ch
Feedback
​🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹

​🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹

前往频道在 Telegram

显示更多
未指定国家未指定类别
1 376
订阅者
+1824 小时
+3637 夊
+64630 夊
帖子存档
💧እህቴ ሆይ ! ለይልሶላት ላይበርች!! አላህተባረከወተኣላእንዲህ ይላል፦ يَا أَيُّهَا الْمُزَّمِّلُ አልሙዘሚል1 አንተ ተከናናቢው ሆይ፡፡ قُمِ اللَّيْلَ إِلَّا قَلِيلًا አልሙዘሚል2 ሌሊቱን ሁሉ ጥቂት ሲቀር ቁም፤ (ስገደ)፡፡ በሌላአንቀፅምየሌሊትንሶላትደረጃና ምንዳእንዲህበማለትይነግረናል* ፦ وَأَقِمِ الصَّلَاةَ طَرَفَيِ النَّهَارِ وَزُلَفًا مِّنَ اللَّيْلِ ۚ إِنَّ الْحَسَنَاتِ يُذْهِبْنَ السَّيِّئَاتِ ۚ ذَٰلِكَ ذِكْرَىٰ لِلذَّاكِرِينَ ሱረቱሁድ : 114 ሶላትንም በቀን ጫፎች ከሌሊትም ክፍሎች ፈጽም፡፡ መልካም ሥራዎች ኀጢአቶችን ያስወገድዳሉና፡፡ ይህ ለተገሳጮች ግሳጼ ነው፡፡ وَمِنَ اللَّيْلِ فَتَهَجَّدْ بِهِ نَافِلَةً لَّكَ عَسَىٰ أَن يَبْعَثَكَ رَبُّكَ مَقَامًا مَّحْمُودًا ሱረቱአል - ኢስራእ79 ከሌሊትም ላንተ ተጨማሪ የኾነችን ሶላት በእርሱ (በቁርኣን) ስገድ፡፡ ጌታህ ምስጉን በኾነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል፡፡ ረሱልﷺ በእዝነት ሲያበስሩን እንዲህ ይላሉ፦ በሌሊት ተነስቶ ሰግዶ ከዚያም ሚስቱን የቀሰቀሰ ሰው አላህ ይዘንለት። ሚስቱ ከእንቅልፏ ለመነሳት ፈቃደኛ ባትሆን እንኳ ፊቷ ላይ ውሃ ይረጭባታል። በሌሊት ተነስታ ሰግዳ ከዚያም ባሏን የቀሰቀሰች ሴትንም አላህ ይዘንላት። ባሏ ከእንቅልፉ ለመነሳት ፈቃደኛ ባይሆን እንኳ  ፊቱ ላይ ውሃ ትረጭበታለች። ረሱል ﷺ

❶#ነገር_አዋሳጅ_ጀነት_አይገባም። 2, ነገረኛ የሸይጧን ተላላኪ ነው ነገረኞች እባካችሁ አስታርቁ እንጂ አጣሉ አራርቁ የሚል መመሪያ የለንም። ነገረኛ ሰምተሽ በእህትሽ ላይ የዘመትሽው እህቴ ሆይ ነገ
❶#ነገር_አዋሳጅ_ጀነት_አይገባም። 2, ነገረኛ የሸይጧን ተላላኪ ነው ነገረኞች እባካችሁ አስታርቁ እንጂ አጣሉ አራርቁ የሚል መመሪያ የለንም። ነገረኛ ሰምተሽ በእህትሽ ላይ የዘመትሽው እህቴ ሆይ ነገረኛ አይታመንምና ነገር የሚያመጣልሽን ሰው ማንንም አትመኝ....!! ሰወች ነገረኛ የሚሆኑት ወይ ሲቀኑ ወይ እሳቸው ያጡትን ነገር ስታገኝ በምቀኝነት ወይም ደግሞ በጥላቻና በውሸት ነው ። ደግሞ ለአንች የነገረችሽ ከአንችም ወስዳ ለሌላዋ እንደምትናገር አትዘንጊ!!!

