ru
Feedback
​🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹

Открыть в Telegram

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
1 376
Подписчики
+1824 часа
+3637 дней
+64630 дней
Архив постов
ተጀመረ
አዲስ የኪታብ ደርስ
      📖ኪታቡ አልቀዋዒዱል ሙስላ 🎤በኡስታዝ አቡ ኢምራን የኪታቡን PDF ለማግኘት https://t.me/sefinetunuh/9009 ደረሱ የሚሰጠዉ 🌙በአህሉ-ተውሂድ መስጂድ  - - ሸር አድርጉት https://t.me/sefinetunuh?livestream=2aa0f105b7a048c75d

"ሥራ አጥቶ እየተንከራተተ ያለን "መቼ ነው ሥራ የምትጀምረው?" ብለህ ሌላ ጭንቀት አትጨምርበት። አማራጭ ሲጠፋው ሀገሩን ለቆ በስደት ያለን "መቼ ነው የምትመለሰው?" እያልክ ብሶቱን አትቀስቅስበት።
"ሥራ አጥቶ እየተንከራተተ ያለን "መቼ ነው ሥራ የምትጀምረው?" ብለህ ሌላ ጭንቀት አትጨምርበት። አማራጭ ሲጠፋው ሀገሩን ለቆ በስደት ያለን "መቼ ነው የምትመለሰው?" እያልክ ብሶቱን አትቀስቅስበት። ትዳር የዘገየባትን ሴት "መቼ ነው የምታገቢው?" እያልክ አትነዝንዛት። ራስ ምታት አትሁንባት! ሀሳብና ጭንቀታቸውን ታግለው አፍነው የአላህን ፈረጅ በትዕግስት የሚጠባበቁን ጥያቄ በማብዛት ሌላ ችግር አትሁንባቸው። ምን እንደሚጠብቁ አትጠይቃቸው! ከመጠበቅ ውጪ ሌላ አማራጭ ቢኖራቸው ያደርጉት ነበር!! ሪዝቅ ያለው በአንተ ሳይሆን በአላህ እጅ ነውና ተዋቸው። ከቻልክ አግዛቸው፤ አልያም ዱዓ አድርግላቸው! ካልቻልክ አትረብሻቸው ዝም በላቸው!   ✍ኡስታዝ ዛኪር

