🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹
کانال بسته
نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
548
مشترکین
-224 ساعت
+177 روز
+5730 روز
آرشیو پست ها
🌸 የዋህ እና ገራገር ለሆኑ ሴቶች አጠር ያለች ምክር
የዋህነትና ገራገርነት በሴት ልጅ ስብዕና ውስጥ ሲገኝ፣ ያቺ ሴት ለቤቷም ሆነ ለዙሪያዋ ሰዎች የአላህ ልዩ ስጦታ ናት።
የዋህነት ማለት ደካማነት አይደለም፤ ይልቁንም የልብ ንፅህና፣ ለሰዎች ክፉ አለመመኘትና ነገሮችን ቀለል አድርጎ የማየት ትልቅነት ነው። ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ "ጀነት የሚገቡ ሰዎች ልባቸው እንደ ወፍ ልብ የለሰለሰ (የዋህ) ነው" (ሙስሊምዘግበውታል)።
1. የዋህነት በትዳርና በቤተሰብ ዙሪያ ያለው ተፅኖ፦ገራገር ሴት የቤት ውስጥ ንግሥት ናት። በትዳር ውስጥ እልህ ከመያዝ ይልቅ በለሰለሰ አንደበት ሰላምን ትመርጣለች።
ውድ እህቴ፣ ገራገርነትሽ ለትዳርሽ ምሰሶ ነው። ነገር ግን የዋህነትሽ ለበደል በር እንዳይከፍት ጥንቃቄ አድርጊ። በትዳርሽ ውስጥ አዛኝና ታዛዥ መሆንሽ አላህ ዘንድ ትልቅ አጅር አለው። ቤተሰቦችሽን ስታገለግዪ "ለአላህ ብዬ" የሚል ኒያ ይኑርሽ፤ ያኔ ድካምሽ ወደ አጅር ይቀየራል።
2. የዋህነት በገንዘብና በዱንያ ዙሪያ ያለው ተፅኖ፦ ገራገር ሴቶች በአብዛኛው ለገንዘብ ስግብግብ አይደሉም፤ ባላቸው ይረካሉ። ይሁንና በዚህ ዘመን የዋህነትን እንደ ሞኝነት የሚቆጥሩ ሰዎች ስላሉ ጥንቃቄ ያስፈልጋል።
እህቴ በገንዘብ ረገድ "እጅሽ ክፍት ይሁን ግን አባካኝ አትሁኚ።" ሰዎች የዋህነትሽን አይተው በገንዘብሽ እንዳይጫወቱብሽ ንቁ ሁኚ። እስልምና ሴት ልጅ የራሷ ሀብት እንዲኖራትና በሀብቷ ላይም ሙሉ መብት እንዳላት ይደነግጋል። አደራሽን! የዋህነትሽ "የለኝም" ማለት መሸማቀቅ እንዳይሆንብሽ።
3. የዋህነት በሚዲያው ዓለም ዙሪያ ያለው ተፅኖ፦ ሚዲያው ለየዋህ ሴቶች ፈታኝ ቦታ ነው። ብዙ ጊዜ ገራገር ሴቶች የሰዎችን ሁሉ ንግግር እውነት ብለው ስለሚቀበሉ ለሐሜት፣ ለተንኮልና ለጭንቀት ሊጋለጡ ይችላሉ።
እህቴ.. በሚዲያ ላይ የምታያቸው ነገሮች ሁሉ እውነት አይደሉም። የሰዎችን "ሰው ሰራሽ" ደስታ አይተሽ በራስሽ ኑሮ ላይ ተስፋ አትቁረጪ። የዋህ ልብሽን በሚዲያ ወሬ አታቆሽሺው። ሚዲያን ለቂርዓት፣ ለጥሩ ግንኙነትና ለደዕዋ ብቻ ተጠቀሚበት። ሚስጥርሽን በሚዲያ አታውጪ፤ የዋህነትሽ የግል ህይወትሽ መጋረጃ እንዲቀደድ አያድርገው።