✍ምናልባት ሁሌ ዱዓ ስታደርጉለት የነበረው ነገር ልታገኙት በጣም ትንሽ ጊዜ ነው የቀራችሁ.... ........እናም በመጨረሻው ሰዓት ተስፋ እንዳትቆርጡ:: ☝️ኢላሂ ጤና መብቃቃትን ለዱንያም ለአኼራ
✍ምናልባት ሁሌ ዱዓ ስታደርጉለት የነበረው ነገር ልታገኙት በጣም ትንሽ ጊዜ ነው የቀራችሁ.... ........እናም በመጨረሻው ሰዓት ተስፋ እንዳትቆርጡ:: ☝️ኢላሂ ጤና መብቃቃትን ለዱንያም ለአኼራ የሚበጀንን ወፍቀን🤲

✅ልዩ ማበረታቻ ለጠንካራ የሱና እህቶቻችን! ✅በዳዕዋው ዘርፍ፣ ቁርኣን በማቅራት፣ ጠቃሚ መረጃዎችን በማጋራት እና ለሌሎችም አርአያ በመሆን ሌት ተቀን የሚለፉ ምርጥ የሱና እህቶች አሉን። 🧕የእነዚህን ውድ እህቶቻችንን ልፋት አሏህ በትልቁ የሚመነዳቸው ቢሆንም እኛም ለስራቸው ተገቢ ምስክር መሆን ማበረታታት እና ማድነቅ ተገቢ ነው ! እናም ቻናሎቻቸውን በቋሚነት ለማሳደግ እና ለሌሎችም መነቃቃት ይሆን ዘንድ ልዩ ፕሮግራም አዘጋጅተናል! ከሚጠቆሙት ውስጥ ከፍተኛ ድጋፍ (Like) የሚያገኙትን ከ1ኛ እስከ 5ኛ የሚወጡ እህቶችን በመለየት ቻናላቸውን በቋሚነት የምናሳድግ ይሆናል። ✅ ምን ማድረግ ይጠበቅቦታል? ይህቺ እህት ልትበረታታ፣ ልትደገፍ እና ልትመሰገን ይገባታል! የምትሏትን ጠንካራ አርአያ ሴት ስሟን እና የቻናሏን ሊንክ (Link) ከታች ባለው ቦት (Bot) ላኩልን። ብዙ ድጋፍ (Like) ያገኙት አሸናፊ ይሆናሉ! 💪 ✔️ ማሳሰቢያ፦ ጥቆማ የምንቀበለው እስከ ዛሬ ማታ 6 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው! አሁን ጀምሮ እጩዎችን ፖስት ማድረግ ስለምንጀምር ጊዜ ሳያጠፉ አሁኑኑ ይላኩልን። 👇 ስማቸውን እና የቻናላቸው ሊንክ ለመላክ ይህንን ቦት ይጠቀሙ ⬇ 👉 @fkr_eske_Jenet_Bot 👈 = t.me/FKR_ESKE_JENET

🍂የነብዩ ሙሐመድ   ሚስቶች 1,ኸድጃ ቢንት  ኹወይሊድ /ረደሏሁ ዐንሀ 2, ሰውዳ ቢንት ዘምዐህ/ረደሏሁ ዐንሀ 3/ዓኢሻ አቡበክር /ረደሏሁ ዐንሀ 4/ዘይነብ ቢንት ጀህሽ ረደሏሁ ዐንሀ 5/ሐፍሷህ ቢንት ዑመር/ረደሏሁ ዐንሁ 6/ኡሙ ሀቢባህ ረምላህ ቢንት አቡ ሱፍያን 7/መይሙና ቢንት አልሀሪስ ረደሏሁ ዐንሀ 8/ጁወይሪያህ ቢንት ሀሪስ ረደሏሁ ዐንሀ 9/ማሪያ አል ቂብጢያ/ ረደሏሁ ዐንሀ 10/ ሪሀና ቢንት ዘይድ  ረዲሏህ ዐንሀ 11/ሶፊያ ቢንት ሁሀይ ረደሏሁ ዐንሀ

