Grade 8 Info & Materials
رفتن به کانال در Telegram
▶ ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች፦ ➤ በተለያቱ ትምህርት ቤቶች የተዘጋጁ:- ➢ Models ➢ Short notes (NotebookLM የታገዘ) ➢ Audio & Videooverview ➢ Ministry Exams ➤ የአጠናን ስልትና የፈተና ጊዜ ሲቃረብ በአላህ እገዛ ጭንቀትን ለማስወገድ የሚረዱ ጥቆማዎችን እንለቃለን። ◉ የቂያማ እለት ከምንጠየቀው ጥያቄ አንዱ ❝በአወቅከው ነገር ምን ሰራህበት❞ ነው!!
نمایش بیشتر2 218
مشترکین
-224 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
-5030 روز
در حال بارگیری داده...
کانالهای مشابه
ابر برچسبها
هیچ دادهای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
ژوئیه '26
ژوئیه '26
+33
در 5 کانالها
ژوئن '26
+106
در 1 کانالها
Get PRO
مه '26
+179
در 1 کانالها
Get PRO
آوریل '26
+74
در 5 کانالها
Get PRO
مارس '26
+90
در 3 کانالها
Get PRO
فوریه '26
+74
در 4 کانالها
Get PRO
ژانویه '26
+98
در 3 کانالها
Get PRO
دسامبر '25
+87
در 7 کانالها
Get PRO
نوامبر '25
+80
در 6 کانالها
Get PRO
اکتبر '25
+90
در 6 کانالها
Get PRO
سپتامبر '25
+54
در 5 کانالها
Get PRO
اوت '25
+49
در 7 کانالها
Get PRO
ژوئیه '25
+40
در 7 کانالها
Get PRO
ژوئن '25
+226
در 7 کانالها
Get PRO
مه '25
+288
در 7 کانالها
Get PRO
آوریل '25
+148
در 6 کانالها
Get PRO
مارس '25
+151
در 7 کانالها
Get PRO
فوریه '25
+103
در 8 کانالها
Get PRO
ژانویه '25
+168
در 10 کانالها
Get PRO
دسامبر '24
+185
در 9 کانالها
Get PRO
نوامبر '24
+150
در 7 کانالها
Get PRO
اکتبر '24
+157
در 11 کانالها
Get PRO
سپتامبر '24
+100
در 8 کانالها
Get PRO
اوت '24
+80
در 12 کانالها
Get PRO
ژوئیه '24
+31
در 7 کانالها
Get PRO
ژوئن '24
+75
در 10 کانالها
Get PRO
مه '24
+179
در 12 کانالها
Get PRO
آوریل '24
+188
در 15 کانالها
Get PRO
مارس '24
+80
در 8 کانالها
Get PRO
فوریه '24
+88
در 6 کانالها
Get PRO
ژانویه '24
+59
در 6 کانالها
Get PRO
دسامبر '23
+187
در 1 کانالها
| تاریخ | رشد مشترکین | اشارات | کانالها | |
| 15 ژوئیه | +2 | |||
| 14 ژوئیه | 0 | |||
| 13 ژوئیه | +3 | |||
| 12 ژوئیه | +5 | |||
| 11 ژوئیه | +5 | |||
| 10 ژوئیه | +5 | |||
| 09 ژوئیه | +2 | |||
| 08 ژوئیه | +1 | |||
| 07 ژوئیه | +3 | |||
| 06 ژوئیه | 0 | |||
| 05 ژوئیه | +1 | |||
| 04 ژوئیه | 0 | |||
| 03 ژوئیه | +1 | |||
| 02 ژوئیه | +1 | |||
| 01 ژوئیه | +4 |
پستهای کانال
📚 የዘንድሮ 8ኛ ክፍል አበቦች፣ አንፀባራቂ ኮከቦች... በ2019 የትምህርት ዘመን ወደ 9ኛ ክፍል ለምትገቡ በሙሉ!