4. የዋህነት በቂርዓትና በመንፈሳዊ ህይወት ዙሪያ፦ የገራገር ሴቶች ትልቁ ውበት ወደ አላህ ያላቸው ቅርበት ነው። ቂርዓት ሲቀሩ በልባቸው ነው፤ ዱዓ ሲያደርጉ በእንባ ነው።
እህቴ ሆይ! የዋህነትሽን በዕውቀት (በቂርዓት) አስጪው። እውቀት የሌለው የዋህነት በቀላሉ ሊታለል ይችላል። ሃይማኖትሽን ጠንቅቀሽ ስታውቂ የዋህነትሽ ጥንካሬ ይሆንልሻል። ቁርአን የልብሽ ጓደኛ ይሁን፤ እርሱ የዋህ ልብሽን ይበልጥ ያጸዳዋል።
🌹የዋህና ገራገር ሴት ማለት፦
🌹በትንሽ ነገር የምትደሰት፣
🌹ሰውን በክፉ የማታስብ፣
🌹ጭንቀቷን ወደ ሶላት የምትወስድ፣
🌹ለሰዎች ስህተት ሰባ ሰበብ የምትፈልግ ምርጥ ባሪያ ናት።
ወዳጆቼ...!! በዙሪያችሁ ገራገር ሴቶች ካሉ ተንከባከቧቸው። እነርሱ የዚህ ዓለም ማጣፈጫዎች ናቸው። የዋህነታቸውን እንደ ድክመት አይታችሁ አትበድሏቸው፤ ምክንያቱም የየዋሆች ጠበቃ አላህ ነው።
ውድ እህቴ፦ የዋህነትሽ የአላህ ስጦታ ነውና አትቀይሪው። ነገር ግን በዕውቀትና በጥንቃቄ አጅቢው። ልብሽን ለአላህ ብቻ ስጪ፤ ያኔ ማንም ሊሰብረውና ሊጫወትበት አይችልም!
ከማ ቃለ ወድም አቡ ሂበቲላህ
➤]]የወላጅ ሀቅ እስኪ ይነበብ
🔹🔹🔹🔹
➤:የወላጅ ሐቅ እና እናት አባትን የማክበር ሲባል …
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
➤:ድምፅህን ከድምፃቸዉ በላይ ከፍ አታድርግ፣
▪️:አጉል ክርክር አትከራከራቸው፣
▫️:እነሱ ሣይጨርሱ አትናገር፣
▪️:በሥማቸው አትጥራቸው፣
▫️:እንቅልፋቸዉን ሣይጨርሱ አትቀስቅሣቸው፣
➤:ለምክኒያት ካልሆነ በስተቀር (አደጋ እንዳያገኛቸዉን ለመሣሠሉት) ከፊት ለፊታቸው አትቅደም፣
▫️:እነርሱ ሣይቀመጡ ቀድመህ አትቀመጥ ፣
▪️:ባሪያ ለጌታዉ እንደሚተናነሰው ሁሉ ተናነስላቸው፣
➤:ጠርተዉህ ሣይጨርሱ ‘
አቤት ’ በላቸው፣
▪️:ከቤት ወጥተህ በመዘግየት እንዲያስቡ አታድርጋቸው፣
▫️:በሀሳብ ተጨንቀህ አታስጨንቃቸው፣
➤:በእይታህ አታፍጥባቸው፣
▫️:በንግግርህ አትዳፈራቸው፣
▪️:በቁጣቸው መልሰህ አትቆጣ፣
▫️:በንግግራቸው አትሣቅ, ሙድ አትያዝ፣
▪️➤:መላና ሀሣባቸዉን አታናንቅ፣
▫️:ሲጨንቃቸዉ አማክራቸው፣
▪️:ሲቸግራቸው እርዳቸው፣
▫️:ሲታመሙ አሣክማቸው፣
▪️:ሲታረዙ አልብሣቸው፣
▫️:ጉዳይቸዉን ሁሉ ጉዳዬ በል፣
▪️:እቅድ ሀሣባቸዉን ተካፈል፣
