fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Sheger Press️️

Sheger Press️️

رفتن به کانال در Telegram

Official channel of sheger press Contact @Birukepromo

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام Sheger Press️️

کانال Sheger Press️️ (@sheger_press) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 36 156 مشترک است و جایگاه 7 101 را در دسته اخبار و رسانه‌ها و رتبه 1 012 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 36 156 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 21 اکتبر, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 897 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر -12 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 17.50% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 13.23% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 6 326 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 4 783 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 25 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
“Official channel of sheger press Contact @Birukepromo”

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 22 اکتبر, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته اخبار و رسانه‌ها تبدیل کرده‌اند.

36 156
مشترکین
-1224 ساعت
-1227 روز
+89730 روز
آرشیو پست ها
የሕወሓት መሪዎች ኤርትራ ይገኛሉ ሲሉ ብ/ጄ ገብረ እግዚአብሔር በየነ ኃይሉ ተናገሩ የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) መሪዎች ኤርትራ ውስጥ ይገኛሉ ሲሉ ከፌዴራል መንግሥት ጋር ተባብሮ የሚሠራው የትግራይ ሰላም ኃይል አዛዥ ተናገሩ ። በትግራይ ክልል ባለ አደራ አስተዳደር፦ የፀጥታና ሰላም ዋና አስፈጻሚ ብ/ጄ ገብረ እግዚአብሔር በየነ ኃይሉ ይህንኑ ለፈረንሣይ ዜና አገልግሎት (AFP) ተናግረዋል ። የኤርትራ የማስታወቂያ ሚንሥትር የማነ ገ/መስቀል የጄኔራሉን አባባል ውድቅ አድርገዋል ። መሪዎቹ ኤርትራ ውስጥ ይገኛሉ ስለመባሉ AFP ወዲያውኑ ማረጋገጫ ኣለማግኘቱን አክሎ ዘግቧል ። ብ/ጄ ገብረ እግዚአብሔር በየነ ኃይሉ ትናንት ማክሰኞ፤ ጥቅምት 10 ቀን፣ 2019 ዓ.ም መቐለ ከተማ ውስጥ ለነዋሪዎች ባሰሙት ንግግር፦ «የሕወሓት መሪዎች ወደ ኤርትራ ድንበር ተሻግረዋል» ማለታቸውን የዜና ምንጩ ጠቅሷል ። አያይዘውም፦ «ከፍተኛ መጠን ያለው የጦር መሣሪያ ቁሳቁስ እና መድኃኒቶችንም» መሪዎቹ መውሰዳቸውን ተናግረዋል ። ከፌዴራል መንግሥት በሚሰጠው አቅጣጫና መመሪያ መሠረት ትግራይ ክልልን ለሚቀጥሉት 6 ወራት እንዲያስተዳድር ከተቋቋመው ባለአደራ አስተዳደር አባላት አንዱ ብ/ጄ ገብረ እግዚአብሔር ያሰሙትን ንግግር ኤርትራም ሕወሓትም አጣጥለዋል ። የሕወሓት ምክትል ሊቀመንበር አማኑኤል አሠፋ፦ የሕወሓት «አመራር ትግራይ ውስጥ እየሠራ ነው» ሲሉ ለዜና ምንጩ ተናግረዋል ።

ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን፤ምልጃው እና ረድኤቱም አይለየን🙏 ድርሳነ ሩፋኤል ላይ ተጽፎ እደምናገኘው 7 ሊቃነ መላዕክት ሲኖሩ አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው፤ የስሙ ትርጓሜም “እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው” ማለት ነው። ከእግዚአብሔር ዙፋን ስር ትዕዛዝ በወጣ ግዜ ኪሩቤል ተቀብለው ለሱራፌል ያስተላልፋሉ፤ ሱራፌልም ለሚካኤልና ለገብርኤል ለሩፋኤልም ያደርሳሉ፡፡ ሚካኤል ለፍጥረቱ በጎም ይሁን ክፉ ትዕዛዙን ይፈጽሙ ዘንድ መላዕክትን ያዛቸዋል፤ ኪሩቤልና ሱራፌል መላዕክቱም ሁሉ አቤቱ የእጅህን ስራ አታጥፋ እያሉ ቀንና ከማታ ይለምናሉ። የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ከዲያቢሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ እግዚአብሔር ይገስፅህ አለው እንጂ የስድብን ቃል አልተናገረውም ሲባል ሰምተናል፡፡ ሊቀ ነብያት ሙሴ እጅግ ታዛዥና የዋህ ስለነበርና ከንዓንን ለማየት ወደ ናባው ተራራ ሲወጣ 2 መላዕክት በአረጋውያን ተመስለው መቃብር ሲቆፍሩ ቢያይ ላግዛቹ ብሎ መቆፈሪያውን ተቀበላቸው፡፡ በመጨረሻ “ሰውየው በአንተ ልክ ነውና እስቲ ገብተህ ለካልን” አሉት፡፡ እሱም በየዋህነቱ ጉድጓዱ ውስጥ ገብቶ እንደተኛ እንደ እንቅልፍ አሸልቦት በዚያው ዐረፈ፤ መላዕክቱም ቀበሩት። እስራኤላዊያን ሙሴን እጅግ ስለሚወዱት የሙሴን መቃብር እንደ ጣዖት እንዳያመልኩት እግዚአብሔር የሙሴን መቃብር ሰወረው፤ ነገር ግን ጠላት ዲያቢሎስ ሊያሳያቸው በመነሳቱ ቅዱስ ሚካኤል ተቃወመው፡፡ በመጨረሻም ቅዱስ ሚካኤል ዲያቢሎስን እግዚአብሔር ይገስጽህ ብሎ ከእርሱም ሰወረበት። በሐዋርያው ይሁዳ መልዕክት ቁጥር 8 የሚገኘው ቃል የቅዱስ ሚካኤልን ትዕግስት ያሳያል፡፡ ዳግመኛም አይሁድ ጌታን ሲሰቅሉት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በቁጣ ሰይፉን አወጣ፤ ቅዱስ ሚካኤል ግን በአይሁድ ስራ አዝኖ ፈጣሪን ፍጡራን ሰቀሉት እያለ በአርምሞና በትዕግስት አያቸው ይላል ድርሳኑ። ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 33÷7 “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል” ይለናል፡፡ በትንቢተ ዳንኤል 10÷13 እና 10÷21 ደግሞ የስሙ ትርጉም እግዚአብሔር ዳኛዬ ነው የተባለው ነብዩ ቅዱስ ዳንኤልም ስለ ቅቅዱስ ሚካኤል እንዲህ ሲናገር ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፣ በተዘጋ ጉድጓድ ሲያጽናናው ደግሞ “ከሚካኤል በቀር የሚያጽናናኝ የለም” አለ፡፡ በዓለም ፍፃሜም ስለህዝቡ የሚቆመው ሚካኤል ይነሳል። በማለትረ በምዕራፍ 12÷1 ጽፎልናል፡፡ በራዕይ 8÷3 “የቅዱሳኑ ፀሎት ከዕጣኑ ጢስ ጋር ከመልአኩ እጅ ወደ እግዚአብሔር ፊት ወጣ” ተብሎ እንደተጻፈውም መላዕክት የቅዱሳኑን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ያሳርጋሉ፡፡ ገዳማውያን የሚያደርጉት ጸሎትና የሚያቀርቡት መስዋዕት በእርሱ ምልጃ ያርጋልና ገዳማቸውን እየረዳን በዓታቸውን እያጠናን የበረከታቸው ተካፋይ እንሁን፡፡ ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

