ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

Открыть в Telegram

ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
321
Подписчики
+124 часа
-77 дней
+5830 дней
Архив постов
✨ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሙስሊም ተማሪዎች ህብረት✨ 📜 ልዩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት! 📜 السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🌟 እንኳን ደስ አላችሁ ውድ አዲስ ገቢ ተማሪዎች! 🌟 በታላቅ ደስታ ና ፍቅር፣ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲን በመምረጥ እኛን ለመቀላቀል በዝግጅት ላይ ላላችሁ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በሙሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታችንን እናቀርባለን። 🗓 የቅበላ ጊዜና የአቀባበል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲያችን የተማሪዎች ቅበላ መርሃ ግብር የሚከናወነው ጥቅምት 3 እና 4 ቀን 2019 ነው። በእነዚህ ቀናት፣ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ለእናንተ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ሞቅ ያለና ደማቅ አቀባበል ያደርግላችኋል። በሰላም ወደ ግቢ እንድትገቡ እና አስፈላጊውን ድጋፍ እንድታገኙ የበኩላችንን እንወጣለን። 🤝 የእናንተ ትብብር ያስፈልገናል! ውድ አዲስ ገቢዎች፣ እኛን በቀላሉ ለማግኘት፣ የተሟላ አገልግሎት ለማግኘት እና የአቀባበል ቡድናችን አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርግላችሁ፡ የምዝገባ ፎርሙን ይሙሉ: https://forms.gle/F7gwvpVVsnsj843Z6 ውድ አዲስ ገቢዎች፣ እኛን በቀላሉ ለማግኘት እና የተሟላ አገልግሎት ለመቀበል፣ ማንነታችሁን ሙስሊም መሆናችሁን ለማሳወቅ የቀና ትብብራችሁን በአክብሮት እንጠይቃለን።እንዲሁም ሙስሊም መሆናችሁን ለማሳወቅ በቅድሚያ ከዚህ በታች ባሉት ስልኮች እየደወላችሁ የአቀባበል ቡድናችንን እንድታነጋግሩ በአክብሮት እንጠይቃለን። 📌 የአካባቢ ምደባ ማስታወሻ ወደ ግቢ ከመምጣታችሁ በፊት የተመደባችሁበትን ካምፓስ ይለዩ፡- ✅ Natural Science ተማሪዎች፡- ወደ Main Campus ትመጣላችሁ። ✅ Social Science ተማሪዎች፡- ወደ Techno Campus ትመጣላችሁ። 📞 ለግንኙነትና ድጋፍ የስልክ ቁጥሮች ወደ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስትመጡ አስፈላጊውን መረጃ ለማግኘት ወይም የአቀባበል ቡድናችንን እንዲቀበሏችሁ ለማድረግ የሚከተሉትን ወንድሞች ማግኘት ትችላላችሁ፡-              📚   Main campus =>ሀሰን      ☎️        090 632 6702 =>አቡዱረዛቅ           ☎️    0942213321 =>ነቢል       ☎️   096 999 0090 =>ጂፋር    affan orromo          ☎️  +251972575000                                                      💻 Techno campu       =>ዐማር ☎️+251925882521                        =>መስዑድ affan oromo ☎️  +251937517651  =>አስዓድ   ☎️   0963298664       🧕 ለሴት እህቶች ልዩ ማስታወቂያ: የእህቶችን ስልክ ቁጥር ለምትፈልጉ እህቶች ብቻ፣ በስልክ ቁጥር ☎️ +251925882521 ደውላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ።    🌹  አላህ   በሰላም ያገናኘን 🤲🌹 🎉መልካም የዩኒቨርሲቲ ቆይታ እንመኛለን!🎉

✨ የደስታችን ተካፋይ ይሁኑ! — ታላቅ የኒያ እና የዳዕዋ ፕሮግራም ✨ ​በአላህ ፈቃድ በደሴ ከተማ ልዩና ታላቅ የኒያ እና የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቶልዎታል! ​📅 ቀን፦ እሁድ — ጥቅምት 1 / 20
✨ የደስታችን ተካፋይ ይሁኑ!        — ታላቅ የኒያ እና የዳዕዋ ፕሮግራም ✨ ​በአላህ ፈቃድ በደሴ ከተማ ልዩና ታላቅ  የኒያ እና የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቶልዎታል! ​📅 ቀን፦ እሁድ — ጥቅምት 1 / 2019 ዓ.ል 💢 ቦታ፦ ደሴ — መስጂደ አስ-ሱና ⏰ ሰዓት፦ ከጧቱ — 2:30 ​🎙 በፕሮግራሙ ላይ የሚገኙ የተከበሩ ዑስታዞች፣ ሸይኾችና ወንድሞች፦ 1) ​ሸይኽ ሙሐመድ መኪን 2) ​ሸይኽ ሙሐመድ አሚን 3) ​ሸይኽ ሙሐመድ ኋዛል 4) ​ሸይኽ ሙሐመድ ሰዒድ 5) ​ሸይኽ ሐሰን አሊ 6)​ሸይኽ አሕመድ አወቀ 7) ​ሸይኽ ጀማል ዘሀቢ 8)​ ሸይኽ ይማም ሰዒድ ​9) ሸይኽ ሰዒድ ሙሐመድ ሚጢቆሎ) 10)ሸይኽ አብዱልአዚዝ 11)ሸይኽ በድሩዲን ዩሱፍ 12) ሸይኽ ሑሴን ኡመር 13) ሸይኽ ሐሰን ነጃሽ        ( ከወንዲሞች) 14) ​ወንድም ሙርሰል ሰዒድ 15) ​ወንድም ኢዘዲን ሻፊ 16)​ ወንድም አቡ ሹራ 17) ​ወንድም አቡ ሒበቲላህ 18) ​ወንድም አቡ ሐፍሷ (ይማም) 19) ​ወንድም አሊ ሰዒድ 20)​ ወንድም አቡ ኢምራን (እንዲሁም ሌሎች በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው ዑስታዞችና ወንድሞች ይገኛሉ) ​📢 ልዩ ጥሪ፦ ይህንን መልእክት ለሌሎች በማጋራትና በዕለቱ በአካል በመገኘት የዚህ ታላቅ በረካና ደስታ ተካፋይ ይሁኑ! ​📌 ለሁሉም እንግዶች ጥሪያችን ክፍት ነው!
ቻናል
https://t.me/yedesse_selfyochi_yedewa_channel
ግሩፕ
https://t.me/yedesse_selfyochi_group
ሼር ይደረግ‼