ተጀመረ       📖ኪታቡ አልቀዋዒዱል ሙስላ 🎙በኡስታዝ አቡ ኢምራን የኪታቡን PDF ለማግኘት https://t.me/sefinetunuh/9009 ደረሱ የሚሰጠዉ 🌙በአህሉ-ተውሂድ መስጂድ  - - ሸር አድርጉት https://t.me/sefinetunuh?livestream=2aa0f105b7a048c75d

ፈጥኖ ማን ቀድሞ ይመልስ  🚀 ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል። 📝 ጥያቄ  እውነት ሀሰት በማለት መልሱ ። የጀሀነም በር ጠባቂ መላዒካ ማሊክ ይባላል፡፡

ዛሬ ለራሳችን ትንሽ ርህራሄ እንስጥ… ሁሉንም ነገር ዛሬ መፍታት አይጠበቅብንም። ሁሉንም መልስ ዛሬ ማግኘትም አይጠበቅብንም። አንዳንድ ቀናት የሚፈለገው ብዙ ነገር ሳይሆን፣ ልባችንን በአላህ ላይ አስ
ዛሬ ለራሳችን ትንሽ ርህራሄ እንስጥ… ሁሉንም ነገር ዛሬ መፍታት አይጠበቅብንም። ሁሉንም መልስ ዛሬ ማግኘትም አይጠበቅብንም። አንዳንድ ቀናት የሚፈለገው ብዙ ነገር ሳይሆን፣ ልባችንን በአላህ ላይ አስቀምጠን ቀኑን በሰላም መጀመር ብቻ ነው። የዘገየው ሁሉ የተረሳ አይደለም። የተዘጋው ሁሉ የተከለከለ አይደለም። ዝም ያለው ሁሉ አላህ እንደተወን ነውጰማለት አይደለም። በእምነት እንቀጥል፤ አላህ የልባችንን ድምፅ ከንግግራችን በፊት ያውቃል።      መልካም ውሎ

🚫 ሴትነት በኮሜንቶች ስር! ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ • የሴትነት ክብር - በየ ኮሜንቱ ስር፤ • ጥፍጥናውን ትቶ - እንደ እሬት ሲመር፤ • መስፈሪያውን ስቶ - እንደ ቁራ ሲበር፤ • መቀመጫን ለቆ - በጎዳና ሲያድር፤ • መኖሪያውን ርቆ - በየሚዲያው ሲዞር፣ • በጣም ያሳዝናል - ያስኮንናል የምር፤ • ሰምተነው አናቅም - ከደጋጎች ሰፈር፤ • ታይቶም አይታወቅ - ከቅኖቹ መንደር፤ ▬▬▬▬▬▬▬▬ • አይናፋሯ እንስት - ሐያእን ስታፈርጥ፤ • በየ ኮሜንቱ ስር - ለመፃፍ ስትሮጥ፤ • ካገኘችው ሁሉ - መልስ ስትሰጣጥ፤ • አድ አድርገዋት - እፍረቷ ሲመጠጥ፤ • ራሷም አድ አድርጋ - ክብሯን ስትረግጥ፤ • በግል እያዋራች - እሳት ስታጨበጥ፤ • ባሏን ችላ ብላ - በሚዲያ ስትማግጥ፤ • ከአጅነቢይ ጋር - በድፍረት ስትዘንጥ፤ ▬▬▬▬▬▬▬▬ • አቤት ሲዘገንን - አቤት ሲሰቀጥጥ፤ • ማየት አይስችልም - ንዴትም አያስውጥ፤ • ሴቶችን ፈታኝ ሆይ - ማጃጃሉን አቋርጥ፤ • መልከስከሱን ትተህ - አቅጣጫህን ለውጥ፤ • ጌታችን ፊት ቀርበህ - በጥያቄ ሳትፈጥ፤ • ማምለጫ የለምና - አይገኝም ማምለጥ፤ • መናገር ይሻላል - ዝም ቦሎ ከማፍጥ፤ ▬▬▬▬▬▬▬▬