ለእነዚያ ላኩላቸው ማንነታቸውን ለረሱ ወዳጅ ሆይ ​ሌሎችን ለመምሰል መሞከር ማለት የእራስህን ታሪክ ሳይሆን የሌሎችን ሁለተኛ ደረጃ ታሪክ መኖር ማለት ነው። የሰው ልጅ ትልቁ ስህተት የእርሱን ጥንካሬ እና ድካም ከሌሎች ጋር ማወዳደሩ ነው። ሌሎች በሄዱበት መንገድ ስለሄድክ ብቻ ስኬታማ አትሆንም፤ የእነርሱ መንገድ ለነርሱ የተዘጋጀ እንጂ ለአንተ የተሰራ አይደለም። ​አስታውስ፦ ኦሪጅናል ሁነህ መኖር እያለህ የሌሎች ኮፒ ሆነህ አትሙት። ​የሰዎችን ፍርድ እና አስተያየት አትፍራ ​ሰዎች ሁልጊዜ ይፈርዳሉ፤ ያማሉ፤ ያወድሳሉ፤ መልሰው ደግሞ ያናንቃሉ። የሰዎችን አስተያየት የህይወትህ መመሪያ ካደረግከው የነርሱ ባሪያ ትሆናለህ። ራስን መሆን ማለት ሁሉም ሰው እንዲወድህ ማድረግ ማለት አይደለም፤ ይልቁንም ሰዎች ቢወዱህም ባይወዱህም እውነተኛ ማንነትህን ሳትደብቅ መኖር ማለት ነው። ​አስብበት፦ የሰው ልጅ ውዳሴ ጊዜያዊ ነው፤ የውስጥ ሰላም ግን ዘላቂ ነው። ሰዎችን ለማስደሰት ስትል ራስህን አታጣ። ​ራስን መሆን ማለት "እኔ ፍጹም ነኝ" ማለት አይደለም። ራስን መሆን ማለት ድክመቶችህን አምነህ መቀበል፣ ስህተቶችህን ለመታረም ዝግጁ መሆን እና እግረ መንገድህንም አላህ የሰጠህን አቅም እና ክህሎት ማወቅ ነው። እውነተኛ ጥንካሬ የሚጀምረው የራስን ማንነት ሙሉ በሙሉ ከተቀበሉበት ቅጽበት ነው። ​ተገንዘብ፦ ነጠብጣብ ያለው እብነ በረድ እንጂ ፍጹም የሆነ ድንጋይ የለም። ድክመትህ የአንተ አካል ነው፤ እሱን ተቀብለህ ወደ ጥንካሬ ቀይረው። ​በቀን ውስጥ ለጥቂት ደቂቃዎች ብቻ እንኳ ቢሆን ፀጥታን ፈልግ። ከውስጥህ ድምፅ ጋር ተነጋገር። - ​በእርግጥ እየኖርክ ያለኸው የሚወዱትን ህይወት ነው? - ​የምታደርጋቸው ነገሮች ከእውነተኛ ፍላጎትህ የመጡ ናቸው ወይንስ ሰዎችን ለማስደሰት የምታደርጋቸው? - ​ከራስህ ጋር ታማኝ ሁን። ራስህን ሳታታልል እውነቱን ስትነግረው ውስጣዊ ድፍረትና ግልጽነት ታገኛለህ። ​ለህይወትህ የሚሆን የወርቅ ህግ ​"ራስህን ሁን፤ ምክንያቱም ሌሎች ቦታዎች በሙሉ ተይዘዋል።" ወዳጄ ​ዛሬ ውሳኔ ወስን፦ ​የሌሎችን ሁኔታ አትከታተል። ​በራስህ መንገድ ላይ በጽናት ሂድ። ​እውነተኛ ማንነትህን፣ እምነትህን፣ እና እሴቶችህን በኩራት ያዝ። ​ራስህን መሆን ስትጀምር፣ ህይወትህ ትርጉም ያገኛል፤ አእምሮህ ሰላም ያገኛል፤ መንገዶችህም ሁሉ ይከፈታሉ። 🖋𝓪𝓫𝓾 𝓶𝓪𝓻𝓲𝔂𝓪𝓱 https://t.me/BerhanFelega https://t.me/BerhanFelega