♦️♦️♦️የትዳር ውበት በግል ይጠበቃል ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ…ተስማምታቹኋል አይደል? አደራ መልስ እጠብቃለሁ 📍ገና ወደ ትዳር እንደገባችሁ ለምን የቤታችሁን ውስጣዊ ሕይወት ለሁሉም ለማሳየት ትቸኩላላችሁ? ወንዱም፦ “የኔ ሚስት እኮ ውብ ናት፣ የዲን እውቀት አላት፣ ታዛዥ ናት፣ አሳቢ ናት… እንደ እሷ ያለች የለችም!” ሴቷም፦ “የኔ ባል እኮ ቆፍጣና ነው፣ በዲኑ ላይ ጠንካራ ነው፣ ለኔ እንደ አባት ነው፣ እንደ ወንድምም ነው፣ እንዲህ ያለ ባል በማግኘቴ …” እንዲህ እያላችሁ የቤታችሁን ውስጥ ለምን ለሁሉም ታሳያላችሁ? ለማን ነው? ምን ለማረጋገጥ ነው? ሰዎች እንዲያደንቁአችሁ? እንዲቀኑባችሁ? ወይስ “የኔ ትዳር እንዲህ ነው” ብላችሁ ለማሳየት? እስቲ ራሳችሁን ጠይቁ፦ በሚዲያ ላይ የምትጽፉትን ሕይወት በእውነት እየኖራችሁት ነው? 📍ሁሉም እንዲህ ነው አልልም። በእውነት የሚዋደዱ፣ የሚከባበሩ፣ በዲንና በመልካም ሕይወት የሚኖሩ ባለትዳሮች ብዙ ናቸው። ነገር ግን ከሚናገሩት ተቃራኒ የሚኖሩ፣ በሚዲያ ላይ ፍጹም ትዳር የሚያሳዩ እና በቤታቸው ግን የተለየ ሕይወት የሚኖሩ ሰዎችም አሉ። አንዳንዶቹንም ከጥቂት ጊዜ በኋላ በመለያየት ይታያሉ። ያኔ የሚያሳዝነው መለያየታቸው ብቻ አይደለም፤ ትናንት ለሰዎች ያሳዩት ምስልና ዛሬ የሚኖሩት እውነታ ሲጋጭ መታየቱ ነው። ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ትዳር መድረክ አይደለም። የሚያጨበጭብልህ ታዳሚ አያስፈልገውም። 📍ትዳር ሁለት ሰዎች በግል የሚገነቡት ቤት ነው። ፍቅሩም በሰዎች አይን ሳይሆን በሁለቱ ልብ ውስጥ የሚኖር ነው። ሌሎችን ማስተማር ከፈለጋችሁ፣ በግል የቤታችሁን ሚስጥር ከማውጣት ይልቅ ጠቃሚ ምክር ስጡ፦ “ባልና ሚስት እንዲህ ይከባበሩ፣ እንዲህ ይተዛዘኑ፣ ከዚህ ይታቀቡ፣ በዲናቸው ላይ እንዲህ ይተባበሩ…” ይህ ሌሎችን ይጠቅማል። 📍ነገር ግን የቤታችሁን ሚስጥር፣ የባለቤታችሁን የግል ባሕሪ፣ በእናንተ መካከል ያለውን ልዩ ቅርርብና የግል ነገር ሁሉ ለሰዎች አታውጡ። ምክንያቱም አንዳንድ ውብ ነገሮች ለማሳየት ሳይሆን ጠበቀን ለናቆያቸው የሚገቡ ናቸው። የባለቤትህን መልካምነት ለማወቅ ሰዎች ማወቃቸው አያስፈልግም። የባልሽን መልካምነት ለማድነቅ የሰዎች ማጨብጨብ አያስፈልግም። እሱ ለአንቺ መልካም ባል ከሆነ፣ አንቺም ለእሱ መልካም ሚስት ከሆንሽ፣ ያ በቂ ነው። ሰዎች ሳያውቁትም ትዳራችሁ ሊያምር ይችላል። ሰዎች ሳያደንቁትም ፍቅራችሁ ሊጠነክር ይችላል። ሰዎች ሳያዩትም ቤታችሁ በሰላም ሊሞላ ይችላል። እናም አደራ… የግል የሆነን ጉዳይ በሚዲያ ላይ አናውጣ። ትዳራችሁን ለሰዎች ከማሳየት ይልቅ ለአላህ አስውቡት። ፍቅራችሁን ለሰዎች ከመናገር ይልቅ እርስ በርሳችሁ ኑሩት። የቤታችሁን ሚስጥር ለሕዝብ ከመንገር ይልቅ እንደ አደራ ጠብቁት። ምክንያቱም የትዳር ውበት ሁሉም ሰው ሲያየው አይደለም፤ ባለቤቶቹ ብቻ እያዩት ሲጠብቁት ነው። ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba

📌የትዳር ውበት በግል ይጠበቃል 🎙አቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba

አሰላሙአለይኩም ወንድም እና እህቶቼ من أصول عقيدة أهل السنة والجماعة للشيخ صالح الفوزان ሚን ኡሱሊ አቂደቱ አሕሊ ሱነቲ ወልጀመኣ ኪታብ ሙሉ ቂርኣት ከነ ፒዲኤፉ ከሚከተለው አስፈንጣሪ (ሊንክ) ማግኘት ይችላሉ፡፡ ከክፍል 1-10 https://t.me/Kitaboch/1832 https://t.me/Kitaboch/1822 https://t.me/Kitaboch/1823 https://t.me/Kitaboch/1824 https://t.me/Kitaboch/1825 https://t.me/Kitaboch/1826 https://t.me/Kitaboch/1827 https://t.me/Kitaboch/1828 https://t.me/Kitaboch/1829 https://t.me/Kitaboch/1830 https://t.me/Kitaboch/1831