photo content

መሳሪያው የሚመጣው ከግብፅ ነው-ጄኔራል ገብረ አድሃና‼️ የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ሜጀር ጀኔራል ገብረ አድሃና የህወሓትን የጦርነት መንገድ በመቃወም ወደ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል። ሜ/ጄኔራል ገበረ አድሃና ከ ኤንቢሲ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ንግግር ህወሃት የታጠቃቸው መሳሪያዎች መነሻቸው ግብጽ መሆኑን ተናግረዋል። መሳሪያዎቹ የሚገቡት ከግብፅ በቀጥታ የገቡ አሉ፣እንደገና ከግብፅ በኤርትራ እና በሱዳን በኩልም የገቡ አሉ ብለዋል። ህወሓት እነዚህን መሳሪያዎች ተርክቦ ድሮን ጭምር ለሌሎች ታጣቂዎች ሲያከፋፍል እንደነበር አውቃለሁ ብለዋል።

የአቡነ ሀብተ ማርያም ምልጃ እና ረድኤት አይለየን🙏 በምጽዋትና በስገድት የምትጋደለው እናቱ ዮስቴና ሀብቷን ሁሉ ለድሆች ሰጥታ ለምናኔ ወደ በረኃ ሄደች። በዚያ ያገኘችው ባሕታዊም በመንፈስ ቅዱስ ተገልጦለት ከእርሷ ቅዱስ ፍሬ እንደሚወጣ ነግሮ ወደ ዓለም እንድትመለስ አዘዛት። እርሷም “እግዚአብሔር የወደደው ይሁን” ብላ እያመሰገነች ተመልሰች፡፡ የአባቱ የትውልድ ሀገር የራውዕይ በምትባል ሀገር ሲሆን ከዚህች የተባረከች ሴት ጋር ተጋባ። እርሷም በበጎ ምግባርና ሥራ የተጌጠች፣ በሕግ ተወስና በጾም፣ በጸሎት፣ የምትተጋ ነበረች። ከጥቂት ጊዜያት በኋላም ወንድ ልጅ ወለደች። እንደ ሥርዓቱም ሲጠመቅ የመጽሐፍ ስሙን “ሀብተ ማርያም” አሉት። በሕገ እግዚአብሔር አንጸው አሳደጉት። ወደ ቤተ ክርስቲያንም ሲወስዱት “እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ” የሚለውን ጸሎት ቢሰማ እጅጉን ወደዳት። እርሷንም ይዞ ከቤቱ ሌሊቱን የሚጸልይና የሚጋደል ሆነ።    አንድ ቀን የአባቱ በጎቹን ሲጠብቅ የበግ ጠባቂዎቹን “ዛሬ ዝናም ይዘንማልና እንግባ” አላቸው። እነርሱም “ምን ደመና አለ፤ ቀኑ ብራ ነው” አሉት። እርሱ ግን በጎቹን ይዞ ወደ ቤቱ እንደገባ ኃይለኛ፣ ነፋስና መብረቅ የቀላቀለ ዝናም ዘነመ። በሌላም ጊዜ እንዲሁ አንድ እረኛ የሀብተ ማርያምን በትሩን በጉልበት ነጠቀው። “መልስልኝ” ብሎ በስመ እግዚአብሔር ቢያምለውም እምቢ አለው። በተወው ጊዜ እግዚአብሔር ያን እረኛ በአየር ላይ ሠቅሎ አዋለው። እረኞቹም ሀብተ ማርያምን ሲለምኑት፣ እግዚአብሔር ነውና ስለ ስሙ ብሎ የቀጣው መሐሪው እርሱ ከወደደ ይማረው ሲል ያ እረኛ ተፈታና ወረደ። መጥቶም ከአባታችን እግር ስር ወደቀ፡፡ በኋላም ስሟ እለ አድባር ወደምትባል ገዳም ገብቶ ከአባ መልከ ጼዴቅ እጅ መነኰሶ ታላቅ ተጋድሎ ይጋደል ጀመር። በባሕር መካከልም በመቆም መዝሙረ ዳዊትን ይደግምና ግንባሩም የባሕሩን አሸዋ እስኪነካ 500 ጊዜ ይሰግዳል። እህልም መቅመስን ትቶ የዱር ቅጠል የሚመገብ ሆነ። ዐርባ ዐርባ፣ ሰማንያ ሰማንያ ቀንም ያከፍላል። በሌሊትም ቁሞ በማደር በቀንም አራቱን ወንጌላት ዘወትር ይጸልያል። ተጋድሎውንም ያየ አምላካችን ተገለጠለት። አባ ሀብተ ማርያምም ከግርማው የተነሣ ደንግጦ በግንባሩ ተደፋ። ጌታችንም እፍ ብሉ አጽናንቶ አሥነሳውና ጽኑዕ ተጋድሎው በሰማያት መጻፉን ነገረው፡፡ ስለ ድንግልናው፣ ስለ ምናኔው፣ ስለ ፍጹም ምንኲስናው፣ አራቱን ወንጌላት አዘውትሮ በማንበቡ፣ ረኃብና ጥምን በመታገሡ፣ በልቡ ቂምንና በቀልን ባለማኖሩ፣ ስለ ንጹሕ የክህነት አገልግሎቱና በንጽሕና ስለሚያሣርገው መሥዋዕቱ ሰባት እጅግ የሚያስደንቁ አክሊላትንም አቀዳጀው። የቅዱስ ማቴዎስንና የቅዱስ ማርቆስን ወንጌል ሲያነብ ከሌሎች ሥውራን አበው ጋር የሚገናኝበትን የብርሃን ሠረገላ ሰጠው፡፡ የቅዱስ ሉቃስንና የቅዱስ ዮሐንስን ወንጌል ሲያነብም ሥጋውን ደሙን ለመቀበል ወደ ኢየሩሳሌም የሚሄድበትን የእሳት ሠረገላ ሰጠውና ቃል ኪዳን ገባለት። መታሰቢያውን ለሚያደርጉና በስሙ ለሚዘክሩ፣ ከእነርሱ ጋር የሚኖርበትን አምስት መቶ የወርቅ አምዶች ያሏትን ቦታ ሰጠሁህ አለው። ቅዱሳን መላእክት ሁሉ እየተደሰቱ አባታችን አቡነ ሐብተ ማርያምን “ወንድማችን ወደማያልቀው ሰማያዊ ደስታ ልንወስድህ መጥተናል” አሉት። ይህንንም በተናገረ ጊዜ ጌታችን በሦስትነቱ ተገልጦ ታየው። በኅዳር 26 ቀን ነፍሱ ከሥጋው በሰላም ተለየች። ቅዱሳን መላእክትም በታላቅ ደስታ እያመሰገኑ አሣረጓት። ገዳማውያን የዓለምን ክብር ንቀው ሔደዋልና ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፡፡ በዓታቸውን እናጽና ገዳማቸውን እንደግፍ የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡      ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