የሁላችሁም የ8ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ (የሚኒስትሪ) ፈተና ውጤታችሁ ልፋታችሁን የሚክስና ያማረ እንደሚሆን ጽኑ ተስፋ አለን።
ወደ ቀጣዩና ወሳኙ የትምህርት ምዕራፍ ስትሸጋገሩ፣ የ9ኛ ክፍል የትምህርት ጉዟችሁ ይበልጥ የተቃና፣ ግልጽና ስኬታማ እንዲሆን ታስቦ ከዚህ ቀደም የተከፈተውን የቴሌግራም ቻናል አሁኑኑ እንድትቀላቀሉ ተጋብዛችኋል።
በዚህ ቻናል ውስጥ የቀጣይ አመት የትምህርት ጉዟችሁን የሚያቀሉ፦
🔸 የተለያዩ የትምህርት ድጋፎችና ወቅታዊ መረጃዎች
🔸 አጋዥ መጻሕፍትና አጫጭር ማስታወሻዎች
🔸 የልምምድ ፈተናዎችና ውጤታማ የጥናት ስልቶች
🔸 ለህይወታችሁና ለትምህርት ጉዟችሁ ስንቅ የሚሆኑ አነቃቂና ጠቃሚ ፅሁፎች፣ እንዲሁም ሌሎች በርካታ ጠቃሚ ግብዓቶች በተከታታይ ይቀርቡላችኋል። ኢንሻአላህ!!
✅ የቀጣይ አመት የስኬት ጉዟችሁ አጋዥ ወደሆነው ማዕከል አሁኑኑ Join በሉ!!👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/Grade9Info
| 2 | 🌟 የኩራትና የብስራት ዜና ከሙምታዝ አካዳሚ! 🌟
የሙምታዝ ድምፅ እንደገና በክብር አስተጋባ! በዕውቀት፣ በስነ-ምግባርና በትጋት ኮትኩተን ያሳደግናቸው ውድ አበቦቻችን በከተማ አቀፉ የ6ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ አዲስ የድል ምዕራፍ ከፍተዋል!
የሙምታዝ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ሚኒስትሪ ፈተና ተፈታኝ አበቦች፣ አንፀባራቂ ኮከቦች ሁሉም የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ወደ 7ኛ ክፍል አልፈዋል! አንድም ተማሪ ሳይቀረው ሙሉ በሙሉ (100%) የማለፋቸው ታላቅ የምሥራች የትምህርት ቤታችንን የላቀ የትጋት ደረጃ በግልጽ ያሳያል።
ይህ አስደናቂ ውጤት የልጆቻችን የሌሊት እቅድና የቀን ጥረት፣ የወላጆች ያላሰለሰ ክትትልና ዱዓ፣ እንዲሁም የመምህራኖቻችን ያልተቆጠበ ፍቅርና ድካም ፍሬ ነው።
💎 የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ለተፈተናችሁ አበቦች በሙሉ፦
በየትኛውም ትምህርት ቤት ሆናችሁ ዘንድሮ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተናን ወስዳችሁ የጥረታችሁን ፍሬ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ ውድ ተማሪዎች በሙሉ፤ አላህ ልፋታችሁን ባርኮላችሁ፣ ልባችሁን በሐሴት የሚሞላና ቤተሰቦቻችሁን የሚያኮራ እጅግ ማራኪ ውጤት እንደምታመጡ ትልቅ ተስፋ አለን።
ለትጋታችሁና በቅርቡ ለምታስመዘግቡት ብሩህ ስኬት ከወዲሁ እንኳን ደስ አላችሁ! ወደ 7ኛ ክፍል የምታደርጉት አዲሱ ጉዞም የላቀ የዕውቀት ብርሃን የሚበራበት፣ የላቀ ራዕይ የምትሰንቁበት ይሁን!
✨ ጥረት ካለ ስኬት አይርቅም፤ ትጋት ካለ ድል አይታጣም!!
ስኬት ለልጆቻችን፣ ለአበቦቻችን፣ ለአንፀባራቂ ኮከቦቻችን! ለመላው የሙምታዝ አካዳሚ ማህበረሰብ፣ ለወላጆችና ለድርጅቱ አመራሮች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳን ደስ አለን!
🤲 ዱዓ
አላህ ሆይ! እነዚህን ብሩህ አእምሮዎች፣ የወደፊት ተስፋዎቻችንን ከመጥፎ ነገር ሁሉ ጠብቅልን። የወላጆቻቸው አይን ማረፊያ፣ የሀገርና የኡማው ኩራትና አለኝታ አድርጋቸው።
አላህ ሆይ! ዕውቀታቸውንና ጥበባቸውን ጨምርላቸው፤ በቀጣዩ የ7ኛ ክፍል የትምህርት ጉዟቸውና በህይወት ዘመናቸው ሁሉ ከዚህ የላቀ፣ ይበልጥ የገዘፈ ስኬትና ድልን አጎናጽፋቸው። በሄዱበት መስክ ሁሉ ሁልጊዜም ቀዳሚ፣ አንፀባራቂና መሪ ኮከቦች ያድርጋቸው!