🌸ልጆቻቹሁን አቂዳ እና ተውሂድን አጠጡዋቸው ልክ እናት ልጆቿን ወተት እንደምታጠባቸው💎 •علم أولادك التوحيد •قبل أن تُحفظهم القرآن •حتى لا يكونوا كالصوفية، يحفظون القرآن ويشركون بالرحمن •لا تتركوا أولادكم يألفون المعاصي بحجة أنهم صغار فيكبرون و قد ماتت تقوى اللّٰه فى قلوبهم •علمو أولادكم التوحيد وهم صغار أَشربوا أطفالكم عقيدة التوحيد ، مثلما تشربوهم حليب امهاتهم ➞°✮ልጆችን ➷መጀመርታ ተውሂድን ➷አቂዳቸውን አስተምሯቸው ➷ቁርአን  ከማስሀፈዛቹሁ ➷በፊት~°✮ ➞°✮ልክ እንደ ➷ሱፍዮች እንዳይሆኑ ➷ሱፍዮች ቁርአንን ➷ሀፍዘው በአላህ ➷ያጋራሉ~°✮ ➞°✮ስለዚህ ➷ልጆቻቹሁን አቂዳቸውን ➷ተውሂድን አስተምሯቸው ➷ልጆቻቹሁ ገና ➷ልጅ ናቸው ➷በሚል ምክንያት ➷ወደ ወንጀል እንዲዳፈሩ ➷እንዲሰሩ አትተዋቸው ➷በዚህ ያዱጉ እና ➷አላህን ከመፍራት ➷በልባቸው ውስጥ ➷ይሞታል~°✮  ➞°✮ልጆችን ➷ገና በልጅነታቸው ➷አቂዳቸውን ተውሂድን ➷አጠጡዋቸው ልክ ➷እናት ልጆቿን ➷ወተት ➷እንደምታጠባቸው~°✮ ➞°✮ልጆቻቹሁን ➷አደብን መልካም ➷ስነምግባር አስተምሩ ➷እውነትን  አስተምሯቸው ➷እንዲሁም ከመዋሸትም ➷ውሸትን አስጠንቁቋቸው~°✮ آلَنــســآء آلَســلَفــيــآت

ወሳኝ ጣፋጭ ምክር 🎙በኡስታዝአረቡ ሰዒድ 🕌በደገር ከተማ ዑሙ አይመን መስጂድ ላይ የተደረገ የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Yedeger_selefioch_jemea

“በእውነት ዘረኝነት እየሠራ ነውን? ወይስ የምንወቅሰው የግሩፑ ስም ብቻ ነው?” ምክንያቱም ስሙን ተመልክተን የሰውን ኒያ መፍረድ አንችልም። እንዲሁም አንድ ሰው ተሳስቶ ከተገኘ፣ ምክር እንስጠውጅ፤ ሰውን በነገር አንውጋ። የሰለፊያ መንሐጅ የሚያስተምረን እውነትን በእውነት እንድንመዝን እንጂ ሰዎችን በግምትና በጥርጣሬ እንድንመዝን አይደለም። 🌍 ከአካባቢ ተነስተን ለሁሉም ተውሒድን ሱናን ሰለፊያን እናድርስ! በእውነት የሚያምረው አካሄድ ይህ ነው፦ የደሴ ልጆች የደሴን ልጆች ይሰብስቡ። የራያ ልጆች የራያን ልጆች ይሰብስቡ። የወረባቦ ልጆች የወረባቦን ልጆች ይሰብስቡ። የመርሳ ልጆች የመርሳን ልጆች ይሰብስቡ። የሀርቡ ልጆች የሀርቡን ልጆች ይሰብስቡ። የአዲስ አበባ ልጆች የአዲስ አበባን ልጆች ይሰብስቡ። ሁሉም በያለበት ይሰባሰብ ይዋደድ ይከባበር ይተጋገዝ አንዱን አንዱ አይጥላ አንዱ ከሌላው የተሻልኩ ነኝ ብሎ አያስብ በሰለፊያ ላይ አንድ እንሁን። ነገር ግን ከዚያ በኋላ፦ ሁላችንም በተውሒድ እንሰብሰብ፣ በሱና እንሰብሰብ፣ በቁርኣን እንሰብሰብ፣ በኸይር እንተባበር፣ በአካባቢ ሳንለያይ በእስልምና በሱና እንደጋገፍ። ይህ ነው የሚያምረው። አንድ አካባቢ ልጆች ተሰብስበው ቁርኣን ይቀራሉ፤ ሌላው አካባቢ ደግሞ ይህንን አይቶ ይማራል። “እነሱ እዚያ ተሰብስበው ቁርኣን እየተማሩ ነው፤ እኛም በአካባቢያችን እንጀምር እንጠክር!”ይላል። ከዚያ ሌላ አካባቢ ይነሳል። ከዚያ ሌላ። በመጨረሻም በውጭ ሀገርም በሀገር ውስጥም የሚኖሩ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች፦ ቁርኣን የሚቀሩ፣ ኪታብ የሚያጠኑ፣ ደዕዋ የሚያደርጉ፣ ወላጅ አልባን የሚረዱ፣ መስጂድን የሚገነቡ፣ መርከዝን የሚደግፉ፣ እርስ በርሳቸው የሚጠናከሩ ትውልድ ይፈጠራል ከዛም ትልቅ የኸይር ንቅናቄ ሊፈጥሩ ይችላሉ። ⚠️ የመጨረሻ ምክሬ ለሰፊይ ወንድምና እህቶቼ የሰለፊይ ወንድማማችነት እንዳይሰበር እንጠንቀቅ። የምንሠራውን ኸይር እንመርምር፤ የምንተቸውንም ሰው በፍትሕ እንመርምር። የአካባቢ ስም መጠቀም በራሱ ዘረኝነት አይደለም። የአካባቢን ስም በመጠቀም ሌሎችን መንቀፍና ማጥላላት ግን የሚወገዝ ነው። የአካባቢን ልጆች ለማጠናከር መሰብሰብ የሚከለከል አይደለም፤ ሌሎችን በማሳነስ ራስን ከፍ ከፍ ማድረግ ግን አይፈቀድም። የሰለፊይ ወንድማማችነት ከደሴ ይበልጣል፤ ከራያ ይበልጣል፤ ከወረባቦ ይበልጣል፤ ከአዲስ አበባ ይበልጣል ከስልጤ ይበልጣል ከኦሮሞ ከአማራ ከትግራ ከሶማሌ ከአሜሪካ ከቻይና ከቱርክ ከሳዑድ ከሁሉ ይበልጣል የትም ሀገር ቢሆን ሰለፊይ አስከሆነ ድረስ ወንድማችን ነው እህታችን ናት ይሄ ነው ሚዛናችን። ስለዚህ ከአካባቢያችን እንነሳ፤ ነገር ግን በአካባቢያችን አንወሰን ደዕዋውን እናስፋው። ከሰፈራችን እንነሳ፤ ነገር ግን ሌላውን አንግፋ። የእኛን ልጆች እናጠናክር፤ ነገር ግን የሌላውን ልጅ አንጠላ አንርሳ። በተውሒድ እንሰብሰብ፣ በሱና እንጠናከር፣ በኸይር እንተባበር፤ የአካባቢ ልዩነታችን ደግሞ የምንተዋወቅበት መንገድ እንጂ የምንለያይበት ግድግዳ አይሁን። 🌿 አላህ ልባችንን በተውሒድና በሱና ላይ ያሰባስበን፤ በኸይር ላይ እንድንተባበር ያድርገን፤ ከጃሂሊያ የወገንተኝነት መንፈስም ይጠብቀን። አሚን። 🌿 ከአካባቢ ተነስተን—ለኡማው  ተውሒድና ሱናን እናድርስ! ውድ ሰለፊይ እህትና ወንድሞች በዚህ ፅሁፍ ላይ ስህተት ካገኛችሁ መታረም ያለበት ነገር ካለ ጠቁሙኝ አስተካክሉኝ ይሄን ፅሁፍ በመልካም ተረዱት መልካም ነገር ታስቦ የተፃፈ ነውና። t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