photo content

ጥቅምት 10 2019 በአዲስ አበባ ጥሬ ስጋ በኪሎ እስከ 6 ሺህ ብር የሚሸጥባቸው ቦታዎች አሉ፡፡ ይህን ተከትሎም ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚድያ ጭምር መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ የከተማዋ ንግድ ቢሮም በጉዳዩ ላይ ከልኳንዳ ነጋዴዎች ማህበር ጋር ሊነጋገር ቀጠሮ መያዙ ተሰምቷል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ሸማቾችን፣ የልኳንዳ ነጋዴዎች ማህበርን፣ የሸማቾች ፣ መብት ተቆርቋሪ ድርጅትን ሃሳብ ጠይቀናል፡፡ የስጋ ተወደደብን ድምፆች ደጋግመን ሰምተናቸዋል፤ ይሁንና ስጋ በገበያው ላይ ያለው ዋጋ ከመቀነስ ይልቅ እየጨመረ መጥቶ በከተማችን አዲስ አበባ በሸማች ህብረት ስራ ምህበራት 1200 ብር በየልኳንዳ ቤቶቹ ደግሞ ከዝቅተኛው 1 ሺህ 800 ብር እስከ 6 ሺህ እየተሸጠ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሰሞኑን ባወጣው የመስከረም ወር 2019 ዓ.ም የዋጋ ግሽበት 14.9 መድረሱን ይፋ ባደረገበት መረጃው የስጋ ዋጋ ግሽበት 22 በመቶ መድረሱን ተናግሯል፡፡ ሃሳባቸውን የሰጡን ሸማቾች እንደሚያነሱት እንደ አብዛኞቹ ሸቀጦች በስጋ ላይ እየተደረገ ያለው የዋጋ ጭማሪ ምክንያታዊ አይደለም፡፡ በየልኳንዳ ቤቶቹ የሚጠራው ዋጋ መካከል በኪሎ እስከ 4 ሺህ ብር የሚደርስ የዋጋ ልዩነት ያለው መሆኑ በመንግስት ምን ያህል ቁጥጥር እንደማይደረግበት የሚያሳይ ነው መንግስት ጣልቃ መግባት አለበት ባይ ናቸው ሸማቾቹ፡፡ ስለ ጉዳዩ ሃሳቡን የጠየቅነው የሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት በበኩሉ ባለፉት ዓመታት ስሰራ የቆየሁት ሸማቹ ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ ሲደረግበት በአግባቡ ጥያቄ እንዲያነሳ፤ ምርቱን ለተወሰነ ጊዜ አለመጠቀምን ጨምሮ ነጋዴው እና መንግስትንም ላይ ጫና በማሳደር መፍትሄ እንዲመጣ እንዲያደርግ ነበር፡፡ አሁን በስጋ ላይ እየተነሳ ያለው ጥያቄ ሸማቹ የባህሪ ለውጥ ማምጣቱን የሚያሳይ ነው ብሏል፡፡ መንግስት ንግዱን ነፃ ገበያ በሚል እንዲሁ ከመተው ይልቅ በአንድ ምርት ላይ እስከ 4 ሺህ ብር የደረሰ የዋጋ ልዩነት ሲፈጠር ምን ተፈጥሮ ነው? ብሎ ወረድ ብሎ በማየት የማስተካከል ሃላፊነት አለበት ያሉን የኢትዮጵያ የሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ቁምላቸው አበበ ናቸው፡፡ ቅሬታው የተነሳባቸውን የልኳንዳ ነጋዴዎች በአባልነት የያዘው የአዲስ አበባ የልኳንዳ ነጋዴዎች ማህበር የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ጥቂት ልኳንዳ ቤቶች አሉ፤ ይህ አግባብ አይደለም ብሎናል፡፡ የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ አየለ ሳህሌ በሰጡን ምላሽ ጉዳዩ መነሳቱ እንድንነጋገር በር ይከፍታል፤ እንደ ማህበር እነዚህን ነጋዴዎች መቆጣጠር አንችልም ይህ የመንግስት ስራ ነው ብለውናል፡፡ ችግር ያለባቸው ነጋዴዎችን መቆጣጠሩ የምንደግፈው ሆኖ ሳለ ህብረተሰቡ ሊያውቅልን ይገባል ያሉትን የእንሰሳቱ ዋጋ መወደድ፣ የሚጣልባቸውን ተደራራቢ ግብር፣ የቤት ኪራይና የሰራተኛ ወጪ ከፍተኛ መሆኑ ከግምት ውስጥ ይግባልን ይላሉ። ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ አሳይቷል በሚል ከማህበረሰቡ ቅሬታ ስለተነሳበት የጥሬ ስጋ ጉዳይ ለመነጋገር የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከልኳንዳ ነጋዴዎች ማህበር ጋር ቀጠሮ መያዙን ማህበሩ ነግሮናል፡፡ ውይይቱ በሁሉም ወገን ያሉ ችግሮች ተነስተው አሁን ላለው የስጋ ዋጋ መናር መፍትሄ ይዞ ይመጣል የሚል እምነት እንዳላቸው የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ አየለ ሳህሌ ነግረውናል፡፡

እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ነገር ሁሉ ትከልለን፤ ምልጃዋ እና ረድኤቷም አይለየን🙏 ቤተክርስቲያናችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን ሁሉ በላይ በማለት ክብሯን ትገልጻለች። ኦርቶዶክሳዊያን ከሕጻንነታችን ጀምረን የእመቤታችንን ምስጋና እንማራለን፣ ሁልጊዜም በአባታችን ሆይ ጸሎት ጀምረን በመልኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን ብለን ድንግል ማርያምን እናመሰግናታለን። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቅዱሳን ሁሉ የምትመሰገን ናት። እርሷ ያላትን ክብር እንዴት እንደሚገልጹት ተጨንቀው በምን በምን እንመስልሻለን በማለት በሰው ህሊና የሚለካ ምሳሌ ማጣታቸውን ብዙ ቅዱሳን ተናግረዋል። የብህንሳው ኤጲስ ቆጶስ አባ ሕርያቆስ፣ ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬምና ኢትዮጵያዊው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ክብሯን ገናንነቷን በስፋት ተናግረዋል፣ አመስግነዋታል፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ናት። ጌታችን አምላካችን ኢየሱ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሳ፤ በእርሷም የመለኮትና የስጋ ፍጹም ተዋህዶ ተፈጸመ፡፡ የማይወሰነውን አምላክ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኗ ወሰነችው፡፡ ከዓለም በፊት ከአብ ያለእናት እንደተወለደ፣ ከእርሷ ደግሞ ድህረ ዓለም ያለ አባት ተወለደ፡፡ አምላክ እኛን ለማዳን ሰው ሆነ፣ ሰው አምላክ ሆነ ስንል በተዋህዶ ነውና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አማላክ ትባላለች፡፡ እመቤታችን በሀሳብም በሥጋም ዘላለማዊት ድንግል ናት። በሀሳቧ በህሊናዋ ከአምላክ ህግና ሀሳብ በስተቀር ስጋዊ ሀሳብ ፈጽሞ ኖሮ አይውቅምና ከሰው ወገን ተለይታ የህሊና ድንግልና አላት፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ከሴቶች ሁሉ ተለይታ የተባረከች መሆኗን በመመስከር ይህን የህሊና ድንግልና ያስረዳናል። መልአኩም ልጅ ትወልጃለሽ ብሎ ሲያበስራት “ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል” ብላ መናገሯ “ስለ ወንድ ፈጽሞ አስቤ አላውቅም” ማለቷ ነውና የህሊና ወይም የሀሳብ ድንግልናዋን ያስረዳናል። ከመፅነሷ በፊት፤ በፀነሰች ጊዜ፤ ከፀነሰች በኋላ፤ ከመውለዷ በፊት፤ በወለደችም ጊዜ፤ ከወለደች በኋላ ድንግል ናት፡፡ ገዳማውያን ይህን ክብሯንና አማላጅነቷን አምነው ዘወትር አማልጂን ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡  ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