▫️:ዓላማህን አትደብቃቸው፣
▪️:የሥጋ ዘመዶቻቸዉን ቀጥል፣
▫️:ወዳጆቻቸን አክብርላቸው፣
▪️:ጉዞ ስትወጣ ንገራቸው፣
▫️:የሚወዱትን ዉደድላቸው፣
▪️:እርግማናቸዉን ተጠንቀቅ፣
▫️:እነርሱን ከማስከፋት ፈፅሞ እራቅ፣
▪️:ነገሮችን ቀስ ብለህ አስረዳቸው፣
▫️:በሚገባቸዉ ሁኔታና ቋንቋ ንገራቸው፣
▪️:ዱዓኣቸዉን ፈልግ፣
▫️:ከምርቃታቸው ተሽቀዳደም፣
▪️:ለወላጆችህ ‘ ጌታዬ ሆይ ! በህፃንነቴ እንዳሳደጉኝ ሁሉ እዘንላቸው ’ የዘወትር ዱዓእህ ይሁን ።
🔹ይህ ልብን የሚሰብርና "የፍቅር ሟች" ተብሎ የሚታወቀው የዑርዋ ቢን ሒዛም አል-ዑዝሪ እና የዐፍራእ ቢንት ማሊክ ታሪክ
#የፍቅር_ሟች_ዑርዋ_ቢን_ሒዛም_አል-ዑዝሪ
ዑርዋ ቢን ሒዛም የተባለ ውብና ተወዳጅ ወጣት "ዐፍራእ ቢንት ማሊክ" በምትባል አረባዊት ሴት ላይ እጅግ ከባድ ፍቅር ወደቀበት። ሁለቱም ከልጅነታቸው ጀምሮ አብረው ያደጉ በመሆናቸው ፍቅራቸው ከጨቅላነት ጀምሮ በልባቸው ውስጥ ሰርጾ ነበር። በሐሰን ቢን ዓሊ (ረ.ዐ) አማላጅነትም ተጋቡ። ዑርዋ ዐፍራእን በጣም ስለሚወዳት አብረው ለተወሰነ ጊዜ በደስታ ኖሩ።
ነገር ግን የዑርዋ እናት ዐፍራእን ትጠላት ነበር፤ እንድትፈታውም ትወተውተው ነበር። እርሱ ግን "እናቴ ሆይ! እሷን በመለየቴ ነፍሴ እንዳትጠፋ እፈራለሁ" ይላት ነበር። እናቱ ግን አልረካችም። በአንድ ወቅት ፀሐይ በበረታችበትና አሸዋው እጅግ በጋለበት ቀን እናቱ በባዶ እግሯ ረመጥ ላይ ቆማ "ዐፍራእን ካልፈታህ ከዚህ አልንቀሳቀስም" ብላ ማለች። ዑርዋም ለእናትየው ካለው አክብሮትና "ቢር አል-ዋሊደይን" (ለወላጅ ታዛዥ መሆን) የተነሳ ዐፍራእን ፈታት።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ዑርዋ በሐዘንና በናፍቆት ተሰበረ። ምግብና መጠጥ መውሰድ አቃተው። በናፍቆት ብዛት እራሱን እስኪስትና እስኪቃዥ ድረስ ተጎዳ። የፍቅሩ ቃጠሎ ሲበረታበት ሆዱን በቀዝቃዛ ውኃ ገንዳዎች ላይ በማጣበቅ ለማቀዝቀዝ ይሞክር ነበር። አንድ ሽማግሌም አይተውት "ልጄ ሆይ! ተጠንቀቅ፤ ይህን አድርጎ የዳነ የለም" አሉት። እርሱም "አጎቴ ሆይ! እኔ ጭንቅ ውስጥ ነኝ፤ በጉበቴ ላይ እሳት ይሰማኛል" አላቸው።
ዑርዋ ወደ ዐፍራእ ቤተሰቦች ተመልሶ እንዲያጋቡት ቢጠይቅም እናቷ ግን ባለጸጋ ትፈልግ ስለነበር እምቢ አለች። ዑርዋም ፊቱ ጠቁሮ፣ እጆቹ ከስተውና መልኩ ተለውጦ ወደ መካ ተወሰደ። ዐፍራእ በአንድ ወቅት የራስ መሸፈኛዋን (ኺማር) ሰጥታው ነበር። ዑርዋ ራሱን በሳተ ቁጥር አገልጋዩ በዚያ ኺማር ሲያቅፈው ይነቃ ነበር።