አሚን ያ ረበል ዓለሚን! 🤲✨
✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል | 766 |
| 3 | 🌟 የኩራትና የብስራት ዜና ከሙምታዝ አካዳሚ! 🌟
የሙምታዝ ድምፅ እንደገና በክብር አስተጋባ! በዕውቀት፣ በስነ-ምግባርና በትጋት ኮትኩተን ያሳደግናቸው ውድ አበቦቻችን በከተማ አቀፉ የ6ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ አዲስ የድል ምዕራፍ ከፍተዋል!
የሙምታዝ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ሚኒስትሪ ፈተና ተፈታኝ አበቦች፣ አንፀባራቂ ኮከቦች ሁሉም የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ወደ 7ኛ ክፍል አልፈዋል! አንድም ተማሪ ሳይቀረው ሙሉ በሙሉ (100%) የማለፋቸው ታላቅ የምሥራች የትምህርት ቤታችንን የላቀ የትጋት ደረጃ በግልጽ ያሳያል።
ይህ አስደናቂ ውጤት የልጆቻችን የሌሊት እቅድና የቀን ጥረት፣ የወላጆች ያላሰለሰ ክትትልና ዱዓ፣ እንዲሁም የመምህራኖቻችን ያልተቆጠበ ፍቅርና ድካም ፍሬ ነው።
💎 ለውድ የቻናላችን አባላት በሙሉ፦
በዚህ ቻናል ውስጥ የምትገኙ፣ ዘንድሮ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የወሰዳችሁ ውድ ተማሪዎች በሙሉ፤ አላህ ጥረታችሁን ባርኮላችሁ፣ ልባችሁን በደስታ የሚሞላና ቤተሰቦቻችሁን የሚያኮራ እጅግ ማራኪ ውጤት እንዳመጣችሁ ሙሉ በሙሉ በአላህ ተስፋ እናደርጋለን። ለጥረታችሁና ለምታስመዘግቡት ስኬት ሁሉ ከወዲሁ እንኳን ደስ አላችሁ! ወደ 7ኛ ክፍል የምታደርጉት ጉዞ የላቀ የዕውቀት ብርሃን የሚበራበት ይሁን!
✨ ጥረት ካለ ስኬት አይርቅም፤ ትጋት ካለ ድል አይታጣም!!
ስኬት ለልጆቻችን፣ ለአበቦቻችን፣ ለአንፀባራቂ ኮከቦቻችን! ለመላው የሙምታዝ አካዳሚ ማህበረሰብ፣ ለወላጆችና ለድርጅቱ አመራሮች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ等级፣ እንኳን ደስ አለን!
🤲 ዱዓ
አላህ ሆይ! እነዚህን ብሩህ አእምሮዎች፣ የወደፊት ተስፋዎቻችንን ከመጥፎ ነገር ሁሉ ጠብቅልን። የወላጆቻቸው አይን ማረፊያ፣ የሀገርና የኡማው ኩራትና አለኝታ አድርጋቸው።
አላህ ሆይ! ዕውቀታቸውንና ጥበባቸውን ጨምርላቸው፤ በቀጣዩ የ7ኛ ክፍል የትምህርት ጉዟቸውና በህይወት ዘመናቸው ሁሉ ከዚህ የላቀ፣ ይበልጥ የገዘፈ ስኬትና ድልን አጎናጽፋቸው። በሄዱበት መስክ ሁሉ ሁልጊዜም ቀዳሚ፣ አንፀባራቂና መሪ ኮከቦች ያድርጋቸው!
አሚን ያ ረበል ዓለሚን! 🤲✨
✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል | 9 |
| 4 | ውጤት ተለቋል....
የክፍለ ከተማችን የ6ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ በጋዜጣዊ መግለጫው ተጠቁሟል። | 669 |
| 5 | 🔹ውጤት ሲለቀቅ ...
የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ሲሆን ለመመልከት ከታች የሚገኘውን ሊንክ መጠቀም ይችላሉ።
👉 https://aa6.ministry.et/#/result | 692 |
| 6 | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ጠዋት ይፋ ይሆናል፡፡ | 664 |
| 7 | የዘንድሮ 8ኛ ክፍል አበቦች፣ አንፀባራቂ ኮከቦች... በ2019 የትምህርት ዘመን ወደ 9ኛ ክፍል ለምትገቡ በሙሉ!