photo content

"ኢንጂነር ታከለ ኡማ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ" የሚለው መረጃ ሀሰተኛ ነዉ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ የሚለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑ ተገ
"ኢንጂነር ታከለ ኡማ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ" የሚለው መረጃ ሀሰተኛ ነዉ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ የሚለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑ ተገለጸ። ​የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ኢንጂነር ታከለ ኡማ ኢትዮ ቴሌኮምን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት እንዲመሩ ተሹመዋል በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ የቆየው መረጃ ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀና ሀሰተኛ መሆኑን ኩባንያው ለካፒታል ጋዜጣ አስታወቀ። ​በአሁኑ ወቅት ኩባንያውን በተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚነት (Acting CEO) እየመሩ የሚገኙት በኢትዮ ቴሌኮም የዳይሬክተሮች ቦርድ ኃላፊነት የተሰጣቸው አቶ ታሪኩ ደምሴ መሆናቸው ተረጋግጧል። Via ካፒታል

ህወሃት ላይመለስ ሄዷል-ጄ/ል ታደሰ ወረደ‼️ የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በወቅታዊ የትግራይና የሀገሪቱ የፖለቲካ እና የደህንነት ሁኔታዎች ላይ ከአውራ አምባ ታይምስ ጋር ቆይታ አድርገዋል። ​የእገታው ሂደት እና የተፈጠረው ውዝግብ ​ጀነራል ታደሰ ወረደ በቃለ መጠይቁ ወቅት በቅርቡ ስለገጠማቸው እገታ ሂደት ዝርዝር መረጃ ሰጥተዋል፦ ​የእገታው አጀማመር፦ ሌሊት በቁጥጥር ስር ለማዋል የተደረገው ሙከራ ተገቢ እንዳልነበር እና በፖሊስ ሽፋን የመጡ አካላት እንደነበሩ ገልጸዋል። ​የተወሰደው እርምጃና ዝውውር፦ ከቤት ከተወሰዱ በኋላ በኤች ዜድ (HZ) ሆቴል እንዲቆዩ መደረጉን፣ በመቀጠልም በአክሱም፣ አድዋ እና ራማ አቅጣጫዎች እንቅስቃሴዎች እንደነበሩ ተናግረዋል። ​የውሳኔው አካላት፦ ውሳኔውን ያሳለፉትና ያስፈጸሙት ይፋዊ የነበረው መንግስታዊ መዋቅር ሳይሆን፣ በፖለቲካ እና በሚሊተሪ ስብስብ የተዋቀረ “የአቋቋምት ኮሚቴ” እና ራዲካል አካላት እንደሆኑ ጠቁመዋል። ​ከመከላከያ ሰራዊት ጋር የተደረገ ግንኙነት፦ ከራማ ከተማ በመውጣት ከአድበራና ከአሮህ መካከል ከአገኘው የመከላከያ ሰራዊት አባላትና አመራሮች ጋር በሰላም መገናኘታቸውን አብራርተዋል። ​በእሳቸው ላይ ለሚነሱ ወቀሳዎችና ዘመቻዎች የተሰጠ ምላሽ ​በተለያዩ ማህበራዊና መደበኛ ሚዲያዎች በጀነራል ታደሰ ወረደ ላይ ለሚሰነዘሩ ቅሬታዎችና ጥርጣሬዎች የተሰጡ ምላሾች፦ ​የህወሓት ሃይል በማደራጀትና ደንብ በማውጣት ሂደት፦ በወቅቱ የተሰሩ ስራዎች በሙሉ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ እና ከካቢኔው አሰራር ጋር የተያያዙ እንደነበሩ ገልጸዋል። ​የአቋም ልዩነቶችና ተቃውሞዎች፦ በየደረጃው በነበሩ ውሳኔዎች ላይ የነበራቸው ተቃውሞና ልዩነት በሰነድና በሪኮርድ የተያዘ መሆኑን አብራርተዋል። ​የጦር መሳሪያዎች ምዝገባና አመጣጥ፦ በስልጣን ዘመናቸው የተከናወኑ የደህንነት ስራዎች ግልጽ እንደነበሩና ከእሳቸው እውቅና ውጪ በድብቅ የተሰሩ ነገሮች ካሉ ማጣራት እንደሚቻል ገልጸዋል። ​ስለ ህወሓት የወደፊት እጣ ፈንታ እና የሽግግር ወቅት ​ጀነራል ታደሰ ወረደ ስለ ድርጅቱ ህልውና እና ስላለው የፖለቲካ ሁኔታ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፦ ​የህወሓት የፖለቲካ ማብቂያ፦ ህወሓት በአሁኑ ወቅት የፖለቲካ ማብቂያው ላይ እንደሚገኝና ድርጅቱን በሰላም ማሳረፍ እንደሚገባ ገልጸዋል። ​ለድርጅት ህልውና የሚከፈል መስዋዕትነት ማብቃት አለበት፦ “ህወሓት ከሌለ ትግራይ የለችም” የሚለው አስተሳሰብ የተሳሳተ መሆኑንና ድርጅቱ ሳይኖርም ትግራይ እንደምትቀጥል አስረድተዋል። "ሰራዊቱም ከሞተ ጋር መሞት የለበትም የTPLF አመራሮች አንድ የተሳካላቸው ነገር ቢኖር፣ ድርጅቱን ወደ መቃብር አውርደውታል፣ላይመለስ ሄዷል" ብለዋል። ​የወጣቱ እና የአዲሱ ትውልድ ድርሻ፦ አመራሩ ከወጣቱ ትውልድ ጋር መቆራረጡን ጠቅሰው፣ የትግራይ ህዝብና አዲሱ ትውልድ የራሱን እድልና ህልም መቅረፅ እንዳለበት አሳስበዋል። ​የሰላም አስፈላጊነት፦ ህዝቡ ተጨማሪ ጦርነትና ውድመት መሸከም የማይችል በመሆኑ ትኩረቱ በፖለቲካዊና በሰላማዊ መፍትሔዎች ላይ መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።