2ኛ — ተውሒዱል ኡሉሂያ (توحيد الألوهية) 📢ተውሒዱል ኡሉሂያ ማለት፦ አላህን በባሮቹ የአምልኮ ተግባራት ብቻውን መለየት ማለት ነው። እንዲሁም “ተውሒዱል ዒባዳ” (የአምልኮ አንድነት) ተብሎ ይጠራል። ትርጉሙም፦ አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እውነተኛው ኢላህ እንደሆነና ከእርሱ ውጭ እውነተኛ ኢላህ እንደሌለ በጽኑ ማመን ነው። ከእርሱ ውጭ የሚመለክ ሁሉ ባዶና ሐሰት ነው። ስለዚህ አምልኮን፣ መገዛትንና ፍጹም መታዘዝን ለአላህ ብቻ መለየት፣ ማንም ይሁን ማን ከአላህ ጋር ማንንም አለማጋራት እና ከአምልኮ አይነቶች ምንም ነገር ለሌላ አለመስጠት ነው። ከአምልኮ አይነቶችም፦ ሰላት፣ ጾም፣ ዘካ፣ ሐጅ፣ ዱዓ፣ እርዳታን መፈለግ፣ ነዝር (ስለት)፣ መስዋዕት ማቅረብ፣ ተወኩል (በአላህ ላይ መመካት)፣ ፍርሃት፣ ተስፋ፣ ውዴታ፣ ወደ አላህ መመለስ፣ አላህን መፍራት፣ መዋረድና ሌሎችም የውጭና የውስጥ የአምልኮ አይነቶች ናቸው። አላህም በውዴታ፣ በፍርሃትናበተስፋ ሁሉም በአንድነት መመለክ አለበት። ከእነዚህ አንዱን ብቻ ይዞ ሌሎቹን መተው ጥመት ነው። 💡አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ይላል፦ ﴿إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ﴾ “አንተን ብቻ እናመልካለን፤ ከአንተም ብቻ እርዳታን እንለምናለን።” 💡እንዲሁም አላህ ይላል፦ ﴿وَمَنْ يَدْعُ مَعَ اللَّهِ إِلَهًا آخَرَ لَا بُرْهَانَ لَهُ بِهِ فَإِنَّمَا حِسَابُهُ عِنْدَ رَبِّهِ إِنَّهُ لَا يُفْلِحُ الْكَافِرُونَ﴾ “ከአላህ ጋር ሌላ አምላክን የሚጠራ፣ ለእርሱም ምንም ማስረጃ የሌለው ሲሆን፣ ሒሳቡ በጌታው ዘንድ ብቻ ነው። በእርግጥ ካፊሮች አይሳካላቸውም።” وتوحيد العبادة من أجله خلق الله الجن والإنس، قال تعالى: “የአምልኮ ተውሒድን ለመፈጸም ነው አላህ ጂንንና ሰውን የፈጠረው፤ አላህም እንዲህ አለ፦” ﴿وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالإِنْسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ﴾ “ጂንንና ሰውን የፈጠርኩት እንዲያመልኩኝ ብቻ ነው።” ተውሒዱል ዒባዳ የዲን መጀመሪያና መጨረሻ፣ ግልጽና ውስጣዊ ነው። ይህም የመልእክተኞች ጥሪ መጀመሪያና መጨረሻ ነው። 🔹መልእክተኞች የተላኩትም ፤ መጻሕፍት የተወረዱትም ፤ የጂሃድ ሰይፎች የተመዘዙትም ለዚህ ነው። በዚህም ምክንያት በሙእሚኖችና በካፊሮች፣ በጀነት ሰዎችና በእሳት ሰዎች መካከል ልዩነት ተደርጓል። ይህም “ላ ኢላሀ ኢለላህ” (لا إله إلا الله) የሚለው ቃል ትርጉም ነው። ተውሒዱል ኡሉሂያ ሁሉም መልእክተኞች የጠሩበት ተውሒድ ነው። እሱን መካድ ደግሞ ቀደምት ሕዝቦችን ለጥፋትና ለውድቀት ያደረሰ ነው። 💡አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ይላል፦ ﴿وَمَا أَرْسَلْنَا مِنْ قَبْلَكَ مِنْ رَسُولٍ إِلا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ﴾ “ከአንተ በፊት የላክነው ማንኛውም መልእክተኛ፣ ‘ከእኔ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፤ ስለዚህ እኔን ብቻ አምልኩ’ ብለን ሳናስተምረው አልላክንም።” ✍በተውሒዱል ሩቡቢያና በተውሒዱል ኡሉሂያ መካከል ያለው ግንኙነት ተውሒዱል ሩቡቢያ ወደ ተውሒዱል ኡሉሂያ ያስገድዳል። ምክንያቱም አንድ ሰው አላህ ጌታ፣ ፈጣሪና ሁሉን ነገር አስተናጋጅ መሆኑን ካመነ፣ አላህን ብቻ ማምለክና ማንንም ከእርሱ ጋር አለማጋራት ይኖርበታል። ሙሽሪኮች ግን