የሁላችሁም የ8ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ (የሚኒስትሪ) ፈተና ውጤታችሁ ልፋታችሁን የሚክስና ያማረ እንደሚሆን ጽኑ ተስፋ አለን።
ወደ ቀጣዩና ወሳኙ የትምህርት ምዕራፍ ስትሸጋገሩ፣ የ9ኛ ክፍል የትምህርት ጉዟችሁ ይበልጥ የተቃና፣ ግልጽና ስኬታማ እንዲሆን ታስቦ ከዚህ ቀደም የተከፈተውን የቴሌግራም ቻናል አሁኑኑ እንድትቀላቀሉ ተጋብዛችኋል።
በዚህ ቻናል ውስጥ የቀጣይ አመት የትምህርት ጉዟችሁን የሚያቀሉ፦
🔸 የተለያዩ የትምህርት ድጋፎችና ወቅታዊ መረጃዎች
🔸 አጋዥ መጻሕፍትና አጫጭር ማስታወሻዎች
🔸 የልምምድ ፈተናዎችና ውጤታማ የጥናት ስልቶች
🔸 ለህይወታችሁና ለትምህርት ጉዟችሁ ስንቅ የሚሆኑ አነቃቂና ጠቃሚ ፅሁፎች፣ እንዲሁም ሌሎች በርካታ ጠቃሚ ግብዓቶች በተከታታይ ይቀርቡላችኋል። ኢንሻአላህ!!
✅ የቀጣይ አመት የስኬት ጉዟችሁ አጋዥ ወደሆነው ማዕከል አሁኑኑ Join በሉ!!
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Grade9Info | 917 |
| 8 | የአዲስአበባ የ8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ
ውጤት ተለቋል
💻ውጤት ለማየት
https://aa.ministry.et/#/result ይጠቀሙ | 1 402 |
| 9 | بدون متن... | 1 376 |
| 10 | ወላጅ እናቱን የሚኒስትሪ ፈተናው ቀን በሞት ያጣው ተማሪ ኻሊድ የባንክ አካውንት ይፋ ሆኗል።
ተማሪ ኻሊድን መርዳት የምትፈልጉ የሲንቄ ባንክ እና የአዋሽ ባንክ አካውንት ተከፍቷል። ተማሪ ኻሊድ እድሜው 18 ስላልሞላውና ዘመድም ስለሌለው፤ ብቻውን ገንዘብ አውጥቶ መጠቀም ስለማይችል፣ አካውንቱ በአካባቢው መስጅድ ኡስታዝ፣ ከሀገር ሽማግሌ እና ከራሱ ጋር በጋራ በመሆን አካውንት ተከፍቶለታል።
①) ስንቄ ባንክ
11 14385901915
②) አዋሽ ባንክ
013201115433100 | 1 702 |
| 11 | የድል ብስራት! የስኬት ማማ! 🏆
📖 «...ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትን ጨምርልኝ በል፡፡» (ሱረቱ ጣሃ: 114)
አልሃምዱሊላህ! የቻናላችን ቤተሰቦች ሆይ፣ ዛሬ ሰኔ 12/2018 ዓ.ል የሀገራችን የዓይን ብርሃን የሆኑት የ8ኛ ክፍል አበቦቻችን፣ የሀገር ድምቀቶች እና አንፀባራቂ ኮከቦቻችን የከተማ አቀፍ የሚኒስትሪ ፈተናቸውን በላቀ የዲሲፕሊን መንፈስ እና በታላቅ ስኬት አጠናቀዋል።
ውድ ልጆቻችን! የለፉበት የጥናት ምሽቶች፣ የደከሙበት የመማሪያ ክፍሎች ውጤት ዛሬ በፈገግታችሁ መታተሙ ያስደስተናል። እናንተ የነገዋ ሀገር ተስፋ፣ የቤተሰባችሁ የኩራት ምንጭ ናችሁ። ይህ ጉዞ ለትልልቅ ስኬቶች መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ አይደለም። ገና ብዙ የስኬት ማማዎችን ትረግጣላችሁ፤ የላቀ ታሪክም ትሰራላችሁ! 🚀
ለወላጆች፣ መምህራን፣ የትምህርት ቤት አስተዳደርና ለመላው ማህበረሰብ፦
ለዚህ ክብር ያበቃችሁ፣ ሌት ተቀን የደከማችሁ፣ በሀሳብ፣ በምክርና በዱዓ ከልጆቻችሁ ጎን የቆማችሁ ሁሉ፤ አላህ ውለታችሁን በጀነት ይክፈለው። የአንድ ልጅ ስኬት የመላው ማህበረሰብ ድልና ኩራት ነው። ✨
🤲 ዱዓችን፦ ሁሉም እጁን አንስቶ አሚን ይበል!