photo content

ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ፣ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ ነበረ 🙏 ነቢዩ ዳንኤል የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤልን አስፈሪ ግርማ በተመለከተ ጊዜ “ዐይኖቼንም አነሣሁ እነሆም በፍታ የለበሰውን፣ ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡ አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡ ይህንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኀይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ ውርደት ተለወጠብኝ ኀይልም አጣሁ፡፡ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምድር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ” አለ፡፡ በዳንኤል 10÷5-9 የተገለጸው የዚህ መልአክ ግርማ የአምላክን ግርማ ይመስላል፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣንም ከእሳት ያወጣ እርሱ ነው፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ “አምላክ ወሰብእ” ሰውና አምላክ ማለት ሲሆን ከዋነኞቹ የመላዕክት አለቆች አንዱ ነው፡፡ አምላካቸው ክርስቶስን አንክድም በማለታቸው የፈላ ውሃ በተሞላውና ወላፈኑ በማያስቀርበው ጋን ውስጥ የተወረወሩት ቅዱስ ቂርቆስና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ አዳናቸው። ቅድስት ኢየሉጣ ልጇ እንዳይገደል ለራሷም ከሚፍለቀለቀው ውሃ ድምፅ የተነሣ ለጊዜው ሥጋዊ ፍርሀት ቢያድርባትም የሦስት ዓመት ልጇ እናቴ ከእቶን እሳቱ የተነሳ አትፍሪ ሶስቱን ሕጻናት ያደነው ያድነናል እያለ በቀሚሷ ጎተታት፤ ወደ ጌታችን ሲጸልይላት ፍርሃቱ ርቆላታል፡፡ መልአከ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤልም ከሰማይ ወርዶ የሚንተከተከውን ውሃ አቀዝቅዞ አውጥቷቸዋል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ከዐበይት የመላእክት ነገዶች መካከል አንዱ በሆነው አርባብ፣ አጋእዝት ወይም ጌቶች በሚባለው ዐቢይ ነገድ ላይ የተሾመ ሲሆን ከበታቹም የሚመራቸው ዐሥር ነገደ መላእክት አሉ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በቈላስያስ 1÷16 በቅዱሳን መላእክት ዘንድ ስላሉት ነገዶች ሲገልጽ “… በሰማይ ያለውን በምድር ያለውን የሚታየውንምና የማይታየውን መናብርትም ቢሆኑ አጋእዝትም ቢሆኑ መኳንንትም ቢሆኑ ቀደምትም ቢሆኑ ሁሉም በእጁ ሆነ፤ ሁሉም በእርሱ ለእርሱ ተፈጠረ” በማለት ነገደ መላዕክትን ይዘረዝራቸዋል፡፡ ቅዱሳን መላእክት በቅዱስ ሚካኤል ፊት አውራሪነት የሰው ልጆች ጠላት ዲያብሎስን ተዋግተው ድል ከመንሳታቸው አስቀድሞ መላዕክት ማን ፈጠረን ብለው ግራ ሲጋቡ ቅዱስ ገብርኤል ፈጣሪ ነኝ ያለውን ሳጥናኤልን በመቃወም “አይዞአችሁ ፈጣሪያችን ፈጥሮ አይጥለንምና አስክናገኘው፣ እስክናውቀው ድረስ በያለንበት ጸንተን እንቁም፡፡” በማለት አረጋግቷቸዋል፡፡ በኢሳይያስ 14÷16ም በሰማያት የሳጥናኤል ትዕቢትና ውድቀት ምን እንደሚመስል ተጽፏል፡፡ “አንተ በንጋት የሚወጣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! ወደ አሕዛብ መልእክትን የላክ አንተ ሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀጠቀጥህ! አንተም በልብህ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደረጋለሁ፤ በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፡፡ ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወድቃለህ፤ ወደ ምድር ጥልቅም ትወርዳለህ” ይለናል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል በቅድስና ሕይወት ለተጋውና በገዢዎች ዘንድ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ያደረበት ሰው ተብሎ ለተመሰገነው ለነቢዩ ዳንኤል ማስተዋልንና ጥበብን የሰጠ፣ እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጆችን ከሰይጣንና ከሞት ባርነት ነጻ ሊያወጣቸው ሰው እንደሚሆንና ሰማይንና ምድርን አሳልፎ በቅዱሳን ላይ ነግሦ እንደሚኖር በምሳሌ ገልጾ ያስተማረው መልአክ ነው፡፡ ዛሬም ዓለምን ትተው የመነኑ ገዳማውያ አማላጅነቱንና ፈጣን ተራዳኢነቱን አምነው ሲጠሩት ይራዳቸዋል፡፡ እኛም ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጸና ከበረከታቸው እንሳተፍ፡፡ ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