ወደ ዐብዱላህ ቢን ዐባስ (ረ.ዐ) ዘንድ አምጥተው "የአላህ መልእክተኛ የአጎት ልጅ ሆይ! አማልዱለት፣ መፍትሔ ፈልጉለት" አሏቸው። ኢብኑ ዐባስም ኺማሩን ገልጠው "ምን ሆነሃል?" ብለው ጠየቁት። ዑርዋም የልቡን ስቃይ በግጥም ገለጸላቸው። ሆኖም ግን ለፍቅር ከባዱ መድኃኒት ወደ አላህ መሸሸግ ብቻ በመሆኑ፣ ዑርዋ ወደ ቤቱ ተመልሶ ጥቂት ቀናት እንደቆየ በመጨረሻው ሰዓት እንዲህ አለ፡-
"የሚያውቁትን መድኃኒት ሁሉ አደረጉልኝ... የሚያውቁትንም መጽናኛ ሁሉ አጠጡኝ።"
"አላህ ይፈውስህ አሉኝ፤ እኛ ግን በጎድን አጥንቶችህ ውስጥ ላለው ስቃይ አቅም የለንም አሉ።"
ከዚያም ትንፋሹ ተቆርጦ ሞተ። አርቲባን የተባሉ ሰዎች አስከሬኑን ይዘው በዐፍራእ ቤት አቅራቢያ ሲያልፉ ሞቱን ረዱ። ዐፍራእም ይህን ስትሰማ በከባድ ሐዘን እንባዋን አፈሰሰች። ወደ ቀብሩም ሄዳ ለሦስት ቀናት ምግብና መጠጥ ሳትቀምስ ስታለቅስ ከቆየች በኋላ፣ እጆቿን በቀብሩ ላይ እንደዘረጋች ነፍሷ ወጣች። ከጎኑም ቀበሯት።
ሙዓዝ ቢን የሕያ የተባሉ ሰው እንዲህ ይላሉ፡- "ከመካ ወደ ሰንዓ ስሄድ ሰዎች ከግመሎቻቸው ወርደው ሲሮጡ አየሁ። የት እንደሆነ ስጠይቅ 'የዑርዋንና የዐፍራእን ቀብር ልናይ ነው' አሉኝ። እኔም ሄጄ ስመለከት ሁለት የተጠጋጉ ቀብሮችን አየሁ። ከእያንዳንዱ ቀብር የአንድ ዛፍ ግንድ ወጥቶ ልክ የአንድ ሰው ቁመት ያህል ሲደርሱ ሁለቱ ዛፎች ተጠምጥመው ተገናኝተዋል። ሰዎችም 'በሕይወትም በሞትም ተገናኙ' ይሉ ነበር።"
ይህ የሆነው በ30ኛው የሒጅራ ዓመት አካባቢ ነበር። ወሬው ሙዓውያ (ረ.ዐ) ዘንድ ሲደርስ "ስለ እነዚህ ሁለት ክቡራን ባውቅ ኖሮ አገናኛቸው ነበር" አሉ።
ዑርዋ በሞተበት ወቅት ኢብኑ ዐባስ (ረ.ዐ) ለ40 ቀናት ያህል ከሶላት በኋላ "አላህ ሆይ! ከፍቅር መከራ ጠብቀኝ" ብለው ሳይለምኑ የቀሩበት ጊዜ የለም ነበር። "ይህ የፍቅር ሟች ነው" ይሉም ነበር።
ምንጭ፡- "አዝ-ዛህራ" በሙሐመድ ቢን ዳውድ አል-ዛሂሪ (ገጽ 144) እና "ታሪኽ ዲማሽቅ" በኢብኑ ዓሳኪር (40/217)።
አላህ ይጠብቀን
ወንድማችሁ አቡ ኢምራን
🌹ቻናላችንን ጆይን ይበሉ🌹
https://t.me/Mf11q
https://t.me/Mf11q
https://t.me/Mf11q
Repost from DARU-TEWHID [ዳሩ-ተውሒድ]
አላህን በመፍራት ላይ አደራ እላቹሃለሁ !