🌿 ውዷ እህቴ፣ ጀግና ሴት ሁኚ! 📚ዲንሽን በማንም አትለውጪ፤ 📚ሐያእሽን ለማንም አትስጪ፤ 📚ሱናን ለማንም አትልቀቂ። 🌿 📚 በእምነትሽ ላይ ጽኚ፤ ብቻሽን ብትቀሪም አትንበርከኪ! 🌿🌿🌿�
🌿 ውዷ እህቴ፣ ጀግና ሴት ሁኚ! 📚ዲንሽን በማንም አትለውጪ፤ 📚ሐያእሽን ለማንም አትስጪ፤ 📚ሱናን ለማንም አትልቀቂ። 🌿 📚 በእምነትሽ ላይ ጽኚ፤ ብቻሽን ብትቀሪም አትንበርከኪ! 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 https://t.me/qdemiy_letwuhide

አንድ ሙስሊም ሴት ሊኖሯት የሚገቡ አደቦች🎀 ➺አሏህን ልትታዘዝ ➺ሰራዋንም ለአሏህ ብቻ ብላ መስራት ➺ የአሏህን መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم ልትከተል ➺እንድሁም ከሌላ ጥመት መንገዶች
አንድ ሙስሊም ሴት ሊኖሯት የሚገቡ አደቦች🎀 ➺አሏህን ልትታዘዝ ➺ሰራዋንም ለአሏህ ብቻ ብላ መስራት ➺ የአሏህን መልእክተኛ  صلى الله عليه وسلم  ልትከተል ➺እንድሁም ከሌላ ጥመት መንገዶች ልትርቅ ➺እሷም ለልጆቿና እና ለእህቶቿ  ጥሩ አምሳያ ልትሆን ➺እውቀትንም ልትማር ባወቀችውም ልትሠራ ➺ሌሎችንም ልታስተምር ➺በሚደርሱባት ችግሮች á‰ á‰€áŒĽá‰°áŠ›á‹ መንገድ ላይ ሶብር ልታደርግ ➺እንድሁም  ሙስሊም የሆኑ እህቶችን ሁሉንም ልትመክር 👌➺ጀሊሉ እዉቀት ከአደብ ከተግባር ጋር  ይስጠን መጨረሻችንን ያሳምርልን ═✿🍃🌺🍃✿═ t.me/qdemiy_letwuhide

አንዳንድ ጧቶች ቃል አይፈልጉም.... አንድ አዲስ ቀን፣ አንድ አዲስ ተስፋ፣ አንድ ዝምታ ውስጥ የተደበቀ ዱዓ ብቻ ይበቃቸዋል ዛሬ ልባችን የሚፈልገውን ሁሉ ላይሰጠን ይችላል፤ ነገር ግን አላህ የሚያ
አንዳንድ ጧቶች ቃል አይፈልጉም.... አንድ አዲስ ቀን፣ አንድ አዲስ ተስፋ፣ አንድ ዝምታ ውስጥ የተደበቀ ዱዓ ብቻ ይበቃቸዋል ዛሬ ልባችን የሚፈልገውን ሁሉ ላይሰጠን ይችላል፤ ነገር ግን አላህ የሚያዘጋጀውን ምን እንደሚመስል አናውቅም ስለዚህ ዛሬን በተስፋ እንጀምር ምናልባት የጠበቅነው ነገር ከእኛ ይልቅ አላህ ዘንድ ቀድሞ ተዘጋጅቶ ይሆናል      አልሐምዱሊላህ  ለዚህ ቀን

ተጀመረ
አዲስ የኪታብ ደርስ
      📖ኪታቡ አልቀዋዒዱል ሙስላ 🎤በኡስታዝ አቡ ኢምራን የኪታቡን PDF ለማግኘት https://t.me/sefinetunuh/9009 ደረሱ የሚሰጠዉ 🌙በአህሉ-ተውሂድ መስጂድ  - - ሸር አድርጉት https://t.me/sefinetunuh?livestream=2aa0f105b7a048c75d