photo content

ዜና ዕደጋ ዕሮብ በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ህወሃት ደብቋቸው የነበሩ ተተኳሾችና ሌሎች ወታደራዊ ትጥቆች ሠራዊቱ በሚያደርገው የተጠናከረ ፍተሻና በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር የማዋሉ ሥራ ቀጥሏል። ኢኮኖሚን ለልማት ከማዋል ይልቅ በጦር መሣሪያ ሸመታ ተጠምዶ የቆየው ህወሃት በየቦታው አከማችቶት የነበረና በቁጥጥር ስር እየዋለ ያለው ተተኳሽና መሣሪያ ብዛት ቡድኑ ጦርነት ናፋቂ መሆኑን ያሳያል። በትላንትናው ዕለትም በማዕከላዊ ትግራይ ዞን ዕዳጋ ዕሮብ አካባቢ ቻይና ስሪት HYTERA ወታደራዊ መገናኛ ራዲዮ ብዛት 31፣ የራዲዮ ባትሪ ብዛት 122 እንዲሁም በምስራቃዊ ዞን ነበለት ወረዳ የሚሳይል ጥይቶቹ HE 37-55 ፀረ ራዳርና ፀረ -ታንክ ብዛት 45 የRPG ጥይት ብዛት 08 የ76 ሚሊ ሜትር መድፍ ተተኳሽ ብዛት 44 በቀጠናው በሚገኘው ሠራዊት ክትትልና በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ሥር ውሏል። የትግራይ ህዝብ ላዩ ላይ ተጨኖት የነበረው ግጭት ጠማቂው ህወሃት መወገዱን በመደገፍ ለመከላከያ ሠራዊቱ አሥፈላጊውን መረጃ እየሠጠ ይገኛል።

ቅዱስ ሚካኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ!!! በጾርዓ ከተማ የሚኖር፣ ከዳን ወገን የሆነና ሚስቱም መካን የነበረች ማኑሄ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የእግዚአብሔር መልአክም ለሴቲቱ ተገልጦ “እነሆ ትጸንሻለሽ፤ አሁንም ተጠንቀቂ፤ የወይን ጠጅን የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል” አላት። ሴቲቱም ለባልዋ የሆነውን ሁሉ ነገረችው፡፡ ማኑሄም የተላከው ሰው ዳግመኛ ወደኛ ይምጣ፤ ብሎ ወደ እግዚአብሔር ለመነ። እግዚአብሔርም የማኑሄን ድምፅ ሰማ፤ መልአኩም ሴቲቱ በእርሻ ውስጥ ተቀምጣ ሳለች እንደገና ተገለጠላት፤ ማኑሄ ግን አልነበረም። ሴቲቱም ፈጥና ሮጠች፤ ባልዋንም ጠራችው። ማኑሄም “ከዚህች ሴት ጋር የተነጋገርህ አንተ ነህን? ቃልህ በደረሰ ጊዜ የልጁ ሥርዓት ምንድን ነው? አለው። መልአኩም ማኑሄን “ሴቲቱ ከነገርኋት ሁሉ ትጠንቀቅ፣ በማለት ለሴቲቱ የነገራትን ደገመለት፡፡ ማኑሔም “የፍየል ጠቦት እስክናዘጋጅልህ ድረስ፤ እባክህ ቆይ” አለው። መልአኩም የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ማዘጋጀት ብትወድድ ለእግዚአብሔር አቅርበው” አለው። ማኑሄም “ነገርህ በደረሰ ጊዜ እንድናከብርህ ስምህ ማን ነው?” አለው፡፡ መልአኩ “ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ?” ብሎ መለሰለት። ማኑሄም የፍየሉን ጠቦትና የእህሉን ቍርባን ወስዶ በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበው። መልአኩም በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ማኑሄና ሚስቱም በግምባራቸው በምድር ተደፉ። ማኑሄም የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አወቀ። ሶምሶን ከተወለደ በኋላም የእግዚአብሔርም መንፈስ በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ሊያነቃቃው ጀመረ። ይህ ሶምሶንና ወላጆቹን የረዳው ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ታላቁ አለቃ ቅዱስ  ሚካኤል ዛሬም ገዳማውያንን በተጋድሏቸው ሁሉ እየተራዳ አብሯቸው ይኖራል፡፡ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ዓለምን ትተው ወጥተዋልና ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡ ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