✍     ቆንጅዬ፣ ዓሊም እና የዓሊም ልጅ የተዳረችበት: ማራኪ እና እውነተኛ ታሪክ!!   ሰዒድ ኢብኑ ሙሰይብ ብርቅዬ ከሆኑ የኢስላም ቀደምት ምሁራኖች ውስጥ አንዱ ነው። የዕውቀት ማዕዱ በጣም በርካታ የሆኑ የዲን ተማሪዎች ተሰብስበው ይጣዱት እንደነበር ታሪክ ያረጋግጣል። ከዕለታት በአንዱ ቀን ተማሪዎቹ ሲመለከት ከመሃል አንድ ወጣት ከትምህርት ቦታው ይጠፋል። ሲጠባበቀው ቆየና ወደ ትምህርት ቦታው የተመለሰ ቀን ጠየቀው። "ወዳጄ ሆይ! የት ሆነህ ነው እስከዛሬ ያልመጣኸው?" ሲል ጠየቀኝ።  ይላል "ባለቤቴ ሙታብኝ እሷን እየደፈንኩ እና በሷ ጉዳይ ተወጥሬ ነው።" ብዬ መለስኩለት ሰዒድ:  "ታድያ አትነግረንም ነበርን? ቢያንስ እኮ መጥተን እንኳ እናፅናናህ ነበር።" አለኝ አስከትሎም:  "እሺ አሁንስ ሌላ ለማግባት ያሰብከው ነገር አለን?" አለኝ "ኣ…ኢ…ኢ እኔ እኮ ከሦሥት ዲርኸም ሌላ የሌለኝ ሰው ነኝ ማን ይድረኛል?" አልኩት። ሰዒድ:  "ሱብሃነላህ!! ሱብሃነላህ!! ሦሥት ዲርኸም አንድን ሙስሊም አትሰትርም ማለት ነው??" አለኝ በመገረም "ማን ይድረኛል??" አልኩት "እኔ!!" አለኝ "ያቺ መሪዎች እና ሚኒስትሮች እየጠየቁ የተከለከለችዋ የሰዒድ ኢብኑ ሙሰይብ ልጅ!?" አልኩት "እኔ እድርሃለው።"   አለኝና እዛው ከመስጂድ አካባቢ የነበሩ ሰዎች ጠርቶ ሰበሰባቸውና   "እከሊት የእከሌ ልጅ: የእከሌ ልጅ ለሆነው እከሌ በሁለት ዲርኸም ድረነዋል!!" ብሎ ኒካህ አሰረልን።   በዚህ ጊዜ በደስታ የምከንፍ እየመሰለኝ ስፈናጠር ወደ ቤቴ ሄድኩኝ። የመግሩብ ወቅት ደረሰ፤ ጾመኛ ነበርኩኝና ለማፍጠር ዳቦዬ ምናምን ይዤ ቁጭ እንዳልኩ የቤቴ በር ተንኳኳ "ማን ነው?" ስል "ሰዒድ ነኝ።" የሚል ምላሽ ሰማሁ   አእምሮዬ ላይ የማውቃቸው ሰዒዶች ሁሉ ተመላለሱብኝ; ሰዒድ ኢብኑ ሙሰይብ ሲቀር፤ ምክንያቱም ሳውቀው አርባ ዓመታት በሙሉ ከቤቱ ወደ መስጂድ: ከመስጂድ ወደ ቤቱ ሲመላለስ እንጂ ሌላ ቦታ አይቼው አላውቅም ነበር። ተነስቼ በሩን ስከፍተው ሰዒድ ኢብኑ ሙሰይብ ነው በውስጤ "በቃ ሀሳቡን ቀይሮ ነው" አልኩኝ "በዚህ ሰዓት ለምን መጣህ? ብታስጠራኝ እኮ እኔ እመጣልህ ነበር።" አልኩት "ኣ…ኣ…ይ የአንተ ዐይነቱ እኮ ወደ እሱ ይመጣል እንጂ እሱ እንዲመጣ አይጠራም።" አለኝ   "እንግዲያውስ ድረንሃል: የዛሬዋ ምሽት ሚስትህ እኔጋ ሆና ላጤ ሆነህ ላሳድርህ ስላልፈለኩ ይዤልህ መጥቼ ነው።" ብሎ ከኋላው ጥቁር ለብሳ ቆማ የነበረችው ወደ ቤት ገፈተራት።   በድንጋጤ መሬት ላይ ወደቀች። "بارك الله لك وبارك عليك እቺ ሚስትህ ናት" አለኝና ትቶን ሄደ።   ስመለከታት የውበት ማማ የተላበሰች ሴት ናት። በአላህ እምላለሁ ዐይኔ ከእሷ በፊት እንደዚህ ያለ ውበት ዐይታ አታውቅም።   እየሮጥኩኝ ወጥቼ ጎረቤቶቼን ጠራኋቸው "ሰዒድ ኢብኑ ሙሰይብ ልጁን ድሮኛል: ይኸው አሁን ከመሸ ነው ይዟት የመጣው: ሄጄ ለእናቴ እስከምነግራት ገብታችሁ አጫውቷት።" ብያቸው ወደ እናቴ ሄድኩኝ። ለእናቴ ሄጄ ስነግራት   "እኔ መጥቼ ሦሥት ቀናት ድረስ ሞሽሬያት እስከምሰጥህ ድረስ ብትጠጋት ፊቴ በፊትህ ላይ ዕርም አድርጌብሃለው: እኔ እስክመጣ እንዳትነካት" አለችኝ።   እናቴ መጥታ ሦሥት ቀናት ሞሽራ አስዋበቻትና ገባሁኝ: "ወላሂ ዐይኔ እንደሷ ያለ ውብ ዐይቶ አያውቅም።" ከተናገረች ያማረ ንግግር ነው የምትናገረው: ዝም ካለችም ያማረ ዝምታ ነው ዝም የምትለው።   ከእሷ ጋ አብሬ አንድ ወር ቆየሁኝ: ከሷ ያየሁት ነገር የለም; ቀን መጾም እና ለይል መስገድ ቢሆን እንጂ። ከወር በኋላ ወደ ሰዒድ ሄጄ ትምህርቴን ለመቀጠል ፈለኩኝ። "ወዴት ነው ምቴደው?" አለችኝ "ለመማር ወደ ሰዒድ" አልኳት "አርፈህ ተቀመጥ!! የሰዒድ ዒልም በአጠቃላይ እኔጋ አለ፤ እሱ የሚሰጥህ እኔ እሰጥሃለሁ።" አለችኝ   ሆኖም ከአንድ ወር በኋላ ወደ ሰዒድ ሄድኩኝ: መቀመጫው ላይ ሆኖ ሲያየኝ ፈገግ አለ። ሁሉም ሰው ጨርሶ እስኪወጣ ድረስ ግን ምንም አላናገረኝም።   የነበረው ሰው ጨርሶ ከወጣ በኋላ መጥቼ ከፊት ለፊቱ ተቀመጥኩኝ። "እንግዳችሁ እንዴት ናት?" አለኝ "በጣም ደስስስ በሚል ሁኔታ" አልኩት። "እንግዲያውስ የማያስደስትህ ነገር ካገኘህ ዱላህን …………:" አለኝና ሀያ ሺህ ዲናር በእጄ አስጨበጠኝና "አንተ እና እሷ ለጉዳያችሁ ተጠቃቀሙባት።" ብሎ ተሰናበተኝ። ይላል።                    ታሪኩ አበቃ! ምንጭ 📚[سير أعلام النبلاء ترجمة سعيد ابن مسيب /ج٤/ ص٢٣٤] https://t.me/Wku_ms_Official_Channel