አንድ አምላክ ብቻ አላመለኩም። አላህ ብቻውን ለአምልኮ የሚገባው መሆኑን ክደው፣ ብዙ አማልክትን ያመልኩ ነበር። እነዚህ አማልክትም ወደ አላህ ያቀርበናል ብለው ያስቡ ነበር። ከዚህ ጋር እነዚያ ሙሽሪኮች የሚያመልኳቸው አማልክት ሊጎዱም ሆነ ሊጠቅሙ እንደማይችሉ ያውቁ ነበር። ስለዚህ አላህ በሩቡቢያ ተውሒዳቸውን በመቀበላቸው ብቻ ሙእሚኖች አላደረጋቸውም፤ ይልቁንም ከአላህ ጋር ሌሎችን በአምልኮ በማጋራታቸው ከካፊሮች መደብ አደረጋቸው። ምክንያቱም አላህ ጌታ፣ ፈጣሪ፣ ሲሳይ ሰጪ፣ ባለቤት፣ የሁሉ ነገር ተቆጣጣሪ፣ ሕይወት ሰጪና ሞት አምጪ ከሆነ፣ የፍጹምነት ባህሪያት ሁሉ ባለቤት ከሆነና ከሁሉም ጉድለት የጸዳ ከሆነ፣ ሁሉም ነገር በእጁ ከሆነ፣ እርሱ ብቻውን ኢላህ ሊሆንና ለእርሱ ምንም አጋር ሊኖረው አይችልም። ስለዚህ አምልኮ ለእርሱ ብቻ መደረግ አለበት። ይሄም የ“ላ ኢላሀ ኢለላህ” ትርጉም ነው እዚህ ላይ የአህሉ-ሱንና ወል-ጀማዓ እምነት ከሌሎች ይለያል። እነሱ “ላ ኢላሀ ኢለላህ” ማለት “ከአላህ በቀር ፈጣሪና ሲሳይ ሰጪ የለም” ብቻ ማለት ነው አይሉም። ይልቁንም ትክክለኛው ትርጉም፦ “ከአላህ በቀር በእውነት ሊመለክ የሚገባው ማንም የለም” ማለት ነው። ይህም ማለት ተውሒዱል ኡሉሂያ አላህን ብቻውን በሁሉም የአምልኮ አይነቶች መለየትን ያስፈልጋል። አምልኮም በልብ፣ በምላስ ንግግርና በልብና በአካል ተግባር ይሆናል። “ላ ኢላሀ ኢለላህ” ለሚለው ምስክርነት ሁለት ታላላቅ መሠረቶች አሉት 1ኛ፦ ሁሉንም የአምልኮ አይነቶች ለአላህ ብቻ ማድረግ፤ ለእርሱም ምንም አጋር አለመስጠት። 2ኛ፦ ከእነዚህ የአምልኮ አይነቶች ምንም ነገር ለሌላ አለመስጠት። ይህ ማለት፦ ፍጡር ለፈጣሪ ብቻ የሚገባውን መብትና ልዩ ባህሪ እንዳይሰጥ ማለት ነው፤ እነዚህም ከአላህ በቀር ማንም ሊያደርጋቸው የማይችላቸው ናቸው። ስለዚህ፦ ከአላህ በቀር ማንም አይመለክም፤ ለአላህ በቀር ለማንም ሰላት ፤  ሱጁድ ፤ ስለት አይገባም፤ ለሌላ መስዋዕት አይታረድም፤ ከአላህ በላይ በሌላ ላይ ፍጹም መተማመን አይደረግም፤ እርዳታ ከአላህ በቀር አይፈለግም፤ ከእርሱ በቀር ማንም አይጠራም። እነዚህና መሰል ነገሮች የአላህ ብቻ ልዩ መብቶች ናቸው። 🔹ለአላህ ብቻ የሚደረግ አምልኮ ሁለት ሁኔታዎች አሉት 1ኛ — ኢኽላስ (ማጥራት): አምልኮው ለአላህ ፊት ብቻ የተጣራ መሆን አለበት። 2ኛ — መከተል (ኢቲባዕ): አላህን መልእክተኛው ﷺ በሸሪዓ ባዘዘው መንገድ ብቻ ማምለክ፣ ባዘዘው መታዘዝ፣ በነገረው ነገር ማመን፣ አምልኮውም በቦታና በጊዜ መልእክተኛው ﷺ ካዘዘው ጋር የሚስማማ መሆን ነው። እርሱ የከለከለውንና ያስጠነቀቀውንም መተው አለበት። 🔹ስለዚህ አላህን በአምልኮ፣ በመገዛት፣ በመታዘዝና በዉዴታ ብቻውን መለየት፦ “ላ ኢላሀ ኢለላህ” የሚለውን ምስክርነት መፈጸም ነው። መልእክተኛውን ﷺ መከተል፣ ባዘዘው ነገር መታዘዝ፣ ከከለከለው መራቅና ለእርሱ ፍጹም መገዛት ደግሞ፦ “ሙሐመዱ ረሱሉላህ” የሚለውን ምስክርነት መፈጸም ነው። 📢የአህሉስ-ሱንና ወል-ጀማዓ መንገድ እነሱ አላህን ብቻ ያመልካሉ፤ ከእርሱም ጋር ምንም ነገር አያጋሩም። ከአላህ በቀር ማንንም አይለምኑም፤ ከአላህ በቀር ማንንም እርዳታ አይጠይቁም፤ በእርሱ ብቻ ይመካሉ፤ ከእርሱ በቀር ማንንም በአምልኮ የሚገባ ፍርሃት አይፈሩም። አላህንም በመታዘዝ፣ በማምለክና በመልካም ሥራዎች ወደ እርሱ ይቀርባሉ። አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ይላል፦ ﴿وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا﴾ “አላህን ብቻ አምልኩ፤ ከእርሱም ጋር ምንም ነገር አታጋሩ።” 📚من كتاب الوجيز في عقيدة السلف الصالح ©https://t.me/Abuimran_alkemisse ©https://t.me/Abuimran_alkemisse