🔷 ያ አላህ! ያጠናቀቁትን ፈተና ለልጆቻችን የላቀ ውጤት እና የደስታ ማብሰሪያ አድርግላቸው፤ ድካማቸውን ከንቱ አታድርግባቸው።
🔷 ያ ረብ! ለእነዚህ የሀገር ድምቀቶች በምድራዊ ሕይወታቸው ጠቃሚ ዕውቀትን፣ በወዲያኛው ዓለም ደግሞ መዳንንና ስኬትን ለግሳቸው።
🔷 ያ አላህ! ለልጆቻቸው ስኬት ደፋ ቀና ለሚሉ ወላጆች፣ ዕውቀታቸውን ለሚለግሱ መምህራንና ለአስተዳደር አካላት በሙሉ ኸይር ጀዛቸውን አብዝተህ ክፈላቸው፤ ማህበረሰባችንንም በዕውቀትና በሰላም ገንባው።
🔷 ያ አላህ! አሁን ላይ የማጠቃለያ ፈተና (Final Exam) መፈተን ለጀመሩ፣ ለቀጣይ የትምህርት ምዕራፍ ሌት ተቀን ለሚተጉ አበቦቻችንና አንፀባራቂ ኮከቦቻችን ሁሉ አእምሯቸውን አብራልን፣ የረሱትን አሳስባቸው፣ የፈሩትን አስወግድላቸው። በዕውቀት አሳድጋቸው፣ በስኬት አስውባቸው፣ በውጤት አበሽብሻቸው!
አሚን ያ ረበል ዓለሚን! 🤲
📚 የዕውቀት ጎዳና፤ ለዘላለም የተባረከ ነው!
✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል | 1 597 |
| 12 | بدون متن... | 893 |
| 13 | ውድ ተማሪዎች እንዲሁም መላው የቻናላችን ቤተሰቦች
ሰላም፣ ጤና እና የአላህ እዝነት በእናንተ ላይ ይሁን፤
አልሃምዱሊላህ! የሀገር ተስፋዎች፣ የ6ኛ ክፍል አበቦቻችን እና አንፀባራቂ ኮከቦቻችን ከተማ አቀፍ የሚኒስትሪ ፈተናቸውን ዛሬ በሰላም፣ በስኬት እና በታላቅ የዲሲፕሊን መንፈስ አጠናቀዋል።
ልጆቻችን ይህንን ምዕራፍ በልበ ሙሉነት እንዲሻገሩ በሃሳብ፣ በምክርና በዱዓ ከጎናቸው ለነበራችሁ ውድ ወላጆች እና መላው ማህበረሰብ አላህ ኸይር ጀዛችሁን አብዝቶ ይክፈላችሁ። 🤲
ቀጣዩ የተስፋ ምዕራፍ፦ የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና
ነገ ሐሙስ፣ ሰኔ 11/2018 ዓ.ል ደግሞ ሌላኞቹ የቤታችን ድምቀቶች፣ የ8ኛ ክፍል አበቦች እና አንፀባራቂ ኮከቦቻችን የከተማ አቀፍ ሚኒስትሪ ፈተናቸውን በይፋ ይጀምራሉ። እነዚህ ልጆቻችን የደከሙበትን የጥናት ፍሬ የሚያዩበት፣ የተመኙትን የላቀ ውጤት የሚያስመዘግቡበት እንዲሆን ሁላችንም በዱዓ እና በቅን ምኞት ከጎናቸው እንቁም!
🤲 ለተማሪዎቻችን ዱዓ
ያ አላህ! ነገ ፈተና ለሚጀምሩት የ8ኛ ክፍል ልጆቻችን አእምሯቸውን አብርቶላቸው፣ ያጠኑትን አሳስባቸው፤ የፈሩትን አስወግደህ ልባቸውን በሰኪና (በረጋ መንፈስ) ሙላው። ብዕሮቻቸውን ቀጥ አድርግላቸው፣ ፈተናውን አግራልላቸው፤ የድካማቸውን አምረውና ደምቀው እንዲያዩ፣ የወላጆቻቸውም የኩራት ምንጭ እንዲሆኑ መልካም ውጤትን ለግሳቸው።
ያ ረብ! ዛሬ ፈተናቸውን በሰላም ያጠናቀቁትን የ6ኛ ክፍል አበቦቻችንንም ድካማቸውን ከንቱ አታድርግባቸው፤ የለፉበትን ውጤት አሳምረህ በመልካም የምስራች ልባቸውን አስደስት። ለቀጣዩ የትምህርት ህይወታቸውም በርካታ ስኬቶችንና ብሩህ ተስፋን ስጣቸው።
አሚን ያ ረበል ዓለሚን! 🤲
📚 አላህ ልጆቻችንን ለታላቅ ስኬት ያብቃቸው!
✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል | 1 482 |
| 14 | 📚 📚 ርዕስ: የድል ዋዜማ ማሳሰቢያ፦ የመጨረሻ ጥሪ ለወደፊቱ የሀገር ብርሃኖች!
ለንጋቱ ፀሐዮች፣ ለውድ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተፈታኝ አበቦቻችን በሙሉ፤
የፊታችን ሰኞ ሰኔ 8 (ለ6ኛ ክፍል) እና ሰኔ 11 (ለ8ኛ ክፍል) የምትወስዱት የከተማ አቀፍ ሚኒስትሪ ፈተና ደርሷል። ይህ ዕለት የድካማችሁ ዋጋ የሚከፈልበት፣ የተስፋችሁ ማማ የሚቆምበት ወርቃማ ቀን ነው። አሁን መደናገጥና ፍርሃትን አውርዳችሁ፣ ሙሉ እምነታችሁን በአላህ ላይ ጥላችሁ፣ በፈገግታና በውስጥ ሰላም ወደ ፈተናው አዳራሽ የምትገቡበት ጊዜ ነው።
የአንድ ዓመት ሙሉ ልፋታችሁ ፍሬ እንዲያፈራ፣ በአላህ ፈቃድና እገዛ የሚከተሉትን ወሳኝና ጥብቅ መመሪያዎች በንቃት ተግብሩ፡
❶. የፈተናው ዋዜማ እና የጠዋት ዝግጅት
የመግቢያ ካርድ እና ቁሳቁስ፡ የመግቢያ ካርዳችሁን (Admission Card)፣ HB ወይም 2B እርሳስ፣ ጥሩ ላጲስ እና መቅረጫ በዋዜማው ምሽት አዘጋጅታችሁ አስቀምጡ።
እረፍትና አመጋገብ፡ በፈተናው ዋዜማ በቂ እንቅልፍ ተኙ። ጠዋት ላይ ቀለል ያለ ቁርስ፣ ከሰዓት ደግሞ ቀለል ያለ ምሳ ተመገቡ፤ በቂ ውሃም መጠጣታችሁን አትርሱ።
በሰዓቱ መገኘት፡ ሳይጣደፉና ሳይደናገጡ፣ አእምሮአችሁ እንዲረጋጋ ከፈተናው መጀመሪያ 30 ደቂቃ ቀድማችሁ በጣቢያው ተገኝታችሁ ተረጋጉ።
❷. የኦፕቲካል (OMR) መልስ መስጫ ወረቀት ጥንቃቄ (እጅግ ወሳኝ!)
የመለያ ቁጥር እና የትምህርት አይነት ኮድ፡ የፈተና ወረቀት እንደደረሳችሁ ከAdmission Card ላይ አይታችሁ ስማችሁን፣ የትምህርት ቤቱን ስም፣ የመለያ ቁጥራችሁን (Registration Number) እና የትምህርት አይነት መለያ ኮዱን (Subject Code) በየሳጥኑ በትክክል ፃፉ።
ሳጥኖችን ማጥቆር፡ ከፃፋችሁት ቁጥር እና ፊደል ትይዩ ያለውን አራት ማዕዘን ቅንፍ [ ] በእርሳስ ብቻ በጥንቃቄ አጥቁሩ።
ምርጫ መቀየር ሲፈልጉ፡ መጀመሪያ ያጠቆራችሁትን ቦታ በላጲስ ምንም አይነት የእርሳስ ዱካ ሳይቀር በደንብ አጥፉት።
የወረቀቱ ደህንነት፡ ወረቀቱ ላይ ምንም አይነት ትርፍ ጭረት፣ ስዕል ወይም ነጥብ አታድርጉ፤ ማዕዘኖቹን አታጥፉ። ማሽኑ (OMR) እንዳያነበው ሊያደርግ ስለሚችል በከፍተኛ ንፅህና ያዙት።
እገዛ መጠየቅ፡ በአጋጣሚ ወረቀቱ ቢቀደድ ወይም ቢበላሽባችሁ፣ ምንም ሳትደነግጡ እጅ በማውጣት ፈታኙን መምህር በአክብሮት ጠይቁ።
❸. ከፈተና በኋላ...