قال النبي صلى الله عليه وسلم: مثلُ المؤمنِ الَّذي يقرأُ القرآنَ كالأُتْرُجَّةِ طعمُها طيِّبٌ وريحُها طيِّبٌ والَّذي لا يقرأُ كالتَّمرةِ طعمُها طيِّبٌ ولا ريحَ لها ومثلُ الفاجرِ الَّذي يقرأُ القرآنَ كالرَّيْحانةِ ريحُها طيِّبٌ وطعمُها مُرٌّ ومثلُ الفاجرِ الَّذي لا يقرأُ القرآنَ كمثلِ الحنظلةِ طعمُها مرٌّ وريحُها مرٌّ شرح الحديث : كلامُ اللهِ المجيدُ له تأثيرٌ في باطِنِ العَبدِ وظاهِرِه، وإنَّ العِبادَ مُتفاوِتون في ذلك؛ فمنهم مَن له النصيبُ الأوفَرُ من ذلك التأثيرِ، وهو المؤمِنُ القارئُ، ومنهم مَن لا نصيبَ له ألبتَّةَ، وهو المنافِقُ الحقيقيُّ، ومنهم مَن تأثَّر ظاهِرُه دون باطِنِه، وهو المرائي، أو بالعَكسِ، وهو المؤمِنُ الذي لا يَقَرُؤه. وفي هذا الحديثِ دَعوةٌ مِن رَسولِ اللهِ صلَّى اللهُ عليه وسلَّم لقراءةِ القرآنِ، وحثٍّ على الانتفاعِ به ظاهِرًا وباطِنًا، ونفعِ النَّاسِ به، وقد ضرَبَ فيه صلَّى اللهُ عليه وسلَّم مَثَلًا يُقسِّمُ فيه الناسَ وعَلاقتَهم بالقرآنِ إلى أربعةِ أقسامٍ: القِسمُ الأولُ: هو المُؤمنُ الذي يَقرَأُ القرآنَ ويَنتفِعُ به، فيَعمَلُ بما يَقرَأُ، ويَنفَعُ عِبادَ اللهِ، وهذا شبَّهه رسولُ اللهِ صلَّى اللهُ عليه وسلَّم بثَمَرةِ الأُتْرُجَّةِ، وهو ثَمَرٌ جامِعٌ لِطِيبِ الطَّعْمِ والرَّائحةِ وحُسْنِ اللَّونِ، ومَنافِعُه كَثيرةٌ. ويُسَمَّى في بَعضِ البُلدانِ بالأُترُجِّ، وهو مِنَ الحِمْضيَّاتِ يُشبِهُ اللَّيمونَ، وحَجمُه أكبَرُ من البُرتقالِ، وقِشرتُه مُتعَرِّجةٌ. وأما القِسمُ الثاني: فهو المؤمنُ الذي طاب باطِنُه لثَباتِ الإيمانِ فيه، وقيامِه بالواجباتِ، غيرَ أنَّه لا يَقرَأُ القرآنَ، باستثناءِ الواجبِ منه كالفاتحةِ، فشَبَّهُه رسولُ اللهِ صلَّى اللهُ عليه وسلَّم بالتَّمْرةِ؛ طَعْمُها حُلْوٌ، ولا رِيحَ لها؛ فاشتِمالُه على الإيمانِ كاشتِمالِ التَّمرةِ على الحلاوةِ، بجامعِ أنَّ كِلَيهما أمرٌ باطنيٌّ، وعدمُ ظُهورِ رِيحٍ لها يَستريحُ الناسُ لشَمِّه؛ لعَدَمِ ظُهورِ قِراءةٍ منه يَستريحُ النَّاسُ بسَماعِها. وأما القسمُ الثالثُ: فهو المُنافقُ الذي يَقرَأُ القرآنَ، ولا يُصلِحُ قلْبَه بالإيمانِ، ولا يَعمَلُ به، ويَتظاهَرُ أمامَ الناسِ أنَّه مُؤمنٌ، فهو من حيثُ تَعطُّلُ باطنِه عنِ الإيمانِ واستراحةُ الناسِ بقراءتِه، مِثْلُ الرَّيحانةِ لها رائحةٌ طيِّبةٌ وطعْمُها مُرٌّ؛ فرِيحُها الطيِّبُ يُشبِهُ قِراءتَه، وطعْمُها المرُّ يُشبِهُ كُفرَه. وأمَّا القِسمُ الرابعُ: فهو المُنافقُ الذي لا يَقرَأُ القُرآنَ، شبَّهه النَّبيُّ صلَّى اللهُ عليه وسلَّم من حيثُ تَعطُّلُ باطنِه عنِ الإيمانِ، وظاهرِه عن سائرِ المنافعِ، وتلبُّسُه بالمضارِّ؛ بالحنظلةِ، حيثُ إنَّها لا رائحةَ لها، وفيها ما فيها منَ المَذاقِ المُرِّ؛ فانعِدامُ رِيحِها أشبهُ بانعدامِ رِيحِه لعدمِ قِراءتِه، ومَرارةُ طعْمِها شَبيهٌ بمَرارةِ كُفرِه. وهذه التشبيهاتُ وارِدةٌ على التقسيمِ الحاصِرِ للنَّاسِ؛ لأنَّ النَّاسَ إمَّا مؤمِنٌ أو غيرُ مؤمِنٍ، والثَّاني إمَّا منافِقٌ صِرفٌ أو مُلحَقٌ به، والأوَّلُ المؤمِنُ إمَّا مواظِبٌ على القراءةِ أو غيرُ مواظِبٍ عليها. وقَولُه صلَّى اللهُ عليه وسلَّم: «يقرأُ القُرآنَ» على صيغةِ المضارعِ ونَفْيِه في قَولِه: «لا يقرَأُ» ليس المرادُ منهما حصولَها مرَّةً ونَفْيَها بالكُليَّةِ، بل المرادُ منهما الاستمرارُ والدَّوامُ عليهما، وأنَّ القِراءةَ دأبُه وعادتُه، أو ليست عادةً له. وفي الحَديثِ: فَضيلةُ حامِلِ القُرآنِ، وفَضْلُ القُرآنِ على غيرِه من الكلامِ. وفيه: أنَّ المقصودَ مِن تلاوةِ القُرآنِ العَمَلُ، كما دَلَّ عليه قَولُه «ويَعمَل به».