"ሥራ አጥቶ እየተንከራተተ ያለን "መቼ ነው ሥራ የምትጀምረው?" ብለህ ሌላ ጭንቀት አትጨምርበት። አማራጭ ሲጠፋው ሀገሩን ለቆ በስደት ያለን "መቼ ነው የምትመለሰው?" እያልክ ብሶቱን አትቀስቅስበት።
"ሥራ አጥቶ እየተንከራተተ ያለን "መቼ ነው ሥራ የምትጀምረው?" ብለህ ሌላ ጭንቀት አትጨምርበት። አማራጭ ሲጠፋው ሀገሩን ለቆ በስደት ያለን "መቼ ነው የምትመለሰው?" እያልክ ብሶቱን አትቀስቅስበት። ትዳር የዘገየባትን ሴት "መቼ ነው የምታገቢው?" እያልክ አትነዝንዛት። ራስ ምታት አትሁንባት! ሀሳብና ጭንቀታቸውን ታግለው አፍነው የአላህን ፈረጅ በትዕግስት የሚጠባበቁን ጥያቄ በማብዛት ሌላ ችግር አትሁንባቸው። ምን እንደሚጠብቁ አትጠይቃቸው! ከመጠበቅ ውጪ ሌላ አማራጭ ቢኖራቸው ያደርጉት ነበር!! ሪዝቅ ያለው በአንተ ሳይሆን በአላህ እጅ ነውና ተዋቸው። ከቻልክ አግዛቸው፤ አልያም ዱዓ አድርግላቸው! ካልቻልክ አትረብሻቸው ዝም በላቸው!   ✍ኡስታዝ ዛኪር

ለእነዚያ ላኩላቸው ማንነታቸውን ለረሱ ወዳጅ ሆይ ​ሌሎችን ለመምሰል መሞከር ማለት የእራስህን ታሪክ ሳይሆን የሌሎችን ሁለተኛ ደረጃ ታሪክ መኖር ማለት ነው። የሰው ልጅ ትልቁ ስህተት የእርሱን ጥንካሬ እና ድካም ከሌሎች ጋር ማወዳደሩ ነው። ሌሎች በሄዱበት መንገድ ስለሄድክ ብቻ ስኬታማ አትሆንም፤ የእነርሱ መንገድ ለነርሱ የተዘጋጀ እንጂ ለአንተ የተሰራ አይደለም። ​አስታውስ፦ ኦሪጅናል ሁነህ መኖር እያለህ የሌሎች ኮፒ ሆነህ አትሙት። ​የሰዎችን ፍርድ እና አስተያየት አትፍራ ​ሰዎች ሁልጊዜ ይፈርዳሉ፤ ያማሉ፤ ያወድሳሉ፤ መልሰው ደግሞ ያናንቃሉ። የሰዎችን አስተያየት የህይወትህ መመሪያ ካደረግከው የነርሱ ባሪያ ትሆናለህ። ራስን መሆን ማለት ሁሉም ሰው እንዲወድህ ማድረግ ማለት አይደለም፤ ይልቁንም ሰዎች ቢወዱህም ባይወዱህም እውነተኛ ማንነትህን ሳትደብቅ መኖር ማለት ነው። ​አስብበት፦ የሰው ልጅ ውዳሴ ጊዜያዊ ነው፤ የውስጥ ሰላም ግን ዘላቂ ነው። ሰዎችን ለማስደሰት ስትል ራስህን አታጣ። ​ራስን መሆን ማለት "እኔ ፍጹም ነኝ" ማለት አይደለም። ራስን መሆን ማለት ድክመቶችህን አምነህ መቀበል፣ ስህተቶችህን ለመታረም ዝግጁ መሆን እና እግረ መንገድህንም አላህ የሰጠህን አቅም እና ክህሎት ማወቅ ነው። እውነተኛ ጥንካሬ የሚጀምረው የራስን ማንነት ሙሉ በሙሉ ከተቀበሉበት ቅጽበት ነው። ​ተገንዘብ፦ ነጠብጣብ ያለው እብነ በረድ እንጂ ፍጹም የሆነ ድንጋይ የለም። ድክመትህ የአንተ አካል ነው፤ እሱን ተቀብለህ ወደ ጥንካሬ ቀይረው። ​በቀን ውስጥ ለጥቂት ደቂቃዎች ብቻ እንኳ ቢሆን ፀጥታን ፈልግ። ከውስጥህ ድምፅ ጋር ተነጋገር። - ​በእርግጥ እየኖርክ ያለኸው የሚወዱትን ህይወት ነው? - ​የምታደርጋቸው ነገሮች ከእውነተኛ ፍላጎትህ የመጡ ናቸው ወይንስ ሰዎችን ለማስደሰት የምታደርጋቸው? - ​ከራስህ ጋር ታማኝ ሁን። ራስህን ሳታታልል እውነቱን ስትነግረው ውስጣዊ ድፍረትና ግልጽነት ታገኛለህ። ​ለህይወትህ የሚሆን የወርቅ ህግ ​"ራስህን ሁን፤ ምክንያቱም ሌሎች ቦታዎች በሙሉ ተይዘዋል።" ወዳጄ ​ዛሬ ውሳኔ ወስን፦ ​የሌሎችን ሁኔታ አትከታተል። ​በራስህ መንገድ ላይ በጽናት ሂድ። ​እውነተኛ ማንነትህን፣ እምነትህን፣ እና እሴቶችህን በኩራት ያዝ። ​ራስህን መሆን ስትጀምር፣ ህይወትህ ትርጉም ያገኛል፤ አእምሮህ ሰላም ያገኛል፤ መንገዶችህም ሁሉ ይከፈታሉ። 🖋𝓪𝓫𝓾 𝓶𝓪𝓻𝓲𝔂𝓪𝓱 https://t.me/BerhanFelega https://t.me/BerhanFelega