ፈተናው እንደተጠናቀቀ "ምን አገኘሁ? ስንት ጥያቄ ተሳሳትኩ?" በማለት ጥያቄዎችን ከጓደኞቻችሁ ጋር አትወያዩ። ይህ ጭንቀትን ስለሚጨምር ለቀጣዩ ፈተና አእምሮአችሁን ያደክማል። ከአላህ እገዛ ቀጥሎ የተረጋጋ አእምሮ ለቀጣዩ ፈተና ትልቅ ስኬት ነው።
ውድ ተማሪዎቻችን፤ እኛ በበኩላችን ሙሉ እምነት ጥለንባችኋል። እናንተ ሰበቡን (ምክንያቱን) በሚገባ አድርሳችኋል፤ ቀሪውን ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ሁሉንም ነገር ማድረግ በሚችለው በፈጣሪያችሁ በአላህ ላይ ጥሉት (ተወኩል አድርጉ)። ጥረታችሁን አምኖ በአላህ ላይ የተደገፈ ተማሪ መቼም አይወድቅም። ከፊት ለፊታችሁ ድልና ስኬት ይጠብቃችኋል!
የግጥም ግብዣ ✍️ ረሻድ 👇
ንፁዎችን አደራ
በተወኩል ልመሳጠር - ከጌታዬ ጋራ
መጥፎን አርቅላቸው - ከሚቀማመጡበት ስፍራ
ወዳጅ አበርክትላቸው - አላህን የሚፈራ፤
ሰውን የሚያከብር - የማያውቅ ጎራ፤
ህይወቷቸው ይመር - ኑሮአቸውም ይብራ፤
በተውሒድ ይሞላ - የህይወታቸው ጎተራ፤
በአላህ ይጠበቁ - ከመጥፎ አሻራ
እባክህ የአላህ - ተማሪዎችን አደራ፤
እባክህ የአላህ - ንፁዎችን አደራ።
🤲 አጭር ዱዓ ለአንፀባራቂ ኮከቦቻችን ⭐
ያ አላህ! አንተ እውቀትን ሰጪ፣ ልብን ከፋች እና ጥበብን መጋቢ አምላክ ነህ። እነዚህን ውድ ልጆቻችንን በፈተና ወንበር ላይ በሚቀመጡበት ወቅት ልባቸውን አስፋላቸው፤ ያጠኑትን ወደ አእምሯቸው መልስላቸው፤ ያልገባቸውን አብራራላቸው። በፈተና ወቅት የሚመጣን ጭንቀት እና መደናገር አንሳላቸው፤ ብዕሮቻቸውን ወደ ትክክለኛው መልስ አቅናላቸው። በጥረታቸው ብቻ ሳይሆን በአንተ ሰፊ እዝነት፣ ልፋታቸውን አሳምረህ አስደሳች እና ያማረ ውጤት ወፍቃቸው። አሚን! ያ ረበል ዓለሚን! 🤲
✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል | 1 610 |
| 15 | بدون متن... | 1 161 |
| 16 | 📚 Review English Questions from Grade 6, 7 and 8
✅ Part 3 (Last)
📚For Grade 8 Students
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
✅ አላህ ይርዳችሁ!! 🤲🤲 | 5 866 |
| 17 | 📚 Review English Questions from Grade 6, 7 and 8
✅ Part 2
📚For Grade 8 Students | 4 771 |
| 18 | 📚 Review English Questions from Grade 6, 7 and 8
✅ Part 1
📚For Grade 8 Students | 4 443 |
| 19 | 📚 ርዕስ: ከፈተና በፊትና በኋላ ማድረግ የሚገቡን ነገሮች
ውድ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች፤ የፊታችን ግንቦት 10 እስከ 12/2018 ዓ.ል ለምትወስዱት የሞዴል ፈተና እንዲሁም ለቀጣዩ የሚኒስትሪ ፈተና ስንቅ ይሆን ዘንድ፣ ይህንን አጭር እና ጠቃሚ ምክር በጥንቃቄ አንብቡት።
የፈተና ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ እና ተፈጥሯዊ ነገር ነው። ይህንን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት።
1. ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገቡን ወርቃማ ዘዴዎች
♦️አመለካከትን ማስተካከል፡ ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አለመሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። መሳሳትን አትፍሩ፤ ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጁ መሆን የብልህ ተማሪ መገለጫ ነው።
♦️የጋራ ጥናት፡ ከጓደኞቻችን ወይም ከወላጆቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ ትልቅ ጥቅም አለው። ይህ ዘዴ የማስታወስ ብቃታችንን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያደርጋል።