የኡስታዞች መታጣት ወይስ ኡስታዞች ገቢ ማጣት? በተቻለ ያህል የዲን ሀላፊነት ላይ ያሉ ሰዎችን ማገዝ ሙስሊሙን ህዝብ ከማገዝ እና ለአኺራ ስንቅን ከማዘጋጀት መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም።ነገር ግን ባሁኑ ሰዓት ትልቁ ችግር ኡስታዞች የሚኖሩበትን ያህል ገቢ ያለማግኘት አይደለም።በብዛት ቁርኣንም ይሁን ኪታብ አስተማሪዎች ወይ በደሞዝ አልያም በክፍያ ነው የሚያስቀሩት ትልቅ ችግር እየሆነ ያለው ነገር ዳዒዎችን አራት አምስቴ እንኳ ጠርቶ ያለማግኘት ነው።በክፍያ እንኳን በተገኙ!!ምክንያቶቹ ብዙ ቢሆኑም ሙሉ በሙሉ በአካባቢ ቂርኣት ቢዚ መሆን እና በዱንያ ጉዳይ መይያዝ ተጠቃሽ ናቸው። ከጥቂት አመታት በፊት ችግሩ በዚህ ደረጃ አልነበረም።በየአካባቢው በጥቂት ሳምንታት ወይም ወራት ውስጥ በቀላሉ የደዕዋ እድል ይገኝ ነበር።አሁን ላይም ቢሆን-አላህ የኸይር ጀዛቸውን ይመንዳቸውና-ጊዜ እና ሌላ ሐጃቸውን መስዋዕት አድርገው ለደዕዋ ቅድሚያ ሚሰጡ ዳዒዎች መኖራቸው አይካድም። ደዕዋ በማድረግ የሚገኘው ጥቅም ኪታብን እንደማስቀራት ጥልቅ ባይሆንም እንኳን ተነሳሽነትን እና ወኔን ከመፍጠር አንፃር የሚናቅ አይደለም።ብዙ መለማመጥ ሳይኖር ዳዒዎች ተናበው የተቀናጀ ስራ ቢሰሩ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ይቻላል።የማይሳካ ከሆነም ሌላ የሚያነቃን አካል ሳንጠብቅ በራሳችን ተነሳስተን መደበኛ የዒልም ማዕዶችን መከታተል እና በአላህ ፍቃድ ለወደፊት ችግሩን ለመፍታት የተቻለንን ያህል ማድረግ ነው።والله أعلم
منقول

