fa
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

رفتن به کانال در Telegram

EEP Communication

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام EEP Communication

کانال EEP Communication (@eepcommuication) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 15 533 مشترک است و جایگاه 8 338 را در دسته فناوری و برنامه‌ها و رتبه 2 162 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 15 533 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 29 ژوئن, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 6 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر -1 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 25.10% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 16.85% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 3 901 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 2 619 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 8 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
EEP Communication

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 30 ژوئن, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته فناوری و برنامه‌ها تبدیل کرده‌اند.

15 533
مشترکین
-124 ساعت
-167 روز
+630 روز
آرشیو پست ها
የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በዌብሳይት ኤክስፐርት 2ኛ እና ኮሙዩኒኬሽን ኦፊሰር 3ኛ የሥራ መደቦች ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር መጋቢት 2 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የውጪ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች ስማችሁ የተገለፀው አመልካቾች በሙሉ ህዳር 03 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ኮተቤ በሚገኘው በተቋሙ ዋና መ/ቤት የማሰልጠኛ አዳራሽ የጽሑፍ ፈተና ስለሚሰጥ ለፈተና እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡ "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 26 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content
+2

ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ        ........///........ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ቡድንን በማሸነፍ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል።                 ጥቅምት 25 ቀን 2016 ዓ.ም. በአበበ ቢቄላ ስቴዲየም በተካሄደው የኢትዮጵያ የጥሎ ማለፍ ዋንጫ የእግር ኳስ ውድድር ኢትዮ-ኤሌክትሪክ የአዲስ አበባ አቻውን አንድ ለባዶ በመርታት ነው ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ የቻለው።                                              ለክለቡ ብቸኛዋን የማሸነፊያ  ጎል በ22ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠረው የአማካይ ክፍል ተጫዋቹ ቢኒያም ካሳሁን ነው።     በጨዋታው ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በኳስ ቁጥጥር እና በፍጥነት በማጥቃት  በተጋጣሚው ላይ የበላይነት መውሰድ ችሏል።                     በ75ኛው ደቂቃ በሰራው ጥፋት የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ግብ ጠባቂ በሽር ደሊል በቀጥታ በቀይ ካርድ ከሜዳ በመሰናበቱ ክለቡ ቀሪዎቹን 15  ደቂቃዎች በ10 ተጫዋቾች ለመጫወት ተገዷል።                       የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በበኩሉ በመከላከል እና መልሶ በማጥቃት ጨዋታውን ለመቆጣጠር ቢሞክርም ከሽንፈት ሳይድን ቀርቷል።                                   የመጀመሪያውን ዙር የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ በድል ያጠናቀቀው ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በቀጣይ በሚከናወን የዕጣ አወጣጥ ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለብ ጋር የሚጫወት ይሆናል።                                              በዚህ የውድድር ዓመት ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እንደገና ለመመለስ ብርቱ ፉክክር የሚጠብቀው ኢትዮ-ኤሌክትሪክ የመጀመሪያ መርሀ ግብሩን ህዳር 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት በአበበ ቢቄላ ስቴዲየም ከሀላባ ከተማ ጋር የሚያከናውን ይሆናል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች በዕለቱ በቦታው ተገኝተው ክለባቸውን እንዲያበረታቱ የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ ለማ ጥሪ አቅርበዋል። "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 26 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content

ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መሰከረም 08 ቀን 2016 ዓ.ም በአውቶ ሜካኒክ 2ኛ፣ አውቶ ሜካኒክ 1ኛ፣ አውቶ ኤሌክትሪሽያን 3ኛ፣ አውቶ ኤሌክትሪሽያን 2ኛ፣ አውቶ ኤሌክትሪሽያን 1ኛ፣ አውቶ ቦዲ 2ኛ የስራ መደቦች ስራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር የውጪ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ በዚህ መሰረት ከዚህ በታች ስማችሁ የተገለፀው አመልካቾች ጥቅምት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት ማንነታችሁን የሚገልፅ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ኮተቤ በሚገኘው በተቋሙ ዋናው መ/ቤት የማሰልጠኛ አዳራሽ የጽሁፍ ፈተና ስለሚሰጥ ለፈተናው እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡

photo content
+3

የማከፋፈያ ጣቢያዎቹ ተጨማሪ የኃይል ጥያቄ የማስተናገድ አቅም አላቸው ………///…….. የሀዋሳ ቁጥር አንድና ቁጥር ሁለት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኃይል የሚፈልጉ ደንበኞችን ማስተናገድ የሚያስችል ትልቅ አቅም እንዳለቸው የጣቢያዎቹ ኃላፊዎች አስታወቁ። የሀዋሳ ቁጥር ሁለት ማከፋፈያ ጣቢያ ኃላፊ አቶ ዳንኤል አንጀሎ እንደገለጹት ባለ 230 ኪሎ ቮልት አቅም ያለው የማከፋፈያ ጣቢያው ሃያ ባለ 33 እና 8 ባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች አሉት፡፡ ይሁንና ዝግጁ ከተደረጉት ባለ 33 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች ውስጥ ሦስቱ እንዲሁም ከባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች ውስጥ ደግሞ አምስቱ መስመሮች ብቻ ለሀዋሳ ከተማ፣ ለሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክና በዙሪያው ለሚገኙ ፋብሪካዎች ኃይል እየሰጡ እንደሚገኙ ሥራ አስኪያጁ አብራርተዋል። ጣቢያው 420 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የመስጠት አቅም ቢኖረውም እየሰጠ የሚገኘው ከ140 ሜጋ ዋት ስለማይበልጥ ለኃይል ጠያቂ ደንበኞች አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ የሚያስችለው አቅም እንዳለው ኃላፊው ተናግረዋል። የሀዋሳ ቁጥር አንድ ማከፋፈያ ጣቢያ ሥራ አስኪያጅ ተወካይ ወ/ሪት ቤዛዊት ብርሃኑ ጣቢያው መስጠት ከሚችለው 62 ነጥብ 5 ሜጋ ዋት አቅም ውስጥ እየሰጠ የሚገኘው እስከ 38 ሜጋ ዋት ኃይል ብቻ መሆኑን ገልጸዋል። እንደ ተወካይዋ ገለጻ ጣቢያው ጣቢያው በ 132 ኪሎ ቮልት ኃይል ተቀብሎ በ15 ኪሎ ቮልት ባሉት ስምንት ወጪ መስመሮች ለሀዋሳ ከተማና በዙሪያው ለሚገኙ የዱቄት ፋብሪካዎች ኃይል እየሰጠ ይገኛል፡፡ በ33 ኪሎ ቮልት ባሉት ሁለት ወጪ መስመሮች ደግሞ በሀዋሳ ዙሪያ እስከ 110 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ለሚገኙ የወረዳ ከተሞች ኃይል እየሰጠ ይገኛል ብለዋል። ጣቢያው በአሁኑ ወቅት ባለው አቅም አገልግሎት ፈልገው ለሚመጡ ተጨማሪ ደንበኞች ኃይል ለመስጠት ዝግጁ መሆኑንም ተወካይዋ ጠቁመዋል። የሀዋሳ ቁጥር አንድ ማከፋፈያ ጣቢያ በ1970ዎቹ መጀመሪያ በዲዝል ጀነሬተር ኃይል መስጠት የጀመረና በተለያዩ ጊዚያት በተደረጉለት የማስፋፊያ ሥራዎች አቅሙን ያሳደገ ጣቢያ ሲሆን የሀዋሳ ቁጥር ሁለት ባለ 230 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ደግሞ ሐምሌ 2011 ዓ.ም አገልግሎት መስጠት የጀመረ ጣቢያ ነው። "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 23 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content
+3

ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ከሱዳኑ አል ሂላል ጋር አቻ ተለያየ ………///……… የኢትዮ - ኤሌክትሪክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ከሱዳኑ አል ሂላል ጋር ባደረገው የወዳጅነት ጨዋታ ሁለት አቻ ተለያይቷል። ጨዋታው በተጀመረ አምስተኛው ደቂቃ አል ሂላል በፍጹም ቅጣት ምት ጎል አስቆጥሮ መምራት የቻለ ቢሆንም በመጀመሪያው አጋማሽ መገባደጃ ሰዓት ላይ ናትናኤል ሰለሞን ለኢትዮ ኤሌክትሪክ የአቻነቷን ጎል አስቆጥሯል። በመጀመሪያዎቹ 15 ደቂቃዎች በኳስ ቁጥጥር እና በተደጋጋሚ የተቃራኒ ቡድን የግብ ክልል በመድረስ አል ሂላል ጫና ማድረግ የቻለ ሲሆን ኢትዮ ኤሌክትሪክ በበኩሉ በአጭር እና ፈጣን የኳስ ቅብብል ወደ ጨዋታው በመመለስ የበላይነት አሳይቷል። በሁለተኛው አጋማሽ የተጫዋች ቅያሬ አድርጎ የገባው ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ይበልጥ ጨዋታውን በመቆጣጠር በአጥቂው አቤል ሀብታሙ አማካኝነት ሁለተኛውን ጎል ማስቆጠር ችሏል። ይሁንና ጨዋታው ሊጠናቀቅ ስምንት ደቂቃዎች ሲቀሩት አል ሂላል አቻ ለመሆን ጫና አድርጎ በመጫወቱ ጥረቱ ሰምሮ በ85ኛው ደቂቃ የአቻነት ጎል አስቆጥሯል። ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባለፈው ዓመት የወረደው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በዚህ የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊግ ተሳትፎ እንደገና ወደ ሊጉ ለመመለስ ጠንካራ ልምምድ በማድረግ ላይ ይገኛል። የሱዳኑ አል ሂላል በበኩሉ በቀጣይ ላለበት ኢንተርናሽናል ጨዋታ በአዲስ አበባ ዝግጅት በማድረግ ላይ ነው። በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ ኢትዮ - ኤሌክትሪክ በመጪው እሁድ ጥቅምት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከአዲስ አበባ እግር ኳስ ቡድን ጋር የሚጫወት ይሆናል። በተመሳሳይ የሴቶች ፕሪሜርሊግ ህዳር 16 ቀን 2016 ዓ.ም የሚጀመር ሲሆን በዚህ ዓመት ለሻምፒዮናነት የሚወዳደረው የኢትዮ ኤሌክትሪክ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን የቅድመ ዝግጅት ልምምዱን ጀምሯል። "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 22 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content
+2