2ኛ — ተውሒዱል ኡሉሂያ (توحيد الألوهية) 📢ተውሒዱል ኡሉሂያ ማለት፦ አላህን በባሮቹ የአምልኮ ተግባራት ብቻውን መለየት ማለት ነው። እንዲሁም “ተውሒዱል ዒባዳ” (የአምልኮ አንድነት) ተብሎ ይጠራል። ትርጉሙም፦ አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እውነተኛው ኢላህ እንደሆነና ከእርሱ ውጭ እውነተኛ ኢላህ እንደሌለ በጽኑ ማመን ነው። ከእርሱ ውጭ የሚመለክ ሁሉ ባዶና ሐሰት ነው። ስለዚህ አምልኮን፣ መገዛትንና ፍጹም መታዘዝን ለአላህ ብቻ መለየት፣ ማንም ይሁን ማን ከአላህ ጋር ማንንም አለማጋራት እና ከአምልኮ አይነቶች ምንም ነገር ለሌላ አለመስጠት ነው። ከአምልኮ አይነቶችም፦ ሰላት፣ ጾም፣ ዘካ፣ ሐጅ፣ ዱዓ፣ እርዳታን መፈለግ፣ ነዝር (ስለት)፣ መስዋዕት ማቅረብ፣ ተወኩል (በአላህ ላይ መመካት)፣ ፍርሃት፣ ተስፋ፣ ውዴታ፣ ወደ አላህ መመለስ፣ አላህን መፍራት፣ መዋረድና ሌሎችም የውጭና የውስጥ የአምልኮ አይነቶች ናቸው። አላህም በውዴታ፣ በፍርሃትናበተስፋ ሁሉም በአንድነት መመለክ አለበት። ከእነዚህ አንዱን ብቻ ይዞ ሌሎቹን መተው ጥመት ነው። 💡አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ይላል፦ ﴿إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ﴾ “አንተን ብቻ እናመልካለን፤ ከአንተም ብቻ እርዳታን እንለምናለን።” 💡እንዲሁም አላህ ይላል፦ ﴿وَمَنْ يَدْعُ مَعَ اللَّهِ إِلَهًا آخَرَ لَا بُرْهَانَ لَهُ بِهِ فَإِنَّمَا حِسَابُهُ عِنْدَ رَبِّهِ إِنَّهُ لَا يُفْلِحُ الْكَافِرُونَ﴾ “ከአላህ ጋር ሌላ አምላክን የሚጠራ፣ ለእርሱም ምንም ማስረጃ የሌለው ሲሆን፣ ሒሳቡ በጌታው ዘንድ ብቻ ነው። በእርግጥ ካፊሮች አይሳካላቸውም።” وتوحيد العبادة من أجله خلق الله الجن والإنس، قال تعالى: “የአምልኮ ተውሒድን ለመፈጸም ነው አላህ ጂንንና ሰውን የፈጠረው፤ አላህም እንዲህ አለ፦” ﴿وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالإِنْسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ﴾ “ጂንንና ሰውን የፈጠርኩት እንዲያመልኩኝ ብቻ ነው።” ተውሒዱል ዒባዳ የዲን መጀመሪያና መጨረሻ፣ ግልጽና ውስጣዊ ነው። ይህም የመልእክተኞች ጥሪ መጀመሪያና መጨረሻ ነው። 