ስለ ጀምዕያ   የተደረጉ በውድ እና በሱና ኡስታዞች  ሙሓደራወች ስብሰብ በቀላሉ ለማገኘት👇👇👇👇👇👇
የተለያዩ መሳጭ ዳእዋወች ርዕሶቹ ከዚህ በታች ናቸው ርዕሱን አንዲ ብቻ በመካት  ማዳመጥ ይችላሉ አከባቢ ❶❹ ሙሓደራወች
❶ጀምዕያ ማለት ምን ማለት ነው ❷ኡለሞች የፈቀዷት ጀምእያ ❸እውን በጀምዕያ ብቻ ሰዎችን ከሱና ማስወጣት ይቻላልን? ❹ጀምዕያ እና ተያያዥ ነጥቦች ❺ጀምእያ በረሱል ጊዜ ከሌለች ለምን ቢድአ አልተባለችም? ❻ጀምእየቱል ኸይርያ ❼ጀምዕያ እና ሹበሀወች ➑በስማቸው የተመሰረት ያቋቋሙት ጀምዕያ ❾ሙስጠፋ ጀምዕያ የፈቀደበት ➓ሙስጠፋ  ጀምዕያን በግልፅ ሲፈቅድ  ጀምዕያ ላይ ውይይት ሰለፍዮች እና ሀጁሪዩች
ኡስታዝ  አቡ ረይስ ሙሐመድ  እና ሌሎችም ወንድሞች እና ሀጁሪዮች
ክፍል ❶ ክፍል ❷ በከለላ ከተማ የተደረገ
በኡስታዝ አቡ ሂዛም አብዱረህማን ሰኢድ &የተለያዩ ሀጁሪዮች
ክፍል ❶ ክፍል ❷

ጊዜ ሰጥተን እያወረድን እናዳምጠው።ምርጥ የአቂዳ ኪታብ ነው እየተቀራ ያለው ባረከላሁ ፊኩም

+3
ደርስ፦ ~ * ዐቂደቱ አህሊ ሱና ወልጀማዐህ * ክፍል - 01 * የሚሰጥበት ቦታ፦ ዘህራእ መስጂድ (አሸዋ ሜዳ ኮንዶሚኒየም ዝቅ ብሎ) * የሚሰጥበት ጊዜ፦ ሰኞና ማክሰኞ ከመግሪብ በኋላ = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ጥያቄ ?   📮📮   ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል። 📝 ጥያቄ እውነት/ ሀሰት በማለት መልሱ ። የጀነት በር ጠባቂ መላዒካ ረድዋን  ይባላል፡፡

⚠️አስቸኳይ የነፍስ አድን ጥሪ 👉ያአህባብ እዪልኝ ይሄን በጭፈራ ላይ የተመሠረተ አምልኮ የልዕለ ሀያሉ ጌታችንን አላህ ሱብሀነሁ ወተዐላ እንደት እንደተዳፈሩት እያያችሁ ነዉ የመኪና ብዛት  የህዝብ ስብስብ  ዶሪህ ለመለመን ችግራቸዉን ለጅን አቤቱታ የሚያቀርቡ  ከሙስሊሙ የወጡ ሰዎች ባሻገር ክሪስቲያኖች ጭምር ለአላህ በመናገር ፋንታ ግን እነሱ ምንም ለማያደርግላቸዉ ዶሪህ ተናግረዉ ይሄዳሉ በአመቱ ተመልሰዉ መተዉ ስለታቸዉን ለጅን ያርዳሉ!! የቦረናው ሸህዬ  የቦረናው ደግዬ እርዱን አባብዬ ይህ የሽርክ ግጥም የሚዘመርባት ከተማ ከ500ሺ ህዝብ በላይ ሽርክን ለማንገስ ከአድስ አበባ እስከ ባሌ ከወለጋ እስከ ሐረር ከወሎ እስከ ጎጃም  ከጎንደር እስከ ሸዋ ሳይቀር ሰው ስለቱን ይዞ ኮርማውን እየነዳ ሽቱውን ገዝቶ መጋረጃ ሸምቶ ልክ እንደ ግሸን ማርያም ክብረ_በዓል መንገድ በአይሱዚና በቅጥቅጥ እንድሁም በህዝብ ብዛት ጥቅምት 15 የዶሪኋን ታቦት በማነገስ ከተማዋ ትጨናነቃለች ። በዚያ ሌሊት  የሚጎራ ጉሪያ የሚወገር ድቤ የሚጮህ ጩኸት የሚለቀስ ለቅሶ የሚጨስ አድሩስ የሚታረድ በግና ፍየል ምን ልበልህ ባጭሩ ራሷ ከተማዋ ታብዳለች ።   ለወንድም እህቶቼ ፦ ወንድም እህቶቼ፣ በየዓመቱ ብዙ ሰዎች ችግራቸውን ይዘው ወደ እዚህ  ቦታዎች ይጓዛሉ። ብዙዎቹ በሕመም፣ በችግርና በጭንቀት የተጎዱ ናቸው።
ስለምንወዳቸው ነው የምናስታውሳቸው፤ ከአላህ ውጭ ሌላ አያድናቸውም።
1️⃣ አላህ ቅርብ ነው وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ «ባሮቼ ስለ እኔ ቢጠይቁህ እኔ ቅርብ ነኝ፤ ለማኙ ሲለምነኝ ልመናውን እቀበላለሁ።»
ሱረቱል -በቀራህ  ምዕራፍ 2:አንቀፅ 186
وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ «ጌታችሁም አለ፦ ለምኑኝ፣ እመልስላችኋለሁ።»
ሱረቱል ጋፊር ምዕራፍ 40:አንቀፅ 60
አላህ ከእኛ ጋር አማላጅ ሳያስፈልገው ቅርብ ነው። በሌሊት፣ በሱጁድ፣ በየትኛውም ቦታ ልንለምነው እንችላለን። 2️⃣ ዱዓ ኢባዳ ነው «الدُّعَاءُ هُوَ الْعِبَادَةُ» «ዱዓ (ልመና) ኢባዳ (አምልኮ) ነው።»
📚ቲርሚዚ፣ አቡ ዳውድ ዘግበውበታል
ኢባዳ ደግሞ ለአላህ ብቻ ይገባል፦ وَأَنَّ الْمَسَاجِدَ لِلَّهِ فَلَا تَدْعُوا مَعَ اللَّهِ أَحَدًا «መስጊዶች የአላህ ናቸው፤ ስለዚህ ከአላህ ጋር ማንንም አትለምኑ።»
ሱረቱል አል-ጂን ምዕራፍ 72:አንቀፅ 18)
«إِذَا سَأَلْتَ فَاسْأَلِ اللَّهَ، وَإِذَا اسْتَعَنْتَ فَاسْتَعِنْ بِاللَّهِ» «ከጠየቅህ አላህን ጠይቅ፤ ርዳታ ከፈለግህ በአላህ ተረዳ።»
📚ቲርሚዚ ዘግበውታል
3️⃣ ከአላህ ሌላ የሚለመኑት ሊጠቅሙ አይችሉም وَالَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِ مَا يَمْلِكُونَ مِن قِطْمِيرٍ ۝ إِن تَدْعُوهُمْ لَا يَسْمَعُوا دُعَاءَكُمْ እነዚያም ከእርሱ ሌላ የምትገዟቸው የተምር ፍሬ ሽፋን ያህል እንኳን አይኖራቸዉም:: ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም:: ቢሰሙም ኖሮ ለእናንተ አይመልሱላችሁም
ሱረቱል ፋጢር ምዕራፍ 35:አንቀፅ 13-14
ምንም ሊያደርጉልን የማይችሉትን መለመን ጊዜና ተስፋ ማባከን ነው። 4️⃣ ማረድ ለአላህ ብቻ قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ ۝ لَا شَرِيكَ لَهُ «በል፦ ሶላቴ፣ እርዶቼ (ሥርዓተ አምልኮዬ)፣ ሕይወቴና ሞቴ ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው። አጋር የለውም።»
ሱረቱል አል-አንዐም ምዕራፍ 6:አንቀፅ 162-163
«لَعَنَ اللَّهُ مَنْ ذَبَحَ لِغَيْرِ اللَّهِ» «ለአላህ ላልሆነ ያረደን አላህ ረግሟል።»
📚(ሙስሊም) ዘግበውታል
5️⃣ ሽርክ ከሁሉ የከበደ ሐጢአትነው إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ «አላህ በእሱ ላይ ማጋራትን አይምርም፤ ከዚያ ሌላውን ለሚሻው ይምራል።»
ሱረቱል   አን-ኒሳእ አን ምዕራፍ 4:አንቀፅ 48
ስለዚህ ነው የምናስጠነቅቀው፤ ስለምንጠላችሁ ሳይሆን ስለምንወዳችሁ። ወደ አላህ መመለስ (ተውበት) በር ግን ዛሬም ክፍት ነው። 6️⃣ ምን እናድርግ❓ 🤲 ችግራችሁን በሌሊት ተነስታችሁ በሱጁድ ለአላህ አቅርቡ። 🩺 ሕመም ካለ ወደ ሐኪም ሂዱ፤ ከሕክምና ጋር ሩቅያ ሸርዒያን (በቁርኣንና በነቢያዊ ዱዓዎች መታከምን) ተጠቀሙ። 💝 ሰደቃ ስጡ፤ ለችግረኛ መርዳት ችግርን ያቀልላል። 📖 ተውሒድን ከታመኑ ዑለማ ተማሩ። 🌿 ቤተሰብና ጎረቤትን በፍቅር፣ በትዕግስትና በግል አነጋግሩ። አላህ ሁላችንንም ከሽርክ ይጠብቀን፣ ችግር ውስጥ ያሉትንም አውጣቸው፣ ወደ ቀጥተኛው መንገድም ይምራን። አሚን። የቴሌግራም ቻናል t.me/yedeger_selefioch_jemea የቴሌግራም ግሩፕ t.me/yedeger_muslim_Wetatoch_jemea