♦️በቂ እረፍት እና እንቅልፍ፡ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ መተኛት ጭንቀትን ይቀንስልናል፤ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል።
💡የሳይንቲስቶች እይታ፡ "እንቅልፍ የተማርነውን አዲስ እውቀት ወደ ዘላቂ ማህደረ-ትውስታ (Long-term memory) የምናሸጋግርበት ወርቃማ ድልድይ ነው።" ስለዚህ በቂ እንቅልፍ ማግኘት ያጠናነውን እንዳንረሳ ያደርገናል።
2. በፈተና ወቅት መከተል ያለብን ጥበቦች
♦️ቅድመ ዝግጅት፡ ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት አለብን።
♦️ድንገተኛ ጭንቀትን ማሸነፍ፡ በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይኖርብናል። ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ወሳኝ ነው።
📖 ነቢዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) ከባድ ሀላፊነት ሲገጥማቸው አላህን እንዲህ ብለው ተማጸኑ፦ ❝ጌታዬ ሆይ! ልቤን አስፋልኝ፤ ነገሬንም ለእኔ አግራልኝ።❞ (ሱረቱ ጣሀ፡ 25-26)። እናንተም በፈተና ወንበር ላይ ስትቀመጡ ይህንን በማሰብ አላህ ነገራችሁን እንዲያገራላችሁ ጠይቁ።
♦️ራስን ማረጋጋት፡ "እኔ የምችለውን አድርጌያለሁ (ሰበብ አድርሼያለሁ)፣ የቀረውን ለአላህ ሰጥቼዋለሁ!" በማለት የማረጋጊያ ቃላትን ለራሳችሁ ንገሩ።
♦️የጥያቄ አያያዝ ስልት፡ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግምት መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይገባናል። በተደጋጋሚ ሰአት በቃን አልበቃን እያልን መጨነቅ የለብንም።
🔴 መሰረዝና መደለዝን መቀነስ፡ ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ሌላ መልስ እንድንሰጥ ስለሚያረግ፣ በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ አለብን።
3. ከፈተና በኋላ...
አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት መገመት አይገባንም።
ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን፣ ከዚህ ይልቅ እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ይመከራል። አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን አለብን።
⭐💫 ማጠቃለያ
ሁሌም ልናስታውሰው የሚገባን ትልቁ እውነት፡- ፈተና ማለት ለጀነት ማለፊያ ትኬት እንዳልሆነ እርግጠኛ መሆን ነው። ሁሉም ነገር አላህ ከወሰነው ውጭ እንደማይሆን ማመን አለብን። ከኛ የሚጠበቀው የአቅማችንን ያህል ማድረግ፣ ሌላውን ለአላህ መተው ነው። አላህ በናንተው ጥረት ብቻ ሳይሆን በሱ እዝነት መልካም የሆነ ውጤትን ይሰጣችኋል።
🤲 ዱዓ
ያ አላህ! አንተ እውቀትን ሰጪ፣ ልብን ከፋች አምላክ ነህና ለእነዚህ ልጆች ልባቸውን አስፋላቸው። ያጠኑትን ወደ አእምሮአቸው መልስላቸው፤ ያልገባቸውን አብራራላቸው። በፈተና ወቅት የሚመጣን ጭንቀት እና መደናገር አንሳላቸው። በጥረታቸው ብቻ ሳይሆን በአንተ ሰፊ እዝነት፣ ልፋታቸውን አሳምረህ አስደሳች እና ያማረ ውጤት ወፍቃቸው። ያረብ... ቀጣዩን የህይወት ዘመናቸውንም በስኬት፣ በኢማን እና በጥበብ የተሞላ አድርግላቸው! አሚን! 🤲
═══════════════
◆ ጥረት ካለ ስኬት አይርቅም፤ ትጋት ካለ ድል አይታጣም!!
✅ ስኬት ለልጆቻችን፣ ለአበቦች፣ ለአንፀባራቂ ኮከቦች!
✨━━━━━━━━━━━━✨
✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል | 1 698 |
| 20 | بدون متن... | 1 007 |