✍ኡኸታየ ◍ውበት ማለት የፊትሽ ማማር አይደለም ◍ውበት ማለት ደረትን ከፍቶ መሄድ አይደለም ። ◍ውበት ማለት የ አፍንጫሽ ሰልካካ መሆን አይደለም ◉ውበት ማለት የ ጥርሶችሽ ማማር ፈገግ ስትይ ሁሉን
✍ኡኸታየ ◍ውበት ማለት የፊትሽ ማማር አይደለም ◍ውበት ማለት ደረትን ከፍቶ መሄድ አይደለም ። ◍ውበት ማለት የ አፍንጫሽ ሰልካካ መሆን አይደለም ◉ውበት ማለት የ ጥርሶችሽ ማማር ፈገግ ስትይ ሁሉን ገዳይ በፈገግታሽ መሆንሽ አይደለም። ♻️ውበት ማለት ሀያእ (አይናፋርነትሽ) ነው 🍂ውበት ማለት ሂጃብ ነው 🍂ውበት ማለት ኢማንሽ ነው 🍂ውበት ማለት የስነምግባርሽ  ማማር ነው ☑እናም ሀቢብቲ የቱ ላንቺ እንደ ሚያስፈልግሽ እራስሽ ታውቅያለሽ።

🖋የዳዕዋ ፕሮግራም ተጀምሯል🖋 ፕ     ሮ        ግ            ራ                ሙ ተ ጀ ም ሯ ል 🎙 በሸይኽ አወል አል-ኬሚሴ https://t.me/Abuimran_alkemisse?livestream=c000cfc296392dbf93

🖋የዳዕዋ ፕሮግራም ተጀምሯል🖋 ፕ ሮ ግ ራ ሙ ተ ጀ ም ሯ ል በወንድም አቡ ሂበቲላህ https://t.me/Abuimran_alkemisse

ፕሮግራም ሊጀምር ነው ገባ ገባ በሉ ከመረከዝ መናሩ ሱና መድረኩን በዋናነት የሚመራልን ወንድማችን ኡስታዝ አቡ አዩብ https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris?livestream=a08579d3fbf28966ef

አላህዬ… ጉዳያችን ከተራራ በላይ ገዝፏል እኛ ግን ለእሱ የሚገባውን ያህል ጥረት እያደረግን አይደለም አላህዬ ድካማችንን አትመልከት ምህረትህንና ችሎታህን ተመልከተን አንተ እንጂ ማንም ሊፈታው የማይች
አላህዬ… ጉዳያችን ከተራራ በላይ ገዝፏል እኛ ግን ለእሱ የሚገባውን ያህል ጥረት እያደረግን አይደለም አላህዬ ድካማችንን አትመልከት ምህረትህንና ችሎታህን ተመልከተን አንተ እንጂ ማንም ሊፈታው የማይችለውን የተወሳሰበ ጉዳያችንን አንተ ፍታልን አላህዬ በራሳችን አቅም የማንችለውን አንተ አቅልልን የተዘጋብንን በሮች ክፈትልን ከማናስበው አቅጣጫ መውጫ አድርግልን ያረብ እኛን አግዘን አትተወን ጉዳያችንን በኸይር ሁሉ አስተካክልልን ከአንተም የመጣ እርዳታ እንጂ ሌላ አንፈልግም

ተጀመረ
አዲስ የኪታብ ደርስ
      📖ኪታቡ አልቀዋዒዱል ሙስላ 🎤በኡስታዝ አቡ ኢምራን የኪታቡን PDF ለማግኘት https://t.me/sefinetunuh/9009 ደረሱ የሚሰጠዉ 🌙በአህሉ-ተውሂድ መስጂድ  - - ሸር አድርጉት https://t.me/sefinetunuh?livestream=2aa0f105b7a048c75d

