻኢኾች እና ኡስታዞች እንጠቀምባቸው
የቻናል እና ግሩፕ ባለቤቶች ደግሞ ሸር እያደረግን እናዳርሰው
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
በመጨረሻም ከሁሉም መሻኢኾች እና ኡስታዞች የተውጣጡ ጥያቄዎችን ጥያቄዎችን በጥሩ ሁኔታ የመለሠ ሠርቲፍኬት(የምስክር ወረቀት) ይሠጠዋል
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
በቴሌግራም 👇👇👇
@Daruhadi21bot
በኢሞ ለመዝገብ 👇👇👇
https://s.imoim.net/wgqDgb
ወደ ደርስ ቻናል ለመቀላቀል 👇👇👇
https://t.me/Muhammed_Ibn_Abdillah
https://t.me/Muhammed_Ibn_Abdillah
በኢሞ ቻናል ለመቀላቀል 👇👇👇
https://s.imoim.net/8ODOAu
https://s.imoim.net/8ODOAu
ماذا قال الشيخ محمد بن حزام الفضلي عن الشيخ محمد بن عبدالله الإمام ودار الحديث بمعبر؟
🎧 استمع 🎧👆👆
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ሸይኽ ሙሐመድ ባሙሳ - ሐፊዞሁላህ - ለዒልም ፈላጊ ተማሪዎች የሚከተሉትን ታላላቅ የየመን መረከዞች ጠቁመዋል:-
١ - مركز الشيخ عبدالله المرعي في الفيوش
٢ ـ مركز الشيخ نعمان الوتر بالمخا
٣- مركز السلام في شبوة للشيخ حسن عليوه
٤- ومركز السنة في الضالع القائم عليه محمد بن علي الضالعي و ياسين الضالعي
እነዚህ ከሑሢዮች ተፅእኖ ነፃ በሆኑ አካባቢዎች የሚገኙ ዋና ዋና መርከዞች ውስጥ ናቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