photo content

በህክምና ታሪክ የመጀመሪያው የመነጋገሪያ ክስተት፦ በአይን ምህዋር ውስጥ የበቀለው ያልተጠበቀ ጥርስ በህክምናው ዓለም እጅግ ያልተለመደ እና አጃኢብ የሚያስብል አጋጣሚ በህንድ አራቪንድ የአይን ህክምና ሆስፒታል የተመዘገበ ሲሆን፣ የ16 ዓመት ታዳጊ በአይኑ አካባቢ ባጋጠመው እብጠት ምክንያት ወደ ህክምና ተቋም ካመራ በኋላ በምርመራ የተገኘው ውጤት መላውን የህክምና ባለሙያዎች አስገርሟል። ታዳጊው በግራ አይኑ የዐይን ሽፋሽፍት አካባቢ ምንም አይነት ህመም የሌለው እብጠት ተስተውሎበት ወደ ሆስፒታል ያመራ ሲሆን፣ ከአንድ ወር ገደማ በኋላ በዐይን ሽፋሽፍቱ እና በቅንድቡ መካከል ሁለት አነስተኛ፣ ጠንካራ እና ነጭ የሆኑ አካላት ብቅ ብለዋል። ጉዳዩ ያሰጋቸው የህክምና ባለሙያዎች የተከሰተው ነገር ጥርስ ይሁን ወይም አልፎ አልፎ የሚከሰት እጢ ለመለየት የሲቲ ስካን ምርመራ አድርገዋል። በምርመራው ውጤትም በቆዳው ስር የታዩት ሁለት ነጫጭ ጫፎች በግራ አይኑ የላይኛው ምህዋር ውስጥ ሙሉ በሙሉ አድጎ ከተገኘ አንድ ጥርስ የተገኙ መሆናቸው ተረጋግጧል። የጥርስ ስርም የአይኑን ምህዋር ከከበበው አጥንት ጋር ተጣብቆ ተገኝቷል። ሐኪሞች ባደረጉት ስኬታማ ቀዶ ህክምና ጥርሱን ከአይኑ ምህዋር ውስጥ ሙሉ በሙሉ ያወጡት ሲሆን፣ ከተወገደ በኋላ በተደረገ ምርመራ ጥርሱ ከምንም አይነት እጢ ጋር የተያያዘ አለመሆኑ ተረጋግጧል። ይህ ህክምናዊ ክስተት ኤክቶፒክ ቱዝ በመባል የሚታወቅ ሲሆን፣ ይህም ጥርስ ከአፍ ውጭ ባሉ የሰውነት ክፍሎች ላይ የሚበቅልበት እጅግ አልፎ አልፎ የሚከሰት ሁኔታ ነው። በጥናት እና በህክምና ታሪክ ጥርስ በአይን ምህዋር የላይኛው ክፍል ሲበቅል የመጀመሪያው ተመዝጋቢ አጋጣሚ በመሆኑ በዘርፉ ትልቅ ትኩረት ስቧል።

የእናታችን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ምልጃ እና ረድኤት አይለየን🙏 የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳኗ ዘወትር ይታሰባል  ኪዳን የሚለው ቃል ተካየደ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ተማማለ፣ ተስማማ፣ ውል ገባ ማለት ነው፡፡ ኪዳነ ምሕረት ማለትም ደግሞ የምሕረት ቃል ኪዳን ማለት ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ስለሰው ልጆች ይቅርታ የገባላት ኪዳን ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት፣ ለሚያከብሩት፣ ለሚወዱትና ለሚወዳቸው ሁሉ በተለያዩ ጊዜያት ብዙ ኪዳናትን ሰጥቷል፡፡ የኪዳነ ምሕረት ሥዕል በመባል የሚታወቀው ሥዕል በቤተ ክርሰቲያናችን በስፋት ከሚሳሉት የወላዲተ አምላክ ሥዕል ጭብጦች ውስጥ አንዱ ሲሆን። ከጌታችን ኢየሱስ ቃልኪዳን ስትቀበል በጎሎጎታ የሚያሳየው ሥዕል ትክክለኛው ገላጭ ሥዕል ሲሆን፤ ይህ ሥዕል እንደ ቤተ ክርስቲያኑ ስፋት የሚጨመረው ጭብጥ ሊለያይ ይችላል፡፡  ለምሳሌ በዚህ ሥዕል ዘይቤ ላይ የሚታዩት መላእክት ቁጥራቸው ሊበዛ አሊያም ሊያንስ ይችላል፡፡ በዚህ ሥዕል እመቤታችንና ጌታችን ቆመው አሊያም ተቀምጠው ጌታችን በቅዱሳን እጆቹ የእናቱን ቅዱሳን እጆች በመያዝ ቃል ኪዳን ሲገባላት አሊያም በቅዱሳት እጁ ቃል ሲገባላት የሚያሳይ ዓይነት ሥዕል ነው፡፡ በዚህ መልኩ እመቤታችን ከተሳለችባቸው አብያተክርስቲያናት መካከል ጎርጎራ ደብረ ሲና (17ኛው መ.ክ.ዘ)፣ አብርሐወ አጽብሐ (19ኛው መ.ክ.ዘ)፣ መቐለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (20ኛው መ.ክ.ዘ)፤ ከጥንታውያን ብራና መጻሕፍት ከተመለከትን በአክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን ግምጃ ቤት የሚገኘው የ17ኛው መ.ክ.ዘ ተአምረ ማርያም ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ገዳማውያንም ዘወትር በሥዕሏ ፊት ቆመው ይለምኗታል፡፡ እርሷም ልመናና ጸሎታቸውን ታሳርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና፣ ከበረከታቸውመ እንካፈል፡፡  ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል  ማርያም የተሰጠው ኪዳን፣ ቀድመው ለነበሩ ኪዳናት ማለትም ኪዳነ አዳም፣ ኪዳነ ኖህ፣ ኪዳነ መልከ ጸዴቅ፣ ኪዳነ አብርሃም፣ ኪዳነ ሙሴና ኪዳነ ዳዊት መደምደሚያ ነው፡፡ ዘለዓለማዊ ስለ ሆነው የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳን እየታሰበም ዕለቱ በመዝሙር፣ በማኅሌትና በቅዳሴ ይከበራል፡፡ በክርስቶስ ክርስቲያን ለምንባል ለእኛ ለሐዲስ ኪዳን የቤተ ክርስቲያን ልጆችም ይህ አዲስ ውል የተደረገልን ለነፍሳችን ድኅነት በመሆኑ በስሟ እየተማጸንን እንዲሁም መታሰቢያዋን እያደረግን ለተራቡት ማብላት፣ ለተጠሙት ማጠጣትና የተቸገሩትን መርዳት ይገባናል፡፡ ገዳማውያን በበቃል ኪዳኗ ታምነው፣ ዘወትር በሥዕሏ ፊት በጸሎት ይተጋሉ፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና ከበረከታቸው እንካፈል፡፡ ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

photo content