🔹መልእክተኞች የተላኩትም ፤ መጻሕፍት የተወረዱትም ፤ የጂሃድ ሰይፎች የተመዘዙትም ለዚህ ነው። በዚህም ምክንያት በሙእሚኖችና በካፊሮች፣ በጀነት ሰዎችና በእሳት ሰዎች መካከል ልዩነት ተደርጓል። ይህም “ላ ኢላሀ ኢለላህ” (لا إله إلا الله) የሚለው ቃል ትርጉም ነው። ተውሒዱል ኡሉሂያ ሁሉም መልእክተኞች የጠሩበት ተውሒድ ነው። እሱን መካድ ደግሞ ቀደምት ሕዝቦችን ለጥፋትና ለውድቀት ያደረሰ ነው። 💡አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ይላል፦ ﴿وَمَا أَرْسَلْنَا مِنْ قَبْلَكَ مِنْ رَسُولٍ إِلا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ﴾ “ከአንተ በፊት የላክነው ማንኛውም መልእክተኛ፣ ‘ከእኔ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፤ ስለዚህ እኔን ብቻ አምልኩ’ ብለን ሳናስተምረው አልላክንም።” ✍በተውሒዱል ሩቡቢያና በተውሒዱል ኡሉሂያ መካከል ያለው ግንኙነት ተውሒዱል ሩቡቢያ ወደ ተውሒዱል ኡሉሂያ ያስገድዳል። ምክንያቱም አንድ ሰው አላህ ጌታ፣ ፈጣሪና ሁሉን ነገር አስተናጋጅ መሆኑን ካመነ፣ አላህን ብቻ ማምለክና ማንንም ከእርሱ ጋር አለማጋራት ይኖርበታል። ሙሽሪኮች ግን አንድ አምላክ ብቻ አላመለኩም። አላህ ብቻውን ለአምልኮ የሚገባው መሆኑን ክደው፣ ብዙ አማልክትን ያመልኩ ነበር። እነዚህ አማልክትም ወደ አላህ ያቀርበናል ብለው ያስቡ ነበር። ከዚህ ጋር እነዚያ ሙሽሪኮች የሚያመልኳቸው አማልክት ሊጎዱም ሆነ ሊጠቅሙ እንደማይችሉ ያውቁ ነበር። ስለዚህ አላህ በሩቡቢያ ተውሒዳቸውን በመቀበላቸው ብቻ ሙእሚኖች አላደረጋቸውም፤ ይልቁንም ከአላህ ጋር ሌሎችን በአምልኮ በማጋራታቸው ከካፊሮች መደብ አደረጋቸው። ምክንያቱም አላህ ጌታ፣ ፈጣሪ፣ ሲሳይ ሰጪ፣ ባለቤት፣ የሁሉ ነገር ተቆጣጣሪ፣ ሕይወት ሰጪና ሞት አምጪ ከሆነ፣ የፍጹምነት ባህሪያት ሁሉ ባለቤት ከሆነና ከሁሉም ጉድለት የጸዳ ከሆነ፣ ሁሉም ነገር በእጁ ከሆነ፣ እርሱ ብቻውን ኢላህ ሊሆንና ለእርሱ ምንም አጋር ሊኖረው አይችልም። ስለዚህ አምልኮ ለእርሱ ብቻ መደረግ አለበት። ይሄም የ“ላ ኢላሀ ኢለላህ” ትርጉም ነው እዚህ ላይ የአህሉ-ሱንና ወል-ጀማዓ እምነት ከሌሎች ይለያል። እነሱ “ላ ኢላሀ ኢለላህ” ማለት “ከአላህ በቀር ፈጣሪና ሲሳይ ሰጪ የለም” ብቻ ማለት ነው አይሉም። ይልቁንም ትክክለኛው ትርጉም፦ “ከአላህ በቀር በእውነት ሊመለክ የሚገባው ማንም የለም” ማለት ነው። ይህም ማለት ተውሒዱል ኡሉሂያ አላህን ብቻውን በሁሉም የአምልኮ አይነቶች መለየትን ያስፈልጋል። አምልኮም በልብ፣ በምላስ ንግግርና በልብና በአካል ተግባር ይሆናል። “ላ ኢላሀ ኢለላህ” ለሚለው ምስክርነት ሁለት ታላላቅ መሠረቶች አሉት 1ኛ፦ ሁሉንም የአምልኮ አይነቶች ለአላህ ብቻ ማድረግ፤ ለእርሱም ምንም አጋር አለመስጠት። 