ትላንት ዙል ቃዒዳ 23/1447 አለም ባንክ ሙስዓብ መስጅድ የቀረበ ምክር።
🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሓፊዘሁላህ
~ t.me/Darutewhide
👑أختي الغالية 🌹
ሊያናድዱሽ ሲሞክሩ... ከመናደድ ይልቅ ፈገግ በይና ግራ አጋቢያቸው። የማትገመች ሴት የማትናደጅ ለእነሱ ቦታ የለለሽ ንቀሻቸው የምታልፊያቸው ጀግና ሴት ኡኚ!!!
እኛ ሙብተዲዕ ያልነውን እናንተም ሙብተዲዕ በሉ ብለው ከሰለፍያ የሚያስወጡ ለመሆኑ የድምፅ መረጃ ከራሳቸው አንደበት ስሙ።
ክፍል 1
https://t.me/fejir_tube
Repost from 📖تلاوه القرأن الكريم📖
📖📚ቃሪአ አስማ ሁዳ 📖📚 ሱረቱል ማኡን
https://t.me/Misbah_sain
https://t.me/Misbah_sain
ሴት ልጅ ሴት መሆኗን የምትረሳ ከሆነ ሁኔታዋ ሁሉ የወንድ ይሆናል ከሂጃብ የራቀች ከቤቷ የምትወጣ ከዛም ከዛም ቦታ የምትሄድ የባሏን ትእዛዝ የማታከብር
የሴትነትን ባህሪ እርግፍ አርጋ እንዲትተው የወንዶችን አይነት ኑሮ መኖር የምትመርጥ መጥፎ ሴት እንዲትሆን
ለትዳር የማትመረጥ ሴት ያደርጋታል
የመጥፎ ወንዶች መጫወቻ ኸይረኛ ወንዶች ለትዳር የማይፈልጓት ያደርጋታል
ሴት ልጅ ሴትነቷን መርሳት የለባትም
አላህ ሴቶችን ባዘዘው መልኩ ልትሆን ይገባል ያኔ ነው የሴትነት ክብር የሚኖራት
አሉ ሸህ አቡ መአዝ ሁሴን አሓጢቢይ
اختي الغاليه
ቴክስት አታብዥ
ወሬ አታብዥ
ምግብ አታብዥ
ቀልድ አታብዥ
ሳቅ አታብዥ
እንቅልፍ አታብዥ
ሲበዙ ልብ ያደርቃሉ
https://t.me/+o7ZrQFQjILVhNDVk
ጠንካራ ሴት ማለት ጉልበት ያላት ሴት ማለት አይደለም፤ ጠንካራ ሴት ማለት በውስጧ ያለውን ጽናት፣ ትዕግሥት እና እምነት በሕይወቷ ላይ በተግባር የምታሳይ ሰው ናት። ችግር ሲመጣ አትፈራም፤ ይልቁንም በጥበብ ትመክራለች፣ መፍትሔ ትፈልጋለች። የልቧ ቁስል ቢኖርም ለሌሎች ብርታት መሆንን ታውቃለች።
ጠንካራ ሴት ራሷን ታከብራለች፣ ክብሯን ትጠብቃለች፣ እና የምትወደውን ነገር ለማግኘት ትጥራለች። ከውድቀት ትማራለች እንጂ አትቆምም፤ ሁልጊዜ ወደ ፊት ትመራለች። ለቤተሰቧ፣ ለጓደኞቿ እና ለማህበረሰቧ መብራት ናት።
በእውነት ጠንካራ ሴት ማለት ራሷን የምታውቅ፣ በአላህ የምታመን፣ በሁሉም ሁኔታ ፀንታ የምትቆም እና ከሁሉ በላይ ተስፋዋን የማትጥል ናት።
እናም እህቴ እችን ሴት ለመሆን ጣሪ!!