Repost from N/a
ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  ብዙ  የሱና ቻናሎችን add የሚለውን በመጫን ያገኛል ። የሱና ቻናል ያላቹ👉 @Quran_mylife1 ጥያቄ 1 💎ተዉሂድ በስንት ይከፈላል?

📍አዲስ አፕልኬሽን ተለቀቀ !! ❝ የአሕባሾች የሽርክ መንዙማ ❞ የተለያዩ ሙነሺዶች { ሙዚቀኞችን } የሽርክ መንዙማ ከነድምፅ ማስረጃ ጋር የተብራራበት ወሳኝ ትምህርት !! ➨ሼር በማድረግ ማህበረሳችንን ከሽርክ እናንቃ ወደ መልካም አመላካች እንሁን ! 🎙የትምህርቱ አቅራቢ ፦ ❴ አብዱረሕማን አቡ ዑሰይሚን حفظه الله ❵ t.me/abuUseyminabdurehman

እሄን የ ቁርአን አያ ተጋበዙልኝ ቆንጆ አርጋችሁ በመቅራት 👌🏾📖 إِنَّ الْمُسْلِمِينَ وَالْمُسْلِمَاتِ وَالْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ وَالْقَانِتِينَ وَالْقَانِتَاتِ وَالصَّادِقِينَ وَالصَّادِقَاتِ وَالصَّابِرِينَ وَالصَّابِرَاتِ وَالْخَاشِعِينَ وَالْخَاشِعَاتِ وَالْمُتَصَدِّقِينَ وَالْمُتَصَدِّقَاتِ وَالصَّائِمِينَ وَالصَّائِمَاتِ وَالْحَافِظِينَ فُرُوجَهُمْ وَالْحَافِظَاتِ وَالذَّاكِرِينَ اللَّهَ كَثِيرًا وَالذَّاكِرَاتِ أَعَدَّ اللَّهُ لَهُم مَّغْفِرَةً وَأَجْرًا عَظِيمًا ሙስሊሞች ወንዶችና ሙስሊሞች ሴቶች፣ ምእምናንና ምእምናትም፣ ታዛዦች ወንዶችና ታዛዦች ሴቶችም፣ እውነተኞች ወንዶችና እውነተኞች ሴቶችም፣ ታጋሾች ወንዶችና ታጋሾች ሴቶችም፣ አላህን ፈሪዎች ወንዶችና አላህን ፈሪዎች ሴቶችም፣ መጽዋቾች ወንዶችና መጽዋቾች ሴቶችም፣ ጿሚዎች ወንዶችና ጿሚዎች ሴቶችም፣ (ካልተፈቀደ ሥራ) ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች ወንዶችና ጠባቂ ሴቶችም፣ አላህን በብዙ አውሺዎች ወንዶችና አውሺዎች ሴቶችም፣ አላህ ለእነርሱ ምሕረትንና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ አላህ ከ እናሱ ያርገን 🤲🏾