2ኛ፦ ከእነዚህ የአምልኮ አይነቶች ምንም ነገር ለሌላ አለመስጠት። ይህ ማለት፦ ፍጡር ለፈጣሪ ብቻ የሚገባውን መብትና ልዩ ባህሪ እንዳይሰጥ ማለት ነው፤ እነዚህም ከአላህ በቀር ማንም ሊያደርጋቸው የማይችላቸው ናቸው። ስለዚህ፦ ከአላህ በቀር ማንም አይመለክም፤ ለአላህ በቀር ለማንም ሰላት ፤  ሱጁድ ፤ ስለት አይገባም፤ ለሌላ መስዋዕት አይታረድም፤ ከአላህ በላይ በሌላ ላይ ፍጹም መተማመን አይደረግም፤ እርዳታ ከአላህ በቀር አይፈለግም፤ ከእርሱ በቀር ማንም አይጠራም። እነዚህና መሰል ነገሮች የአላህ ብቻ ልዩ መብቶች ናቸው። 🔹ለአላህ ብቻ የሚደረግ አምልኮ ሁለት ሁኔታዎች አሉት 1ኛ — ኢኽላስ (ማጥራት): አምልኮው ለአላህ ፊት ብቻ የተጣራ መሆን አለበት። 2ኛ — መከተል (ኢቲባዕ): አላህን መልእክተኛው  በሸሪዓ ባዘዘው መንገድ ብቻ ማምለክ፣ ባዘዘው መታዘዝ፣ በነገረው ነገር ማመን፣ አምልኮውም በቦታና በጊዜ መልእክተኛው  ካዘዘው ጋር የሚስማማ መሆን ነው። እርሱ የከለከለውንና ያስጠነቀቀውንም መተው አለበት። 🔹ስለዚህ አላህን በአምልኮ፣ በመገዛት፣ በመታዘዝና በዉዴታ ብቻውን መለየት፦ “ላ ኢላሀ ኢለላህ” የሚለውን ምስክርነት መፈጸም ነው። መልእክተኛውን  መከተል፣ ባዘዘው ነገር መታዘዝ፣ ከከለከለው መራቅና ለእርሱ ፍጹም መገዛት ደግሞ፦ “ሙሐመዱ ረሱሉላህ” የሚለውን ምስክርነት መፈጸም ነው። 📢የአህሉስ-ሱንና ወል-ጀማዓ መንገድ እነሱ አላህን ብቻ ያመልካሉ፤ ከእርሱም ጋር ምንም ነገር አያጋሩም። ከአላህ በቀር ማንንም አይለምኑም፤ ከአላህ በቀር ማንንም እርዳታ አይጠይቁም፤ በእርሱ ብቻ ይመካሉ፤ ከእርሱ በቀር ማንንም በአምልኮ የሚገባ ፍርሃት አይፈሩም። አላህንም በመታዘዝ፣ በማምለክና በመልካም ሥራዎች ወደ እርሱ ይቀርባሉ። አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ይላል፦ ﴿وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا﴾ “አላህን ብቻ አምልኩ፤ ከእርሱም ጋር ምንም ነገር አታጋሩ።” 📚من كتاب الوجيز في عقيدة السلف الصالح Šhttps://t.me/Abuimran_alkemisse Šhttps://t.me/Abuimran_alkemisse