https://t.me/+o7ZrQFQjILVhNDVk
"አንቺ ሷሊህ ሴት ሆይ!🌸
የፈተና ማዕበሎች በሚላተሙበት በዚህ ዘመን፣ በዲንሽ ላይ ለመፅናት የምታሳዪው ትዕግስት በአላህ ፈቃድ በከንቱ አይባክንም።
አንቺ በታላቅ ኸይር ላይ ነሽ፤ ሷሊህ ሴትማ በሴቶች ስብስብ ውስጥ መገኘቷ ብርቅ እየሆነ መጥቷል።
ስለዚህ ታገሺ፣ በትዕግስትሽም ጽኚ፤ ከአላህ ዘንድ በሆነው እዝነትና ውዴታም ተበሰሪ።"
https://t.me/+o7ZrQFQjILVhNDVk
"🎀አንዲት ሴት ጨዋነቷ በተሟላ ቁጥር ዲኗም ይሟላል፤
🎀የሴት ውበቷ ደግሞ በሐያእ ውስጥ ነው፤
🎀ሐያእዋ ደግሞ የሚጠበቀው ሐያእዋን ከሚገፏት ሰዎች ጋር ባለመቀላቀሏ ነው።"
🌸ሸይኽ አብዱሰላም አል-ሹወይዒር ሀፊዘሁሏህ🌸
https://t.me/+o7ZrQFQjILVhNDVk
فضل طلب العلم
ዒልም መማርና መፈለግ ያለው ደረጃ በሚል ርዕስ
በኡስታዝ አቡ ረያን
قناة سلفية تهدف نشر السنة على فهم السلف
الصالح والرد على أهل البدع والأهواء ممن لم ينتهج منهج السلف الصالح
https://t.me/nuruya76
https://t.me/nuruya76
ይህን ያክል ሀድስ አስተላልፈዋል👏👏
1""አቡ ሁረይራ ረደሏሁ አንሁ - - - 5374
2""አብዱላህ ኢብኑ ኡመረ ረደሏሁ አንሁ - - - "2630
3"""አነስ ኢብኑ ማሊክ ረደሏሁ አንሁ - - - 2286
4"""አኢሻ ረደላህ አንሀ--- 2210
5"" ኢብኑ አባስ ረደሏሁ አንሁ---- 1696
6"""ጃቢሪ ኢብኑ አብደላህ ረደሏሁ አንሁ--- 1540
7""" አቡ ሰኢድ አልኹድሪ ረደሏሁ አንሁ - - - 1170
እኔ አንተን ስወድህ
በፍቅርህ ስረታ እኔ አንተን ስወድህ
አይምሰልህ ውዴ አማሎኝ ውበትህ
አይቼም አይደለም ተሟልቶ ህይወትህ
ወይ ደሞ ጓጉቼ ለቤት ለመኪናህ
ጥቅሞችን ፈልጌ ፍፁም እንዳይመስልህ
በጥሩ አስተሳሰብ በስነ መግባርህ
በማራኪ አንደበት በጣፋጩ ለዛህ
ሰርቀህብኝ እንጂ የኔን ልብ በልብህ
ግራ ቀኝ ሳልል ሁሌ የምከተልህ
ተብትበከኝ እንጂ አስረከኝ በፍቅርህ
አስገድዶኝ እንጂ እረቶኝ መውደድህ
አፍቃሪህ ሁኜ ነው የልብ ወዳጅህ
ጥቅም ፈላጊ ነው አስመሳይነው ብለህ
ፍፁም እንዳታስብ እመነኝ ከልብህ
በፍቅር ታስሮ ነው የኔልብ ከልብህ
አፍቃሪወች ዉሰዱ
አፍቃሪወች ሲባል ሀላላችሁን ነው ያልኩት
ፍቅር ያለ ኒካ የለዉም በረካ
https://t.me/+o7ZrQFQjILVhNDVk
Repost from ስለ ቀልባችን
ክፍል--➋--
📚 የኪታቡ ስም፦
❞ذَمُّ قَسْوَةِ الْقَلْب❝
(የቀልብ መድረቅ አደገኝነት፣ መንስኤውና መፍትሔው)
🎙 በኡስታዝ፦ ዐብዱ ረዛቅ አል-ባጂ (ሐፊዘሁላህ)
➡️ t.me/Sle_qelbachn1