✍<የኒቃቢስቷ ንግስት> ➛ከሀያዕ'ዋ ጋራ አጂብ ነው ውበቷ ➛ከሩቅ ይናገራል ግሩም ስረኣቷ ➛ለዛዋ ደስ የሚል ቁጥብ ንግግሯ ➛ሰዎች ማትረብሽ ደሞም በተግባሯ ➛የኒቃቡ ግርማ ቆንጆ አረማመዷ
✍<የኒቃቢስቷ ንግስት> ➛ከሀያዕ'ዋ ጋራ አጂብ ነው ውበቷ ➛ከሩቅ ይናገራል ግሩም ስረኣቷ ➛ለዛዋ ደስ የሚል ቁጥብ ንግግሯ ➛ሰዎች ማትረብሽ ደሞም በተግባሯ ➛የኒቃቡ ግርማ ቆንጆ አረማመዷ ➛ከሙስሊሞች ኩራት አንዷ'ኮ ነሽ ውዷ

🟢 ዛሬ ምሽት 3:00 እንዳያመልጣችሁ ! ሳምንታዊ የጥያቄና መልስ ውድድር ዛሬ ምሽት 3:00 ላይ ይቀጥላል። 📱 ይሳተፉ፣ ይማሩ፣ እውቀትዎን ይፈትሹ ይሸለሙ ! ለመቀላቀል እና ለመሳተፍ ከታች ይጫ
🟢 ዛሬ ምሽት 3:00 እንዳያመልጣችሁ ! ሳምንታዊ የጥያቄና መልስ ውድድር ዛሬ ምሽት 3:00 ላይ ይቀጥላል። 📱   ይሳተፉ፣ ይማሩ፣ እውቀትዎን ይፈትሹ ይሸለሙ ! ለመቀላቀል እና ለመሳተፍ ከታች ይጫኑ  👇 👉 t.me/FKR_ESKE_JENET

የጅሙአ ቀን ወቅተል ኢጃብ የተባለው ሰአት እቤታችሁም ሆናችሁ ማግኘት ትችላላችሁ። በተለይ የጅሙአ የቀኑ መጨረሻ ፀሀይ ልትገባ በምትቃረብበት ሰአት ጌታችሁን በመለመን ላይ በርቱ። ምናልባትም የተለመነ ነገር ሁሉ እሺ ሚባልበት ወቅት ሊሆን ይችላልና። ``

"አስተውሉ! ከመፀፀታችሁ በፊት መልካምን ስራ ፈፅሙ። በዱንያ አትሸወዱ።ምክንያቱም ፦ ጤነኞች መታመማቸው ፤ አዲሶቿ ማርጀታቸው፤ ፀጋዎቿ ማለቃቸው ወጣቶቿ ማርጀታቸው አይቀርምና።" 📚【አዙህዱልከቢር
"አስተውሉ! ከመፀፀታችሁ በፊት መልካምን ስራ ፈፅሙ። በዱንያ አትሸወዱ።ምክንያቱም ፦ ጤነኞች መታመማቸው ፤ አዲሶቿ ማርጀታቸው፤ ፀጋዎቿ ማለቃቸው ወጣቶቿ ማርጀታቸው አይቀርምና።" 📚【አዙህዱልከቢር ሊልበይሀቂ (1/197)】

❶#ነገር_አዋሳጅ_ጀነት_አይገባም። 2, ነገረኛ የሸይጧን ተላላኪ ነው ነገረኞች እባካችሁ አስታርቁ እንጂ አጣሉ አራርቁ የሚል መመሪያ የለንም። ነገረኛ ሰምተሽ በእህትሽ ላይ የዘመትሽው እህቴ ሆይ ነገ
❶#ነገር_አዋሳጅ_ጀነት_አይገባም። 2, ነገረኛ የሸይጧን ተላላኪ ነው ነገረኞች እባካችሁ አስታርቁ እንጂ አጣሉ አራርቁ የሚል መመሪያ የለንም። ነገረኛ ሰምተሽ በእህትሽ ላይ የዘመትሽው እህቴ ሆይ ነገረኛ አይታመንምና ነገር የሚያመጣልሽን ሰው ማንንም አትመኝ....!! ሰወች ነገረኛ የሚሆኑት ወይ ሲቀኑ ወይ እሳቸው ያጡትን ነገር ስታገኝ በምቀኝነት ወይም ደግሞ በጥላቻና በውሸት ነው ። ደግሞ ለአንች የነገረችሽ ከአንችም ወስዳ ለሌላዋ እንደምትናገር አትዘንጊ!!!