ሀዘን ልብን ይሰብራል። ተስፋን ያደበዝዛል። ቁርጠኝነትን ይነጥቃል። ስለነጋችን ማለም፣ ስለወደፊታችን ማቀድን ከንቱ ድካም አድርገን እንድንወስደው ያደርጋል። ጌታችን እንደጠቆመን ሸይጧን በሙእሚን ሀዘን የሚደሰተውን ያክል በምንም ነገር አይደሰትም።
{إنما النجوى من الشيطان ليحزن الذين آمنوا}
ለዚያም ነውኮ አላህን ከሀዘን እንዲጠብቀን መማጸንን ነብዩ صلى الله عليه وسلم ያስተማሩን።
አላህ ከሀሳብ ጭንቀትና ሀዘን ይጠብቃችሁ።
=
https://t.me/+o7ZrQFQjILVhNDVk
ልቧ ድክም ብሏል አይኗ ደርቆ ልቧ ያነባል ጩሀ አታለቅስ ምነው ይሏታል ይች ነፍስ ጥሪዋን የምታሰማው ለጌታዋ ብቻ ነው___ በዚህ ስሜት ውስጥ ያለች ሩህ
አላህዬ ሙሳን ከፊርዓውን ፈተና ነጃ ያልክ ጌታ ይችን ደካማ ነፍስ ከገባችበት ፈተና ነጃ በላት
አላህዬ _ ዩኑስን ከሶስት ጨለማ ያረብ ሲልህ የሰማህ ጌታ ባሪያህን ሹክትክታዋን ስማት
አላህዬ የሱፍን ከችግር ከፈተና ከስቃይ አውጥተህ ለንግስና ያበቃህ ሀያሉ ጌታዬ _ባሪያህን ሁሉንም አቅለህላት የስኬት ማማ ላይ አድርሳት ያረብ!!!!
https://t.me/+o7ZrQFQjILVhNDVk
Repost from []ትዳር የአማኞች ምሽግ[]
የጁሙአ ግብዣ
🎙ሱረቱል ካህፍ
سورة_الكهف
📚][]ሱረቱል ከህፍ 📎🥀ውብ ቲላዋ@[]
ቁርአን የልብ መርጊያ ለደረቀ ልብ ማረስረሻ ነው።
💐የጁመዓ ቀን ሱናዎች💐
➖➖➖➖➖➖➖
↩️💎 سنن يوم الجمعة
➊ 💎الغسل
➋💎 الطيب
➌ 💎السواك
➍💎 لبس الجميل
➎💎 قراءة سورة الكهف
➏💎 التبكير لصلاة الجمعة
➐💎الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
➊ 🌺መታጠብ
➋ 🌺ሽቶ መቀባት
➌🌺 ሲዋክ መጠቀም
➍ 🌺ጥሩ ልብስ መልበስ
➎ 🌺ሱረቱል ካህፍን መቅራት ከቻልን
➏ 🌺ለጁመዓ ሶላት መጣድ
➐ 🌺በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማብዛት
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
«اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ،
كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ،
اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ،
كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ
🌺በሰለዋት በዚክርያውለን
ﷺ 🌹 .................🌹
ﷺ ﷺ🌹 ..................🌹 ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ ﷺ🌹🔹🔹🌹
ﷺ ﷺ ﷺ 🌹🔹🔹🌹
በነብዩ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ !!
